cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

📚የአንብብ ትውልድ📚

☞ይህ ቻናል የተከፈተው የሰዎችን የማንበብ ልምድ ለማሳደግና አንባቢ የሆኑ ትውልዶችን ለመፍጠር ነው!! ✔አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች ✔ግጥሞች ✔ምክር አዘል ቁም ነገሮች ✔እንዲሁም የተለያዩ መፅሀፎች በ pdf ይቀርብበታል አንባቢ ከሆኑ ይቀላቀሉን💝አንባቢ መሆን ብልህነት ነው💝 for any comment☞ @Anbabyan2bot

Show more
Advertising posts
655
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🧿     “ዝሙተኛዋ”……… ተብላ እስከምትታወቅበት ድረስ አፀያፊ ሾል ላይ የኖረች ሴት;    ለውሻ ባጠጣችው ውሀ የምትድን ከሆነ, አንድ ሙስሊም………    ከመንገድ ላይ “ሙስሊሞች ዐዛ ያደርጋል” ብሎ ያሰበው;   እንቅፋት በማስወገዱ ጀነት የሚወርስ ከሆነ, አንድ ሰው………    ብዙም ቦታ ሳይሰጣት በተናገራት ንግግር;         የአላህ ውዴታ የሚጎናፀፍ ከሆነ, መቶ ሰው የገደለ ነፍስ ገዳይ………    ወደ አላህ ተውበት አድርጎ ባለበት ቅፅበት ሙቶ;     የጀነት መላኢካዎ የሚያነሱት ከሆነ, እንዴት ብለህ ከኸይር ሾል ትሳነፋለህ???? እነዚህ………    ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በእርግጥም እንዳንተው ሙስሊሞች ነበሩ። እንዳንተው ከሰላትም ይሁን ከፆም የየራሳቸው ድርሻ ነበራቸው። ለመዳናቸው ጀነት ለመውረሳቸው ለየት ባለ መልኩ ሰበብ የሆናቸው ግን የተጠቀሰው የቅፅበት ስራቸው ነው። ተውሒድህን ጠብቅ!!    በማስከተል የትኛውንም ኸይር ሾል መስራት እየቻልክ "እቺ ምን አላት" ብለህ እንዳታስመልጥ። ከስራዎችህ አላህ በየትኛው ሰበብ እንደሚያድንህ አታውቅም። ደግሞም ዕወቅ………   መዳን የሚገኘው በብዛት በተሰራው ሳይሆን:           በኢኽላስ በተሰራው ነው!!
Show all...
👏 2👍 1
وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡(ሱረቱ አን ነህል 18) ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል ፡- ✦ የሰው ልጅ  ከሚያስደንቀው ፀጋዎቹ መካከል አንዱ የመርሳት ፀጋው ነው፡ መርሳት ባይኖር  ማንም አይለምንምም፣  አይጸጸትምም እንዲሁም በገጠመው መከራም አይጽናናም ነበር"   በሀዘን አይሞትም ፣የጠላትን ቸልተኝነት ተስፋ አያደርግም፣ ማንም ጀግና ቂም አይዝም፣  ያጣውን ነገር እያሰበ ከዚች ዓለም መጠቀሚያዎች ውስጥ በአንዱም  አይደሰትም። በማስታወስ እና በመርሳት መካከል ያለውን ልዩነት በማስተንተን የአላህን ፀጋ አስታውሱ:: በእያንዳንዳቸው ላይ የራሳቸው ተፈላጊነትን አድርጓል ❤️❤️❤️
Show all...
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
Show all...
👍 3
«ያ ረቢ! ይህ ሁሉ እያመፅኩህ አልቀጣኸኝም!» አለ። እንዲህ ተባለ: ‐ «ይህን ሁሉ እየቀጣሁህ እስከሁን አላወቅክም!?… ከኔ ጋር የማንሾካሾክን ጣዕም አልከለከልኩህም?!» [ኢማም ኢብኑል‐ጀውዚይ፥ ሶይዱል‐ኻጢር] :
Show all...
« ሙትቻ ላሉህ ሰዎች እራስህን ለማስረዳት አትሞክር። ለሞትክባቸው ሰዎች የምታባክነው ጊዜ አይኑርህ። ውበትህ ግለፅ ሲወጣ የመጣ ሁሉ ውበትህን አይቶ ላይሆን ይችላልና በአመዳምነት ዘመንህ ላይ ውበትህ የታያቸውን ጠበቅ አድርገህ ያዝ። ቆንጆ መሆንሽን ከሚያደንቁት የበለጠ የሚያስጠላብሽን ሊያስውቡልሽ የሚጣጣሩትን አትዘንጊ። ቁስልሽን በሰው አትከልዪ። የሚመክሩሽ ሁሉም ከጥቃት አይጠብቁሽም። ጥንቃቄ የብልሆች መንገድ ነው። በጣም ነፃነት በሚሰማሽ ሰው በኩል ስስ ነሽና አትራቆቺ። ዋጋ የምትከፍዪላቸው ከጌታሽ መንገድ እንዳያስቱሽ አስተውዩ! የምወድሽዋ ልብሽን በቀደር አረጋጊ! የምወድህዋ እራስህ ካልወደቅክ አይጥሉህምና በጌታህ ታግዘህ ፅና። መንገዱ ምን እንዳለው አይታወቅምና ሰላም ለልባችሁ! © [አብዱልሀኪም ሰፋ] ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ ልባችን ሰላም የሚያገኝበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
Show all...
❤ 6👏 2
يَا وَيْلَتَىٰ لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡ (ሱረቱል ፉርቃን 28) ዛሬ እስኪ ቆም በሉና ጓደኞቻችሁን ፈትሹ ዋ ጥፋቴ ያስብላሉ ወይስ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት  "ወደ ጀነት ይዞን የሚገባ ጀነት ውስጥ ሲያጣን የሚያዝን እና ሸፈዓ የሚሆን ወዳጅ ጓደኛ ነው ያለን??? ጥላ በሌላት ቀን ለሱ ብለን ተዋደን ከጥላው ስር የሚያደርጉንን የአላህ ወዳጆችን በዙርያችን ያብዛልን!!!
Show all...
👍 4
#አስተማሪ #ቂሳ            በጠዋት አንድ ሰአት ላይ አንድ ጓደኛዬ ደውሎ እርዳታ ከምንሰጣቸው ሰዎች አንድ ደካማ አሮጊት በጣም ታመዋል፤ ከጎናቸው ማንም የለምና እባክህ አጅሩን ከአላህ እናገኛልን ሀኪም ቤት እናድርሳቸው አለኝ።        ልምዴ ሆኖ በረመዳን ከፈጅር ሰላት በኋላ እንቅልፍ የምተኛበት ወቅት ነው ፤ ሆኖም አንድ ኡዝታዜ ተጨማሪ (ናፊላ) የሆኑ ኢባዳዎችን ከመስራት የሰዎችን ጉዳይ (ሀጃ) መፈፀም ይቀድማል ሲል የተናገረውን አስታወስኩና እያመነታሁ እንድ እግሬን ወደ ፊት ሌላኛውን ወደ ኋላ  እየጎተትኩ ከቤቴ ወጣሁ።       ወደ አዛውንቷ ሴትዮ ቤትም ሄደን ሀኪም ቤት ወስደናቸውና በአላህ ፍቃድ አስፈላጊውን ህክምና ካደረግንላቻው በኋላ ፤ ጤንነታቸው መለስ አለ። እናም ወደ ቤታቸው ይዘናቸው ተመለስን። አዛውንቷ ምላሳቸው ዱዓእ ከማድረግ አልቦዘነም ነበር። መንገዱን ሙሉ ዱዓእ ሲያደርጉልን ቆዩና ከቤታቸው አድርሰናቸው ጓደኛዬን ተሰናብቼ ወደ ቤቴ አመራሁ፤ ቤት ስገባም እናቴ የመኝታ ክፍሌን ስታፀዳ አገኘኋትና ፦ እማዬ ምን ነው!? ምን ሆነሻል!? ምን እየሰራሽ ነው? ስል ጠየቅኳት። እሷም፦ ተኝቼ ሳለ ከክፍልህ ከባድ ድመፅ ሰማሁ ልጄ ላይ ምን ወድቆ ነው ብዬ እየጮህኩ ስሮጥ ወደ ክፍልህ መጣሁ አልሀምዱሊላህ አንተ የለህም ቁም ሳጥኑ ግን አልጋህ ላይ ተደፍቶ አገኘሁት ቆይ ግን የት ነበርክ !? ብላ ጠየቀችኝ። ይህን ግዜ ፈገግ አልኩና እንዲህ የሚለውን የረሱልን ﷺ ቃል አስታወስኩ፦ 《 (ለሰዎች) መልካምን መስራት ከመጥፎ አደጋ (አሟሟት) ይጠብቃል።》 የታሪኩ ባለቤት አህመድ ሀሳኒ የተባለ ግብፃዊ!
Show all...
👍 9
ሑጀቱል—ኢስላም ኢማም አቡሓሚድ ገዛሊ እንዲህ ይላሉ: — "ምክንያቱ ያልታወቀ ጭንቀት ኃጢኣትን ከመፈፀም እና ለመፈፀም ከማሰብ የሚመነጭ ነው። ቀልብ አላህ ፊት መቆምና መተሳሰብ እንዳለ ሲያስብና አስፈሪውን የቂያማ ድባብ ሲያስተውል ከሚሰማው ሃሳብ ይህ ጭንቀት ይወለዳል።" : ኢማም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ: — "ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና ምክንያቱ ስለማይታወቅ ጭንቀት ተጠየቁና እንዲህ አሉ: — "መንስዔው በልብህ አስበኸው ያልፈፀምከው ኃጢኣት ነው። በልብህ ባሰብከው ኃጢኣት ምክንያት በጭንቀት ትቀጣለህ። ኃጢኣት የማይቀር ቅጣት አለው። በምስጢር ለተሰራው በምስጢር፤ በይፋ ለተሰራው በይፋ።" ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ ውስጣችንም ላያችንም ሰላም የሚያገኝበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ ራህመት የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
Show all...
👍 3
ጠቃሚ ቃላቶች <የትሕትና ፍሬዋ ፍቅር ነው ፤ የትዕቢት ግን ፍሬዋ ጥልና ውርደት ነው።> <ዓለም አስቀድማ  ከምትንቅህ አንተ አስቀድመህ ናቃት ፤ ባትንቃትም እሷ ወረተኛ ሳትሆን አትቀርምና።> <ተናግሮ አናግሮ የሆድን ጨርሶ ጠላት ይሆናል ወዳጅ ተመልሶ ።> <ታማኝ ትሆን ዘንድ አማኝ ሁን። > <ሳይርበው የሚበላ ርሀብን አያውቅም።> <ሰው ያለፈውን ሲያመሰግን ፣ ያለበትን ሲጠላ ፣ የሚመጣውን ሲጠራጠር እድሜውን ይገፋል።> <የዓለም ገዥ ጥበብና ሼል ነው።> (ከመጽሐፍ የተወሰደ) አሊ መህዲ እንዳጋራው! 📚 @Bemnet_Library
Show all...
ያንተን ሪዝቅ ማንም አይበላውም አንድ ሰውዬ ነበር በአንድ ካንፓኒ ተቀጥሮ በሚሰራው እናቱን ሚስቱን እና ልጆቹን ያስተዳድራል። ዘውትር ስራውን በአግባብ እና በእምነት ለአለቃው ይሰራ ነበር። እናም አንድ ቀን ሙሉ ስራ ሳይገባ ይቀራል... የካንፓኒው ባለቤትም፦ ''በርግጠኝነት ክፍያ አንሶት ነው የቀረው ስለዚህ ነገ ሲመጣ ክፍያ እጨምርለታለሁ።" ብሎ ይወስናል። በነጋታው ይህ ሰው ስራ ቦታ ከመግባቱ ክፍያውን ከነ ጭማሪው ሰጠው። ቆጥሮ ተቀበለው። ግን ስለጭማሪው ምንም አልደነቀውም ለምን ክፍያ እንደተጨመረለትም አለቃውን አልጠየቀም...ዝም ብሎ ስራውን ቀጠለ። ለተወሰኑ ቀናት እንደበፊቱ ስራውን በአግባብ ሰራና የሆነ ቀን ስራ ሳይገባ ቀረ። አለቃው በቃ የሌለ ተቆጣ የጨመረለትንም ደሞዝ መልሶ ቀነሰበት። የጨመረለትን እንደቀነሰ አወቀ አሁንም ምንም ሳይል ትቶ ወጣ። በሰራተኛው ሁኔታ የተገረመውም አለቃው፦ "ባለፈው ክፍያ ስጨምርልህ ምንም አላልክም ዛሬም ስቀንስብህ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረብክም ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው። እሱም፦ የመጀመሪያ ግዜ ስራ የቀረሁት የዛን ቀን አላህ ልጅ ረዝቆኝ ነው (ሚስቴ ወልዳ) ያን ቀን ደሞዝ ስትጨምርልኝ ስለጭማሪው ያልጠየቅኩህ የደሞዙ ጭማሪ ያ አዲስ ለተወለደው ህፃን አላህ የመደበለት ሪዝቅ እንደሆነ ስላወቅኩ ነው። ትናንት ስራ የቀረሁት እናቴ ሞታ ነው። አሁን ደሞ ደሞዝ ስትቀንስብኝ ዝም ያልኩት ያ ከዚህ በፊት ትበላው የነበረው የእናቴ ሪዝቅ በሷ መሞት ምክንያት አላህ አቋርጦት እንደሆነ ስላወቅኩ ነው።" ብሎ መለሰለት።
Show all...
👍 9