en
Feedback
እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

Open in Telegram

@Eiduka ቻናል ገራሚ #ፎቶዎች 📂 #የፍቅር_መልክቶች📜 #ቪዲዮ 📀 #ደብዳቤዎች📝 #የልብን_የሚናገሩ_ሙዚቃዎች 🎶🎶 #ሌሎችንም.......... Administrators & create 👇👇👇👇 👇👇👇 @MarH_23 @eiduka23 Join&share Be happy Be smile

Show more
403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ዝምታዬ ገርሞሀላ ...!!😏 ... ቢገባህ... ከአይሁዶች ጫጫታ ይልቅ ጲላጦስን ሰላም የነሳው የክርስቶስ ዝምታ ነበር .... @eiduka

.... ታውቃለህ ውዴ?? በዓለም ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ.... ነገር ግን በኔ አለም ውስጥ አንድ ልዩ ሰው ብቻ ነው ያለው.... ያም ሰው አንተ ነህ አንተ ብቻ 😍❤️ 💌─━━━━ @eiduka 💓⊱✿⊰💗@eiduka ━━━━─💌

ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት😂 ... አቶ ደም ምላሽ😡 .....mr. blood return😊 ወ/ሮ አልጋነሽ🛏 .....lmrs you are a bad 😂 ልጅ ሺመልስ☺️ .....son returan a thousand 🤑 ዱባለ😂 .....drop he said 🙊 አልጋወራሽ🙄 .....bad take over 🛏 ዘራበዛ🤔 .....increases race🤷‍♀️ አለማየሁ🙈 ..... I saw world 👀🌍 አይናለም☹️..... eye world 👁🪐 ግራ አዝማች ሺበሺ👨‍✈️ ....left leader thousand 👨‍✈️ አቶ ማስረሻ 😒....mr. you make me forget 😢 ሙሉ ነህ🧍🧍 ... you are full 😂 መንግስቱ😱 .....the government 😒 በልሁ🤷‍♀️..... by this stubborness 😁 ማንያዘዋል😠 ....who order him 🙄 አለም ፀሀይ😝..... world sun 🌎🌞 😂😂😂😂😂😂😂😂😂 @eiduka🦋 @eiduka 🦋

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣5⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 አንድ ቀን ማክ ስራ ሄዶ እኔ እቤት መቀመጥ ስለሰለቸኝ ግቢ ውስጥ ዝም ብዬ ወዲያና ወዲህ እያልኩ ነው ድንገት የግቢያችን በር ተንኳኳ... ከደቂቃዎች በኀላ ዘበኛው ፖስታ ይዞልኝ መጣ "ለሄዋን መኮንን" በእጅ የሚሰጥ ይላል የላኪ ስም አልተገለጸም እጆቼ ተንቀጠቀጡ ለተወሰነ ደቂቃ ካለሁበት ሳልነቃነቅ በጄ የያዝኩትን ፖስታ ፈዝዤ ተመከትኩት ምን እንደማደርገው ግራ ገባኝ እየሮጥኩ ወደቤት ገባሁ እርግጠኛ ነኝ እስከዛሬ በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ፋይል ነው ግን እጄ ላይ ሲደርስ ለማየት አቅም አነሰኝ ልከፍተው አስቤ ተውኩና ለማክ ልደውልለት ስልኬን አነሳሁ መልሼ ተውኩት በቃ ግራ ተጋብቼ ፈዝዤ እንደቆምኩ ነኝ እጆቼ አሁንም ይንቀጠቀጣሉ አምላኬ ሆይ እርዳኝ አልኩኝ እና እንደምንም እራሴን ለማረጋጋት ቁጭ አልኩኝ ከፖስታው ጋር ተፋጠናል በዛ ግራ መጋባት ውስጥ እያለሁ ስልኬ ሲጮህ ከተቀመጥኩበት በድንጋጤ ተነሳሁ ማክ ነበር እንደምንም አየር ስቤ ስልኩን አነሳሁ ሄ....ሄሎ አልኩኝ በተቆራረጠ ድምጽ የኔ ፍቅር ምነው አመመሽ እንዴ አለኝ እ..ደ..ደህና ነኝ ማክ አልኩት አሁንም በተቆራረጠ ድምጽ አጠገቤ ከተቀመጠው ፖስታ ጋር አሁንም ተፋጠናል ደህናማ አደለሽም ምንድነው የሆንሽው አትደብቂ ንገሪኝ የተፈጠረ ነገር አለ አሞሻል ወይስ ምንድነው አለኝ የኔ ፍቅር ደህና ነኝ ትንሽ ቆይቼ ልደውልልህ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት ያስቀመጥኩትን ፖስታ አንስቼ በድፍረት ስቀደው ውስጡ ፎቶና አንድ ፍላሽ አለ..... ፎቶውን ገና ከማየቴ አቅለሸለሸኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሮጥኩ ሄድኩኝ ሲያዞረኝ ይታወቀኛል ከዛ በኋላ የሆንኩትን አላስታውስም ስነቃ ማክ እና ዶክተሬ አጠገቤ ቆመው ስለኔ ጤንነት ያወራሉ ዙሪያዬን ስቃኝ ሆስፒታል አልጋ ላይ ተንጋልያለሁ ሆዴን ዳበስኩኝ ማክ ል....ልጄ ብዬ ስጮህ እየሮጠ መጥቶ አቀፋኝ ልጃችን ደህና ነው ተረጋጊ የኔ ፍቅር አለኝ ኡፈይይይ... ብዬ ተነፈስኩ.... ተስፋ በሌለው ባዶ ስሜት ውስጥ ሆኜ እነዛን ፎቶዎች ዳግም አስታወስኩኝ..... አባቴ እንዴት ይሄንን ይፈፅማል አይሆንም አልኩና ካልጋ ለመውረድ ከማክ ጋር መታገል ጀመርኩኝ ማክ በግድ አረጋግቶ አስቀመጠኝ አንገቱ ስር ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ማክ ምድር ላይ ያለኝ ብቸኛው ሰውገዳዩ አባቴ ነው የማዋን ባል የገደለው አባቴ ነው እያልኩ ሳለቅስ በግድ እንድረጋጋ ዝም እንድል ያባብለኝ ጀመር ትዝ ሲለኝ ፍላሹ ውስጥ ምን እንዳለ ገና አላየሁም ማክ ፍላሹስ ፍላሹ የታል አልኩት አሁንም ማልቀሴን ሳላቆም የኔ ፍቅር ተረጋጊ...እቤት ነው አሁን ለልጃችን ብቻ አስቢ አለኝ እንደህፃን እያባበለኝ በዚህ በተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ሆኜ ቀናቶች ተቆጠሩ ማክ ካጠገቤ ለሴኮንድ መራቅ ፈራ ያንን ፎቶም ሆነ ፍላሽ ዳግም አላየዋቸውም ግን አንዴ ውስጤ የተቀረጸው አባቴ የገዛ ጓደኛውን ሲገል የሚያሳየው ምስል ከውስጤ አልጠፋም ተኝቼም ያባንነኛል ሙሉ ሚስጥሩን የማዎቅ ፍላጎቴ በረታ ማክ ከያንዳንዷ እርምጃዬ ጎን ነው ያንን ለማድረግ እድሉን አልሰጠኝም ነበር.... ድንገት የማክ የበፊት ሁኔታዎች ታወሱኝ ማክ ታውቅ ነበር አደል ስለዚህ ጉዳይ ለዛም ነበር ስትከላከል የነበርከው አልኩት ስለዚህ ጉዳይ ምንም እንደማያውቅ ምሎ አረጋገጠልኝ ቆይ ቢያውቅስ ምን ለውጥ አለው አባቴ እንደው አንዴ ሰው ገድሏል ምን የሚመጣ ለውጥ አለ ግን ያባቴን ወንጀል ተለባብሶ እንዲቀር አልፈቅድም ተለባብሶ የሚቀር ምንም ነገር መኖር የለበትም ለሱ ሀፂያት እዳ መክፈያ እኔን መስዕዋት ማድረጉ ጭራሽ እንድጠላውና እንድፀየፈው አደረገኝ የማዋ ካባቴ ጋር በሰላም መኖርና ከሽፈራሁ ጋር የሚያገናኛቸው ሚስጥርስ ምንድነው ሰው እንዴት ከደመኛው ጋር ፍቅር ይሆናል የማይመለስ ጥያቄ ውስጤ ተጫረ..... ድንገት ፍላሹ ትዝ አለኝ ምን አልባት የዚህ ጥያቄዬ መልስ እዛ ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክ በኔ ቅዠትና በየደቂቃው ከንቅልፌ መንቃት ምክንያት እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አድሮ አሁን ሸለብ አድርጎታል ቀስ ብዬ ካጠገቡ ተነሳሁ.....ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka23 https://t.me/eiduka

4_5983227405714590012.ogg2.04 KB

🔥ተመልሻለው ደሞ 🔥 🤎🤎 ይቅርታ ስለጠፋው 🤎🤎🔥 በልክህ ተሰርቶ ቀልዴ ቁም ነገሬ🔥🤎 👏 @Marsilas_23🥀 🦋 @Hayitiye 💝

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣4⃣ ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ሮማንቲክ አደረኩት አሁን የቀረኝ ነገር ማክን መቀስቀስ ነው ክፍላችን ስገባ ጥልቅ እንቅልፍ ወስዶታል እንደሁል ጊዜው ለረጅም ደቂቃዎች በዝምታ ስመለከተው ቆየሁ ማክን ተኝቶ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም ብዙ ነገሮች አስባለሁ ለምሳሌ ያህል እድለኛነቴን ፍቅራችንን፣ መልካም ሰው መሆኑን ፣ የዋህነቱን ፣ በተለይ ደሞ እሱ ህይወቴ ውስጥ ባይፈጠር ምን ልሆን እችል እንደነበር በቃ ይሄን ሁሉ ነገር አንዳንዴ ከዚህም በላይ ስለማክ አስባለሁ ከጥቂት ዝምታ በኃላ ከንፈሩን ስስመው ተገልብጦ ተኛ ማክዬ የኔ ፍቅር ተነስ ብዙ ተኛህ ማታ የት ልታድር ነው አልኩት ፀጉሩን እየደባበስኩት እናቴም የማክም እናት የሞቱት ገና ሳንጠግባቸው በልጅነታችን ነው፡፡ ለማክ የእናትን ያህል እንክብካቤ መስጠት ባልችልም ግን የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ ሁሌም ጥረቴ እሱን ለማስደሰት ነው አሁን ደግሞ ልጆች እንዲኖሩንና ደስተኛ የሆነ ቤተሰብ እንዲኖረን ጥልቅ ፍላጎት አለኝ የፍላጎቴ መጠን ያማልፍ ይመስለኛል ካባቱ ጋር በግድ ያስተሳሰረኝን ቃልኪዳን ሳላፈርስ የማክ እውነተኛ ሚስት ለመሆን የቆረጥኩት ማክ ከተነሳ በኃላ ባየው ነገር እጅግ ደስተኛ ነበር ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ አሳለፍን የመጀመሪያዬንም የሚስትነት ሌሊት በማክ እቅፍ ውስጥ አሳለፍኩ፡፡ እንደእብድ ከምወደው የኔ ማክ ጋር በራሳችን ፍቃድ "ሀ" ብለን የትዳር ህይወትን ጀመርን ይሄ ለኛ ልዩ ስሜት ነበረው ምክንያቱ አንድ ነው ያባቱ ሚስት ነበርኩኝ ደሞም አሁንም ነኝ ጠዋት ስነሳ አልፎ አልፎ እንደሚያደርገው ማክ ነበር ቁርስ ያዘጋጀው ማክን ሳየው የማላውቀው አይነት ስሜት ተሰማኝ አይኑን ለማየት ህፍረት ተሰማኝ ሲቀሰቅሰኝ ቀና ብዬ ላየው አልደፈርኩም እሱም ይሄን ሳይረዳ አልቀረም እንደህፃን ልጅ አባብሎ አስነስቶኝ አቅፎ መታጠቢያ ቤት ወስዶ የምለብሰው ልብስ አቀበለኝና ቁርስ ላይ እንዳልቆይ አስጠንቅቆኝ ወደሳሎን ሄደ ለደቂቃዎች ውሀ ውስጥ ቆየሁ ያሳለፍነውን ለሊት እያሰብኩ ብቻዬን ፈገግ እላለሁ አንዳንዴ ኮስተር ህመሙን ሳስበው ህልም ነበር የሆነብኝ በዚህ መሀል ነበር የማክ ጥሪ ከሀሳቤ ያነቃኝ ሄዊዬ ዛሬ ከውሀ ውስጥ ላለመውጣት ወስነሻል ወይስ ባልሽ እንዲናፍቅሽ ሙከራ እያደረግሽ ነው? ባልሽ ??? እውነትም ባሌ ማክና እኔን ማንም እልል ብሎ ሳይድረን ተጋባን በራሳችን የፍቅር ቃልኪዳን አሰርን "ባልና ሚስት" ለራሳችን የሰየምነው የክብር ስያሜ ቁርስ ላይ ሆነን ማክ እ...ተጨማሪ የሳምንት እረፍት ሳያስፈልገን አይቀርም አለኝ በፍቅር እያየኝ በሀሳቡ በደስታ ተስማማሁ ከከተማ ወጥተን አራት የሚገርሙና የተዋቡ ቀናቶችን አሳለፍን ወደ አ/አ በተመለስን ሁለተኛ ቀን አባቴ ደውሎ ሆስፒታል እንደገባ ነገረኝ አባቴ ደም ግፊት አለበት ካልሄድኩኝ ብዬ ማክን አስቸገርኩት ማክ መሄድ ካለብኝ መጀመሪያ እኔ ነኝ የምሄደው አባትሽ አንቺን ለማግኘት ሆን ብሎ ይሆናል አለኝ እንደዛ ሲለኝ ትንሽ እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ማክም እንዲሄድ አልፈለኩም ሰው ለመላክ ወሰንን የማክን ጓደኛ አባቴ ተኛሁ ያለበት ሆስፒታል ሄዶ ሲያጣራ እውነትም በዛ ሰው ስም የተኛ ሰው እንደሌለ ተነገረው አባቴ አሁንም ሊያጠቃኝ እየሞከረ ነው ግን ለምን አልኩ ለጥቂት ቀናት እረስቼው የነበረውን ያባቴን ሚስጥር ማወቅ ዳግም እንደ አዲስ አገረሸብኝ ግን እስካሁን ምንም መፍትሄ አላገኘውም ያባቴ የስልክ ጥሪ አንዳንዴ እማዋ ለማክም አባቱ ማስፈራሪያና ሲለውም ሰው ይልክበታል በዚህ ሁኔታ ሁለት ወራቶች ተቆጠሩ ቁርስ ልንበላ ገና ቁጭ ከማለቴ ነበር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማኝ ወደመታጠቢያ ቤት የሮጥኩት ማክ ተከትሎኝ መጥቷል ምን ሆነሽ ነው ሄዊዬ አለኝ በስስት አላውቅም ማክ ትላንትም እንደዚህ አይነት ስሜት ነበረኝ አልኩት በይ ወደሆስፒታል እንሄዳለን አለኝ ለባብሼ ቅርባችን ወዳለው ሆስፒታል አመራን ከምርምር በኃላ የሰማነውን ውጤት ማመን አልቻልንም ተቃቅፈን አለቀስን ተደሰትን ዘለልን በቃ የምንሆነውን አጣን በርግዝናዬ ምክንያት ማክ በጣም ነበር የሚሳሳልኝ ስራ እንዳቆም አድርጎ በቃ እቤት ውስጥ እንደሚሰበር እንቁላል ነበር እንክብካቤው ከስራ እስከሚመጣ ስልኬ ሰላም የለውም እቤት ከመጣ በኃላ ራሱ ነበር እያበሰለ ምግብ የሚያበላኝ አንዳንዴ በጣም ከመጨናነቁ የተነሳ በእንክብካቤ እስከመማረር እደርሳለሁ በዚህ ሁኔታ ሶስተኛ ወር ላይ ገብቻለሁ አንድ ቀን ማክ ስራ ሄዶ እኔ እቤት መቀመጥ ስለሰለቸኝ ግቢ ውስጥ ዝም ብዬ ወዲያና ወዲህ እያልኩ ነው ድንገት የግቢያችን በር ተንኳኳ......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣3⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ አለመሆኑን ነገሮኝ ባልደውልለት የተሻለ እንደሆነ አስጠነቀቀኝ ቢሮ ከገባሁ በኃላ ግን ደጋግሜ አባቴን ማሰብ አላቆምኩም የመጣውን ለመቀበል ራሴን አሳምኜ አባቴ ጋር ደወልኩ ገና ድምፄን ሲሰማ ነበር አንቺ መድረሻ ቢስ ምን ይሁን ብለሽ ደወልሽ አታገኘኝም ነው ... እ ... እንደናቅሽኝ እየነገርሽኝ ነው? ይኼውልሽ እናትሽ የገባችበት ጉድጓድ ብትገቢ አታመልጭኝም መድረሻ ቢስ ሰላም እንደነሳሽኝ እንደዶሮ አንቄ ለሽፈራው ካልሰጠሁሽ ወንድ አይደለሁም አለኝ ይሄንን ሁላ ሲያወርድብኝ አንድም ቃል አልተናገርኩም ብቻ ባይሆን ድምፁን ስለሠማው ትንሽም ቢሆን ደስ ብሎኛል ወይ አባ ምን ብትደብቅ ነው ሰላም አተህ ሰላም የነሳኸኝ አልኩ ለራሴ ስልኩን ዘግቼ ማክን ከሹፌሩ ጋር ሲገናኙ አብረን ብናገኘውስ ብዬ ልጠይቀው ስላሰብኩ ወደሱ ሄድኩ ማክ ቢሮ አልነበረም... ፀሀፊውን ስጠይቃት ተቻኩሎ እንደወጣ ነገረችኝ ደወልኩለት ስልኩን አያነሳም ሱማክ የትም ቢሄድ ለኔ ሳይነግረኝ አይሄድም ስልኩን አለማንሳቱ ይበልጥ አስጨነቀኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ደጋግሜ ብደውልም አይነሳም... በጭንቀት ራሴ ተወጠረ ማክ ከቢሮ ከወጣ 4 ሰዓታት ተቆጠሩ በዛ ሁኔታ ቢሮ ምንም ስለማልሰራ ወደቤት ሄድኩ... ለተጨማሪ 1 ሰዓት ጠበኩ ምንም የለም የማክ ስልክ አይነሳም... በመጨረሻም ሁሉም የማክ ጓደኞች ጋር ደወልኩ ከማንም ጋር አልተገናኘም መልሶ ካልደወለ እንድደውልላቸውና ለፖሊስ እንደምናመለክት ነገሩኝ ሁለቱ ጓደኞቹ እንደሚመጡ ነግረውኝ ስልኩን እንደዘጋሁ ስልኬ ጠራ ማክ ነበር ማክ የኔ ፍቅር የት ሆነህ ነው ለምንድነው የማታነሳው በጭንቀት ልትገድለኝ አስበህ ነው... የጥያቄ መዓት አደራረብኩበት... የኔ ቆንጆ ስላስጨነኩሽ ይቅርታ እየመጣሁ ነው አለኝ በደከመ ድምፅ ማክ የት ነህ የሆንከው ነገር አለ ድምፅህ ልክ አይደለም ምንድነው የተፈጠረው ያለህበት ልምጣ አልኩት እያለቀስኩ አያስፈልግም ማሬ እየደረስኩኝ ነው ትንሽ ታገሺኝ አለኝ ልቤ በሀይል ይመታል በጣም እያለቀስኩ ነው ምን እንደማደርግ ግራ ተጋብቼ ግቢ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እያልኩ የማክን መምጣት መጠባበቅ ጀመርኩ ከግማሽ ሰዓት በኃላ የመኪና ድምፅ ስሰማ እየሮጥኩ ወደበሩ ስሄድ የማክ ጓደኞች ነበሩ ... አዲስ ነገር ካለ ሲጠይቁኝ የሆነውን ነግሬያቸው ማክን አብረን መጠበቅ ጀመርን ትንሽ ቆይቶ ሌላ የመኪና ድምፅ ስንሰማ ሁላችንም ወጣን ዘበኛው በሩን ሲከፍተው መኪናው ውጪ እንደቆመ ነው ማንም ጋቢና የለም እየሮጥኩ ወጥቼ ሳይ ማክ በደም ተነክሮ ከኃላ ተኝቷል እየጮህኩ ጓደኞቹን ለርዳታ ጠራኻቸው ወደሆስፒታል ንዳው ብዬ አንዱ ጓደኛው ላይ ጮህኩኝ... ማክ በደከመ ድምፅ ደህና ነኝ የኔ ፍቅር አለኝ ማክ ማነው እንደዚህ አድርጎ አምጥቶ የጣለህ ማክ ክፉ ሰው ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረገው እያልኩ ያለማቋረጥ አለቅሳለሁ እሱ እንደዛ ሆኖ እኔን ለማፅናናት ይሞክራል ጓደኞቹም እንድረጋጋ እየለመኑኝ ሆስፒታል ደረስን ህክምና ተደረገለት የማክ እጁ ላይ ቅጥቅጥና ግንባሩ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ የከፋ ነገር እንደሌለውና ግንባሩ መሰፋት እንዳለበት ዶክተሩ ነግሮኝ ወጣ ከሰዓታት በኃላ ወደቤታችን ተመለስን የማክ ጓደኞች ተሰናብተውን ከሄዱ በኃላ ማክን በጥያቄ አጣድፈው ጀመር... ሄዊ የኔ ቆንጆ ተረጋጊ አባቴ ነው በቃ እንደዚህ ያደረገው ሹፌሩ ከኛ ጋር መሆን አልቻለም ከኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ላባቴ ነግሮት ነው አባቴ ከሱ ምን እንደፈለግን አውቋል በር ላይ ጥሎኝም የሄደው ሹፌር የሱ ነው አሁን መኖሪያችንን አውቋል መጠንቀቅ አለብሽ ግን አንቺን በአካል ማግኘት ነው የሚፈልገው ይሄን ደግሞ እኔ አልፈቅድም አለኝ እና እንዴት ልጁን ጨክኖ እንደዚህ ያደርጋል በጣም ተናዶብኛል ሰዎቹ ሲደበድቡኝ እንኳን ለማየት አልደፈረም ውጪ ቆሞ ነበር አንቺን እንድመልስሽ ለማስፈራራት እንጂ ሌላ ነገር ማድረግ ቢፈልግ ይችል ነበር አሁን እሱን እርሽው የኔ ማር የምትፈልጊውን ነገር በየትኛውም መንገድ አደርጋለሁ አንቺ ግን ራስሽን አደጋ ላይ የሚከት ተግባር እንዳትፈፅሚ አባቴ ቢያገኝሽ አንዴ እጁ ከገባሽ አይለቅሽም እስረኛው ነው የምትሆኚው እኔም ላድንሽ አልችልም ቢቻል ራስሽን አሳምነሽ ከዚህ አገር እንውጣ ካልሆነ ግን ታገሽ አለኝ የማክ ንግግር ጠንካራ ነበር፡፡ እኔም ያለኝን እንደማደርግ ቃል ገባሁለት ከዛን ቀን በኃላ ለሳምንት ስራ አልገባንም ነበር በጣም ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ እያሳለፍን ነው፡ የሁለታችንም ፍቅር ጨምሯል ፍቅር እንጂ እኛ ጋር ፀብ የለም ከማክ ጋር በጣም ነው የምንዋደደው ሁለታችንም ደስተኞች ነን... ዛሬ የማክ እውነተኛ ሚስት የመሆን ፍላጎቴ ጨምሯል የምንጋባበት ጊዜ ገና ገደብ የለውም ሽፈራው እስከሚፈታኝ ከታገስን ልናረጅ ነው ብቻ በቃ ከፍቅረኝነት የሚስትነት ህይወት አማረኝ ..እኔና ማክ እንደባልና ሚስት አንድ ላይ እንኑር እንጂ ገና መጋባታቸውን የሚጠባበቁ ፍቅረኛሞች ነን እኔና ማክ ለመጋባት የሚከለክለን የአባቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ደሞም ለማክ አባት የወረቀት ሚስት እንጂ የእውነት የትዳር አጋሩ አይደለሁ ይሄንንስ አምላክ ከሀፂያት ይቆጥርብኝ ይሆን አልኩ ለራሴ አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ እየተፋቀርን አንተን ፈርተን እስካሁን ቆይተናል አሁን ግን የትግስቴ ጥግ ላይ ደርሻለሁ አንተ ማረኝ አልኩ በልቤ በጣም ጣፋጭ እራት በራሴ እጅ አዘጋጅቼ ቤቱን ሮማንቲክ አደረኩት......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣2⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 በሁለተኛው ቀን ለአዙ ደወልኩላት ባባቴና በሽፈራው መሀል ምንም አዲስ ነገር እንደሌለና ግን ሽፈራውን ለማግኘት አንድ ሴትዮ መጥተው እንደነበረና ስለኔ ስም ሲያነሱ ገና ሽፈራው አዙ እንድትሰማ ስላልፈለገ እንዳስወጣትና ብቻቸውን ለእረጅም ሰዓት አብረው እንደቆዩና እንደሄዱ እሷ ምንም መስማት እንዳልቻለች በር ላይ ሆነው ግን በቃ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ሲሉት ብቻ እንደሰማች ነገረችኝ መቼ እንደነበር የተገናኙትና ደግመው መጥተው እንደሆነ ስጠይቃት ደግመው እንዳልመጡና እንዳሉትም ከሁለት ቀን በኃላ ሹፌሩ አንድ ትንሽ ፖስታ አምጥቶ ሲሰጠው እንዳየችው ሹፌሩን ስጠይቀው ከሁለት ቀን በፊት የመጡት ሴትዩ እንደሰጡት ነገረችኝ አዙ ሲዲው እንዳይሆን ታዲያ ያስቀመጠበትን ወይ ደሞ ምን እንዳረገው አላየሽም ስላት ምን አውቄ አለሜ ጋሽዬ ጥንቁቅ እንደሆኑ እያወቅሽ አለችኝ ስልኩን ከዘጋው በኃላ የናቴ ጓደኛና ሽፈራው ምን እያደረጉ ነው ምኑንስ ነው በሁለት ቀን ውስጥ የሚያሳውቁት ስለምንስ ነው ረጅም ሰዓት ወስደው ሲያወሩ የነበሩት ሹፌሩስ ለሽፈራው ምንድነው አምጥቶ የሰጠው? በነዚህ ሀሳቦች ተጠምጄ እያለሁ ድንገት ስልኬ ጠራ የእናቴ ጓደኛ ነበሩ ልቤ ሲመታ ይታወቀኛል ስልኩን እያየሁት ለማንሳት ጊዜ ወሰደብኝ ላንሳው አላንሳው በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ስልኬን አይን አይኑን እያየሁት ስልኩ ዘጋ በድጋሚ ሲጠራ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ሄ...ሄሎ አልኩኝ እየተንተባተብኩ ሄዋኔ እንዴት ዋልሽ አሉኝ ምላሽ አልነበረኝም ምን ሊሉኝ ነው ጥያቄ ውስጤ ተወጥሯል ሄሎ ሄዋኔ አሉኝ ደግመው አ....አቤት እማዋ አልኳቸው በተቆራረጠ ድምፅ ስንጠራቸው እማዋ እያልን ነው፡፡ ምነው ደህናም አደለሽ አሉኝ ...እንደምንም ራሴን ለማጠንከር እየሞከርኩ ደና ነኝ እማዋ እንዴት ነዎት አልኳቸው ምነው ጠፋሽ ባለፈው ከመጣሽ በኃላ ድምፅሽ ጠፋ እኔም እደውላለሁ እያልኩ ያው እንደምታውቂው የልጆች ነገር ከሰሞኑ ብደውልም ስልክሽ አይሰራም አሉኝ የማዋ ባለቤት የሞቱት ከናቴ ጋር በተቀራራቢ ወቅት ነበር እንደውም አስታውሳለሁ ያኔ የ9 አመት ልጅ ነበርኩ የማዋ ባል ባልታወቀ ሰው ተገድሎ ነው የሞተው ያው ዱርዬዎች ለመዝረፍ ብለው ገድለውት ይሆናል በሚል ሰበብ ነገሩ ተረሳ እንጂ እናቴና እኔ ለቅሶ ቤት ደርሰን ስንመጣ አባቴ ከናቴ ጋር በጣም እንደተጣሉ አስታውሳለሁ ምክንያቱን እረስቼዋለሁ ኧረ እንደውም በግርግር አባቴ አንድ ጥፊ አቅምሶኛል ከዛ የማዋ ባል ከሞተ ሳምንት ሳይሞላው እናቴ በድንገት አረፈች፡፡ ይገባኛል እማዋ አይመችም አልኳቸው አዎ ልጄ አይመችም አሉ ስለኑሮ ምናምን ሲጠይቁኝ ቆይተው በመጨረሻም እናቴ ስላባቴ የነገረቻቸው ነገር ካለ ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ እንደነገርኳቸውና ትዝ ያላቸው ነገር ስላለ ለዛም ሲሉ እንደወሉልኝ ነገሩኝ ስለሳቸው ምንም ያላወቀ በመምሰል ውይ እማዋዬ ምን አስታወሱ አልኳቸው ለመስማት የጓጓሁ እንዲመስል አድርጌ አይ ሄዋኔ በስልክ አይሆንም እንደው ከተመቸሽ ወደከሰዓት ብትመጪና ያቺ የምትወጃትን ሽሮ ስርቼልሽ ቡናም አብረን ጠጥተን ተጫውተሽ ትሄጃለሽ አሉኝ ምን አይነት ወጥመድ እንደተዘጋጀልኝ ባላውቅም ግን አንድ ነገር እንዳሰቡ ግልፅ ነው፡፡ ስልኩን ከዘጋው በኃላ ማክ ጋር ሄጄ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ልትሄጂ አስበሽ እንዳይሆን ብቻ አለኝ...ማክዬ አላሰብኩም ግን ሹፌሩ ለአባትህ የሰጠው ሲዲው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ ስለዚህ ማግኘት አለብን አልኩት ማክ እንድረጋጋ እየለመነኝ እሱ በየትኛውም መንገድ ሲዲውን እንደሚያመጣውና እስከዛ ምንም እንዳላደርግ አስጠነቀቀኝ ማክን በደስታ አቅፌ ሳምኩት ከስራ ወጥተን ውጪ ትንሽ ዘና ብለን ወደቤት ከተመለስን በኃላ በሀሳብ ብወጠርም ደስ የሚል ቀን አሳለፍን፡፡ እማዋ ደጋግመው ደውለው ነበር እንደነቃውባቸው እንዳያውቁ ትንሽ ራሴን ስላመመኝ ሰሞኑን ከስራ መልስ እንደምመጣ አሳውቂያቸዋለሁ ማክ አንድ ሀሳብ እንደመጣለት ነገረኝ ምን ስለው ሁሉም የቤት ሰራተኞች በኛ ሳይድ ስለነበሩ በተለይ ላባቱ በጣም ቅርብ የሆነው ሹፌሩ ብር ሰጥቶ ፋይሉን እንዲሰርቅ ማድረግ ምክንያቱም እሱ ስለሆነ ካባቴ ጋር ብዙን ጊዜ የሚያሳልፈው ብዙ ነገር ያውቃል አለኝ ማክ የፈለገ ቅርብ ቢሆን ትልቅ ሚስጥር ላያውቅ ይችላል አልኩት እኛ እንሞክር ካልሆነ ከወር በኃላ ወንድሜ ስለሚመጣ ሁሉንም ነገር ስለነገርኩት እሱ ይረዳናል አለኝ የወንድሙ ሀሳብ ጥሩ ቢሆንም ወር ሙሉ እሱ እስከሚመጣ የሚያቆይ ትግስት እንደማይኖረኝ ስለማውቅ በማክ በመጀመሪያ ሀሳብ ተስማምተን ማክ ላባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣1⃣ ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የማስታውሰውም ነገር የለም ምክንያቱም እኔ እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ስለሆንኩ በዚህ ሀሳብ ላይ ሆኜ ማክ በር አንኳክቶ ገባ ማሬ ምን ሆነሽ ነው ሰላም አይደለሽ አለኝ አዙ የነገረችኝን ቴክስቱን ማን እንዳጠፋው ሳላውቅ ልነግረው አልፈለኩም እ..... ..ደና አይደለሁም ማክ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም የደበቅኩህ ነገር ነበር አልኩ እየተንተባተብኩ ንገሪኝ ምን ደብቀሽኝ ነበር አለ በተጨነቀ አይነት ስሜት እያየኝ ማክዬ እንዳትቆጣኝ አልኩት አልቆጣም ንገሪኝ ምን ተፈጠረ ምንድነው የደበቅሽኝ ማክ ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ጥፋት ይሁን መልካም ላንተ ሳልነግርህ ከወራት በፊት የናቴ ጓደኛ ጋር ሄጄ ነገር ብዬ ቀና ብዬ አየሁት ቀጥይ በሚል አስተያየት ሲመለከተኝ ከናቴ ጓደኛ ጋር እንዳወራንና በማግስቱ በማላውቀው ቁጥር ቴክስት እንደተላከልኝ አሁን ቴክስቱን ላገኘው እንዳልቻልኩም ጭምር ነገርኩት ምንም ባለመገረም ስሜት ነበር የሚያዳምጠኝ ስጨርስ ምን እንደሚለኝ ለመስማት በጉጉት እጠብቀው ጀመር ሄዊዬ ቆይ ይሄ ነገር ለምን አይቀርብሽም ለምን አዲስ ህይወት "ሀ" ብለን አንጀምርም? በርግጥ የእናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽ አላውቅም ግን ሌላ ተጨማሪ ቴክስት ካንድ አይነት ቁጥር ተልኮልሽ ነበር አንቺ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ነበርሽ በወቅቱ ከፍቼ ሳየው አባቴ አንቺን የሚያገኝበት አጋጣሚ እየፈለገ እንደሆነ ስለተረዳው አጠፋሁት ቁጥርሽን ከየት እንዳመጡ ልጠይቅሽ ነበር ግን የባስ እንዳላስጨንቅሽ ስላሰብኩ ተውኩት አንቺም ከዛ በኋላ የረሳሽው መስሎኝ ነበር ስላልጠየቅሽ እና አሁን በምን በምን ትዝ አለሽ አለኝ በውስጤ ተመስገን ማክ ከኔ ጋር ነው ምንም አልዋሸኝም አልኩኝ ለደቂቃ ምንም ሳልናገር ቆየሁ በያ ንገሪኝ አለኝ ማክ ምንድን ነበር ሁለተኛው መልዕክት አልኩት "ይሄ የመጨረሻ እድልሽ ነው ያባትሽን ሚስጥር ማወቅ ከፈለግሽ በላክንልሽ አድራሻ ጠዋት 4 ሰዓት ነይ" ነበር የሚለው ይሄን መልዕክ ብታይ ኖሮ በርግጠኝነት ሄደሽ እራስሽን አባቴ መዳፍ ላይ ትጥይ ነበር አለኝ ማክ መሄድ ነበረብኝ ሁኔታው ከምታስበው በላይ አሳሳቢ ነው ዛሬ አዙ ጋር ደውዬ ሚስጥሩን የያዘው ፋይል ሲዲ እንደሆነ ነግራኛለች ይሄ ሲዲ ደግሞ እኔ እጅ ከገባ አባቴን እኔ ራሴ እንደሆንኩ የምበቀለው ሲያወሩ ሰምታለች፡፡ እኔ እዚህ ሲዲ ውስጥ ምን እንዳለ ሳላውቅ እንቅልፍ አይወስደኝም ምንድነው ሚስጥሩ እራሴ ሊፈነዳ ነው እባክህ አግዘኝ የኔ ፍቅር አልኩት ማክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አቅፎ ያፅናናኝ ጀመር በቃ መፍትሄ አናጣም ትንሽ ብቻ ታገሺ እራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ምን ይመስልሻል ትንሽ እንድትረጋጊ ሁኔታዎችንም ተረጋግተን ለማሰብ አንድ ሳምንት ወጣ ብለን ብንመጣ አለኝ ሀሳቡ ጥሩ መስሎ ታየኝ ወዴት እንሂድ አልኩት አሁንም ግራ እንደተጋባሁ ነኝ ዱባይ ደርሰን እንምጣ እስከዛ ነገሮችን በደንብ የምናስብበት ጊዜ ይኖረናል በዛውም ካለንበት ጭንቀት ትንሽ እናርፋለን አለኝ በሀሳቡ ተስማማሁ ከሳምንት በኃላ ዱባይ ሄደን በጣም አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፍን ነው ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ ማክ ወደበፊቱ ማንነቴ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ሆኗል ድንገት አየሽ አይደል ሁሉንም ነገር ጥለን ወደ አውስትራሊያ ብንሄድ ሁሉን ነገር መርሳት እንደምንችል አለኝ ማክዬ ለጊዜው መርሳት ስለፈለኩና አንተም ማስከፋት ስላልፈለኩ እንጂ እስከመጨረሻው ማንነቴንና ያባቴን የተደበቀ ማንነት እረስቼ መኖር አልችልም በተለይ ጉዳዩ ከኔ ጋር እንደሚያያዝ ካወቅኩ በኃላ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል ይህን ጉዳይ እልባት ካገኘሁለት በኃላ የፈለክበት እንሄዳለን አልኩት ማክ ይሄን ሲሰማ ሀሳቤን እንደማልቀይር ስላወቀ በቃ እሺ እኔም ይሄ ነገር ሰላም እየነሳኝ ነው ስለዚህ ወደኢትዮጵያ ስንመለስ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን ግን አንድ ነገር ቃል ትገቢልኛለሽ አለኝ ምንድነው ማክ የፈለግከውን አልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮኝ እንደሆነ ሲነግረኝ በመደሰት ያባትሽ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን ጠንካራ እንደምትሆኚና ምንም ለማድረግ እንደማትሞክሪ እንደዛ ሲለኝ ማክ የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ይሰማኛል አልኩት ሄዊዬ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን ያው ከሁኔታዎች አንፃር ጉዳዩ እንደሚከብድ በመጠርጠር ነው ብሎ አቅፎ ሳመኝ ነገሩ ባይዋጥልኝም ከማመን ውጪ አማራጭ አልነበረኝም የዱባይ ቆይታችንን ጨርሰን እንደተመለስን.......ይቀጥላል @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣0⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 አይ የለም ምን ይኖራል በቃ ይኼ ነገር ስለሰለቸኝ ነው አለኝ እኔ ግን ላምነው አልቻልኩም ምክንያቱም አባቱ ጋር ደርሶ ከመጣ በኃላ ወሬው ሁሉ ይችን አገር ለቀን እንውጣ ሆኗል እንዴት እንዳደኩና ማን ስለእናቴ የሚያውቀው ነገር ካለም በተደጋጋሚ እየጠየቀኝ ነው፡፡ ማክ አላመንኩም ባለፈው ከአባትህ ጋር ያወራችሁትን ንገረኝ ምንድነው ከእኔ የምትደብቀው ነገር አልኩት? ሄዊ እኔ ከአንቺ የምደብቀው ነገር የለም ምንም አልደበኩሽም አለኝ ባላምነውም እሺ በቃ ተወው አልኩት ግን ባባቴ እና ባባቱ መካከል ያለውን ሚስጥር እንድደርስበትና ሊነግረኝ እንደማይፈልግ ሁኔታው ያስታውቅ ነበር፡፡ እኔም ባባቴ ሚስጥርና በሁኔታቸው እዚህ መሆን ደስታ አጥቻለሁ ቀን ከሌሊት የማስበው ይኼ ሆኗል ማክ እኔ ወደቀድሞ ደስታዬና ማንነቴ እንድመለስ የማያደርገው ነገር የለም ከጎኔ በመሆኑ እድለኛ ነኝ ወደኋላ ተመልሼ አስተዳደጌንና አባቴ ለኔ የነበረው አመለካከት ማሰብ ጀመርኩ አባቴ ለኔ ግድ የለሽና በራሴ ጥረት ጎበዝ ተማሪ እንደነበርኩ ከማስታወስ ውጪ አዲስ ነገር ማስታወስ አልቻልኩም ከቤት ከወጣን ወራትን አሳልፈናል ማክም የራሱን ስራ እዚህ ጀምሯል እኔና ማክ አንድ ላይ ብንኖርም እስካሁን በመካከላችን የተፈጠረ አንድም ነገር የለም ግን አንዳችን በአንዳችን ደስተኞች ነን አንድ ቀን ማክ ሳላስበው የንጋባ ጥያቄ አቀረበልኝ ጥያቄው ቢያስደስትም ከአባቱ ጋር የፍቺ ውል አልፈፀምኩም እንዴት እንጋባለን የሚለው ነገር አስጨነቀኝ ማክ የፍቺ ጥያቄ እንዳቀርብ ነገረኝ እንደዚህ ካደረኩ አባቴን አቶ ሽፈራው እንደማይተው ለማክ ነገርኩት መጀመሪያ ባባቴ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ማግኘት እንዳለብን ስነግረው ሀሳቤን ባይወደውም ተስማማ የማክ በዚህ ጉዳይ ላይ ግድ የለሽ መሆን ይበልጥ የሚያውቀው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ የአባቴ ሁኔታ አስጨንቆኛል እንዴት መፍትሄ እንደማገኝ አሰብኩኝ ቀናቶች ተቆጥረው ሳምንታትን ወለዱ አንድ ቀን ሰኞ ማክን ወደስራ ከሸኘሁ በኋላ ወደ አባቴ ሰፈር ሄጄ የእናቴን የቅርብ ጓደኛ አግኝቼ እናቴ ከመሞቷ በፊት ስለአባቴ ያጫወተቻቸው ነገር ካለ ጠየኳቸው የናቴ ጓደኛ በጣም ነበር በጥያቄ የደነገጡት ምንም እንደማያውቁና በባሏና በሷ መካከል ያለ ሚስጥር ነግራቸው እንደማታውቅና ለምን እንደፈለኩት ጠየቀችኝ ዝም ብዬ ስለአባቴ ማወቅ ፈልጌ እንደሆነና ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ ቁጥሬን ሰጥቻቸው ካለ ምንም መፍትሔ ወደቤቴ ተመለስኩ በማግስቱ ጠዋት በማላውቀው ቁጥር የአባትሽን ሚስጥር ከሆነ የምትፈልጊው በዚህ አድራሻ ነይና እንነግርሻለን የሚል የፅሑፍ መልዕክት ነበር ደጋግሜ ስልኩን ስሞክር አይነሳም ቴክስትም ባደርግ አይመልስም የማደርገው ነገር ጨነቀኝ ለማክ ብነግረው ለምን እንደዚህ አደረግሽ ብሎ ይጣላኛል ደሞ ብሄድ እራሴን አደጋ ላይ የምጥል ስለመሰለኝ ፈራሁ በዚህ ውጥረት መሀል እያለሁ የናቴ ጓደኛ ከዚህ ሚስጥር ጋ ምን እንደሚያያይዛቸውና ድንጋጥያቸው ትዝ አለኝ ደግሜ እንዳላገኛቸውም ፈራሁ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንደምዘልቅ ሀሳብ ሆነብኝ የማክ ሁሉን እረስተን የንጋባ ጥያቄው አቶ ሽፈራው አባቴና የናቴ ጓደኛ ወይዘሮ እልፍነሽ ግንኙነት ሀሳብ ሆኖብኛል ጠዋት ቁርስ እየበላን ማክ ዛሬ አባትህን ፊት ለፊት ማናገር ወስኛለሁ የመጣው ይምጣ መናገር አለብኝ ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል አልኩት ማክ እንደማይሆንና እሱ በራሱ መንገድ አባቱ ጋር ያለውን ማስረጃ የሚያገኝበትን መንገድ እየፈለገ መሆኑንና ትንሽ ጊዜ እንድታገሰው ነግሮኝ ወደ ስራ ሄደ እኔ ግን ከዚህ ሚስጥር ጀርባ ያለውን ነገር ከዚህ በላይ ታግሶ የመጠበቅ ትግስቴ አልቋል እስከመቼ እንደምታገስ ባላውቅም ትንሽ ጊዜ እንድታገስ ለራሴ አሳመንኩት ስራ መስራት እንዳለብኝና ቤት መቀመጥ እንደሰለቸኝ ለማክ ነግሬው ከሱ ጋር ስራ ጀምሬአለሁ ትንሽ ቢሆንም ከቤት እየወጣው ስራ ላይ መዋሌ ጭንቀቴን ቀንሶልኛል ከማክ ጋር ያለን ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ተጋብተን እንደማንኛውም ጥንዶች ህይወትን የመኖር ፍላጎታችን እየጨመረ ነው፡፡ ማክና አባቱ ጭራሽ ተቆራርጠዋል አባቱም እኔን መፈለጉን አቁሞ አባቴ ተረኛ ፈላጊዬ ሆኗል ከስራ ስገባም ሆነ ስወጣ ከማክ ውጪ አልንቀሳቀስም የትም ስንሄድ አብረን ነው፡፡ አንዳንዴ አዙ ጋር እየደወልኩ ያለውን ሁኔታ እከታተላለው አባቴና አቶ ሽፈራው ሁሌም ይገናኛሉ ሁሌም ይጨቃጨቃሉ፡፡ አንድ ቀን ስደውልላት አባቴ እኔን አግቶ አሳምኖ ወደቤቴ ካልመለሰልኝ ሲዲውን ለኔ እንደሚሰጠኝና በኔ በልጁ እጅ እንደሚጠፋ እንደነገረው ነገረችኝ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም እየሮጥኩ የማክ ቢሮ ሳላንኳኳ ዘልዬ ስገባ ስብሰባ ላይ ነበር ይቅርታ ጠይቄ ተመልሼ ስወጣ ማክ ተከትሎኝ ወጣና የሆንኩትን ጠየቀኝ ሲጨርስ ላገኘው እንደምፈልግና ማውራት እንዳለብን ነግሬው ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ። ምንም መረጋጋት አልቻልኩም ነበር የማክ ይበልጥ ያባቴ ነገር እና ከኔ ጋር የሚያያይዘው ነገር ሰላም ነሳኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ድንገት ከወራት በፊት የተላከልኝን ቴክስት አስታወስኩ ስልኬን አንስቼ ቁጥሩን መፈለግ ጀመርኩ መልዕክቱ ስልኬ ላይ የለም አጥፍቼው እንደሆነ ለማስታወስ ሞከርኩ ግን አላጠፋሁትም ማን ሊያጠፋው ይችላል?? ማክ እንኳን ስለዚህ የስልክ መልዕክት የሚያውቀው ነገር የለም እኔም እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ነኝ ታዲያ ማን ሊያጠፋው ይችላል?..... ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 9⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 እሱዋን አመስግኜ ዘግቼ ማክ ጋር በድጋሚ ስደውል አነሳ የኔ ፍቅር ይቅርታ አሁን ነው የጨረስኩት ልደውልልሽ እያሰብኩ በአጋጣሚ እህቶቼ ደውለው እያወራው ነበር አለኝ ፍፁም መረጋጋት አይታይበትም እሺ ግን ሰላም አልመሰለኝም ድምፅህ ምን ተፈጠረ ለመስማት እየጓጓው ማሬ እየደረስኩ ነው ስመጣ እነግርሻለው ግን አታስቢ ምንም አልተፈጠረም አለኝ እኔም እስከሚደርስ በጉጉት እንደምጠብቀው ነግሬው ምሳ ምን እንደተሠራ ላይ ወደ ኪችን ሄድኩኝ ማክ ሲመጣ ግን በጣም ተረጋግቶል ምሳ እየበላን ሄዋኔ ከእኔ ጋር የትም ለመሄድ ዝግጁ ነሽ አለኝ አዎ የኔ ማር እስከአለም ጥግ ድረስ አልኩት ተነስቶ እቅፍ አርጎ ሳመኝ በቃ ወደ አውስትራሊያ እንሂድ እዛ በሰላም እንኖራለን ሁሉንም ወደ ኃላ ትተሽ ከእኔ ጋር ተጋብተን አዲስ ህይወት እንኖራለን አንቺን የሚመስሉ ቆንጆ ልጆች ትወልጅልኛለሽ ከልጆቻችን ጋር ደስተኛ ቤተሰብ መስርተን በሰላም እንኖራለን አለኝ ምንም እንኳን በማክ ሀሳብ ብስማማና ብደሰትም ያለናት ብቻውን ያሳደገኝን አባቴን ለሽፈራው አሳልፌ ልሰጠው አልፈቀድኩም በርግጥ አባቴ ለኔ ጥሩ አልነበረም አባት እያለኝ አባት እየናፈቀኝ ነው ያደኩት እሱ ለኔ መጥፎ ቢሆንም ለኔ አባቴ ነውና ክፋቱን በክፋት ልመልስለት አልፈልግም ምን አልባት የሰራው ወንጀል እንደሽፈራው አባባል አባቴን ክፋ ችግር ላይ የሚጥለው ከሆነ ፀፀቱን አልችለውም አይሆንም ማክዬ አባቴን ጥዬ መሄድ አልችልም አልኩት ልመና በተቀላቀለበት አንደበት ተነጋግረን ቃል ገብተሽልኛል አሁን ለምን ሀሳብሽን ቀየርሽ አባትሽ ምንም አይሆንም ከዚህ አገር ከወጣን አባቢ እንደማያገኚሽ ስለሚረዳ ምንም እንኳን አባትሽ ላይ የሆነ ማስረጃ አለኝ ቢልም ምንም አያደርገውም አትጨነቂ ሄዊ በቃ ወስኚ አይዞሽ እስከዛሬ ህይወትሽን ያለደስታ ኖረሻል አሁን ጥሩ ህይወትን የምትኖሪበት ጊዜ ነው ጠንካራ ሁኚ ወደኋላ አትመልከች አለኝ እኔ ያባቴ ነገር ምንም ሊሆንልኝ አልቻለም ጊዜ ወስጄ እንዳስብበት ለምኜው ዛሬ አባቱ ምን እንዳለው ጠየኩት ሄዊ የኔ ውድ በቃ ዛሬ ሁሉንም ነገር ለመስማት ሞክሪ ምንም የተለየ ነገር አላወራንም ያው ሚስቱን ከቤት ይዤበት ስወጣ ምን ሊያስብና ሊናገር እንደሚችል መገመት አይከብድም በቃ ትንሽ ተጣላን መጣው አለኝና ርዕስ ማስቀየር ጀመረ ያባቴና የሽፈራው ሚስጥር አስጨንቆኛል በምን መንገድ ማወቅ እንደምችል እያሰብኩ ነው ማክን ላለማስጨነቅና እንዳይከፋው ለማድረግ ደስተኛ ለመሆን እየጣርኩ ነው፡፡ያባቴ የመጨረሻው ንግግርና የሽፈራሁ ጋር ሊኖረው የሚችለው ሚስጥር ሰላሜን ነስቶኛል ማክ አባቱ እያፈላለገኝ ስለሆነ ከቤት እንዳልወጣ አስጠንቅቆኛል ግን ያባቴን ሚስጥር የሚያውቅ ሌላ ተጨማሪ ሰው ማን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ጀመርኩ ማወቅ አለብኝ ከዛ በኋላ አባቴን ከችግሩ የሚወጣበትን መንገድ አመቻችቼ ከማክ ጋር አዲስ ህይወት መስርቼ በሰላም መኖር ይሄን ካላደረኩ ግን ደስተኛ ሆኜ መኖር እንደማልችል አውቃለሁ አንድ ቀን ጠዋት አዙ ጋር ስደውል አባቴ ከሽፈራው ጋር ሲጨቃጨቁ ቆይተው አሁን እንደወጣ ነገረችኝ የተነጋገሩትን ነገር ሰምታ እንደሆነና እንዳልሆነ ስጠይቃት ሽፈራሁ በገዛ ልጅህ አማካኝነት ወቀመቅ እንድትወርድ ነው የማደርግህ ሲለው እንደነበርና አባቴ በጣም ሲለምነው እንደነበር ነገረችኝ ሌላ ተጨማሪ ነገር ሰምታ እንደሆነ ስጠይቃት አይ ይኼን ብቻ ነው የሰማሁት አለችኝ ከኔ ጋር ሊያገናኘው የሚችለው ነገር ምንድነው ለምንስ በኔ ያስፈራራዋል በቃ በጭንቀት እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ ለማክ ነገርኩት፡፡ ማክ ምንም አልተገረመም ነበር ምነው ማክ የምታውቀው ነገር አለ አልኩት በጥያቄ አስተያየት እያየሁት እ.....ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 8⃣ ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 የማክ አባት ለማክ ወደ አውስትራሊያ መቼ ልትመለስ አሰብክ አለው ማክ አባቱ ቶሎ ሊገላገለው መፈለጉን ቢረዳም እንዴ አባዬ ሰለቸውህ እንዴ አለው በቀልድ መልክ አይ ነገሩን ነው ለእህቶችህ የምትወስደውን ነገሮች እንድናዘጋጅልህ ነው አለው ለመሄድ እየተነሳ ሽፈራው እንደወጣ ካረጋገጥን በኃላ እኔና ማክ ልክ ከተገናኘን የቆየን ይመስል ተናንቀን ተሳሳምን ማክ ይሄ የድብቅ ህይወት ማብቃት አለበት አልኩት ልክ ነሽ የኔ ፍቅር እኔም እያሰብኩበት ነው አለኝ ግን እንዴት እንደሆነ ለሁለታችንም ግራ ገብቶናል ማክ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ ለምን አንወጣም አልኩት አዎ እንደውም ልወስድሽ ያሰብኩበት ቦታ አለ ዛሬ አለኝ የት አልኩት እንደህፃን እየተቁነጠነጥኩ እሱማ ሰርፕራይዝ ነው ባይሆን ተነሽ ልበሽና እንውጣ አለኝ ጊዜ አላባከንኩም እየፈነደኩ ወደ ላይ ስወጣ ማክ በግርምት ቆሞ ያየኛል ልብሴን ለመልበስ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበር ለባብሼ ከመቅፅበት ወጣው አቤት ፍጥነት ይሄኔ ሰርፕራይዝ ባይሆን ባመትሽም አትወጪም ነበር አለኝ ከእቅፉ እያስገባኝ ታዲያ ሁሌ ቶሎ እንድወጣ ለምን ሰርፕራይዝ አታዘጋጅም? አልኩት እየሣምኩት እኔና ማክ ብቻችንን ስንሆን አለምን እንረሳለን በቃ ምንም ትዝ አይለንም አሁን እንኳን እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ እያለፍን እንኳን በኛ ፍቅር መካከል ምንም የተቀየረ ነገር የለም እንደውም ፍቅራችን በጣም እያማረበት ነው አንዳችን ካላንዳችን መኖር እስከማንችል እስከሚመስለን ድረስ ፍቅር ጨምረናል ልክ ማክ ያለኝ ቦታ ልንደርስ ስንል አይኔን እንድጨፍን ነገረኝ ማክዬ ቸኮልኩ አልኩት ደርሰናል ብሎ መኪናውን ሲያቆም ተሰማኝ አይኔን እንደጨፈንኩ በማክ መሪነት ወደሚገርመው የማክ ሰርፕራይዝ አመራን አይኔን ማመን ነበር ያቃተኝ እኔ አላምንም ብዬ ማክ ላይ ተጠምጥሜ የደስታ እንባ አነባሁ ማክ ወደገዛው አስደናቂና ውብ ቤት ስንገባ እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልዕልት የሚል በሰፋፊው ተፅፏል ቤቱ በሚያማምሩ የቤት እቃዎችና አበባዎች አሸብርቋል፡፡ ደስታዬ ወደር አጣ የምናገረው ጠፋብኝ ማክ ላይ ተጠመጠምኩበት እንደኔ የታደለች ሴት አለም ላይ የለችም እኮ አልኩት እየሳምኩት እኔም እድለኛ ነኝ አባቴ አንቺን ስላመጣልኝ አለኝ ወዲያው ደስታዬ ጠፋ የረሳሁትን ነገር አስታወሰኝ ማክ የፊታችን ገፅታ መቀያየር አይቶ አትዘኝ የኔ ማር የምታዝኚበት ቀን አብቅቷል አለኝ እንዴ ማክ አልኩት ሽሽሽ....አለኝ ወዳንገቱ ስር እያስገባኝ በቃ አብቅቷል አለኝ ያባትና የልጅ ፍልሚያ ተጀመረ የዛን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ውጭ አደርን፡፡ ሽፈራው ደጋግሞ ቢደውልም አላነሳንም ማክ ሁሉንም ነገር ተዘጋጅቶበት ነበር እኔ ሳላውቅ ከአዙ ጋር ተመካክረው ጠቃሚ የምላቸውን ነገሮችና ልብሶች በሻንጣ አዘጋጅተዋል እሱም እንደዛው በሁኔታው መገረሜን እስካሁን አላቆምኩም ሁሌም የማክ መልካምነት ይገርመኛል ቤታችን የመጀመሪያዋን ለሊት አሳለፍን የነፃነት ትንፋሽ እየተነፈስኩ አደርኩ ከማክ ውጪ የነበርኩዋቸው አስቀያሚ ትርጉም አልባ ጊዜቶች ሳስታውስ ይበልጥ ነፃነት ታወቀኝ ማክን እንደተኛ ይበልጥ እቅፍ አደረኩት ማክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ አትተኛም እንዴ የኔ ውድ አለኝ ደረቱን ተደግፌ አሸለበኝ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችንን አስቆጥረናል ከቤት ከወጣን ሽፈራውና አባቴ እያፈላለጉን እንደሆነ አዙ ነግራናለች ማክ አባቱን ማናገር እንዳለበትና ነገሮችን በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማይችሉ ነግሮኝ ከቤት ወጣ፡፡ ማክ አባቱን አናግሮ እስከሚመጣ በጭንቀት ሞትኩ በተደጋጋሚ ስደውልለት አያነሳም ሲጨንቀኝ አዙ ጋር ስደውል ማክና አባቱ ለረጅም ሰዓት ሲጨቃጨቁ ቆይተው በመጨረሻም ተጣልተው እንደተለያዩ እና ከቤት ከወጣም እንዳልቆየ ነገረኝ......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

     #ቀናሽ አሉ በቆምሽበት ሌላ ሳቆም ማዶ ሆነሽ አየሽ አሉ ስሜን ጠራሽ ጮሽም አሉ አውለበለበሽ በጅሽ ሁሉ በእንባ ጠፋ የአይንሽ ኩሉ ግን ስህተቱ አንቺ ጋ ነው አጉል ቅናት መለየት ነው ሺ ቢመጣ ሚወደድ ሰው ንግስቴ አንቺ  ፍቅሬ እኮ ላንቺ ነው 👸❤️‍🔥         @eiduka

💘😔🌹😔❤😔 #አለሁ..😔 መንገድ ዳር ቁጭ ብየ አግዳሚ እያየሁ የሚያስጠብቀኝን ይኸው 'ጠብቃለሁ አልፎ ሂያጅ መኪና መንገደኛ ጥንዶች ብርድ ያዘለ ንፋስ ሚጓረሱ ወፎች ጠቁሮ የተቆለለ አልቃሻ ደመና ፀሐዩዎን ለመከለል እድሜው የማይፀና መንገደኛ ዝናብ ምሽቱን አስታኮ ጨረቃን እንዳላይ በሰይጣን ተልኮ ሌተ ቀን መንገድ ዳር እንዲያም ሲል ከቤቴ ተጎሳቁየ አለሁ ለዛች ልጅ ናፍቆቴ.. 💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘 ✍Daniel😑eidu ,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,         •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•         @eiduka 🦋🦋

የአንተም ጊዜ ይመጣል! "ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??” ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ” የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡ የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል" ❤️❤️❤️ @eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 7⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ማክ በሩቅ ሁኔታዬን አይቶ ከመኪናው እየወረደ ምነው ፍቅር ምን ሆንሽ ተረጋጊ እንጂ ታውቆሻል እንዴት እንደሆንሽ ብሎ አቀፈኝ ማክ እባክህ አርቀህ ከዚህ ውሰደኝ አልኩት ምን እንደሚል ግራ ገብቶት ካስገባኝ በኃላ ወዴት እንደሚሄድ እንኳን ሳያውቅ ነዳው መንገድ ከጀመርን በኃላ ነበር ወዴት ልንዳው ብሎ ጠየቀኝ ደስ ወዳለህ ግን በቃ ፀጥ ያለ ቦታ አልኩት በሚያስገርም ፍጥነት ከከተማ የሚያስወጣውን መንገድ ያዘ፡፡ እኔ ዝም እንዳልኩኝ ነኝ ማክ አልፎ አልፎ ምን እንደሆንኩ እየጠየቀኝ ነው ማልቀስና ዝም ብቻ የሆነ ጭር ያለ ቦታ ላይ ስንደርስ አቆመ ምንድነው የኔ ቆንጆ በጭንቀት ልትገይኝ እኮ ነው አለኝ ማክ ሁሉም ነገር ተስፋ የለውም አልኩት እያለቀስኩ በጭንቀት እያየኝ የሆንኩትን ጠየቀኝ አባቴ ያለውን ስነግረው ለደቂቃዎች ዝም ብሎ ባባቢና ባባትሽ መካከል ያለው ሚስጥር ከባድ ነው ማለት ነው አለኝ አዎ በትክክል አልኩት ስለዚህ አባትሽ ለሱ ሚስጥር ብሎ ለሚስጥሩ ከሸጠሽ አንቺ ለምን ተባባሪው ትሆኛለሽ ከኔ ጋር ነሽ በሀሳቤ ትስማሚያለሽ አለኝ በቆራጥነት የአባቴ የጭካኔ ፈተና ሁኔታው ታወሰኝ አዎ ማክ ከአንተ ጋር ነኝ አልኩት እንግዲያውስ ነይ ብሎ መኪናውን አዙሮ ተመለሠ ማክ ምን ሰልታደርግ ነው አልኩት አባቴን ላናግረው ነው እንደምንዋደድ ነግሬው ያመጣውን ያምጣ ካስፈለገውም ቤት ለቀን እንወጣለን አለኝ ማክና አባቱ በእኔ ምክንያት እንዲጣሉ አልፈልግም ማክን በስንት ልመና አባቱ የሰጠኝ ገደብ ስላለ እስከዛ ተረጋግተን መፍትሔ እንፈልጋለን አሳምኜ ሀሳቡን አስቀየርኩት ወደ ቤት ስንመጣ የማክ አባት ቤት አልነበረም እንደምንም ወደ በፊት ደስታችን ለመመለስ ሞከርን ምሳ እየተሳሳቅን በፍቅር በላን ትንሽም ቢሆን ካለንበት ሙድ ወጣን ማክ ሻወር እስከሚጨርስ ያባቴን ንግግር ማሰብ ጀመርኩ ምንድነው የአባቴ ከባድ ሚስጥር ለምንስ እንደዛ ደነገጠ የኔ የልጁ ሚስጥሩን ማወቅ ቢረዳው እንጂ ምንድነው ጉዳቱ ይሄን እያብሰለሰልኩ ማክ በሩን ከፍቶ ወጣ ማክዬ ይሄን ደረት እንዴት እንደምወደው እኮ አልኩት ከንፈሩን እየሳምኩ አስቀናሽኝ እኔንስ አለ እየቀለደ አይ ....አይ አንተንኳን አይመስለኝም አልኩት በዚህ እየተቃለድን ቤቱን ስንዞረው አዙ ድንገት በሩን በርግዳ ገባች ጋሽዬ መጡላችሁ አለችን ማክም እኔም ወደየክፍላችን እሮጥን ይሄ የቃቃ ጨዋታ መቼ እንደሚያልቅ ጨነቀኝ ያባቴ የክፋት ፊትና የሽፈራው ዛቻ ሳስበው እንባዬ ሳይታወቀኝ ሲወርድ ተሰማኝ አባቴ ለኔ ግድ የለውም ቢሆንም እኔ ግን አባቴ ነውና እወደዋለው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የአባቴንም ሆነ የኔን ህልውና ልታደግ የምችልበት መፍተሄ እንዴት እንደማገኝ ማሰብ እንዳለብኝ ወሰንኩ ያባቴ ለኔ ያለው ጥላቻና ግዴለሽነቱ ምንነቱን በማላውቀው ሚስጥር ምክንያት እንዲጎዳው መፍቀድ እንደሌለብኝ ወሠንኩ፡፡ ያባቴ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን አሳልፌ ልሰጠው አልፈቅድም፡፡ ምንም ቢሆን አባቴ ነዋ......!! ግን በዚህ ባንድ ሳምንት ውስጥ ምን አይነት ተአምር መፍጠር እና ከዚህ ችግር ማምለጥ ይቻላል ግራ ተጋብቻለሁ ይህን እያሰብኩ ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ አሳለፍኩ ማክም እኔም በጭንቀት የማይገፋ ለሊት አሳለፍን በማግስቱ ጠዋት ሁላችንም ለቁርስ ተሰብስበናል ድንገት የማክ አባት......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ @eiduka https://t.me/eiduka

#ስጀምር ማፍቀር ምንማለት ነው እያልኩ የነበረ በኔ ሲደርስብኝ ገባኝ እያደረ ለካ ማፍቀር ማለት ስለሰው መኖር ነው ከራስ ላይ ቀንሶ ለሰው መጨነቅ ነው አይመስለኝም ነበር ተችሎ የሚኖር የራስን ፍላጎት የትም ሚወረወር ሳፈቅር ግን ገባኝ ላንቺ ብቻ ሳስብ ማፍቀር እንደሚልቅ ከሰው አስተሳሰብ አዎ ዛሬ አወኩኝ የፍቅርን ትርጉም ለካ የተፈቃሪን ህመም ነው አብሮ መታመም አሁን ግን ኮራሁኝ አፍቃሪ ስለሆንኩ ለራሴ ብቻ ሳይሆን ለሰውም ስለኖርኩነው #Hani            @eiduka @eiduka

​​​​​​​​​​🌹​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍..........🌹 ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 6⃣🌷🌺 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ አምላኬ ሆይ አንተ ትግስቱን ስጠኝ አልኩኝ በውስጤ ደስታዬ ላይ ውሀ ቸለሰበት ክፍሌን ዘግቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ምንድነው የማረገው አሁን ለማክ ልንገረው ወይስ ይቅር እያልኩ ሳስብ ማክ ደወለ ሄዋንዬ እስካሁን ተኝተሻል እንዴ አለኝ ገና መነሳቱ ነበር አይ ቆየው አልኩት ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ በስልክ አይሆንም ናና እናወራለን አልኩት ደቂቃ አልፈጀበትም ነበር አባቱ ያለውን ስነግረው በጣም ደነገጠ ምን ማድረግ እንዳለብን እያሰብን በቃ አይዞሽ አንቺ ብቻ አትከፊ መፍትሔ አናጣም አለኝ ድንገት ለምን አባትሽ እና አባቴን የሚያስተሳስራቸውን ነገር አባትሽን አጠይቂውም ከዛ በምንችለው መንገድ ዶክሜንቱን መውሰድ ከዛ በኃላ ያለውን ነገር እንጋፈጣለን አለኝ አባቴ ለነገሮች ድብቅና ሀይለኛ እንደሆነ ባውቅም በማክ ሀሳብ ተስማማው ጥሩ በቃ ዛሬ ከአባቴ ጋር እናወራለን አልኩት ተነስቼ እንድተጣጠብና አባቴ ጋር አብረን እንደምንሄድ እሱ ውጪ እንደሚጠብቀኝ ተነጋግረን እሱም ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡ በተባባልነው መሠረት ወደ አባቴ ጋር ለመሄድ ስንወጣ የማክ አባት ወዴት ነው አለን ከላይ መኝታ ቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ እንዴ አባዬ አለህ እንዴ አለው ወደ አባቱ እየተመለከተ አዎ አለው ወዴት ነው አለ ደግሞ እየጠየቀ ምን ትላንት ለሰው መስጠት የነበረብኝ እቃ ነበር ቦታውን ስላላወኩት አሁን ሄዋንን አሳይኝ ብያት እሺ ብላኝ እየሄድን ነው እንዳለህ አላወኩም ነበር አለው ጥሩ ቶሎ ተመለሱ አለው ፊቱ ሳይፈታ ዋናው መፍቀዱ ነው አልኩ ተመለሽ የሚለኝ መስሎኝ በጣም ፈርቼ ነበር ከግቢ እንደወጣን ተረጋጊ የኔ ቆንጆ ብሎ ሳመኝ ማክ ፈራሁ አልኩት እጁን አጥብቄ ይዤ አትፍሪ ምንም አይመጣም መቼም አንለያይም ካልሆነ እንጠፋለን አለኝ ለመቀለድ እየሞከረ እስኪ አትቀልድ ለራሴ ጨንቆኛል አልኩት አይዞሽ የኔ ቆንጆ ሁሉም ይስተካከላል አለኝ አባቴ ቤት ደረስን አናግረሻቸው ነይ አለኝ ማክ እሱም ጨንቆታል አባቴ ቁጭ ብሎ ስልኩ ላይ ካርታ ይጫወታል አባዬ አልኩት እንዴ ሄዋኔ ምን እግር ጣለሽ ለምን መጣሽ አለኝ ቀና ብሎ እየሳመኝ እንዴ እንደዚህ ይባላል እንዴ አልናፍቅህም አልኩት አይ እንዴት ሳትነግሪኝ ብዬ ነው አለኝ ምንም ሳይመስለው አባቴ ለኔ ግድ የለውም ሁሌ ይገርመኛል እናቴ ከሞተች በኃላ ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው ያደኩት ፈልጌህ ነበር አባ አልኩት አሁንም ቀና ብሎ ሳያየኝ ምነው በሰላም አለኝ አዎ ምንድነው አቶ ሽፈራው አንተን የሚያስፈራራበት ሚስጥር ምንድነው አልኩት የሰማውን ማመን አልቻለም በጣም ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለና አንቺ እንዴት አወቅሽ ሊመታኝ በሚመስል ሁኔታ አፍጥጦ እንዴ አባ የዚህን ያህል ከባድ ሚስጥር ነው እንዴ ለኔ ለልጅህ የማይነገር ?? አልኩት ልጅ ያሳጣሽ ዝም በይ ብሎ ጮኸብኝ ሁኔታው በጣም ነበር የሚያስፈራው ምንም ሳልተነፍስ ጥጌን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ ነኝ አባቴ በንዴት ቤቱን እየዞረው ነው ድንገት ቆም ብሎ ቆይ አንቺ በመሀላችን ሚስጥር እንዳለ በምን አወቅሽ አለኝ ስሩ እስጊገተር እየጮኸ እ ....ያው ሽፈራው ነው የነገረኝ አልኩት እየተንቀጠቀጥኩ እኮ እንዴት አለኝ አይኑን እንዳፈጠጠ እ ...አብረን መተኛት አለብን ነው የሚለው አልኩት ቃላቱን ለመጨረስ እየፈራው ያባቴ ንዴት ይባስ ጨመረ እና ለምን አተኝም ታዲያ ያገባሽ የቤቱ ጌጥ ሊያረግሽ ኖሯል አንቺን ቤቱ አስቀምጦ የሚቀልብበት ምንም እዳ የለውም ትሰሚኛለሽ ምንም ጊዜ ሳታባክኚ አሁኑኑ ሄደሽ ይቅርታ ጠይቀሽ የሚልሽን ካለምንም ድርድር ፈፅሚ አለኝ ቁርጥ ባለ ድምፅ ጌታዬ ሆይ መፍትሔ ፍለጋ መጥቼ ጭራሽ አጣብቂኝ ውስጥ ልግባ አልኩኝ ለራሴ፡፡ አሁን ማጉረምረሙን ትተሽ ዳይ ወደ ባልሽ ደሞ ከኔ ጋር እንዳወራንም ሆነ እንደመጣሽ እንዳትነግሪው አለኝ ቦርሳዬን አንሴቼ ሳልሰናበተው እንኳን እየሮጥኩ ወጣሁ......ይቀጥላል ꧁༺༒༻꧂ ​​ @eiduka https://t.me/eiduka