cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ ጺሆንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ(መዝ 97-12) ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ ግሩፓቸንን ለመቀላቀል 👇 @kidanemihiret212121

Show more
Advertising posts
866
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#የብፁዓን_አባቶች_የአዲስ_ዓመት_መልዕክት የጥፋት መሳሪያችሁንም አስቀምጣችሁ ወደ ሰላም ማድ ቀርባችሁ በወንድማማችነት መንፈስ ችግራችሁን በክብ ጠረጴዛ በውይይት በመፍታት የሀገሪቱንና የሕዝቡን አንድነት እንድታስቀጥሉ ሁሉን በሚያይ እግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን፡፡" (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ) "ትናንት የነበረው ችግር እንዳይደገም ሁሉም በየአለበት ለአብሮነትና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ችግሮቻችንን ሁሉ በመደማመጥና በመግባባት በመፍታት ለሀገራዊ አንድነት ትኩረት መስጠት አለብን" (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሊቀ ጳጳስ) "ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት  ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው" (ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ) "ባለፈው ዘመን ተለያይተን እርስ በእርስ የተጋጨንባቸውና ያለያዩንን ጉዳዮች በአዲሱ ዘመን በእርቅና በአንድነት ካልተካናቸው አዲስ ዘመን ብለን ማክበራችን ትርጉም አይኖረውም" (ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳስ) "ይህን ክፉ ዘመን በሚገባ አውቀንና ተረድተን ከክፉው ዘመን ጋር ተጠቅልለን ሳንጠፋ ዛሬን ለንስሐ ፤ ነገን ለአዲስ ሕይወት እንድንዘጋጅ ጥላቻውን በፍቅር ለውጠን ይህን አዲስ ዘመን ተቀብለን ልናከብረውም ልንከብርበትም ይገባል" (ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ)
Show all...
#የብፁዓን_አባቶች_የአዲስ_ዓመት_መልዕክት የጥፋት መሳሪያችሁንም አስቀምጣችሁ ወደ ሰላም ማድ ቀርባችሁ በወንድማማችነት መንፈስ ችግራችሁን በክብ ጠረጴዛ በውይይት በመፍታት የሀገሪቱንና የሕዝቡን አንድነት እንድታስቀጥሉ ሁሉን በሚያይ እግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን፡፡" (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ) "ትናንት የነበረው ችግር እንዳይደገም ሁሉም በየአለበት ለአብሮነትና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ችግሮቻችንን ሁሉ በመደማመጥና በመግባባት በመፍታት ለሀገራዊ አንድነት ትኩረት መስጠት አለብን" (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሊቀ ጳጳስ) "ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት  ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው" (ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ) "ባለፈው ዘመን ተለያይተን እርስ በእርስ የተጋጨንባቸውና ያለያዩንን ጉዳዮች በአዲሱ ዘመን በእርቅና በአንድነት ካልተካናቸው አዲስ ዘመን ብለን ማክበራችን ትርጉም አይኖረውም" (ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳስ) "ይህን ክፉ ዘመን በሚገባ አውቀንና ተረድተን ከክፉው ዘመን ጋር ተጠቅልለን ሳንጠፋ ዛሬን ለንስሐ ፤ ነገን ለአዲስ ሕይወት እንድንዘጋጅ ጥላቻውን በፍቅር ለውጠን ይህን አዲስ ዘመን ተቀብለን ልናከብረውም ልንከብርበትም ይገባል" (ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ)
Show all...
ቅዱሳን አባቶቻችን ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፏል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡ (አረጋዊ ታዴዎስ)
Show all...
ቅኔ ከአፌ ፈሰሰ አጭር video ነው ይክፈቱት 👇👇👇👇👇👇👇 @kidanemihiret2116
Show all...
❤️
👍
🤲
"መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡ "እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡ ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡" ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ 👇👇👇👇👇👇👇 @kidanemihiret2116
Show all...
༒ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ሥላሴ ༒ እንኳን ለቅደስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የሌሊቱን ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ በዕለቱ የሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። ፩. ነግሥ / ሰላም ለአብ / ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ፤ ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ፤ ኃይልየ ሥላሴ ወፀወንየ ሥላሴ፤ በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ። ዚቅ፦ አምላክነሰ ኃይልነ ፨ አምላክነሰ ፀወንነ ፨ አምላከ አሕዛብ ዕብነ ወዕፀ ኪነት ኢኮነ። ፪.  ለአጽፋረ እግርከ / መልክአ ሚካኤል / ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤ ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤ አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡ ዚቅ፦ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘይሴባሕ እምትጉሃን ፨ ወይትቄደስ እምቅዱሳን ፡፡ ፫. ተፈሥሒ ማርያም / ማኅሌተ ጽጌ / ተፈሥሒ ማርያም እንተ ዘተአምሪ ብእሴ፤ ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ፤ እንዘ እዘብጥ ከበሮ ቅድመ አእላፈ ኤፍሬም ወምናሴ፤ ለተአምርኪ እነግር ውዳሴ፡ ማርያም እኅቱ ለሙሴ። ወረብ፦ ተፈሥሂ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ ተፈሥሂ ማርያም ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ ዘጸገይኪ ለነ። ዚቅ ፦ ይሴብሑኪ ወይገንዩ ለስምኪ ፨ ዘእምሥሉስ ቅዱስ ቃል ኃደረ ላዕሌኪ ፨ ወትሰመዪ ማኅደረ መለኮት ። ፬. ለህላዌክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላዌያተ፤ ለረኪበ ስሙ ኅቡእ አመ ወጠንኩ ተምኔተ፤ እምግብርክሙ #ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ፤ መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚኣክሙ ገጻተ፤ እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ። ዚቅ፦ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ አአትብ ወእትነሣእ ፨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፨ሠለስተ አሥማተ ነሢእየ እትመረጐዝ ፨ እመኒ ወደቁ እትነሣእ፨ ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት ፨ እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ ፡፡ አመላለስ ዘዚቅ ፦ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ። ፭ . ለሕጽንክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሕጽንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ ።   ዚቅ፦ በአፍዓኒ አንትሙ ፨ ወበውሣጤኒ አንትሙ ፨ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለዘርዓ ያዕቆብ (ለኢያሱ) አንትሙ ፡፡ ወረብ፦ በአፍአኒ አንትሙ ወበውሣጤኒ አንትሙ/፪/ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለኢያሱ ንጉሠ ነገሥት/፪/ ፮. ለሕሊናክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሕሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ፤ እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ፤ ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ፤ ፫ተ ዕደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ኀይምት ርእየ፤ ወለ፩ዱ ነገሮ ረሰየ። ዚቅ፦ ወጽአ አብርሃም እምድረ ካራን ፨ ወቦአ ብሔረ ከነዓን፨ ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር ፨ እንበይነዝ ጽድቀ ኮኖ ፡፡ ወረብ፦ ወጽአ እምድረ ካራን ወቦአ ብሔረ ከነዓን፤ ተአመነ አብርሃም አብርሃም በእግዚአብሔር/፪/ ፯. ለሐቌክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሐቌክሙ ዘቅናተ ኂሩት ቅናቱ፤ ሊሉያነ ፆታ ሥላሴ እምአምላከ በለዓም ከንቱ፤ ኀበ መስፈርትክሙ ጽድቅ እስመ ያበጽሕ ትእምርቱ፤ ተደለዉ ከመ ይሑሩ ምሕዋረ ዕለታት ሠለስቱ፤ በዓለ መሥዋዕት አብርሃም ወይስሐቅ መሥዋዕቱ።  ዚቅ፦ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ ፨ አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ፨ እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ ፨ ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል ፨ አብርሃምኒ ርእዮ በውስተ ምሥዋዕ ፨ ሕዝቅኤልኒ ርእዮ በልዑላን ፨ ሙሴኒ ርእዮ በዓምደ ደመና ፨ በነደ እሳት ፨ ፈያታዊኒ ርእዮ በዲበ ዕፀ መስቀል አምነ ፡፡ ወረብ፦ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ፤ አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ቤዛሁ በግዓ። ፰. ለዘበነጊድ / መልክአ ሥላሴ / ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ፤ መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ስብዐተ፤ ህየንተ ፩ዱ ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምእተ፤ ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ፤ ወዲበ ፲ቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ ። ዚቅ፦ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ፨ ስብሐት ለወልድ ለዘአክበራ ለማርያም ፨ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት። ወረብ፦ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኲሉ ዓለም፤ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት። ፲. ለሕሊናከ / መልክአ ተክለሃይማኖት / ሰላም ለሕሊናከ ዘኮነ መምለኬ፤ ሥላሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ፤ ተክለሃይማኖት ቄርሎስ ዘላፌ ረሲዓን እለ እውጣኬ፤ ባርከኒ አባ ለወልድቅዱስ፤ኬ፤ እስመ ልማዱ ለመምህር ቡራኬ። ዚቅ፦ አንትሙሰ ከመ ዕብነ ሕይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ ፨ ወለክህነቱ ቅዱስ ፨ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ ለዘጸውዓክሙ ፨ አባ ባርከኒ ተክለሃይማኖት አባ ፨ ከመ ባረኮ አብርሃም ለይስሐቅ ወልዱ። ወረብ፦ አንትሙሰ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ወለክህነቱ ቅዱስ ታዕርጉ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ።      °༺༒༻° ምልጣን °༺༒༻° ዕምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም ፤ መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም፤ እንዘ ይብሉ ይዜምሩ ፤ በልሳን ዘኢያረምም፤ አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም። አመላለስ፦ አማን በአማን ፤ መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም። °༺༒༻° እስመ ለዓለም ° ༺༒༻° ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ ፨ ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ፨ ወይቤሎ አብርሃም ንግሮ ለእግዚአብሔር ፨ እንዘ ትብል ተዘከር እግዚኦ ኪዳነከ ፨ አብርሃም ፍቊርከ ይስሐቅ ቊልዔከ ፨ ወያዕቆብሃ ዘአስተባዛሕከ ፨ ነሥአ ሙሴ ሠለስተ አስማተ ፨ ከመ ዘይወስድ አምኃ ለንጉሥ ፨ ወሰማዕትኒ ይጸውሩ ሥላሴ። ወረብ ዘአመላለስ፦ ሰአለ ሙሴ ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ፤ ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ። °༺༒༻°  አቡን በ ፫  °༺༒༻° ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ እስመ በሥላሴ ትሄሉ በሰማይ ወበምድር ፤ (ሥ) ወሠናያቲሃ ይሰብክ ቃለ ኢያሱ ሐዋርያ ፍቅር ፤ ( ሥ ) ውስተ ሀገሩ ሐዳስ ደብረ ብርሃን ንግሥ አድባር ፣ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ። °༺༒༻°   ሰላም  °༺༒༻° ሰላመ አብ  ሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ ኃይለ መስቀሉ እትመረጐዝ፤ የሃሉ ማእከሌክሙ እኃው።
Show all...
መጻፈ ሲራክ ም2 /24-25 ጠላት በከንፈሩ ተስፋ ይሰጣል፥በልቡ ግን ተንኰልን ያኖራል። በልቡ ሰባት ርኵሰት አለበትና በቃሉ አሳምሮ ቢናገርህ አትመነው።
Show all...