en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
609
Subscribers
-124 hours
-37 days
-1130 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ጥር ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን #በቤተ_ልሔምና_አውራጃው ላሉ ንጉሥ ኄሮድስ በግፍ ለገደላቸው #ለዐሥራ_አራት_እልፍ_አራት_ሺህ_ለንጹሐን_ሕፃናት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓልና  ከዘጠኙ ቅዱሳን ቀድመው ወደ አገራች ኢትዮጵያ ለመጡ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የሴቶችን ጠጉር ሹሩባ ሲሠሩ ከኖሩ# ከአባ አሞን፣ ከታላቁ ነቢይ #ከቅዱስ_ኢሳይያስና_ከቅዱስ_ስምዖን ግብፃዊ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                   ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን ኄሮድስ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸው ከዚያም በታች የሆኑ በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ ሁሉ ያሉ ሕፃናት ተገደሉ። ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት እልፍ ከአራት ሺህ ነው እነርሱም ከሴቶች እንደ ተወለዱ ንጹሐን የሆኑ ናቸው። ❤ በከበረ ወንጌል እንደተነገረ ሰብአ ሰገልም ከሔዱ በኋላ "እነሆ ኄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ ተመለስ ብዬ እስከምነግርህም ከዚያ ኑር" ብሎ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ነገረው። እርሱም በሌሊት ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብጽ ሔደ ኄሮድስ እስቲሞት ድረስም በዚያ ኖረ ከእግዚአብሔር ዘንድ "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ። ከእነዚህ ውስጥ የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስ አንዱ እንደሚሆን ኄሮድስ አስቧልና። ❤ ጌታችንም ሥራውን ሁሉ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር ሠራ በረቀቀ ጥበቡም ከኄሮድስ ፊት ሸሸ ኄድሮስ አግኝቶት ሊገድለው ቢአስብ ያለ ጊዜው መግደል ባልተቻለውም ነበርና ሰነፎች ሰዎች ሰው መሆኑን ምትሐት ነው ብለው በአሰቡ ነበር ስለዚህ የክብር ባለቤት ጌታችን ሸሸ ሁለተኛም እግዚአብሔር "በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል" ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ዳግመኛም ከክፉ ነገር እንድንሸሽ ለእኛ ሊአስተምረን የግብጽንም ጣዖታት ያጠፋቸው ዘንድ ነው። ❤ ይህን ያህል ብዛት ያላቸውን ሕፃናት መሰብሰብና መግደል ለኄሮድስ እንዴት ተቻለው ተንኰለኛ ኄሮድስ ምክንያት ፈጥሮ "የሁለት ዓመትና ከዚያም ያነሱ ሕፃናትን አሳድገን ጭፍራ እንሠራለት ዘንድ የሚያዝ የንጉሥ ነገሥት ቄሣር ደብዳቤ ከእኔ ዘንድ ደርሷል ወርቅ፣ ብር፣ ቀለብ ልብስም እንሰጣለን" ብሎ ወደ አገሩ ሁሉ ላከ። ስለዚህም ከእናቶቻቸው ጋር ተሰብሰቡ ያን ጊዜ ከእርሱ ዘንድ አንድ ሽህ ሁለት መቶ ወታደሮችን አውጥቶ በተራራ ላይ አረዱአቸው። ነቢይ ኤርምያስም የተናገረው ተፈጸመ "ራኄል ስለ ልጆቿ ስታለቅስ ብዙ መከራ ጨኸት ሙሾ ልቅሶ ዋይታ በራማ ተሰማ ልቅሶ መተውን መጽናናትን እምቢ አለች ልጆቿ ልጆችን አልሆኗትምና"። ❤ ዮሐንስም በራእዩ እንዲህ አለ "በታላቅ ቃል ጮኹ የተመሰገንህ እውነተኛ አቤቱ እስከ መቼ ነው ስለ ደማችን ተበቅለህ በምድር ላይ በሚኖሩ ሰዎች አትፈርድባቸውምን?" አሉ። ከእነርሱም ወገን ለየአንዳንዱ ብሩህ ልብስ ሰጥተው "እንግዲህ ጥቂት ቀን ዕረፉ" አሉዋቸው። እንነርሱ ይሞቱ ዘንድ ያላቸው ወንድሞቻቸው እስከሚፈጸሙበት ቀን ድረስ እንዲህ የእሊህን ሕፃናት ነፍሳቸውን አይቷልና። ❤ ዳግመኛም እንዲህ አለ "በዙፋኑ ፊት በአራቱ እንስሶችና በሃያ አራቱ አለቆች ፊት አዲስ ምስጋና ያመሰግናሉ ከግብጽ ምድር ከተዋጁ ከዐሥራ አራት እልፍ አራት ሽህ በቀር ያቺን ምስጋና ሊያውቃት የሚቻለው የለም። እነርሱ ከሴቶች እንደ ተወለዱ ንጹሐን የሆኑ ናቸው"። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                                                ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ዕለት የሴቶችን ጠጉር ሹርባ ሲሠራ የኖረ #የአባ_አሞን መታሰቢያው ነው። እንዲህ ባለ ሥራም ሲኖረሰ የኃጢአት ማዕበል ሊአሠጥመወሰ አልቻለም በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አመረን። ምንጭ፦ የጥር 3 ስንክሳር።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በርህ ሠረቀ ለጻድቃን። ወለርቱዐነ ልብ ትፍሥሕት። ይትፌሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር"። መዝ 96፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ። ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም። መዝ 43፥22-23። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 11፥25-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥1-11 እና የሐዋ ሥራ 28፥17-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥13-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቤተልሔም የመቶ አርባ አራት ሺህ ህፃናት የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሊባኖስ የዕረፍት በዓልና የብርሃን ልደቱ በዓል ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።

ወስዶ በዚያ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱም በሰለቸው ጊዜ ትከሻውን በሰይፍ ይሠነጥቁ ዘንድ ራሱንም ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ መሞቱን አውቆ አማንያን ከሆኑ መርከበኞች አንዱን እንዲህ ብሎ አዘዘው "ወደ ወደቡ ስትደርሱ ሥጋየን በኮረብታ ላይ አድርግ" እርሱም እንዳዘዘው አደረገ። ❤ ከዚህም በኋላ ምዕመናን ሰዎች መጥተው ሥጋውን ወስደው ገነዙት የስደቱም ወራት እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተደረጉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አላኒቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኚ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 2 ስንክሳር።                                                     ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይንዕዋ ለነፍሰ ጻድቅ። ወይኴንን ደመ ንጹሐ። ወኮነኒ እግዚአብሔር ፀወንየ"። መዝ 93፥21። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥1-8፣ 1ኛ ዮሐ 3፥6-13 እና የሐዋ ሥራ 12፥18-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 23፥13-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አቤል የዕረፍት በዓልና የብርሃን ልደቱ በዓል ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ጥር ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ለሙታን_መዠመርያ በወንዱሙ ቃየን ተገድሎ ደሙ በግፍ ለፈሰሰ #ለጻድቁ_ለቅዱስ_አቤል ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና #ለሕርቃስም_ልጅ ሕልምን ለምትተረጒም #ለነቢዪት_ለቅድስት_ሳቤላ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ አባት ከኤጲስቆጶስ #ከአባ_አላኒቆስ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ ከእስክድርያ ዐሥራ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ ከከበረ አባት #ከአባ_ቴዎናስ ዕረፍት፣ በአባ ሲኖዳ ገዳም ውስጥ #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያኗ ከከበረችበት፣ #ከቅዱስ_ፊላታዎስ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሩ #ከዘጠኝ_ሽህ_ሰባት_መቶ ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ #የሙታን_በኵር_ጻድቁ_ቅዱስ_አቤል፦ ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፎ እንዳይበላው የታዘዘውን ዕፅ በላ ያን ጊዜ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞት ሠለጠነ ለኃጢአትም ተገዥ ሆነ። ሰይጣንም ሰውን ለማሳት ሠለጠነ ከዚህም በኋላ አዳም ከገነት ወጥቶ ወደታችኛዋ ምድር ወረደ ስለ በደለና የፈጣሪውንም ትዕዛዝ በመተላለፉ ፈጽሞ እያዘነና እያለቀሰ መቶ ዓመት ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ አዳም ሔዋንን በግብር አወቃት ፀንሳ ቃየልንና እኅቱን ኤልዩድን ወደለች ሁለተኛም ዐወቃት አቤልንና እኅቱን አቅሌማን ወለደቻቸው አዳምም ሔዋንን "እነሆ ልጆችሽ አካለ መጠን አደረሱ ጐለመሱ ቃየል የአቤልን እኅት አቅሌማን ያግባት አቤልም የቃየልን እኅት ኤልዩድን ያግባት" አለ። ቃየልም እናቱን ሔዋንን እንዲህ አላት "ለእኔ ከእኔ ጋር የተወለደች እኅቴን ማግባት ይገባኛል አቤልም ከእርሱ ጋር የተወለደች እኅቱን ያግባ" ቃየል ከእርሱ ጋር የተወለደ ኤልዮድም እናቷ ሔዋንን የምትመስል እጅግ የምታምር መልከ መልካም ናትና። ❤ አዳምም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ ጭንቅ ሆነበት ቃየልንም "አብራህ የተወለደች እኅትህን ታገባት ዘንድ አይገባህም አለዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቅርቡና መሥዋዕቱን ለተቀበለው ይሁን" አለው። መሥዋዕትንም በአቀረቡ ጊዜ የአቤልን መሥዋዕት እግዚአብሔር ተተቀበለ የቃየልን ግን አልተቀበለም ስለዚህም ቃየል ፈጽሞ አዘነ ሰይጣንም ተገናኘውና "ምን ያሳዝንሃል?" አለው ቃየልም "ለወንድሜ ለአቤል እኅቴን እተውለት ዘንድ አባቴ አዘዘኝ" አለው። ሰይጣንም "ምክርን ከኔ ስማ ወንድምህን ወደ ውኃ ምንጭ ይዘኸው ሒድ ውኃንም ሲጠጣ ራሱን በደንጊያ ምታው በሞተ ጊዜ ሁለቱንም ታገባቸዋለህ የሚከለክልህ ማነው" አለው ለቃየልም የሰይጣን ምክር ደስ አሰኘው ልቡም በዝሙት እሳትነት ነደደ ሰይጣን እንዳስተማረውም ወንድሙን አቤልን ገደለው ለሴት ስለ መቅናትም ጻድቁ አቤል በወንድሙ እጅ ሞተ እንዲህም ሞት ወደ ዓለም ገባ። ❤ እግዚአብሔርም ቃየልን "ወንድምህ አቤል ወዴት ነው" አለው። ቃየንም "አላውቅም በውኑ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝን" አለው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው "ቃየል ምን አድርገሃል የወንድምህ የአቤል ደም ጩኸት ከምድር ወደኔ ደርሷል። አሁንም በእጅህ የፈሰሰውን የወንድምህን ደም ትጠጣ ዘንድ አፍዋን የከፈተች ምድር የተረገመች ትሁን አንተ ታርሳታለህና በረከቷን ትሰጠሰህ ዘንድ አትጨምርም በምድር ላይ ፈሪ ተቅበዝባዥ ሁን"። ይህም መርገም ዘሩ በጥፋት ውኃ ከምድር ገጽ እስከ ሚደመሰስ በቃየል ላይ የበዛ ሆነ። ❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም ጸሐፍት ፈርሳውያንን ሲዘልፋቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነቢያትን፣ ሊቃውንትን፣ ጥበበኞችን ወደናንተ እልካለሁ ከነርሱ የምትገድሉት አለ የምትሰቅሉትም አለ በምኵራባችሁ የምትገርፋት አለ ካንድ አገር ወዳንድ አገር ታሳድዷቸዋላችሁ። ከጻድቁ ከአቤል ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እሰሰከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በዓለም የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርስ ዘንድ"። ❤ ቅዱስ ጳውሎስም አለ "ቃየን ካቀረበው መሥዋት ይልቅ አቤል በሃይማኖት ለእግዚአብሔር ያቀረበው መሥዋዕት ተሻለ" ስለ እርሱም ደግ እንደሆነ መሰከረለት መሥዋዕቱንም በመቀበሉ ምስክሩ እግዚአብሔር ነው ደግ እንደሆነም ከሞተ በኋላ ተናገረ። ❤ ከዚህም በኋላ አዳም ልጁን በአጣው ጊዜ "ወንድምህ አቤል ወዴት አለ" ብሎ ቃየልን  ጠየቀው ቃየልም በቁጣ "አላውቅም" ብሎ መለሰ አዳምም ልጁን ይፈልግ ዘንድ ወደ ዱር ሮጠ በወንዝ ዳርም በድንኑን አገኘና አንገቱን አቅፎ "ማን ገደለህ?" አለው ከበድኑም "ወንድሜ ቃየን ገደለኝ" የሚል ቃል ወጣ። አዳምና ሔዋንም በልጃቸው በአቤል ሞት ሃያ ስምንት ዓመት ያህል ሲያለቅሱ ኖሩ። ❤ ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ አዳም መጥተው "የዓለሙ ሁሉ አባቶች አባት አዳም የምሥራች እነሆ ልጅህ አቤል የገነትን ዛፎች ተሳለመ ነፍሱም እንደ ተወደደ መሥዋዕቶ ወደ እግዚአብሔር ዐረገች" አሉት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባቶቻችንም በረከት ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ቴዎናስ፦ እርሱም ለእስክንድር ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ስድስተኛ ነው። ይህም ቅዱስ አዋቂ ብልህ በቀናች ሃይማኖት የጸና በሥራው ሁሉ ያማረ ስለ ዕውቀቱም ሰዎች ሁሉ የሚወዱትና የሚሹት ነው። በዚያም ወራት ከሀድያንን በመፍራት በሥውር ከዋሻ ውስጥ በቀር በግልጥ ሊጸልዩና ሊቀድሱ ለክርስቲያኖች አልተቻላቸውም ነበር ይህም አባት አብያተ ክርስቲያናትን እስከሠሩ ድረስ አግባባቸው በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠሩ ከከሀድያንም ብዙዎችን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ በተሾመባት በመጀመሪያ ዓመት ተፍጻሜተ ሰማዕት የሆነ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስን ያጠመቀው እርሱ ነው። በተሾመ በአምስተኛ ዓመቱም አናጒንስጢስነት ሾመው በዐሥራ ሁለተኛም የሹመቱ ዓመት ቅስና ሾመው። ❤ በዚህም አባት ዘመን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ገጽ የሚል ከሀዲ ሰባልዮስ በእስክንድርያ አገር ተነሣ ይህም አባት አውግዞ ለየው የከፋች ሃይማኖትንም አጠፋት። ዳግመኛም በዘመኑ ቆዝሞስና ድምያኖስ ወንድሞቻቸው እናታቸው ቴዎዳዳም በሰማዕትነት ሞቱ ይህም አባት ያመረ ጒዞውን በመጓዝ እግዚአብሔርን አገልግሎ በዚች ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቴዎናስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ኤጲስ_ቆጶስ_አባ_አላኒቆስ፦ ጣዖታቱን እንዲአቃልሉ ለሰዎች እንደሚያስተምራቸው ከሀዲው ንጉሥ በሰማ ጊዜ ይዘው ጽኑ ሥቃይን ያሠቀሠዩት ዘንድ መልክተኞችን ላከ። የንጉሥ መልክተኞች መላካቸውን የተመሰገነ አላኒቆስ ሰምቶ በአገረ ስብከቱ ያሉትን ሕዝቦች ሰበሰባቸውና የቊርባን ቅዳሴን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ "በቀናች ሃይማኖት ጽኑ ከእንግዲህ ፊቱን አታዩኝም" አላቸው። እነርሱም አለቀሱ ሊስተውትም አልተቻላቸውም ወጥቶም ራሱን ለንጉሥ መልክተኞች አሳልፎ ሰጠ እነርሱም ወስደው ለእዴናው አገር መኰንን ሰጡት። እነርሱም ወደ አገረ እንድኩ

❤ በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት። ያን ጊዜም የክብር ቅዱስ ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ድል አድራጊ ቅዱስ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥታትን ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው። ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋራ ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው። በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ፣ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ። ❤ ከዚህም በኋላ ወታደሮቹ የቅዱሳን የከበረች ራሱን ቈረጡት ደም፣ ውኃና ወተት ፈሰሰው፤ ጌታም ቅዱስ ሚካኤልን በብርሃን ልብስ ደሙን እንዲቀበለው አዘዘ። ጌታችንም የኃያሉ የቅዱስ ጊዮርጊስን ነፍስ በእጁ ተቀብሎ ሳማት፤ በሰማያዊ ልብስም አጐናጥፎ ከእርሱ ጋራ ወደ ሰማይ አሳረጋት። አየር በሙሉ ቅዱሳን መላእክትን ተሞላ። ለቸር አባቱና ለመንፈስ ቅዱስ ቊርባን አድርጎ እስኪያቀርበው ድረስ ቅዱሳን ሁሉ በየወገናቸው ያመሰግኑ ነበር። የብርሃን ልብስ አለበሰው። በዕንቈ ባሕርይ ያጌጠ ከጽሩ ወርቅ የተሠሩ መከራ በተቀበለባቸው ሰባት ዓመታት ልክ ከዕፀ ሕይወት አበቦች የተሠሩ አክሊሎች ያሉበትን ዘውድ አቀዳጀው ለዘላለም ከማኅበረ በኵር ጋራ ስሙን ጻፈው። ሰማያውያን መላእክትና ቅዱሳንንም ሁሉ በየወገናቸው በመንበሩ ላይ እንዲአስቀምጡት፤ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በዓል እንዲ ያደርጉለት አዘዛቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ከመብረቁ፣ ከነጐድጓድ፣ ከንውጽውጽታው ጽናት፣ ከዝናሙ ብዛት የተነሳ በምድር ላይ ትልቅ ድንጋፄ ሆነ። ምድርም ሦስት ጊዜ ተናወጸች ከዚያ ቆመው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ሸሹ ወደ ከተማም ሔዱ ጭፍሮችም ይህንን በአዩ ጊዜ በቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ አመኑ። ነፍሱም ወደ ሰማይ በዐረገች ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ሰገደች። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምታምን ነፍስ ከሥጋዋ በተለየች ጊዜ አስቀድሞ ለሥሉስ ቅዱስ ትስገድ ከዚህ በኋላ ወደ ወዳጄ ወደ ጊዮርጊስ ይወሰዷት እና ለርሱ እጅ ትንሣ ብሎ አዘዘ፤ በዚህ ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስክርነቱ ሚያዝያ በባተ በሃያ ሦስት ቀን በዕተ ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት ተፈጸመ። አገልጋዮቹም ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሀገሩ ልዳም ወስደው ቤተክርስቲያን ሰርተው በውስጡ አኖሩት፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊስም በረከትቱ ረድኤቱ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ከሥጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ገድለ ጊዮርጊስ እና የሚያዚያ23 ስንክሳር።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ገብረ_ክርስቶስ_ዘዳግና፦ የጻድቁ ንጉሥ የዐፄ ይኩኖ አምላክና የልዕልተ ወይን ልጅ ሲሆኑ ንግሥናን ትተው በመልአክ መሪነት አክሱም ሄደው ነው የመነኑት፡፡ በዚያም አስደናቂውን ባለ12 ቤተመቅደስ ገዳም ገድመዋል፡፡ ቀደምት የተባሉትን ብዙ መነኰሳትንም አመንኩሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ጻድቁ በአንድ ወቅት ርሃብ ሆኖ ከብቶች አልቀው የሚታረስ ቢጠፋ እጃቸውን አጨብጭበው አንበሳና አጋዘንን ጠርተው በአንድ አድርገው ጠምደዋቸው አርሰውና ዘርተው ዕለቱን አድርሰው ሕዝቡን የመገቡ የበረከት አባት ናቸው፡፡ ❤ ጻድቁ በተከዜ ወንዝ ላይ ሕዝቡን በተአምራት በገመድ ያሻገሩ አባት ናቸው፡፡ እንግዶች መነኰሳት ሊጠይቋቸው ሲመጡ ለእንግዶቹ ብለው ቆቅ ይዘው አርደው በድስት አድርገው ሰርተው አቀረቡላቸው፡፡ እንግዶቹ ግን"እኛ መነኵሴዎች ነን እንዴት ሥጋ ያበላናል?" እያሉ ሲያሙ ጻድቁ የውስጣቸውን ዐውቀውባቸው ታርደው ወጥ የተሠሩትን ቆቆቹ እፍ ቢሉባቸው ቆቆቹ ነፍስ ዘርተው ከድስቱ ላይ በረው ሄደዋል፡፡ ይህን ተአምር ያዩ እንግዶቹም እጅግ ደንግጠው ይቅር በሉን ብለው ንስሓ ገብተዋል፡፡ ጻድቁ ከጌታችን ታላቅ ብዙ ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኋላ በዚች ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ምንጭ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ጥር ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጽያዊ_ጻድቅ በዓለም ላይ በንግሥና መኖርን ንቀው ለመነኑትና ብዙ ተአምራትን በማድረግ ለሚታወቁት #ለንጉሥ_ዐፄ_ይኩኖ_አምላክ ልጅ ለሆኑት #ለአቡነ_ገብረ_ክርስቶስ_ዘዳግና ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሊቀ ሰማዕታት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_ለልደት በዓል በሰላም አደረሰን።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #ፀሐይና_የአጥቢያ_ኮከብ የተባለ ታላቁና ክቡር የሆነ ሰማዕቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ፦  የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍስጥዓዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ ዐረፈ። ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ። ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው። ❤ ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም። ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቊስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደ ሚሞት እርሱም እንደሚአስነሣው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊል እንደሚቀበል ነገረው። ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው። ❤ ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር። ቅዱሱም ያንን ጽዋ በመስቀል መልክት አማትቦ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም። ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱ ጋራ ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቊጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው። ❤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ። ቅዱሱንም "እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን" አሉት። በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቊጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት። አቃጥለው አሳርረው ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ይድራስ ከተባለ ተራራላይ በተኑት። ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው። ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ። ቊጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታስነሳ አምላክህ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን በእርሱም እናምናለን" አሉት። ቅዱሱም ጸለየ ከመቃብር ጒድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጐልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሀነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው ዐረፉ። ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ። ❤ ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበለት። የዚያች መበለትም ቤቷ ምሰሶ ቅርጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ። ያቺም መበለት በተመሰለች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ "የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደእኔ መጣ" አለች። ቅዱሱም "እኔ አምላክ አይደለሁም የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ" አላት። እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው "የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለሁ። ዕውር፣ ደንቆሮ፣ ዲዳ፣ ጐባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምህሃለሁ"። ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያንጊዜም አየ። ቅዱስም "በሌላ ጊዜ እንዲሰማ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ" አላት። በዚያን ጊዜ ንጉሡ በአገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት። ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኰራኵር አበራዩት ሙቶም በከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለሰ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ። ❤ ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት "ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ" አለው። ንጉሡም ዕውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው። ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለእስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው  እንደሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀምረ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች። ❤ በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ ዕውነት መስሏት እጅግ እያዘነች ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች። ቅዱስ ጊዮርጊስ በአያት ጊዜ ፈገግ አለ "ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው" አላት ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ "ወደ አጵሎን ሒድ ወደእኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እዘዘው" አለው። ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሒዶ አዘዘው። በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለበት መጥቶ "እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም" ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ። ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ከወገኖቹ ጋራ ዐፈረ። ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ። እርሷም "አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖች አትጣላቸው አላልኩህምን" አለችው። ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት  ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ። ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጐትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።

ጥር ፩  /1/
በዚችም ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አባ መቃርስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነጳጳሳት ስልሳ ዘጠነኛ ነው። ከእርሱ በፊት የነበረ አባ ሚካኤልም በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና ሊቃውንቱ የግብጽም ታላላቆች ሁሉም ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥተው ለዚች ለከበረች ሹመት ስለሚገባ ከዋሻ ውስጥ ከሚኖሩ ደጋጎች ገዳማውያን ሲጠያየቁና ሲመረምሩ ኖሩ። ከዚህም በኋላ አንድ ጻድቅ ሰው ስለዚህ አባት ነገራቸው እንዲህም አላቸው በአባ መቃርስ ገዳም የሚኖር ቀሲስ አባ መቃርስ እርሱ ለዚች ሹመት ይገባል። በዚያንም ጊዜ ፈልገው ያዙት እርሱም እኔ ለዚች ሥራ የማልጠቅም በደለኛ ነኝ እያለ ሲጮህ ያለ ፈቃዱ አሥረው ወሰዱት ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እንጂ እርሱ የሚላቸውን ቃሉን አልሰሙትም። ከዚህም በኋላ የሊቀ ጵጵስናውን ሥራ መሥራት ጀመረ በግብጽ አገር በሁሉ ቦታ ኤጲስቆጶሳትን ካህናትን ሾመ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትንም አደሰ ጊዜውም ያለ ኀዘን የጤንነትና የሰላም ጊዜ ነበር። ሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ከአርባ አንድ ቀን ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

❤ አርያኖስም አክሚም ከተማ በደረሰ ጊዜ ኤጲስቆጶስን አባ ብኑድያኖስን ያዘውና አሥሮ ወደ አገር ውስጥ ገባ። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም ለዲዮሰሰቆሮስና ለሰከላብዮስ ተገለጸላቸው ወደ መኰንኑም ሒደው የምስክርነት አክሊልን እንዲቀበሉ ነገራቸው እነርሱም ታኅሣሥ ሃያ ስምንት ቀን  ሃያ አራት መነኰሳት ሁነው ሔዱ። ወደ አክሚም ከተማም ሲደርሱ በመድኃኒታችን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የከበረ የልደትን በዓል ለማክበርና ስለ ከበረ ስሙም ይሞቱ ዘንድ የክርስቲያን ወገኖችን ከሴቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ተሰብስበው አገኙአቸው ኤጲስቆጶሱ አባ ብኑድያኖስም ከእርሳቸው ጋር ገባ። በማግሥቱም አባ ብኑድያኖስ ቀደሰ አግዮስ ወደሚባለው በደረሰ ጊዜ መላእክት እንዲህ ብለው በታላቅ ድምጽ አመሰገኑ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር አሸናፊ ፍጹም የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው"። ያን ጊዜ መድኃኒታችንን በመሠዊያው ታቦት ላይ ተቀምጦ መላእክትም በዙሪያው ቁመው ቊርባኑን እያነሣ በካህኑ እጅ ላይ በማድረግ የተሰበሰቡትን ሲያቆርባቸው ቅዱሳኑ አዩት። ❤ በዚያንም ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ደረሰ ተቆጥቶም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ስማቸው ብሕዋፋና ውኒን የሚባሉ ሁለት የአገር አለቆችን ይዞ ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጠ ከእነርሱም በኋላ ዲያቆናትን ንፍቀ ዲያቆናትን መዘምራንን የቤተ ክርስቲያን ሹሞች ደማቸው ከቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወጥቶ ሃያ ክንድ ያህል እስቲጎርፍ ሴቶችና ልጆችንም ሳያስቀር አረዳቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሱን አባ ብኑድያስን ዲዮስቆሮስን ሰከላብዮስን ከእርሳቸውም ጋር ያሉ መነኰሳትን ከእርሱ ጋር ወሰዳቸው ለጣዖትም ይሰግዱ ዘንድ ሸነገላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ዐጥንቶቻቸው እስከሚለያዩ ድረስ ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾላቸው አዳናቸው የአርያኖስም የጭፍሮቹ ታላላቆች ኮርዮንና ፊልሞና ከጭፍሮችም አርባ ሰዎች ይህን ድንቅ ተአምር አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ወደ እሳት ማንደጃም እንዲጥሏቸው አዘዘ። ተጋድሏቸውንም ታኅሣሥ ሠላሳ ቀን ፈጸሙ ከተሰበሰቡትም ውስጥ ብዙዎች የሚያስገድዳቸው ሳይኖር በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ እናምናለን እያሉ ወደ እሳቱ ማንደጃ ራሳቸውን ወረወሩ ምስክርነታቸውንም እንደዚህ ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ ጥር አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ታሥረው ሳሉ የመላእክት አለቃ ቅዱሰሰ ሚካኤል ተገለጠላቸውና ምስክርነታቸውን እንደመፈጽሙ አበረታቸው በነጋም ጊዜ ለአማልክት ስለ መስገድ አርያኖስ ተናገራቸው አይሆንም በአሉትም ጊዜ የዲዮስቆሮስን ዐይኖቹን ያወልቁ ዘንድ አዘዘ ቅዱሱም የወለቁ ዐይኖቹን አንሥቶ ወደ ቦታቸው መለሳቸው መኰንኑ ሉክዮስ አይቶ ከሠራዊቱ ጋር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ወደ እሳትም ወርውረዋቸው ምስክርነታቸውንም ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበሩ ሰማዕታትን ይገደሏቸው ዘንድ አርያኖስ አዘዘ ሲጸልዩም የክብር ባሌበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸው ስማቸውን ለሚጠረሠ መታሰቢያቸውንም ለሚያደርግ ገድላቸውንም ለሚጽፍ ከቅዱሳን አንድነት ይቈጥረው ዘንድ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ከዚህም በኋላ ወታደሩ ቀርቦ የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ራሱ ቆረጠ ሰከላብዮስንም ከወገቡ ላይ ቆረጡት ሃያ አራቱን መንኰሳትም ከቁመታቸው ሠነጠቋቸው በዚች በጥር አንድ ቀን ተቆረጡ ከዘመዶቻቸው የሆነ ሳሙኤልም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበራቸው በአገረ አክሚም የተገደሉ ሰማዕታትም ቊጥራቸው ስምንት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሁሉ ቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር1 ስንክሳር።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በ­ቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ78፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ማር13፥9-23።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ በጻሕኮ በበረከት ሠናይ። ወአንበረከ አክሊለ ዲበ ርእሱ ዘእምዕንቊ ክቡር። ሐይወ ሰአለከ ወወሀብኮ"። መዝ 20፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥51-58። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥33-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ ሰሞን፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ የልደትና የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የተባረከ_የጥር_ወር_የመዓልቱ_ሰዓት_ዐሥር ነው ከእንግዲህ ይጨመርለታል።               ❤ #ጥር ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ፣ #ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ፣ #ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                     ✝ ✝ ✝ ❤ #ቀዳሜ_ሰማዕታት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ፦ ለዚህም ለከበረ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር ኃይልን ጸጋ የተመላ ሰው እንደነበረና በሕዝቡም መካከል ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ሥራን ይሠራ እንደነበረ የሐዋርያት ሥራ የተባለ መጽሐፍ ስለርሱ ምስክር ሆነ። ከዚህም በኋላ አይሁድ ቀኑበት የሐሰት ምስክሮች የሚሆኑ ሰዎችንም አስነሡበት "ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር  ላይ የስድብ ቃልን ሲናገር ሰምተነዋል እንዲሉ ሐሰትን አስተማሩአቸው። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን ጸሐፊዎችንም አነሣሡአቸው አዳርሱን ብለው ከበው እየጐተቱ ወደ ሸንጎ ወሰዱት። ❤ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት እነርሱ ይህ ሰው በቤተ መቅደስ ላይ በኦሪትም ላይ ስድብን ሲናገር ተው ብንለው እምቢ አለ። "የናዝሬቱ ኢየሱስ ቤተ መቅደሳችሁን ያፈርሰዋል ሙሴ የሰጣችሁን ኦሪታችሁንም ይሽራል" ሲል ሰምተነዋል አሉ። በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሁሉ ተመለከቱት ፊቱም የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ሁኖ አዩት። ሊቀ ካህናቱም "እውነት ነውና እንዲህ አልክ" አለው። እርሱም እንዲህ አለ "ወንድሞቻችንና አባቶቻችን ስሙ ወደ ካራን ከመምጣቱ አስቀድሞ በሶርያ ወንዞች መካከል ሳለ ለአባታችን ለአብርሃም የክብር ባለቤት እግዚአብሔር ተገለጠለት። ካአገርህ ውጣ ከዘመዶችህም ተለይ እኔ ወደማሳይህ አገርም ና" አለው። ❤ "ከዚህም በኋላ ከከላውዴዎን ወጥቶ በካራን ተቀመጠ አባቱም ከሞተ በኋላ ዛሬ እናንተ ወደ አላችሁባት ወደዚች አገር አመጣው። ከዚህም በኋላ የግዝረትን ሥርዓት ሰጠው ይስሐቅም በወለደው ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገዘረው እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን ገዘረው ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን ነገድ አባቶች ገዘረ። የቀድሙ አባቶቻችንም በዮሴፍ ላይ ቀንተው ወደ ግብጽ አገር ሸጡት እግዚአብሔር ግን አክብሮት ነበር። ከመከራው ሁሉ አዳነው በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ዕውቀትን መወደድን ሰጠው በግብጽ አገር ሁሉና በቤቱ ሁሉ ላይ ሾመው"። ነገርም በማስረዘም በሰሎሞን እጅ እስከተሠራችው ቤተ መቅደስ ያለውን ተረከላቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ "እናንተም እንደአባቶቻችሁ ዘወትር መንፈስ ቅዱስን የምታሳዝኑት ዐይነ ልቡናችሁ የታወረ ዕዝነ ልቡናችሁ የደነቈረ አንገተ ደንዳኖች" አላቸው። "አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ያልገደሉት ማን አለ እናንተ ክዳችሁ የገደላችሁትን ገደላችኋቸው። በመላእክት ሥርዓት ኦሪት ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም"። ❤ ይህንንም ሰምተው ተበሳጩ ልባቸውም ተናደደ ተነሠሣ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። በቅዱስ እስጢፋኖስም መንፈስ ቅዱስ አደረበት ሰማይም ተከፍቶ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ የእግዚአብሔርን ክብር አየ። "እነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ አያለሁ" አለ። ❤ ዶሮአቸውን ይዘው በታላቅ ድምፅ ጮኹ በአንድነትም ከበው ጐተቱት። እየጐተቱም ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው በደንጊያ ወግረው ገደሉት የገድሉትም ሰዎች ልብሳቸውን ሳውል ለሚባል ጐልማሳ ልጅ ያስጠብቁ ነበር። "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" እያለ ሲጸልይ እስጢፋኖስን በደንጊያ ወገሩት። ❤ ዘለፍለፍ ባለ ጊዜም ድምፁን ከፍ አድርጎ "አቤቱ ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው በደልም አታድርግባቸው" ይህንንም ብሎ ዐረፈ። ደጋግ ሰዎችም መጥተው የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ ወስደው ቀበሩት ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ሐዋርያና ሰማዕት በሆነ በቅዱስ እስጢፋኖስ  አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ለውንድዮስ፦ የዚህም ቅዱስ ዜና እግዚአብሔርን የሚያመልክ ተጋዳይ እንደሆነ ንጉሥ መክስምያኖስ በሰማ ጊዜ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሃይማኖቱንም ትቶ አማልክቶቹን ያመልክለት ዘንድ ብዙ ገንዘብ አቀረበለትና ይሸነግለው ጀመረ የከበረ ቅዱስ ለውንድዮስ ግን ዘበተበት ስጦታውንም  በማቃለል ክብሩን አጐሳቈለ የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመ። ❤ ያን ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በመንኰራኵር ውስጥ ሰቅለው ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን እንዲ አሠቃዩት አዘዘ። ንጉሥ እንዳዘዘ አደረጉበት የክብር ባለቤት ጌታችን ግን ያለ ጥፋት በጤና አወጣው። ዳግመኛም በብረት ዘንጎች ይደበድቡት ዘንድ ቅባትና ስብንም በታላቅ ድስት አፍልተው ቅዱስ ለውንድዮስን ከውስጡ ይጨምሩት ዘንድ አዘዘ ይህን ሁሉ ሥቃይንም አሠቃዩት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያጸናውና ያስታግሠው ያለ ጉዳትም በጤና ያስነሣው ነበር። ❤ ማሠቃየቱንም በደከመው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ከሥጋውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራቶች ተገለጹ ዜናውም በሶርያ አገር ሁሉ ተሰማ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተሠሩለት ከገዳማቱም በአንዲቱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው የከበረ ሳዊሮስ በሕፃንነቱ ተጠመቀባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንድዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበሩ_የአክሚም_ሰማዕታት_ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ፦ እክሚም በሚባል አገር ሹም የሆነ አንድ ሰው ነበር በወርቅ በብር ባለጸጋ ነው ስሙም አልሰመማልዮስ ይባላል ስማቸው ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ የሚባል ሁለት ልጆቹን ወለደ እነርሱም ከመጾምና ከመጸለይ ጋር እግዚአብሔርን በመፈራት አደጉ። አባታቸው በሞተ ጊዜ ምንኵስናን ተመኙ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦላቸው ወደ ገዳማዊ አባ ሙሴ ገዳም እንደመሔዱ አዘዛቸው ሒደውም በዚያ መነኰሱ ድንቆች ተአምራቶችንም እያደረጉ በብዙ ተጋድሎ ኖሩ። ከጥቂት ወራትም በኋላም ዲዮስቆሮስ ቅስና ሰከላብዮስም ዲቁና ተሾሙ። ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት ክርስቶስን በካደው ጊዜ ለጣዖታት የማይሰግዱ ክርስቲያኖችን ሁሉ ይገድል ዘንድ የእንዴናው ገዥ አርያኖስን አዘዘው።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በግ/ደ/አ/ቅ/አ/ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀው የገና ዕጣ የወጣው ቁጥር 1ኛ ዕጣ 1244 2ኛ ዕጣ 0113 3ኛ ዕጣ 1189 ይህ ቁጥር የደረሳችሁ በ0907176727 / 0945455578 በመደወል መውሰድ ትችላላችሁ።

❤ በሆሣዕና ዕለት ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያበራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አብሮዋቸው ሔደ። ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጐበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎች በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል "አባት ሆይ ሲመግበን የነበረው ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ"  ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበ ምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው። አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ። ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 30 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15 ወይም መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 3፥15-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥12-21 እና የሐዋ ሥራ 19፥8-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ታኅሣሥ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጥፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ኄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ተጋዳይ የምንኵስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በአገሩ ሁሉ ተሰማ። ይህም አባ ዮሐንስ ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገድደው ነበር እርሱም "የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም" አላት።  ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም "በእግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምለሠታለሁ" አለው። ❤ በዚያችም ሌሊት የከበረ ዮሐንስ ለዚያች ሴት በሕልም ተገልጾ እንዲህ አላት "ጻድቅ ያልሆንኩ ወይም ነቢይ የኔን ፊት ታዪ ዘንድ የምትሺ አንቺ ሴት ከእኔ ምን አለሽ እኔስ ካንቺ ምን አለኝ እንግዲህስ ፊቴን ማየት አትሺ" ይህንንም ብሎ በላይዋ ጸልዮ ባረካት። በማግሥቱም የከበረ አባ ዮሐንስ በመንፈስ እንደታያት ለባሏ ነገረችው። መልኩንና አምሳያውን አመለከተችው ከዚያም በኋላ ከብዙ ሙገሳና ምስጋና ጋር ባሏን ወደ አባ ዮሐንስ ላከችው። ❤ የከበረ ዮሐንስም ባሏን በአየው ጊዜ ፈገግ ብሎ "የሚስትህ ምኞቷ የተፈጸመላት አይደለምን በዚች ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ አግኝታኛለችና" አለው መኰንኑም ሰምቶ ከትሩፋቱና ከደግነቱ የተነሣ እጅግ አደነቀ። ይህም አባ ዮሐንስ ጭንቅ በሆነ ተጋድሎ ዘጠና ዓመት ያህል ኖረ ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ የአስቄጥ ገዳም አበ ምኔት አባ ዮሐንስ፦ ይህም አባት በተሾም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸው ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የአገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የአገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኞውና ጻድቁ ይገለጥለታና ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው። ❤ በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጠሠ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የእግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ሥጋውና ደሙን አቀበላቸው። ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እነዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት። አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው "በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የክርስቲያን ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና"። ❤ ዳግመኛም በምሳሌ እንዲህ አላቸው "በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳዱ እንደሠራው ይከፍለዋል እንጂ"። ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማርከው ወደ አገራቸው ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው። ❤ ከመሞቱ በፊት የሚሞትበት ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ኮርዮንና_ፊልሞና_አርባ_ወታደሮች፦ የሰማዕትነታቸውም ምክንያት የአክሚም ታላላቆች ከሆኑ ከሰማዕታት ዲዮስቆሮስ፣ ከሰከላብዮስና ከብኑድያስ የተደረገውን ተአምራት በአዩ ጊዜ የወታደርነት የማዕርግ ሽልማታቸውን ጣሉ በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁመው "እኛ በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ የምናምን በግልጥ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ ራሳቸውንም ሲወረውሩ ብዙዎች አዩአቸው ገድላቸውንም እንዲህ ፈጸሙ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ተጋዳይ_አባት_ቅዱስ_ዘካርያስ፦ ይንም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን በርበር ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በእግዚአብሔርም ፍቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያች ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ። ቅዱስ ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የአገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኲሚስ ገዳም ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና "መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና" አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው። የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ።

💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥💥✨💥✨💥 ሉቃስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።   አቅራቢ :- ሳሙኤል ገዛኸኝ 📣 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት  በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡መልካም በዓል🙏      ✍️ኪነ - ጥበብ ክፍል

❤ ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ "እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ በተዋሕዶም ወለድኩህ አለኝ። ለምን አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው"። ዳግመኛ "አብ አለ ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ከአንተ ጋር ሳለሁ ከአጥብያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ እንደ መልከጼዴቅ አንተ የዓለም አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ ከማለም አይፀፀትም"። ❤ ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደገኘ በእስራኤል በበርሃ ውስጥ ከኅቱም ዐለት ውኃ እንደ ፈለቀ የደረቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደአፈራች። በሶምሶንም እጅ ወስጥ ከአህያ መንጋጋ ዐጥንት ውኃ እንደፈሰሰ። እንዲሁ የጌታችን ልደት በህቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደነደደች እጺቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁም የመለኮት እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክል ይገባል ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ29 ስንክሳር።                                       ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ነገሥተ ተርሴስ ወደሰያት አምኃ ያበውዑ። ነገሥተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመጽኡ። ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ ነገሥተ ምድር"። መዝ71፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ1፥1-18።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥4-12፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልእ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሥጋ_ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች #ለብርሃነ_ልደቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በእዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤፍሬም ወገን ከመስፋኑ #ከቅዱስ_ኢያሱ_ልደት፣ #ከከበሩ_ከያዕቆብ_ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ #ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሮሀ_ንጉሥ_ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው #ከቅዱስ_ቆሪል ዕረፍትና #ከአክሚም_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                                                   ✝️ ✝️ ✝️ ❤ በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ #ታላቅ_የልደት_በዓል_ሆነ_የጌታችንና_የመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከከበረች_ድንግል_ማርያም_የተወለደባት ዕለት ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት። ❤ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን የከበረ የልደትን በዓል በሁለት ቀኖች ያከብሩ ዘንድ በምክራቸው ተስማሙ ከወደኋላ ባለ በሃያ ስምንት ሌሊቱ የልደት በዓል ነው በሃያ ዘጠኝ መዓልቱ ጳጒሜን ስድስት በሆነ ጊዜ በዚያች ዓመት የልደት በዓል በሃያ ስምንት ከሆነ ግን በሃያ ዘጠኝ ይሆናል ስለዚህ የበዓላት ሁሉ ራስ የሆነ የከበረ የልደት በዓል በሁለት ቀኖች እንዲከበር አዘዙ ወሠኑ። ❤ የበዓላት ራስ ስለሆነ ስለ ከበረ የልደት በዓል የከበረ ወንጌል እንዲህ አለ "በንጉሥ በኄሮድስ ዘመን በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ጌታ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ኮከብን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ። እሊህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው በመጽሐፋቸው በበለዓም መጽሐፍም የአይሁድ ንጉሥ ሊወለድ እንዳለው ተጽፎአል እርሱ በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤልም ንጉሥ ብሎ ነበርና። ❤ ይቅር ባይ እግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ አለበማቸው በሚያምኑበትም ሳባቸው እነርሱ ከዋክብትን በመጠባበቅ የሚፈላሰፉ ናቸውና ይህንንም ኮከብ ገለጠላቸው በአዩትም ጊዜ ደስ አላቸው መልኩ በብዙ አይነት ልውጥ ነውና። ሕፃን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን ይመስላል እርሱም በቀን ይጓዛል በሌሊትም ይሠወራል ከሰውም ሲገናኙ ይሠወርና ሲቆሙ በሌላ አንጻር ይገለጥላቸዋል። ❤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ያ ኮከብ ተሠወራቸው እጅግ አዘኑ የሚያድረጉትንም አላወቁም ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው ስለተወለደው ንጉሥ ጠየቁ። የእሊህም ሰዎች ቊጥራቸው ሠላሳ ሽህ ነው ነገሥታቱ ሦስት ናቸው ለእያንዳንዳንዱ ንጉሥ ዐሥር ዐሥር ሺህ ሠራዊት አለው። ንጉሡ ኄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። የካህናት አለቆችና የሕዝቡን ጸሐፊዎች ሁሉ ሰብስቦ "ክርስቶስ በየት ይወለዳል?" ብሎ ጠየቃቸው። "በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ነው" አሉት በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና። "የኤፍራታ ዕፃ ቤተ ልሔም አንቺም ከይሁዳ ነገሥታት አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ካንቺ ይወለዳልና"። ❤ ከዚህም በኋላ  ኄሮድስ ሰብአ ሰገልን በጭልታ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከነሱ ተረዳ። "ሔዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር እርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግደለት ዘንድ በኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ" ብሎ ወደ ቤተልሔም ሰደዳቸው የነገራቸውንም ሰምተው ከንጉሡ ሔዱ እነሆ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ወደ ቤተልሔም እስኪያደርሳቸው ይመራቸው ነበር ሕፃኑ ካለበትም ዋሻ ላይ ደርሶ ቆመ። ኮከቡንም ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር አገኙት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ ከርቤ ዕጣን እጅ መንሻ አቀረቡለት። ❤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስ በዚያች ዕለት ወደ ቤተልሔም መጡ ስለዚህም ሰብአ ሰገል አገኙአቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ናዝሬት በሌላ ቦታ አላደገምና ከተወለደም ዕድሜው ሁለት ዓመት ሁኖት ነበር። አምላክ ነውና ስለ መንግሥቱ ወርቅን ገበሩለት ክህነትም ገንዘቡ ነውና ዕጣንን ገበሩለት ማሕያዊ ለሆ ሞቱ ምልክትም ከርቤን ገበሩለት። ወደ ኄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራቸው በሌላ መንገድም ወደ አገራቸው ተመልሰው ገቡ። አምላክ በሥጋ ስለመገለጡ ዓዋጅ ነጋሪዎችና ሰባኪዎች ሆኑ። ❤ ይችም ዕለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ስለርሷ የተናገረላት ናት እንዲህ ብሎ "እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው"። ስለዚችም የከበረች ድንግል ነቢይ ሕዝቅኤል እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "እግዚአብሔርም አለኝ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች አትከፈትም የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር" አለ። ❤ ነቢዩ ዳንኤልም አለ "ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ ዘመኑን ወደ ሚያስረጅ ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው። ❤ ዳግመኛም ኢሳይያስ "እግዚአብሔር እንደእኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጸልኝ" አለ። "አሁኑም ደግሞ አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ" አለ ሁለተኛም "ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል" አለ። ዳግመኛም "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው። ስሙም ድንቅ መካር የዘላዓለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል" አለ። ❤ ኤርምያስም አለ "እግዚአብሔር እንዲህ አለ ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ በምድር የቀና ፍርድ ያደርጋል እግዚአብሔር ያመኑበትን ያድናቸዋል"። ኤልሳዕም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር ከሰማ ይወርዳል በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ እውነትን ያስተምራቸዋል ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆነች ወገኖቹ በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል"። ናሆም ነቢይም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል ልብሱም እንደ ልብሴ ነው"። ❤ ነቢዩ ኢዩኤልም እንዲህ ተናገረ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር ስለርሷም ይቺ ማናት ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይች ድንግል ናት በርሷም የተጎሳቈሉ ይድናሉ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት።

ታኅሳስ 27/2017 ዓ,ም በደብራችን ለሰ/ት/ቤት አባላት ለወጣት መንፈሳዊ ማህበር አባላት ከጥምቀት በዓል አገልግሎት በፊት የአገልግሎት ትምህርት 💦 ወጣትነት ለቤተክርስቲያን 💦 በሚል ርዕስ መነ
+9
ታኅሳስ 27/2017 ዓ,ም በደብራችን ለሰ/ት/ቤት አባላት ለወጣት መንፈሳዊ ማህበር አባላት ከጥምቀት በዓል አገልግሎት በፊት የአገልግሎት ትምህርት 💦 ወጣትነት ለቤተክርስቲያን 💦 በሚል ርዕስ መነሻነት በዶ/ር ቆሞስ አባ ጌድዎን ብርሃነ አማካኝነት ለግማሽ ቀን ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ይህ መርሐ ግብር የተዘጋጀው በደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል ከደብሩ ሰ/ት/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ነው ።

ታሕሳስ ፳፰ /28/
በዚችም ዕለት መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ። እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ ። ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት ። በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና። ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ ። የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው። ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር