cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ETHIO NEWS

✍ በየእለቱ ትኩስ እና አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ ለእውነተኛ ለትክክለኛ መረጃ ብቻ እንሰራለን። ✍

Show more
Advertising posts
6 162
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-3430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from Skyline media
ይህን ያውቁ ኖረዋል..🇪🇹🇸🇴 ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት ከገባች ምን ይፈጠርባታል! በሶማሊያ ያለው 20,000 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ከወጣ የአልሸባብ ሃይል ሶማሊያን ከ72 ሰአት በነሰ ጊዜ ይቆጣጠራታል።ምክንያቱም ሶማሊያ ሶማሊያ በጣም ደካማ ከአልሸባብ ራሷን መከላከል የማትችል ደካማ ሀገር ናት። በዚህም ከአለም ደካማ የሚሊተሪ ሃይል ካላቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፋለች። የሶማሊያ በ2023 የሚሊተሪ ሃይል መረጃዋ ከዚህ በታች አስቀምጣለሁ። ➠የሰራዊት ብዛት.... 17,000 ➠ተጠባባቂ ሃይል.... 00 ➠ ጀነራል መድፍ ..... 40 ➠ሮኬት ፕሮጀክት......00 ➠ ተዋጊ ጀት ..........  00 ➠ተዋጊ ሄሊኮፕተር .....00 ➠ባህር ሃይል .............00 ➠ የውጊያ ታንክ...........15 ብቻ ያላት ሀገር ናት። ለዚህም ነው በጀግና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምትጠበቀው። አይበለውና አልሸባብ ድጋሚ ሞቃዲሾን ከተቆጣጠረ በአሜሪካ መሪነት ሃያላኑ ሶማሊያ ላይ ቁጥር ስፍር የሌለው የሰብዓዊ እርዳታን ጨምሮ ከፍተኛ ማዕቀቦች ይጣላሉ።ብዙ ሀገራት ከሶማሊያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ግንኙነት ያቋርጣሉ። አሸባሪው የአልሸባብ ሃይል የሶማሊያ ህዝብ ላይ የበቀል ሰይፋቸውን መዘው የሶማሊያን ህዝብ ቁምስቅል ያሳያቸዋል ወ.ዘ.ተ ክፉኛ ችግር ይገጥማታል። ስለዚህ ሶማሊያ ይሄ ሁሉ ኪሳራ ከሚመጣባት ኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ድንፋታና ፉከራ ብትቀንስ ይሻላታል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሶማሊያ የመኖር ያለመኖር ዋስትና ናት። መረጃው ከተለያዩ ዌብሳይቶች ያሰባሰብኳቸው ናቸው። Ahmed
Show all...
Repost from Skyline media
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ‼ ሰበር ‼ ሰበር ‼ ◌ የወንድም ጅቡቲ ህዝብና መንግስት ለሶማሊላንድ ሪፑብሊክ እውቅና ሰጥቷል። የእኛም ይቀጥላል!! ኢትዮጵያ — የጥቁር ህዝቦች የነጻነት መንፈስ !! https://t.me/Skyline7777 https://t.me/Skyline7777
Show all...
Repost from Skyline media
የጃፓን አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ዛሬ በቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳረፈ #በእሳት ተያይዟል። 12 የበረራ ቡድን አባላትን ጨምሮ 379 ሰዎችን ያሳፈረው አውሮፕላን በእሳት ቢያያዝም አንድም ሰው ህይወቱ ሳያልፍ ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል። 367 መንገደኞችን ያሳፈረው የጃፓን አየርመንገድ አውሮፕላን መነሻው በሆካይዶ ደሴት ሺን ቺቶሴ ከተባለ አካባቢ እንደነበር ተገልጿል። አውሮፕላኑ 6 ሰዎችን አሳፍሮ ከነበረ ሌላ  የጃፓን ባህር ዘብ ትንሽ አውሮፕላን ጋር መጋጨቱ ተነግሯል። ከ6ቱ አምስቱ ሲሞቱ ፓይለቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በህይወት ተርፏል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ግን የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን አቋቁመዋል። የመረጃ ምንጭ፦ ሮይተርስ፣ አልአይን፣ ዶቼቨለ ናቸው። https://t.me/Skyline7777 https://t.me/Skyline7777
Show all...
Repost from Skyline media
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሶማሊ ላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሠነድ በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበበ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ አባላት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያው ላይ እንደገለጹት÷ አዲስ የተፈረመው የመግባቢያ ሠነድ ለኢትዮጵያ የባሕር በር እና የወደብ አማራጮችን ያሰፋል፡፡ ሠነዱ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ከማስጠበቅ አንጻር ትልቅ ሚና አለው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የመግባቢያ ሠነዱ ለኢትዮጵያ የባሕር በር እና ወደብ ከማስገኘቱ ባሻገር በተፈራረሙት ሀገራት መካከል የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ግብርና እና ቱሪዝም ትብብርና አጋርነትን ስለማካተቱ አብራርተዋል፡፡ የጠቅላይ ሚንስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር እና የወደብ ባለቤት መሆን እንደሚቻል አሳይታለች ብለዋል።
Show all...
Repost from Skyline media
Photo unavailableShow in Telegram
ከአንታርክቲካ ድረስ እየመጡ ባለበት ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን መፈለጓ እንደ ስህተት መቆጠር የለበትም- የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በዛሬው መግለጫ ላይ የተነሳው ጉዳይ የኢትዮጵያ የወደብ ጉዳይ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጠቅላይ ሚንስትሩ ያነሱት የቀይ ባህር ወደብ ጉዳይ ዙሪያ ያለው አመለካከት ምንድን ነው? በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ተነስቷል። ቃል አቀባዩ በምላሻቸውም "ጠቅላይ ሚንስትሩ የሀገሪቱ የመጀመሪያው ውጪ ጉዳይ ግንኙነት የሚመለከታቸው መሪ ናቸው ነገር ግን በወደብ ጉዳይ ያደረጉት ንግግር በስህተት ተተርጉሟል" ብለዋል።ኢትዮጵያ ከዚህ በፊትም አማራጭ ወደብ እንዲኖራት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስትሰራ ነበር የአሁኑ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግርም ለጋራ ጥቅም በትብብር እንስራ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል። "ከአንታርክቲካ ድረስ ወደ ቀይ ባህር የመጡ አካላት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያ አጠገቧ ያለው ቀይ ባህርን መፈለጓ ስህተት ሊሆን አይችልም" ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
Show all...
Repost from Skyline media
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል። እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል። አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል። ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ። አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/ አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል። https://t.me/Skyline7777 https://t.me/Skyline7777
Show all...
Repost from Skyline media
ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በአዳማ ከተማ ከመስከረም 03 2016 ዓ፣ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ማጠናቀቁን አስታውቋል። ፓርቲው፣ በስልጠናው ማብቂያ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርቲው ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሥራ መመሪያና ስምሪት መስጠታቸውን ገልጧል። የአመራር አባላቱ ሥልጠና፣ በአገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ፈጥሯል ተብሏል በሥልጠናው ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ኹለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች መሳተፋቸው ተመላክቷል። ፓርቲው፣ ተመሳሳይ ሥልጠና በየደረጃው ለሚገኙ የፓርቲው አመራሮች በቀጣይነት እንደሚሰጥም ገልጧል። https://t.me/Skyline7777 https://t.me/Skyline7777
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም አዲስ ዓመት 2016
Show all...
❤️
😍
🙏
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
DATANOMICS TECHNOLOGY

#Datanomics #Technology #videos