cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን ስዕለ አድህኖ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ፅሁፎች

ይህ ቻናል በየቀኑ የቅዱሳን ስዕለ አድህኖ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ፅሁፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

Show more
Advertising posts
201Subscribers
No data24 hours
+17 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከሰማዩ ከፍታ(አርሴማ ወልደአምላክ) https://youtube.com/watch?v=duzxddWAncg&si=T9bnUl-CCkucm7zA
Show all...
ከሰማዩ ከፍታ(አርሴማ ወልደአምላክ)

ዚቅ ሚድያ ZIQ MEDIA @ZIKMEDIA ይህ ቻናል በቤተክርስቲያናችን እጅግ ድንቅ ፀጋ የተሰጣቸው ልጆችን በማበረታታት እና በፀጋቸው እንዲያገለግሉ እድሉን በመፍጠር እና በተለያዩ አለማዊ ህይወት ለተዋጥነዉ የቤተክርስቲያናችን ድንቅ ወጣቶች የተለያየ የዝማሬ ፀጋቸዉን ወደ እናንተ የምናደርሰበት ቻናል ነው ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አጋርነታችሁን አሳዩን እናመሰግናለን

እንኳን ለጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሃዊ ክብረ በዓል፣ለቁስቋም ማርያም ወርሃዊ ክብረ በዓል፣ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዘአርማንያ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!! የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዘአርማንያ በረከት አይለየን!!! አሜን አሜን አሜን!!! #ታህሳስ6
Show all...
አንድ አባት ወጣኒ ደቀመዝሙሩን አለው''ሂድና ሙታንን ተሳደብ ''ወደ መቃብር ሄዶ ቀኑን ሙሉ ሙታንን ሲሳደብ ዋለ። `በቀጣዩ ቀን ደቀመዝሙሩን አለው ''ሂድና ሙታንን አመስግን!'' ወደ መቃብር ሄዶ ምስጋናውን ሲያቀርብ ዋለ። ማታ ሲመለስ መምህሩ ጠየቀው''በሰደብካቸው ጊዜ ሙታንን ተሰማቸው?'' ''የለም አልተሰማቸውም''አለና መለሰ ''ባመሰገንካቸው ጊዜስ?''አለው ''የለም አልተሰማቸውም ''ብሎ መለሰ አረጋዊውም ''''ሂድ አንተም እንዲሁ ሁን!!'''ብሎ ነገረው። ስለዚህ ከመመስገን ይልቅ መነቀፍ ይበልጥ ብፅዕና ነው...ሰወች ሲያመሰግኑን ለኛ መንፈሳዊነት አደገኛ እንደሆነና ሲነቅፉን ደግሞ ማመስገንን በአእምሯችን ልንተክል ይገባናል .... አቡነ አትናቴዎስ እስክንድር እንደፃፉት 🍂መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ🍂 @slehiwetwe ይ🀄️ላ🀄️ሉን።
Show all...
✞ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ✞   ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን  ውስተ አፍላገ ባቢሎን  ህየ ነበርነ ወበከይነ እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ጒዓቲሃ ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን አለቀስን መሰንቆዋችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዶዋልና አህዛብም ዘበቱብን እንዲ ብለው በየተራ ዘምሩለት ላምላካቹ ቢያድናቹ ከመከራ   እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና   ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና   ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም   ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን   አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን            አዝ= = = = = የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ   እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና   ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና   ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም   ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን   አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን            አዝ= = = = = ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም እናልፋለን ሁሉን ባንቺ  የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅድስት ሆይ ከባረክሽን እንድናለን ከደወዌያችን ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን    እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና    ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና    ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም    ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን     አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን                     መዝሙር ዘማሪ መጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Show all...
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!! የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣የልጇም ቸርነት ከእኛ ከሁላችን ጋር ይሁን፣የልቦናችንን መሻት ትፈፅምልን፣ለነፍስ እና ለስጋችን ዋስ ጠበቃ ጋሻ መከታ ትሁነን!!! አሜን አሜን አሜን!!! #ህዳር21
Show all...
የኅዳር ጽዮን 21 የነግህ (የማኅሌት) 😍ምስባክ 😍 ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ: ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ: ደዩ ለበክሙ ውስተ ኀይላ::     ዲ/ን አቤል (ፍቅረ አብ) ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian    💚 💛 @seratebtkrstian    💚 💛 @seratebtkrstian    💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙      🙏join👍 ለጥያቄ ለአስተያየት 👇 @Men_Lerdawobot #ሼርርርርርርርርርርር
Show all...
እሁድ/16-03-16/ በፉሪ ፈለገ ዮርዳኖስ ማሩ መጥምቁ ዮሐንስ እና ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን (ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ማርያም) የበዓታ ለማርያም ፅላት ስለሚገባ ሁላችንም ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘናል ።  ሼር በማድረግ ላልሰሙ ወንድም እና እህቶቻችን እናድርስ!
Show all...