Peka - ፔካ
Open in Telegram
The Great source of Knowledge. ፔካ ብሩህ የሆነ ነጭ ዕንቁ ነው። እውቀትም ብርሃን ነው። You Tube => ? Channel 2 => t.me/Peka369 Owner - @Lumos1
Show more2 958
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-2930 days
Posts Archive
2 958
📌 የጥንታዊት ግብጽ ታሪክ
ለጀማሪዎች - ሙሉ ትምሕርት...By Hailemichael D.
👉 በዚህ ጽሑፍ ስለ ጥንታዊ ግብጻውያን ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋና የሚባሉ ነጥቦችን እንመለከታለን።
ጥንታዊ ግብጻውያን ወይም ጥንታዊት ግብጽ ስንል ወደ አዕምሯችን በርካታ ጉዳዮች ይመጣሉ። ከነዚህም ውስጥ ፒራሚዶች፣ መሚዎች፣ ታላላቅ ፈርዖኖች፣ ሲፊኒክስ፣ ብሉ ናይል(ኒል)፣ የግብጽ አማልክት .... ተጠቃሽ ናቸውና አንድ በአንድ እንያቸው።
👉 ይህ ስልጣኔ መሠረቱን ያደረገው በአባይ ወንዝ ላይ ሲሆን ይህንንም ብዙ አጥኝዎች ይደነቁበታል።
“ግብጽ የአባይ ሥጦታ ናት፤ አባይም የግብጽ ሥጦታ ነው።”
“ያለ አባይ ግብጽ የሚባል ሥልጣኔ አይኖርም ነበር”
(There would be no Egypt without the Nile)
ይህም ብቻ ሳይሆን
ሃፒ (አፒስ, Hapi-The god of the Nile) ብለው ለሚጠሩት የአባይ ወንዝ አምላክ ሳይቀር ስለ አባይ በጸሎቶቻቸው ምስጋናን እንዲ ብለው ያቀርባሉ “Hail to you, O Nile, who flows from the Earth and comes to keep Egypt alive…”
👉 በመልክአ ምድራዊ ይዞታዋ፤ የግብጽን መሬት በሁለት ከፍለን እናጠናለን።
1. ጥቁር መሬት/Black Land፡ ኬሜት(Kemet) ተብሎ ይጠራል፤ ትርጉሙም ጥቁሩ መሬት ማለት ሲሆን በአባይ ጎርፍ ተጠርጎ ወደ ግብጽ የሚሄደው ለም አፈር ነው።
2. ቀይ መሬት/Red Land፡ ታላቁ በርሃ - እስከ ሳሃራ(Sahara Desert) በርሃ ድረስ ያለው ለሕይወት አስቸጋሪው ስፍራ
👉 ይህ ስልጣኔ 5500 ቅ.ል.ክ/BCE አካባቢ የተመሰረተ እንደሆነ ብዙዎች ሲስማሙ ይኸውም ፈረዖን/ንጉሥ ሜኔስ(Menes) የተከፋፈሉትን አውራጃዎች አንድ አድርጎ በመጀመሪያው ዳይናስቲ ከአሁኒቷ ካይሮ ቅርብ በሆነችው በሜምፌስ(Memphis) ከተማን ገንብቷል።
ይህ ስልጣኔ በአጠቃላይ 31 ሥርወ መንግሥታት(Dynasty) ያሉት
በጣም ሰፊ የሆነ የታሪክ ጊዜ አሳልፏል።
👉 እኒህን 31 ሥርወ መንግሥታት/ዲናስቲስ በሦስት የታሪክ ጊዜ ክልሎች/Periods ተለይተው ይጠናሉ።
1. የድሮው ሥርወ መንግሥት/Old Kingdom – 2700 BCE – 2200 BCE
2. መካከለኛው ሥርወ መንግሥት/Middle Kingdom – 2040 BCE – 1786 BCE
3. አዲሱ ሥርወ መንግሥት/New Kingdom – 1570 BCE – 1085 BCE
👉 እነዚህን የታሪክ ክልሎች በጥቂቱ እንመልከት።
1, የድሮው ሥርወ መንግሥት/Old Kingdom (2700 BCE – 2200 BCE)
C. 2600 BCE የታላቁ የጊዛ ፒራሚድ(The great pyramid of Giza) ግንባታ ተጀመረ። ይህ ፒራሚድ በጊዛ(Giza Complex) ከሚገኙ ፒራሚዶች በሙሉ ትልቁና ጥንታዊው ሲሆን በፈርዖን ክሁፉ(Pharaoh Khufu) እንደተገነባ ይታወቃል። ይህ ፒራሚድ 2 × 106 ብዛት ባላቸው እንዲሁም እያንዳንዳቸው 2000 ክብደት በሚመዝኑና በትክክለኛ ቦታ ላይ ብቻ ከተቀመጡ በሚገጥሙ(ልክ እንደ Puzzle) ድንጋዮች በሚገርም ጥበብ ተሰርቷል።
C. 2550 BCE የሲፊኒክ(Sphinx) ሀውልት ግንባታ በጊዛ ተገነባ። ሲፊኒክስ ከወደላይ ያለው አካሉ ግማሽ ሰው የታችኛው አካሉ ደግሞ ግማሽ አንበሳ ሁኖ የተሰራ ሃይውት ነው። በፈርዖን ካፍሬ(Pharaoh Khafra) በ2494 BCE እንደተገነባ መረጃዎች ይገልጻሉ።
2, መካከለኛው ሥርወ መንግሥት/Middle Kingdom (2040 BCE – 1786 BCE)
C. 1991 - 1800 BCE ግብጽ እስከ ታችኛው ኑቢያ(Lower Nubia) ድረስ ግዛቷን አሰፋች።
C. 1991 - 1800 BCE የስዕልና የጥበብ ጊዜ ነበር። በዚህም ጊዜ የባለሐብቶች ልጆች ወደ ቤተመቅደስ ገብተው መጻፍና ማንበብ ይማሩ ነበር።
C. 1878 - 1840 BCE በሴኑስሬት(Senusret III) ታላቅ ጠንካራ መንግሥት ነበራት።
c. 1720 BCE ግብጽ በባለ ሠረገላ ተዋጊዎች ሃይኮስ(ሂክሶስ፣ Hykos) ተወራ ነበር፤ ይህ የሆነው በመካከለኛው ኪንግደም መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ኒው ኪንግደም ሲጀምር ግብጽን ለቀው ወጠዋል።
3, አዲሱ ሥርወ መንግሥት/New Kingdom (1570 BCE – 1085 BCE)
c. 1503 – 1482 BCE ፈርዖን ሃትሽፕሱት (Hatshepsut- Female pharaoh) የገዛችበት ግዜ
c. 1361 – 1351 BCE ፈርዖን ቱት (pharaoh Tut) የገዛበት ጊዜ
c. 1290 – 1224 BCE ፈርዖን ራምሴስ 2ኛ(Pharaoh Ramses II) የግብጽን ግዛት አስፍቷል።
📌 ታላላቅ ፈርዖኖች/ The Greatest Pharaohs
የጥንታዊ ግብጽ ነገሥታት ፈርዖን ተብለው ሲጠሩ በሕዝቡ ዘንድ እኒህ ፈርዖኖች መለኮታዊ ኃይል እንዳላቸው ተደርጎ ይታመን ነበር።
👉 ቱትሞሲስ 3ኛ (Tuthmosis III) - ይህ ፈርዖን ጦርነት ጥበቡ ታዋቂ ሲሆን ሠራዊቱን ከ17 ጊዜ በላይ ወደ ጦርነት መርቷል። በአገዛዙም ዘመን ግብጽ ታላቅ ሥልጣኔ ነበረች።
👉 አኬኔቴን (Akeneten/ አሜኖፌስ 4ኛ/ 1352-1336 BCE) - ይህ ፈርዖን በጥንታዊ ግብጽ ሃይማኖት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ አድርጎ ነበር። ይህም ብዙ አማልክትን የሚመለክበት(Polytheism) የነበረውን ሥርዓት አንድ የፀሐይ አምላክ(Monotheism) የሚል አስተምሕሮና እምነት ይዞ የተነሳ ፈርዖን ነው።
👉 ሜኔስ(Menes) - የላይኛውንና የታችኛውን ግብጽ አንድ አድርጎ በ3100 የገዛ ፈርዖን ነው።
👉 ራምሴስ 2ኛ(Ramses II) - ከግብጽ ከፍ ብለው ከሚገኙትና ታላቅ ጠላቶች ከሆኑት ከሃይታይቲስ(Hittites) ጋር ከ 30 ዓመት በላይ የተዋጋ ፈርዖን ሲሆን በስተመጨረሻም የሃይታይት ግዛትን ልዕልት አግብቶ ሰላምን አድርገዋል።
👉 ራምሴስ 3ኛ(Ramses III) - ይህ ፈርዖን የመጨረሻው ታላቁ ተዋጊ ፈርዖን ሲሆን ግብጽን ከSea Peoples ጥቃት የጠበቀ ነው። ይህ ፈርዖን ካረፈ በኋላ ግን የጥንታዊት ግብጽ ሥልጣኔ እንየደከመና እየደከመ ሂዷል። ከዛም በተከታታይ በአሦራውያን፣ በኑቢያን፣ በፐርሺያን ተወራለች።
በርካታ ፈርዖኖችን መዘርዘር የሚቻል ቢሆንም እንደ መግቢያ ይህ በቂ ይመስለኛል።
2 958
🖤 YouTube ላይ የተለቀቁት ቪዲዮዎች[የጥንታዊ ግብጽ ሙሉ ታሪክ፣ ቀመረ ፊደል ሙሉ ትምህርት፣ ጣናና የጣና ገዳማት ታሪክ] በጽሑፍና በPDF አዘጋጅቼ እዚጋ ይለቀቁ ?
2 958
Watch "የጥንታዊት ግብጽ ድንቅ ታሪክ - The history of the Ancient Egypt in 30 minutes!" on YouTube
https://youtu.be/QyfXkQEreNU
2 958
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ! አደረሰን!
መልካም በዓል! ይሁንላችሁ እያልኩ በቀመረ ፊደል ዙሪያ እንደምታውቁት የ30 ደቂቃ ቪዲዮ ለቅቄ ነበር፤ ሌሎቻችሁ ታሪክ ይለቀቅልን ስላላችሁ በጥንታዊ ግብጻውያን ዙሪያ የ30 ደቂቃ መርኃግብር አዘጋጅቻለሁ።
ከበዓል በኋላ የሚለቀቅ ይሆናል።👍
መልካም ጊዜ! መልካም በዓል!🙏
✍ @Hailemichaeldt
2 958
Watch "ቀመረ ፊደል ሙሉ ትምህርት - Gematria / Numerology FULL COURSE in just 30 MINUTES!" on YouTube
https://youtu.be/cQmy7algbOI
2 958
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ YouTube ላይ የቀመረ ፊደል ሙሉ ትምህርት ቪዲዮ Live የሚለቀቅ ገብታችሁ እንድትመለከቱ ተጋብዛችኋላ።
Youtube.com/@Haile12
2 958
ሻሎም
በሁሉም ሶሻል ሚዲያዎች እንደጠፋሁና እንድመለስ የነገራችሁኝ አላችሁና ስለሱ ምላሽ ለመስጠት ነው የመጣሁት።
በመጀመሪያ ሁላችንም አመሰግናለሁ ።
የጠፋሁበት የራሴ ምክንያት ቢኖረኝም በየወሩ በቻልኩት መጠን የተለያዩ ጠቃሚ የምላቸውን ትምህርቶች በYouTube, በTelegram በአጫጭር ደቂቃዎች በአጭር ጊዜ አዘጋጅቼ እስከምችለው ጊዜ ለመልቀቅ እሞክራለሁ ።
ሌላው የTelegram Members ቀንሷል ለሚለው አዎ ከ7000 ወደ 5000 ቀንሷል። ምንም ነገር ስለቅ ስላልነበረ ይህ የኔ ችግር ነው። 🙌 ግን ይህ አያስጨንቅም ትንሽም ብንሆን እኛ መጓዝ እንችላለን ።
በዚህ ሳምንት በአዲስ ትምህርት እንገናኝ።👍
አመሰግናለሁ !
መልካም ጊዜ።
✍ Hailemichael D.
👉 From @EthiopeTowoderos ( @pekatube )
2 958
በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ከ100- 200 ቢሊዮን የሚሆን ከዋክብቶች ሲኖሩ በዩንቨርስ ውስጥ ያሉት ጋላክሲዎች ደግሞ 200 ቢሊዮን ሲሆኑ በዮንቨርስ ውስጥም ያሉትም ከዋክብትም ብዛትም 10 ሴክስቲሊየን 10(12) ነው። አስገራሚ እውነተኛ የሆኑትን መረጃዎች ለማግኘት 👇👇👇👇
2 958
በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ከ100- 200 ቢሊዮን የሚሆን ከዋክብቶች ሲኖሩ በዩንቨርስ ውስጥ ያሉት ጋላክሲዎች ደግሞ 200 ቢሊዮን ሲሆኑ በዮንቨርስ ውስጥም ያሉትም ከዋክብትም ብዛትም 10 ሴክስቲሊየን 10(12) ነው። አስገራሚ እውነተኛ የሆኑትን መረጃዎች ለማግኘት 👇👇👇👇
2 958
📚 የመናፍስቱ መንደር part 1
📌 ይህን ማራኪ መጽሐፍ እንድታነቡት እመክራችኋለሁ። በተለይ በጥንታዊ አፈታሪኮች ተረቶችና ጥንታዊ መናፍስት ዙሪያ ጥናት መስራት ለምትፈልጉ ሰዎች ሀገር አቀፍ የመናፍስት ኢንሳይክሎፔዲያ እንደማለት ነው። ከዚህ በላይ ከታሪክ እንዲሁም Beyond ፊዚክስ ተብሎ ከሚጠራው ከMETA-PHYSICS አንጻር ብዙ ጥናቶችን እንደምትሰሩበት ተስፋ አደርጋለሁ።
@EthiopeTowoderos
