993
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-3230 days
Posts Archive
📎 የአልፋ ጥቅል ስልጠና
📍በአርባምንጭ
- በሁበቴ ሆቴል
- ኃያል ሂደት
📍በሐዋሳ
- በሌዊ ሆቴል
- ኃያል ሂደት እና ልምድ ግንባታ
=== አልፋ ለስኬትዎ ጉልህ ድርሻ! ===!
📍አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 3 አለምነሽ ፕላዛ 6ተኛ ፎቅ
🌐 www.alphagenuine.com
☎️ +251930020395 ቦሌ ቅርንጫፍ
+251988010611 መገናኘት ቅርንጫፍ
+251943120133 አዳማ ቅርንጫፍ
#GeneralMeetingRecap
Unforgettable Moments from our General Meeting at Ethiopia Skylight Hotel!
በዚህ ደረጃ Personal Development በሃገራችን እያደገ መምጣቱ ይበል የሚያሰኝ ነው።
Yene is a psychologically proven product using the Holland Code and 250 Data points to analyze the personality and worker type of a person so that a person can identify what type of personality they have and to find out what career path they should take.
የኔ በስነ-ልቦና የተረጋገጠ ምርት
ሲሆን በሆላንድ ኮድ እና 250 የመረጃ ነጥቦችን በመጠቀም አንድ ሰው ምን አይነት ስብዕና እንዳለው ለመለየት እና የትኛውን የሙያ መስመር መከተል እንዳለበት ለማወቅ የሚረዳ ነው።
የወደፊት ህይወትዎን ዛሬ ያስተካክሉ!
👇👇👇👇
@Robi32110 90 / አስር ዘጠና!
የህይወት አስር እጅ (10%) የሚደርስብህ ነገር ጉዳይ ነው፤ ዘጠናው እጅ (90%) ግን የምትመልሰው መልስ ጉዳይ ነው። የደረሰብህ ሁሉ ለምን ደረሰብኝ ማለትን አቁምና ስለደረሰብህ ነገር ስለምትሰጠው ምላሽ ማሰብ ጀምር። እራስህን አዘጋጅ፣ እራስህን አቅና፣ ከባዱን ለመቋቋም፣ ህይወትህንም ለማሸነፍ እራስህን አበርታ። መቀበል ያሉብህ እጅግ በጣም ብዙ የህይወት እንቆቅልሾች አሉብህ፣ መርሳት ያለብህ፣ መተው የሚኖርብህ፣ ጥለሀው ልታልፈው የሚገባ የህይወት ክስተት ይኖራልና ለመተው ቆራጥ ሁን። ዋጋ መክፈል ያለ ነው፣ ምላሹንም በቶሎ መጠበቅ ያለ ነው፣ እራስህን ግን አሸናፊ ለማድረግ ለሁሉም የህይወት ክስተቶች እራስህን ማዘጋጀት ይኖርብሃል። ለ100% አሸናፊነት ታቅዳለህ ነገር ግን የትኛውንም የአሸናፊነት ደረጃህን አሜን ብለህ ትቀበላለህ፣ እራስህንም በሒደት እያሻሻልክ ወደፊት ትጓዛለህ።
አዎ! ጀግናዬ..! ዘጠናው ፐርሰንት ምላሽህ ላይ በርታ፣ ህይወትህን የምትረዳበትን መንገድ በሚገባ መርምር፣ ከደረሰብህ በላይ ለደረሰብህ የምትሰጠው ምላሽ ትልቅ ስፍራ እንደሚይዝ ተገንዘብ። አሁን ምን ማድረግን ታስባለህ? ስለምኑ ብትል፦ አስበህም፣ ሳታስብም ስለሆነብህ እያንዳንዱ የህይወት ክስተት፤ በየሰዓቱ ለሚገጥምህ የህይወት ውጣውረድ፣ ስለሚደርስብህ ፈታኝ ሁነት፣ ለሚመጣብህ ከባድ ህመም ምላሽህ ምንድነው? ባለህ ነገር ምን እያደረክ ነው? አንተን ብሎ ለመጣ ምን ምላሽ ትሰጣለህ? ስለሆነው ታለቅሳለህ ወይስ ለምላሹ እራስህን ታተጋለህ፣ እራስህን ታዘጋጃለህ? እራስህን በብዙ ታበረታለህ? ምን ይቀናሃል? የሆነውን መቀበል ወይስ ስለሆነው ምክንያት መደርደር? የቱ ይገልፅሃል? በትንሹም በትልቁም እራስህን መተቸት ወይስ እያንዳንዷን እርምጃዎችህን ማድነቅ፣ በእያንዳንዱ የህይወትህ ቅፅበታት ውስጥ ህይወትን መፈለግ፣ እራስን ማግኘት፣ እራስን ማነፅ።
አዎ! የከበደህ አክብደህ ስላሰብከው፣ አክብደህ ስለተቀበልቀው እንደሆነ እወቅ። የህይወት ጫናዎች ሁሌም አሉ፣ ህመሞች ዘወትር ይከተሉናል፣ ወደፊት እስከተጓዝን ድረስ መሰናክሎች ሁሌም ከፊታችን አሉ፣ እስከመጨረሻውም ከፊት እየቀደሙ ይፈትኑን ዘንድ የግድ ነው። የትኛውም መጪው የህይወትህ ክፍል የተለየውን አንተን ይፈልጋል። የጂም ሮንን ድንቅ አባባል አስታውስ "ነገሮች እንዲቀየሩ አንተ መቀየር አለብህ፣ ነገሮች እንዲሻሻሉ አንተ መሻሻል አለብህ።" የምንም ነገር መነሻ አንተና አንተ ነህ። ጨለማውን ህይወትህን በብረሃን ለመቀየር እራስህ ብረሃን መሆን ይጠበቅብሃል፤ እራስህን በተለየ ሰው ቦታ ለመመልከት የምቾት ቀጠናህን የመሰናበት ግዴታ አለብህ። ምቾት ማጣትህን እንደ እድለቢስነት መመልከት አቁም። ፈተናህ አሻጋሪህ፣ ምቾት ማጣትህም የለውጥህ መሰረት እንደሆነ ተረዳ። በምላሾችህ ላይ ሰልጥን የህይወትህንም ጠዓም በገዛ ስልጣንህ ቀይረው።
═════════❁✿❁ ═════════
💪💯 ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
