cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dil Ber General Secondary School/ድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Show more
Advertising posts
1 313
Subscribers
-124 hours
+147 days
+4430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡ (ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም) ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር የሚከተለው መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የገለጸ ሲሆን ተፈታኞችና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስባል፡፡ የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/ You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Show all...
Here is the solution!
Show all...
Repost from N/a
ዉድ የት/ቤታችን መምህራን፤ አ/ ሰራተኞች፤ተማሪዎች፤ የተማሪዎች ወላጅ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እየገለጽኩ በአሉ የፍቅር ፣የመተሳሰብና የአንድነት እንዲሆንልን እመኛለው። መልካም በዓል። ወንዳፍራሽ ለገሠ Kabajamttoota Barsiisota: hojjettoota bulchiinsaa: barattoota: maatii barattootaa fi hordofttootni amantaa kiristaanaa hundi baga ayyaana Yaaddannoo Du’aa ka’uu Gooftaa keenyaa Iyesuus Kiristoosiin nagaaf fayyaan geessan jechaa, Ayyaanichi kan jaalalaa; kan waliif yaaduu fi kan tokkummaa akka nuuf ta’u hunda keessaniif nan hawa! AAYYAANA GAARII!!! Wendafrash Legese!!
Show all...
የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ 9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን። የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Show all...
ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ የትሞህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። (ቀን ሚያዚያ 23/ 2016 ዓ.ም)የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናና ኦላይን ለመስጠት ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በወረቀት ከሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ጎን ለጎን በቴክኖሎጁ ተደግፎ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመሆኑም ፈተናው እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ከተሞች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ወ/ሮ አየለች አሳስበዋል። በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ከወዲሁ በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ወላጆች ስለፈተናው የተሻለ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ልጆቻቸውን እንዲደግፉና በራስ መተማመን ወደፈተናው ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ሊፈጥሩ እንደሚገባም አመላክተዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በኦን ላይን የሚሰጠውን ፈተና በተሻለ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናን ለተማሪዎች በኦንላይን መስጠት ምቹና ቀላል መሆኑን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
Show all...