Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
Відкрити в Telegram
Показати більше
2 376
Підписники
+724 години
+937 днів
+36330 днів
Архів дописів
Repost from N/a
የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ውጤታማነት እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ኢንተርፕራይዞች ፍትሃዊ መንግስታዊ ድጋፎች ተጠቃሚ በማድረግ የኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አድርገዋል።
ኮሌጆቹ ድጋፍ በመስጠት በአስተዳደሩ ጉልህ ስራዎችን እየሰሩ ሲሆን በተለይም በ4ቱ የድጋፍ ማእቀፎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችንና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪግ ኢንደስትሪዎችን የምርትና ምራታማነት በማሻሻልና ብቁ የሆነ የሰዉ ሐይል በማፍራትና የሥራ እድል እንዲፈጥሩ በማስቻል ድጋፍ እየሰጡ እንደሚገኙ ይታወቃል፤
የሁለቱ ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬቶች በጋራ በመሆን ይህን መድረክ ያዘጋጁ ሲሆን ለባለድርሻ አካላትም የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ጽንሰ ሃሳብ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ደካማ ጎኖችን በመንቀስ ለቀጣይ የመፍትሔ አማራጮች የ2016 ዓ.ም የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ውጤት አምጪ ተግባራት ላይ ትኩረት ይደረጋል፤
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመድረኩ ተገኝተው የክትትልና ድጋፍን በማጠናከር፤ ከኢንተርፕራይዝ ልየታ ጀምሮ እስከ ምዘና እና ሀብት ልኬት እንዲሁም ደረጃ ሽግግር ድረስ ያሉት ተግባራት በጥብቅ ቅንጅት መከናወን እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 4/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋማት መካከል የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ አቅሞችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለ ድርሻ ተቋማት ጋር እካሄደ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የጥ/ቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አገልግሎት አቅዶ ከሚሰራባቸው ግቦች መካከል በዘርፉ ላይ የሚታዩ ውስነቶችን በሚያሻሽል መልኩ የጥናትና ምርምር፣ የፈጠራ ስራዎች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር የSTEM እውቀቶች እንዲሁም የማህበረሰብ አገልሎትቶችን የማሳደግ ስራዎች የሚገኙበት ሲሆን እነዚህን ስራዎች ውጤታም ለማድረግ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር አጋርነትና ትብብር አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጅ የውይይት መድረክ ነው::
በዕለቱ በነበረው መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ክበብ ተጠሪዎች በውይይት መድረኩ የተካፈሉበትም ነበር::
በመድረኩ ለተካፈሉ ባለ ድርሻ ተቋማትም በቴ/ሙ/ት/ስ ስትራቴጂ ላይ ሰፊ ገለጻ በማድረግ በSTEM እና INNOVATION እንዲሁም ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እና የ2016 ረቂቅ ሰነድ ላይ በመወያየት የጋራ ስምምነት ላይ መድረስም ተችሏል፡፡
በመጨረሻም ግንዛቤ ከመፍጠሩ ባሻገር በቴ/ሙ/ት/ስ ዘርፍ ኮሌጁ ውስጥ ያለው አቅምን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ባዩት ነገር መደነቃቸውን እና ከኮሌጁ ጋር በትብብር ለመስራት ይበልጥ ፍላጎት እንዳሳደረባቸው ጨምረው ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስራ ሂደት በስሩ ለሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እንደ ተቋም በሂደቱ በኩል በወረደው ዕቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና ሰጠ::
ሂደቱ በዛሬው እለት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሽ/ኢ/ኤ አገልግሎት ዕቅድ ዙሪያ በሂደቱ እስተባባሪዎች ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የሂደቱ ፈፃሚ አሰልጣኝ መምህራን የግል እቅድ ዝግጅትና አተገባበር ላይም ያተኮረ ስልጠና ያካተተም ነበር::
የስልጠናው ተሳታፊ እሰልጣኝ መምህራንም በተሰጣቸው ስልጠና ላይ ያላቸውን ሀሳብ በማጋራት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም በስራ ሂደቱ ሃላፊ ማብራርያ ተሰቶባቸው መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም
