cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Addis News

Advertising posts
461
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
♦ ከግፍ እስር ተፈቷል! ከበርካታ ወራት የግፍ እስራት በኋላ በላይ በቀለ ወያ ከእስር ተፈቷል!
670Loading...
02
🔴🔴🔴 ፋኖ በከባድ መሳሪያ ታጅቦ በአራት አቅጣጫ የመጣውን የብልፅግና ጦር መጨረሱን ይፋ አደረገ። በደቡብ ጎንደር በአምስት ግንባሮች እየተደረገ በሚገኘው ከባድ ውጊያ ፋኖ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን አስታውቋል። በደብረታቦር ማህደረ ማርያም ፣ በጭስ አባይ ፣ በአንዳቤቴ ፣ በእስቴና በደራ ዓርብ ገበያ ልጫ ግንባሮች እየተደረገ በሚገኘው ውጊያ ነው ድል ማስመዝገባቸውን የተናገሩት። ከፍተኛ ቀጠና ሸፍኗል በተባለው ውጊያ የብልፅግናው መንግስት የመጨረሻውን ከፍተኛ ሃይል ይዞ ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። በጎንደርና በጎጃም ፋኖዎች ጥምረት እየተደረገ የሚገኘውን ውጊያ መቋቋም ያቃተው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ከባህር ዳር ከፍተኛ ሃይል በ16 ወታደራዊ መኪና ጭኖ እያንቀሳቀሰ መሆኑን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። 🔴🔴🔴 በባህር ዳር ዙሪያ ዘንዘልማ ከተማ ውጊያ ተካሂዶ እንደነበርም ተነግሯል። ለሰባት ሰዓት ተደርጓል በተባለው ውጊያ ከ10 በላይ የብልፅግናው መንግስት ወታደሮች መገደላቸው ሲነገር 4ቱ መቁሰላቸውና 10 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በፋኖዎች መማረካቸው ተገልፃል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ ድረስ ተኩሱ ይሰማ ነበር ያሉት ምንጮቻችን ውጊያው ከእኩለ ቀን በኋላ ረገብ ማለቱን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ በአካባቢው አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ ተነግሯል። በተመሳሳይ በጎጃም ጎዛመን ወረዳ የቦቅላ የሚደረገው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ተነግሯል። ከአምስት ወራት በላይ ፋኖዎችን ቀልባችኋል የተባሉ የኩብራ ከተማ ነዋሪዎች መገደላቸው የገለፁት ምንጮቻችን በአማኑኤል ቤተክርስቲያን መሽጎ የሚገኘው የብልፅግና ጦር ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንፁሃን እየጨፈጨፈ መሆኑ ተነግሯል። በወረዳው ቀኝ አቦ በተባለው ቦታም ከባድ ውጊያ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልፃል። ውጊያ እንደከዚህ ቀደሙ የደፈጣ ሳይሆን የእጅ በእጅና የጨበጣም ነው ብለዋል። ሞገሴ ሽፈራው
1330Loading...
03
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 129.7 ሚሊዮን መድረሱን አስታወቀ ኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ የሥነ ሕዝብ ፈንድ ድርጅት እ.ኤ.አ. የ2024 የኢትዮጵያን የሥነ ሕዝብ ሪፖርት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተመድና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋጥር ዘንድሮ 129.7 ሚሊዮን መድረሱንና ቁጥሩም በ28 ዓመት ውስጥ ራሱን እጥፍ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ0 እስከ 14 ዕድሜ 39 በመቶ፣ ከ10 እስከ 19 ዕድሜ 23 በመቶ፣ ከ10 እስከ 24 ዕድሜ 32 በመቶ፣ እንዲሁም ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ክልል 55 በመቶ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ዓመታዊ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ከአገሪቱ ሕዝብ ሦስት በመቶው 65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ዜጎች ሲሆኑ፣ የአገሪቱ የውልደት መጠን 3.9 በመቶ እና የመኖሪያ ዕድሜ ጣሪያ ወንዶች 64 እንዲሁም ሴቶች 70 መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
1480Loading...
04
🔴🔴🔴 ሰኔ 2/2016 ዓ.ም 1) የደፈጣ ጥቃቶች 1.1) ጎንደር ዙሪያ ድንዛዝ በተባለ ቦታ  በመንግሥት ኃይሎች ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደረሰ። 1.2) አሰቃቂ ዕልቂት ያደረሰ የተባለው የደፈጣ ጥቃት የተፈጸመው በደቡብ ወሎ ዞን  መካነ ሠላም  ከተማ አቅራቢያ መነዩ ማርያም በተባለ ቦታ ነው። በዚህ ጥቃት  ቁጥራቸው ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ የመንግሥት ኃይሎች ሳይጎዱ አይቀርም የሚሉት ምንጮች ሦስት ወታደራዊ  ኮንቮይዎች ሲወድሙ አንዱ ደግሞ ገደል ገብቷል ብለዋል። ይህን የመሰለ እልቂት አላየንም የሚሉት የዓይን እማኞች አስክሬን የማንሳቱ ሥራ እንደቀጠለ ነው ብለዋል። 1.3) ከወልዲያ ከተማ በቅርብ እርቀት በሚገኙ ሦስት ቦታዎች የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሟል። ጋ×ላ ጊዎርጊስ እዜት በር ወጠጥ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጸመው ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት አድርሷል። 🔴በ መርሃ ቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ አልማዝ ሜዳ ሞያ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም አዲሱ ገበያ በተባሉ ሁለት ቦታዎች በሌሊት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት የሚሊሺያ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። 🔴የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ከተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት አመለጡ! Belete Kasse
1780Loading...
05
🔴🔴🔴ዜናዎች 🔴የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚባባስና የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋ እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን ከአንድ የድርጅቱ ሰነድ ላይ መመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነትና ላኪነት እና በችርቻሮና ጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የፈቀደው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት ሲል ሊኾን እንደሚችል ሰነዱ ማመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለቱ ተቋማት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም እንደሚፈልጉና የእስካኹኑን የዋጋ ንረት ከአለመረጋጋትና ከዓለማቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ጋር እንደሚያያይዙት ሰነዱ ያብራራል ተብሏል። ብሄራዊ ባንክ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ማብቂያ የመደበኛውንና የጥቁር ገበያውን የምንዛሬ ልዩነት ልዩነት ለማጥበብና ለ7 ወራት የሚበቃውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ አንድ ወር ለማሳደግ ማቀዱን ሰነዱ ይጠቅሳል ያለው ዘገባው፣ ባንኩ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን ወደ ኹለት ወር ለማሳደግ ማሰቡንም እንደጠቆመ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ከእያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት። 🔴ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል። በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል። ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል። በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው። 🔴የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ኩመር እና አውላላ ከተባሉ የተመድ የስደተኞች መጠለያዎች ለቀው የወጡ ሱዳናዊያን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር እንቅስቃሴ እያደረኩ ነው ማለቱን ቪኦኤ ዘግቧል። የተቋሙ ሃላፊዎች፣ ሱዳናዊያኑን ስደተኞች በዞኑ ውስጥ ወደሚገኝ አፍጥጥ የተባለ ቦታ የማዛወሩ ሂደት እንደተጀመረ መግለጣቸውን እንደገለጡ ዘገባው አመልክቷል። ተቋሙ፣ በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ኹኔታ ለማሻሻል እየሠራ እንደኾነም ገልጧል ተብሏል። በሺዎች የሚቆጠሩት ስደተኞች ከመጠለያዎቹ አቅራቢያ መንገድ ዳር የከተሙት፣ ታጣቂዎች በመጠለያዎቹ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ስላደርሱ፣ ተደጋጋሚ እገታዎችን ስለፈጸሙና አገልግሎቶች በማሽቆልቆላቸው እንደኾነ መናገራቸውን የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን መግለጡ ይታወሳል። ስደተኞቹ በበኩላቸው፣ ተመድ በሦስተኛ አገር እንዲያሠፍራቸው ይፈልጋሉ ተብሏል። መንገድ ዳር የከተሙት ስደተኞች አኹንም የጥቃት ሰለባ እየኾኑ እንደሚገኙ መናገራቸውን ሮይተርስ ትናንት ዘግቦ ነበር። 🔴የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል። የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው። አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው። አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል። 🔴ዓለም ባንክ፣ በአውሮፓዊያኑ 2023 የዓለም የወደቦች የብቃት መለኪያ ለሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ወደቦች ቀዳሚውን ደረጃ ሰጥቶታል። በድርጅቱ የደረጃ ምደባ መሠረት፣ በርበራ የካርጎ መርከቦችን በማስተናገድ አቅሙ ከዓለም 348 ወደቦች 106ኛ ደረጃ አግኝቷል። ጅቡቲ ወደብ በዓለም 379ኛ ደረጃ የተሰጠው ሲኾን፣ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ደሞ 328ኛ ደረጃ አግኝቷል። የጅቡቲ መንግሥት፣ ለጅቡቲ ወደብ የተሰጠውን ደረጃ "አድሏዊ" በማለት ውድቅ አድርጎታል። ዓለም ባንክ፣ የዓለም ወደቦችን ለማወዳደር የተጠቀመው መስፈርት፣ ካርጎ ጫኝ መርከቦች ወደቦች ላይ ጭነታቸውን ለማራገፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ነው።
2060Loading...
06
♦ በአልሞ ተኳሾች የአዲስ አበባ ወጣት መሰዋዕትነት !! የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የወጣቶች ደምና ሰቆቃ ፣ የእናቶችን ዋይታና ለቅሶ ያስተናገዱበት መቼም የማይረሳ ጥቁር ቀን ! የምርጫ 1997 ውጤት መሰረቁን ተከትሎ፣ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ ህዛባዊ እንቅስቃሴ እና ተቃውሞ ተካሂዶአል፡፡የምርጫው መሰረቅ ለመቃወም አደባባይ የወጡት ዜጎቻችን ላይ ፋሽስታዊ እርምጃ በአገዛዙ ስርዓት ጠባቂዎች አማካኝነት ተወስዶባቸዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮች ፣አደባባይ ባዶ እጃቸውን በወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ በአልሞ ተኳሾች የተወሰደው እርምጃ የስርዓቱ ልኬለሽ አምባገነን ባህሪ ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በወቅቱ የነበረው አስከፊ ጭፍጨፋ የአገዛዙ ስርዓት ዋና መሪ የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ፣ የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ሰንሰለት ሥር ገብቶ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለእሳቸው እንደሆነ፣ በሬዲዮና በቴሌቭዥን መመሪያና አዋጅ ማስነገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ የእሳቸው እና የመንግስታቸውን ጥሪ የተቀበለው በልዩ ስሙ የአጋአዚ ጦር የሚባለው፣ በአዲስ አበባ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሰው ሕይወት ቀጠፈ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነፃነት ጠያቂዎች በአገዛዙ ሥርዓት አገልጋዮች አማካኝነት ወደተለያየ የማጎሪያ ስፍራ በመውሰድ በዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አደረጉ ። ሰኔ 1 ቀን 1997 ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ፤ ሁሌም የማንረሰው ዛሬም ድርስ በሁላችን ህሊና የሚታወሰው ነው፡፡ በተለይ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት ግንባሯን በጥይት ተመታ የተገደለችው የ18 አመቷ ወጣት ሽብሬ ደሳለኝ፤ቀድሞ በተተኮሰ ጥይት የወደቀውን ወንድሙን አብረሃም ይልማ አስከሬን ታቅፎ ያለቅስ የነበረው በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው የፈቃዱ ይልማ አሟሟት እንዴት ይረሳል ? የ14 አመቱ ነብዩ አለማየሁ ደብተሩን ይዞ ከትምህረት ቤት ሲመለስ አልሞ ተኳሽ በሆኑ ወታደሮች መገደሉ እና የወላጅ እናቱ የይድረሱልኝ እሮሮና ለቅሶ ዛሬም ድረስ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ የተቀመጠ ሐዘን ነው፡፡ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕትነት የከፈሉ ወገኖቻችንን መቼም አንረሳቸሁም ! ክብር ለሠኔ 1/1997 ዓ.ም.እና ለጥቅምት 22/1998 የአዲስ አበባ የነፃነት እና ዴሞክራሲ ሰማእታት 🙏 ይድነቃቸው ከበደ
1651Loading...
07
Media files
2070Loading...
08
🔴🔴🔴 ግንቦት 29/2016 ዓ.ም 1) ለሌሎች ኢትዮጵያውን ያልተፈቀደ  ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ የተፈቀደ ሆኗል። ይህን የሚሉት የመረጃ ምንጮች ባለፉት አስር ወራት ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች በርካታ ስራተኞች በሹመትና በዝውውር ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርገዋል። በሲቪል ሰርቪስ በፖሊስ እና በደህንነት ተቋማት እንዲመደቡ የተደረጉት በከንቲባ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ነው ተብሏል። የከተማ አስተዳደሩ በጀት የለኝም በሚል የከተማዋ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ባገለለ መንገድ ይህንን ማድረጉ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል። የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። 2) በሰሜን ጎንደር ወገራ ቆላ እና በደባት ቆላማ ቦታዎች በተደረገው ውጊያ የዳባት ወረዳ ሚሊሺያ አባላት ሙሉ በሙሉ አልቀዋል። የወረዳው ምድብተኛ የዐድማ ብተና አባላትም እንዲሁ አልቀዋል። በአጅሬ ጃኖራ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ሚሊሺያ ዐድማ ብተና አባላት ከፋኖ ኃይሎች ጋር ባደረጉት ከባድ ውጊያ ነው 133 በላይ የሚሊሺያ እና የዐድማ ብተና አባላት የተገደሉት ተብሏል። 3) ጋዜጠኛና ደራሲ ታዲዮስ ታንቱ በተመለከተ ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት አዛውንቱ ጋዜጠኛ ከእስር ተለቀዋል ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዘገባ ስህተት ነው ተብሏል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀጋ ለ Ethio News- ለኢትዮ ኒውስ ቻናል 2 እንዳረጋገጡት ባለቤታቸው አለመፈታታቸውን ለቀጣዩ ሰኔ 4/16 ዓ.ም የመጨረሻ ምስክሮች ለማሰማት ቀጠሮ መኖሩን ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ በቂሊንጦ የቀጠሮ ማቆሚያ እስር ቤት ይገኛሉ። 4)ግንቦት 29/2016 ዓ.ም በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን  በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ በደርጌ ኮትቻ ቀበሌ በመከላከያ 4 የአንድ በተሰው አባላት ተረሽናዋል። በዚሁ ወረዳ አማራውን ለስብሰባ እንፈልጋችኋለን በማለት 170 የአማራ አርሶአደሮችን  በአሊቦ ከተማ እስርቤት ያለምግብና እና በቂ ጥበቃ አስረዋቸዋል። ፖሊሶቹ እነዚህን እስረኞች በሸኔ ታጣቂዎች ለማስጠቃት ዕቅድ አላቸው ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ስጋታቸውን ገልፀዋል። ሆን ተብሎ ጠንካራ አማራዎች መሣሪያ ተነጥቀው በአንድ እስር ቤት የታጎሩት በተቀነባበረ የአካባቢው አስተዳደር እና የሸኔ ታጣቂዎች ዕቅድ ነው የሚሉት ቤተሰቦቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። Belete kassa
1540Loading...
09
♦ ከወራት በፊት ለዐቢይ አሕመድ መወድስ አቅርበው የነበሩት ቄስ ወንድም አማረ በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ! "ከሕዝቡ እና ከቤተክርስቲያኗ ምዕመን ጋር ካጣሉኝ በኋላ ቃል የገቡልኝ ሳይፈፅሙልኝ ተጠቅመው ጥለውኛል " ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በየአከባቢው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ እሳቸውና ስለሚመሩት ፓርቲ መወድስ ያቀረቡት ከደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ ተወክለው የሄዱት ቀሲስ ወንድም አማረ በጉና ክ/ጦር ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ ዘግቧል። በወቅቱ ቀሲስ ወንድም አማረ፤ ዐብይ አህመድ ለሚመሩት ፓርቲ የዜማ መወድስ ማቅረባቸውን ተከትሎ "እንዴት አማራ ሆነው የአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀን የአገዛዝ ስርዓት ያወድሳሉ? ህፃናትና ነፍሰ ጡር እናቶችን ሳይቀር የአማራን ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድል መከላከያ ሰራዊትን ያሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትርን እንዴት ያሞግሳሉ? በርካታ ካህናትና ምዕመናን በቤተ መቅደስ እንዳሉ በታጣቂዎች ሲገደሉ ምንም አይነት ምላሽ ለማይሰጥ መንግስት እንዴት ክህነታቸውን ተጠቅመው የዜማ መወድስ ያቀርባሉ?" በሚል በርካታ ሰዎች ማህበራዊ ትስስር ገፃቸውን በመጠቀም ትችታቸውን ሲሰነዝሩ እንደነበር ይታወሳል። "በዞኑ ተወክየ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጠሩት ውይይት ለመሄድ ስዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ይርጋ በዞንናችን አመራሮች በኩል አስጠርተውኝ እውቀትህን ተጠቅመህ ለመንግስት የዜማ መወድስ ካቀረብ የከተማ ቦታ እንሰጥኃለን በሚል ቃል ገብተውልኝ ነበር" ያሉት ቀሲስ ወንድም ፤ ነገር ግን ከሕዝቡ እና ከቤተክርስቲያኗ ምዕመን ጋር ካጣሉኝ በኋላ ቃል የገቡልኝ ሳይፈፅሙልኝ ተጠቅመው ጥለውኛል ማለታቸውን የፋኖ ደህንነት አባላቱ ለአማራ ድምፅ ሚዲያ ገልፀዋል።
1430Loading...
10
Media files
1520Loading...
11
🔴🔴🔴የሕግ አስፈጻሚው አካል ስልጣኑን አላግባብ በመጠቀሙ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይራዘም ኢሰመጉ አሳሰበ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የሕግ አስፈጻሚው አካል ስልጣኑን አላግባብ መጠቀሙን ተከትሎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳያራዝም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን አሳስቧል። አዲስ ማለዳ ከጉባኤው መግለጫ እንደተመለከተችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በአዋጁ ወቅት ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በመፈጸማቸውና የተፈጸሙ ኢ ሰብዓዊ ድርጊቶችን በመመርመር ፈጸሚዎችን ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜ በመጠናቀቁ በተለያዩ መደበኛ እና ኢ መደበኛ ማቆያ ስፍራዎች ውስጥ በአዋጁ ምክንያት ተይዘው የሚገኙ ሰዎችን የአካል ነጻነት አንዲያከብር ወይም በተገቢው ጊዜ በመደበኛው ሕግ እና ስነ ስርዓት መሰረት ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ እና ወደ መደበኛ ማቆያ ስፍራዎች እንዲያዘዋውር ኢሰመጉ ጠይቋል። ኢሰመጉ አክሎም በአዋጁ ወቅት ከፍተኛ የሆነ እስር፣ የቤት ለቤት ብርበራ፣ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር እና ሌሎችም ልዩ ልዩ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አዋጁ ለሕግ አስፈጻሚው አካል በሰጠው ሰፊ ስልጣን ምክንያት ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብሏል። እንዲሁም ብዙ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ አርቲስቶችና ሌሎችም ሰዎች ታስረዋል አንዳንዶቹም ላይ የእገታና የአስገድዶ መሰወር ድርጊቶች መፈፀማቸውን ጠቁሟል።
1621Loading...
12
🔴🔴🔴 1) ሸዋሮቢት የቀወት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚኒሹ በቀለ ምሽት 1:30 ገደማ ባልታወቁ ኃይሎች መገደሏ ተገለፀ። ሚኒሹ በቀለ የአስተዳደር ጽ/ቤ ኃላፊነት ከመቀበሏ በፊት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ ቀጥሎም የብልጽግና ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ሆና ሰርታለች። ይህንን የብልጽግና ሹመት እንዳትቀበል ተደጋጋሚ ምክር ተስጧት ነበር የሚሉት ምንጮች የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር እና የቀወት ወረዳ አስተዳደር የካቢኒ አባላት ለደህንነታቸው በመስጋት ዙጣ ጀጀባ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ነው የሚኖሩት ብለዋል። ከአምስት ቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አልብስ መገደሉ ይታወቃል። በሸዋሮቢት ባለፉት ስምንት ወራት 9 የብልጽግና ተሻሚዎች ባልታወቁ አካላት ተገድለዋል ሲሉ ምንጮች አስታውሰዋል። 2) አንድ ሱዳን ጀኔራል ከ19 አጃቢዎች ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጥገኝነት ጠይቋል። 600 የሱዳን ወታደሮች ይህንን ተከትሎ ዛሬ ወደ ኢትቲገብተው ጥገኝነት ይጠይቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጀኔራሉ የአልቡርሃን ወገን ነው። 3) በደቡብ ጎንደር የተለያዩ ቦታዎች ከባድ ውጊያዎች ተደርገዋል። ጋይንት አስቴ ጉና ፋርጣ አካባቢ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ያስከተሉ ውጊያዎች መደረጋቸውን ምንጮች ገልፀዋል።
1570Loading...
13
የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚያደርጉት ፍተሻ በአብዛኛው ከስራ ሰዓት ውጭ መሆኑ ስጋት እና እንግልት ፈጥሯል ሲል ኢሰመጉ አሳሰበ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚያደርጉት ፍተሻ ህብረተሰቡን ስጋት ውስጥ የሚከት እና ለእንግልት የዳረገ ነው አለ። አዲስ ማለዳ የተመለከተችው የጉባዔው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ፤በአማራ ክልል፤ በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት የፀጥታ አካላት ቤት ለቤት ፍተሻ እና ብርበራ ይደረጋል ተብሏል። ፍተሻው በሚካሄድበት ጊዜ አንዳንድ ቦታዎች ፈታሾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያም ሆነ ከየት እንደመጡ የሚገልጽ ማስረጃ እንዲሁም ከፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ፈቃድ እንደማያሳዩ እንዲሁም የብርበራው ሰዓት በአብዛኛው ከስራ ሰዓት ውጭ አንዳንዴም በሌሊት እንደሆነና በዚህም የተነሳ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደገባ እና ለከፍተኛ እንግልት እንደተጋለጠ ኢሰመጉ አረጋግጫለሁ ሲል አስታዉቋል። ኢሰመጉ አክሎም በተለያዩ አካባቢዎች በመንገድ ላይ የሚፈጸሙ አላግባብ የገንዘብ ብዝበዛዎች እና እገታዎች መቀጠላቸውን ገልጾ መንግስት የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አክብሮ እንዲያስከብር ጥሪ አቅርቧል። ግንቦት 18 ቀን 2016 በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቡር ዞን በጉርዶም ድቻኖ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት በተሰጠ የአምልኮ ስፍራ የእምነቱ ተከታዮች ያልሆኑ ሰዎች ወደ አምልኮ ስፍራው በመግባት የአምልኮ ስፍራውን እንዳቃጠሉ እና የቤተ ክርስቲያኑን ንብረትም ያወደሙ መሆኑን አረጋግጫለሁ ሲል ኢሰመጉ ገልጿል።
1570Loading...
14
Media files
1640Loading...
15
ለቤተ ክርስቲያኗ አገራዊ ምክክር ላይ እንድትሳተፍ በይፋ የቀረበላት ጥያቄ አለመኖሩ አሳዛኝ ነው- የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባዉን ማጠናቀቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን ለቤተ ክርስቲያኗ ያቀረበው የተሳትፎ ጥሪ እንደሌለ አስታወቀ። አዲስ ማለዳ ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እንደተመለከተችው "ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል" ተብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኗን መብት የሚያስከብር ኮሚቴ ማወቀሩም ተገልጿል። በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኗ እና በመንግስት መካከል የሚኖረውን የሥራ ግንኙነት በተመለከተ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተረድታለች። ቅዱስ ሲኖዶስ ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ ዝርዝር መግለጫ ለመስጠት እንዲሁም የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ እንዲሻሻል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችም "ተገቢው" ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል። የቤተ ክርስቲያኗ የ10 ዓመታት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው መዋቅራዊ አደረጃጀትን በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
1840Loading...
16
Media files
1470Loading...
17
🔴🔴🔴ዜናዎች 🔴ዓለማቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ቀውስ የሰጡት ምላሽ በቂ እንዳልነበር ድርጅቶቹ ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት የግምገማ ሪፖርት አስታውቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ እስካለፈው ዓመት ታኅሳስ ድረስ፣ “የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራ አመራሩ በዋናነት የተበታተነ" እንደነበርና ይህም የዕርዳታ አሰጣጡ ውጤታማ እንዳይኾን እንዳደረገው ሪፖርቱ ገልጧል። ሪፖርቱ፣ በግጭት ወቅት ወሳኝ የኾነው "በመርህ ላይ ያተኮረ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራ" በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች "በበቂ ኹኔታ" ተግባራዊ አልሆነም ብሏል። ኾኖም ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በጦርነቱ ለተጎዱት ሦስት ክልሎች አስፈላጊውን ዕርዳታ በማድረስ ረገድ በርካታ መሰናክሎችን ማለፍ እንደቻሉ ሪፖርቱ ጠቅሷል። 🔴የከባድ መኪና ሹፌሮች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መስራት አስቸጋሪ ኾኖብናል ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የከባድ መኪና ሹፌሮች፣ "የኮቴ" በሚል በእያንዳንዱ ኬላ ላይ በሕገወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፍሉ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ባንድ ኬላ ላይ የተሰጠ ደረሰኝ ሕጋዊ ይኹን አይኹን እንደማይታወቅና ቀጣዩ ኬላ ላይ ደረሰኙን አሳይቶ ገንዘብ ሳይከፍሉ ማለፍ እንደማይቻልም አሽከርካሪዎች መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። አሽከርካሪዎች ለኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ማጠናከሪያ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱም ገልጠዋል ተብሏል። 🔴መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ከሳዑዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 188 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። ከተመላሾቹ መካከል፣16ቱ ጨቅላ ሕጻናትና 20ዎቹ ደሞ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ አስታውቋል። ብሄራዊ ኮሚቴው ከሚያዚያ 04 ጀምሮ እስከ ትናንት በጠቅላላው ከ37 ሺህ 500 በላይ ዜጎችን መልሷል ተብሏል። 🔴ኬንያ፣ የተቃዋሚ መሪውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው እንዲመረጡ በሰኔ መጨረሻ ማመልከቻ ሰነዱን ለኅብረቱ እንደምታስገባ አስታውቃለች። የአገሪቱ መንግሥት ኦዲንጋ እንዲመረጡ በአሕጉር ደረጃ የሚያስተባብር ቢሮ ከፍቷል። ከኦዲንጋ ሌላ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲና ሲሸልስ ለኮሚሽኑ ሊቀመንበርነት ዕጩዎቻቸውን አቅርበዋል። የኅብረቱ መሪዎች ቀጣዩን የኮሚሽኑን ሊቀመንበር የሚመርጡት በቀጣዩ ዓመት የካቲት ወር ላይ ነው። 🔴ደቡብ ኮሪያ፣ በተመድ ውስጥ ሰሜን ኮሪያን በሚመለከቱ ጉዳዮች የአፍሪካ አገራትን የፖለቲካ ድጋፍ እንደምትፈልግ ይፋ አድርጋለች። የደቡብ ኮሪያና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ምሽት ሲጠናቀቅ ባወጣው መግለጫ፣ በቁልፍ ማዕድናት አጠቃቀም ላይ የሚመክር የኮሪያ-አፍሪካ የምክክር መድረክ እንዲቋቋም እንደተወሰነ ገልጧል። አገሪቱ፣ እስከ አውሮፓዊያኑ 2030 ለአፍሪካ አገራት 10 ቢሊዮን ዴላር እርዳታ ለመስጠት ቃል የገባች ሲኾን፣ ኩባንያዎቿም በኢንቨስትመንት ዘርፍ በአፍሪካ እንዲሠማሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጣለች።
1610Loading...
18
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙና ዳይሬክተሩን ጨምሮ የሚዲያ ባለሙያዎችና የፖሊስ አባላት ፋኖን በገንዘብና በሎጀስቲክ በመደገፍ በአገዛዙ ተወነጀሉ በእስር ላይ የሚገኙትን ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙንና ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሀያ የሚሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎችና የፖሊስ አመራሮች በብልፅግናው አገዛዝ ፋኖ በገንዘብና በሎጀስቲክ በመደገፍ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል። ዝነኛው ተዋናይ አማኑኤል ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ እንዲሁም ዳይሬክተሩን ጨምሮ ከ20 በላይ ሰዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ሮሃ የተመለከተችው የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ክስ አርቲስቶቹንና የፖሊስ አባላትን በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘቡን ለፋኖ ሎጂስቲክስ መግዣ ለማዋል ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግታዊ ስርዓቱን በኃይል በትጥቅ ትግል ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ጠርጥሪያቸዋለሁ ብሏል። ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፖሊስ በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት የተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ክልሎች የፀጥታ አካላት ካምፖች፣የህዝብ መሰብሰቢያ አደባባዮች፤ትምህርት ቤቶችና እና የመሳሰሉ ስፍራዎች ላይ የቦንብ ፍንዳታዎችን ተከስተዋል በማለት ሐስተኛ መረጃ ለህብረተሰቡ አሰራጭተዋል የሚል ክስም አቅርቧል።
1530Loading...
19
በ ወልዲያ ከተማ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተነገረ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ በዚህ ሳምንት ብቻ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ በተነገረው ጥቃቶች የሰዎች ሕይወት እንዳላለፈ ተገልጿል። የመጀመሪያው ጥቃት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ሙጋድ በተባለ ሰፈር ተከራይተው በሚኖርበት ቤት ላይ እንደተፈጸመባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፤ በጥቃቱ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። ግንቦት 25/2016 ዓ.ም. እሁድ ምሽት ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የገዢው ፓርቲ ኃላፊ ላይም ሆነ በቤተሰባቸው ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ሁለት ነዋሪዎች ሰዎች ተናግረዋል። ሌላ የአካባቢው ነዋሪ ግን በጥቃቱ የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊው ሳይጎዱ አልቀረም ያሉ ሲሆን፤ ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የነዋሪዎች እንቅስቃሴ ታግዶ እንደነበር ገልጸዋል።
1400Loading...
20
ክርስቲያን ላቃቸው የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ አረፈ የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ 17 ዓመት የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም፣ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ባለቤቷ፤ ( የ3 ልጆቿ አባት ) የተወዳጁ የምንጊዜም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋች የመንግስቱ ወርቁ ልጅ ላቃቸው መንግስቱ ነው። በድንገት ያረፈው ክርስቲያን ላቃቸው - የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበር። እያንዳንዳችን እምነታችን የሚፈተንበት ፣ አምላካችንን የምንጠይቅበት ፣ ልባችን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የሚሰበርበት ጊዜ ይመጣል ። አንዳንዴ እምነታችንም የማይረዳን ይመስለናል ። እግዚአብሔር የጨከነብን ይመስለናል ። የልጅ በሕይወት መለየት እንደዚያ ይመስለኛል ። ሟች መቼም ተጎድቶ አያውቅም ። ቋሚ ያዝናል ። ከማዘንም አልፎ ይሰበራል ። ዘሪቱ ድሮም እንደ ዝናዋ ፣ እንደ መታየቷ የውጪ ሰው አልነበረችም ። በከተማ ውስጥ ልጆቿን ገዳም አድርጋ የመነነች ነበረች ። መቸም ያሳዝናል ። ለአምላክ አስተያየት ቢሰጥ እናት የልጇን ህልፈት ባታይ ፣ ባትሰማ ። ግን እግዚአብሔር የፈቀደውን አደረገ ። እህት ዘሪቱ እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጥሽ ።
1370Loading...
21
Media files
1440Loading...
22
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዛሬ ያልቃል፤ ኢሰመኮ በአዋጁ የታሰሩ እንዲለቀቁ አሳሰበ ምክንያቱን በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ያደረገው እና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ዛሬ መጠናቀቁን ኮሚሽኑ አሳትውሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የገለጸው ኮሚሽኑ ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ መግለጫችን ሲያወጣ የቆየ ሲሆን በዚህም የመንግስት እና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች በመብት ጥስቶች ላይ መሳተፋቸውን እንዳረጋገጠ አዲስ ማለዳም በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም። በመሆኑም በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።
1490Loading...
23
🔴🔴🔴 1) ብአዴን ብልጽግና አዲስ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ጀምሯል ተባለ። ሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች በሚደረጉ የሕዝብ ስብሰባዎች ራያን በተመለከተ ሕዝብ ለሚያነሳው ጥያቄ ፋኖ ምክንያት ነው ብላችሁ ምላሽ ስጡ ሲል ለካድሬዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። ፋኖ ጦርነት ባይጀምር ራያ አይወረርም ነበር። የምትደግፉት ፋኖ ለምን ራያን አያስመልስም የሚለውን ፕሮፖጋንዳ በሰፊው እያሰራጩ ነው። 2) ወልዲያን ጭምር ለህወሓት እንሰጣለን ሲል ጀኔራሉ ዛተ። በወልዲያ ከተማ ዛዲግ አብረሃ ጀኔራል ተስፋዬ ሕዝብ ሰብስበው ነበር ተብሏል። በስብሰባው ላይ ጀኔራል ተስፋዬ ህወሓት ምንም ዓይነት መሣሪያ አላስረከበም ትጥቅ አልፈታም። ራያ የተወረረው በፋኖ ጦርነት ምክንያት ነው። አሁንም ፋኖ ውጊያ ካላቆመ እስከ ወልዲያ ለህወሓት እንሰጠዋለን ብሏል። ህወሓት በብልጽግና ግብዣ ራያን መውረሩን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ታዳሚዎች የጄኔራሉ ምስክረነት ማሳያ ነው ብለዋል። 3) ስምንት የወረዳ አመራሮች በፋኖ ተይዘው ተወሰዱ። በደቡብ ወሎ ዞን ዐምሓራ ሳይንት ቀጠና 8 የብልጽግና አመራሮች በፋኖ ተይዘው ተወስደዋል። አመራሮች ሰኞ ገበያ በተባለ ቦታ ግብር ለመሰብሰብ በገበያ ቦታ እንዳሉ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም ነው ተብሏል። 4) የፖሊስ ኮሚሽነሩ ሳይገደል አልቀረም። በደቡብ ወሎ ከላላ ወረዳ ሰሞኑን በተደረገ ውጊያ የፖሊስ ኮሚሽነር ሳይገደል አልቀረም ያሉቴ ምንጮች የፖሊስ መኮነኑ ያረፈበት ሆቴል በቦምብ ተጠቅቷል በመትረጊስ ተደብድቧል። አጃቢዎች ተገድለዋል ብለዋል። በዚህ ጥቃት 70 በላይ ሚሊሺያዎች ዐድማ ብተናና መከላከያ አባለት ተጎድተዋል ሲሉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ግንቦት 28/2016 ዓ.ም Belete Kassa
1511Loading...
24
በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው ከነበሩ እስረኞች መካከል አስራ ዘጠኙ መፈታታቸው ተነገረ በአፋር ክልል በሚገኘው አዋሽ አርባ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በእስር ላይ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ጋዜጠኞች መካከል አስራ ዘጠኙ “የተሃድሶ ስልጠና’’ ከወሰዱ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቃቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በተመሳሳይ ቀን ሌሎች 20 እስረኞች ከአዋሽ አርባ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የእስረኞች ማቆያ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን እና ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። እስረኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ በዋነኛነት በአማራ ክልል እና እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ “በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ” ተፈጻሚነት እንዲኖረው ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ወደሚገኝ “መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ” የተወሰዱ እስረኞች ብዛት 53 መሆናቸውን አስታውቆ ነበር። ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የቀድሞ አባል የሆኑት መምህር ናትናኤል መኮንን፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ጋዜጠኛ አብነት ታምራት በአዋሽ አርባ በእስር ላይ እንዳሉ ማስታወቁ አይዘነጋም። ሆኖም መግለጫው ከወጣ በኋላ መምህር ናትናኤል እና ጋዜጠኛ አብነት ከእስር መለቀቃቸውን ማረጋገጡን በኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል የሪጅን ዳይሬክተር ሰላማዊት ግርማይ “ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በኢሰመኮ የነሐሴ ወር ሪፖርት ተጠቅሰው የነበሩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ስንታየሁ ቸኮል፤ ግንቦት 25፤ 2016 ከአዋሽ አርባ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደተዘዋወሩ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። “የኢትዮ ኒውስ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች የሆነው ጋዜጠኛ በላይም በቢሮው ስር ወዳለው የእስረኞች ማቆያ መዘዋወሩንም አክለዋል።
1570Loading...
25
Media files
1560Loading...
26
በአዲስ አበባ ከተማ፤ የአየር ብክለት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ጥናት አሳየ። ከአለም አቀፍ እና ከሀገር ውስጥ አየር ብክለት ስታንዳርድ መለኪያ አንጻር ሶስት እና አራት እጥፍ መጨመሩም ተነግሯል። በከተማዋ ከፍተኛ የአየር ብክለት መጠን የተፈጠረው በተለይ በተሽከርካሪ ጭስ፣ ከማገዶ ወይም ከከሰል እንዲሁም አግባብ ባልሆነ የቆሻሻ አወጋገድ የመጣ መሆኑም በጥናት ተመላክቷል። በከተማዋ አሁን ያለው የአየር ብክለትም ከፍተኛ ስጋት ከመሆን ደረጃ ላይ መድረሱም ተነግሯል። አሁን ያለው የአየር ብክለት መጠንም ከአለም አቀፍ የአየር ብክለት መለኪያም ባለፈ ከሀገር ውስጥ መለኪያም አልፎ 25% ጨምሯል ተብሏል። በዚህም በህብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑም ተነግሯል
1720Loading...
27
🔴🔴🔴 1) በወልዲያ ሦስት ቦታዎች የቦምብ ፍንዳታዎች ተፈጽመዋል ግንቦት 26/2016 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የቦምብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። በማዘጋጃ ቤቱ ም/ ኃላፊ መኖሪያ ቤት በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ቆስለዋል። በዞኑ ጽ/ቤት ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። 2) ጎንደር ቀጠና ጠዳ ጎንደር ዙሪያ በለሣ ጋይንት ክምር ድንጋይ ውጊያዎች ተደርገዋል። 3) ጎጃም ደጋ ዳሞት መራዊ ሜጫ አካባቢዎች ውጊያ ነበር 4) ሸዋ በተለያዩ ቦታዎች በመከላከያ ሰራዊት ላይ የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞ ከባድ ጉዳት ተስተናግዷል። ግንቦት 27/2016 ዓ.ም Belete Kassa
1630Loading...
28
የቤት አከራዮች ተከራዮችን ለማስወጣት የ2 ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጡ የሚያስገድደው አዋጅ ከሰኔ 1 ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 24 ቀን 2016 የጸደቀው 'የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016' ከሰኔ 1 ቀን 2016 ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገለጸ። አዲስ ማለዳ ከከተማ አስተዳደሩ ኮምኒኬሽን ቢሮ ባገኘችው መረጃ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ እንደገለጹት አዋጁ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር የተረጋጋ ፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሁም የአከራይ እና የተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለመፈፀም የተደነገገ ነው። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን ለመተግበር የሚያስችል ውይይት ተካሄዷል። ስድስት ክፍሎችና 32 አንቀጾች ያሉት አዋጁ በውስጡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ፣ የአስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተካተቱበት አዲስ ማለዳ ማዘገቧ አይዘነጋም። በተጨማሪም የቤት አከራዮች ቅድመ ክፍያ መጠየቅ የሚችሉት የሁለት ወር ብቻ እንዲሆን የሚደነግግ ሲሆን ተከራዮችን ለማስለቀቅም የሁለት ወራት የዝግጅት ጊዜ እንዲሰጥ ያስገድዳል። ከዚህ ባለፈም መንግስት ማግኘት\ ያለበትን ግብር እንዲያገኝ እንደሚያስችል የምክር አባላት ገልጸው ነበር። ነምቤኦ (NUMBEO) የተባለ በሰርቢያ አገር መቀመጫውን ያደረገ የአገራትን የኑሮ ደረጃ የሚመዝኑ መረጃዎችን የሚያጋራ ድረ ገጽ የአገራቱን ዜጎች ገቢ እና የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጥምርታን በማነጻጸር ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት የሚያወጡት ዋጋ ከገቢያቸው ላይ 43 ነጥብ 1 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል።
1530Loading...
29
Media files
1490Loading...
30
“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ ማመልከቻው በ15 ቀናት ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚያደርግ አዋጅ ነገ በፓርላማ ሊጸድቅ ነው “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ “በልዩ ሁኔታ” ለመመዝገብ ማመልከቻ ባቀረበ “በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ምዝገባው እንዲፈጸም” የሚያደርግ አዋጅ በነገው ዕለት ለፓርላማ ቀርቦ ሊጸድቅ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ መልኩ የቀረበለትን ማመልከቻ ውድቅ የማድረግ አማራጭ በአዋጁ ባይሰጠውም፤ በፓርቲው ላይ ለሁለት ዓመታት “ክትትል እና ቁጥጥር” የማድረግ ስልጣንን ግን ያገኛል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ምዝገባ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ምርጫ ቦርድ የሚኖረውን ስልጣን የሚወስኑ ድንጋጌዎች የተካተቱት፤ ይህንኑ በተመለከተ በ2011 ዓ.ም የጸደቀን አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ የህግ ረቂቅ ላይ ነው። “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ” የሚያሻሽለው ይኸው የህግ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ባለፈው አርብ ግንቦት 23፤ 2016 ነው። በሚኒስትሮች ምክር ቤት “በሙሉ ድምጽ” እንደጸደቀ የተነገረለት ይህ የአዋጅ ረቂቅ፤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑም በወቅቱ ተገልጿል። የተወካዮች ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራሩ ወጣ ባለ መልኩ፤ አዋጁ በተመራለት በሶስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ለውይይት እንዲቀርብ ቀጠሮ ይዟል። ምክር ቤቱ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 26፤ 2016 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው ከሚመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ ይኸው የአዋጅ ማሻሻያ እንደሆነ፤ ፓርላማው ለመገናኛ ብዙሃን በሚልከው የስብሰባ አጀንዳ ማሳወቂያ መልዕክቱ ላይ አስፍሯል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ለፓርላማ አባላት የተሰራጨው የአዋጅ ረቂቅ፤ በነባሩ አዋጅ የተካተቱ ሶስት አንቀጾች ላይ ብቻ ማሻሻያ የሚያደርግ ነው።
1611Loading...
31
Media files
1521Loading...
32
🔴🔴በአዲስ አበባ የተገደለው የ ፋኖ አመራር ሽኝት አስክሬን በሌለበት ጎንደር ውስጥ ተደረገ ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ የሽኝት ሥነ ሥርዓት #ጎንደር ውስጥ መፈጸማቸውን ተናገሩ። ፖሊስ በ #አማራ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው ያላቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ "የሽብር ድርጊት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሶባቸው መገደላቸውን" መግለጹ ይታወሳል። የሁለቱ ወጣቶችን ሞት ተከትሎ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ለፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጥያቄ ቢያርቡም ምላሽ ሳያገኙ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን ተናግረዋል። ዛሬ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብ እና በወዳጆች የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው የናሁሰናይ አንዳር ጌ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት በርካታ ሕዝብ ታድሞ እንደነበር አንድ የቤተሰብ አባል ተናግረዋል። የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት ሥነ ሥርዓትም በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት መግለጻቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
1570Loading...
33
Media files
1640Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
♦ ከግፍ እስር ተፈቷል! ከበርካታ ወራት የግፍ እስራት በኋላ በላይ በቀለ ወያ ከእስር ተፈቷል!
Show all...