en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Open in Telegram
2 387
Subscribers
+424 hours
+677 days
+35730 days
Posts Archive
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ #የኢንዱስትሪ_ቴክኒካል_አማካሪ_ቦርድ ለአዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎች በሙያ ስልጠና እና የስራ አለም እንዲሁም በኢንዱስትሪው ተቀባይነት ዙሪያ ኦረንቴሽን ሰጥቷል። በተጨማሪም አሁን በስራ ላይ የሚገኙ የኮሌጁ ሴት ሰልጣኝ ተማሪዎች ለአዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎች ያላቸውን ተሞክሮ አካፍለዋል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 8/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቅርቡ በሳውዲ አረብያ የስራ ዕድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ።   ኮሌጁ የሀገራችን መንግስት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር በተፈራረመው ስምምነት መሰረት በአስተዳደሩ ስራና ክህሎት, ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  በኩል የተፈጠረውን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡ ወጣቶችን በተመረጡት የሞያ ስልጠናዎች ላይ ወጣቶችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀምሯል። ይህም ስልጠና ቀጣይነት ያለውና በዙር የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛው ዙር ላይ ስልጠና እየተሰጣቸው የሚገኙት #ምሩቃን ሆነው የተመቻቸውን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡ ወጣቶች ናቸው። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 5/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በዘንድሮ የትምህርትና ስልጠና ዘመን የተቀበላቸውን አዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወደ መደበኛ ስልጠና ከመግባታቸው አስቀድሞ ሰልጣኞችን በሁሉም ረገድ ዝግጁ የሚያደርጋቸውን የLife Skill ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።  የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 5/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በዘንድሮ አመት አዲስ ገቢ ለሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በ TVET Policy & Strategy ላይ ያተከሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።    በቀጣይ ቀናትም አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ትምህርትና ስልጠናቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ የLife Skill ስልጠና የሚወስዱም ይሆናል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ከ የካቲት 27 ጀምሮ ለ 1 ሳምንት እየመዘገ እንደሆነ ይታወቃል።   ሆኖም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡና  ከአጎራባች ክልሎች ጭምር የሚመጡትን ተመዝጋቢዎች ታሳቢ በማድረግ ኮሌጁ ምዝገባውን እስከ ሚቀጥለው ሳምንት  ያራዘመ መሆኑን እየገለፀ  እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች መታችሁ መመዝገብ ያልቻላችሁ ትምህርትና ስልጠና ፈላጊዎች በአካል በመገኘት መመዝገብ እንደምትችሉ ኮሌጁ ለመግለፅ ይወዳል።

የ2015 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ።