cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Addis News

Advertising posts
462
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🔴🔴🔴ዜናዎች 🔴የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ረገድ መዘግየት እንደሚታይ ትናንት በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጀኔራል ታደሠ በሂደቱ ላይ መጓተት የሚታየው፣ መከላከያ ሠራዊት ሊሠራው የሚገባውን ሥራ ባለመስራቱ እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ኾኖም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮችን በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ወደ ቀያቸው ለመመለስ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀና የጋራ ማስፈጸሚያ እቅድ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል ተብሏል። ጀኔራል ታደሠ፣ መከላከያ ሠራዊት "በኃይል በተያዙ" አካባቢዎች የተቋቋሙ ሕገወጥ አስተዳደራዊ መዋቅሮችን የማፍረስ፣ የታጠቁ ሃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ ምቹ ኹኔታዎችን የመፍጠርና ሕገወጥ ሠፋሪዎችን ወደመጡበት የመመለስ ኃላፊነት አለበት ማለታቸውንም ዘገባዎቹ ገልጸዋል። 🔴ኡጋንዳ፣ የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል የኬንያዋን ላሙ ወደብ ለመጠቀም ፍላጎት እንዳላት መግለጧን የኬንያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኡጋንዳ ፍላጎቷን የገለጠችው፣ ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይነው። ማዳበሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በላሙ ወደብ በኩል ከሳምንት በፊት ባስገባች ማግስት ነው። ኾኖም በኬንያ በርካታ ግዛቶች የተከሰተው ከባድ ጎርፍ ከላሙ ወደብ ወደ ሞያሌ የሚወስደውን መንገድ በመቁረጡ፣ ኢትዮጵያ ማዳበሪያውን እስካሁን ማጓጓዝ አልቻለችም። ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ዓመት ብቻ በሌላኛዋ ሞምባሳ ወደብ በኩል ከ14 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ካርጎዎችን ማስገባቷን ዘገባዎች ያመለክታሉ። 🔴የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግብዣ የሦስት ቀናት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። የፕሬዝዳንት ሩቶ እና ፕሬዝዳንት ባይደን ውይይት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ ዲሞክራሲ፣ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ እንደሚኾን የኬንያ መንግሥት ገልጧል። ፕሬዝዳንት ሩቶ ጉብኝቱን የሚያደርጉት፣ የኬንያንና አሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 60ኛ ዓመት በማስመልከት ነው። የአሜሪካ ኮንግሬስ አፈ ጉባዔ፣ ፕሬዝዳንት ሩቶ ለኮንግሬሱ የጋራ ስብሰባ ንግግር እንዲያደርጉ እንዲጋብዟቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተወካዮች ግፊት አድርገው የነበረ ቢኾንም፣ አፈጉባዔው ግን ግብዣውን ውድቅ ማድረጋቸው አይዘነጋም። 🔴ደቡብ ሱዳን፣ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥትንና አማጺውን የሱዳን ነጻ አውጪ ሠራዊት ለማደራደር በምታደርገው ጥረት ውስጥ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ጣልቃ ገብታለች መባሉን ደቡብ ሱዳን አስተባብላለች። ሱዳን የደቡብ ሱዳንን አሸማጋይነት የጠየቀችው፣ በብሉ ናይል እና ደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች መንግሥትን ከሚዋጋው አማጺ ቡድን ጋር ተኩስ አቁም ለማድረግ ነው። ሱዳን ተኩስ አቁሙን የፈለገችው፣ በየብስ እና አየር በግዛቶቹ ለሚኖሩ የጦርነት ተጎጂ ሱዳናዊያን ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ እንዲቻላት እንደኾነ ገልጣለች። ይህንኑ ተከትሎ፣ ደቡብ ሱዳን የሽምግልና ሂደቱን ለጥቂት ቀናት ማቋረጧን አስታውቃለች። ሱዳን፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል ወታደራዊ ድጋፍ ታደርጋለች በማለት ትከሳለች።.
Show all...
የሊቢያው ፓን - አፍሪካኒስት ሞአመር ጋዳፊ ህልፈት በአሜሪካ እና NATO ሴረኛ ዘመቻ በፈረንጆቹ 1951 ሊቢያ ከዓለማችን ድሃ ሀገር ውስጥ አንዷ ነበረች። ጋዳፊ በዘመኑ ስልጣኑ፣ ሀገሪቱን የ 150 ቢሊዮን ዶላር የምንዛሪ መጠባበቂያ በማስቀመጥ፤ ሊቢያን ከማንኛውም ዕዳ ነፃ አድርጎ በአፍሪካ የቀዳሚ ኢኮኖሚ ባለቤት ሀገር አድርጓት ነበር። በሙአመር ጋዳፊ ዘመነ ስልጣን የሊቢያ ከአለማችን እጅግ ጠንካራ የመገበያያ ገንዘቦች መካከል አንዱ ማድረግ ችሎ ነበር። 1 የሊቢያ ዲናር በፈረንጆቹ 2011 የነበረው ዋጋ 0.82781 የአሜሪካ ዶላር ነበር - የ 20 ሳንቲም ብቻ ብልጫ። ጋዳፊ የሁሉንም አፍሪካዊ ሀገራት ኢኮኖሚ ለማጠናከር ይህንኑ ዲናር ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር። በዚህም ከ 140 ቶን በላይ ወርቅ፥ ተመሳሳይ መጠን ያለው የብር መጠን በማዘጋጀት በአህጉረ አፍሪካ ውስጥ ለንግድ እንዲውል እየሰራ ነበር። ታዲያ አሜሪካ - መራሹ የሀገራት ጥምረት የጋዳፊን መንግስት በማስወገድ ሊቢያን የመከራ ምድር ከማድረጋቸው በፊት ሞአመር ጋዳፊ በሀገሪቱ ያሰፈኑት ምቾት ምን ይመስል ነበር? 1. የሊቢያ ዜጎች ለመብራት አገልግሎት bill አይከፍሉም። የመብራት አገልግሎት ከሊቢያ መንግሥት በነፃ ያገኙ ነበር። 2. ሊቢያዊያን ከባንክ ብድር ሲቀበሉ ከወለድ ነፃ እንዲሆን ይደረግላቸዋል። 3. በሊቢያ መኖሪያ ቤት እንደ ሰብዓዊ መብት ይቆጠራል፥ ለዜጎች በነፃ ነበር የሚሰጣቸው። የመአመር ጋዳፊ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙት የሀገሪቱ ዜጎች ካገኙ በኋላ ነዉ የሚሰጣቸው። የጋዳፊ እናትና አባት በክራይ ቤት እያሉ ነበር የሞቱት። ምክንያቱም ሁሉም ሊቢያዊያን ቤት እስኪያገኙ ድረስ የጋዳፊ ቤተሰቦች እንዲሁም ዘመዶች ቤት እንዲያገኙ አይፈቀድምና መጠበቅ ስለነበረባቸው ። 4. ለመጀመሪያ ጊዜ ጋብቻ የሚፈፅሙ ጥንዶች $60,000 የአሜሪካ ዶላር ከመንግስት ይሰጣቸዋል። ይህም ቤት እንዲገዙና ህይወታቸዉን ከጥገኝነት ተላቀዉ እንድጀምሩ ይረዳቸዋል። 5. የትምህርትና ህክምና ወጪ ለሁሉም ዜጎች በመንግሥት ይሸፈናል። ከሞአመር ጋዳፊ በፊት በሀገሪቱ የተማረ ዜጋ ብዛት 25 በመቶ ነበር። በጋዳፊ ጊዜ ይህ አሃዝ ወደ 83 በመቶ ማደግ ችሏል። 6. ሊቢያዊያን በግብርና ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ከፈለጉ የእርሻ መሬት፣ ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የመስሪያ ቦታ፣ የእርባታ እንስሳት እንዲሁም ትራክተር እና መሠል ለእርሻ ሥራ አስፈለጊ ግብዓቶችን መንግሥት በነፃ ያቀርብላቸዋል ። 7. ሊቢያዊያን ትምህርትና ህክምና በቀላሉ ለማግኘት በማይችሉበት ቦታ ከሆኑ ከዛ አካባቢ ወደ ፈለጉበት ሌላ ቦታ ሄደዉ እንዲማሩና እንዲታከሙ ይደረጋል። በሄዱበት ቦታ መኪና እንደፍላጎታቸው እንደጠቀሙ መንግስት ያዘጋጅላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በዬወሩ $2,300 ዶላር ክፍያ ያገኛሉ። 8. በጋዳፊ ዘመን መኪና ለመግዛት የሚፈልግ ሊቢያዊ ዜጋ የ 50 ቅናሽ/ድጎማ ይደረግለታል ። 9. በጋዳፊ የአስተዳደር ዘመን አንድ ሊትር ነዳጅ ሊቢያ ውስጥ በ $ 14 ሳንቲም ዋጋ ነበር የሚሸጠው። 10. ሊቢያ ምንም አይነት የዉጭ ሀገርም ሆነ የ IMF - World Bank ብድር ወይም ዕዳ የለባትም ነበር። በሊቢያ መንግሥት ካዝና $150 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሪዘርቭ ነበራት። ከጋዳፊ ህልፈት በኋላ ይህን ገንዘብ የአለም ባንክ world bank ወርሶታል። 11. ከዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ የተመረቀ ዜጋ በተማረበት መስክ ሥራ እስኪገኝለት ድረስ ደሞዝ ይከፈለዋል ። ደሞዝ እያገኘ ሥራውን ይፈልጋል ። 12. ሊቢያ በነዳጅ ሀብት የታደለች ሀገር ናት። መንግሥት ነዳጅ በሸጠ ቁጥር ለሁሉም ሊቢያዊ ዜጎች ከነዳጅ ሽያጩ በተገኘው ገቢ ተሰልቶ ገንዘብ በአካውንታቸው ገቢ ይደረግላቸዋል። 13. አንዲት እናት ስትወልድ ለራሷና ለልጇ መንከባከቢያ የሚሆን $5000 ዶላር ይሰጣታል ። 14. (በፍሬ) የአርባ ዳቦ ዋጋ በ $0.15 ሳንቲም ነበር የሚሸጠዉ። 15.በጋዳፊ ጊዜ ከዩኒቨርሲቲዎች በዲግሪ የተመረቁ ዜጎች ቁጥር 25 ደርሶ ነበር። 16. ጋዳፊ በአለማችን ግዙፍ የሆነውን የመስኖ ፕሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ አድርጎ ነበር። ይህ ሰው ሰራሽ ወንዝ በሀገሪቱ በረሀማ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች እንዲጠቀሙበት የታለመለት ሲሆን ስሙም "The Great Man Made River" የተሰኘ ነው NB: ከሞአመር ጋዳፊ ሞት ወዲህ ሊቢያ እንደ ሀገር ፈራርሳለች። የአሸባሪዉ ISIS መፈንጫ ሆናለች። እስካሁንም ድረስ የሀገሪቱ ዜጎች እንደተጎሳቆሉ፣ እንደተሰቃዩ ነው የሚገኙት። በሀገሪቱ ከሁለት በላይ መንግስታት ተፈጥረው ሀገሪቱን ተከፋፍለው እየገዟት ነው የሚገኘው። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመናቸው ካበቃ በኋላ ባደረጓቸው ቃለ ምልልሶች ላይ ተከታዩን ተናግሮ ነበር፤ "በስልጣን ዘመኔ ጋዳፊ እንዲገደል እና ሊቢያ እንድትፈርስ ማድረጌ ይፀፅተኛል" - ባራክ ኦባማ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🔴🔴ዜናዎች 🔴መንግሥት፣ ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው የተሻሻለ ረቂቅ የግብር አዋጅ፣ በኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ቴሌኮምንኬሽን፣ ትራንስፖርትና ኢ-ኮሜርስ አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ለመጣል የሚያስችል እንደኾነ ሪፖርተር ዘግቧል። ረቂቅ አዋጁ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪዎችንና ከስምንት መቀመጫ በታች ያላቸውን የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክሱ ነጻ እንዳደረጋቸው ዘገባው አመልክቷል። ባጃጆች ግን ተጨማሪ እሴት ታክስ ውስጥ እንዲታቀፉ ረቂቅ አዋጁ ደንግጓል ተብሏል። ኾኖም በውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ላይ የሚጣለው ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የመክፈል አቅም ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ተፈጻሚ እንዲኾን ለማድረግ ገንዘብ ሚንስቴር ዝርዝር ደንብ ያወጣል መባሉን ዘገባው አመልክቷል። 🔴በራያ አለማጣ ወረዳ ሰብዓዊ ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ባለሥልጣናት መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። ሰብዓዊ ቀውሱ የተባባሰው፣ በተለይ የጤና አገልግሎቶች በመቋረጣቸው እንደኾነ ባለሥልጣናቱ እንደተናገሩ ዘገባው አመልክቷል። የአላማጣ ከተማ ሆስፒታል ለአንድ ወር ያህል አገልግሎት ያቋረጠ ሲኾን፣ የሕክምና አገልግሎት በማጣት ስምንት ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ የከተማዋ ከንቲባ ኃይሉ አበራ ተናግረዋል ተብሏል። አላማጣ ከተማ፣ ራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ እና ኮረም ከተማ አካባቢ ከሚገኙ 123 ትምህርት ቤቶች፣ ከ42 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑም ተገልጧል። 🔴የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንደገና በዘመናዊ መንገድ አስፋፍቶ ያስገነባውን የአገር ውስጥ ተርሚናል ዛሬ አስመርቋል። አየር መንገዱ ለተርሚናሉ 50 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣ የገለጠ ሲኾን፣ የተርሚናሉ ስፋት በኹለት እጥፍ ጨምሮ ወደ 25 ሺሕ 750 ስኩዌር ሜትር ማደጉን አየር መንገዱ ገልጧል። 22 የመንገደኞች ትኬት ማረጋገጫዎች ያሉት ተርሚናሉ፣ በቀን ከ22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎቹ 200 በረራዎችን የማስተናገድ አቅም አለው። አየር መንገዱ ተርሚናሉን በዘመናዊ መንገድ ያስፋፋው፣ ተጨማሪ የአውሮፕላን ማረፊያዎች የመገንባት እቅድ ስላለና የአገር ውስጥ ተጓዦቹ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ በመጨመር ላይ በመኾኑ እንደኾነ ዛሬ ባሠራጨው መግለጫ ገልጧል። አየር መንገዱ በቅርቡ ወደ ደሚቢዶሎ በረራውን እንደገና የጀመረ ሲኾን፣ ከመጭው ሰኔ ጀምሮ ደሞ ለሦስት ዓመታት ያቋረጠውን የአክሱም በረራ እንደሚጀምር መግለጡ አይዘነጋም። 🔴የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ፣ የአፍሪካ ኅብረትን ጦር እስከ ቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ድረስ ከሱማሊያ ጠቅልሎ ለማስወጣት የተያዘው እቅድ እንደገና እንዲከለስ ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ፣ የኅብረቱን ጦር ሙሉ በሙሉ የማስወጣቱ እቅድ ከአገሪቱ ነባራዊ የጸጥታ ኹኔታ ጋር መጣጣም እንዳለበት ከሙሴቪኒ ጋር ተስማምተናል ብለዋል። ኬንያና ኡጋንዳ ባኸኑ ወቅት በኅብረቱ ተልዕኮ ሥር በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሏቸው። ሩቶና ሙሴቪኒ የኅብረቱን ጦር የማስወጣቱ እቅድ እንዲከለስ የጠየቁት፣ አልሸባብ ነጻ የወጡ አካባቢዎችን መልሶ እየተቆጣጠረ በመኾኑ እንደኾነ ሩቶ ገልጠዋል። ኅብረቱ ከወራት በፊት 5 ሺህ ወታደሮችን ከአገሪቱ ያስወጣ ሲኾን፣ በቀጣዩ ሰኔ 4 ሺህ ተጨማሪ ወታደሮችን ለማስወጣት አቅዷል። ሱማሊያ፣ ከኅብረቱ ጦር መውጣት በኋላ ለቁልፍ ተቋማት ጥበቃ የሚያደርግ ሌላ ኅብረ ብሄራዊ ተልዕኮ እንዲሠማራላት ትፈልጋለች።
Show all...
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ፐርፐዝ ብላክን አሰናብቷል። በአዲስ አበባ ሜክሲኮ የሚገኘውን የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በ 1 ቢሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን ገልጾ ነበር። ፐርፐዝ ብላክ ለቢጂአይ ክፍያውን ሳይፈፅም፣ ባለ 3 መኝታ ቤት በ1.5 ሚልዮን ብር ብቻ ገንብቼ አቀርባለሁ በማለት በአክሲዮን ስም ከሕዝብ ገንዘብ ሲሰበስብ እንደነበር የሚታወስ ነው። ከወቅታዊ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አንፃር እቅዱ ፈፅሞ የማይመስል እንደነበር በወቅቱ በዘሐበሻ መዘገባችን ይታወሳል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍሰሃ እሸቱ የዘሐበሻን ዘገባ በማጣጣል ጋዜጣዊ መግለጫ ቢሰጡም እውነታው አሁን ገሀድ መውጣቱ አልቀረም። ፐርፐዝ ብላክ ሙሉ ግዢ ሳይፈፅም ልተገብረው ነው ብሎ ከተናገረው የገበሬው ታወር ሼር ሆልደር ሞዴል ህንጻ ብዙ ውዝግቦች አስነስቶ የቆየ ሲሆን በመጨረሻ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ እልባት አግኝቷል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከፐርፐዝ ብላክ የወሰደውን ቀብድ በመመለስ መሬቱን ወደ ራሱ አዙሯል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን የግዢ መቋረጥ ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል። አሁን ሚነሳው ከህዝብ በሀሰተኛ መረጃ የተሰበሰበው ገንዘብ እንዴት ሊሆን ነው? የሚለው ጥያቄ ነው። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍሰሃ እሸቱ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ግዙፍ ህንፃ ልገነባ ነው በሚል በመኖሪያ ቤት ስም ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማሸሽ ለሌላ ጉዳይ እንዳዋሉት በስፋት እየተነገረ ይገኛል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ "ውንጀላ አቅርበዋል"፤ "መንግሥት አገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለበትም ያልተጠየቁትን ምክር ለግሰዋል" በማለት ወቅሷል። የአምባሳደሩ ንግግር "ትርጉም የማይሰጡ" እና "በበቂ ኹኔታ ያልተጤኑ" ሃሳቦችን ያካተተ ነው ያለው ሚንስቴሩ፣ አምባሳደሩ "በምርጫ የተመረጠውን መንግሥት በኃይል ለመጣል የሚሠሩ ቡድኖችንም በስም ጠቅሰዋል" በማለት ተችቷል። ኢምባሲው፣ በአምባሳደሩ መግለጫ ላይ የተንጸባረቁትን "የፍሬ ነገር ስህተቶች" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ ገልጧል። አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት የመን የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ውስጥ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በሲቪሎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳይ በመጥቀስ "አገር ዓቀፍ የተኩስ አቁም" እንዲደረግ ጠይቀው ነበር። ዋዜማ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
♦ "በተፈናቃዮች ብር የተሰራው ሆቴል" የዛሬ 7 ዓመት አካባቢ ከሱማሌ ክልል የሃረርጌ ኦሮሞዎች ይፈናቀላሉ። በዚህ ምክንያትም ለወገን ደራሽ ወገን ነው በማለት የቶምቦላ ሎተሪ ተዘጋጅቶ በኦሮሚያ ከክልል እስከ ቀበሌ ተሸጠ። የዚህ ሎተሪ ኮሚቴዎች መሀከል ደሞ በምስሉ ላይ የሚታየው ሞቲ ሞረዳ ነው።( ቀሲስ በላይም እንዳሉበት ተነግሯል) ለማንኛውም ይሄ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የተሸጠ ሎተሪ እጣው ሳይወጣ ደብዘው ከጠፋ 7 ዓመት ሆነው። ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ሆኖ ሰንብቷል 😜 ገንዘቡ የተሰበሰበው በክልሉ መንግስት መዋቅር እና አስተባባሪነት እንደሆነ ልብ ይሏል።ለማንኛውም ከኮሚቴዎቹ አንዱ የሆነው ጀለስ የግዜው ሰው ሞቲ በተፈናቃዮቹን ስም የተሰበሰበውን ገንዘቡን አምስት ሳንቲም ሳያጠፋ ቦሌ ላይ ይሄን መሰል ቅንጡ ሆቴል ከፍቷል። እልልልልልልልልላልልልል በሉ የኦሮሞ ህዝብ ልጅህ ገንዘቡን አላጠፋም 😜 በማለት ሃኒ Hanna R Waktolaa መረጃውን ወዲህ ብላላች ! እኛም ፤ እልልልልልልልልላልልልል ብለናልና የግዜው ሰው ሞቲ 🙊
Show all...