cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Show more
Advertising posts
985
Subscribers
-324 hours
+37 days
+3130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
840Loading...
02
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ): ✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ 🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ 📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል። 💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። 📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው። 📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል። 📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።      ቅዱሱ በኤፌሶን 📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ። 📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። 💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ። 📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች። 📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። 📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። 📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። 💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች። 📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት። 📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል። የፍቅር ሐዋርያ 📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል።  በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር። 💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ) 📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና። 📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል። 📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡ ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት። 📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው። 📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት። 📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦
650Loading...
03
1. ወንጌላዊ 2. ሐዋርያ 3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም 4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ) 5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) 6. ወልደ ነጐድጓድ 7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር 8. ፍቁረ እግዚእ 9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) 10. ቁጹረ ገጽ 11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) 12. ንስር ሠራሪ 13. ልዑለ ስብከት 14. ምድራዊው መልዐክ 15. ዓምደ ብርሃን 16. ሐዋርያ ትንቢት 17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን 18. ኮከበ ከዋክብት 🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲 🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ https://t.me/felegetibebmedia
830Loading...
04
Media files
963Loading...
05
Media files
1300Loading...
06
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+ +በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: +ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: +ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: +በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: +ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል:: +ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: +ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: +የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል:: ❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከበረከቱም አይለየን:: =>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) 2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ 3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት 4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ 4.ቅድስት እንባ መሪና 5.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
1260Loading...
07
#የኔ_ትውልድ_ባለውለታውን_ያሳክማል "ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ታሟል" ብዙዎቻችንን ወደ መንፈሳዊ መንገድ የመራን፣ በሐጢአት የገገረውን ዓለት ልባችንን በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ ያቀለጠልን፣ ልንጠፋ ጫፍ ስንደርስ በሚስረቀረቅ ድምፁ የመለሰን፣ በአገልግሎቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነ፣ መዝሙሩ ወደ ጸሎት ያደገለት ታላቁ አባታችን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ሕክምና ይፈልጋል። ጠንካራ ቤተ ክህነት ቢኖረን ኖሮ ይህ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መታከሚያ ባላጣ ነበር። ዳሩ ግን...ሆድ ይፍጀው። እኛ የመዝሙራቱ ተጠቃሚዎች ግን ባለውለታችንን አንተውም። ዘማሪ ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስን ለማሳከም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ....እነሆ በረከት! መርዳት የማትችሉ በማጋራት ተባበሩ። ድጋፋችንን አድርገን ወዳጅነታችንን እንግለጥ CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch
2132Loading...
08
Media files
1742Loading...
09
Media files
1670Loading...
10
✝✝✝ እንኩዋን የመነኮሳት አባት ለተባለው "ቅዱስ ዻኩሚስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ቅዱስ ዻኩሚስ (አባ ባኹም) "*+ =>ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም:: +ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል:: +በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ : ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል:: +ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር:: +ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን : ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር:: +ከዚያም በጾም : በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል:: +አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል:: <<< የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች >>> 1.በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል:: 2.ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር:: 3.የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል:: 4.መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል:: 5.መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል:: 6.ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: (ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው) +ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል:: =>የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: =>ግንቦት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ ዻኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ) 2.አባ ሲማኮስ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት =>+"+ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: +"+ (ማቴ. 19:11) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
1691Loading...
11
#እናቴ_ሆይ "ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፤ ባዝንም ባንቺ እፅናናለሁ፤ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ።" (#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - በመጽሐፈ አርጋኖ)
1891Loading...
12
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ አርሳኒ +"+ =>ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ ቅዱሳን ነው እንጂ:: +ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም:: እነርሱ በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን አንዱ ደግም ቅዱስ አርሳንዮስ ነው:: +ቅዱሱ የተወለደው በ345 ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው:: በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና ሰው ነበር:: በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር ነበር:: አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር:: +በድንግልና እስከ 40 ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ:: ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ በሕልም ወደ ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን ብሕትውና ምርጫው ሆነ:: +ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል:- 1.በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: (ለ60 ዓመታት በአርምሞ ኑሯል) 2.በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር:: ከእንባው ብዛት ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር:: 3.በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ ውስጥ አሉ:: 4.ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና ብሎ አያይም ነበር:: 5.ለጸሎት አመሻሽ 11:00 አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው:: 6.ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ (ሐካይ) እያለ ይገስጽ ነበር:: 7.በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን ጽሕሙን በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው የወረደ ነበር:: +እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው:: +ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ60 ዓመታት በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ100 ዓመቱ በዚሕች ዕለት ዐርፏል:: ❖አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ በረከት አይለየን:: =>ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.እግዚአብሔር አብ 2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት 3."99ኙ" ነገደ መላዕክት 4.ቅዱስ አስከናፍር 5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች 6.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ =>+"+ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን:: ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: +"+ (ያዕ. 3:7-11) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
1900Loading...
13
Media files
1920Loading...
14
Media files
2253Loading...
15
Media files
2284Loading...
16
Media files
2301Loading...
17
❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር) 2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው) 3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን የተቀበለችበት) 4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ 5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ 7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ) 8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት) 9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ 3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ 5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ 6፡ ቅዱስ ላሊበላ 7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ ++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
2121Loading...
18
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ): ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +°✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✝°+ =>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: << ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >> +ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: +ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: +ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: +ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: +ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: +በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: +አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: +ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: +በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: +"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: +"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: +'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: +አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: +ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: +ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል:: ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኳር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል - - - +እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን:: +ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56 ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: +እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን::
1941Loading...
19
https://youtu.be/03ZU6ia-c-U?si=JFbHQWaPPWKqkg8V
1600Loading...
20
Media files
1800Loading...
21
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ††† ††† ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን : ክብራችን : ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን? *አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም):: *ልቡናው የቅድስና ማሕደር:: *ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: *እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ! ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::" ††† የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ ††† ††† ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም:: በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ:: ምን ትምሕርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር:: አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው:: ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ:: ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ : ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ:: ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው:: ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ:: በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር:: ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት : ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር : ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት:: ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ:: ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ : ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ:: ††† ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:- 1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል:: 2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል:: 3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል:: ††† በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል:: ††† አባቶቻችን:- *ጥዑመ ልሳን *ንሕብ *ሊቀ ሊቃውንት *የሱራፌል አምሳያ *የቤተ ክርስቲያን እንዚራ *ካህነ ስብሐት *መዘምር ዘበድርሳን *ማኅሌታይ *ልዑለ ስብከት እያሉ ይጠሩታል:: ††† የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: ††† ግንቦት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ 2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 3.ቅዱሳን ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች) 4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች) 5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት 6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት 8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ 9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ) 10.አባ በኪሞስ ጻድቅ ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና ††† "እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ:: እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ:: በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም:: እግዚአብሔር ያውቃል:: ወደ ገነት ተነጠቀ:: ሰውም ሊናገር የማይገባውን: የማይነገረውን ቃል ሰማ::" ††† (2ቆሮ. 12:2-5) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
1970Loading...
22
Media files
2540Loading...
23
††† እንኳን ለቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ††† ††† አናንያ : አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ (ሦስቱ ሕጻናት) እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም : በጸጋም : በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው:: ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል:: ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ : ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ:: አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው:: ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ "ስገዱ" ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም:: ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ:: ከዚያች ቀን በኋላ አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው : በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል:: ቅዱሳን አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል (ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ) ያረፉት ግንቦት 10 ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ 500 ዓመት በፊት ነው:: ††† አምላካቸው ከእሳት ባወጣቸው ቀንም:- "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ:: ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: (በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል:: ) ድርሰታቸው 2 ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ600 ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና 33 አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ33 ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል:: ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ900 ዓመታት በኋላ (ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ400 ዓመታት) ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ:: ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት:: ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::" "ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም መጥቶ መልእክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ : ቄርሎስ : ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ:: እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል:: ††† በረከታቸው ይደርብን:: ††† ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል) 2.ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት) 3.አባ ሚካኤል ገዳማዊ 4.አባ ይስሐቅ ግብጻዊ ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" ††† (ዳን. 3:28) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
2340Loading...
24
Media files
2162Loading...
25
''እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው!'' (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) https://t.me/felegetibebmedia
2701Loading...
26
Media files
2120Loading...
27
††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት እሌኒ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† እሌኒ ንግሥት ††† ††† ቅድስት እሌኒ የታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ እናቱና እግዚአብሔር ለበጐ አገልግሎት የጠራት ቡርክት ሴት (ንግሥት) ናት:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- የቅድስቲቱ ሃገረ ሙላዷ ሮሃ (ሶርያ) አካባቢ ነው:: ነገዷ ከእሥራኤል ዝርዋን እንደሆነም ይነገራል:: ጣልያኖች "Helena" : በእንግሊዝኛው "Helen" ይሏታል:: እኛ ደግሞ "እሌኒ" እንላታለን:: ትርጓሜው "ጥሩ ምንጭ" : አንድም "ውብና ደግ ሴት" ማለት ነው:: ቅድስት እሌኒ በመልካም ክርስትና አድጋ እንደ ቤተ ክርስቲያን መተርጉማን ተርቢኖስ የሚባል ነጋዴ አግብታ ነበር:: ወቅቱም ዘመነ ሰማዕታት ነበር:: በማይሆን ነገር ጠርጥሮ ባሕር ላይ ጥሏት ንጉሥ ቁንስጣ አግኝቷታል:: እርሱም የበራንጥያ (የኋላዋ ቁስጥንጥንያ) ንጉሥ ነበር:: ቅድስት እሌኒ ከቁንስጣ የተባረከ ልጅን ወለደች:: ቆስጠንጢኖስ አለችው:: በልቡናው ፍቅርን : ርሕራሄን : መልካምነትን እየዘራች አሳደገችው:: ቅዱሱ አባቱ በሞተ ጊዜ ተተክቶ ነገሠ:: ቅድስት እሌኒንም ንግሥት አደረጋት:: ያንን የአርባ ዓመት ግፍ በአዋጅ አስቀርቶ ለክርስቲያኖች ነፃነትን : ክብርን በይፋ ሰጠ:: አንድ : ሁለት ብለን የማንቆጥረውን ውለታ ለምዕመናን ዋለ:: ከነዚህ መልካም ምግባራቱ ጀርባ ታዲያ ቅድስት እናቱ ነበረች:: ቅድስት እሌኒ ጾምን : ጸሎትን ከማዘውተሯ ባሻገር አጽመ ሰማዕታትን ትሰበስብ : አብያተ ክርስቲያንን ታሳንጽ : ለነዳያንም ትራራ ነበር:: በኢየሩሳሌምና አካባቢው ብቻ ከሰማንያ በላይ አብያተ መቃድስ አሳንጻለች:: እነዚህንም በወርቅና በእንቁ ለብጣቸዋለች:: በዘመኗ መጨረሻም የጌታችንን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ከተቀበረበት አውጥታ ለዓለም በረከትን አስገኝታለች:: እናታችን ቅድስት እሌኒ እንዲህ በቅድስና ተመላልሳ በሰማንያ ዓመቷ በ330ዎቹ አካባቢ ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያናችንም ስለ ቅድስናዋና ውለታዋ በዓል ሠርታ : ታቦት ቀርፃ ስታከብራት ትኖራለች:: ††† ከቅድስት እናታችን ምልጃና በረከት አምላካችን ያድለን:: ††† ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት እሌኒ ንግሥት 2.ቅዱስ ስልዋኖስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ነገር ግን ለበጐ ነገር ጥበበኞች : ለክፉትም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ:: የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን::" ††† (ሮሜ. ፲፮፥፲፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
2261Loading...
28
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።» ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰናይ አዳር #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
2562Loading...
29
Media files
2290Loading...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ): ✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ 🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ 📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል። 💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። 📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው። 📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል። 📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።      ቅዱሱ በኤፌሶን 📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ። 📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። 💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ። 📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች። 📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። 📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። 📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። 💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች። 📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት። 📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል። የፍቅር ሐዋርያ 📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል።  በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር። 💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ) 📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና። 📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል። 📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡ ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት። 📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው። 📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት። 📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

1. ወንጌላዊ 2. ሐዋርያ 3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም 4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ) 5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) 6. ወልደ ነጐድጓድ 7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር 8. ፍቁረ እግዚእ 9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) 10. ቁጹረ ገጽ 11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) 12. ንስር ሠራሪ 13. ልዑለ ስብከት 14. ምድራዊው መልዐክ 15. ዓምደ ብርሃን 16. ሐዋርያ ትንቢት 17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን 18. ኮከበ ከዋክብት 🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲 🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+ +በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: +ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: +ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: +በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: +ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል:: +ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: +ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: +የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል:: ❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከበረከቱም አይለየን:: =>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) 2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ 3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት 4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ 4.ቅድስት እንባ መሪና 5.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

#የኔ_ትውልድ_ባለውለታውን_ያሳክማል "ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ታሟል" ብዙዎቻችንን ወደ መንፈሳዊ መንገድ የመራን፣ በሐጢአት የገገረውን ዓለት ልባችንን በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ ያቀለጠልን፣ ልንጠፋ ጫፍ ስንደርስ በሚስረቀረቅ ድምፁ የመለሰን፣ በአገልግሎቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነ፣ መዝሙሩ ወደ ጸሎት ያደገለት ታላቁ አባታችን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ሕክምና ይፈልጋል። ጠንካራ ቤተ ክህነት ቢኖረን ኖሮ ይህ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መታከሚያ ባላጣ ነበር። ዳሩ ግን...ሆድ ይፍጀው። እኛ የመዝሙራቱ ተጠቃሚዎች ግን ባለውለታችንን አንተውም። ዘማሪ ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስን ለማሳከም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ....እነሆ በረከት! መርዳት የማትችሉ በማጋራት ተባበሩ። ድጋፋችንን አድርገን ወዳጅነታችንን እንግለጥ CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch
Show all...
👍 2

🙏 1