Peka - ፔካ
Open in Telegram
The Great source of Knowledge. ፔካ ብሩህ የሆነ ነጭ ዕንቁ ነው። እውቀትም ብርሃን ነው። You Tube => ? Channel 2 => t.me/Peka369 Owner - @Lumos1
Show more2 958
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-2930 days
Posts Archive
2 958
ከስነ መለኮት ጽሁፎች አንጻር የመጀመሪያው ራማያና(የራማ የፍቅር ታሪክ) ሲሆን ሁለተኛው ማሃባራታ(የብሃራታ ስርወ መንግስት ረጅሙ ግጥም ወደ መቶ ሺህ ስንኝ ይዟል፤ አስባችሁታል? ፤ ከዚህ በተጨማሪ ማሃብራታ ታዋቂውን ውብ ባሃጋቪድ ጊታ የተሰኘ ጽሁፍ ይዟል፤ ማለትም የጌቶች መዝሙር እንደማለት ሲሆን በ18 ክፍል የተከፈለ በልኡል አርጁን እና በክሪሽና() መሃል የተደረገ ንግግሮችን የያዘው ነው፡፡ ዋና ምክሮቹም ስለ መልካም ስራ፣ እውቀትና ለፈጣሪ ስለመታመን ነው ) እኒህ ሁለቱ ተዋቂ ሁነው ሲጠቀሱ ብዙ ጊዜ የማይነሳው ፑራናስ(ፑራኒ ከሚለው ቃል የመጣ ነው ትርጉሙም ጥንታዊ እንደማለት ነው) አስገራሚ ኢፒኮች ውስጥ ይመደባል፡፡
ወደ ነገስታት ታሪክ ስንመለስ ልዑል ሲዳሃርታ ጋውተማ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከጤና እና ከደስታ በቀር ምንም ሳያውቅ በቤተ መንግስት ውስጥ በወላጆቹ ተጠብቆ ቆይቷል። አንድ ቀን ግን ቤተ መንግሥቱን ለቆ ወደ ውጭው ዓለም እንዲሄድ ጠየቀ፣ እናም የታመሙ ሰዎችን ሲያይ በጣም ደነገጠ፣ እና ይባስ ብሎም የሞቱ ሰዎችን ተመለከተ፡፡ የሰው ልጅን ስቃይ እና የእራሱን ሟችነት አስተዋለ፤ ከዛም በጫካ ውስጥ ብዙ ጊዜ አሳለፈ ቀጥሎም በህንዶች እንደተመዘገበው የኒርቫና ደረጃ ላይ በመድረሱ ቡድሃ( ትርጉሙም የበራለት እንደማለት ነው፡፡) በመባል ተጠራ፡፡
ከጊዜም በኋላ የሱ ትምህርቶች እንደ ሃይማኖት እየሆኑ አሁን ደርሰዋል፡፡
የዛሬውን ቪዲዮ ለማሳጠር ያህል እንደምታውቁት ታላቁ እስክንድር የኢንዱስ ወንዝን ማለፍ ተስኖት ወደ መጣበት ከተመለሰ በኋላ ቻንድራጉፕታ የተባለ የክሻትሪያ ቫርና አባል ሰሜናዊ ህንድን ድል በማድረግ የህንድ የመጀመሪያው ትልቅ የሆነውን የማውርያ ኢምፓየር መሰረተ። ( 322 ቢሲኢ ላይ)
አዲሱ ኢምፓየር ከጥንታዊቷ(ሄለንስቲክ) ግሪክ እና ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርቷል። ቻንድራጉፕታ ለሁለት አስርት አመታት በስልጣን ላይ የቆየ ጠንካራ ገዢ ነበር፡፡ በኋላም በታሪክ ውስጥ ስሙ የማይጠፋው የልጅ ልጁ አሾካ ወደ አለም ስሙ ከፍ ብሏል፡፡
ታላቁ አሾካ በ273 ቢሲኢ ወደ ዙፋኑ ሲወጣ፣ ወደ ምሥራቅ እስከ ካሊንጋ(ጥንታዊ ግዛት) የባሕር ዳርቻ ድረስ ደም አፋሳሽ በሆነ እስከ መቶዎች የሚደርሱ ሰዎች በሞቱባቸው ጦርነቶች ግዛቱን አስፍቷል፡፡ በኋላም ላይ በዚህ ልቡ ስለተነካ በዋናነትም ካሊንጋ ላይ በነበረው ጦርነት ፤ አሾካ። በግዛቱ በሙሉ ይቅርታ በመጠየቅ ቡዲስት ሆኖ ሰላማዊና ተወዳጅ ገዢ ሁኗል፡፡
ከዚያም የንግድ ግንኙነቶችን ለመገንባት እና የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል ብዙ ሰርቷል፤ ለሌሎች እምነቶችም ጥሩ የሆነ አመለካከት ነበረው፤ እና በቡድሂዝም ወደ ውስጣዊ ሰላም ስላደረገው ጉዞ በሰፊው ጽፏል፡፡
ከታላቁ አሾካ በኋላ የነበሩት ነገስታት ግን ያንያህል የህንድን ግዛት የሚያስጠብቅ ሃይል ነበራቸው ለማለት ይከብድ ነበር ፤ በዚህም ምክንያት የማውሪያ መንግስት ፍጻሜ በ180 ቢሲኢ አካባቢ ሆነ፡፡ እንግዲህ ጥንታዊ ህንድ ይህን ትመስላለች፤ ከኢንዱስ ወንዝ ሸለቆ ጀምሮ እስከ ታላቁ አሾካ ግዛት ድረስ አለምን የሚያስደንቅ ስራ ሰርተው አልፈዋል፡፡
በዛሬው የፔካ ቪዲዮ ስለጥንታዊ ህንድ በቻልኩት መጠን ለማጠቃለል ሞክሬአለሁ፤ በቀጣይ ስለምን እንዳቀርብላችሁ እንደምትፈልጉ ኮመንት ላይ አሳውቁኝ፡፡
ሰናይ ሶቤ!
Join & Share
@EthiopeTowoderos
2 958
📌 የፔካ ጉዞ በጥንታዊ ህንድ - PEKA
ያልተፈታችው ሀገር - የጥንታዊ ህንድ ታሪክና ለአለም ያበረከቱት ስጦታዎች
📌 የህንድ ሥልጣኔ ቀደምት ማስረጃችን በ ኢንዱስ ሸለቆ ውስጥ ባሉ ስፍራዎች በሁለት እና በሦስት ሺዎች ቢሲኢ ጀምሮ እስከ የነሃስ ስልጣኔ መዳረሻ ድረስ የቆየ ጥንታዊ ስልጣኔ ነው፡፡ መልካ ምድሩ ለማልማት እና ለመገንባት አመች ነበር, ስለዚህም ይህ ማህበረሰብ በሚያስደንቅ ሁኔታ የሰለጠነ ነበር፡፡
በ1800 እና በ1900 ዎቹ በብሪትሽ የአርኪዮሎጂስቶች ተቆፍረው የወጡት ሃራፓ እና ሞሄንጆ-ዳሮ ከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ጡቦች፣ ንፋስ ለመያዝ እና ከተማዋን ለማቀዝቀዝ በፍርግርግ ስርዓት ላይ የተዘረጉ መንገዶችን ተገኝተዋል፡፡ በአስደናቂ ግንባታ የተዋቀሩ የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎች እና ግዙፍ የህዝብ መታጠቢያዎች ቦታዎች ነበሩ፡፡ ከግብጽ ታላቁ የጊዛ ፒራሚዶች ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ቀድማ ህንድ ለ2000 አመታት የትኛውም ስልጣኔ ያልበለጣት ምድር ነበረች፡፡
የግንባታው ጥራት ደግሞ የኢንዱስ ሸለቆ ህዝብ ከጊዜያቸው በላይ እንደሆኑ ያሳይ ነበር ፤ የተቀሩት የነሐስ ዘመን ሥልጣኔዎች ገንዘቦቻቸውን በቤተመቅደሶች እና በቤተ መንግሥቶች ላይ ሲያውሉ፣ ኢንደስ ሸለቆ ህዝቦች ግን ከረጅም ጊዜ በፊት ታላላቅ የህዝብ መገልገያ ስፍራዎችን ሰርተው፤ የተለያዩ ህጎችን አውጥተዋል! ከሜሶጶጣሚያ ጋር የነበራቸው የንግድ ትስስር በጣም ፈጣን ስለነበር ከዓረቢያን ባህር አሳ ያስመጡ ነበር።
በተጨማሪም ሞሄንጆ-ዳሮ እና ሃራፓ በትክክል ጎረቤቶች አይደሉም፣ስለዚህ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት አንድ አይነት የበላይ የሆነ መንግስትን ያመለክታሉ፣ነገር ግን ለምን፣ ማን እንደሆነ አናውቅም፣ ምክንያቱም ጽሑፎቻቸውን መፍታት ስላልተቻለ ነው። ምናልባት አንድ ቀን እናንተ ትፈቱት ይሆናል?
ሌላ በጣም አስገራሚ የሆነው ነገር፤ በየትኛውም ቦታ ምንም አይነት መሳሪያ አለመገኘቱ ሲሆን ። መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ፍጹም ሰላማዊ ህዝቦች ነበሩ።
ግን ያ የነሐስ ዘመን ነው! በኋላም በ 1700 እና 1500 ዎቹ ቢሲኢ መካከል የኢንዱስ ሸለቆ ሥልጣኔ ምክንያቱ አሁን ድረስ ባልተፈታ ሁኔታ ጠፋ፡፡ ብዙ የታሪክ አጥኝዎች የሚስማሙበት ግምትም አፈሩ ለምነቱን በማጣቱ ምርታማ ባለመሆኑ ምክንያት ስልጣኔው ጠፋ ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ አልያም ሌላ የተፈጥሮ አደጋ የኢንዱስ ወንዝን መንገድ በማዛባቱ ምክንያት በተፈጠረ ድርቅ ነው ይላሉ፤ ግን ሁለቱንም መላምቶች የሚደግፍ በቂና አጥጋቢ ማስረጃ አሁን ድረስ አልተገኘም፡፡
ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን፣ የኢንዱስ ሸለቆ ሰዎች የበለጠ ወደ ባሕረ ገብ መሬት የገቡ እና በመጨረሻም በደቡቡ ስፍራ የሰፈሩ ይመስላል። ስለዚህ የሸለቆው ፍርስራሽ እስከ 1800ዎቹ ድረስ ተቀብሮ ነበር።
ነገር ግን ታሪኩ ከኢንዱስ ሸለቆ ሥልጣኔ በኋላ ባሉት መቶ ዓመታት ውስጥ ኢንዶ-አሪያውያን ከመካከለኛው እስያ ፍልሰት ቀጥሏል። ይህም በታሪክ ውስጥ አወዛጋቢ ክስተት ሁኖ ቀጥሏል፡፡
አርያንስ፣ ከግንበኝነት ይልቅ ጥበብና እውቀት ላይ ትኩረት ነበራቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የቬዲክ ህዝቦች ተብለው ይጠራሉ፣ ይህም የመጣው ከቅዱስ መጽሃፎች ከአራቱ ቬዳ ነው። ካስፈለገ ስለመጽሀፍቶቻቸው በቀጣይ የምናይ ይሆናል፡፡ እነዚህ ከትልቅ ኮስሞሎጂያዊ ትንበያዎች ጀምሮ እስከ ራሳቸው የዕለት ተዕለት አኗኗር ድረስ ያሉትን ጨምሮ የያዙ ታሪኮች ነበሩ። እኒህ መጽሃፍ እንደ መዝሙረ ዳዊት የሚሸመደዱና የማህበረሰቡ የህይወት አካል ናቸው፡፡
እነዚህ መለኮታዊ መዝሙሮች የሂንዱይዝምና የህንድ ባህል መሰረት ናቸው፡፡ ከታሪክ አኳያ፣ ሂንዱይዝም ከጥንታዊ አመጣጥ እስከ ሰፊ ዘመናዊ አሰራር ድረስ ባለው ቀጣይነት ምክንያት በጣም ልዩ ነው።ደስ የሚልና እጅግ በጣም የተወሳሰበ ታሪክ ነው።
ስለዚህ በቀጥታ ወደ ቀጣዩ የኢንዶ-አሪያን ባህል ዋና ገጽታ እሄዳለሁ፡፡ በመጀመሪያም አርያንስ በማህበረሰቡ ውስጥ እንደታላቅ ተምሳሌት ሲወሰዱ ነበር፤ በኋላም ከኔቲቭ ነዋሪዎች ጋር ለዘመናት ስለተደባለቁ፣ የማህበረሰብ ክፍፍል ሥርዓቱ ከጊዜ በኋላ በብሔረሰብ ሳይሆን አሁን እንደምናውቀው ሆኖ በሙያ ደረጃ ወጥቷል።
በዚህም የምድብ/ ካስት ስርአት ወይም በህንድ ቋንቋ ቫርናስ ተብሎ በሚጠረው ምድብ ከላይ ያሉት የብራህማን ቄሶች፣ ከዚያም የክሻትሪያ መሪዎች እና ተዋጊዎች፣ የቫይሽያ ነጋዴዎች እና ገበሬዎች፣ የሱንድራ ሰራተኞች፣አገልጋዮችና የእጅ ስራ ጠቢቦች በመጨረሻም ንኡስ ምድብ ወይም በጥንታዊው ህንድ አጠራር ዳሊት ወይም አቾት (የማይነኩ እንደ ማለት ነው) የሚባሉት ናቸው፤ እኒህ ምድብ እንደ ከቫርናስ ማለትም ጃቲ ወይም ካስት ሲስተም ውስጥም አይመደቡም ነበር፤ በህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ የተገለሉ ነበሩ። ስለዚህም አራት ቫርናስ ወይም ካስቶች በካስት ሲስተም ጃቲ ውስጥ ይገኛሉ ማለት ነው፡፡
የቬዲክ ባህል ከክርስቶስ ልደት በፊት በመጀመርያው ሺህ ዓመት እያደገ እና እየተሻሻለ ሲመጣ፣ ኡፓኒሻድስ በሚባሉ ተከታታይ ጽሑፎች አማካኝነት አዲስ የፍልስፍና አስተሳሰብ እያደገ መጣ። ትርጉሙም በጥንታዊውና ከጥንታዊ ቋንቋዎች የኔ ፌቨራይት በሆነው ሳንስክሪት ቋንቋ "በቅርብ መቀመጥ" እንደማለት ነው፡፡ ይህም ጥበብ ከመምህር ስር በመቅረብና በመቀመጥ በውይይት ትገኛለች ሚለውን የማስረዳት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡
እንደ ኮንፊሺየስ ወይም ዳኦጂንግ ፤ ኡፓኒሻድስ ተከታታይ የሆነ አጭር ትምህርቶች ይዟል። የቀደሙት በአራቱ ቬዳዎች ላይ ይታያሉ፣(አራቱ ቬዳ የሚባሉት፤ ሪግ፣ ያጃር፣ ሳማና አትሃርቫ ናቸው) ነገር ግን ብዙዎች ኡፓኒሻድስ የተቀናበሩ እና በኋላ የተጨመሩ ናቸው። ስለዚህ ከዚህ የምንረዳው የቬዳ መጽሃፍት የሕንድ ሃይማኖት እና አፈ ታሪክ መሠረት እንደመሆናቸው መጠን ኡፓኒሻድስ የሕንድ ፍልስፍና መሰረት ናቸው።
ምናልባትም የማታውቁ ከሆነ አንድ ሁለት ፋክት ልንገራችሁ የቬዳ መጽሃፍትን ለማጥናት ማለትም ለመሸምደድና ለመረዳት ፈጣን ለሆነ ሰው በትንሹ አርባ አመት እንደሚጨርስ ታውቃላችሁ? እንደዛም ሁኖ በመረዳት አቅም ምክንያት ምንም ላትረዱት ትችላላችሁ፤ በነገራችን ላይ ኳንተም ፊዚክስ ጋርም የሚገናኙ ጥቅሶች ከመጽሃፉ እንደተገኙ ታውቃላችሁ? ብቻ ጊዜ ወይም ተመራማሪ የሚፈታው ጉዳይ ነው፡፡
ከኢንካርኔሽን ዑደት ጀምሮ፣ እንደ ሰው የምናደርጋቸው አክሽኖች ሪአክሽን ፎርስ እንዳላቸው(ማለትም ካርማ)፣ እንዲሁም በዩኒቨርስ ውስጥ ያለን በራስ የመተማመን ስሜት የመጀመሪያዎቹን ርዕሶች ያገኘነው እዚህ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ኡፓኒሻድስ የእውቀት ማህደሮች ነበሩ፡፡
2 958
🛑 ያልተፈታችው ሀገር - የጥንታዊ ህንድ ታሪክና ለአለም ያበረከቱት ስጦታዎች - የፔካ ጉዞ በጥንታዊ ህንድ
የጥንታዊት ህንድ ከተሞች ሞሄንጆ ዳሮ ፣ ሃራፓ፣ ሎታል ... እና የመሳሰሉት ታሪኮቻቸው፣ አስገራሚ ግንባታዎች ፤ እንዲሁም የዓለማችን ጥንታዊ መጽሃፍት የሆኑት በአስገራሚው ሳንስክሪት ቋንቋ የተጻፉት አራቱ ቬዳዎች(ምናልባትም ከግል ልምድ አንጻር ካየሁት ከኳንተም ፊዚክስ ጋር ሊንክ ያላቸው) እንዲሁም ማሃባራታና ራማያና እንዲሁም ፑራና እና ኡፓኒሻድስ ይዘታቸው ምን ይመስላል፤ ሌላም ስለ ህንድ ካስት ሲስተም ማለትም ጃቲ እና ቫርናስ ይዘት ተዘርዝሯል፤ በመጨረሻም ከነገስታት የማውሪያ ሥርወ መንግስትን ቻንድራጉፕታ ማውሪያ እንዲሁም የሲድሃርታ ጋውተማ የልጅ ልጅ የሆነው ታላቁ አሾካ ስለሰሩት ስራዎች በዚህ ቪዲዮ ተቃኝቷል።
https://youtu.be/Mz0mGjIJJvI
2 958
📌 የፔካ ጉዞ በጥንታዊ ሜሶጶታሚያ - PEKA
የዓለማችን የመጀመሪያው ስልጣኔ? ለዛሬው ስልጣኔ መሰረት የሆኑት ህዝቦች ፈጠራ
📌 የአጻጻፍ፣ የሥነ ፈለክ ጥናት እና የሕግ ታሪክ። የስልጣኔ ታሪክ ራሱ የሚጀምረው ከአንድ ቦታ ነው። ግብፅም፣ ግሪክም፣ ሮምም አይደለችም። ሜሶፖታሚያ።
ሰላም ውድ የፔካ ቤተሰቦች፤ ከብዙ ጊዜ በኋላ ተመልሻለሁ፤ ይመቻቹ።
ሜሶጶጣሚያ በጤግሮስ እና በኤፍራጥስ ወንዞች መካከል የሚገኝ እጅግ በጣም ለም ስፍራ ነው። ለአምስት ሺህ ዓመታት፣ ዛሬ ኢራቅ፣ ኩዌት እና ሶሪያን ያካልል በነበረው ስፍራ አለምን እስከሌላኛው ጥግ ድረው የሚገይሩ ፈጠራዎች የተጀመረበት ነው ፡፡
ወደ 12,000 አመታት ለሚጠጉ ዓመታት የኖረችው ሜሶጶጣሚያ የተረጋጋ የአየር ንብረት፣ በማእድናት የበለፀገ አፈር እና የማያቋርጥ የንጹሕ ውሃ አቅርቦት ለእርሻ ልማትና እድገት ተስማሚ አድርጎታል። የዛሬ 6,000 ዓመታት ገደማ፣ በአንድ ሌሊት የሚመስሉ፣ ከእነዚህ የግብርና ሰፈራዎች አንዳንዶቹ ወደ አንዳንድ የዓለም የመጀመሪያ ከተሞች አድገዋል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ4,000 እስከ 3,100 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ሜሶጶጣሚያ በውስጧ በሚገኙ ተወዳዳሪ የከተማ ግዛቶች ህብረ ከዋክብት የተሞላች ነበር።
በአንድ ወቅት፣ በአካድያን ግዛት ሥር አንድ ሆነዋል፤ ከዚያም ተለያይተው የአሦርንና የባቢሎንን ግዛቶች መሠረቱ። የማያቋርጥ ጦርነት ቢፈራረቁም በጥንቷ ሜሶጶጣሚያ ውስጥ ፈጠራ እና ልማት ሁሌም ነበሩ። ከቤተ መንግስቶች እስከ ዚጉራት ድረስ ባለው ግዙፍ ደረጃ የተገነቡ፣ ግዙፍ ቤተመቅደሶች ከአማልክት ጋር ለመነጋገር እንደ የአምልኮ ስፍራ ሆነው አገልግለዋል።
ወደ ሳይንሳዊ ጉዳዮች ስንመጣ የ60 ሰከንድ ፣ የ60 ደቂቃ፤ እና የ360 ዲግሪ ክብ ማዕዘን የፈጠሩ 60ን መሰረት ያደረገ ስርዓትን ጨምሮ የላቀ የሂሳብ ትምህርት ነበራቸው። ባቢሎናውያን የረቀቀውን የሒሳብ ሥርዓታቸውን ተጠቅመው ሰማይን በካርታ በማጥናት አለምን አስገርመዋል። አንድን የምድር አመት በ12 ክፍለ ጊዜዎች ከፋፍለዋል። እያንዳንዳቸው የተሰየሙት በሰማያት ውስጥ በጣም ታዋቂ በሆኑት ህብረ ከዋክብት ሲሆን ይህን መሰረት አድርገው በኋላ ላይ ግሪኮች ዞዲያክን ፈጥረዋል።
በተጨማሪም ሳምንቱን በሰባት ቀናት ከፋፍለው እያንዳንዳቸው በሰባት አማልክቶቻቸው የሰየሙት በሰማይ ላይ የሚታዩት ሰባት ፕላኔቶች ናቸው። ነገር ግን ምናልባት ከሜሶጶጣሚያ የሚመጣው በጣም ተፅዕኖ ያለው ፈጠራ ማንበብና መጻፍ ነው። በ 3,200 BCE ወደ አንድ የተራቀቀ የአጻጻፍ ስርዓት የዳበሩትን እቃዎች እና ሀብቶች ለመከታተል ቀለል ያሉ ስዕሎችን ለመሳል በእርጥብ ሸክላ ላይ መቅረጽ ጀመሩ፡፡ በዚህም ታዋቂው አይን ለአይን እየተባለ የሚጠራው ደረጃውን የጠበቀ የፍትህ ስርዓት የሃሙራቢ ህግ በታላቁ ንጉሥ ሀሙራቢ ዘመን(1750 BCE) ተጽፏል፡፡
የሜሶጶጣሚያ ስኬት ከጊዜ በኋላ ሌሎችን ስልጣኔዎች ትኩረት መሳብ ጀመረ። በተለይ ባቢሎን የውጭ ግዛቶችን አይን በሀብቷ ምክኛት ስባለች፡፡ በ539 BCE. የፋርስ ንጉሥ የነበረው ታላቁ ሳይረስ ባቢሎንን ድል አደረገ እና ሙሉ ሜሶጶጣሚያን ተቆጣጠረ፤ ይህም የሆነበት ምክኛት በጊዜው ዋናዋ ግዛት ባቢሎን ነበረች፡፡ ለብዙ መቶ ዘመናት ይህ አካባቢ የውጭ ግዛቶች ሲቀባበሉት ኖረዋል፡፡ በኋላም ሜሶጶታሚያ በታሪክ ውስጥ ስሟ ደብዝዟል።
ከተሞቿም ከኢራቅ አሸዋ በታች ተደብቀዋል። ነገር ግን ሃሳቦቿ በንባብ፣ በህግ፣ በሂሳብ፣ በሥነ ፈለክ ጥናት እና በሥልጣኔ ስጦታ በራሱ ዘመናትን ተሻግረው አሁን ላለንበት ስልጣኔ መሰረት ሁነዋል፡፡
የዛሬው ቪዲዮ ይህን ይመስል ነበር፤ እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቀጣይ ምን እንደማቀርብ ኮመንት ላይ አስቀምጡልኝ፡፡
ሰናይ ሶቤ!
@EthiopeTowoderos
2 958
🛑 የዓለማችን የመጀመሪያው ስልጣኔ? ለዛሬው ስልጣኔ መሰረት የሆኑት ህዝቦች ፈጠራ
የፔካ ጉዞ በጥንታዊ ሜሶጶታሚያ - PEKA
https://youtu.be/o-4jFLxIPu0
2 958
+5
ያልተፈታው ትርጉም🤔
ስለ ሀገራችን ስታስቡ፤ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ብቻ ለመተርጎም አንድ ሙሉ መጻሕፍ ምናልባት ከዚያም በላይ እንደሚያስፈልገው አስባችሁት ታውቃላችሁ?
2 958
CODE ⓵⓸
በሰላሳ ዲናር የተሸጠች ሀገር
ማነው ባለ ተራ ይሁዳን መሳይ?
በዚህ እየሳመ ሀገሩን 'ሚሸጥ አስመሳይ፣
የታል አጭበርባሪው ያ ቀማኛ?
እስቲ በሉ ጠቁሙኛ፣
ሀገሬን ሚሸጣት እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ፣
እናቱን 'ሚረግጥ ሚከፋ ከባዳ፣
እሱንም ላይጠቅመው እሷም ልትጎዳ፣
ይቺ ምስኪን እናት አለች ተቆራፍዳ።
ዛሬም እንደሌላት፣
ዛሬም እንዳጣች በችጋር ኮስምና፣
በአጥንቷ ቀርታ እጅጉን መንምና፣
ገፅታዋ በኖ በሀዘን ተሰብራ፣
በሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ አዴራ፣
ችንካር ተቸንክራ፣
እያረፉ የሚገርፏት ፣
መራራውን የሚግቷት፣
ሳትበድል ተበቀሏት።
እንደ ዐለቅት ደሟን የመጠጠ፣
የወረሰውን እምነት ትውፊት ትውልዷን የሸጠ፣
ከእህት ወንድሞቹ ገንዘብ የመረጠ፣
እከኩን ሳያረግፍ አንዱ ሀገሩን ሸጠ፣
እከኩን ላያረግፍ አንድ ሀገሩን ሰጠ።
ማነው?
ማነው ባለ ተራ ይሁዳን መሳይ?
የአባቶቹን መሬት መቃብር ፈንቃይ፣
እስቲ በሉ ጠቁሙኛ፣
የታል አጭበርባሪው ያ ቀማኛ?
ሰው ኖሮ እንደሌላት ሆነች እማምዬ፣
ተጠማሁ አለች ልክ እንደ ጌታዬ፣
ከራሷ አልፋ ለስንቱ የተረፈች፣
ዛሬ አፍ አውጥታ "ጠማኝ ጠማኝ" አለች፣
በዓባይ በጣና ባ'ክሱም ላሊበላ፣
በፀጋ ተከባ ሳለ እንዲህ አንጀት ስበላ፣
ማን ይከሰስ? ማን ይንኳሰስ?
ማነው ከሃዲ ይሁዳን መሳይ?
ካደገበት ቀዬ ከቤቱ ኮብላይ፣
ማነው እኮ?
ማነው ባንዳ የነጭ ምርኮ?
ቤቱን የሸጠ ህሊናውን ያከራየ፣
አደራውን ዘንግቶ ከበጎቹ የተለየ፣
ባጠመደው ወጥመድ እራሱ ተበላ፣
ከኅብረቱ ወጥቶ ተያዘ በተኩላ።
እንግዲህ እማማ ምን ይሆን ሚሻልሽ?
ለስንቱ ታለቅሺ ስንቱን ትችይዋለሽ?
ስለ ከዳሽ ልጅሽ ወይስ ስለ ሌሎቹ?
ስለ ተስፋ ቢሶች ወይስ ስለ ጠቢቦቹ?
ስለ ኮብላዩ ወይስ ስለ አገልጋዩ?
ስለ ሽማግሌው ወይስ ስለ አራሱ?
ወይንስ ስለ ይሁዳ ስለ እራሱ?
✍ረቂቅ ፊደል
2 958
Repost from Peka - ፔካ
📌 ዓለምን የሚቀይረው የሚናገሩት ቃል አስገራሚ ኃይል
👉🏻 ስለ ቃላት ኃይል ከመናገሬ በፊት ስለ ቃላት ምንነት መረዳትና መገንዘብ አስፈላጊ መስሎ ይታየኛል። ስለዚህ ቃላት ምንድን ናቸው? አንድ ቃል በጆሯችን እናደምጠዋለን ነገር ግን አይያዝም አይጨበጥም ረቂቅ ነገር ነው። ይህም የፊደላት ጥንቅር ሲሆን ይህም ቫይብሬሽን በመሆኑ ምድር ላይ አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖ አለው። ምክንያቱም የቃላት መነሻ ልብ ነው፤ ይህ ሲብራራም የሰው ልጅ ከሰባቱ{7} ባሕርያት የተፈጠረ ነው።
👉🏻 እነዚህም 4ቱ የሥጋ ባሕርያትና 3ቱ የነፍስ ባሕርያት ናቸው። የሰውም የስሙ ምስጢር 7 መሆኑ ስለዚህ ነው። 3ቱ የነፍስ ባሕርያት፦ 1. ሕያዊት ነፍስ(ሕያው የሆነች) 2. ነባቢት ነፍስ(የምትናገር) 3. ለባዊት ነፍስ(የምታውቅ)
👉🏻 በዚህ ሥነ ፍጥረታዊ እሳቤ መሰረትም ነባቢት የምንለው ከላይ እንደተገለጸው መናገር ነው፤ ስለዚህ መናገር የነፍስ ውጤት ነው። ስለዚህም ነው የሞተ ሰው የማይናገረው ምክንያቱም ሞት የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው።
ቃል የልብ ውጤት ነው ካልን፤ ሰው ከልቡ ያለውን ነው አውጥቶ የሚናገረው።
👉🏻 ስለቃላት ይህን ካየን ስለቃላት አይነቶች እንመልከት...
ጥሩና መጥፎ ቃላት ተብለው በ2 ይከፈላሉ።
1️⃣ጥሩ ቃላት: መልካም የሆኑና የሰው ልጅን የመፈወስ አቅም ያላቸው ቃላት ናቸው። ስለዚህም ነው የዕብራውያን ንጉሥ ሰሎሞን “ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው” ብሎ የተናገረው፤ ስለዚህ እነዚህ መልካም ቃላት የሰው ልጅን ሊጠግኑ የሚችሉ ናቸው። እኒህ ቃላት መልካም ልብ ካለው ሰው ከልቡ መዝገብ የሚወጡ ናቸው።
2️⃣መጥፎ ቃላት፡ በNegative Energy የተሞሉ ዓለምን፣ የተናገረውን ሰውን፣ እንዲሁም የሚሰማውንም ሰው የሚጎዱ ቃላት ናቸው። እኒህ መጥፎ ቃላት ክፉ ልብ እንዲሁም በማይጠቅሙ ነገሮች የቆሸሸ ልብ ካለው ሰው የሚወጡ ናቸው።
📜 ከቃላት ጋር በተያያዘ መልኩ ወደ ኢትዮጵያውያን መዛግብት ስንመጣ አንድ የፍልስፍና መጽሐፍን ማስታወስ ግድ ይለናል። አንጋረ ፈላስፋ ተብሎ ይጠራል። ስለ ቃላት እንዲህ እያለም ይገልጻል
👉🏻 “አፍና አንደበት የጥበብ መጀመሪያ ናቸው፤ የጥበብ መጀመሪያ አፍና አንደበትን መጠበቅ ነው”
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሚለውን ወስዶ ስለምን እንዲ አለ? ብንል አፍና አንደበትን መጠበቅ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ወይም እግዚአብሔርን መፍራት የሚገለጸው አፍና አንደበትን በመጠበቅ ነው ማለቱ ነው።
👉🏻 “የሰው ልጅ ጠላቱ አንደበቱ ነው”
ይህስ ምን ማለት ነው? ብትሉኝ ሁሉም ሰው ለተናገራት እያንዳንዷ ንግግር በመጨረሻ ሰዓት መልስ ይሰጥባታል ሲል ነው።
? ለምን ብንል “የጥበብ ቦታ አንደበት ነው” ይለናል፤ “ሞትና ሕይወት በአንደበት እጅ የተያዙ ናቸው” ይህንም ምሳሌ 18፥21 ላይ እናገኘዋለን። ይህ መጽሐፍ ስለአንደበት ብቻ ሳይሆን ስለምንስቀው ሳቅ ሳይቀር ይመክራል፤ ያልታረመ ሰውሲስቅ አፉን ከፍቶ ድምጹን አሰምቶ ነው፤ አዋቂ ብልህ ሰው ሲስቅ ግን አፉን በመጠኑ ከፍቶ ይስቃል፡ ይለናልና ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ ስለቃላትም ስለአሳሳቅም ያስተምረናልና ነገሩ መልካም ስለሆነ ልንማርበት ይገባል።
📜አንጋረ ፈላስፋን እዚጋ አመስግነን ዘጋነው።😁
👉🏻 የምንናገረው ቃላት ከነዚህ በተጨማሪ ያለንበትን ንቃተ-ሕሊና፣ የምናይበትን መነጽር፣ እያንዳንዷን ነገር የምንመለከትበትን “ዐይን” የሚገልጹ ናቸው።
📌 ሌላው ከቃላት ጋር ተያይዞ ጥናቶች ከሰሩ የውጭ ምሁራን መካከል አንዱ Dr Emoto Masaru ናቸው። Dr Emoto Masaru በJapan Yokohama city በ1943 AC የተወለዱ ሲሆን በYokohama University ተምረው። በውሃ ላይ እንዲሁም ስለ ቃል ኃይልም በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። በመጀመሪያ ያሳተመው መጽሐፍ በ45 በላይ ቋንቋዎች የተተረጎመና ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ኮፒዎች የተሸጠው መጽሓፋቸው “Messages from water” ይሰኛል። ከዚህም በመቀጠል “Hidden messages in water” የሚል መጽሐፍ አሳትሟል።
👉🏻 እነዚህ መጻሕፍት ምንድን ነው የሚናገሩት?
ውሃ መረጃን Memorize & Transmit ማድረግ ይችላል የሚል ጥናት ነው። ይህንም በሙዚቃ፣ በጸሎት፣ በፎቶ፣ በቦታ ለውጥ ውሃ እንደሚለዋወጥ፣ መልክ እንደሚለውጡ፣ ጥሩው መጥፎ መጥፎው ጥሩ እንደሚሆን በጥናቱ አረጋግጧል።
ይህ ጥናት ከርሳቸው በኋላ በሌሎችም ሳይንቲስቶችም ተሰርቷል።
👉🏻 ሁለት የውሃ እቃዎችን አስቀምጠው፤ ተመሳሳይ መጠንና አይነት ያለው ውሃ ሞሉባቸው፤ አንደኛው ላይ “እወድሃለሁ አመሰግንሃለሁ” ሌላኛው ላይ “አልወድህም አላመሰግንህም” ብለው ጻፉ። በመቀጠልም ለውጡን ለማየት ወደ በረዶነት ቀይረው ተመለከቱ። “እወድሃለሁ አመሰግንሃለሁ” የተባለው ጠርዙ Transparent ውስጡ ነጭ እንደሆነና ስንጠቃ ብዙም የሌለው በረዶ ሁኖ ሲገኝ ሌላኛው “አልወድህም አላመሰግንህም” የተባለው ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስንጠቃ ያለበት እንዲሁም መሃሉ የጠቆረ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።
👉🏻 Dr Emoto masaru በዚህ ብቻም አላቆሙም፤ Water & Peace Global Forumን አዘጋጁ(1999)። ለዚህም ጥናት በጃፓን የሚገኘውን ትልቁን ሐይቅና በክረምት ወራት ሽታው ነዋሪዎችን የሚረብሻቸው የነበረውን ቢዋ ሐይቅን(Lake Biwa) መረጡ። በዚህ መርኃግብርም “Thank You, lake biwa” እያሉ ወደዛ ሐይቅ መጮኽ ጀመሩ። በነርሱ አጠራርም ጸሎት ሲሆን በዚህ ጸሎታቸው ውስጥ አርምሞና ተመስጦን ገንዘብ አድርገው ነበር። ከዚህ ዝግጅት በኋላም በሐይቁ ላይ የነበረው ክፉ ጠረን እንደጠፋ ጥናቱ ይገልጻል።
👉🏻 Dr Emoto Masaru የቃላትን ኃይል በቀመር(Formula) አስቀምጧል። ይህ Formula ቀድሞ የሚታወቅ ነው፡ E=MC2 ።
E = Energy of words
M = NuMber of people
C2 = Consciences(ንቃተ-ሕሊና)
እኒህ 3ቱ ለቃላት ኃይል ወሳኝ ናቸው ይላል።
👉🏻 ለዚህም ነው በጸሎት ጊዜ የማይታጠፍ ንቃተ ሕሊና፣ ተመስጦ የሚያስፈልገን፤ በሀገራችን ኢትዮጵያም ምህላና መሰል የሕብረት ጸሎቶች ከዚህ ቀመር ጋር የሚሄዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በየገዳማቱ፣ በየቤተክርስቲያኑ የሚጸለዩት ጸሎቶች ውሃውን ወደ ቅዱስ ውሃ(Holy Water) ቀይረው ከግዙፉና ረቂቁ ነገር ሲፈውሱ አይተናል፤ በዚህም ተጠቅመናል።
📌 ከዚህ የምንረዳው የDr Emoto masaru የቅርብ ጊዜ ግኝት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የጥንታዊ ስልጣኔ አሻራ ባረፉባቸው ስፍራዎች ቀድሞ ከብዙ ሽህ ዓመታት በፊት ጀምረው ሲጠቀሙበት እንደኖሩ ታሪክ ይዘግባል።
በዚህ መርሃግብር እንድትይዙልኝ የምፈልገው “ ቃላትን ስንናገር ዓለምን ሊለውጥ የሚችል ኃይል ከአንደበታችን እያፈለቅን ነውና ስለምንናገረው ቃል በደንብ ልናስተውል ይገባል። ”
✍🏾 የዛሬው ጽሑፌ ይህን ይመስላል፤ ከወር በፊት በYouTube ቻናሌ(Peka Tube) ከለቀቅሁት ቪዲዮ የተወሰደ ሲሆን Platformን ለማትጠቀሙ በጽሑፍ ጽፌ ለጠፍኩላችሁ፤ ሃሳብ አስተያየት በ @hailemichaeldt እቀበላለሁ።
መልካም አሁን!
@Ethiopetowoderos
@Pekatube
2 958
📌 ፕሮሞሽን እያሰራን ስለሆነ Leave ማለማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏፤
ሰላም ተወዳጆች በተለያየ ምክንያት በአዲስ ቻናል መጥቻለሁ ከተመቻቹ 👍SUBSCRIBE እያደረጋችሁ።
https://www.youtube.com/@peka369
2 958
📌 የኑሮ ደረጃዎች/ የዕለት ተዕለት ኑሮ በጥንታዊ ግብጽ
በጥንታዊ ግብጽ የነበሩትን የኑሮ ደረጃዎች በ6 ከፍለን ከታችኛው ደረጃ እስከ ላይኛው ጫፍ እንመልከት።
1. ባርያና አገልጋይ(Slaves & Servants)፡ ከደረጃው ታች ላይ የምናገኛቸው ሲሆን ባርያዎች ተብለው የሚጠሩት በዋናነት የጉልበት ሥራ ላይ ልክ እንደ ፒራሚድ ግንባታ... ላይ የሚሳተፉ ሲሆን አገልጋዮች ደግሞ ከሩቅ ለፈርዖኑ የተለያዩ ግብርና ገጸበረከቶችን ይዘው የሚመጡትን እንግዶች የሚቀበሉና የሚያስተናግዱ ናቸው።
እኒህ እንግዶች በአቅራቢያ ከሚገኙ ግዛቶች የሚመጡ ሲሆን ይዘዋቸው ከሚመጧቸው ገጸበረከቶች ውስጥ መዳብና ተርክዌዝ ከሲና’ይ፤ ወርቅ፣ መዳብና አሜቴስጢኖን ከኑቢያ፤ ወይንና ቅባቶች ከክሬት፤ ጨው፣ ተምርና የቀንድ ከብቶች በአቅራቢያ ከሚገኘው በርሃ...... ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም አገልጋዮች ቅባትና የተነጠሩ ቅቤዎችን ከእንግዶች አናት ላይ ያደርጋሉ። ይህም እንግዶችን ለማቀዝቀዝና መልካም መዓዛ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ይታመናል።
2. ገበሬዎች(Farmers)፡ እኒህ የአባይን ጎርፍ የሚመጣበትን ጊዜ ጠብቀው በየዓመቱ መልካም ፍሬ እየዘሩ ጥንታዊ ግብጽን በግብርናው ዘርፍ የያዙ ናቸው። መሬቱ በጎርፍ በሚሞላበት ጊዜ የፒራሚድ ግንባታ ላይ እንደሚሳተፉ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
3. ሰአሊዎችና ጠቢባን(Craftsman)፡ እኒህ ሰዎች የተለያዩ ሃይውልቶችን፣ ስዕሎችን፣ ቅርጻ ቅርጾችን እንዲሁም ለመገልገያ እንደ ማሰሮ የሚሆኑ እቃዎችን፤ በአጠቃላይ የእጅ ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ ናቸው።
4. ጸሐፊዎች(Scribers)፡ እኒህ ሰዎች የጽሕፈት ስራዎች የሚሳተፉ ሲሆኑ ጥንታዊ ግብጽን እንድናውቅ ከረዱን የዘመኑ ነዋሪዎች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህም የምልክት/ስዕላዊ የጽሕፈት ዘዴ የሆነውን ሂሮግሊፍስ(Hieroglyphs) በመጠቀም በፓፒረስ(Papyrus) ላይ የታዘዙትን ጽሑፍ፣ መልእክት፣ ዜና መዋዕል ይጽፋሉ።
• ሂኖግሊፍስ(Hieroglyphs)፡ ይህ ስዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ጥንታዊ ከሚባሉት ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆን ጥንታዊ ግብጻውያን ለግብር ምዝገባ፣ በመቃብርና በግድግዳዎች ላይ መልዕክትን ያስቀምጡበታል። በጥንታዊ ግብጻውያን ሃይማኖትም ይህን የጽሕፈት ዘዴ የጥበብና የጽሕፈት አምላክ የሆነው ቶት(Thoth – god of wisdom and writing) እንደሰጣቸው በሊቃውንቱ ዘንድ ተመዝግቦ ይገኛል። በዘመናችን በተሻለ ሁኔታ የተተረጎመው የሮሴታ ድንጋይ(Rosseta Stone) ከተገኘ በኋላ ነው።
• ፓፒረስ(Papyrus)፡ ይህ መጻፊያ ፓፒረስ ተብሎ ከሚጠራ የዛፍ ልጥ ለጽሕፈት ተዘጋጅቶ የሚወጣ ነው። ይህ ዕፅ በሳይንሳዊ መጠሪያው Cyperus papyrus ሲባል ፋሚሊው Cyperaceae ሲሆን በአባይ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚበቅል ተክል ነው። በዚህ ልጥ ላይ ብዙ የጥበብ፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ... መጻሕፍትን የጻፉ ሲሆን በዋናነት ግን የሚታወቀው በርካታ ገጾች ያሉት የሙታን ግንዘት ጸሎት መጽሐፍ አሁን ድረስ ዓለምን የሚያነጋግር ነው።
5. ቄሶች(Priests)፡ እኒህ በማኅበረሰቡ በጣም የሚከበሩና የሚፈሩ ሲሆኑ በፈርዖኑ ዘንድም ትልቅ ቦታ ይዘጣቸዋል። አንዳንድ ነገሥታትም መንፈሳዊውንም ዓለማዊውን አስተባብረው ይዘው ቄስና ፈርዖን ነበሩ። በርካታ አማልክትን የሚመለኩበትን የጥንታዊ ግብጽን ሃይማኖት በየአማልክቱ ቤተመቅደስ ውስጥ በመግባት ዕጣንና ከርቤን ያጥናሉ። እንዲሁም ከምድር በኋላ ላለው ሕይወት በር ከፋች ነው ተብሎ ለሚታመነው የሙታን የግንዘት ሥርዓት ላይ አስገራሚ የሚባል ጥበብና እውቀትን ተጠቅመው ክንዋኔዎችን ይፈጽማሉ፤ በእጽዋትና ማዕድናት ጥበብም ሳይቀር የተካኑ እንደሆኑ መረጃዎች ይናገራሉ።
6. ፈርዖኖች(Pharaohs)፡ እኒህ ነገሥታት ናቸው፤ ግዛታቸውን በእጃቸው የያዙ የሚፈሩ፣ የሚከበሩና መለኮታዊ ኃይል እንዳላቸው የሚነገርላቸው ናቸው።
📌 የጥንታዊ ግብጻውያን ታላላቅ ሥራዎች
ጥንታዊ ግብጽን በርካታ ሊቃውንት ግሪካውያን ፈላስፎችን ጨምሮ የትምሕርት ሀገር(Land of learning) ብለው ይጠሯት ነበር። በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ከዘመናቸው ቀድመው ጥናቶችን የሰሩ ሕዝቦች ነበሩ። በጽሕፈት፣ በሥነጠፈር፣ በሕክምና፣ በልዕለአካላዊ ጥናቶች ተሳትፈዋል። በጥቂቱ እንመልከት።
👉 በጽሕፈት(Literature)፡ ቅድም እንደጠቀስኩት ከዛፍ ልጥ ፓፒረስ አዘጋጅተው ሂሮግላፊስ በተባለ የጽሕፈት ሥርዓት ጽሕፈቶችን ጽፈዋል፤ ይህ በሰው ልጅ የልውጠት ታሪክ ውስጥ ዋና ስልጣኔ ነው።
👉 ሥነ ጠፈር(Astronomy & Astrology)፡ በርካታ የጠፈር አካላትን በልየታ በመመርመር መረጃዎችን የጻፉ ሲሆን በዋናነት ጊዜን ሚለዩበት ሳይረስ ኮከብ ተጠቃሽ ነው።
ሳይረስ(Sirus) - በውሻ የሚመሰል ኮከብ(The Dog Star) ሲሆን፣ ከአባይ ጎርፍ መምጫ ጊዜ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ይታያል፤ በዚህም ለይተው የአባይን ጎርፍ መምጫ ይተነብዩበት ነበር።
👉 ሕክምና(Medicine)፡ በሕክምናው ሳይንስ ዘርፍ ጥንታዊ ግብጻውያን በርካታ ጽሕፈቶችን ጽፈዋል፤ ከነዚህ ውስጥም:-
ምን ዕፅዋት ለምን በሽታ እንደሚሆን እንደሌሎቹ ጥንታዊ ሕዝቦች ሁሉ መዝግበው ከዘመናቸው ቀድመው ተራቀውባቸዋል። ለዕለት ተዕለት በሽታዎች መድኃኒቶችን ይጠቀሙ ነበር፤ ይህም ጥንታዊ የእጽዋት እውቀትን(Herbalism) ይጠቀሙ እንደነበር ያስረዳናል። ይህንን የሕክምና መዛግብትንም በኋላ ዘመን ላይ ጥንታዊ ግሪካውያንና ሮማውያን እንደተጠቀሙት ታሪክ ይመሰክራል። ሌላ በዚህ ምድብ ውስጥ መድበን ማየት የምንችለው መሚን ነው።
• መሚ(Mummy)፡ ጥንታዊ ግብጻውያን የሞተን ሰው አስክሬን በማድረቅ ሳይበሰብስ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የሚያደርጉበት ነው። በጥንታዊው ሃይማኖት መሚን የሙታን አማልክት የሆነው አኑቢስ(Anubis – god of the dead) እንደፈለሰፈውና ከምድር በኋላ ላለው ሕይወት በር እንደሆነ ይነገራል። በዚህ ሂደት ውስጥ ጥልቅ የሆነ የሰውን ልጅ የአካል ክፍሎች እውቀት ይጠቀሙ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል። ከመሚፊኬሽን በፊት የሚበሰብሱ የሰውነት አካላት(organs) በቀዶ ጥገና ወጥተው በ4ቱ የካኖፒክ¬¬¬¬¬¬ ጃሮች(Canopic Jars) ውስጥ ይቀመጣል። መሚፊኬሽን(Mummification) በአጠቃላይ ከ2-3 ወራትን ይጨርሳል። እያንዳንዱን ሂደት እንይ ብንል ለብቻው ረጅም ቦታን ስለሚይዝብኝ እስከዚህ ከጻፍኩ በቂ ነው።
📌 ውድ የፔካ ቲዩብ ( t.me/EthiopeTowoderos or t.me/PekaTube ) ቤተሰቦቼ ለዛሬው ይህንን ታሪክና እውቀት አጋርቻችኋለሁ፤ ይህ ጽሑፍ የጥንታዊ ግብጽን ታሪክ ለማጥናት እንደጅማሮ መግቢያ ይሆናል ብየ አምናለሁ። ወደ ውስጥ እያንዳንዱን ጉዳዮች ስታጠኑ ግን በጣም ሰፊ ታሪክ፣ እውቀትና ጥበብ እንደምታገኙበት አምናለሁ።
ተጻፈ/Written by፦ Hailemichael D.( @hailemichaeldt )
