Wasa Maintenance Center
Open in Telegram
አላማችን በአለም ደረጃ ቁጥር አንድ ተመራጭ የጥገና እና የዝርጋታ ድርጅት መሆን ነው ! ዋሳ የጥገና ማዕከል !
Show more3 750
Subscribers
No data24 hours
-147 days
-6330 days
Posts Archive
ውሎ - ቲቪ ለማስጠገን ቀጠሮ የያዙ ደንበኛችንን ስናገለግል
ዋሳ የጥገና ማዕከል
📞 𝟗𝟒𝟗𝟐 ወይም 𝟎𝟗-𝟒𝟔-𝟎𝟎𝟎-𝟏𝟏𝟏
ይደውሉ - ቀጠሮ ይያዙ - መፍትሄ ያግኙ
#የፍሪጅ #ብልሽት እና #መፍትሄዎቻቸው
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
👉 ፍሪጁ በበቂ ሁኔታ አያቀዘቅዝም፦ የቅዝቃዜ መቆጣጠሪያው(thermostat) በትክክል መሞላቱን ማረጋገጥ፣ የኮንዴንሰር ጥቅሉ(condenser coil) ቆሻሻ አልመያዙን ማረጋገጥ፣ በሩ ግጥም ብሎ መዘጋቱን ማረጋገጥ፣ ፍሪጁ ውስጥ የምናስቀምጣቸው እቃዎች ባግባቡ መደርደራቸውን እና አየር ባግባቡ እንደሚዘዋወር ማረጋገጥ፣ አየር ማራገቢያው(Fan) እንደሚሰራ ማረጋገጥ፣ በረዶ ቤት ውስጥ በረዶ አለመጋገሩ ማረጋገጥ ይኖርብናል፣ ፍሪጁ ውስጥ ያለው ጋዝ መጠን በጥሩ ሁኔታ ቅዝቃዜ መስጠት የሚችል ምሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል(ጋዙ የሚያንስ መስሎ ከታየን ጋዝ ከመሞላቱ በፊት ያፈሰሰበትን ቦታ ለይተን ማወቅ ይኖርብናል)።
👉 ፍሪጁ ከፍተኛ ድምፅ አለው፦ የኢቫፖሬተር ወይም የኮንዴንሰር አየር ማራገቢያ(Fan) ውስጥ ቆሻሻ አለመግባቱን ማረጋገጥ፣ በረዶ ቤት ውስጥ በረዶ አለመጋገሩን ማረጋገጥ፣ የላሉ ብሎኖች እና የታሰሩ ነገሮች ካሉ ማጥበቅ ይኖርብናል።
👉 ውሃ ያፈሳል፦ ውሃ ማጠራቀሚያው አለመሙላቱ ማረጋገጥ፣ ውሃ ማውርጃ ትቦው አለመደፈኑን እና አለመቀደዱን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ፍርጁ ዝም ብሎ ይስራል(በራሱ ጊዜ አያጠፋም)፦ የኮንዴንሰር ጥቅሉን አለመቆሸሹን ማረጋገጥ፣ በሩ በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ፣ ቅዝቃዜ መቆጣጠሪያው(thermostat) በትክክል መሞላቱን እና እንደሚሰራ ማረጋገጥ፣ ፍሪጁ ውስጥ ከመጠን በላይ እቃ አለመቀመጡን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ፍሪጁ መጥፎ ሽታ አለው፦ ፍሪጁ ውስጥ የተብላሸ ምግብ አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ የፍሪጁን ውስጥ ባግባቡ ማፅዳት፣ የፍሳሽ ውሃ ማጠራቀሚያውን ማፅዳት፣ የውሃ ማፍሰሻውን ማፅዳት ይኖርብናል።
👉 ፍሪጁ አይበራም፦ ሶኬቱ ባግባቡ መሰካቱን ማረጋገጥ፣ የተቋረጠ የኤሌክትሪክ መስመር አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ የተቃጠለ ፊዩዝ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ፍሪጁ ይበራል ግን ምንም ቅዝቃዜ የለውም፦ የቅዝቃዜ መቆጣጠሪያውን(thermostat) መስራቱን ማረጋገጥ፣ የተቋረጠ የኤሌክትሪክ መስመር አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ ኮምፕረሰሩ እንደሚነሳ ማረጋገጥ፣ ጋዝ መስምሩ ውስጥ እንዳለው ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ማስታወሻ፦ እነዚህን መፍትሄዎች ተጠቅመው ካልተስተካከለልዎ የጥገና ባለሙያ ማናገር ይኖርቦታል
ለማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገና አገልግሎት ይደውሉልን ያሉበት ድረስ ባለሙያዎቻችንን እንልክሎታለን እንዲሁም ህጋዊ ዋስትናም እንሰጦታለን ::
ስልክ :- 0903-76-00-76 ወይም 0903-75-55-75
አድራሻ :- 22 ሃያ ሁለት ጌታሁን በሻህ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ 612
ዋሳ የጥገና ማዕከል
"ሁሉንም አገልግሎት በተመቸዎት ጊዜ እና ባሉበት ቦታ"
#የቴሌቪዥን #ብልሽት እና #መፍትሄዎቻቸው
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
👉 ቴሌቪዥኑ አይበራም፦ ሶኬት መሰካቱን ማረጋገጥ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚመጣበት ሶኬት ላይ ሌላ እንደሚሰራ እርግጠኛ የሆንበትን እቃ ሰክቶ መስራቱን ማርጋገጥ፣ ቲቪውን ለማብራት በሪሞት ፋንታ ቲቪው ላይ ያለውን ማብሪያ እና ማጥፊያ መጠቀም፣ ብሬክር አለመጥፋቱን ማርጋገጥ፣ ሃይል መቆጣጠሪያ ፊዩዝ አለመቃጠሉን ማረጋገጥ
👉 ድምፅ አለው ነገር ግን ምስል የለውም፦ የምስል እና የድምፅ ማስተላለፊያ(HDMI or JACK) መስመር እንደሚሰራ ማረጋገጥ፣ ይባክ ላይት ችግር አለመሆኑን ማረጋገጥ ይህን ደግሞ ለማረጋገጥ እስክሪኑ ላይ መብራት በማብራት ድብዝዝ ያለ ምስል መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል የደበዘዘ ምስል ካለ ባክላይቱ ችግር ሊኖርብት ይችላል፣ ምስል ካልታየን ደግሞ የእስክሪን ችግር ሊሆን ይችላል።
👉 ምስል አለው ነገር ግን ድምፅ የለውም፦ የምስል እና የድምፅ ማስተላለፊያ(HDMI or JACK) መስመር እንደሚሰራ ማረጋገጥ፣ ድምጽ ሴቲንግ ውስጥ አለመጥፋቱን ማረጋገጥ፣ የውስጥ አስፒከር ችግር አለመሆኑን ማርጋገጥ ይህን ለማረጋገጥ ሌላ እስፒክር ቲቪው ላይ ሰክቶ ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ሪሞት ባግባቡ አይስራም፦ ባትሪው አለመሞቱን ማረጋገጥ፣ የቲቪው ሪሞት ሴንሰር አለመሸፈኑን ማረጋገጥ፣ ሪሞቱ ተበላሽቶ ሊሆን ስለሚችል በሌላ ተመሳሳይ ሪሞት ወይም ዩኒቨርሳል ሪሞት ተጠቅሞ ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ቲቪው በራሱ ይበራል ይጠፋል፦ የሃይል ችግር አልምሆኑን ማርጋገጥ፣ የሃይል መቆጣጠሪያው ባግባቡ እንደሚሰራ ማርጋገጥ፣ ቲቪው በቂ አይር እንደሚያገኝ እና አለመጋሉን ማረጋገጥ፣ የሶፍትዌር ችግር አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ምስሉ ብዥ ማለት ውይም መንቀጥቀጥ፦ የቲቪውን የመስል ጥራት ሴቲንግ(resolution setting) ማስተካከል ይኖርብናል፣ የምስል መቀብያው ጥራት(signal strength) አሪፍ መሆኑን ማረጋገጥ፣ እስክሪኑ ችግር እንደሌለበት ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ከዋይፋይ ጋር አይገናኝም፦ ዋይፋዩ መብራቱን ማርጋገጥ፣ቲቪውን አጥፍቶ ማብራት፣ ቲቪው ዋይፋዩ የሚደርስበት ቦታ መቀመጡን ማረጋገጥ፣ የቲቪውን ሶፍትዌር ማዘመን(update) ማድርግ፣ የዋይፋዩን ሚስጥር ቁጥር ባግባቡ ማስግባት ይኖርብናል።
👉 ቲቪው ላይ ያሉ አፕሊኬሽኖች በአግባቡ አለመስራት፦ ቲቪውን አጥፍቶ በማብራት የምንፈልገውን አፕሊኬሽን ማብራት፣ አፕሊኬሽኑን ማዘመን፣ ቲቪው ከዋይፋይ ጋር መገናኘቱን ማረጋገጥ፣ የማይሰራውን አፕሊኬሽን አጥፍቶ ድጋሚ መጫን፣ ቲቪ ላይ የማይሰሩ አፕሊኬሽኖች ስላሉ የምንጠቀመውን አፕሊኬሽን መስራቱን ማርጋገጥ ይኖርብናል።
ለማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገና አገልግሎት ይደውሉልን ያሉበት ድረስ ባለሙያዎቻችንን እንልክሎታለን እንዲሁም ህጋዊ ዋስትናም እንሰጦታለን ::
ስልክ :- 0903-76-00-76 ወይም 0903-75-55-75
አድራሻ :- 22 ሃያ ሁለት ጌታሁን በሻህ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ 612
ዋሳ የጥገና ማዕከል
"ሁሉንም አገልግሎት በተመቸዎት ጊዜ እና ባሉበት ቦታ"
+4
ያረጀ የጋዝ ስቶቭ ወደ ኤሌክትሪክ ስቶቭ በመቀየር ላይ
ዋሳ የጥገና ማዕከል
📞 9492 ወይም 09-46-000-111
ይደውሉ - ቀጠሮ ይያዙ - መፍትሄ ያግኙ
#የልብስ #ማጠቢያ #ማሽን #ብልሽት #እና #መፍትሄዎቻቸው
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
ማሽኑ አይበራም፦ ቅድሚያ የማሽኑ ሶኬት በአግባቡ መሰካቱን ማረጋገጥ፣ ቀጥሎ የሰካንበት ሶኬት ላይ ሃይል መኖሩን ማረጋገጥ፣ የማሽኑ በር ባግባቡ መዘጋቱን ማረጋገጥ ምክንያቱም አንዳንድ ማሽኖች በራቸው ካልተዘጋ አይበሩም።
ማሽኑ ውሃ አይሞላም፦ ውሃ ማስተላለፊያ ትቦው ሙሉ ለሙሉ ክፍት አንደሆነ ማርጋገጥ፣ ውሃ መስመሩ ላይ እንዳለ ማረጋገጥ፣ ውሃ ማስገቢያው አለመደፈኑን ማረጋገጥ
ማሽኑ ውሃ ያፈሳል(ያንጠባጥባል)፦ የውሃ ማፍሰሻው ትቦ አልመቀደዱን እና በአግባቡ መታሰሩን ማረጋገጥ፣ በሩ ላይ ያለው ጎሚኒ አለመቀደዱን ማረጋገጥ፣ ልናጥበው ያስገባነው ልብስ ክብደት ከማሽኑ አቅም በላይ አለመሆኑን ማርጋገጥ
የማጠቢያ ወይም መጭመቂያ ሳህኑ አይሽከረከርም፦ በሩ ላይ ያለው ማብሪያ እና ማጥፊያ እየሰራ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ሞተሩን እና ሳህኑን የሚያገናኘው ችንጋ አልመበጠሱን ማርጋገጥ፣ ሞተሩ በአግባቡ መስራቱን ማርጋገጥ
ማሽኑ ከመጠን በላይ ይንቀጠቀጣል፦ ማሽኑ የተቀመጠበት ቦታ ውሃ ልክ ያለው ቦታ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ልናጥበው ያስገባነው ልብስ ክብደት ከማሽኑ አቅም በላይ አለመሆኑን ማርጋገጥ፣ የላላ ወይም የዛገ እስፕሪንግ እና ንዝረት መቆጣጠሪያ አለመኖሩን ማረጋገጥ
ማሽኑ የሚደብር ጠረን አለው፦ ቆሻሻ ማሽኑ ውስጥ ተጠራቅሞ ሊሆን ስለሚቸል በደንብ ማፅዳት፣ የሳሙና መክተቻውን ማፅዳት፣ ሁል ጊዜ አጥበን ከጨረስን በኋላ ውስጡን በአግባቡ አፅድተን በሩን ለትንሽ ሰሃት ክፍት ማድረግ ይኖርብናል
ማሽኑ ውሃ በግባቡ አያፈስም፦ የውሃ ማፍሰሻው ትቦ አለመደፈኑን ማረጋገጥ፣ የፓምፕ ማጣሪያው አለመዘጋቱን ማርጋገጥ፣ ፓምፑ ባግባቡ መስራቱን ማረጋገጥ
ማሽኑ የሚረብሽ ድምፅ አለው፦ ማሽኑ ውስጥ የገባ ግኡዝ አካል አለመኖሩን ማርጋገጥ፣ ክታሰረበት ቦታ ላይ የተላቀቀ ወይም ይላላ አካል አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ ኩሽኔቱ አለመበላሸቱን ማረጋገጥ
ማሽኑ የብልሽት ምልክት(Error code) ያሳያል፦ የተጠቃሚ መመሪያው (user manual) ላይ የሚያሳየውን የብልሽት ምልክት ምክንያት ማንበብ እና ቅደም ትከተሉን በመጠበቅ ማስተካከል
ማስታወሻ፦ እነዚህን መፍትሄዎች ተጠቅመው ካልተስተካከለልዎ የጥገና ባለሙያ ማናገር ይኖርቦታል
ለማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገና አገልግሎት ይደውሉልን ያሉበት ድረስ ባለሙያዎቻችንን እንልክሎታለን እንዲሁም ህጋዊ ዋስትናም እንሰጦታለን ::
ስልክ :- 0903-76-00-76 ወይም 0903-75-55-75
አድራሻ :- 22 ሃያ ሁለት ጌታሁን በሻህ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ 612
ዋሳ የጥገና ማዕከል
"ሁሉንም አገልግሎት በተመቸዎት ጊዜ እና ባሉበት ቦታ"
#ጄኔሬተር #ስንገጥም #መከተል #ያሉብን #መንገዶች #ምንድናቸው?
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
👉 ቦታ መምረጥ፦ ጄኔሬተሩን የምንገጥምበት ቦታ ክበር እና መስኮት የራቀ ቦታ መሆኑን እና በቂ አየር የሚዘዋወርበት ቦታ መሆኑን ማርጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ቦታ ማዘጋጀት፦ የሚገጠምበትን ቦታ ማፅዳት እና ጄኔሬትሩን ማስቀመጫ የሚሆን ውሃ ልኩን የጠበቀ ማስቀመጫ መደብ(pad) ማዘጋጀት።
👉 ጄኔሬተሩን የተዘጋጀው ቦታ ላይ በጥንቃቄ ማስቀመጥ።
👉 ከቆጣሪ የሚመጣና ከጄኔሬተር የሚመጣውን መስመር መቀየሪያ(ATS ወይም MTS) መግጠም።
👉 የኤሌክትሪክ መስመር መዘርጋት እና ጄኔሬተሩን እና መቀያየሪያውን ማገናኘት።
👉 ነዳጅ መሙያ መስመር ማዘጋጀት እና ነዳጅ እንደማያፈስ እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል።
👉 ጭስ ማውጫ መስመር መዘርጋት።
👉 የግራውንድ መስመር መታሰሩን ማረጋገጥ።
👉 የሞተር ዘይት አለመጉደሉን ማረጋገጥ።
👉 ጄኔሬተሩን በማስነሳት በአግባቡ እንደሚነሳ እና እንደሚጠፋ ማረጋገጥ።
👉 ጄኔሬተሩ ከበራ በኋላ የምንጠቀምባቸውን እቃዎች በማብራት ያለምንም ችግር እንድሚሰሩና የጄኔሬተሩ ድምፅ ጥሩ መሆኑን ማረጋገጥ።
👉 የዘረጋናቸውን ኤሌክትሪክ መስመሮች እና ሌሎች መረጃዎችን በማደራጀት አንድ ምዝገብ ላይ መዝግቦ ማስቅመጥ። ይህም የሚያስፈልገን ለወደፊት ሰርቪስ እና ጥገና ሲያስፈልግ ጠቃሚ ስለሆነ ነው።

📞 9492 #ከቤቱ
ET : ሃያ ሁለት ጌታሁን በሻህ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 612
USA: 50 S Pickett Street Unit #225 Alexandria VA 22304
Telegram :- t.me/Wasa_express
የአየር ማቀዝቀዣ(AC) ስንገጥም መከተል ያሉብን መንገዶች ምንድናቸው?
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
👉 መምረጥ፦ የምንገጥመውን የቤት ማቀዝቀዣ አይነት እና የምንገጥምበትን ቦታ መምረጥ ይኖርብናል፤ ምክንያቱም ይምንገጥመው ማቀዝቀዣ ማቀዝቀዝ ለምንፈልገው ክፍል በቂ ቅዝቃዜ መስጠት እንደሚችል እና የምንገጥምበት ቦታ ለሙሉ ክፍሉ ቅዝቃዜ መድረስ ሚችልበት ቦታ መሆኑን ማረጋገጥ ስላለብን ነው።
👉 የአጠቃቀም መመሪያውን ማንበብ፦ ከማቀዝቀዣው ጋር አብሮ የሚመጣ መመሪያ ስላለ ማንበብ ይኖርብናል፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ማቀዝቀዣዎች የተለያየ የአገጣጠምና አጠቃቀም ስርሃት ስላላቸው ነው።
👉 የሚያስፈልጉንን መሳሪያዎችን ማዘጋጀት፦ አብዛኛው ጊዜ የቤት ማቀዝቅዛ ለመግጠም የሚያስፈልጉን መሳርያዎች ዋና ዋናዎቹ ብሎን መፈቻ፣ ፒንሳ፣ ድሪል፣ ሜትር፣ ውሃ ልክ፣ መሰላል፣ ኪያቤ(Adjustable wrench)፣ አለንኪ እና የመሳስሉት ናቸው።
👉 የምንገጥምበትን ቦታ ማዘጋጀት፦ የምንገጥመው ማቀዝቀዣ መስኮት ላይ ሚገጠም ከሆነ መስኮቱን ለማሽኑ እንዲመች አድርጎ ማዝጋጀት ይኖርብናል። ነገር ግን ግርግዳ ላይ ሚገጠም ከሆነ ማቀዝቀዣው ቤት ውስጥ እና ውጪ ሚገጠሙ ማሽኖች ስላሉት ሁለቱም ጋር ቦታ ማዘጋጀት ይኖርብናል(በተቻለን አቅም ሁለቱ ማሽኖች በመሃላቸው ያለውን ርቀት ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል)።
👉 መግጠም፦
o መስኮት ላይ ለሚገጠም ማቀዝቀዣ
ቅድሚያ ከማቀዝቀዣው ጋር የሚመጣ የመስኮት ፍሬም እና ማሽኑን የሚያገናኝ ፍሬም አለ(ከሌለ እራሳችን እናዘጋጃለን) የፍሬሙን ውሃ ልክ ካስተካከልን በኋላ ከመስኮቱ ጋር ጥብቅ አድርገን በብሎን እናስረዋለን።
ማቀዝቅዣውን ያሰርነው ፍሬም ውስጥ አሾልከን ፍሬሙን እና ማሽኑን የምናስርበት ቦታ መግጠሙን ካረጋገጥን በኋላ በብሎን ጥብቅ አድርገን እናስረዋለን። የማቀዝቅዣው ኢቫፖሬተር ወደውስጥ ኮንዴንሰር ደግሞ ወደውጪ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ማሽኑን ከገጠምን በኋላ በማሽኑ እና በመስኮቱ መሃል ከፍተት ካለ መድፈን ይኖርብናል።
o ግርግዳ ላይ ለሚገጠም ማቀዝቅዣ
ቅድሚያ ውጪም ውስጥም የሚገጠሙትን ማሽኖች ከታሸጉበት ካርቶን ውስጥ ማውጣት እና መስቀያዎቹን ማዘጋጀት ይኖርብናል
ውስጥ የሚገጠመውን ማሽን (indoor unit) መስቀያውን ግርግዳ ላይ ውሃ ልኩን ጠብቆ መለጠፍ
ውጪ የሚገጠመው ማሽን (outdoor unit) ማስቀመጫ ግርግዳ ላይ ወይም መሬት ላይ ማሰር(ብዙ ጊዜ ማስቀመጫው አብሮ ላይመጣ ስለሚችል እራሳችን ማዘጋጀት ይኖርብናል)። ቦታው አየር እንደልብ ሚዘዋወርበት ቦታ መሆኑን እና ከባድ ዝናብ ማያገኘው መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል።
ቤት ውስጥም ውጪም የሚገጠሙትን ማሽኖች ያዘጋጀነው መስቀያ ላይ በመመሪያው መሰረት መግጠም።
የውጪውን እና የውስጡን ማሽን የሚያገናኙትን የጋዝ ትቦዎች እና ኤሌክትሪክ ገመዶች ማሳለፊያ ቀዳዳ በማዘጋጀት ማሳለፍ እና ከማሽኖቹ ጋር በመመሪያው መሰረተ ማገናኘት።( የጋዝ ትቦዎቹን ስናስር እና ብሎኖቹን ስናስር ጥንቃቄ ማድረግ እና መጥበቃቸውን ማርጋገጥ ይኖርብናል።)
በእየር መሳቢያ(vacuum pump) የጋዝ ትቦ ውስጥ ያለውን አየር ማውጣት።
ሂያጅ እና ተመላሽ ትቦዎች ላይ ያሉ ጋዝ መክፈቻና መዝጊዎቹን ሁለቱንም መክፈት (አብዛኛው ጊዜ በአልንኪ ነው ሚከፈቱት)። አብዛኛው ጊዜ ማሽኖቹ ጋዝ ተሞልተው ስለሆነ የሚመጡት ስንከፍት ቀስ ብለን ከፍተን ትቦዎቹ ጋዝ አለማፍሰሳቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል፤ ካረጋገጥን በኋላ እስከመጨረሻው ድረስ መክፈት ይኖርብናል።
👉 ማሽኑ በሚሰራበት ሰሃት ከማሽኑ ውስጥ የሚፈስ ውሃ ስላለ ከውሃ ማፍስሻው ውደ ውጪ ወይም ፍሳሽ ወዳለበት ቦታ የውሃ ትቦ መዘርጋት ይኖርብናል።
👉 ኤሌክትሪክ ሃይል ከማገናኘታችን በፊት የዘረጋነው ኤሌክትሪክ መስመር ትክክል መሆኑን እና ግራውንድ መታስሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 የኤሌክትሪክ ሃይል ማገናኘት እና ማሽኖቹ በቂ ሃይል ማግኘታቸውን ማረጋገጥ።
👉 ማሽኖቹ ጋዝ ያልተሞሉ ከሆነ ጋዝ መሙላት ይኖርብናል።(ጋዝ ሲሞላ መሙላት ያለብንን የጋዝ አይነት ማርጋገጥ ይኖርብናል።)
👉 ማቀዝቅዣውን በማስንሳት በቂ ቅዝቃዜ እንደሚሰጠን እና ያልተለመደ ድምፅ እንደሌለው ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ድርጅታችን ዋሳ በስሩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሁሉ ለደንበኞቻችን በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን እና ወረፋን ለማስቀረት የደንበኛ አገልግሎታችንን ወደ ጥሪ ማዕከል ማሳደጋችንን ስንገልፅ በደስታ ነው !
የጥሪ ማዕከላችን ቁጥር
𝟗𝟒𝟗𝟐
ጄኔሬተር #ስንገዛ #ግምት #ውስጥ #ማስገባት #ያሉብን # ነገሮች
የፌስቡክ ገፃችንን ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ተጠቀሙ
https://www.facebook.com/wasaelectronics
👉 የሃይል ፍላጎት፦ ከሚገዛው ጄኔሬተር የምንፈልገው ሃይል ምን ያህል እንደሆነ ቅድሚያ ማወቅ ይገባናል። ይሚያስፈልገንን ሃይል ለማወቅ የምንጠቀማቸውን የኤሌክትሪክ እቃዎች መለየት እና ሚያስፈለጋቸውን ሃይል መጠን ማወቅ ይጠበቅብናል።
👉 የሚጠቀመው የነዳጅ አይነት፦ የምንገዛው ጄኔሬተር የሚጠቀመው የነዳጅ አይነት ማወቅ ይኖርብናል ምከነያቱም በአካባቢያችን ያለውን የነዳጅ አቅርቦት ጋር ሊመሳሰል ይገባል። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ጄኔሬተሩ የሚተከለው ቤንዚን የሚጠቀም ጄኔሬተር አይመከርም ምክንያቱም ከአዲስ አበባ ውጪ ቤንዚን በበቂ ሁኔታ ስለሌለ።
👉 የምንጠቀምበት የጊዜ ቆይታ፦ ጄኔሬተሩ ለምን ያህል ጊዜ ሳይቋረጥ መስራት እንዳለበት መወሰን ይኖርብናል ምክንያቱም የነዳጅ ማጠራቀሚያው ስፋት እንድንወስን ይረዳናል።
👉 ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ በምቹ መሆኑን፦ የምንገዛው ጄኔሬተር ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል። ምክንያቱም ለጥገና ጄኔሬተሩን ለማንቀሳቀስ ምቹ መሆን ይኖርብናል። በተጨማሪም እግሮቹ ጎማ ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል።
👉 የድምፅ መጠን፦ የሚገዛው ጄኔሬተር ሲሰራ የሚያወጣው ድምፅ ዝቅተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል። አብዛኞቹ ጄኔሬተሮች ድምፃቸው ከፍተኛ ስለሆነ ፀጥታ ሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ውስጥ ልንቸገር እንችላለን።
👉 የምናስነሳበት መንገድ፦ ጄኔሬተሩን ማስነሳት ሰንፈልግ የምናስነሳበት መንገድ ቀላል መሆኑን ማርጋገጥ ይኖርብናል። ጄኔሬተር በተለያየ መንገድ ሊነሳ ይችላል ከነዚህ መካከልም
በእጅ የሚነሳ(manual start)፦ ገመድ በመጎተት ሞተሩ እንዲነሳ በማድረግ
በኤሌክትሪክ የሚነሳ፦ በሚገፋ ማስነሻ ወይም በቁልፍ እንዲነሳ በማድረግ
በራሱ ጊዜ የሚነሳ(automatic start)፦ ዋናው መሰመር ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ሲቋረጥ ያለ ሰው ድጋፍ እንዲነሳ በማድረግ እና ሌሎች መንገዶች ይኖራሉ
👉 ለጥገና ምቹ መሆኑን፦ ጄኔሬተሩ ጥገና በሚያስፈልገው ጊዜ የመልዋወጫ እቃዎቹ በበቂ ሁኔታ ማግኘት እንደምንችል ማረጋገጥ ይኖርብናል። እና ያለብለሽት ረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 እራሱን ከብልሽት የመጠበቅ አቅም፦ የሞተር ዘይት በሚቀንስበት ጊዜ ፣ የተሰበረ አካል ሲኖር እና ሌሎች ድንገተኛ ጉዳዮች ሲከሰቱ ቀድሞ እራሱን ሚያጠፋ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ዋጋ፦ ጄኔሬተሩን የምንገዛበት ዋጋ እና መስራት ከጀመረ በኋላ የምናወጣውን ወጪ ለምሳሌ የነዳጅ ፍጆታ፣ የዘይት አጠቃቀም እና ሌሎች ወጪዎችን ማጣራት ይኖርብናል።
👉 ብራንድ እና ዋስትና፦ የምንገዛው ብራንድ እውቅና እና የሚሰጠን ዋስትና ምን ያህል እንደሆነ ማረጋገጥ ይኖርብናል።