cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ-ህይወት ሰ/ት/ቤት ዘደ/ቅ/ቅ/ገ ዶዶላ

✥✥✥✥✥✥ የጌታች የአምላካችን የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ !!!! ይህ የደደላ ደ/ቅ/ቅ/ ገብረ-ክርስቶስ ፈለገ-ህይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ቻናል ነው እናም ለመንፈሳዊ እውቀቶና ህይወቶ ትምህርት ለማግኘት ይቀላቀሉን✥✥✥✥ @felgehiwot @felgehiwot @felgehiwot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
203
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከላይ ☝️☝️☝️ የቀጠለ። ጥብቅ መልእክት ለኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ። "…ሁለቱንም የድምጽ መልእክቶቼን ስሟቸውና ምላሻችሁን በጽሑፍ ትሰጡኝ ዘንድ በጉጉት እጠብቃለሁ። "ስልክ ተደውሎ የተቆረጠውን የመጀመሪያውን መልእክቴን በሁለተኛው መልእክቴ ላይ ታገኙታላችሁ። አደራ ምላሻችሁን እጠብቃለሁ። ይሄ የመጨረሻ መልእክቴ ነው የሚሆነው። ተሰብስባችሁ ስሙት። አድምጡት፣ ተወያዩበትና ምላሽ ስጡኝ። አመሰግናለሁ።
Show all...
ጥብቅ መልእክት ለኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ። "…ሁለቱንም የድምጽ መልእክቶቼን ስሟቸውና ምላሻችሁን በጽሑፍ ትሰጡኝ ዘንድ በጉጉት እጠብቃለሁ። "ስልክ ተደውሎ የተቆረጠውን የመጀመሪያውን መልእክቴን በሁለተኛው መልእክቴ ላይ ታገኙታላችሁ። አደራ ምላሻችሁን እጠብቃለሁ። ይሄ የመጨረሻ መልእክቴ ነው የሚሆነው። ተሰብስባችሁ ስሙት። አድምጡት፣ ተወያዩበትና ምላሽ ስጡኝ። አመሰግናለሁ። 👇👇👇
Show all...
የ 🔟 ደቂቃ መልእክት ናት ስሟትና ሃሳብ ለመስጠት ተዘጋጁ። ፅንፈኛ የወሃቢ እስላም ነኝ ባይ ክፍት አፎች ወደ ፔጄ መታችሁ እንድትጸዳዱ የማልፈቅድ መሆኔን በጥብቅ አሳስባለሁ።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንዴ ፥ ይደክመኛል ተስፋ እቆርጣለሁ ፥ የሕይወት ትርጉም ይጠፋኛል ፡፡ ሕይወቴ ከደስታ ይልቅ በሀዘን ፣ ከብሩህ ተስፋ ይልቅ በፍርሃት ይሞላል ፡፡ ግን ግን ሁል ጊዜ መጓዜን አላቆምም ፡፡ ነገ በሕይቴ የበለጠ መከራ ወይንም ትልቅ ደስታ ቢመጣም መጓዜን አላቆምም ፡፡ በዚህች ምድር ሁለት ሕይወት የለም ፡፡ አንዴ ኑሬ ላልመለስ እሄዳለሁ ግን ግን በሕይወቴ ሁሉ የምጥረው ነገር ቢኖር ሌላ ሰውን ላለማሳዘን ፣ ላለማስከፋት በኔ ምክንያት ሕይወትን እንዳይጠላ ለማረግ ነው ፡፡ ወዳጆቼ ቆም ብለን እናስብ ! ለማይደግሞ ሕይወት ወደኀላ አንመልከት በቀና አስተሳሰብና ማንነት እንኑር እንጓዝ ፡፡ አንድ ቀን እኛም ታሪክ እንሆናለን @Loveerdey @Loveerdey @Loveerdey
Show all...
ለተጨማሪ ግንዛቤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያስተላለፍናቸውን መልእክቶች እንዲመለከቱ ሊንኮቹን እንደሚከተለው አያይዘናል👇👇👇 https://t.me/c/1172495782/38368 https://t.me/c/1172495782/38183 https://t.me/c/1172495782/38033
Show all...
👉🏾👉🏾👉🏾 ለምን ርቀህ ቆምክ? ስለ #ንስሐ እና ስለ #ቅዱስ #ቁርባን የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ  የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ አንደተጠቀሰው 'ለምን ርቀህ ቆምክ?"' ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ንስሐ እና ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚመለከተውን ጠቃሚ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን። 1. ንስሐ ንስሐ ማለት መጸጸት፤ መቆርቆር፣ ኃጢአትን ስለሠሩ ማዘን፤ ማልቀስ፣ መቆጨት ነው፡። የበጎ ሥራ ጠላት ዲያብሎስ የሰው ልጅ መንግሥተ ሰማያትን እንዳይወርስ ክፉ መርዙን እየረጨ ከንስሐ መንገድ ያርቀናል፡፡ ኃጢአትን በኃጢአት ላይ ደርቦ ደራርቦ ያሠራህና ራስህን እንደ ሰው መቁጠር እስኪያቅትህ ድረስ ያስጨንቅሃል። ንስሐ ለመግባት ስትፈልግ "ይህን ያህል ኃጢአት በሙሉ እንዴት ነው ለንስሐ አባትህ የምትነግራቸው? የሚያሳፍር ኃጢአትም ሰርተሃል። ስለዚህ አሁን ተወውና ስታረጅ አንድ ጊዜ ትገላገላለህ።" ይልሃል፡፡ የዕድሜ ዘመንህንም ረዘም አድርጎ ያሳይሃል፡፡ አንተም ትታለላለህ «ኃጢአተረን በሙሉ አንድ ጊዜ ልገላገለው» እያልህ ኃጢአትን ማጠራቀም ትጀምራለህ፡፡ እግዚአብሔር በሞት የሚጠራህ መቼ እንደኾነ ግን ታውቃለህ? በፍጽም አታውቅም፡ ጠላት ግን ሺህ ዘመን የምትኖር አስመስሎ ያሳይሃል፡፡ ጠላት አሁንም ይቀርብና «የሰራኸው ኃጢአት በጣም ከባድ ነው። ለንስሐ አባትህ ከነገርካቸወሰ በኋላ ለሌላ ሰው ቢነግሩብህሳ» ይልሃል፡ አንተ ግን አትስማው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ለንስሐ አባቴም ተሰጥቷቸዋል በለው። /ማቴ 17:19/ ዲያብሎስ ግን አሁንም ሌላ ወሬ ይጀምራል።፡ «ንስሐ አባት ምናምን እያልክ ለምን ጊዜ ትፈጃለህ ዝም ብለህ ወደ አምላክህ ቀርበህ ይቅር በለኝ ብትለው ይቅር ይልህ የለምን?» ይልሃል፡፡ አንተ ግን ምክሩን አትቀበል በኃጢአት ማሰሪያ እንደታሰርኽ ወደ ክርስቶስ ብትቀርብ «ራስህን ለካህን አሳይ» ይልሃል እንጂ አይቀበልህም፡፡ «ክርስቶስ ወደ አንዲት መንደር ሲገባ በሩቁ የቆሙ አስር ለምጻሞች ተገናኙት እነሱም እየጮሁ ኢየሱስ ሆይ ማረን አሉ።አይቶም ሂዱ ራሳችሁን ለካህን አሳዩ አላቸው።" ይላል። /ሉቃ 17፥12-14/ ላይ። ስለዚህ የንስሐ አባት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ ልትረዳ ያስፈልጋል። ንስሐ ሳትገባ መንግሥተ ሰማያት መግባት አትችልም፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ «መንግስቸ ሰማያት ቀረሸባለችና ንስሐ ግቡ » አያለ ይሰብክ የነበረው ለዚህ ነው፡ /ማቴ3 ፥1-2/ በንስሐ መመለስ ኃጢአትን ኹሉ እንዳይታስብ (እንዲሠረይ) ግዱፍ እንዲኾን ያደርጋል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል «ሕመምተኞን እንጂ ባለጤናዎች ባለመድኃኒት አያስፈልጋቸውም ነገር ግን ሄዳችሁ ምህረትን እወዳለሁ መስዋእትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ተማሩ። ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጀመ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና»። (ማቴ 9፥12-13) ይላል፡፡ ስለዚህ ንስሐ መግባት ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር የወረደ ኃጥአንን በንስሐ ለመጥራት እንጂ ለጻድቃን አይደለምና፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰ ለአብርሃም፤ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አይደለም ኃጢአትን ላደረጉ ኃጥአን ነው እንጂ፡፡ ንስሐ ኃጢአተኛን ንጹሕና ጻድቅ የሚያደርግ ልዩ ምስጢር ነው: «በደላቸውን እምራቸዋለሁና ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና» ተብሎ አንደተጻፈ /ኤር 31፥34/ ላይ፡፡ ጠላት ያንተን ይቅር መባል አይወድምና ከዚህ ምስጢር እንድትርቅለት በርካታ መሰናክሎችን ያስቀምጥብሃሃል። ኃጢአት ስትሠራ እንደ ማር ይጣፍጥሃል። በኃጢአት ላይ ኃጢአት በበደል ላይ በደል ትደራርባለህ፡፡ የኃጢአት ካባ ሙቀት ይኾንሃል፤ የጽድቅ ሥራ ይቀዘቅዝሃል፡፡ ከዚህም የተነሣ ኃጢአት ባሪያው ያደርግሃል አንተም አገልጋዩ ትኾንለታለህ።፡ የታሰርክበትን ሰንሰለት ለመፍታት ስታስብ እንቅልፍህ ይመጣል፡። ዕድሜህ አንደ ዋዛ በከንቱ ትሮጣለች።: አንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች የአግዚአብሔር ቁጣ ሳታስበው መጥቶ ንፍር ውኃ ቢዘንብብህ የት ትገባለህ? /ዘፍ6 እና ዘፍ 7 ሙሉውን ተመልከት/ የሞትህ ቀን መቼ አንደኾነ አታውቅምና ንስሐ ገብተህ ተዘጋጅተህ መኖር ተገቢ ነው፡፡ ሙሸራው ሲመጣ ዘይት ፍለጋ ልትሄድ አይገባም ዘይትህን ከመብራት ጋር ይዘህ መጠበቅ ነው አእንጂ፡፡ /ማቴ 25፥1--ፍጻ ተመልክት/ የጠላትን መሰክር አትቀበል ምክንያቱም እርሱ ጥሩ ምክር አይመክርህምና። እናታችን ሔዋን የጠላትን ምክር በመቀበሏ ስትጎዳ እንጂ ስትጠቀም አላየናትም።፡ ስለዚህ ለጠላት ጆሮ ሰጥተህ አትስማው: ንስሐ አትግባ እያለ የሚያስጨንቅህ ወደ ዘላለም ቅጣት ሊጥልህ እንጂ የዘላለም ሕይወትን እንድታገኝ አይደለም። የቀደመው እባብ ጠላት ዲያብሎስ አሁንም ንስሐ አይጠቅምም እያለ የሚጨቀጭቅህ ከኾነ የጥጦስን (የፈያታዊ ዘየማንን) ታሪክ ዘርዝረህ ንገረው፡፡ ጥጦስ ቀማኛ፣ ሽፍታ እና ወንበዴ ነበር፡። በዕለተ ዓርብ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ በኩል ተሰቀለ፡፡ ሰባቱን ተአምራት በዓይኑ ተመሰከተ። በመስቀል ላይ ያለበደሉ የተሰቀለው ክርስቶስ አምላክ እንደኾነም አመነና «ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ገመዜ አስበኝ» የሚል ታላቅ ልመናን ለመነ፡። ኢየሱስ ክርስቶስም በንስሐ ተቀበለውና «እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኾናለህ።» አለው፡፡ ይህ ወንበዴም አዳምን ቀድሞ በክርስቶስ ደመ ማኅተም ፶፭፻ ዘመናት ያህል ተዘግታ የነበረችን ገነት ከፍቶ ገባ። /ሉቃ 23፥39-43) ፤ ሕማማተ መስቀልን ተመልከት/ ስለዚህ ንስሐ ቆሻሻን ኹሉ እንዲህ የሚያጠራ ሳሙና ነውና አታጠብበታለሁ እንጂ አልርቀውም አልሸሸውም በለው፡፡ የኅሊናን ሸክም የሚያራግፍ ኃጢአትን ኹሉ የሚደመስስ ልዩ መድኃኒት ነውና በየሰዓቱ ውሰደው ንስሐን፡፡ 2. ሥጋ ወደም (ይቀጥላል) ለተጨማሪ ግንዛቤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያስተላለፍናቸውን መልእክቶች እንዲመለከቱ ሊንኮቹን እንደሚከተለው አያይዘናል👇👇👇 https://t.me/c/1172495782/34692 ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
Show all...
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/ "" አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። "" (መዝ. ፺:፲፫) "ዝክረ ቅዱሳን ዳዊት ወዳንኤል (ዘወርኃ መጋቢት)" (መጋቢት 23 - 2014) ✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር። " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
አዎ እህታለሜ ምን ትያለሽ አሁን...? በሃይማኖት ኖረን ባድላይ ሁላችን፣ ሰማያዊ ዋጋ ከላይ እዲኖረን። የጨለማው ዘመን ከእኛ ላይ እዲርቅ፣ በንስሃ እንባ ካምላክ እንታረቅ፣ አስበንም ባይሆን ወይም ሳናስበው፣ ክፋትን አድርገናል ይህ የማይካድ ነው፣ ስለዚህ እህቴ ሁላችን አንድ ነን፣ ቃሉን እያወቅን የምናጠፋው እኛ እንብሳለን፣ በእኛ ስራ አይደለም እስካሁንም ያለን፣ በእርሱ ቸርነት ነው ፍቅሩን ስለሰጠን፣ አሁን አስቢበት ሳትጨናነቂ፣ ይሻላል መመለስ እውነቱን እወቂ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ! የኪነጥበብ ተከታታዮች ወቅቱም የዓብይ ጾም ስለሆነ ይኽ ድንቅ የንስሐ መንፈሳዊ መነባንብ ነውና በታላቅ የሰንበት ት/ቤት መርሃግብሮች ላይ ተጠቀሙበት ልዩ ተሰጥኦ ያላችሁ ! ! የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
Show all...
++ ኪነጥበብ - መነባንብ ! ( ርዕስ - ለምን ትፆማለህ? /ለምን ትፆሚያለሽ? ) በል ወድሜ መልስ ለምን ትፆማለህ? ፆምን በመፆህ ምንስ ታገኛለህ? የመፆምስ ሚስጥር ምድነው ትላለህ? ንገረኝ ወድሜ ሚስጥሩን ካወቅህ ፆምን የምፆመው ከምን ከምድን ነው? እንጀራና ውሃ ብቻ ነው? ወይስ ስዓት ይዞ ጊዜን መገደብ ነው? በተወሰነ ወቅት ጠብቆ መብላት ነው? እባክህ አስረዳኝ ፆም ማለት ምድን ነው?። እሽ እህታለም እመልሳለሁኝ... አንቺም ነይ ቁጭ ብለሽ ከልብሽ አድምጭኝ፣ ጥያቄ እንኳ ካለሽ እድትጠይቂኝ፣ በጥሞና ሆነሽ በይ ተከታተይኝ። እኔ የምፆመው ይህን የአዋጁን ፆም፣ ዝምም ብዬ በግምት ለይምስል አይደለም፣ ለምዕመኑ ሁሉ ስለምታውጅ ነው ቤተክርስቲያንም፣ ከቤተክርስቲያን አዋጁን ስታወጅ ክርስቲያኑ ሁሉ እየፀና ከደጅ፣ መፆም ይገባዋል ዘመኑን እዲዋጅ። ሰው ውቶ እዲገባ ሰላም ፍቅር በዝቶ፣ መፆም ያስፈልጋል በትጋት በርትቶ፣ ስጋችን ሲደክም ነፍስ ትታደሳለች፣ ስጋችን ሲገራ ነፍስ ታይላለች፣ በፀሎት በእባ ነፍስ ታብባለች በቁራሽ እንጀራ ቦታን ትገዛለች፣ በምፅዕዋት ዋጋ ቤቷን ትሰራለች። ፆም የሚሏት ነገር የነፍስ መዳኒት ናት... አየሽ እታለም ሰዎች ካወቁባት፣ የቆሰለን ፈዋሽ አዳኝ ናት በእውነት፣ ሚስጥሩን ተረድቶ በእውነት ለሚፆማት፣ በፀሎት በእንባ እድሁም በመፅዕዋት፣ ክፈን ከመስማት እዲሁም ከማየት፣ የሰዎች ገንዘብ ሳይነኩ በሐሰት፣ ወደ መጥፎ ቦታ ሳይሄዱ በምኞት፣ በመቆጠብ ሆኖ ባሉበት በመፅናት፣ መፆም አለው ዋጋ ይኽነው የማይሉት። አዋጅ ፆም ታዉጆ ሰው በፍቅር ሲጾም፣ ትንሽ ትልቅ ሳይል ድሃና ሃብታምም፣ ሁሉም በኩልነት አምላኩን ሲለምን፣ ያለውም ለሌለው ሲያካፍል የኪሱን፣ አንዱ ላንዱ ሲያዝን ያለውን በመስጠት፣ እግዚአብሔር ይሰማል የህዝቦቹን ጩኸት። ኑ ልጆቼ እያለ እጁን ይዘረጋል፣ ዘመኑን በደስታ ፍስሐን ይሞላል፣ ክፉውን መከራ በደስታ ይተካል። እኛ ስንመለስ ከክፉ ስራችን፣ አምላክ ይመለሳል ቸሩ ፈጣሪያችን። ኑ ተመለሱ እያለ ሁልዬ የሚጠራን፣ ስለሚራራ ነው በምክኒያት ሊያድነን። አየሽ እህታለም ፆም ብቻውን አይመጣም፣ ፀሎትና ስግደት ይጨምራል ለቅሶም፣ መፀፀት መተከዝ አለበት መስጠትም። ጾም መጾም ያለበት ዝምም ተብሎ አይደለም። ምፅእዋት የሌለው ቢዘረጋ ባዶ እጅ፣ ዋጋ ሳይቀበል ይመለሳል ከደጅ፣ በጸሎት በስግደት ካጀብናት ነውጅ፣ ጾም ዋጋ እሚኖራት ከፈጣሪ ደጅ፣ እህልን ብቻ መተው አያስብልን ልጅ። ልጆቼ ተብለን ክብር የሚሰጠን፣ መጾም ስንችል ነው ሁሉንም አሟልተን ። በይ እህታለሜ አሁስ ገብቶሻል? ለምን እደምንፆም ግልፅ ሆኖልሻል? ወይስ አልገባሽም ያልኩሽ ነገር ሁሉ? በይ ንገሪኝ እስኪ ላዳምጥሽ በውሉ። በእውነት ወድማለን ፀጋውን ይብዛልህ... ምን እደምን አላውቅም እውነቱን ስነግርህ። እኔ ምንም አላውቅ ፆም ስለሚሉት ነገር፣ በጧት ተነስቼ ጥሩ ቁርስ መብላት ነው ደስ የሚለኝ ነገር፣ መልበስ መዘነጥ ነው አምሬ መታየት፣ የምንስ ምፅዋት ነው ያለን ለሰው መስጠት፣? ጭራሽንም ስግደት ጎንበስ ቀና ማለት፣ አስቤውም አላውቅ እኔ ካለሁበት። ደግሞስ ቆይ ልጹም ብል ማንስ ይሰማኛል፣? ያለሁት ከሰው ቤት ካህዛብ መካከል። ምግባችን ባአንድላይ የምበላው ሰርተን፣ እንዴት አድርጌ ነው የምፆመው ጾሙን፣? እንዴትስ ብዬ ነው መስገድ የምችለው?፣ እኔ የለመድኩት መዝፈን መደነስ ነው፣ አንተ የምትለኝ ጭራሽ አይቻልም የማይሆን ነገር ነው። ቆይ እህታለሜ እኔንም አዳምጭኝ... ትንሽ ተረጋግተሽ እኔንም አድምጭኝ። ይኸ የምትይው ነገር ሁሉም ይገባኛል ከሰው ቤት መሆንሽ አውቃለሁ ይከብዳል፣ ግን ደግሞ ካሰብሽበት መመለስ ይቻላል። ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም ግልፅ ነው፣ በእግዚአብሔር ቸርነት በቃሉም ጭምር ነው፣ ሰው ሲበላ ሲጠጣ ሲጨፍር ቢኖርም፣ የሞት እዳ አለበት ዘላለም አይኖርም፣ ዛሬን ሳንዘጋጅ ብልን እንኳን ችላ፣ ምክኒያት እያበዛን ብንል ወደ ኃላ፣ ምንም አይጠቅመንንም የምድር ተድላ። ነፍሳችን ተርባ መቆም ሲኪያቅታት፣ በብርድ ስትጠበስ አይናችን እያያት፣ ኀፍረት ተከናንባ ከፈጣሪዋ ፊት፣ ምን ይጠቅም ብለሽ ለዛሬ መደሰት፣ ምኪኒያት መደርደር አይቻል ካም ላክ ፊት፣ ዛሬን ካልተመለስን ምክኒያታችን ትተን፣ መከራው ብዙ ነው በሞት ከተወሰድን፣ ስለዚህ እህቴ ባይሆን በምትችይውን፣ መመለስ ሞክሪ ተይ እና ምክኒያትሽን፣ ለማይጠቅም ነገር አትስጭ ጊዜሽን፣ ይብቃሽ መጨፈሩ በዘፈን መዝናናት፣ ወቅቱ የለቅሶ ነው በደንብ አስቢበት። *እሽ በቃ ተውት ጥፋቱ የእኔ ነው፣* ሳቀብጠኝ ጠይቄ በጭንቀት ልሞት ነው፣ ምነው ቢቀርብኝ ጥያቄ ባልጠይቅ፣ እራሴን ከማዞር ልቤንም ከማደርቅ አፌን በቆረጠው ጥያቄ ስጠይቅ። ምነው እህታለም ከዚህ ሁሉ ጣጣ አርፌ ብቀመጥ ይሻለኝ ነበረ ዝምም እዳልኩ መቀመጥ፣ ዝና ብትን እያልኩ ምንም ሳልሳቀቅ፣ መኖር ነበር ጥሩ ጥያቄን ሳልጠይቅ። አሁን በእኔው ጥፋት ችግር አመጣሁኝ፣ መንፈሴ ታወከ እኔም ተጨነኩኝ፣ የምትሉኝ ሁሉ እንግዳ ሆነብኝ፣ ጭራሽ የሞት እዳ ተሸክሜያለሁኝ። ሳልሞት የማልከፍለው መሆኑን አውቃለሁ፣ ግን ደህሞ እድዚህ ምንም አላስብሁ፣ አሁን ምን ላረግ ነው? እንዴት ልሆን ነው?፣ በወሬ የማውቀውን ጾም እኔም ልፆም ነው፣? ወይስ ዝም ብዬ እዳ ልሸከም ነው?። ጭራሽ ግራ ገባኝ በጣም ተጨኑኩኝ፣ መንፈሴ ታወከ የምሞት መሰለኝ። የስከዛሬው ሰላም እንዴት እንደከዳኝ፣ ወኔዬ ሲጠፋ ለእራሴም ገረመኝ፣ እንዴት እደማረግ አሁንም አውቃለሁ፣ በሙሉ ሰላም ዋሉ ዳግም ላልመለስ ከእናተ ሄጃለሁ፣ ሰላሜን ፍለጋ ትንሽ እጠጣለሁ። ምነው ምነው እታለሜ ጥያቄ ጠየቅሽ...? የምን ትጾማለህ ለምን ትጾሚያለሽ፣ ብለሽ የጠየቅሽው እርስዎ እኮ ነሽ ታዳ ምን አጠፋን ለምን እደምንፆም ነው እኛ የነገርንሽ፣ ታዳ ምን አጥፍተን መንፈስሽን አወክንሽ?፣ በይ እህታለሜ ተረጋጊና አሁን ፣ ትንሽ አርፍ ብለሽ እንማማራለን። በችኮላ አይሆንም ማንኛውም ነገር፣ ማሰብ ይጠይቃል ለመስራት ቁም ነገር። ምን ይላል መሰለሽ እግዚአብሔር ሲናገር፣ መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፣ በመካሞች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል። ቅኖችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፤ ወስላቶች ግን በምኞታቸው ይጠመዳሉ። ኀጥእ በሞተ ጊዜ ተስፋውን ይቈረጣል፣ የኃያል አለኝታም ይጠፋል። ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥ ኀጥእም በእርሱ ፋንታ ይመጣል። ዝንጉ ሰው በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፣ ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናል። ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፣ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል። ይላል መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 11ን ካነበብሽው እናም እታለሜ እደኀጣተኛ እንደሚጠፋው ሰው። እደዛ አትሁኝ መንፈስ ሽን አውከሽ፣ ይልቅስ በእራስሽ ንስሃሽን ገብተሽ፣ ያለፈውን ታሪክ በንስሃ ከድነሽ፣ ወደ አባታችን ቤት ውይም ወደ አባትሽ፣ ተመለሽ እህቴ ቀኑ ሳይመሽብሽ። ሐጥያትን ከምሰሪ በጭኮላ ሄደሽ፣ ተረጋግቶ ማሰብ ነው ላንቺ የሚጠቅምሽ፣ አሁን ከእኛ ጋራ ነይ ሻይ እንጠጣ፣ ወዲያው እንማማር ቅጣት እዳይመጣ፣ ቀድመን ተዘጋጅተን እንጠብቀው አድስ ቀን ሲመጣ።
Show all...
👉🏾👉🏾👉🏾 ኦርቶዶክሳዊ #ሥርዓተ #አምልኮ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ  የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በተጠቀሰው ርዐሰስ መነሻነት 'ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን' መጽሐፍ ላይ ያለውን ጠቃሚ አጭር ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን። ሐዋርያዊት፣ ቅድስት፣ ከሁሉ በላይ እና አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ልጆቿ ከልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ እንዳይወጡ ፣በተቀደሰውና በጠበበው መንገድ እንዲጓዙ፣ የጉዟቸውም ፍሬ ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም መኖር እንዲሆን አምላካዊ የሆነ የአምልኮ መመሪያና ሥርዓት አላት: እነዚህ. የአምልኮ ሥርዓቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆነው፣ በአገልግሎታቸውም በሰው ልጆችና በፈጣሪ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ናቸው። ከዚህ ቀጥለን በቤተክ ርስቲያናችን በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ - የምትጠቀምባቸውን - አምላካዊ - ሕግጋት ከትርጉማቸው፣ ከአፈጻጸማቸው እና ከጠቀሜታቸው ጋር እንመለከታለን፡፡ እነሱም በክርስቲያኖች የመዳን ጉዞ ላይ የተቀመጡና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው። የጸሎትን፣ የጾምን፣ የምጽዋትን፣ የቅዱሳት ሥዕላትን ትርጉምና በአምልኮት ሥርዓት ዉስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ እናያለን፡፡ 1. ሥርዓተ ጸሎት “ጾማችሁ ሀገራችንን ከክፉ ፣ጾሎታችሁም የከተማችንን ቅጥር የሚጠብቅ ነው፡፡ " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ። ጸሎት፣ ሰው በሃይማኖት ፈጣሪውን እያመሰገነ እና ሥርየተ ኃጢለትን እየለመነ ከፈጣሪው ጋር የሚነጋገርበት መንገድ ነው፡፡ 'ጸሎትሰ ይእቲ ተናግሮተ ሰብእ ምስለ እግዚአብሔር" እንዲል /ፍትሕ መንፈሳዊ አን. 14/ የጸሎት ዋናው ዓላማ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ እንደመሆኑ ከዚህ በረከት ላለመራቅ መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ የጸሎት መሠረቱ "እሹ ታገኛላችሁ፣ ለምኑ ታገኛላችሁ፣ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋል" የሚለው አምላካዊ ቃል ነው፡፡ /ማቴ. 7፡7/ በውስጡም አምልኮትን፣ ልመናን፤ ምስጋናን፣ ንስሐን፣ ምልጃን፣ ስግደትን፤፣ ፍቅርን ስእለትንና ይቅር ባይነትን አካቶ የያዘ ነው፡ ለጸሎቱ አፈጻጸምም የተለየ ጊዜና ቦታ አለው፡፡ የጸሎት ጊዜያት ሰባት ናቸው፡፡ "ስለጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ" እንዲል መዝ.118፥164 “ዘወትር ለምእመናን ሁሉ የታዘዘው ጸሎት ግን በሰባቱ ጊዜያት ነው።" ፍትሕ መንፈሳዊ.እ.14 እነርሱም፥ 1. ጸሎተ ነግህ /የጠዋት ጸሎት/ - “በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ” መዝ.5፥3 2. ጸሎተ ሠለስት /የሦስት ሰዓት ጸሎት/ - “ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ጸለየ ዳንኤል ወአርኀወ መሳክወ ቤቱ፤ ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ዳንኤል የቤቱን መስኮት ከፍቶ ጸለየ፡” ዳን. 6፥10 3. ጸሎተ ቀትር /የስድስት ሰዓት ጸሎት/ - “በማታና በጠዋት በቀትርም እናገራለሁ እጮህማለሁ፥ ቃሌንም ይሰማኛል” መዝ. ይ4፥+17 4. ጸሎተ ተሰዓት /የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት/ - “ኢየሱስ፡ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ" “ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር” እንዲል ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን የሐዋርያትን ጉዞ በማሰብ በዘጠኝ ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ማቴ.27፥46 ፤ የሐዋ. 3፥1 5. ጸሎተ ሠርክ /የአስራ አንድ ሰዓት ጸሉት/ - “ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መስዋዕት ትሁን" መዝ. 140፦፥2 6. ጸሎተ ንዋም /የመኝታ ሰዓት ጸሉት/ - “በመኝታዬም አስብሀለሁ፤ በማለዳም እናገርሃለሁ፤ ረዳቴ ሆነኸኛልና፡፡' መዝ. 62:6 7. ጸሎተ መንፈቀ ሌሊት /የእኩለ ሌሊት ጸሉት/ - “በእኩለ ለሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሳለሁ” መዝ. 118፡62 ከሰባቱ ጊዜያት ካህናትና ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው በማኅበር የሚጸልዩባቸው ነግህና ሠርክ ናቸው። በቀሩት ጊዜያት ግን በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በያሉበት ሆነው ሊጸልዩ ይገባል፡፡ ጸሎት የእግዚአብሔርን አምላክነት አምጻኤ ዓለማትነትና አባትነት የምንገልጽበት መንገድ ነው።፦ የመጀመሪያው የሥርዓተ አምልኮ ደረጃ እግዚአብሔርን "ሥራህ ግሩም ነው" ብሎ ማድነቅ ነው፡፡ መዝ. 65:3 የዚህ ዓለም ሠራዒና መጋቢ ለሆነው፤ መነሻና መድረሻ ለሴለው ለልዑል እግዚአብሔር የአምልኮትና የምስጋና ጸሎት እናቀርባለን፡፡ የምናቀርበው የአምልኮ /የምስጋና/ ጸሎት ልባዊ የሆነና ከታይታ የራቀ፣ በሰውነታችንና በቤታችን እግዚአብሔርን የምናነግስበት ሊሆን ይገባል፡፡ ጸሎት የፈለግነውንና የጎደለንን ለማግኘት እንዲሁም ለተደረገልን እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት መሳሪያ ነው። መንፈሳዊ የሆነ ሰው እግዚአብሔር በሥጋዊ ሕይወቱ የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን እንዲሰጠው፤ ለቀዊመ ሥጋ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እንዲያሟላለት፣ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ደግሞ ለንስሐና ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ እንዲያበቃው፣ በሃይማኖት እንዲያአጸናው፣ ምግባር ትሩፋት /ከታዘዙት በላይ አብልጦ መሥራት/ ለመሥራት እንዲያበቃው በእምነት ይለምናል፡፡ “የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁ እመኑ ይሆንላችሁማል” ማር 7፥7 የሚጸልይ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈሳዊ ኃይልን ያገኛል፡፡ “የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች፡” ያዕ.5:16 የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች ሁሉ በድል ለመወጣትም ይችላል። "የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ...በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ " ኤፌ.6፡፥11-18 ኤፌ. 6፥1ዑ18 *ጸሎትን የሚወዱ ሰዎች እግዚአብሔር ያድርባቸዋል መከራ ከሚያመጣባቸው፥ ከሚያሳዝናቸው ከሰይጣን ያሳርፋቸዋል” አረጋዊ መንፈሳዊ የሚጸልይ ሰው ምስጢር ይገለጥለታል፡ “በእዉነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም፡፡ አሞ. 3፥7 አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 14 ላይ በጸሎት ሀብታት ምስጢራት ይገለጻሉ" ይላል፡፡ ጸሎት ኃጢአትን ለማስተስረይና የታመመንም ለመፈወስ ጽኑ መድኃኒት ነው፡፡ “ከአናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያን ቀሳውስትን ወደ እርሱ ይጥራ፥ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት፡፡ የአምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል፣ ጌታም ያስነሳዋል፥ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደሆነ ይሰረይለታል፡፡ ያዕ. 5፥14 ጸሎት ከቅጣትና ከመክራ የምታድን ናት፡፡፥ “በመከራ ቀን ጥራኝ አድንህማለሁ” መዝ. 49፥15 “ወደ መከራ እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ" ሉቃ. 22፥40 በርትዕትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ጸሎት በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን ራሱን የቻለ የአፈጻጸም ሥርዓት አለው፡፡ “ሁሉ በአግባቡ እና በሥርዓቱ ይሁን" እንዲል፡፡ 1"ቆሮ.14፥40፡፡ ዝግጆቱንም አፍአዊ/ውጫዊ/ እና ውስጣዊ በሚል ለሁለት ከፍለን አንመለክታል፡፡ ሀ. አፍአዊ ዝግጅት ፦ -ንጽህናን መጠበቅና አለባበስን ማስተካከል፥ ጻሎት ከማድረጋችን በፊት የሰውነትንና የልብስን ንጽህና መጠበቅ፣ ነጠላን መስቀለኛ አጣፍቶ መሄድ ይገባል፡፡ ቀዊም/አቋቋም/፥ ለጸሎት የተዘጋጀ ሰው ሁሉ የጠየቀው ጥያቄ ፈጥኖ እንደሚደርሰው በማመን ዓምድ ወይም ግድግዳ ሳይደገፍ በጥብአት መቆም ይኖርበታል፡፡ “በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ” መዝ. 5፥3 ይቀጥላል ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦ https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
Show all...