1 741
Subscribers
+224 hours
+37 days
-730 days
Posts Archive
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የስራ ሂደት በስሩ ከሚገኙ የአራቱ ማዕቀፍ አስተባባሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር ላለፉት 3 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፓርትን ግምገማ አጠናቀቀ።
ስራ ሂደቱ ባለፉት ቀናት በነበረው መድረክ በስሩ የሚገኙ ኬዝ ቲሞችና ፈፃሚዎችን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ያደመጠ ሲሆን ከቀረቡት ሪፓርቶች በመነሳትም ሰፋ ያለ ግብረ-መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን ገንቢ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግም ለቀጣይ የትግበራ ወቅት እንደ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የጋራ መግባባትና የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም
የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የስራ ሂደት በስሩ ከሚገኙ የአራቱ ማዕቀፍ አስተባባሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርትን መገምገም ጀምሯል።
የአፈፃፅም ሪፓርት ግምገማው በስራ ሂደቱ መሪና የኮሌጁ ም/ዲን በሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ የሚመራ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋም በመድረኩ ተገኝተዋል።
መድረኩ በቀጣይ ቀናትም ቀጥሎ የሚደረግ ሲሆን የሁሉም ሪፓርት በቅደም ተከተል ከቀረበ በኋላ ግብረ መልስ በመስጠትና ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚጠናቀቅም ይሆናል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሐምሌ 24.2015 ዓ.ም
በ2015 ዓ.ም የተቋማት ውድድር 3ኛ ጨዋታውን ከብዙሃን መገናኛ ጋር ያደረገው ብድናችን ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ኢትዮ-ጣሊያን 2-1 ብዙሃን መገናኛ
ዳዊት አበራ⚽️
እዮብ መሰለ⚽️
የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህትና ስልጠና የስራ ሂደት በስሩ የሚገኙ ዲፓርትመንቶችና የስራ ክፍሎችን ጥራትን መሠረት ባደረገው የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ ካላንደር የሶስተኛ ተርም እና አመታዊ ሪፖርት ግምገማ የሂደቱ ሃላፊና አቶ ኤሊያስ አህመድ እንዲሁም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በተገኙበት አካሂዷል።
በመድረኩ የሁሉም ዲፓርትመንት ሀላፊዎች በቅደም ተከተል ሪፓርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሪፓርቶች ላይም ጠንካራ ጎኖችን እና ውስንነት የታየባቸው ተግባሮች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም የታዩ ጠንካራ ጎኖች በቀጣዩ የትምህትና ስልጠና ዘመንም በተሻለ ጎልብተው እንዲቀጥሉ በማበረታታት እንዲሁም የነበሩ ውስንነቶች ላይ በጋራ በመስራት ትምህትና ስልጠናውን ከዚህ ከፍ ባለ ጥራት ለመስጠት መግባባት ላይ ተደርሶ የእለቱ መድረክ ፍፃሜውን አጊኝቷል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሐምሌ 20.2015 ዓ.ም
ነገን ዛሬ እንተክላለን!
በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ 800 ሺህ ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በዛሬው ቀን ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች ችግኝ በመትከል መርሃ-ግብሩ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ለዚሁ መርሃ-ግብር በተዘጋጀው የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ በመገኘ ችግኞችን ተክለዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛ ዓመተ ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ ይላል።
ኢድ ሙባረክ!!
Calling all innovative minds in Ethiopia! Solve IT 2023 registrations are now OPEN! Don't miss your opportunity to be part of the most exciting innovation competition in Ethiopia.
Register at solveit-et.com
Telegram bot @solveit_et_bot
.
.
.
የሶልቭ ኢት 2023 ምዝገባ ተጀምርዋል! በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አጓጊ የሆነውን የፈጠራ ውድድር አካል ለመሆን ዕድሉ እንዳያመልጥዎት።
#SolveIT2023 #SolveITEthiopia #SolveITet #SolveITWithTech #InnovationCompetition #Startups #icogacc #USEmbassy #DashenBank
.
.
.
ለበለጠ መረጃ ፔጃችንን ይከታተሉ!
facebook.com/SolveIT.et
Instagram.com/SolveIT.et
Telegram: @solveit2023
TikTok.com/Solveit2023
Email: contact@solveit-et.com
Phone no: +251 991 440049
Available now! Telegram Research 2025 — the year's key insights 
