en
Feedback
Kamil_official

Kamil_official

Open in Telegram

. 'የሚያካፍሉት ትንሽ እውቀት ከማያካፍሉት ብዙ እውቀት በእጅጉ ይበልጣል።' ዶ/ር ሙስጦፋ #ለአስተያየት * @Kamil_official2 t.me/kamil_official .

Show more
2 756
Subscribers
No data24 hours
-67 days
-4230 days
Posts Archive
በዚህ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን የዩቲዩብ ገፅ የሚታላለፉ ኢስላማዊ ዕውቀቶች ከርስዎም አልፎ ለሌሎች እንዲደርስ ሰብስክራይብ ብሎም ላይክና ሼር በማድረግ ለሌሎችም በማስተዋወቅ ከኢስማዊ ዕውቀት ማንም እ
በዚህ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን የዩቲዩብ ገፅ የሚታላለፉ ኢስላማዊ ዕውቀቶች ከርስዎም አልፎ ለሌሎች እንዲደርስ ሰብስክራይብ ብሎም ላይክና ሼር በማድረግ ለሌሎችም በማስተዋወቅ ከኢስማዊ ዕውቀት ማንም እንዳይቀር የበኩሎን ያድርጉ! ይህን ገፅ 100.000 የማስገባት ሂደት ሰብስክራይብ አድርገው ሌሎችንም በማስደረግ ይቀላቀሉ፡፡ https://www.youtube.com/@sheikhmohammedhamiddinoffic017

🧡🍂🧡🍂🧡🍂🧡🍂🧡🍂🧡🍂🧡🍂🧡🍂 💡አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ብሏል፦ 🧡{{يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوۡمِ ٱلۡجُمُعَةِ فَٱسۡعَوۡاْ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَذَرُواْ ٱلۡبَيۡعَۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ}} 💡{{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጁመዐ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ አላህ ወደሚወሳበት ሂዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡}} 🧡{{فَإِذَا قُضِيَتِ ٱلصَّلَوٰةُ فَٱنتَشِرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ}} 💡{{ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡}} [አል ጁመዐ: 9 እና 10] 🤲ያ አላህ ከሚድኑት ባሮችህ አድርገን🥺……🧡 🧡🧡🧡መልካም ጁመዐ🧡🧡🧡

🥰🥹🥰ስለየትኛው ኒዕማህ እናመስግንህ.....🥹🥰🥹 🥰በዚህ ምርጥ ቀን አዲስ ጀንበርን…አዲስ ጅማሮን... ስላሳየኸንና ስላስጀመርከን💚 ....ወይስ….. 🥰የምሽት ወንጀላችንን ደብቀህ...ዛሬን እድል ስለሰጠኸን💚 .....ወይስ….. 🥰ለሊት ላይ ወደቅርቢቱ ሰማይ ወርደህ የቀን ወንጀላችንን ለመማር ስለምጠራን💚……ወይስ…… 🥰በስንዝር ስንቀርብ እየፈጠንክ በክንድ ስለምትቀርበን💚 ……ወይስ…… 🥰ስንጠይቅህ እምቢ ማለትን በባዶ መመለስን ስለምታፍረው💚 ……ወይስ…… 🥰በአንድ መልካም ስራ አስር አጅር ስለምትከፍለን💚 ……ወይስ…… 🥰በፈራንህ ልክ ልባችንን በፍቅረህ ስለምትሞላው💚…… ወይስ…… 🌞ፀሀይ ከወጣችበት ምርጡ ቀን ጁመዐ 🌱የጠየቅነውን መሰጠትን የተረጋገጠልን ቀን 🌱ጀነት የተፈጠረበት ቀን 🌱የሰው ልጆች ጀነት የሚገቡበት ቀን 🌱በአንድ ሰለዋት ስማችን ሀቢቡላህﷺ ዘንድ የሚጠራበት ና የአላህ 10 ሰለዋት የሚወርድብን ቀን… 🥰……ወይስ…… እነዚህ ሁሉ ኒዕመዎች በአንድ ላይ በተሰበሰቡበት ቀን ሙስሊም አድርገህ ስላነቃኸን💚…… …ስለይተኛው ፀጋህ ያ ረህማን……?! 💚🥰ለከል ሃምዱ ያ ረቢ.....ሀምደን ዩዐፊ ኒዕመሁ ወየካፊኡ መዚዳ🥹💚 💚ያ አላህ አንተን መፍራትና ማፍቀርን ወፍቀን፤ ለልባችንን ከሁሉም ነገር የበለጠ ተፈቃሪ አስክትሆን🤲 💚ያ አላህ! የክብር ሀገር የሆነችውን ጀነት ያለ ሂሳብና ያለ ቅድመ ቅጣት ከሚገቡት አድርገን🤲 💚ባርያም ለሰላት በቆመና አላሁአክበር ባለ ቁጥር በፍጥረታቱም ብዛት ልክ የአላህ ሰላምና ውዳሴ በውዱ ነብይﷺ ላይ ይስፈን🤲💚           🌱💚🌱መልካም ጁመዐ🌱💚🌱

🥹🤗🥹🤗🥹🤗አልሀምዱሊላህ🥹🤗🥹🤗🥹🤗 🍃ምስጋና በችሮታው መልካም ነገሮችን ለሚሞላ ጌታ🥰 🌱ከአመት እስከ አመት…… 🌱ከሳምንት እስከ ሳምንት…… 🌱በቀን ውስጥ ከሰላት እስከ ቀጣዩ ሰላት…… ከወንጀላችን መጥራሪያን ላደረገልን ጌታ ምስጋና ይገባው☺️ 🌼እኛን ለመማር ወንጀላችንን ይቅር ለማለት ሰበቦችን ያበዛ ጌታ ምስጋና ይገባው!!🥹 🍃አልሀምዱሊላህ! ከሳምንት ወንጀላችን ማበሻ በሆነው ቀን ላይ ሙስሊም አድርጎ ላነቃን ጌታ🥰 🌼ከቀኖች ሁሉ ምርጡ ቀን በሆነው ጁመዐ!!!… 🌱ሰለዋት ባልን ቁጥር ስማችን ረሱልﷺ ዘንድ ተደጋግሞ በሚጠራበት ቀን 🤗 🌱አንድ ሰለዋት ስንል አላህ እኛን አስር ጊዜ የሚያወድስበት ቀን 🥰 🌱የጠየቅነውን ነገር መስጠቱ የተረጋገጠበት ሰዐት ባላት ቀን ላይ ሙስሊም አድርጎ መልካም ነገሮችን የሞላልን አላህ ምስጋና ይገባው🤗🥰 🌼ጌታዬ ሆይ! ለልዕልናህ እና ለግርማዊነትህ የሚመጥን ምስጋና ለአንተ የተገባ ይሁን🥹 🍃የአላህ ሰላምና ውዳሴ አላህን ማመስገንን ባስተማሩን ለሰው ልጅ ብርሀን በሆኑት ውዱ የአላህ መልዕክተኛﷺ ላይ ይስፈን🥰 🍃🤗🍃መልካም ጁመዐ🍃🤗🍃

🌊💪🌊💪🌊"ዐሹራ" አሸናፊነት🌊💪🌊💪🌊 የአሹራ ፆም 10ኛው  ቀን ነገ ማክሰኞ ስለሆነ  በመፆም እንበርታ!!! “የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።” ነቢዩ (ሰ•ዐ•ወ) 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 🤲አላህ አሹራን ፆመው ወንጀላቸውን ከሚምርላቸው ሰዎች ያድርገን!!! በመልካም ዱዐቹ አስታውሱኝ🥺🙏

☘🤍☘🤍የአመቱ የመጨረሻ ጁመዐ🤍☘🤍🍀 🎍{خير الناس من طال عمره، وحسن عمله.} ☘ከሰዎች ሁሉ መልካማቸው እድሜው ረዝሞ ስራው ያማረለት ሰው ነው። (رسول الله  ﷺ) 🎍ሁሌም ቢሆን ባለቤት በሆንበት ጊዜ "አሁን" ላይ ተውበት ማድረግና ኸይር ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ☘ስለትላንት ወንጀሎቻችን ተውበት በማድረግ ይቅርታውን በመጠየቅ… 🎍አሁን ደግሞ ስራችንን በማሳመር ላይ በመበርታት… ☘በኃላ በአላህ እጅ ነው መድረሳችን አይታወቅም… 🎍ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ወደአላህ መመለስ ላይ መዘውተር አለብን።👍 ☘ባሪያዎችህን በጥበብህ ወደራስህ የምትመልስ ጌታ🥹 🎍የዩኑስን (ዐ.ሰ) ህዝቦች በጥበብህ ወደራስህ ያማረ መመለስን እንደመለስካቸው… ☘ያ ሀኪም..... እኛንም በጥበብህ ወዳንተ ያማረ መመለስን መልሰን🥺🤲 🎍አንተ ጥበበኛ የሆንከው ጌታ "በጥበብህ"… በማለት እንበርታ👍 ☘በአመቱ ጁመዐዎች ያደረግናቸውን ዱዐዎች ሁሉ አላህ ይቀበለን፤ 🎍በአመቱ ውስጥ በተሰጡን መልካም እድሎች ከተጠቀሙበት፤ ☘ኢባዳቸውንም ከተቀበላቸው መልካም ነገራቸው ከባለፈው አመት ከጨመረላቸው፤ መጥፎ ነገራቸውም ከቀነሰላቸው፤ 🎍ሁሌም ወደሱ ተመላሾች ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን!!🥺🤲 ☘🤍☘መልካም ጁመዐ☘🤍☘

♥️♥️♥️الصَلاةُ عَلى النَبِي ﷺ♥️♥️♥️ 📌 ወንጀልን ከሚያሥምሩ እና ሀሳብ እና ጭንቀት ከሚያስወግዱ ነገሮች መካከል በአላህ ነብይ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ ትልቁ ነው። ♦️ጁሙዐ ቀን ሲሆን ደግሞ ሰለዋት ማብዛት     ይወደዳል። 🖍የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) እርሳቸው ላይ ሰላት የሚያወርድን ሰው የሚከተለውን ብለዋል:–                     ♦️(تُكْفِى هَمَكْ وَيُغْفَرُ لَكَ ذَنْبَكْ) ♦️{{ ለሚያሳስብህን ነገር አላህ ይበቃሀል ወንጀልህም ይማራል}} ♥️የአላህ ሰላምና ወዳሴ በዚያ ፍቅሩ ልቦችን በሚያረጋጋው 🥀አይኖችም እሱን ለማየት በሚናፍቁት ወዱ ነብይ ላይ ይስፈን🥰 ♥️صَلُّوا عَلى خَيْرِ الاَنَامِ المُصطَفَى بَدرِ التَّمَامِ❣ ♥️صَلُّوا عَلَيهِ وَسَلِّمُوا يَشفَـع لَنَا يَومَ الزِّحَامِ❣                ♥️❣♥️መልካም ጁመዐ♥️❣♥️

🌅🌞🌅🌞🌅🌞ንጋት🌅🌞🌅🌞🌅🌞 🍁የስኬት ፣የብሩህ ተስፋ ፣ የመከራ መወገድ ተምሳሌት ነው ፤የንጋቶች ሁሉ አውራና ምርጡ ደግሞ ጁሙዐህ ነው ፣ በውስጣችን ያለው የ ነቢ ውዴታ ዘር እንዲያብብ እና እንዲለመልም ፣ በርሳቸው ላይ ውዳሴና ሰላም ይሰፍን ዘንድ አብዝተን መለመን ከኛ ይጠበቃል ፤ 🍂 የዛሬን ሰለዋት ለየት የሚያደርገው በቀጥታ ነቢ ጆሮ የሚደርስ መሆኑ ነው 🍂 🧡ዘንጊዎች በዘነጉ፣አስታዋሾች ባስታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት ልክ፣ከበረሀው አሸዋ የበረከተ፣ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ ሰላም እና ውዳሴ ባንቱ ላይ ይስፈን ያ ረሱለላህﷺ🥰 🧡🤎🧡መልካም ጁመዐ🧡🤎🧡

🥳🤍🥳🤍عيد الله عليكم مبارك!!!🥳🤍🥳🤍 🤍تقبل الله طاعتنا!!! 🍃وتجاوز تقصيرنا!!! 🤍وستجاب داعوتنا!!! 🍃‏ أعاده الله علينا وعليكم بالخير والبركه♥️.

🤍🕊🤍🕊🤍🕊🤍🕊🤍🕊🤍🕊🤍🕊🤍 🕊ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹የአረፋን እለት(ዙልሂጃ 9) የፆመ ሰው ያለፈውን የአንድ አመትና የሚመጣውን የአንድ አመት ወንጀሉን ያስምርለታል ብየ እከጅላለሁ››። ብለዋል (ሙስሊም) 🤍የነገው ውድ ቀን (የዙልሂጃ 9ኛው ቀን) ለወንጀላችን ምህረት የምንጠይቅበት፣ከእሳት ነጃ እንዲያወጣን አልቅሰን የምንማፀንበት ፣ ሃገራችንን እና አለማችንን ሰላም እንዲያደርግልን የምንለምንበት፣ ላስጨነቀን ሁሉ ነገር መፍትሄ ለማግኘት አላህን የምንማጸንበት ቀን ነው፡፡ 🕊ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) " በላጩና ምርጡ ዱዓ በዐረፋ ቀን ውስጥ የተደረገ ዱዓእ ነው"።(ቲርሚዚ) ለበይክ❕የደከመች ነፍስ ወዳንተ ትንበረከካለች፤ ለበይክ❕በአንተ ብቻ ሊድን በሚችል ስብራት እና ቁስል፤ ለበይክ❕አይንም በእንባዋ ማእበል ተውጣ ወዳንተ ቅሬታዋን ታሰማለች ፤ ለበይክ❕ልባችን በሀዘን ተሞልታለች ከአንተ ውጪም መፍትሄ የላትም፤ ለበይክ❕የሐሰት ሳቃችንን ፣ የደከሙ አካሎቻችንን እና በአይናችን ዙሪያ ያለን ጨለማ አንሳልን፤ ለበይክ❕ድክመት ወደ ነፍሳችን መድረሱን እና ሽበትም በድምፃችን ላይ ግልፅ ነው ፤ ለበይክ❕ቸርነትህን እንሻለን፣ቅርብ የሆነውንም እርዳታህን ለበይክ❕በስምህ እንለምንሀለን ፤ ለበይክ❕እኛ ፈሪዎች ነን ደህንነትም ካንተው ነው፤ ለበይክ❕ካንተ ለሚመጣ ነገር ሁሉ ምስጋና ላንተ የተገባ ይሁን፤ ለበይከ ረቢ❕የደስታ ዝናብ ከሰማይይህ በእኛ ላይ አውርድ። 🤍ለበይከላሁመ ለበይክ! 🤲🏻🕊

🥰♥️🥰♥️{فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ}🥰♥️🥰♥️🥰♥️🥰 ♥️[እስታውሱኝ አስታውሳቹሀለው!!!] 🥰ምን ያለ መታደል ነው በፍጥረተ አለሙ ገዢ ከሰባት ሰማይ በላይ በሰማይ ቀበሌ ከመላዕካን ጋር መታወስ🤗 ♥️አላህ! ያ የነገራት ሁሉ አስገኚ የሆነው ጌታ በሱ መታወስ እንዴት ያስደስታል ነው🥰🤗 🥰ዛሬ ከቀናት ሁሉ አውራ እና ምርጡ ቀን ጁመዐ♥️ ♥️አላህ ከማለባቸው አስሩ ቀን 8ኛው የውሙ ተርዊያህ🥰 🥰{وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَعْلُومَاتٍ} ♥️[በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ] 🥰በነዚህ ቀናት ውስጥ "ተክቢር" "ተህሊል" እና "ተህሚድ" አብዙ የተባለበት ቀን♥️ 🥰በእኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያለ (1 ጊዜ ያወደሰኝ) አላህ በሱ ላይ 10 ሰለዋትን ይላል (10 ጊዜ ያወድሰዋል)🤗 ♥️በአላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ መወደስ ሲሆን ደግሞ እንዴት ይለያል🥰🤗 🥰ንጉሰ ነገስት የንግስና ባለቤት ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘን አላህ♥️…… ያወድሰናል🤗 ♥️የእድለኝነት ቀን በአላህ መታወስና መወደስን 🥰ስማችን ረሱልﷺ ዘንድ መጠራትን ♥️ሰለዋታችን በቀጥታ ነቢ ጆሮ መድረስን የታደልንበት ቀን ነው። 🥰🤲አላህ እሱን በማስታወስ የሰማይ ቀበሌ ላይ ባርያዬ አሰታወሰኝ እያለ ከሚኮራባቸው ባርያዎቹ ያድርገን🥹 ♥️የአላህ ሰላምና ውዳሴ በተከቢራዎቹ ብዛት ልክ እሱን ማወደስን ባስተማሩን ውዱ የአላህ ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰 🥰♥️🥰መልካም ጁመዐ🥰♥️🥰

🌾🌞🌾🌞🌾🌞🌾🌞🌾🌞🌾🌞🌾🌞🌾🌞 🍂አላህ የማለባቸው አስሩ ውድ ቀናት መጡ…🥰 🌾{وَالْفَجْرِ (1) وَلَيَالٍ عَشْرٍ (2) وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ (3)} 🌞{በጎህ እምላለሁ(1) በዐሥር ሌሊቶችም(2) በጥንዱም በነጠላውም(3)} 🌾ከረመዳን በኋላ ሌላ ወርቃማ እድል ይዘው መጡ…🥰🤗 🍂ከረመዳን ቀናት ይበልጣሉ የተባለላቸው ቀኖች መጡ…🤗 🌾በውስጣቸው የሚሰራው ስራ አላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደባቸው ቀኖች መጡ…🥰 🍂«ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » ረሱል ሰ.ዐ.ወ 🌾ልክ ለረመዳን እንደምንዘጋጀው ለነዚህም ቀናት እንዘጋጅ እንጠቀምበት… 🍂በተከበሩት የአላህ ወራት ላይ ኢባዳ በመስራት ከወንጀል በመጠበቅ ላይ እንበርታ👍 🌾«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» ረሱል ሰ.ዐ.ወ 🌾🌞🌾መልካም ጁመዐ🌾🌞🌾

🩵❣🩵❣🩵❣🩵❣🩵❣🩵❣🩵❣🩵❣ 🩵ታላቁ ሰሀባ አብበክር ረዲየላሁ ዐንሁ ሲያለቅሱ ተመለከቷቸውና ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉ ጠየቋቸው እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ... "ረሱሉ ﷺ ሲያለቅሱ ተመለከትኳቸው... እኔም አለቀስኩኝ አሉ" ❣ምን ያማረ ፍቅር ነው !?❣ አፍቃሪውም ታላቁ ሰሃባ አብበክር (ረ.ዐ)ናቸው ተፈቃሪውም ታላቁ ሰው ረሱሉ ﷺ ሆነው ነው 🩵ያ አላህ‼ አንተንም ሆነ የፍጥረተ አለሙን ፀደይ ለመውደድ የተገባን አድርገን🤲 ❣صلُّوا على خير العباد وسلِّـموا فصلاتنا ذُخـــــرٌ لنا ووسَـــامُ يا ربُّ صَـلِّ على النَّبيِّ محـمَّدٍ مَــا لاحَ برقٌ وأسـتهلَّ غَمـــامُ اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمدﷺ❤ 🩵አላህ ሆይ ሰላም እና እዝነትህን የልባችን ብርሀን የሆኑት መልክተኛህ ላይ አውርድ🤲 ❣🩵❣መልካም ጅመዐ❣🩵❣

የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ እንዲህ ይላሉ፡- “ከታላላቅ ከንቱ ተስፋዎች መካከል፣ ሳይፀፀቱ በወንጀሎች ውስጥ በመቆየት የአላህን ይቅርታ መጠበቅ ነው። ያለ አንዳች መታዘዝ ተግባራትን ሳይፈጽሙ ወደሱ መቅረብን መመኘት፣ የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነትን ፍሬ መጠበቅ፣ በኃጢአት ዉስጥ ተዘፍቀው የታዛዦችን አገር መመኘት፣ ሳይሠሩ ምንዳን ማሰብ፣ በእጅጉ ተዘናግተው እያሉ አላህ ላይ አጓጉል ምኞት ማሳደር ነው።”

የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ እንዲህ ይላሉ፡- “ከታላላቅ ከንቱ ተስፋዎች መካከል፣ ሳይፀፀቱ በወንጀሎች ውስጥ በመቆየት የአላህን ይቅርታ መጠበቅ ነው። ያለ አንዳች መታዘዝ ተግባራትን ሳይፈጽሙ ወደሱ መቅረብን መመኘት፣ የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነትን ፍሬ መጠበቅ፣ በኃጢአት ዉስጥ ተዘፍቀው የታዛዦችን አገር መመኘት፣ ሳይሠሩ ምንዳን ማሰብ፣ በእጅጉ ተዘናግተው እያሉ አላህ ላይ አጓጉል ምኞት ማሳደር ነው።”

🎋🎋🎋 ትውስታዎ ብርታታችን ነው🎋🎋🎋 🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕🌕 ♥️ከ ነብዩ ዐለይሂ ሰላት ወስሰላም ህልፈት በኃላ በሰሀቦች መካከል ከባድ የሆነ የሀዘን ድባብ ነግሶ ነበር፤ ታዲያ ዑመር አልፋሩቅ ረዲየላሁ አንሁ ባሉበት ቦታ ሁሉ ነቢ ሲወሱ የሚከተለውን ንግግር ደጋግመው ያወሱ ነበር። 🍃ﻟَﻮْ ﻛُﻨْﺖَ ﻣِﻦ ﺷَﻲﺀٍ ﺳِﻮَﻱ ﺍﻟﺒَﺸُﺮْ ...... 🍃ﻛُﻨْﺖَ ﺍﻟﻤُﻀِﻲﺀ ﻟﻠَﻴْﻠَﺔ ﺍﻟﺒَﺪْﺭ .…🥰 🍃ከሰውነት መደብ ውጪ ቢሆኑማ *** 🍃ያደምቁት ነበረ የበድርን ጨለማ ***🥰 🕊የአላህ ሰለም🕊 💛በዚያ በጨለማ ዘመን ብርሀን በሆነ 💛በዚያ ፍቅርን ባስተማረ 💛በዚያ ልቦችን በወንድምነት ባስተሳሰረ 💛በዚያ በሁሉም ነገር መልካምነትን ባሳየ 💛በዚያ በጭንቅ ቀን ኡመቴን በሚለው ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰 🌾💛🌾መልካም ጁመዐ🌾💛🌾

🥰♥️🥰♥️🥰♥️እወድሃለሁ🥰♥️🥰♥️🥰♥️ ♥️ሙዓዝ ረ.ዐ በአንድ ወቅት ረሱል ሰዐወ ወደ የመን እየሸኙት ...ከትንሽ ቆይታ ቡኃላ በህይወት ዘመኑ ሁሉ አድምጦት የማያውቀውን ከሱ ውጪ ለማንም ያልተባለውን ውብና ማራኪ የሆነ ንግግር ከውብ አንደበት እንደሚሰማ አያውቅም ነበር... 🥰ረሱሌ ወደሱ ቀረቡና እጁን በእጃቸው ያዙት እንዲህም አሉ:– 🥰" ሙዓዝ ሆይ በአላህ ይሁንብኝ እኔ እወድሃለሁ" 🥰🤗 ♥️ሙዓዝ ሆይ ከዚህ ንግግር ቡኃላ ልብህ ምን አይነት የደስታ ጥግ ላይ ነበረች?!😍 🥀እንዴትስ ይሁን በደስታ የሰከርከው?! ♥️ዱንያ ከዚያ ንግግር ቡኃላ እንዴት ሁናልህ ይሁን?! 🥀ከዚያ ቡኃላ ያሉህንስ ረስተህ ይሁን?! ♥️ረሱሉኮ ሰ.ዐ.ወ ይወዱሀል ሙዓዝ ረዲየላሁ ዐንከ🥰😍 🥀እኛንምኮ ይወዱናል…… አዎ ረሱሉና ሰ.ዐ.ወ ይወዱናል🥰 ♥️ናፍቀናቸውም በሀሳብ ተክዘዋል🥰 🥀እና ውዴታን በውዴታ አንቀይርምን !?😍🥰 ♥️በዚህ ከቀኖች ሁሉ ምርጥ በሆነው ቀን ሰለዋት በማለት ድምፃችን በቀጥታ ነቢ ጆሮ ሲደርስስ?!🤗🥰 ♥️የአላህ ሰላምና ወዳሴ በዚያ ፍቅሩ ልቦችን በሚያረጋጋው 🥀አይኖችም እሱን ለማየት በሚናፍቁት ወዱ ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰 🥀♥️🥀መልካም ጁመዐ🥀♥️🥀

♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️ 🥀“ …ከኡመቶቼ መሀከል አንዱ ሲራጥ (ጀሀነም ላይ የተዘረጋን ድልድይ) ለመሻገር አንዴ እየዳኸ፣ አንዴ እየተንፋቀቀ ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ሊወድቅ እየተንጠለጠለ ሲሰቃይ አየሁ፤ በዚህ የጭንቅ ወቅት ታዲያ በኔ ላይ ያወረደው ሰለዋት ከገባበት መከራ ታድጎ በሁለት እግሩ አቆመው … ” ❣{ነብዩ ﷺ ❤️} ♥️ያ አላህ በሱናቸው ላይ አኑረን፤ 🥀በመንገዳቸውም ላይ ግደለን፤ ♥️ከጭፍራዎቻቸውም ጋር ቀስቅሰን፤ 🥀ከስብስባቸውም ውስጥ አድርገን🤲🥺 ♥️ከቀናት ሁሉ አውራና ምርጥ በሆነው ጁመዐ ቀን በታላቁ ሰው ﷺ ላይ ሰለዋት ማለት በቀጥታ ነቢ ጆሮ ነው የሚደርሰው። 🥀እከሌ የእከሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሰለዋት አውርድዋል ተብሎ ስምህ የዓለማት ነቢይﷺ ፊት መነሳቱ ምን ያማረ ነው🥰🤗 🕊የአላህ ሰለምና ውዳሴ🕊 ♥️በዚያ በጨለማ ዘመን ብርሀን በሆነ፤ 🥀በዚያ ፍቅርን ባስተማረ ፤ ♥️በዚያ ልቦችን በወንድማማችነት ባስተሳሰረ፤ 🥀በዚያ በሁሉም ነገር መልካምነትን ባሳየ፤ ♥️በዚያ በጭንቅ ቀን ኡመቴን በሚለው ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰 ❣🤍❣🤍መልካም ጁመዐ🤍❣🤍❣

🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍🍀🎍 🍀{{…فَٱخۡلَعۡ نَعۡلَيۡكَ إِنَّكَ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوٗى}} [ጫማዎችህንም አውልቅ አንተ በተቀደሰው በጡዋ ሸለቆ ነህና፡፡] 🎍በረመዳን መምጣት ወደ ተቀደሰው ሸለቆ ለመግባት እንደ ሙሣ ዐ.ሰ የወንጀል ጫማችንን አውልቀን ነበር....... 🍀በረመዳን አላህ ወንጀላችን ሁሉ እንደማረልን እናስብ…… 🎍እና ከአላህ ሱ.ወ ቅርብ የመሆንን ጥፍጥና ከቀመስን በኃላ ያንን የተቀደሰ ሸለቆ እንዴት ትተን እንሄዳለህን ????!!…… 🍀እንደ መልዕክተኛውﷺ መሆን አይጠበቅብንም?!.... ተጠየቁ "ያለፈውንም የሚመጣውን ወንጀልህ ተምሮልህ አይደል እንዴ ስለምን እንዲህ ትለፋለህ?" ..... "አመሰጋኝ ባሪያ መሆን አይገባምን?!" እንዳሉት🥹 🎍ኢባዳ ይቅር መባያ ካልሆነ ስለውለታዎቹ ማመስገኛ ይሁን። 🍀በረመዳን ወንጀላችን ተምሮልን እንደሆነ ኢባዳን በማስቀጠል ይቅር ስላለን ጥቂት ናቸው ከተባሉት ሰዎች እንሁን። 🎍{……وَقَلِيلٞ مِّنۡ عِبَادِيَ ٱلشَّكُورُ…} {ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡} 🍀ያ አላህ ረመዳንን ስላስጨረስከን በተቀደሰው ሸለቆ ውስጥም የኢባዳን ጥፍጥና ስላስቀመስከን ላንተ የሚገባህ ምስጋና ይድረስህ!🤲 🎍🤲ያ ረብ ኢባዳ ላይ በመዘውተር ከሚያመሰግኑህ ባሮችክ አድርገን🥺 🍀የአላህ ሰላምና ውዳሴ ኢባዳን በማስቀጠል አመስጋኝነትን ባስተማሩን ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰 🍀🎍🍀መልካም ጁመዐ🍀🎍🍀

ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የመጽሐፍ አውደርዕይና ባዛር ዛሬም እንደቀጠለ ነው :: ወቅታዊ መጻሕፍትን ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘናል :: ጎራ በሉና ጎብኙን !!
+2
ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የመጽሐፍ አውደርዕይና ባዛር ዛሬም እንደቀጠለ ነው :: ወቅታዊ መጻሕፍትን ከልዩ ቅናሽ ጋር ይዘናል :: ጎራ በሉና ጎብኙን !!