en
Feedback
እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

Open in Telegram

@Eiduka ቻናል ገራሚ #ፎቶዎች 📂 #የፍቅር_መልክቶች📜 #ቪዲዮ 📀 #ደብዳቤዎች📝 #የልብን_የሚናገሩ_ሙዚቃዎች 🎶🎶 #ሌሎችንም.......... Administrators & create 👇👇👇👇 👇👇👇 @MarH_23 @eiduka23 Join&share Be happy Be smile

Show more
403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
':::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ........ . ................. ...... .. ✍✍በዚህ አለም ከባዱ ነገር የሚወዱትን ማጣት ነው እጅግ ከባዱ ነገር ግን የሚወዱትን አግኝቶ ማጣት ነው' ይለናል ጆርጅ በርናርድ ሾው የተባለ ደራሲ። ወዳጄ ቢያንስ እጅህ ላይ ያለህን እንዳታጣ አሁን ባለህ ነገር ተመስገን በል! ምክንያቱም ተመስገን የማይሉ ናቸው ያላቸውን ሁሉ እያጡ ያሉት። 🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍀🍁🍁🍀 መልካም ቀን🙏🙏🙏🙏 .............. ....... ......... .... 🍁🍂💐🍁💐🍁🍂🍁💐 @eiduka 🦋

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓ #እሺ_በይኝ_እንጂ…😍 እሺ በይኝ እንጂ አለሜ ከልብሽ ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ:: አለሜ እሺ አትይኝም እንጂ እሺ ብትይማ አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ:: ያው እንደነገርኩሽ አለሜ እኔ ያንቺ ትንሹ😍 እሺ ብትይኝ ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም:: ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ስወድሽ የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው እያሉ:: ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው:: እሺበይኝ እንጂ ! እሺ በይኝእንጂ ! እኔኮ ስወድሽ ያው እንደነገርኩሽ አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ:: እኔማኮ ስወድሽ ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ:: እምልልሻለሁ "በኔ ይሁንብሽ እሺ በይኝ ብዬ" ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ:: እኔ ከወደድኩሽ እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን :: አትጠራጠሪ ፍቅሬ እኔኮ ስወድሽ ሳፈቅርሽ ስለ እውነት ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት:: እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም:: ግን እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ አለት በሆነ ልብ በማይጎድል ተስፋ በማይናድ ፅናት ቅፅበት በማይጠፋ በውበትሽ ሰክረው ቅኔ እየዘረፉ በነበልባል ፍቅርሽ ነደው እየጠፉ ያንቺው ትንሹ😍 @eiduka🦋🦋

#ማቆም_የለም!! ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት የምትጀምሩት ነገር በእርግጥም ያመናችሁበትና ከዋናው የሕይወት ዓላማችሁ ጋር የተገናኘ መሆኑን እርግጠኛ ሆኑ፡፡ ያንን ለማድረግ ማሰብ፣ ማቀድ፣ ማማከር . . . ካስፈለጋችሁ ያንን አደርጉ፡፡ ሆኖም አንድ ጊዜ ካመናችሁበት በኋላ ግን መብረር ነው፡፡ “መብረር ካልቻላችሁ ሩጡ፣ መሮጥ ካልቻላችሁ ተራመዱ፣ መራመድ ካልቻላችሁ ተንፏቀቁ፣ ምንም አረጋችሁ ምንም ወደፊት መንቀሳቀሳችሁን አታቁሙ” - Martin Luther King Jr. በሆነው ባልሆነው እየወላወልን፣ ተስፋ እየቆረጥን፣ እየቆምንና ወደኋላ እየተመለሰን ዓላማ ላይ መድረስ የሚባል ነገር የለም፡፡ አትቁሙ! አትመለሱ! በርቱ! መልካም ቀን❤️ @eiduka

😘ግን በቃ እረሳውህ አውቃለሁ ከባድ ነው ትዝታ፣ ከምንጩ ማድረቅ የፍቅርን ጠብታ፣ ግን በቃ እረሳሁህ፣ ከአዕምሮዬ ፋቅኩህ፣ ከልቤ አወጣሁህ፣ አዲስ ሕይወት ጀመርኩ፣ ትዝታህን ትቼ በተስፋ ተራመድኩ።

የሰሞኑ ጨረቃ በጣም ታምራለች እንደተለመደው ማንም ማይጋራኝ በረንዳዬ ላይ ወጥቼ ቁጭ ብዬ እያየዋት ነው የ ውስጤን ሁሉ ብነግራትና እንደዚ አድርጊ እንድትለኝ እፈልጋለው ግን ካወራው በኋላ ዝም ብለን እንደምንተያይ ሳስበው ድካም ይመስለኛል እንደውም ሳስበው ከስዋ ጨለማው ሚረዳኝ መፍትሔ ሚሰጠኝ ይመስለኛል ቢያንስ ካወራውት በኋላ እንዳለቅስ ይፈቅድልኛል ብሶቴን እንደፈለኩ እንዳወጣ ሚረዳኝ ይመስለኛል እሷ ከትዝታ ውጪ ምንም መፍትሔ የላትም አንዳንዴም ሙሉ ከምትሆን ይልቅ ግማሽ ስቶን ታስደስተኛለች ምክንያቱም በደንብ የማይታይ ግን ሙሉ ምትሆንበት ደብዛዛ ክፍል አላት ያ ደብዛዛ ክፍል እኔን ይመስለኛል ሙሉ ስትሆን ገመናዬን ያወጣች የተሰማብኝ ይመስለኝና እፈራለሁ ጨላማን እናፍቃለሁ ሙሉ ሆና ደምቃ ስትበራ ብታስደስተኝም ሚስጥሬን ምታወጣ እየመሰለኝ ልክ አሁን እንደተቀመጥኩት ጨለማ ውስጥ ሆኜ ተደብቄ አያታለሁ የኔን ገመና እንዳወጣች የስዋንም ገመና ማውጣት እመኛለሁ በስዋ ፊት ላይለያዩ ቃል ሚገቡትን እንደማይለያዩ ምስክር እንደምትሆን ግን ምስክርነትዋ የውሸት እንደሆነ ውሸታም መሆኗን ለመናገር እመኛለሁ ግን ልናገር ስወጣ ስለምታይ እደበቃለሁ ግን እኮ እወዳታለሁ #እናት 😔😔😔

💔የማያሽር...ጠባሳ💔 ፨።።።💘💘💘።።።፨ ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ . . . ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።።። @eiduka 🦋

ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። እኛ ገንዘብ የካዱንን ይቅር ማለት ሲያቅተን፣ አዳም ገነትን ያሕል ቦታ፣ እግዚአብሔርን ያሕል አመኔታ ያሳጣችውን ሞት የሚባል እንግዳ ነገር ያመጣችበትን ሔዋንን ይቅር አላት። ይቅርታ ለትውልድ የምናቆየው ውለታ ነው በእርግጥ ይቅርታ የማይገባንን በሰጠን በእግዚአብሔር ፊት ሰውዬው የማይገባውን መስጠት ነው ይቅርታ ሰዎች እንዲለወጡ ዕድል የምትሠጥና እስከ ሞት ድረስ እንዲታመኑልን የምታደርግ ናት። ድንቅ ወዳጅ የሚገኘው ከይቅርታ በኃላ ነው። የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ይቅር ስትል በትክክል መኖር ትጀምራለህ። የበደሉህን ይቅር ማለት የመንፈስ ጥንካሬ እና በራስ የመተማመን ምልክት እንጂ የደካማነት መገለጫ አይደለም። ይቅር ስትል ታድጋለህ። ይቅር ስትል ልብህ ይሽራል። ይቅር ስትል ቀጥ ብለህ ትቆማለህ። ይቅር ስትል አይኖችህ ንፁህ ይሆናሉ፣ ከዚያም ፊት ለፊትህ ያለውን መንገድ በግልፅ ታየዋለህ ብስጩነት የመንፈስ ህመም ነው። @eiduka 🦋🦋 አስተያይት ካለ 👉👉👉 @eiduka23

.......♦️አሳና አሞራ♦️........ ከጊዜያት ብዛት ምንም ብንላመድ ከትውውቅ ጥልቀተ ወዳጅነታችን ምን እንኳ ቢገመድ በጠንካራ ገመድ መላመዱ አይሎ ቢሆንም መዋደድ በእኔና አንቺ መሀል ትልቅ ገደል አለ የሚያስቀር ከመንገድ ምክንያቱን በተረት ላስረዳሽ የኔ ውድ ከእለታት አንድ ቀን በሰማይ ሚኖረው በራሪው አሞራ ምግብ ለመፈለግ ሲወርድ ከተራራ ክንፉን እያማታ በተራ በተራ ድንገት ሳያስበው በፍቅር ተያዘ በውሃ ውስጥ ካለች ካንዷ አሳ ጋራ ከዚያም በየቀኑ አሳዋን ለማየት ቀዬውን ቀይሮ ወረደ ከመሬት አሳዋም በፍቅሩ ተልክፋ ኖራለች ድምፁን እንደሰማች ከባህር ወደ የብስ ቶሎ ትዘላለች ብሎም ከውሃ ውስጥ ለመውጣት ትሻለች ግና ምን ያረጋል ተፈጥሮ ሆነና ምንም ቢዋደዱ በመፋቀር ዳና አንድ ሆነው አይኖሩም አይቻልምና አሞራው ውሃ ውስጥ ለመግባት ቢሞክር አሳዋም መሬት ላይ ለመኖር ብትጥር ሁለቱም አንድ ላይ መሞታቸው አይቀር በዚህ የተነሳም አልሆንልህ ሲለው ማየት እንጂ መንካት እንደማይችል ሲያውቀው ፍቅሩን በልቡ አርጎ በረረ አሞራው ....... አሳዋም ሰረገች ከጥልቅ ከባህሩ እንደማይሆን ስታውቅ ከአሞራ ጋራ አንድ ላይ መኖሩ የእኔና ያንቺም ነገር እንዲሁ ነው በቃ በእጄ ሚያስገባሽ የለኝም ጠበቃ ኑሮሽ ከኑሮዬ ሀሳብሽ ካሳቤ ለየቅል ሆነና ልብሽና ልቤ እጅጉን አራቀሽ ከቅርብ ካጠገቤ የኔን አለም ጥዬ ወዳንቺ እንዳልመጣ ቀሊል እኮ አይደለም የኛማ ጋሬጣ እንግዲያው እኔማ አንቺን ባልጠላሽም ብዙ አትድከሚ እኔ አልሆንሽም ምንም ብንላመድ ብንቀራረብም አሳና አምራ ነን አንድ ላይ አኖርም !!! ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇 @eiduka https://t.me/eiduka

🔊🔊🔊🔊🔊የማይረሳው ጌታ🤲 ❤️‍🩹❤️‍🩹❤️‍🩹❤️‍🩹❤️‍🩹አንቻን አድሎኛል🙏 ☺️☺️☺️☺️☺️አንቻን አድሎኛል✨ 😍😍😍😍😍የማይረሳው ጌታ🤲 ብየው ነበር ይኔ አንተ እይለክ እስኪ ለፍቅር❤️ረሀቤ የማይረሳው 🤲ጌታ🤲 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍭🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫🍫

ፍቅሬ እወድሃለሁ ግን ያተን ስሜት ማወቅ አልቻልኩም😔💔 #eidu

አስችሎህ ይሆን 😔😔😔😔😔😔😔😔😔 💔💔💔💔💔💔💔💔💔 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀@eiduka

ወንድ አውቃለሁ✍ ወንድ አውቃለሁ ለሴት ክብር ግድ የሌለው ፍቅር መውደድ የማይገባው ለሴት ገላ ሲስገበገብ ፍቅርን ክዶ ለስሜቱ ሲራብ አዎን ፍቀሬ ወንድ አውቃለሁ የወንድ ትንሽ በፍቅር ስም ሴትን ሲዋሽ ወረድ ብሎ ከቀሚሷ ክብሯን ሲወስድ ከነነፍሷ አዎን ውዱ ወንድ አውቃለሁ ባንዷ ሴት ላይ ተረማምዶ ለስሜቱ ከእሳት ነዶ ከሌላኛዋ ሴት የሚሄድ አውቃለሁኝ ከሀዲ ወንድ,,, ግን ደግሞ ወንድ አውቃለሁ ለፍቅር♥ ቃሉ ያደረ በሴት ክብር የከበረ ❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ለእምነት ቃሉ የሚኖር ሰው ድንቅ የሆነ ወንድ አውቃለሁ ስሜት ሳይሆን ፍቅር ያለው እምነት ፅናት የተሰጠው እንዳንተ አይነት መልካሙን ወንድ ታድያለው @eiduka23🥀

😘የላይብረሪዋ😘 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አጠናለሁ ብዬ ከገባሁበት ቤት ልቤን አሸፈትሽው ባክሽ የኔ እመቤት ድምፅሽ ከፍ ብሎ ወደኔ ቢመጣ ብድግ አልኩኝና ውዴ አንቺን ልቆጣ ግን ገና እንዳየሁሽ ልቤ ጥሎኝ ወጣ ምን አይነት ውበት ነው ያደለሽ ፈጣሪ ልብ የሚያሸፍት ነው ሆነሽ ላይብረሪ ሚጠናበት ቦታ መሆኑን ባላጣም ሳልነግርሽ አላልፍም ቆንጆ ነሽ ግን በጣም።                             ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌        @eiduka 🦋🦋

መላው አለም ከኔ በተቃራኒው ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለሁ የሆንኩትን ሆኛለሁ። እናተም እራሳችሁን ሁን!!! #edel @eiduka 🦋

ለሰው ልጅ የወረደ አመለካከት አይኑርህ አንተም ሰው ነህና ! ምን አልባት የጊዜ መቀያየር ይኖራልና በዛን ጊዜ አንተ ላይ የሚደርስብህን አታውቅም ፨ @eiduka

U know girl 😒 ሴት የላከው ሞት አይፈራም አድምጪ oky😏 @eiduka🦋🦋

"አንቺ ቆንጆ"tolo neyema fkr altema 👌 @eiduka🦋🦋

💗 እወድሀለው💗 የመልኬ መስታወት የፀባዬ ማያ ያላማየ ውጥን ያሳቤ መለያ ያይኖቼ መነፅር  ግማሽ አካላቴ መቼም #አልረሳህም  እስክታልፍ ሂወቴ❤️ ትዝ ባልከኝ ቁጥር ልቤ  ስራ ፈቶ ደሜ ሊረጋ ነው   መንቀሳቀሻ አቶ እወድሀለሁኝ ካሳቤም ሳልኮራ ፈዝዤ #አይሀለሁ😊 እንደንጋት ጮራ፡፡       ✨Join & Share🙏✨       ✨✨ @eiduka23🥀 @eiduka