cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Advertising posts
464
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝       #መልካም_በአል https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ (ቅዱስ ታዴዎስ በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ ቆይቶ ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራ ከደረሰበት በኋላ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሐምሌ ፪ ቀን ዐርፏል፡፡ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘመንም ሐምሌ ፳፱ ቀን የከበረ ዐፅሙ ከሦርያ ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ ፈልሷል፡፡  የቅዱሱን ዐፅምም ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ በውስጡ ተቀምጦ በዐፅሙም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገልጠዋል፡፡)
Show all...
አባቱ እልፍዮስ ይባላል /ማቴ.፲፥፫/፡፡ ታዴዎስ ልብድዮስና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ እየተባለም ይጠራል /ሉቃ.፮፥፲፮፤ ዮሐ.፲፵፥፳፪፤ ሐዋ.፩፥፲፫፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት አስቀድሞ እንደ መረጠው መጽሐፈ ስንክሳር የሚናገርለት ይህ ሐዋርያ  በየሀገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ብዙዎችን በክርስትና ሃይማኖት አሳምኖ አስጠምቋል፡፡       አንድ ቀን ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሦርያ ለስብከተ ወንጌል ሲሔድ ነበር ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጐልማሳ አምሳል ተገልጦ "ወዳጄ ታዴዎስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ" ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ያረገው።የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ አብሮት ሔዶ ነበረ፡፡ ከከተማዋ አጠገብ ሲደርሱም አንድ ሽማግሌ በሮችን ጠምደው ሲያርሱ አገኙ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ሽማግሌውን ምግብ በለመናቸው ጊዜ በሬዎቼን ጠብቁ ብለዋቸው ምግብ ሊያመጡላቸው ወደ ቤታቸው ሔዱ፡፡ ሽማግሌው እስኪመለሱ ድረስም ቅዱስ ጴጥሮስ በሬዎችን ጠምዶ ሠላሳ ትልም ካረሰ በኋላ ቅዱስ ታዴዎስም በዚያ የነበረውን የሥንዴ ዘር መዝራት ጀመረ፡፡ የተዘራው ዘርም ወዲያዉኑ በቅሎ፣ አድጎ፣ እሸት ኾነ፡፡ሽማግሌው ምግብ ይዘው ከቤታቸው ሲመለሱም ሐዋርያት ያደረጉትን ተአምር አይተው ደነገጡ፡፡ ከእግራቸው ሥር ወድቀው ለሐዋርያት ከሰገዱላቸው በኋላም "እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን?"  አሏቸው፡፡ እነርሱም "እኛ የእግዚአብሔር ባሮች እንጂ አማልክት አይደለንም" አሉ፡፡ ሽማግሌውም "ስላደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ኹሉ ልከተላችሁን?" ባላቸው ጊዜ "ይህንን ልታደርግ አይገባም፤ ነገር ግን በሬዎቹን ለጌታቸው መልስና በቤትህ የምንበላውን ታዘጋጅልን ዘንድ ለባለቤትህ ንገራት፡፡ እኛ ወደዚህች ከተማ ገብተን እግዚአብሔር እስከሚጠራን ጊዜ ድረስ እንቆያለንና" አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም ከሥንዴው እሸት ይዘው፣ በሬዎችን እየነዱ ወደ ከተማ ሲሔዱ የከተማው ሰዎች ወቅቱ የእርሻ እንጂ የእሸት ጊዜ አልነበረምና እየተገረሙ "ይህንን እሸት ከወዴት አገኘኸው?" አሏቸው፡፡ሽማግሌው ግን ምላሽ አልሰጧቸውም ነበር፡፡ሐዋርያት እንደዘዟቸው በሬዎቹን ለጌታቸው መልሰው ቤታቸውን አዘጋጅተው ራት እንድታዘጋጅላቸው ለሚስታቸው ነገሩ፡፡ ወሬውን የከተማው መኳንንት በሰሙ ጊዜም ሽማግሌውን "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት እሸቱን ከወዴት እንዳገኘኸው ንገረን" ብለው መልእክተኞችን ላኩባቸው፡፡ ሽማግሌውም "ሕይወት ከእኔ ጋራ ሳለ ሞትን አልፈራም" ካሉ በኋላ ሐዋርያት ያደረጉትን ኹሉ ነገሯቸው፡፡ መኳንንቱ "ሐዋርያቱን አምጣቸው" ሲሏቸውም ሽማግሌው ወደ እርሳቸው ቤት ሲመጡ ማግኘት እንደሚችሉ ነገሯቸው፡፡ መኳንንቱ ግን ሰይጣን ልቡናቸዉን ስለ ለወጠው ሐዋርያቱን ለመግደል ተነሳሡ፡፡ እኩሌቶቹ ግን "አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ኹሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ልንገድላቸው አንችልም፡፡ ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማው በር ርቃኗን እናስቀምጣት፡፡ እርሷን ሲያዩ ወደ ከተማችን አይገቡም፤" አሉ፡፡ እንደተባባሉትም ሴትዮዋን በከተማው በር ርቃኗን አስቀመጧት፡፡ ሐዋርያው ታዴዎስ ባያት ጊዜም "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ ይህቺን ሴት በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላክልን" ብሎ ጸለየ፡፡ ጌታችን ጸሎቱን ተቀብሎት ሴትዮዋ በተሰቀለች ጊዜም የከተማው ሰዎችና መኳኳንንቱ ኹሉ እያዩአት "አቤቱ ፍረድልኝ" እያለች ትጮኽ ጀመር፡: መኳንንቱ ግን ሰይጣን ልቡናቸውን አጽንቶታልና የሐዋርያትን ትምህርት አልተቀበሉም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ታዴዎስ ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ የሰዎቹን ልቡና የማረኩ መናፍስትን ርኩሳንን አባረረላቸው፡፡ ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀብለው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ሐዋርያው ታዴዎስም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ካጠመቃቸው በኋላ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው፡፡ በአየር ላይ የተሰቀለችውን ሴትም አውርዶ ዲያቆናዪት አደርጎ ሾማት፡፡ በሐዋርያት እጅም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተደረጉ፡፡ ዕውሮች አዩ፤ ሐንካሶች ቆመው ሔዱ፤ ዲዳዎች ተናገሩ፤ ደንቆሮዎች ሰሙ፤ ለምጻሞች ነጹ፤ አጋንንትም ካደሩባቸው ሰዎች እየወጡ ተሰደዱ፤ ሙታንም ተነሡ፡፡ የከተማው ሰዎችም ይህንን ተአምር አይተው በቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ በእግዚአብሔር አመኑ፡፡ አንድ ሰይጣን ያደረበትና ገንዘብ የሚወድ ጐልማሳ ባለጸጋም ወደ ሐዋርያው ታዴዎስ መጥቶ ሰገደለትና "የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው፡፡ ሐዋርያው ታዴዎስም "እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደደው፡፡ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አታመንዝር፡፡ በአንተ ሊደረግብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ፡፡ ደግሞም ገንዘብህን ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ብትሰጥ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ" አለው፡፡ ጐልማሳውም ይህንን በሰማ ጊዜ ተቈጥቶ ሐዋርያውን አነቀው፡፡ የእግዚአብሔር ኀይል በይረዳው ኖሮ ሐዋርያው ከመታነቁ ብዛት የተነሣ ዓይኖቹ ሊወጡ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም "የክርስቶስን አገልጋይ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ?" ባለው ጊዜ ጐልማሳው ቅዱስ ታዴዎስን ለቀቀው፡፡ ያን ጊዜም ቅዱስ ታዴዎስ "ጌታችን ሀብታም መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ሲል በእውነት የተናገረው እንዳንተ ላለው ሀብታም ነው" አለው፡፡ ጐልማሳውም "ይህ ሊኾን አይችልም" ባለ ጊዜ ሐዋርያው ታዴዎስ በመንገድ ሲያልፍ ያገኘውን ባለ ግመል አስቁሞ መርፌ ገዝቶ ሊያሳየው ወደደ፡፡ መርፌ ሻጩም ሐዋርያውን ለመርዳት ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የኾነ መርፌ አመጣለት፡፡ ቅዱስ ታዴዎስም "እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ፤ ነገር ግን በዚህች ሀገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የኾነ መርፌ አምጣልን!" አለው፡፡ ሐዋርያው ቀዳዳው ጠባብ የኾነውን መርፌ ተቀብሎም "ኀይልህን ግለጥ" ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡ እጁንም ዘርግቶ ባለ ግመሉን "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከግመልህ ጋር በመርፌ ቀዳዳው ውስጥ እለፍ" አለው፡፡ ሰውየውም እስከ ግመሉ ድረስ በመርፌ ቀዳዳው አለፈ፡፡ ዳግመኛም "ሕዝቡ የፈጣሪያችንን የክርስቶስን ኀይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ" አለውና ሦስት ጊዜ በመርፌ ቀዳዳው አለፈ፡፡ ሕዝቡም ይህንን ተአምር አይተው "ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡ ያ ጐልማሳ ባለጸጋም ከሐዋርያው ታዴዎስ እግር በታች ወድቆ ሰገደና "ኃጢአቴን ኹሉ ይቅር በለኝ፡፡ ገንዘቤንም ኹሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፋፍልኝ" አለው፡፡ ሐዋርያውም እንደ ለመነው አደረገለት፡፡ የክርስትናን ሃይማኖትን ሕግ አስተምሮም አጠመቀውና ሥጋውንና ደሙን አቀበለው፡፡ ኹሉንም በቀናች የክርስትና ሃይማኖት አጸናቸው፡፡ ከዚያ በኋላም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ታዴዎስ ከዚያች ከተማ ወጡ፤ ሕዝቡም በሰላም ሸኟቸው፡፡ ኹላችንንም የሐዋርያው ጸሎት ይጠብቀን፤ በረከቱም ይደርብን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Photo unavailableShow in Telegram
#አሜሪካ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ፤ በሉዊዚያና ግዛት ከታች አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ባሉ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት እንዲለጥፉ ታዟል። ትላንት ደግሞ የኦክላሆማ ግዛት በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲጀመር አዟል። የግዛቱ ትምህርት ቢሮ በግዛቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው በአስቸኳይ እንዲያካትቱና እንዲያስተምሩ መመሪያ አስትላልፏል። በግዛቱ የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ሪያን ዋልተርስ የተላከ መመሪያ " አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን " የሚፈልግ አስገዳጅ ድንብ ነው ይላል። ዋልተርስ " መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ነው "  ብለዋል። " ያለ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ እውቀት የኦክላሆማ ተማሪዎች የአገራችንን መሠረት በትክክል መረዳት አይችሉም " በማለት ነው በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲሰጥ መታዘዙን ያመለከቱት። በግዛቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ይተገበራል። ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ እያንዳንዱ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረው ይገባል ተብሏል። ሁሉም አስተማሪዎች በክፍሉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማስተማር እንዳለባቸው ታዟል። የሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን ይህንን ውሳኔ ተቃውመዋል። ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ብለዋል። አንድ መንግሥትን ከሃይማኖት መለያየት እንዳለበት የሚሰራ ተቋም ፥ " የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች አይደሉም " ብሏል። " ሪያን ዋልተርስ የተሰጠውን የመንግሥት ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ሃይማኖታዊ እምነቱን በሌሎች ላይ ለመጫን እየተጠቀመበት ነው። ይህ እኛ ባለንበት ሊሳካ አይገባም " ብሏል ተቋሙ። በአሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ለማስጠበቅ የሚሰራው ኢንተርፌይዝ አሊያንስ ፤ " መመሪያው ግልጽ በሆነ መልኩ ሃይማኖትን መጫን ነው " ሲል ገልጾታል። " እውነተኛ የእምነት ነፃነት ማለት የትኛውም የሃይማኖት ቡድን አመለካከቱን በሁሉም አሜሪካውያን ላይ እንዳይጭን መከላከል ነው " ብሏል። #BBC #CNN @tikvahethiopia
Show all...
ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ፫ ምሥጢረ ሥላሴን የሚያስረዱ ተፈጥሮአዊ ምሳሌዎች መስማትም በሚችሉበት መጠን እንዲህ ባለ ብዙ ምሳሌ ቃሉን ነገራቸው ያለ ምሳሌ አልነገራቸው ማርቆስ 4:33-34 ሊቃውንት አባቶቻችን በምሳሌ ሲያስተምሩን ምሳሌ ተመሳዩን አክሎ ሳይሆን ለኛ የመረዳት አቅም እንዲሆን አርገው መሆኑን መገንዘብ አለብን ፀሐይ ፀሐይ በክበቧ በአብ በብርሃኗ በወልድ በሙቀቷም በመንፈስ ቅዱስ ትመሰላለች፡፡ ለፀሐይ ብርሃንና ሙቀት መገኛቸው ክበብ ነች፡፡ ይሁን እንጂ በክበብ በብርሃንና በሙቀት መካከል መቀዳደምና መከፈልም የለባቸውም ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስም መገኛቸው አብ ሲሆን ለመገኘታቸው ቅደም ተከተልና መከፈል የላቸውም፡፡ ምሳሌው ግን ምሳሌ ዘየሐፅፅ ነው፡፡ ምክንያቱም ፀሐይ ለመገኘቷ ጥንት ያለው ሲሆን ለሥላሴ ዘመን አይቆጠርላቸውምና፡ እሳት እግዚአብሔር በእሳት ይመሰላል፡፡ “አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነው" እንዲል ዘዳ 4÷24። ሊቃውንቱ ይህን መነሻ አድርገው ለትምህርተ ሥላሴ አስረጂ ምሳሌነት የእሳት ተፈጥሮን ይጠቅሳሉ፡፡ የእሳት አካሉ አንድ ሲሆን ሦስት ነገሮች አሉትና፡፡ ይኸውም ነበልባል፣ ብርሃን እና ሙቀት ናቸው፡፡ እሳት በነበልባሉ በአብ፣ በብርሃኑ በወልድ በሙቀቱ/በዋዕዩ/ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡ እሳት እነዚህ ሦስት ኩነታት ቢኖሩትም አንድ እሳት እንጂ ሦስት አይባልም፡፡ ሥላሴም በአካል በግብር በስምና በኩነት ሦስት ቢባሉም አንድ እግዚአብሔር እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡ የሰው ነፍስ የሰው ነፍስ በአካል አንዲት ስትሆን ሦስት ግብራት ደግሞ አላት፡፡ ይኸውም ልባዊነት፣ ነባቢነት እና ሕያውነት ናቸው፡፡ ሥላሴም በባሕርይ በፈቃድ በሥልጣን እና ይህን በመሰለ ሁሉ አንድ ሲሆኑ በአካል በስም በግብር እና በኩነት ሦስት ይባላሉ። የሰው ነፍስ በልባውነቷ በአብ፤ በነባቢነቷ /በቃልነቷ/ በወልድ በሕያውነቷ ደግሞ በመንፈስ ሲሆኑ በአካል በግብር በስም እና በኩነት ሦስት ይባላሉ፡፡ የሰው ነፍስ ቅዱስ ትመሰላለች፡፡ የሰው ነፍስ ለባዊት፣ ነባቢት እና ሕያዊት ናት ስትባል በሰው ነፍስ ሦስትነት መኖሩን ያስገነዝባል፡፡ ሆኖም አንዲት ነፍስ /አንድ ሰው/ ቢባል እንጂ ሦስት ነፍሳት/ ሦስት ሰው አይባልም፡፡ ሥላሴም በአብ ልብነት ያስባሉ /ያውቃሉ/ በወልድ ባሕር "የሁሉ መገኛ አብን ነፋስ በሚያማታት ባሕር ባለች በውሃ እንደ መሰሉት እወቅ፤ በሁሉ ዘንድ የሚመሰገን ወልድንም በውሃ እርጥበት እንደመሰሉት፤ በሁሉ ዘንድ የሚመሰገን መንፈስ ቅዱስንም፣ በባሕር ባለ በውሃ ሁከት ይመሰላል (ይመስላል):: የባሕርን ኃይልከጠባዩ መለየት ለማን ይቻለዋል? ባሕር ያለ እርጥበትና ያለ መታወክሊኖር ይቻላልን? ሁከትን ከእርጥበትና ከስፋት ለይቶ ለብቻዋ ማቆምለማን ይቻለዋል? ስፋትንና እርጥበትንስ ከሁከት ለይቶ ለብቻቸው ማቆም ለማን ይቻለዋል? ከእነዚህስ አንዱን ብቻውን ቁሞ ያየው ማንነው? በሦስትነቱ ነው እንጂ:: ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸውና፣ ሦስትሲሆኑም አንድ ይባላሉና፣ ሦስት ኲነታት እንዳለ ቢታይ ቢታሰብም፣ ስፍሐት ኃይሉን የሚገልጥባቸው እርጥበትና ሁከትም ከስፍሐት አይለዩም:: ስፍሐትም ከርጥበቱና ከሁከቱ:: ስለተመሰገኑ ጠባያትምእንዲሁ እናገራለሁ” ብሏል:: / ከ ፍኖተ እግዚአብሔር ከ ነገረ ሃይማኖት ከ እውነተኛ ክርስትና መጽሐፍ የተወሰደ
Show all...
ርግብ ማነው? ታሪኩ የኖኅ ታሪክ ነው። በታሪክ ታላቁ የሰው ልጅ ጥፋት የነበረበት። ሙሴ ይኽንን የጥፋት ውኃ ታሪክ በዝርዝር ነው ያሰፈረው።  የጥፋት ውኃው በመቶ ሃምሳኛው ቀን መጉደል ጀመረ። ከአሥር ወር በኋላ ተራሮች ሲገለጡ በአርባኛው ቀን ኖኅ መስኮቱን ከፍቶ ቁራውን ላከው “ቁራንም ሰደደው፤ እርሱም ወጣ፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።” ዘፍ.8:7 ቁራው ውኃው ጥቂት በመጉደሉ የሞተ የሰውና የእንስሳት ስጋ በውኃው ላይ ተንሳፎ በማግኘቱ ምግቡን አግኝቶ በደስታ መመገብ በመጀመሩ ወደ ኖኅ የሚያስመልሰው ነገር አልታየውም። የአካባቢው ጠረን ለቁራው ከመርከቢቱ ይልቅ የሚስብ የሚስማማ ነበር።  ኖኅ ቁራው በመዘግየቱ ዳግመኛ ርግብን ላካት  “ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት።” ዘፍ.8:8 ርግቧ ግን መቆሚያ ማሪፊያ ማግኘት አልቻለችም። “ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አላገኘችም፥ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች፥ ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ፤ እጁን ዘረጋና ተቀበላት፥ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት።” ዘፍ.8:9  ርግብን ኹለት ጊዜ በመላክ ለምለም ቅጠል ይዛም በመምጣት ለኖኅ የጥፋቱ ውኃ መቅለሉን አረጋግጣለች። “ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች፤ በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ።” ዘፍ.8:10 ኖኅ የላከው ቁራ የሰይጣን ምሳሌ ነው። የሞተ ሕይወት የሌለውን ጠረኑ የከረፋውን የሚወድ ነው። ሰይጣን ሰዎችን ሲያያቸው ይኽንን ጠረን ያሸታል ሰዎች ከኃጢአት ጋር ተላምደው ካየ አይለያቸውም እየተከታተለ ኃጢአት ይጨምሩ ያበዙ ዘንድ ንሰሐ እንዳይገቡም እያከበደ ወደ ሞት ይመራል። ሰው ኃጢአት ሲሰራ በኃጡአቱ ሲሞት ይደሰታል።  ርግብ መንፈስ ቅዱስ ነው። መጥፎ ሽታ አይስማማውም መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን ይቃወማል። መንፈስ ቅዱስን በሰዎች ሕይወት ውስጥ ክርስቶስን እንዲሸቱ ይፈልጋል።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን ✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝       #መልካም_ጾም https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture
Show all...
ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ፪ ( በሦስት የተገመደ ገመድ አይበጠስም ) መክብብ 4:12          ሦስቱ ኩነታት በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በአንድ መለኮት ሦስት ኩነታት(መሆኖች) አሉ:: እነዚህም ከዊነ ልብ /ልብ መሆን/፣ ከዊነ ቃል /ቃል መሆን/፣ ከዊነ እስትንፋስ /እስትንፋስ መሆን/ ናቸው፡፡ አብ ለራሱ ልብ ሆኖ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው፣ ወልድም ለራሱ ቃል ሆኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው፣ መንፈስ ቅዱስም ለራሱ እስትንፋስ /ሕይወት/ ሆኖ ለአብና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው፡፡ ስለዚህ ሥላሴ በአብ ልብነት ያስባሉ፤ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ እንጂ ሦስቱ አካላት ለየራሳቸው ልብ፣ ለየራሳቸው ቃል፣ ለየራሳቸው እስትንፋስ የላቸውም ማለት ነው፡፡ ኩነታት መከፈልና መለየት ሳይገባቸው በተዋሕዶ፣ በአንድነት አካላትን በህልውናና በአኗናር እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ ያሉና የሚኖሩ ናቸው፡፡ የኩነት ሦስትነት ከሌሎች ሶስትነት የተለየ ነው ማለትም የአብ ልብነት ለአብ ብቻ ሳይኾን ለወልድም ለመንፈስ ቅዱስ ነው የወልድም የመንፈስ ቅዱስም እንደዛው          አንድነት ሥላሴ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም በመለኮት፣ በአገዛዝ፣ በባሕርይ አንድ ናቸው፡፡ መለኮት በአካል ልዩ ሳይሆን በቅድስት ሥላሴ አንድ መለኮት በሦስት አካላት ህልው ነው፡፡ "በዕውቀት ማነስ የተሳሳቱ ስዎች ልዩ በሆነች ሦስትነት /ቅድስት ሥላሴ/ የመለኮትን ልዩነት የአካላትን አንድነት አግብተው ይናገሩ ዘንድ አይድፈሩ ለአንድ አምላክ እንሰግዳለን እንጂ ለሦስት አማልክት አንሰግድምና:: አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ብለን በሦስት ስም እንጠራቸዋለን፡፡ እኒህም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በአንድ መለኮትና /ሕይወት/ በአንድ ህልውና አንድነት የተገናዘቡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ባሕርይና ኃይል ናቸው (ሃ.አበው ፬፡፳፪)። በአጠቃላይ ቅድስት ሥላሴ በፈቃድ፣ በምክር፣ በመፍ ጠር፣ በአምላክነት፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን ፣ በአገዛዝ፣ ቀድሞ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ በመፍጠር፣ ኋላም ይህን ዓለም ከመኖር ወደ አለመኖር በማሳለፍ፣ መዓልትና ሌሊቱን በማመላለስ፣ ክረምትና በጋውን በማፈራረቅ፣ ኃያሉን ድኩም ድኩሙን ኃያል፣ ባለጤናውን ድውይ ድውዩን ባለጤና፣ ድኃውን ባለጸጋ ባለጸጋውን ደኃ በማድረግ አንድ ናቸው:: "አሐቲ ልቡና፣ አሐቲ ቃል፣ አሐቲ እስትንፋስ፣ አሐቲ መንግሥት፣ አሐቲ ሥልጣን፣ አሐቲ ክብር፣ ወአሐቲ ምኵናን = አንድ ልብ፣ አንድ ቃል፣ አንድ ሕይወት፣ አንድ ስልጣን፣ አንድ ክብር፣ አንድ አገዛዝ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም:: ስለዚህ መጠቅለል('ጠ" ጠብቆ ይነበብ)፣ መቀላቀል የሌለባቸው ሦስት አካላት በሕልውና እየተገናዘቡ በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ በመንግሥት፣ በአምላክነትና በጌትነት በአንድነት ፀንተው ይኖራሉ፡፡ በመሆኑም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ብለን እናምናለን፡፡ ይቀጥላል ከነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ የተወሰደ ከትላንት በሰጣቹን ሃሳብ የዛሬውን ለማሳጠር ሞክሬያለው እግዚአብሔር በፈቀደ መልኩ ነገም በዚ ርዕስ የምንቀጥል ይሆናል ✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝       #መልካም_ጾም https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture https://t.me/OrtoPicture
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.