403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ከግል ልምዴ
1 የሰው ልጅ እንዳላጣው ብሎ የሚፈራውን ነገር ካጣ በኋላ ትክክለኛ ህይዎት ይኖራል።
2 ፈሪ ካደረገን ምክንያታችን ጀርባ ታላቅነታችን ተደብቋል። ታላቅ ለመሆን ያን ምክንያት ሰብረን ማለፍ አለብን።
3 እዚህ ነኝ እስካላልን ድረስ ማንም የት እንደሆን አያውቅም። ከማንም በፊት ግን ለራሳችን ያለንበትን ሁኔታና ቦታ ልንነግረው ይገባል።
መልካም ምሽት❤❤❤
ከተመቻችሁ ሼር አድርጉ
@eiduka
🌹.......... 👩ሄ ዋ ን 👩..........🌹
🌺🌷ክፍል 5⃣🌷🌺
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
የምገዛቸውንም ሆነ የምለብሳቸውን ልብሶች የሚመርጥልኝ የፀጉር ስታይሌን የሚመርጥልኝ እሱ ሆኗል የማክ አባት ጭራሽ ባሌ መሆኑን እረስቼዋለሁ አንድ ቀን አምሽተን ከውጪ እንደገባን ከመኪና ሳንወርድ ሄዋኔ ብሎ ጠራኝ ወዬ ማክ አልኩት በፍቅር እያየሁት ነይማ የሆነ ነገር አለ ፀጉርሽ ላይ አለኝ ወደኔ እየተጠጋ ወደሱ ስቀርብ ድንገት ሳመኝ በደስታ ልሞት ምንም አልቀረኝም ጉንጮቼ ቀሉ ሲያልበኝ ይታወቀኛል ክፍሌ ገብቼ በደስታ አልጋዬ ላይ ዘለልኩኝ ወንድ ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ነው እሱም ብቻ ሳይሆን እኔ የምወደው ቀን ከሌሊት የማስበው ማክ እኮ ነው የሳመኝ!!! በደስታ የምሆነውን አጣው ልብሴን ቀይሬ ለመተኛት ብሞክር አልቻልኩም የማስበው ማክንና የማክን የመጀመሪያ ኪስ ብቻ ነበር ድንገት መደወልና ድምፁን መስማት ፈለኩ ልደውል ስል ደውዬ የምለው ነገር ግራ ገባኝ ስልኬን ይዤው ለብዙ ደቂቃዎች ማሠብ ጀመርኩ በመሀል ስልኬ ጠራ ማክ ነበር ሴኮንድ አላባከንኩኝም ማክ አልኩት ወዬ አልተኛሽም እንዴ አለኝ እንቅልፍ እንቢ አለኝ አልኩት ለምን ምን እያሰብሽ አለኝ አንተን አልኩት ድንገት ከአፌ ያመለጠ ቃል ነበር ስለኔ ምን አለኝ አፍሬ ዝም አልኩት እኔም ስላንቺ እያሰብኩ ነበር
የዛን ቀን ለረጅም ሰአታት አወራን ሌሊቱ አላልቅ ብሎኝ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ማክን እያሰብኩ ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ አሸለበኝ ጠዋት የአዙ ድምፅ ነበር ያነቃኝ ሄዋንዬ ዛሬ ተኝተሽ ልትውይ ነው እንዴ አለችኝ መጋረጃውን እየከፈተች በይ ተነሽ አለችኝ የለበስኩትን እየገለጠች በግድ አይኔን ገልጬ እንዴት አደርሽ አዙ አልኳት ለመነሳት እየተንጠራራው እግዛሄር ይመስገን ጎሽ ተነሽ! ጋሽዬ ለቁርስ እየጠበቁሽ ነው አለች ልነሳ የነበረው እንደዛ ስትለኝ ተመልሼ ተኛሁ በግድ አስነሳችኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሄድኩ ትላንት የሆነውን እየፈነደኩ ነገርኳት
አንቺ ልጅ እኔ አላማረኝም አለች የመከፋት ፊት እየተነበበባት እኔ ንግግሯን ከምንም ሳልቆጥር አዙ ደግሞ ዝም ብለሽ ታካብጂያለሽ አልኳት የምለብሰውን እየመረጥኩ አዙ ይሄ ያምራል ወይስ ይሄ አልኳት በሁለት እጆቼ የያዝኩትን ልብስ እያማራጥኳት ኤዲያ እኔ ምኑም አላማረኝም አንዱን ልበሽና ይልቅ ተከተይኝ አታስጠብቂያቸው ብላኝ ጥላኝ ወጣች እኔ እየዘፈንኩና በደስታ እንደ ህፃን እየፈነደኩ ወደታች ስወርድ የማክ አባት ፊት ተቀያይሯል ምነው ደና አይደለህም እንዴ አሞሀል አልኩት መልስ የለም ዛሬ ከቤት እንዳትወጪ አለኝ ማስጠንቀቂያ በሚመስል ድምፅ እንዴ ለምን አልኩት ግራ እየተጋባው ባልሽ መሆኔን ላስታውስሽ አለኝ ቀና ብሎ ያልተለመደ ፊት እያሳየኝ በዚህ መሀል ነበር ማክ እንደምን አደራቹ እያለ የወረደው የማክ አባት ምንም ሳይመልስ ከተቀመጠበት ተነስቶ ያልኩሽን እንዳትረሺ መልካም ቀን ብሎኝ ወጣ
ማክ ግራ በመጋባት እያየኝ ምን ሆኖ ነው ተጣለቹ አለኝ ያለኝን ነገርኩት ማታ ስስምሽ አይቶ ይሆን እንዴ አለኝ ባባቱ ሁኔታ ግራ እንደተጋባ እ ይሆናል አሁን ምን እናድርግ አልኩት ትንሽ እስከሚረጋጋ በቃ አንወጣም ነገሮችን እናስተካክላለን አይዞሽ አለኝ ተነስቶ በድጋሚ እየሳመኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱ እስኪረጋጋ ከቤት ባንወጣም ግን አንድ ላይ ሆነ የምናሳልፈው ሁለታችንም በፍቅር ከንፈናል አባቱ ሲመጣ ፊት ለፊቱ እንደበፊቱ እናወራለን ግን በቃ ቤቱን በአንድ እግሩ ስናቆመው ነው የምንውለው የቤቱም ሰራተኞች በእኛ ሳይድ ነበሩና ማንም ለማን ምንም አይናገርም ነበር እኛ በድብቅ ፍቅራችንን እያጣጣምን ነው ከማክ ጋር ከመሳሳም ውጪ ምንም አናደርግም ሲውል ሲያድር በድብቅ አንድ ቀን እኔ ጋር ሌላ ቀን እሱ ጋር ነው የምናድረው እስከምንጋባ ምንም ላናደርግ ወስነናል በቃ በጣም የሚያስቀና ፍቅር ውስጥ ገብተናል ማክ ወደ አውስትራሊያ ላለመመለስ ከተመለሰም አብረን እንደሆነ ወስኗል
አንድ ቀን እሁድ የማክ አባት እንደሚፈልገኝ በአዙ በኩል ልኮብኝ ስሄድ በረንዳ ላይ አኩርፎ ተቀምጧል ሄዋን አለኝ የሆነ ቁጣ ባዘለ ድምፅ አቤት አልኩት ምን ሊለኝ ነው በሚል ፍራቻ እንደተጋባን ዝግጁ አይደለሁም ምናምን በሚል ተራ ምክንያት እስካሁን ለብቻሽ እየተኛሽ ነው እኔም ስለምወድሽና ስሜትሽን ላለመጋፋት ታግሼሻለሁ አሁን ግን የሚበቃ ይመስለኛል የማሰቢያ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ ካልሆነ ግን ወደ ነበርሽበት ህይወት ትመለሻለሽ አለኝ ዛቻ ባዘለ ድምፅ ንግግሩ አናዶኝ ልሄድ ስል አልጨረስኩም አለ ቆጣ ብሎ ከልጄ ጋር ያለውን ነገር የማላውቀው እንዳይመስልሽ ከዚህ ቤት ብወጣ እሱ አለልኝ ብለሽ ከሆነ እንዳታስቢ ሁሉን ነገር አሰቤበታለው ደግሞ ማክቤል ለአንቺ የሚሆን ልጅ አይደለም አባትሽን በማታገኚው ነገር ላይ ተማምነሽ እንዳታሳዝኚው የአባትሽ ከባድ ሚስጥር በእጄ ላይ ነው አለ አንቺ አይሆንም የምትይ ከሆነ ባባትሽ ፈርደሽ ነው አለኝ.....
ይቀጥላል....
꧁༺༒༻꧂
#share
@eiduka
https://t.me/eiduka
🌹.......... 👩ሄ ዋ ን 👩..........🌹
🌺🌷ክፍል 4⃣🌷🌺
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
አዙ ሆነ ማክ ሽፈራውን አስፈቀደ እሱም ተስማማ ደስ አይልም አልኳት እረ እኔስ ምኑም ደስ አላለኝም ሄዋንዬ ምን አስበው እሺ አሏችሁ ጋሼ ለማንኛውም ተጠንቀቂ አለሜ ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ እኔም ተመልሼ መዋኘቴን ጀመርኩ ግን የአዛለችን ንግግር እያሰብኩ ነበር የዛሬው ደስታዬ ምንም ነገር እንዲያጠወልገው አልፈልግም እቤት ገብቼ መዘገጃጀት ጀመርኩ
አንዲት ሙሽራ እንኳን ለሰርጓ እኔ ያባከንኩትን ሰአት አታባክንም በጣም ለማማርና ቀልቡን ለመሳብ የቻልኩትን ያህል ለፋሁ ልክ እንደጨረስኩ በሬ ተንኳኳ ማክቤል ነበር አልጨረሽም አለኝ ኧረ ጨርሻለሁ አልኩት መኪናው ጋር እጠብቅሻለሁ እሺ መጣው አልቆይም አልኩት የት መሄድ እንደምፈልግ ጠይቆኝ በኔ ምርጫ ወደ አንድ ሬስቶራንት እየሄድን ነው ስትዋኚ ጎበዝ ነሽ አለኝ ድንገት ነበር የተናገረው አባባሉ አስደነገጠኝ እ...የት አየኸኝ አልኩት እንደማፈር እያልኩ ቅድምም ሌላም ቀን አይቼሻለሁ ማን አስተማረሽ አለኝ ትምህርት ቤት እያለን አንድ ዋና በጣም የምትወድ ጓደኛ እንደነበረችኝና እሷ እንዳስተማረችን ነገርኩት አሪፍ ነው እኔም ዋና እወዳለሁ አለኝ እንደዚህ እያወራንና ስለግል ታሪኬ አንዳንድ ነገሮችን እየተጫወትን ደረስን ከመኪናው ወርዶ በር ከፍቶ እጄን ይዞ አወረደኝ
ማክቤል ስርአቱ በጣም ነው የሚገርመው ምሳ እየበላን ድንገት ለምንድነው አንቺና አባዬ የተለያየ ክፍል የምትኖሩት አለኝ ጥያቄው ድንገተኛ ስለሆነ የጎረስኩት ትን አለኝ እንዴ ምነው ጥያቄዬ የዚህን ያህል ያስደነግጣል አለኝ ውሀ እያቀበለኝ አ..አይ እንደሱ ማለቴ አይደለም አልኩት እና እንዴት ነው አለኝ ለመስማት የጓጓ በሚመስል ድምፅ?
እስኪ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ አለኝ ተመቻችቶ እየተቀመጠ ያለውን ነገር በግልፅ ነገርኩት ላባቱ የሚሰማኝ ነገር አባት ለልጁ ከሚያደርገው እንክብካቤ ያልዘለለ እና የኔም እዛ ቤት ኑሮ ከስር ቤት ያልተናነሰ መሆኑንም ጭምር በሀዘኔታ እያየኝ አይዞሽ እሺ አለኝ ከዚያ ሌላ እኔን የሚያፅናናበት መንገድ የለምና እሺ አልኩት አንገቴን ደፍቼ እንዴ ከድብርት እንድታሶጭኝ ይዤሽ ብመጣ ጭራሽ ልታስደብሪኝ ነው እንዴ አለ ለመቀለድ እየሞከረ ይቅርታ አልኩት ፈገግ ብዬ ታዲያ አሁን የት እንሂድ ዛሬ በአንቺ ምርጫ ነው አለኝ ዛሬ የምትለዋ ቃል ሌላም ጊዜ አብረን እንደምንወጣ ተስፋ ሰጠችኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱን እያስፈቀድን አንዳንዴ ዝም ብለን እየወጣን መዝናናቱን ተያያዝነው ሲለንም እያመሸን መግባት ጀመረናል በቃ የማንሄድበት ቦታ የለም ከማክ ጋር ስሆን ሁሉን ነገር እረሳለሁ ህይወቴ በደስታ ተሞላች ቅልጥ ያለ ፍቅር ይዞኛል ቀንም ሌሊትም የማስበው ስለማክ ብቻ ሆኗል
ማክም ፍቅር ሳይዘው አይቀርም......
ይቀጥላል.....
꧁༺༒༻꧂
@eiduka
https://t.me/eiduka
🌹.......... 👩ሄ ዋ ን 👩..........🌹
🌺🌷ክፍል 3⃣🌷🌺
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
በራሴ የባህሪ ለውጥ ግራ ብጋባና ማክቤልን ላለማሰብ ብሞክር ሊሆንልኝ አልቻለም ቀን ከለሊት እሱን ብቻ ነው የማስበው በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለው ቀናቶች ተቆጠሩ፡፡ ማክቤል ያሉት ጓደኞች ውስን በመሆናቸውና እነሱም ከስራ ውጪ ብቻ ስለሚያገኙት አብዛኛውን ጊዜ ብቻውን ነው የሚያሳልፈው አንድ ቀን ታዲያ ወደ ውጭ ስወጣ ስፖርት ሰርቶ ደክሞት በጀርባው መሬት ላይ ተኝቷል በላብ የራሰው ሰፊ ደረቱና ተክለ ሰውነቱ ከከለሩ ጋር ታይቶ አይጠግብም እዛው እንደተኛ ቀና ብሎ እያየኝ እንደምን አደርሽ አለኝ፡፡
ሰላም እንዴት አደርክ ደክሞህ ነው አልኩት አዎ ትንሽ አለ ለመነሳት እየሞከረ በናትሹ በድብርት እኮ ልሞት ነው ላባቴ ልንገረውና ከፈቀደ ምን ይመስልሻል ዛሬ ከእንጀራ እናቴ ጋር ምሳ ውጪ አብረን ብንበላ አለኝ አባባሉን ስላልወደድኩት ቀና ብዬ አይቼው ወደ ውስጥ ልገባ ስል እየሮጠ መጥቶ እጄን ያዘኝ ልቤ በሀይል ሲመታ ይታወቀኛል ፕሊስ እንዳይከፋሽ ለመቀለድ ያህል ነው ይቅርታ እሺ በልምምጥ እሺ ግን ሁለተኛ እንዳትደግመው አልኩት አልደግመውም እና ተስማማሽ አባቴን ላስፈቅደው አለኝ እሱ እንደምንሄድበት ቦታ ይወሰናል አልኩት ቁርስ ላይ ተቀምጠን አባዬ ዛሬ ሚስትህን ባስኮበልልብህስ እቤት መቀመጥ ሰልችቶኛል ብቻዬን ደግሞ ምንም አላውቅም ምሳ አብረን ብንበላና አንዳንድ ነገሮችን አብረን ብናይስ አለው ባለቤቴ ቀና ብሎ ሲያየኝ ምንም አይነት ቅር የመሰኘት ነገር የለብኝም እንደውም ፈገግ ሁላ ብያለሁ ባይሆን የሱ ገፅታ ተቀያይሯል ግን ምንም ማለት ስላልቻለ ባይፈልግም ጥሩ ግን አትቆዩ አለው በውስጤ ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም እረ ፊቴ ላይ ሁላ ያስታውቃል የማክቤል ውበቱ እርጋታውና ስርአቱ ከቀን ወደቀን ልቤን እየገዛው ነው፡፡ ቁርስ በልተን ስንጨርስ ባለቤቴ ተሰናብቶን ወደቢሮው ሄደ ማክቤልም እስከምንወጣ ጓደኞቼን በስካይፕ ላውራ ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ እኔም ወደ ክፍሌ ገብቼ የምለብሰውን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ የቁምሳጥኑ ልብስ አንድ አልቀረኝም በየተራ ሁሉንም ሞከርኩት በመጨረሻ ያመንኩበትን አዘጋጅቼ ሰአቱ እስከሚደርስ አላስችል ስላለኝ ልዋኝ ወደውጪ ሄድኩ በደስተኝነቴ አደለም ባለቤቴ ሰራተኞቹ ተገርመዋል፡፡ ሁሌም ካጠገቤ የማጠፋውና የሚሠማኝን ሁላ የማልደብቃት አዛለች ሄዋንዬ አለችኝ የሚጠጣ ይዛልኝ እየመጣች ከሷ ጋር ማውራት ደስ ይለኛል እንደ እናት ነው የምታዝንልኝ ወዬ አዙ አመሠግናለሁ አልኳት ብርጭቆዬን እየተቀበልኳት አለሜ ምን ተገኝቶ ነው እንደዚህ በደስታ የከነፍሽው አለችኝ በደስታዬ መደሰቷ ፊትዋ ላይ እያስታወቀ አዙ ብነግርሽ አታምኚም አልኩዋት ከገንዳው ወጥቼ አጠገቧ እየተቀመጥኩ አቤት አቤት ንገሪኝ ልስማው ታዲያ አለች እንደናት እየደባበሰችኝ ከማክ ጋር ለምሳ ልንወጣ ነው አልኳት እንደህፃን እየፈነደቅኩ ኧረ ቆይ ..ቆይ ..ቆይ ..እንዴት ሆኖ አለች ፊቷን ፈታ ኮስተር እያረገች.....ይቀጥላል
꧁༺༒༻꧂
@eiduka
https://t.me/eiduka
🌹.......... 👩ሄ ዋ ን 👩..........🌹
🌺🌷ክፍል 2⃣🌷🌺
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
ባለቤቴ እንኳን የሱን ያህል አልተማረረብኝም ነገሮችን ገና መቀበል እንዳልቻልኩና ትንሽ ጊዜ እንዲታገሰኝ ለባሌ ነግሬው መስማማቱን ስነግረው....
እስከመቼ ነው የሚታገስሽ አመት ሊሞላችሁ ምን ቀረ ባይሆን ውለጂና ይሄን ሀብት የሚወርስ ልጅ ሰጥተሽ አስደስችው አለኝ እኔ ብወልድ ሀብቱ የሱ የሚሆን ይመስል ነገሮችን እንደማስተካክል ቃል ገብቼለት ከስንት ጭቅጭቅ በኃላ አሳመንኩት ባሌ ደውሎ የመጨረሻ ልጁ ነገ ከአውስትራሊያ እንደሚመጣ እና የሚያስፈልግ ነገር ካለ ለሰራተኞች ነግሬ እንዲያስተካክሉ በትህትና ጠየቀኝ ፡፡ ሁሉን እንደማሟላና እንዳያስብ ነግሬው አመስግኖኝ ስልኩ ተዘጋ.....ዛሬ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል! በጠዋት ተነስቼ ቤቱ መስተካከልና አለመስተካከሉን ቼክ አደረኩ ፡፡
ምሳ ምን መዘጋጀት እንዳለበት ነግሬያቸው ተጣጥቤ ፀጉሬን ልሰራ ወደፀጉር ቤት ሄድኩ... ከፀጉር ቤት እንደጨረስኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ገዛዝቼ እቤት ስገባ ነበር ባየሁት ነገር ባለሁበት ደርቄ የቀረሁት... ሀይ እንዴት ነሽ ሄዋን አለኝ ደስ የሚል ቃና ባለው ጎርናና ድምፅ.. .. እ..እንኳን ደህና መጣህ ማክቤል?? አሀ ማክቤል ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋልኝ.... ለደቂቃዎች እጁን ሳለቅ ፈዝዤ በቆምኩበት ቀረሁ... ዋው አባቴ ሚስቱ ቆንጆ እንደሆነች ቢነግረኝም እንደዚህ አልጠበኩሽም ነበር አለ እጁን ከጄ እያላቀቀ...
እ...አመሠግናለሁ እባክህ አረፍ በል መኝታ ቤት ገብቼ መጣሁ ብዬው የመሮጥ ያህል ካጠገቡ ጠፋሁ....
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ የማክቤልን ውበት ከፎቶ ይበልጥ በአካል እንደሚያምርና የኔ ሳየው መደንገጥ እያሰብኩ ነበር ድንገት በሬ የተንኳኳው... ሄዋን... የባሌ ድምፅ ነበር...አቤት አልኩት በድንጋጤ ካልጋዬ እየተነሳው ...
ነይ እንጂ ምሳ እየጠበቅንሽ ነው አለኝና ወደታች ወረደ .... ሊያምርብኝ የሚችለውን ቀሚስ በመምረጥና እራሴን በማስዋብ ጊዜ ወሰደብ... ልክ ወደ ታች ስወርድ ማክቤል ፊት ለፊት ነበር የተቀመጠው እግሬ ሲተሳሰር ታወቀኝ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ስላስቆየኃቹ ይቅርታ ብዬ ከባሌ አጠገብ ተቀመጥኩ....ባሌ ዛሬም እንደሁልጊዜው አምሮብሻል አለኝ እጄን እየሳመኝ ... ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ ሲያረግ !
ደንግጬ እጄን ከእጁ መነጨኩትና የማክቤልን ገፅታ ተመለከትኩ ምንም አልመሠለውም.... ሚስትህ ቆንጆ ናት አባዬ ለራስህ ታውቅበታለህ አለው እየቀለደ.... ለምን እንደሆነ ባላውቅም በንግግሩ ተናደድኩ ብሽቅ አልኩ በውስጤ.... ምን ነካሽ ሄዋን አንቺ ያገባሽ ሴት ነሽ...አልኩ ለራሴ
ምሳ ተበልቶ እንዳለቀ ማክቤል ማረፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወደክፍሉ ገባ ሳላስበው ባይኔ ተከተልኩት... ቆሞ ሁኔታዬን ሲመለከት የነበረው ባሌ ....
"ዛሬ ደስ ያለሽ ትመስያለሽ "....አለኝ የባሌ ድምፅ ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ... ... ም ..ምምን ተገኝቶ ያው እንደበፊቱ ነኝ.... ል....ልግባና ልረፍ ትንሽ እራሴን አሞኛል አልኩት እየተርበተበትኩ ... ...
መድሀኒት ውሰጅ ምን አልባት ፀጉርሽን ስለተሰራሽ ይሆናል አለኝ ይሆናል ልግባና ልረፍበት ብዬው ወደክፍሌ ሄድኩ.....
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ነኝ .... የማላውቀው የተዘበራረቀ ስሜት ይሰማኛል ደጋግሜ ማክቤልን አስብና ፈገግ እላለሁ.....ይቀጥላል
꧁༺༒༻꧂
ይቀጥላል...
@eiduka
https://t.me/eiduka
/ተለያየን በቃ //
እስኪ ልጠይቅሽ መልሽልኝ አንዴ ፣
አፈቀርኩሽ ብየ አጠፋሁኝ እንዴ ?
አሁንማ ገባኝ ስተት ነው መንገዴ ፣
እ/ር ሳይፈቅደው አንችኑ መውደዴ ፣
በፍቅርሽ ነበልባል በሳቱ መንደዴ ፣
በይ እንግዲ ቻውቻው ውጭልኝ ከሆዴ ፣
የሄድሽበት መንገድ ይስመርልሽ ውዴ ።
ስሚኝ የኔ ፍቅር ልንገርሽ እውነታ ፣
ፍቅር ህይወት እንጅ አይደለም ጨዋታ ።
አጥፍቸም ከሆነ ይቅርታ ብያለሁ ፣
ከዛሬ በኃላ ተስፋ ቆርጫለሁ ፣
7 አመት ሁሉ ተሰቃይቻለሁ ፣
በስተት ጎዳና ሩቅ ተጉዣለሁ ፣
እኔ ባንች ፍቅር ራሴን ጥያለሁ ፣
አሁንማ ገባኝ እኔን አውቄአለሁ ፣
ስሀቱ ቢረፍድም እንዳልመሸ አውቃለሁ ።
አንችኑ ላላስብ እዚጋ ላበቃ ፣
ትመስክር ጀምበሯ ትመስክር ጨረቃ ፣
ትዝታሽ ላይመጣ ላይሆነኝ ሶቀቃ ፣
ደግመን ላንገናኝ ተለያየን በቃ ፣
ደግመን ላንገናኝ ተለያየን በቃ
@eiduka 🦋
@eiduka 🦋🦋
.......... 👩ሄ ዋ ን 👩..........
🌺🌷ክፍል 1⃣
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
ገና በልጅነቴ ነበር አባቴ ለሀብታም ጓደኛው እኔን እንደሚድረው ቃል የገባለት
እኔ ባባቴ ሀሳብ ባልስማማ አማራጭ አልነበረኝምና ባልፈልገውም ሁለተኛ ጀረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ያባቴ ጓደኛ ከዚህ በኃላ እንድማር ባለመፍቀዱና ካባቴ ጋር በመስማማታቸው እንዳገባ ተወሰነ .....
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ አለሜን ሳላይ አለምሽ ተብሎልኝ ተጋባን...ለመጀመሪያ ቀን ባሌ ቤት ስገባ የእስር ቤት ህይወት አንድ ብዬ መጀመሬን ለራሴ አሰብኩት...
መረረኝም ጣፈጠኝም አማራጭ አልነበረኝምና የቤት እመቤትነት ኑሮ ሳልፈልግ አንድ ብዬ ጀመርኩት.. ..
ቀናቶች ተቆጥረው ወራትን ወለዱ ባሌ ትልቅ ሰው ከመሆኑ ባሻገር ለኔ መልካም ለመሆንና ካለሀብት የሀዘን ኑሮ ሊያወጣኝ ይጥራል... እውነት ለመናገር ክፋ የሚባል አይነት ሰው አይደለም አንዳንዴ ፈገግ ብዬ ካየኝ በደስታ የሚሆነውን ነው የሚያጣው......
የሚጎድልብኝ አንድም ነገር የለም ባዶ የሚባል አይነት ኑሮ ልኑር እንጂ ማንኛዋም ሴት የምትመኘው አይነት የድሎት ህይወት ነው የምኖረው፡፡
ያልኩትንም ነገር በመፈፀም ሆነ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በማሟላት ወደኋላ አይልም ግን እኔ ከአባቴ እኩያ ጋር በፍቅር አብሮ መክነፍ የማላስበው ሆነ...በቃ ጭራሽ የሚሆንልኝን ነገሮች አባት ለልጁ የሚያደረገው እንክብካቤ አድርጌ እስከመቁጠር ደርሻለሁ .....
ከባለቤቴ አቶ ሽፈራው ጋር እስካሁን አንሶላ አልተጋፈፍንም ለየብቻ ነው የምናድረው እንዲህ ፍላጎቴን ማሟላት ከዚህ ከባድ መስዕዋትነት ይጀምራል እኔ ፍቃደኛ ባለመሆኔና ለዚህ ነገር ዝግጁ እስከምሆን እንዲታገሰኝ ስነግረው ቅር ቢለውም ፍላጎቴን አልተቃወመም ለዛም ነው ጥሩ ሰው መሆኑን ባንደበቴ የምመሰክረው ..... ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ እንደሚወደኝ... አንድ ቀን አባቴ ሊጠይቀኝ ሲመጣ እኔ ሌላ ክፍል እንደምተኛ አውቆ በጣም ተበሳጨ..... ይህን አይነት ወርቅ ህይወት ሰጥቼሽ ምን ፈልገሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው አለኝ...... ያባቴ እንደዛ መበሳጨት አልገባኝም......
꧁༺༒༻꧂
@eiduka
https://t.me/eiduka
ጥቁር እና ነጭ
ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል
ለዛ ቢስ ከንፈርሽ
ዋጡኝ ዋጡኝ ምትል
ከሲታዋ ጉንጭሽ
ቻይኖችን የሚያስንቅ
ውበት ያላት አይንሽ
የሚያንፀባርቀው
ድደ ብዙ ጥርስሽ
ብቻ ምን ልበልሽ
ከእግዜሩ ተችሮሽ በዛና ቁንጅናሽ
ያነም ለኔ ሲልሽ
ይህም ለኔ ሲልሽ
እኔም ለኔ ስልሽ
ካንቺ በላይ ቆንጆ የሌለ መሰለሽ
ካናትሽ ላይ ወቶ
ድንቅ ውበትሽ በዝቶ
ለኔ ለኔ ስንልሽ
ለልማት መሆኑን መች አወቅሽው ከቶ።
(ስንቱ ላይ አሹፈናል
ስንቱ ላይ አላግጠናል
ስንቱን የኔ ብለን በቃል ኳኩለናል
አንኳንስ እሱን መልክ
ሰይጣንን እራሱ ቆንጆ ነህ ብለናል.......yoni atan)
@eiduka
💍. . .እኔና አንቺ ማለት እሳት እና ብረት ግለን የተዋሃድን ቀልጠን የተስማማን ዳግም ላንለያይ አንዴ የተጣመርን ሰምና ወርቅ ነን።👩❤️👨
♥️. . .አፈቅርሻለው. . .♥️
◆💌─━━━━💓⊱✿⊰💗━━━━─💌
# ༒︎༆
┈••◉❖◉●••┈
🇯 🇴 🇮 🇳 𝐔 @eiduka
✍ስትበስል መረዳት ያለብክ ወሳኝ ነገሮች ° ° °
☞ፍቅር ፊልም ላይ እንዳየኸዉ ፈፅሞ አይደለም፡፡
☞ያለህን ነገር ካልተጠቀምክበት ታጣዋለህ፤ይህም ማለት እዉቀትህን፣አቅምህን፣የምትችላቸዉ ቋንቋዎች ወዘተ. . .
☞ሁሉም ነገር ልክ አለዉ፤ባበዛኸዉ ቁጥር አንተን መጉዳት ይጀምራል፡፡
☞ያለሀዘን ደስታን ልታዉቅ አትችልም፡፡
☞ከባህሪዋ ጋር ልትስማማት የምትችል ሴት ምረጥ!!
☞ለማግኘት ስጥ፤ ህይወት ተጋርተህ የምትኖርባት ስፍራ ናት፡፡
☞ትንሽ ተናገር፤ብዙ አዳምጥ!!
☞ጓደኛ ማለት ረጅም ጊዜ ያወቅከዉ ሰዉ ሳይሆን ወደህይወትህ መጥቶ ‹ከጎንህ ነኝ› ብሎህ የደገፈህ ማንነት ነዉ፡፡
☞ማንኛዉንም ሰዉ አለመጠን አትደገፍ ፤በጣም ከተደገፍክ ብዙ ትጠብቃለህ ብዙ መጠበቅህ ደግሞ ጥልና ሀዘን ዉስጥ ይከትሃል፡፡
☞አንድን ሰዉ ከልብህ ከወደድክ ለመለየት ሚሊየን ምክንያቶች ቢኖሩህ እንኳን ለመቆየት አንድ ምክንያት ትፈልጋለህ፡፡
☞ሰዎች የምትሰራዉን ስራ ይጠይቁህና ስትነግራቸዉ የምትሰራዉን ያህል ክብር ይሰጡሃል፡፡
☞ማንንም ልታምን ልብህን አትስጥ፡፡አለቀ! አለበለዚያ ሊከዳኝ አይችልም ያልከዉ ሰዉ ባልጠበከዉ ሰአት ይከዳሃል!
☞ብቻህን በመሆንህ አታማርር፡፡እራስህን የምትፈትሽበት አሪፍ ጊዜ ይኖርሃል፡፡
☞ሰዎች ሃሳብህን ካልተረዱህ አትዘን ወይም ለማስረዳት ብዙ አትድከም፡፡ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ይሰማሉና፡፡
☞እራስህን ከሰዎች ማነፃፀር ሞራልህን አያነቃቃም፤ቅናትና ንዴት ብቻ እንዲሰማህ ያደርጋል፡
ለማንኛው አስታየት 👉 @eiduka23
#ሼር_ማረግ_አትሩሱ
@eiduka 🦋
https://t.me/eiduka
#ስማኝ_ወዳጄ
•✍✍✍ ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም !ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ ።
•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ ።
•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ ።
•| አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም !ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ ።
•| ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም ! በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ ።
•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም !ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ ።
•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ ።
•| ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ :
@eiduka
=========================
🍁🍂🍁🍂🍁🍂🍁🍂🍁🍂🍁🍁
--------------------------------------------------
#ወጣትነት_ማለት✍✍✍
ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!
ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!
ወጣትነት ይሄንንም፣ ያንንም፣ ይቺንም፣ ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...
ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው።
ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው። ወጣትነት መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።
ምንጭ ፦ " ኤጭ...! " መጽሐፍ ከገጽ 170-172
ደራሲ ፦ አዘርግ
ሼር ማረግ አይርሱ
@eiduka
https://t.me/eiduka
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
ሶስተኛው አለሜ 🌍👼💘
🌍
በፊተኛው አለም በአካል ማንነት
ችግር ከሞላበት
ተድላውም ካለበት
አንዴ ጣፋጭ እለት
ቀጥሎም ውጥንቅጥ
መላ ቂጡን ያጣ ሁሉ ሚታይበት።
👼
ሁለተኛው ደግሞ መንፈሳዊው አለም
የሚታይ አይደለም
ሚዳሰስ አይደለም
ትልም ነው ሚተለም
በምናብ ሚታለም።
🌍👼
ስጋና መንፈሴ በጎራ ሲፋጅ
አንዱም ሳያሸንፍ ህይወቴን ሲፈጅ
ነፍሴም ከጭንቀት ለመውጣት ስትዳክር
ስትደርስ ከደጅ
💘💘💘
መጣሽና አንቺ
ፈጥረሽ ሌላ አለም ልቤ ምታርፍበት
ፍቅርና መውደድ ደስታ የሞላበት
ነፍሴ ሳትወጣ ከስጋዬ ላይ
ሌላኛውን አለም ገብቼ ሳላይ
በአካል እንዳለው እኔ በዚች አለም
ከልቤ ጥላቻ ክፋት ሲጠራቀም
ከዛ ወጣሁና
❤❤❤
የፍቅርሽን አለም ሳየው አስቀድሜ
መንፈሴ ሲነግረኝ እንዳለ ሰላሜ
ላልወጣ ወሰንኩኝ ዘጋሁት ጠርቅሜ
ፍቅርሽ
ፍቅርሽ ነው ሶስተኛው አለሜ
✍ተፃፈ;-በበሱ
@eiduka
🍃🌹🍃....✍
💞. . .አንዳንዴ ባላስተዋልነው የጊዜ እንቅፋት ላይ መውደቅ ፤ በከንቱነት ስሜት ውስጥ መዘፈቅ፤ በፅልመት መታጠር አንዱ የህይወት ነጎድጓድ መታያ ጭላንጭል ነውና ስለዚህ በእያንዳንዱ የህይወት፣ ትንታ እጅ አንስጥ አለም ተሸናፊዎች የሚገበሩባት አሸናፊዎች በኩራት የሚታዩባት ማራኪ ቲያትር ናትና።❥︎
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
@eiduka
https://t.me/eiduka
::::::::::"":::::::""::::::"":::::
-------------'------'-------'---
:አንድ አንዱ ዛሬ የሚያስደስተው ሲያገኝ ትላንት መስዋእት የሆነለትን ይረሳል
💍ቃል የእምነት እዳ ነው ፍቅርም ልክ እንደ ማህተም ነው ከቃልም በላይ እውነት እና እምነት ነው፡፡💍
🙏``አትበሳጭብስጭትየስይጣን ነውና``
አትዘን
'' አምላክያልፈቀደውአይሆንምና``አትቸኩል
``ላንተ ያለው አይቀርምና``
✔️ፍቅርማለት በሀብት ብዛትያልታጠረችበድህነት ወስን ያልተገደበችበወርቅሚዛንላይ ያልተቀመጠች
በግለስቡ ማንነት ብቻ የምትገለፅ ጥበብነች💋💋
✔️ሴት ልጅ የማይቻለውን ነገር አድርግልኝ ብላ አትጠይቅህም ነገርግን አንት ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ውንድ ሁንላት ይሄ ብቻ በቂዋ ነው፡፡
❤️ፍቅር እንኳዋን ርቀት መከራንም ይታግሳል
`
✍ዓለም ሙሉ ጎድቶህ አንድ ስው ሊያስደስትህ ይችላል
©°ያው ስው አንድ ቀን ይጎዳህና
ዓለምሙሉ አንተን ማስደስት የቅተዋ
✍ ከድብቅ ጓደኛ ግልፅ ጠላት ይሻላል
•
✍ወዳጄ ሆይ! ልብህ ለፍቅር ህሊናህን ለእውነት ነብስህን ለፀሎት አድርግው!
🍀መልካም ቀን🍀
🍀🍀💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍀
@eiduka
https://t.me/eiduka
