cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

Show more
Advertising posts
1 368
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-4930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስልጤ ዞን ጅብ በአንድ ቀን ሁለት ህጻናቶች ላይ ጉዳት አደረሰ 👉 መኖሪያ ቤቷ በራፍ ላይ በጅብ የተበላችው ህጻን የመትረፍ እድሏ አነስተኛ ነው በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ጦራ መልታሜና ጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌዎች ላይ በሁለት ህፃናት ላይ ጅብ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የጦራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ አማን ከድር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በትላትናው እለት አመሻሽ 12:30 አካባቢ በጦራ መልታሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ መናፈሻ መንደር አካባቢ በመኖሪያ ቤቷ በር ላይ የቆመች አንዲት የሶስት አመት ህፃን ጀቡ ወደ ጫካ ይዟት ሊገባ ሲል በህብረተሰቡ ብርቱ ትግል መትረፏ ተገልጿል። ህፃኗ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ሪፈር ተልካ ህክምና እየተደረገላት የሚገኝ ሲሆን የመትረፍ እድሏ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።በተመሳሳይ በትላንትናው እለት በጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌ ላይ የ10 አንድ ህፃን ወደ መስኪድ እየተጓዘ እያለ በጅብ ተበልቷ በህይወት ተርፎ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን አቶ አማን ከድር ጨምረው ተናግረዋል። @Addis_News @Addis_News
Show all...
መርጌታ የሐንስ የበህል ህክምና    በውጪም ላሉ በስልክ በቴሌግራም ማውራት እንችላለን በኮሜንት ስልኮትን አያስቀምጡ!!!! # ለስንፈተ ወሲብ # ለንግድ ንግድ ጀምረው እንቢ ላላቸው ገና ለሚጀምሩ # ብር ለሚያጠፋ ገንዘብ ለመያዝ # ለውጪእድል እንቢ ላላቸው # ለፍርሀት ሰፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ # ለትምህርት እያነበቡ አልያዝ ላላቸው ለማንኛውም ትምህርት # ለፀጉር መመለጥ እንዲሁም ፂም ለሌላቸው # ፍርሀት ጭንቀት አይነጥላ ላለባቸው ብቻ ያለቦትን ችግር ምንም ቢሆን እንመካከርበትና መፍትሄ እንፈልጋለን።ጥንታዊ ጥበባችን አሁንም አለ እባካችው ነጭ አምላኪ አንሁን እነሱም የኛን ሰርቀው ነው ። # ይህ መልክት ላላዩ እንዲደርስ ሼር በማድረግ ይተባበሩ። በሀገር ውስጥም በውጪም ላሉ መፍትሄ አለን ይምጡ ፡፡፡በስልክ 0929917645
Show all...
ካህኑ በድንጋይ ተወግረው መገደላቸው ተሰማ አርብ መጋቢት 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ትናንት መጋቢት 14/2015 ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች አረጋግጠውልኛል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎች ተናግረዋል። ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙም ተሰምቷል። @Addis_News @Addis_News
Show all...
የትግራይ ክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች፤ ለሰራተኞቻቸው ብድር እንዲሰጡ ተፈቀደላቸው ‼️ በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ እስከሚከፈላቸው ድረስ ከመስሪያ ቤቶቻቸው ብድር እንዲወስዱ ተፈቀደላቸው። የክልሉ መስሪያ ቤቶች ለሰራተኞቻቸው ማቅረብ የሚችሉት ከፍተኛ ብድር፤ አራት ሺህ ብር እንደሆነ ተገልጿል። የትግራይ ክልል መንግስት ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት ክልሉን ለቀቆ ከወጣበት ከሰኔ 2013 ዓ.ም አንስቶ፤ ላለፉት 21 ወራት ደመወዝ አልተከፈላቸውም። የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ባደረጉት ስምምነት መሰረት ሊቋቋም ይገባ የነበረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስት እስካሁን ባለመቋቋሙ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር ወደ ክልሉ ገንዘብ አለመላኩን ባለፈው ሳምንት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቆ ነበር። እስካሁን በጀት ያልተለቀቀላቸው የክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፤ በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ ካለው ገንዘብ ውስጥ ለሰራተኞቻቸው ብድር ለመስጠት ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱን የክልሉ የገንዘብ እና ፕላን ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ ገብረሚካኤል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ቢሮው በክልሉ ለሚገኙ ለሁሉም የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም መስሪያ ቤቶች ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 7፤ 2015 በጻፈው ደብዳቤ፤ ብድር እንዲሰጡ መፍቀዱን ኃላፊው አስታውቀዋል። የዶ/ር አረጋዊ ፊርማ ያረፈበት ይኸው ደብዳቤ፤ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች “ሙሉ ለሙሉ ባልተከፈተው ከበባ” ምክንያት አሁንም ችግር ውስጥ መሆናቸውን አትቷል። ለክልሉ የመንግስት ተቋማት ደመወዝ መክፈል የሚያስችል በጀት እስከሚመደብ ድረስም፤ መስሪያ ቤቶቹ በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ ካለው ገንዘብ ላይ ከአራት ሺህ ብር ያልበለጠ ብድር ለሰራተኞቻቸው እንዲያቀርቡ እንደተፈቀደ በደብዳቤው ላይ ሰፍሯል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር @Addis_News @Addis_News
Show all...
Good News : ባለፈው ሳምንት በሰራተኛዋ ተሰርቃ የነበረችው ህጻን ሱሉልታ ተገታለች:: ህጻኗን ከሱልሉታ ቤተሰቦቿ ተረክበዋል ቀሪው መረጃ ይዤ እመለሳለሁ:: @Addis_News @Addis_News
Show all...
ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ የተግባር ሥራ በተያዘው መጋቢት ወር በድሬዳዋ ከተማ ይጀመራል! ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር እና የአሠራር ሥርዓት ላይ ሰነዶችን በማዘጋጀት የዝግጅት ጊዜውን እያጠናቀቀ በመሆኑ የተሳታፊ ልየታ የተግባር ሥራ በተያዘው የመጋቢት ወር በድሬዳዋ ከተማ ይጀመራል። (ኢ ፕ ድ) @Addis_News @Addis_News
Show all...
የፓለቲካ ተንታኙ ተደበደበ! የኛ ቴቪ በተባለው የበየነ መረብ ሚድያ የምስራቅ አፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው ንጉሴ ብርሃኑ ሲቪል በለበሱ የመንግስት አካላት ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት ተገለፀ። የስራ ባልደረባው ለኢሳት እንደገለፀው ንጉሴ ብርሃኑ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፈው ማክሰኞ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት መተቸቱን ተከትሎ በማግስቱ ረቡዕ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ሲቪል የለበሱ  የታጠቁ አካላት ከመካኒሳ አካባቢ አይኑን ሸፍነው አፍነው ወስደውታል፡፡ እነዚህ አካላት ግለሰቡን ታርጋ በሌለው ሎንግ ቤዝ መኪና ከመካኒሳ ወደ ገላን አካባቢ ወስደው ከፍተኛ ድብደባ እንዳደረሱበት ነው የተገለፀው፡፡ ግለሰቦቹ ከፍተኛ ድብደባ ካደረጉበትና ማስጠንቀቂያ ከሰጡት በኋላ ገላን አካባቢ ጥለውት እንደሄዱ የገለፀው የስራ ባልደረባው ቤተሰቦቹ ደርሰው ወደ ሆስፒታል ሊወስዱት እንደቻሉ ተናግሯል፡፡ የፖለቲካ ተንታኙ ንጉሴ ብርሃኑ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ራሱን ስቶ የነበረ ቢሆንም ላለፉት ሶስት ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ አርብ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም ወደ ቤቱ መመለሱን ባልደረባው ለኢሳት ገልጧል፡፡ ከዚህ በኋላ በሚድያ ላይ ብናይህ እንገድልሃለን ሲሉ አስጠንቅቀውኛል ሲል የፖለቲካ ተንታኙ ንጉሴ ብርሃኑ እንደነገረው ባልደረባው አክሏል፡፡ ( ኢሳት ) @Addis_News @Addis_News
Show all...
ሰበር መረጃ! በራያ እና ዋግ ግንባር ያለውን የመከላከይ ሰራዊት ለማስወጣት በርካታ ተሽከርካሪዎች መቅረባቸው ተሰማ! ዛሬ ማምሻውን እስከ 200 የሚደርሱ አይሱዙ እና FSR ተሽከርካሪዎች ባዷቸውን በመከልከያ ሰራዊት አባላት ታጅበው ወደየግንባሮቹ ሲጏዙ ማምሸታቸውን ምንጫችን የገለፀ ሲሆን ሰራዊቱን ከግንባር ለማስወጣት እንደሆነ ገልፆል:: ቀደም ሲል በምዕራብ ትግራይያለው ሰራዊት በጎንደር በኩል አድርጎ መውጣቱን ገልፀን የነበረ ሲሆን ይሄኛውም በተመሳሳይ ሊወጣ ዝግጅቱን ጨርሷል::*ትህነግ ትጥቅ ባልፈታበት እና ባልተበተነበት : ባስ ብሎ ለዳግም ወረራ ዝግጅት እያደረገች ባለበት ሁኔ ሰራዊቱ ከትግራይ ለቆ መውጣቱ ህዝቡን ግራ አጋብቶታል ያለው ምንጫችን ሀኔታውን በትኩረት መከታተል ይገባል ብሏል::     (ሮሐ ኒውስ ) @Addis_News @Addis_News
Show all...
🟢 ትርፋማነቱ የተረጋገጠ አዋጭ ኢንቨስትመንት እነሆ ‼️ 🟢 የመጨረሻዎቹን የአያት አክሲዮን ማህበር ባለ ድርሻዎች ይቀላቀሉ ◼️ አያት አ.ማ በ 2014 ዓ.ም 44% ወይም 392,853,318 ብር የትርፍ ክፍፍል ለባለ አክሲዮኖቹ አከፋፍሏል ◼️ ይህም ማለት የ 1,000,000 ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለ አክሲዮኖች በ2014 ዓ.ም. ብቻ 440,000 ብር ትርፍ አግኝተዋል ◼️ ከትንሽ ገንዘብ ጀምሮ :- 17,675 ብር እስከ ሚሊዮኖች መግዛት ይችላሉ ◼️ ከፍ ያለ የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ዳጎስ ያለ የአክሲዮን ትርፍ ያግኙ ◼️ ሁሉም ድርጅቶች በስራ ላይ ስለሆኑ አክሲዮኑን ከገዙ ከአንድ ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ ◼️ ቀላል የክፍያ አማራጭ አለው 35% ቅድሚያ ከፍለው ቀሪውን በየዓመቱ በሶስት ዓመት ከፍለው መጨረስ ይችላሉ ለበለጠ መረጃ  ፦ ☎️  በ 0911085103 ይደውሉ ( Telegram, whatsApp )
Show all...
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በባለ ሶስት እና አራት እግር የ“ባጃጅ” ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 8፤ 2015 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታወቀ። የ"ባጃጅ" ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከአምስት ብር በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ ቢሮው ገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @Addis_News @Addis_News
Show all...