cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Sabian Secondery & Preparatory School (ሳ\ሁ\ደ\መ\ት\ቤት)

Wel Come To Our School.

Show more
Advertising posts
2 602
Subscribers
+124 hours
+47 days
+830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ግንቦት 2/2016 ዓመት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በማዐከል ደረጀ ለማዘጋጀት ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ ላይም የቢሮ ምክትል ቢሮ ኋላፊ እና የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳሪክቶሬት ዳሪክተር አቶ አቡበክር አዶሽ ለስርዓት ትምህርት ባለሞያዎች ዝግጅት አስመልክቶ አቅጣጫ ሰተዋል ።
Show all...
ግንቦት 2/2016 ዓ.ም በድሬዳዋ አሰተዳደርትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል በበይነ መረብ (ኦን ላየን) ፈተናን አሰመልክቶ ለአስፈታኝ ት/ቤት ር/መራን፣ም/ር/መ/ራንና የአይሲቲ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ተጀመረ። በመድረኩ ላይ በመገኘት ስለስልጠናው አሰፈላጊነት እንዲሁም በቀጣይ ወደ ት/ቤት ወርደው ምን መስራት እንዳለባቸው የስራ አቅጣጫ የሰጡት ም/ቢሮ ኃላፊና የስ/ት/ት/ዝና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡበከር አዶሽ ሲሆኑ በመቀጠልም የቢሮ ኃላፊው አቶ ሱልጣን አሊይ እንዳሉትም የኦን ላየን ፈተና የማይቀር በመሆኑ ሁሉም ት/ቤቶች አሰፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያሟሉ ያስገነዘቡ ሲሆን ይህንንም የፈተና ሂደት የሚከታተል በክቡር ከንቲባው የሚመራ ስትሪንግ ኮሚቴ የሚቋቋም መሆኑን ገልፀዋል። ለአይሲቲ መምህራን ቴክኒካል የሆኑ ስልጠናዎችን የሰጡት የቢሮው የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይርጋ ሙሉነህ ሲሆኑም ስልጠናውም እንዴት ለፈተና የሚረዱ ብራውዘሮች እንደሚጫኑ፣ተማሪዎች እንዴት user name and password በመጠቀም ፈተና መስራት እንደሚችሉ በተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥተዋል። በመጨረሻም የቢሮው የፈተና ጉዳዮች አሰተባባሪ የሆኑት አቶ አስቻለው ሸዋረጋ ርዕሰ መምህራንና የአይሲቲ ባለሙያዎች የወሰዱትን ስልጠና ወደ ት/ቤት በማውረድ ሌሎች ባለሙያዎችን በማሰልጠን ፈተና እስከሚደርስ ድረስ ተከታታይ የሆነ ስልጠና ለተማሪዎች መሰጠት እንዳለበት ያሳሰቡና የቢሮ አይሲቲ ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል። ስልጠናው በነገው እለት የቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የጋራ ውይይት በማካሄድ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
Show all...
👍 2
በድሬዳዋ እስተዳደር እና በመማር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን የጋራ ትብብ ከመጋቢት 14/2016 ጀምሮ እየተካሄደ የሚነኘው ማወቅ ያሸልማል የ12 ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ግንቦት 10/2016 በወጣቶች ማዕከል /ኮንጎ ሜዳ/ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ይጠናቀቃል። ሁላችንም የፍፃሜ ውድድሩን እንድንታደም ተጋብዘናል ። ይ ቀ ር ም!!
Show all...
👍 3
Repost from ETHIO-MEREJA®
#ጤናመረጃ ኩላሊት የሚጎዱ ልማዶች (ይነበብ) አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ? ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም 1. ሽንትን መቋጠር ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል። 2. በቂ ውሃ አለመጠጣት አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። 3. ጨው ማብዛት ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። 4. የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። 5. ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት 6. መጠጥ ማብዛት መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። 7. ሲጋራ ማጨስ 8. ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመታከም። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የኩላሊት ህመም ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ። ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር! T.me/ethio_mereja ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 2
ለክርስትና እምነት ተከታይ የት/ቤታችን ማህበረሰብ መምህራን የአስተዳደር ሰራተኞች የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ አደረሰን በአሉ የሰላም የመተሳሰብ የአንድነት የፍቅር እንዲሁም ለሀገራችን ሰላሙን የሚሰፍንበትን ያውርድልን :: መልካም በአል መልካም አውዳመት ይሁንላችሁ!!!
Show all...
👍 7
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 1
በዚህ አመት በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ የትሞህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። ----------------------------------- የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በወረቀት ከሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ጎን ለጎን በቴክኖሎጁ ተደግፎ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመሆኑም ፈተናው እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ከተሞች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ወ/ሮ አየለች ገልጸዋል። በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ከወዲሁ በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ወላጆች ስለፈተናው የተሻለ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ልጆቻቸውን እንዲደግፉና በራስ መተማመን ወደፈተናው ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ሊፈጥሩ እንደሚገባም አመላክተዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በኦን ላይን የሚሰጠውን ፈተና በተሻለ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናን ለተማሪዎች በኦንላይን መስጠት ምቹና ቀላል መሆኑን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
Show all...
እንኳን ቀዳም ሥዑር አደረሳችሁ::
Show all...