en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Open in Telegram
2 366
Subscribers
+1224 hours
+977 days
+37130 days
Posts Archive
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ።  በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙት የመንግስት ኮሌጆች አንዱ የሆነው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ስርዓት የጥራት ማረጋገጫ እና የብቃት መመዘኛ ISO 9001:2015 QMS አለም አቀፍ ሰርተፊኬት አገኘ። በሰርተፊኬት ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ በድሬዳዋ 233 አነስተኛ ፣ 70 መካከለኛ እና 36 ከፍተኛ የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንደተመዘገበ ጠቁመው የምስራቋ የኢንደስትሪ ኮሪደር እንደመሆኗ መጠን በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎችና ከፍተኛ የሰው ሃይል እንደሚያስፈልጋት አረጋግጠዋል። ጥራት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት ፤ ጥራት ባለው የትምህርት ስርዓት እና ምዘና ማለፍ ይገባል ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ በብቃት የሰለጠነ የሰው ሃይልን በማፍራት ለኢንደስትሪው ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ በእንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃ እድሉን ካገኙ 20 ትቋማት መካከል 5ቱ እራሳቸውን በጥራት ደረጃ ማሳለፍ መቻላቸውንና ከእነዚህም መካከል የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዱ መሆኑን አስታውቀዋል። አክለውም ይህ የጥራት ማረጋገጫ ከምስራቅ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ገልፀው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የስራ እድልን ከመፍጠር በዘለለ ትልልቅ ድርጅቶችንና ኩባንያዎችን የሚያንቀሳቅሱ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል። የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን ለኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ያስረከቡት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ተቋማቸው በሀገሪቱ 9 የተደራጁ የጥራት ላቦራቶሪዎችን በማደራጀት እየፈተሸ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በግብርና ፣ በምግብ ስርዓት ፣ በኢንደስትሪ ምርት እና በትምህርት ስልጠና የብቃት ደረጃዎችን የመለካት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው በአጠቃላይም 50 ሚሊየን ዶላር በመመደብ የጥራት ደረጃዎችን ለማሻሻልና ለመፈተሽ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በመርሃግብሩ ማጠቃለያም ለኮሌጁ የትምህርት ስርዓትና የጥራት ደረጃ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን የእውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል። ©️ Diretv ህዳር 3/2017

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ አዲስ ለማሰልጠን የተቀበላቸውን ሰልጣኞች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን አስጎበኘ:: ኮሌጁ ያዘጋጀው የጉብኝት መርሃ-ግብር በእስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን በዚህም ሰልጣኝ ተማሪዎች ጉብኝታቸውን በኮካኮላ፣ናሽናል ሲሚንት፣ሬድዋ ሞተርስ እና ኒውዌቭ ፋብሪካዎች ላይ ተዘዋውረው እዲጎበኙ ማድረግ ተችሏል:: ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በኢንዱስትሪ ጉብኝት ቆይታቸው በኮሌጁ ለመሰልጠን ከመረጡት የሙያ ዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፉብሪካዎች ላይ ተመድበው የጎበኙ ሲሆን ይህም በኮሌጁ ቆይታቸው ስለሚሰለጥኑት የሙያ ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙም አስችሏቸዋል:: ይህን መሰል መርሃ-ግብር ሰልጣኝ ተማሪዎች በኮሌጁ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኃላ ያሏቸውን የስራ እድሎች ምን እንደሚመስሉ ከውዲሁ እንዲረዱና በቴ.ሙ.ስ ዘርፍ በሚኖራቸው ቆይታ መነቃቃትን እንዲፈጥርላቸው ታስቦ የተዘጋጀ የጉብኝት መርሃ-ግብር ነው:: ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኞች የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠ ጀመረ:: አዲስ ገቢ ሰልጣኞቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት የህይወት ክህሎት(Life skill )ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚቆዩ የተገለፀ ሲሆን ይህ ስልጠናም ሰልጣኞች የቀጣይ ህይወታቸውን በእቅድ እዲመሩ እንዲሁም ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙና ሚገጥማቸውን የተለያዩ ፈተናዎች በራስ መተማመን እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ልምድ የሚያገኙበት ስልጠና ጭምር መሆኑም ተነግሯል:: ሰልጣኞቹ ይህን ስልጠና አጠናቀው ሲጨርሱ በእስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎችንና ድርጅቶችን ተዘዋውረው የሚጎበኙ ሲሆን ይህም በተሻለ ግንዛቤና መነቃቃት መደበኛ ስልጠናቸውን እንዲጀምሩ የሚያደርጋቸውም ይሆናል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም

በተመሳሳይ መልኩ ለምሽት አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችም የተሰጠ Orientation መድረክ በፎቶ📸

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ኦረንቴሽን በመስጠት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አደረገ:: ሰልጣኝ ተማሪዎቹን ለመቀበል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት መድረኩን ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በቅድሚያ አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን በኮሌጁ ለመሰልጠን እዚህ በመገኘታቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ወቅቱ ሚጠይቀውን ምርጫ መርጣችሁ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለመሰልጠን ዘርፉን በመቀላቀላችሁ እጅግ እድለኞች ናችሁና እንኳን ደስ አላችሁም ብለዋል:: የኮሌጁ ዲን ቀጥለውም እንዳሉት በኮሌጁ በተለያዩ ሙያዎች ለመሰልጠን እዚህ የተገኛችሁ ወጣቶች አሁን የምትገኙበት እድሜ በራሳችሁ ውሳኔ ምትወስኑበት እድሜ ነውና ትክክለኛውን መንገድ በመምረጥ የወጣትነት እድሚያችሁን በአግባቡ በመጠቀም ለቀጣይ ህይወታችሁ ፍሬ የምታፈሩበት ሊሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል:: እሁን ላይ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ራሱን ችሎ እስከ ከፍተኛው የትምህርት እርከን ድርስ ማሰልጠን እንደጀመረ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አንድ ሰልጣኝ ከታች ከ ደረጃ 1(ሰርተፊኬት) ጀምሮ እራሱን እያሻሻለና እያበቃ እስከ ደረጃ 8(ዶክትሬት) ድረስ መድረስ እንደሚችልና መንገዱም የተመቻቸ መሆኑን ለሰልጣኞቹ ገልፀው ሰልጣኞችም ህንን ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም ለራሳቸውም ብሎም ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ብቁ ዜጋ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል:: የኮሌጁ ዲን በመጨረሻም በኮሌጁ የትኩረት ዘርፍ ተብለው የተያዙትና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት ጭምር የሚደገፉ ሁለት ዘርፎች መኖራቸውን ገልፀው እነርሱም የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት እና የኤክትሪካል/እሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ናቸው ያሉ ሲሆን በእነዚህ ሁለት ዘርፎች ውስጥ ያሉ ሙያዎችን ለመሰልጠን የመረጡ ሰልጣኞችም ከምንም በላይ እድለኞች ያረጋቸዋል ብለዋል:: በመጨረሻም ሰልጣኝ ተማሪዎች በኮሌጁ የሚኖራቸው ቆይታንና የትምህርትና ስልጠናው ሂደት ምን እንደሚመስል በዝርዝር ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በተጨማሪም ስልጠናቸውን አጠናቀው እስኪወጡ ድረስ በኮሌጁ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ወቅት የተቀመጠላቸውን መብትና ግዴታዎች ከወዲሁ እንዲያውቋቸው በትምህርትና ስልጠና አስተባባሪው በኩል ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል:: ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት በኮሌጁ በሚኖራቸው ቆይታ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን እሱን እንዳጠናቀቁ የትብብር ስልጠና የሚወጡባቸውን የተለያዩ እንዱስትሪዎችና ተቋማትን እንዲጎበኙ መርሃ-ግብር መያዙም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ሊሰሩ በታቀዱ ቴክኖሎጂዎች ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ:: በመድረኩ አሰልጣኝ መምህራን በበጀት አመቱ ሊሰሯቸው ያቀዷቸውን የቴክኖሎጂ አርዕስቶች ለጥናትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል በግልና ቡድን ባስገቡት መሰረት ስለሚሰሩት ቴክኖሎጂ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል:: በተጨማሪም በዕለቱ በቀረቡት የቴክኖሎጂ አርዕስቶች ላይ ከሚመለከታቸው ዲፓርትመንቶች እና ከክፍሉ ባለሙያዎች እንዲሁም አሰልጣኝ መምህራን ጋር በመሆን ከማህበራዊ ጠቀሜታ፣ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፣ከአካባቢ ደህንነት እና ከቴክኖሎጂ አንጻር ገንቢ አስተያየት ተሰጥቶባቸው ወደ ቀጣይ ስራ እንዲገቡም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት እቅድ እና የዝግጁነት ምዕራፍ አፈፃፀም ሪፖርት በተመለከተ የኮሌጁ ማህበረሰብ በተገኘበት የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ በቅድሚያ በኮሌጁ የዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን በዋነኛነትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሆነውን የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት እውቅና ያገኘበትን የላቀ ትግበራ ያከናወነበት ምዕራፍም ነበር:: በተጨማሪም በዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት እንደ ተቋም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ከዋና ስራ ሂደቶች ጀምሮ እስከ ፈፃሚው ድረስ የጠራ እቅድ ዝግጅት የተከናወነበት ወቅት ሲሆን እንዲሁም የአረንጏዴ አሻራ፣የደም ልገሳን ጨምሮ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና መሰል ትግበራዎችም በዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት እንደተከናወኑ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ሪፖርት ቀርቧል:: በመጨረሻም የ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የቀረበ ሲሆን የቀረበውን እቅድ መነሻ በማድረግም ከመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ ተሰቶበት ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጎበታል:: በማጠቃለያውም በተጠናቀቀው በጀት አመት የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማስቀጠል እንዲሁም በ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተገልፆ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም