cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Show more
Advertising posts
979
Subscribers
-124 hours
No data7 days
+4330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

††† እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ኤርምያስ ††† ††† ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በስድስት መቶ አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካህናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕፃንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማኅጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: (ኤር. 1:5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከሰባ ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል:: ዘመኑ ዘመነ-ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ በ722 አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው:: በኋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ በ586 ባቢሎን አወረዳቸው:: ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብጽ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት : ነቢይ : መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ : ሕዝቡን ከሰባ ዓመታት በኋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት : ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል ሰባ ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ሃምሳ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ : በመጽሐፈ ባሮክ : በገድለ ኤርምያስ : በዜና ብጹዐን : በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: ††† ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ††† ግንቦት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ (ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ ††† "ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል : ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር : ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና : በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም::" (ማቴ. ፳፫፥፴፯-፴፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

እንኳን ለዳግማ ትንሳኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሰን አደረሳችሁ። መልካም በዓል
Show all...
👍 6
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† እንኩዋን ለጻድቁ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† +"+ አቡነ መልከ ጼዴቅ +"+ =>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ መልከ ጼዴቅን ብዙ ሰው ሽዋ (ሚዳ) ውስጥ በሚገኘው አስደናቂ ገዳማቸው ያውቃቸዋል:: ገዳሙ በእድሜ ጠገብ ዛፎች ያጌጠ ከመሆኑ ባሻገር በጻድቁ ቃል ኪዳን ምክንያት በቦታው የሚቀበር ሁሉ አካሉ አይፈርስም:: የጻድቁስ ዜና ሕይወታቸው እንደምን ነው ቢሉ:- +አቡነ መልከ ጼዴቅ በሸዋ ነገሥታት ዘመን የነበሩ: የንጉሱ ዓምደ ጽዮን የቅርብ ዘመድ ነበሩ:: የጻድቁ ወላጆች ፍሬ ጽዮንና ዐመተ ማርያም ይባላሉ:: አቡነ መልከ ጼዴቅ ገና በሕጻንነታቸው ሥርዓተ መንግስትን አጥንተዋል:: +በሁዋላ ከመምሕር ዘንድ ገብተው ብሉይ ከሐዲስ ተምረው ሲያጠናቅቁ ይሕንን ዓለም ናቁና ከቤተ መንግስቱ አካባቢ ጠፍተው ወደ አቡነ አሮን መንክራዊ ዘንድ ሔደው መንኩሰዋል:: +ነገሩ በቤተ መንግስት አካባቢ ሲሰማ ወላጆች አለቀሱ:: አቡነ አሮንም ተከሰው ነበር:: ነገሩ ግን ከእግዚአብሔር ነበርና አቡነ መልከ ጼዴቅን መልዐክ እየመራ አምጥቶ አሁን ገዳማቸው ያለበት ሸዋ (ሚዳ) አደረሳቸው:: +በዚያ ትንሽ በዓት ሰርተው ለዘመናት ተጋድለዋል:: ዋሻዋም ደብረ መድኃኒት ትባላለች:: ጻድቁ ከጾምና ጸሎታቸው በተረፈ ዓርብ ዓርብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሕማማት በማሰብ ጀርባቸውን 300 ጊዜ ይገርፉ: ደቀ መዛሙርቱንም ግረፉኝ ይሉ ነበር:: አንድ ጊዜም እጃቸውንና እግራቸውን በትልልቅ ችንካሮች ቸንክረውት ደማቸው ሲፈስ ተገኝቷል:: +በመጨረሻ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጌታን ኢትዮዽያውያንን ማርልኝ አሉት:: ጌታችንም መለሰ:- "በስምህ ያመኑትን: በቃል ኪዳንህ የተማጸኑትን: ገዳምሕን የተሳለሙትን እምርልሃለሁ::" +ጻድቁም ብዙ ተአምራትን ሰርተው በዚሕች ቀን አርፈዋል:: አቡነ አምሃ ኢየሱስም በክብር ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀብሯቸዋል:: =>አምላካችን እግዚአብሔር ከጻድቁ ዋጋና በረከት አይለየን:: =>ግንቦት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አቡነ መልከ ጼዴቅ ካህን (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ) 2.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት 3.ቅዱሳን ሶሲማና ኖዳ ሰማዕታት (የታላቁ ፊቅጦር ተከታዮች የነበሩ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው) 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) =>+"+ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትን ወደ እርሱ ይጥራ:: በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት:: የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል:: ጌታም ያስነሳዋል:: ኃጢአትም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሠረይለታል:: እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ:: ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ:: የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች:: +"+ (ያዕ. 5:14) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

✝✞✝ እንኩዋን ለእናቶቻችን "ቅዱሳት አንስት" ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +*" ቅዱሳት አንስት "*+ =>ከትንሳኤ ሳምንት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" (የተቀደሱ ሴቶች) ተብላ ትጠራለች:: +በወቅቱ በኢየሩሳሌምና ዙሪያዋ ከተከተሉት ሴቶች ጌታችን 36ቱን መርጧል:: እነዚህ እናቶች ከዋለበት ውለው : ካደረበት አድረው : የቃሉን ትምሕርት ሰምተዋል:: የእጁንም ተአምራት አይተዋል:: ፈጽመውም አገልግለውታል:: +መጽሐፍ "አንስተ ገሊላ ኩሎን:: አዋልዲሃ ለጽዮን:: አስቆቀዋሁ ለመድኅን:: ከመ ዖፈ መንጢጥ እንዘ ይሤጽራ ገጾን::" ይላልና በዕለተ ዐርብ ፊታቸወውን እየነጩ : ደረታቸውን እየደቁ : እንባቸውም እንደ ጐርፍ እየፈሰሰ አብረውት ውለዋል:: +ጌታም ፍጹም ፍቅራቸውን ተመልክቷልና ከሁሉ አስቀድሞ ትንሳኤውን ለእነሱ ገለጠላቸው:: እነርሱም ትንሳኤውን በመፋጠን አብሥረዋል:: "ሰበካ ትንሳኤ፡ አዋልዲሃ ለጽዮን" እንዳለ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" ተብላ ትከበራለች:: =>አምላካችን በፍቅርና በቅድስና ጌጥ ካጌጡ እናቶቻችን በረከትን ያድለን:: =>+"+ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው:- 'እናንተስ አትፍሩ:: የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና:: እንደተናገረ ተነስቷልና በዚሕ የለም:: የተኛበትን ሥፍራ ኑና እዩ:: ፈጥናችሁም ሒዱና ከሙታን ተነሣ: እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማቹሃል:: በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው' . . . እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው:: እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት:: +"+ (ማቴ. 28:5-10)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+ +ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል:: +አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል:: +በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል:: +እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና:: +ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል:: +ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም:: +ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች:: +ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር:: +ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች:: ❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ) 2.አባ ብሶይ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ 4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን 4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5፡ አባ ዜና ማርቆስ 6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት 8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
Show all...
👍 1