cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗ መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Show more
Advertising posts
208 895Subscribers
-65024 hours
-3 4137 days
+1 24530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ምዝገባ በኦንላይን መጀመሩ ተገለጸ‼️ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድን በኦንላይን ተመዝግቦ ማግኘት እንደሚቻል የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ፤ የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብር እና በባንክ መክፈል እንደሚቻል ለኢፕድ ገልጸዋል። ካርዱን ለማግኘት card-order.fayda.et ድረ ገጽ ላይ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ያስታወቁት አቶ አቤኔዘር፤ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ካሉበት ቦታ እንዲመጣላቸው ማዘዝ ይችላሉ ብለዋል። ይህ አገልግሎት በተለይ በክፍለ ሀገር የሚኖሩ ዜጎችን ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል። ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በኪስ የሚያዝ ወረቀት ብቻ ሳይሆን የራሱ መለያ /ፋይዳ/ የሚባል ቁጥር ይዞ በማንኛውም ቦታ በቁጥሩ ምክንያት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር መሆኑን አቶ አቤኔዘር አስረድተዋል። ዲጂታል መታወቂያ፤ አንድ ሰው ከቤቱ ሆኖ የባንክ አካውንት መክፈት፣ የኢንሹራንስ አገልግሎት ማግኘትና በአገልግሎት ሰጭውና ተቀባዩ ዘንድ መተማመን መፍጠር የሚያስችል መሆኑን አክለው ጠቅሰዋል።
Show all...
👍 55 9😱 4🔥 3🙊 2
በመላ ሀገሪቱ ኃይል ተቋርጧል‼️ ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙን መልሰን እስከምናገናኝ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን። የኢትዮጵያ መብራት አገልግሎት
Show all...
🔥 23👍 22 8🙏 4🥰 2👻 2👏 1
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ‼️ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች  ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። ኮሚሽኑ በሰራተኝኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል። በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።
Show all...
👏 48👍 42 7🫡 6👻 5😱 2🤡 2
እንድታውቁት ‼️ አዲስ አበባ ከተማ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፍጹም መቆም የሚከለክሉ የትራፊክ ምልክቶች ተተክለዋል። በስራ መግቢያ እና ከስራ መውጪያ ሰዓትም በአካባቢው ላይ በመንገድ መዘጋጋት ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል። በዚሁ መሰረት ፤ " ፍጹም መቆም የሚከለክሉ " ምልክት የተተከለባቸው ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ መታሰቢያ የሚወስድ ዋና መንገድ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ አድዋ ሙዚዬም ዙሪያ እና ማዘጋጃ ዙሪያ ከዛሬ መጋቢት 19/2016 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር ይጀመራል ተብሏል። በአካባቢው በግዜያዊነት ለተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚውል የአድዋ ሙዚዬም "ሰርፌስ ፓርኪንግ" አገልግሎት መስጠት ስለጀመረ አሽከርካሪዎች እንደ አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል። በመንገድ ግንባታ ስራ ፦ - ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ - ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ፣ አማራጭ መንገድ ከአራት ኪሎ-አባድር  - ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ - ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዘበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለመቅረፍ ፤ አማራጭ #ማስተንፈሻ የሚሆን መንገድ በተለምዶ ከቀይባሕር ኮንደሚንየም ወደ ደጎል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዛሬ ከሰዓት ለተሽከርካሪዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
Show all...
👍 32 3🙏 2
🔖 ይህ የአዲስ ሚድያ የቴሌግራም ገፅ ነው በቻናሉ ፈጣን ፥ትኩስ ፥ ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! https://t.me/+LirM8eQ0TjdhNDlk
Show all...
👍 11 2😱 2🥰 1
ወቅታዊ ጉዳዮች
አዳዲስ መረጃዎች
የውጪ ጉዳዮች
አዲስ ሚድያ
በአውሮፓዊቷ ሀገር ፖላንድ ክትባት አንከተብም የሚሉ ሰዎች ቁጥር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ መጨመሩ አስደንጋጭ ሆኗል-ባለስልጣናት‼️ የሀገሪቱ ብሄራዊ የህዝብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው ባለፉት አምስት አመታት የክትባት እምቢታዎች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል ፣ በ 2019 ከ 48,600 እምቢታዎች በ 2023 ወደ 87,300 አድጓል ብሏል። በሕዝብ ጤና ጉዳይ ብሔራዊ አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ያሮስዋ ፒንካስ “በፖላንድ ያለው እምቢተኛነት ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ ክስተት ነው፣ እናም ይህ አዝማሚያ አሁንም ቀጥሏል” ብለዋል።
Show all...
👍 32 3
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች አንጻራዊ ሰላም መስፈኑ ተገለጸ‼️ የተኩስ ልውውጦችን ሲያስተናግዱ በቆዩት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ውስጥ፣ ካለፉት ሦስት ቀናት ወዲህ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተያየት ሰጭዎች፣ በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች የተፈናቀሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን በአሳሳቢ ችግር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት፣ የሰላማውያን ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የንብረት ውድመት መድረሱንና ዘረፋ መፈጸሙን አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የጠቆሙ አስተያየት ሰጭዎች፣ አልፎ አልፎ ግን የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተዋል፡፡ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የፌደራል መንግሥቱ መፍትሔ እንዲያፈላልግም ጠይቀዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን መጡ የተባሉ ታጣቂዎች፣ አሁንም በአጣዬ ከተማ የተወሰኑ ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚገኙ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ ገልጸዋል፡፡
Show all...
👍 36 4🥰 1
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት "ሹገር ማሚ" እና "ሹገር ዳዲ" እናገናኛለን የሚሉትን ጨምሮ ከ166 ሺህ በላይ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ተነሱ‼️ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት 166 ሺህ 875 ህገወጥ ማስታወቂያዎች እንዲነሱ መደረጋቸውን የከተማ ውበት እና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የከተማ ውበት ልማት ክትትል ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ከበደ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፣በአዲስ አበባ  በሁሉም  ክፍለ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጃ በርካታ ህገወጥ ማስታወቂያዎች ይለጠፋሉ።በተለይም ደግሞ የህብረተሰቡ ዋንኛ መዳረሻ በሆኑት እንደ ሜክሲኮ እና መገናኛ ባሉት የአዲስ አበባ ቦታዎች ይህ ሁኔታ በስፋት ጎልቶ ይታያል ሲሉ ተናግረዋል።
Show all...
👍 31 3🤡 2🔥 1🥰 1😱 1
በቀይ_ባሕር የሚፈጸሙ ጥቃቶች በ #ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ አንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠራቸው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ‼️ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ በቀይ ባሕር የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ትልልቅ የመርከብ ኩባንያዎች ወደ #ጅቡቲ ወደብ ሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማቆማቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና የሚወጡ ጭነቶች እንዳይገቡና እንዳይወጡ ችግር ሆኗል ሲል ገልጿል፡፡ አጓጓዥ መርከብ ድርጅቶች በአሁኑ ሰዓት ወደ ጅቡቲ መምጣት ቀንሰዋል ብሎም አቁመዋል ያለው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም በተለይ የኢትዮጵያን #ቡናን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት የአገልግሎት ክፍተት እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ የራሱን መርከቦች በማሰማራት እና ምልልሳቸውን በመጨመር ጭነቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቋል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ የወጪ ንግድ ጭነቶችን ወደ #ቻይና ቲያንጂ እና ሻንጋይ /ታይካንግ/ ወደቦች ወደ #ህንድ ሙንድራ እና ናሃቫሼቫ ወደቦች እንዲሁም ወደ ተባበሩት #አረብ ኤምሬት ጀበል አሊ እና ሻርጃ ወደቦች በመደበኛነት በማጓጓዝ ላይ መሆኑን በመግለጽ፤ ላኪዎች፤ ቡና እና ሌሎች የወጪ ንግድ ጭነቶችን የድርጅቱ መርከቦች በሄዱባቸው ወደቦች ማጓጓዝ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡ ከቅርብ ግዚ ጀምሮ የየመን ሁቲዎች በቀይ ባሕር በሚተላለፍ መርከብ ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየፈጸሙ ይገኛል። የንግድ መርከብ ላይ በሚፈጽሙት የሚሳዔል ጥቃቶች የሰዎች ህይወት ማለፉና በርካታ ንብረቶች መውደማቸው ይታወቃል።
Show all...
👍 49 6😱 2
በዮሐንስ_ቧያለው፣ #ክርስቲያን_ታደለ፣ #እስክንድር_ነጋና #ዘመነ_ካሴ ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ‼️ ዮሐንስ ቧያለውና ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ፤ ክሱን የመሰረተው የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ነው። በተከፈተው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የሚለው ይገኝበታል ያለው ዘገባው ተከሳሾች ያደራጁትን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሰብስበዉ በመደራጀት፤ የአማራ ሕዝብ “ሀገር ተወስዶበታል ርስቱን ተቀምቷል” የሚል አቋም በመያዝ የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና ሀገርን ‹‹በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት›› በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል እንደሚገኝበት አስታውቋል። ከ90 በላይ የመንግስት እና የግለሰቦች መኪኖች እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ለአርሶ አደር የሚከፋፈሉ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ የዘረፉ እና እንዲዘረፉ ያደረጉ በመሆኑ የሚል ክስም እንደተመሰረተባቸው አመላክቷል።
Show all...
👻 82👍 51🙊 20🤡 14😭 12👏 11 7😢 6😱 3
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!