en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
610
Subscribers
-124 hours
-37 days
-1130 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን በጦርነት ድል አድራጊው ከቤተ መንግሥት ወገን ለሆነ #በንጽሕናው_የመላእክት_አርያ_ላለው #ለከበረ_ሰማዕት_ለቅዱስ_ገላውዴዎስ ለተጋድሎው ፍጻሜ #ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም በእስክንድርያ ከተማ ከሠራችበት #ከአርባ_ሰማዕታት #ከቅዳሴ_ቤተ_ክርስቲያንና #ከእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት #ከቅዱስ_ክርዳኑ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ገላውዴዎስ፦ ይህ ቅዱስ ምድራዊ መንግሥትንና የዚህን ዓለም ክብር የናቀ ነበረ መልካም ገድልንም ተጋደለ። የማይጠፋ ሰማያዊ መንግሥትንና የማያልቅ ክብርንም ወረሰ። ❤ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብጥልዎስ ነው እርሱም ለሮሜ ንጉሥ ለኑማርያኖስ ወንድሙ ነው መልኩም እንደ እስራኤል ያዕቆብ ልጅ እንደ ዮሴፍ ውብ ነበር። እርሱም በጦርነት ላይ የበረታ ነበር። የአንጾኪያ ተወላጆችም ይመኩበት ነበር። ስለ ደም ግባቱና ጽናቱ በሁሉ ዘንድ የተወደደ ነበር። እርሱንም ከመውደዳቸው ብዛት የተነሣ ጠላቶችን ድል እንዳረጋቸው እነርሱም ድል ሁነው በውርደት በብዙ ድንጋጤ ከፊቱ እንደሸሹ አድርገው ሥዕሉን ሥለው በከተማው መግብያ በር ላይ ያኖሩት ነበር። ❤ ቅዱስ ገላውዴዎስ የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር። የሮሜ ንጉሥም ዜናውን ሰምቶ ሊያየው ወደደ ልጁ ገላውዴዎስንም ይልክለት ዘንድ ወደ አባቱ ላከ እርሱም ላከለት። በደረሰም ጊዜ በደስታ ሊቀበለው ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋራ ወጣ በአየውም ጊዜ ደስ ተሰኘበት የሮሜ ከተማ ሰዎች ሁሉም ደስ አላቸው። ከእነዚያ ወራቶችም በኋላ ከቊዝ አገር ሰዎችና ከአርማንያ ታላቅ ጸብ ተነሣ ይህም ቅዱስ ገላውዴዎስ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታምኖ ወደ እነርሱ ወጣ ድልም አደረጋቸው ንጉሣቸውንም ያዘው ጣዖታቶቻቸውንም ሰበራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ዲዮስቆሮስም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክዶ አምልኮ ጣዖትን በአጸና ጊዜ እጅግ አዘነ ፊቅጦር የሚባል የኅርማኖስ ልጅ ወዳጅ ነበረው ሁልጊዜም የመጻሕፍትን ቃል ይሰሙ ነበር ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ያነቡ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ ተስማሙ። በዚያ ጊዜም ሰይጣን በሽማግሌ አምሳል ታያቸው ያዘነላቸውም መስሎ እንዲህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ መልካምች ጐልማሶች ናችሁ የነገሥታት ልጆችም ናችሁ። ስለ እናንተ እፈራለሁ አዝንላችኋለሁም እኔም ከንጉሡ ጋር ትስማሙ ዘንድ ለአማልክትም ታጥኑ ዘንድ እመክራችኋለሁ ሲአዝዛችሁም ትእዛዙን አትተላለፉ እናንተም ክርስቶስን በቤታችሁ አምልኩት ይህ ንጉሥ ኃይለኛ ርኅራኄም የሌለው ጫካኝ ነውና" አላቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገራቸው ሰይጣን እንደሆነ አስገነዘባቸው "ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሐሰት አባት ሆይ ከእኛ ራቅ አንተ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ሕግ ትቃረናለህና" አሉት። ያን ጊዜም መልኩን ለውጦ እንደ ጥቁር ባሪያ ሆነ እንዲህም አላቸው "እነሆ ከንጉሥ አጣልቼ ደማችሁን እንዲአፈስስ አደርገዋለሁ" ሰይጣኑም ይህንን ብሎ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ሔዶ "ፊቅጦርና ገላውዴዎስን ካልገደልካቸው በአንተ ላይ ይነሣሉ አንተንም ገድለው መንግሥትህን ይወስዳሉ እነርሱም የመንግሥት ልጆች ናቸውና" አለው። ❤ ስለዚህም ንጉሡ ወደ ቅዱስ ገላውዴዎስ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ለጣዖታቱም እንዲሠዋ ለመነው የአባቱንም ሹመት ይሾመው ዘንድ ቃል ገባለት ሰምቶም አልታዘዘለትም። ንጉሡም ክፉ ቃልን ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን በድፍረት ይናገረው ነበር ያለ መፍራትም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ሰደበ። ኅርማኖስም ቅዱስ ገላውዴዎስን ወደ ግብጽ እንዲልከውና በዚያ እንዲገድሉት ንጉሡን መከረው እርሱ እንደ ልጄ እንደ ፊቅጦር ዐመፀኛ ነውና። ❤ ንጉሡም ወደ እንዴናው ገዥ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ገላውዴዎስ ትእዛዛችንን አልተቀበለም ቃላችንንም አልሰማም አንተም ወደ ትዕዛዛችን ይመለስ እንደሆነ በብዙ ድካም ሸንግለው ይህ ካልሆነ ራሱን በሰይፍ ቁረጥ"። ቅዱስ ገላውዴዎስ ወደ እስክንድርያ ይወስዱት ዘንድ ንጉሡ እንደ አዘዘ በአወቀ ጊዜ የእኅቱ ባል የሆነ ሲድራማኮስን ጠርቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን በማመን እንዲጸና ወገኖቹንም እንዲያጸናቸው አደራ አለውና በሰላምታ ተሰናበተው። ❤ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም በደረሰ ጊዜ አርያኖስ አይቶ ደነገጠ ተነሥቶም እጁን ሳመው እንዲህም ብሎ ለመነው "ጌታዬ ገላውዴዎስ ሆይ ይህን ሥራ አትሥራ የንጉሥንም ትዕዛዝ አትተላለፍ። ቅዱስ ገላውዴዎስም እንዲህ ሲል መለሰለት "ንጉሥ ያዘዘህን ልትፈጽም እንጂ በነገርህ ልታስተኝ አልተላክሁም" አለው። መኰንኑም እስከሚቆጣ ድረስ እንዲህ እርስበርሳቸው ይነጋገሩ ነበር በመኰንኑም እጅ ጦር ነበር ቅዱስ ገላውዴዎስ ወጋው ነፍሱንም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ሰኔ 11 ቀን ሰጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ምዕመናንም መጥተው የቅዱስ ገላውዴዎስን ሥጋ ወሰዱ በመልካም አገናነዝም ገነዙት ከቅዱስ ፊቅጦር ሥጋ ጋርም በሣጥን ውስጥ አኖሩት። የስደቱም ዘመን እስኪሚፈጸም ጠበቁት። ❤ ከዚህም በኋላም የቅዱስ ፊቅጦር እናት ቅድስት ሶፍያ ወደ እንዴናው አገር መጣች የቅዱሳን ገላውዴዎስንና የፊቅጦርን ሥጋቸውንም ወስዳ ወደ አንጾኪያ አደረሰች። የቅዱስ ገላውዴዎስ ሥጋ አስዩጥ በሚባል አገር ይኖራል የሚልም አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መስተጋድል በቅዱስ ገላውዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሀሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 11 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መድኃኒነ። በእስክንድርያ ዘኮነ። ኀቤከ እግዚኦ አንቃዕዶና አዕይንተነ። ከመ ተሀበነ እምቅኔ ኃጢአት ግዕዛነ። ንጸንሐከ ንሕነ እምዘመን ዘመነ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_11።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት። እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት። እምግብር ዘየሐውር በጽልመት"። መዝ 90፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 5፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 5፥7-12 እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ አቡነ መዝሙረ ድንግልና የቅዱስ ገላውዴዎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። በሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ነገረ ማርያምን ወደ ግእዝ ቋንቋና አራቱ ወንጌልን ወደ ተለያየ ቋንቋ ለተረጎሙት #ለአቡነ_መዝሙረ_ድንግል ለዕረፍታቸው በዐልና #በግብጽ_ቤተ_ክርስቲያ_ጨምር_ቅድስና ለተሰጣቸው #ለአብረ_ገብረ_ኢየሱስ_ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል፦ የተባሉት ጻድቅ አገራቸው ጎጃም ነው፤ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው። ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል። ❤ ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር። በጣም ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው። ከአቡነ መዝሙረ ድንግል እግዚአብሔር አምላክዐ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ፦ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በአገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌል ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብጽ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብጽ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ። ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ። አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብጻውያን ይቀኑባቸው ነበር። ❤ ስልሳ ስድስተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ። በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ አቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው "ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባው ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ" በላቸው ብሎ ነገራቸው። አቡነ ገብረ ኢየሱስም "ከመካከላችሁ ስሙ ገአርጊ የሚባል ጻድቅ አለና እርሱን ሹሙት" ብለው መልአኩ የነገራቸውን መልእክት ነግረዋቸው አባ ገአርጊን ስልሳ ሰባተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል። ❤ አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል። የጻድቁ አባታችን ገዳላቸው በጣና ይገኛል። ሰኔ11 ቀን ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል። ከአቡነ ገብረ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።

ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም
ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም ኮርስ ያልተማራችሁ እና ከቀዳማይ ኮርስ 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁ ሁሉ ያለን ጊዜ አጭር ስለሆነ ሙሉ ኮርሱን በመከታተልና በመጨረስ ለአገልግሎት ብቁ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏 🔴 ማሳሰቢያ :- 👉 ኮርሱ የሚጀመረው በቀን 09/10/2017 ዓ. ም 👉 ኮርሱ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ 👉 ቀዳማይን ያልጨረሰ ሁሉ ሙሉውን የመማር ግዴታ አለበት ( 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁን ጨምሮ ) 👉 ያልተማራችሁ ትምህርቱ ላይ እንድትገኙ እና ላልሰሙ ወንድም እህቶቻችሁን እንድትጋብዙ ስንል በአምላከ ቅድስት አርሴማ ስም እናሳስባለን 🙏                                አዘጋጅ: ት/ት ክፍል

ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም
ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም ኮርስ ያልተማራችሁ እና ከቀዳማይ ኮርስ 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁ ሁሉ ያለን ጊዜ አጭር ስለሆነ ሙሉ ኮርሱን በመከታተልና በመጨረስ ለአገልግሎት ብቁ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏 🔴 ማሳሰቢያ :- 👉 ኮርሱ የሚጀመረው በቀን 09/10/2017 ዓ. ም 👉 ኮርሱ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ 👉 ቀዳማይን ያልጨረሰ ሁሉ ሙሉውን የመማር ግዴታ አለበት ( 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁን ጨምሮ ) 👉 ያልተማራችሁ ትምህርቱ ላይ እንድትገኙ እና ላልሰሙ ወንድም እህቶቻችሁን እንድትጋብዙ ስንል በአምላከ ቅድስት አርሴማ ስም እናሳስባለን 🙏                                አዘጋጅ: ጉባኤ ደማስቆ : ት/ት ክፍል

1 ቀን ቀረው እርሶስ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል
1 ቀን ቀረው እርሶስ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል

✨✨✨ሠናይ ዕለት ✨✨✨
✨✨✨ሠናይ ዕለት ✨✨✨

❤ ከዚህም በኋላ አንጾኪያ ከተማ አደረሱበት ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አቀረቡት እርሱም በእሳት በአፈሉት በወይን በሙጫ ድፍድፍ በማቃጠል አሠቃየው ከዚያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አዳነው። ዳግመኛም በአንገቱ ከባድ ደንጊያ በሰንሰለት አሥረው ወደ ባሕርም አንከባለው ግማሽ ሥጋውን እንዲአሠጥሙ ግማሹን ግን እንዳያሠጥሙ አዘዘ እነርሱም በባሕሩ ዳር ታላቅ ምሰሶ ተከሉ በዚያም እንዳዘዛቸው አድርገው አሥረው ተዉት በዚህ ሥቃይም ከቀኑ እስከ ሰባት ሰዓት ዋለ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ፈትቶ አወጣው እንደ ቀድሞውም ጤነኛ አደረገው ንጉሡም አይቶ አደነቀ ሰያፊውንም ፈጥኖ አንገቱን ሰኔ 5 ቀን ቆርጦ በባሕር ዳር ከምድር ላይ ጣለው ሥጋውንም አንሥቶ ከቊርበት በተሠራ ጋን ውስጥ ጨምረው ሥጋውም ከራሱ ጋራ ተገናኘና እንዳልተቆረጠ ሆነ ጋኑም በሃያ ቀን እስክንድርያ እስከሚደርስ ድረስ ሰው ሳይሸከመው ብቻውን የሚጓዝ ሆነ። ❤ የቦሀ አገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ መጡ ተሸክመውም በቦሀ አገር ከአለው ቤቱ ውስጥ አስገብተው ከወንድሙ አባ ጴጥሮስ ጋራ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባ ብሶይና በአባ ጴጥሮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ቢፋሞን፦ ይህ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ የእናቱ ወንድም ልጅ ነበር ዮሐንስም ታሥሮ ሳለ ያገለግለው ነበር። ዮሐንስም ገድሉን በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ገነዘ በበድኑ ላይም እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእግዚአብሔር የተለየሁ ሁኜ ብቻዬን እንዴት ትተወኛለህ" ከቅዱስ ዮሐንስ ሥጋም እንዲህ የሚል ቃል ወጣ ወዳጄ ቢፋሞን ከእኔ ጋራ መኖርን ከፈለግህ ፈጥነህ ወደ መኰንኑ ሔደህ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመን ነገም ወደ እኔ ትመጣለህ"። ይህንንም ሰምቶ የዮሐንስን ሥጋውን ቀበረ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሔደ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ የረከሱ ጣዖታቱን ሰደበ። መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚህም በኋላ ራሱን ሰኔ 5 ቀን በሰይፍ ቆረጠ የምስክርነቱንም አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #መነኰሳዪት_ቅድስት_ማርታ፦ ይቺም ቅድስት ሃይማኖቷ የጸና ምግባርዋም የቀና ክርስቶስ ያደረባት ናት። በስደትም ዐረፈችና በተራራ ውስጥ ተቀበረች የመነኰሳዪት የቅድስት ማርታ በረከቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 5 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለብሶይ_ዘምድረ_ቦሀ_ሀገሩ። እለ አውጽኡ በመጥባሕት አሥራወ እዴሁ ወእግሩ። ላዕሌሁ ዳግመ እንዘ ይትዔየሩ። መንፈቀ ሥጋሁ ውስተ ባሕር ወገሩ። ወመንፈቆሰ ኢይረድ ዲበ ዐምድ አሠሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የሰኔ_5።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ይትነሥእ እግዚአብሔር ወይዘረዉ ፀሩ። ወይጒየዩ ጸላእቱ እምቅድመ ገጹ። ከመ የኀልቅ ጢስ ከማሁ የኀልቁ"። መዝ 67፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 2፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 3፥1-11 እ የሚነበበው የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥8-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ   ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ሰሞንና የጾም ጊዜ ይሁንልን። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለታማኛና ተጋዳይ ለሆነ ለምሥራቃዊው አባት #ለቅዱስ_ያዕቆብ ፣ ለተመረጠ ኃያል ተጋዳይ #ለአባ_ብሶይ_ለዕረፍታቸው_በዓል፣ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅል ለአጎት ልጅ #ለቅዱስ_ቢፋሞን ምስክር ለሆነበትና ሃይማኖቷ ለጸና ምግባርዋም ለቀና ክርስቶስ ላደረባት #ለመነኰሳዪት_ለቅድስት_ማርታ_ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከቅዱሳን_ከመርቆሬዎስና #ከመቃርስ፣ #ከይስሐቅና_ከዕብሎን_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ #ከአብላርዮስም ከምስክርነቱ መታሰቢያና በጌታችን ስም በባሕር ውስጥ በመስጠም ከዐረፈ #ከቅዱስ_መቃርስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ምሥራቃዊው_አባት_ቅዱስ_ያዕቆብ፦ ይህም ቅዱስ ከምዕመን ዋልንጦስ ዘመን በኋላ የታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ በሆነ በታናሹ ቈስጠንጢኖስ ዘመንና በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን በምሥራቅ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም በገድል ተጠምዶ ኖረ። ዋልንጦስ ከተገደለ በኋላም በእርሱ ፈንታ ወንድሙ ነገሠ እርሱም አርዮሳዊ ነበር የጣዖት ቤቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሃይማኖታቸው የቀናውን የምዕመናንን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲዘጉ አርዮሳውያንን አዘዛቸው ምዕመናን በግዳጅ እስቲገቡ ድረስ እንዲሁ አደረጉ። ይህም የንጉሡ ትእዛዝ በሚገዛው አገር ሁሉ ደረሰ። ❤ ይህም አባ ያዕቆብም ይሁን በሰማ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ ያንጊዜም ተነሥቶ ወደ ቊስጥንጥንያ ሔደ በምዕራብ በኩል የተነሡበትን ጠላቶቹን ሒዶ ለመውጋት ሲወጣ ንጉሡን አገኘው። ይህ አባት ያዕቆብም በፊቱ ቆሞ "ንጉሥ ሆይ በጠላቶችህ ላይ እግዚአብሔር ይረዳህ ዘንድ ምዕመናን እንዲጸልዩልህ አብያተ ክርስቲያናቸውን ክፈትላቸው ብዬ እለምንሃለሁ ይህን ካላደረግህ ግን እግዚአብሔር ይጥልሃል ከጠላቶችህም ሸሽተህ በእሳት ቃጠሎ ትሞታለህ" አለው። ንጉሡም ይዞ ለሚጠብቀው ወታደር "በሰላምና በደኅንነት እስከምመለስ ጠብቀው" ብሎ ሰጠው። ቅዱስ ያዕቆብም "አንተ በደኅና ከተመለስክ በእኔ አንደበት እግዚአብሔር አልተናገረም ማለት ነዋ" አለው። ❤ ያንጊዜም ቅዱሱን ይዘው ደብድበው አሠሩት ንጉሡም ከሠራዊቱ ጋራ ወደ ጦርነቱ ሔደ በረከሰች ጸሎታቸው አርዮሳውያን ምንም ቢራዱት ክብር ይግባውና ጌታችን በጠላቶቹ አንጻር ጣለው እነርሱም ጠላቶቹ እየተከተሉት ሸሽቶ ከአንዲት ዐፀድ ውስጥ ገባ በዚያም በረከሰች ሃይማኖቱ ከሚያምን ወገኖቹ ጋር በእሳት አቃጠሉት። የቀሩትም ሠራዊት ሁሉ ሸሽተው ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ ይህንንም መልካም ዜና ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን ተናገሩ የዚህም ጻድቅ አባት ያዕቆብም ትንቢቱ ተፈጸመ ከእሥር ቤትም በክብር አወጡት። ምዕመናንም ከሀድያንም በላዩ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ተረዱ ከአርዮሳውያንም ብዙዎቹ የአባቶቻችን ሐዋርያት ወደሆነች ቅን ሃይማኖት ተመለሱ በዚህ አባት እግር በታች ሰግደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ ታመነ። ❤ ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ቦታው ተመለሰ አርፎ የሕይወትና የሰማዕትነት አክሊልን እስከ ተቀበለ ድረስ እንደ ቀድሞው በገድል ተጠምዶ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ በቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ብሶይ፦ የዚህ ቅዱስ አባቶቹ ክብር ይግባውና ጌታ ክርስቶስን የሚያመልኩና ትዕዛዙን የሚጠብቁ ክርስቲያን ነበሩ የአባቱም ስም ታግኅስጦስ ነው እርሱም ከአንጾኪያ የቃው ገዥ ነበር የእናቱም ስም ክሪስ ይባላል። እነርሱም ልጅ ሳይኖራቸው ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖሩ ስለዚህም እጅግ እያዘኑ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ይለምኑ ነበር። ከሌሊቶችም በአንዲቱ ለታግኅስጦስ ብርሃን የለበሰ ሰው ተገልጦለት እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቷል ሚስትህም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች ስሙንም ብሶይ ትለዋለህ እርሱም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ዕቃ ይሆናል እርሱም ደግሞ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ ምስክ ይሆናልና ሥቃይና መከራም ተቀብሎ የሰማዕትነት አክሊልን ይቀዳጃል"። ከእንቅልፉ ነቅቶ ራእይ እንዳየ ለሚስቱ ነገራት። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ፀንሳ ይህን ቅዱስ ሚያዝያ አንድ ቀን ወለደችው ዕውቀትን ጥበብንና ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት። ❤ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ አክሚም ዮሴፍ ወደሚባል አንድ አረጋዊ መምህር ላኩት በዚያም እየተማረ ከወንድሙ ጴጥሮስ ጋር በጸሎትና በጾም ተጠምዶ ድንቆች ተአምራትን እያደረገ ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃያ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ የስዒድ መኰንን ወዳለበት ወደ ቃው ከተማ መጣ እርሱም ክርስቲያኖችን እያሳደደ ከእርሳቸው ይገድል ነበር። ያን ጊዜም ክፉዎች ሰዎች ወደ መኰንኑ መጥተው "ለቃልህ የማይታዘዙና ለአማልክት መስገድንም እምቢ የሚሉ ሁለት ዲያቆናት አሉ" ብለው እኒህ የከበሩ አባ ብሶይንና አባ ጼጥሮስን ከሰሱአቸው። በዚያም ጊዜም እንዲአቀርቧቸው አዘዘና አቅርበው በፊቱ አቆሙአቸው ስለ ሥራቸውም መረመራቸው ክርስቲያን እንደ ሆኑም ከቃላቸው ሰምቶ እንዲአሥሩአቸው አዘዘ። ❤ ከሦስት ወር በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦላቸው "እኔ የምሥራች የምናገር ገብርኤል ረዳችሁና እነግራችሁ ዘንድ ወደእናንተ እግዚአብሔር ላከኝ ስም አጠራራችሁና መታሰቢያችሁ ለዘላለሙ ይኖር ዘንድ አለውና" አላቸው። "አንተም ወዳጄ ብሶይ ታላቅ ተጋድሎ አንተን ይጠብቅሃል ወደ እስክንድርያ ከተማ ሊሰዱህ አላቸው። ከዚያም ወደ አንጾኪያ ወስደውህ በዚያ የምስክርነትህ ገድል ይፈጸማል"። ❤ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ከወህኒ ቤት አውጥቶ ለጣዖት እንዲሰግድ አስገደደው እምቢ ባለውም ጊዜ ከባላ ላይ አውጥተው በግንድ ውስጥ እጅግ እንዲጨምቁት ወታደሮቹን አዘዘ። በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወሪዶ ግንዱን ሰብሮ ቅዱስ ብሶይን በመዳሠሥ አዳነው። ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ጨምሩት በዚያም ብዙ በሽቶኞችን ፈወሳቸው። ዳግመኛም እንዲህ አዘዘ ከወህኒ ቤት አውጥተው በመርከብ ሆድ ውስጥ አስገብተው አንገቱን በብረት ማሠሪያ እንዲአሥሩት እንጀራና ውኃ እንዳይሰጡት አዘዘ እንደዚህም ኖረ ዐሥር ቀን ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ አውጥተው በፊቱ አቁሞ "ለአማልክቶቼ ስገድ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከባላ ግንድ ላይ አውጥተው አጥብቀው እንዲጨምቁት ሁለተኛ አዘዘ። እንዲሁም በእርሱ ላይ አድርገው በወህኒ ቤት አሠሩት። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ ተገለጠለትና "አይዞህ መልካም ገድልህን እስከምትፈጽም እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አትፍራ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወደ ቁልቁልያኖስ መኰንን ሰደዱት እርሱም ስለ ሥራው ሁሉ መረመረውና ሕዋሳቱ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ። ሁለተኛም ዘይትን አፍልተው በጆሮው፣ በአፉና በደረቱ ላይ እንዲአፈስሱ ጐኖቹንም በእሳት ሠብራት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ደግሞም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በዐይኖቹ ውስጥ አደረጓቸው። ሁለተኛም የእጆቹንና የእግሮቹን ሥሮች ሕዋሳቱንም ሁሉ እንዲነቅሉ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሕዋሳቱን ሁሉ ፈወሰው።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ሰኔ ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን መጀመርያ ዘማዊ ሆና በንስሓ ከተመረሰች በኋላ #በትኅርምትና_በተጋድሎ_ለሃያ_አምስት_ዓመታት ለጸናች #ለቅድስት_ማርታ_ለዕረፍቷ_በዓል፣ #ለኤጲስቆጶስ_ለአባ_ኤላርዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት #ኮርዮን_ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅድስት_ማርታ፦ ይቺም ቅድስት ከምስር ተወላጆች ውስጥ ነበረች ወላጆቿም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ከታናሽነቷም ጀምራ የረከሰ ዝሙትን የምትወድ ነበረች የከተማ ጐልማሶችና ታላላቆችም በሥውር ወደርሷ እየመጡ ያመነዝሩ ነበር። ከዚህ በኋላም ሥራዋ ተገለጠ የርኵሰት ሥራንም በግልጥ አብዝታ የምትሠራ ሆነች። ❤ ክብር ምስጋና ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ ልደቱ በዓል በሆነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ልትገባም በፈለገች ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ከለከላት እንዲህም አላት "አንቺ በምግባር የረከስሽ ስለሆነ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት አይገባሽም" ይተዋትም ዘንድ አባበለችው እርሱ ግን ከለከላት በመካከላቸውም ታላቅ ጸብ ሆነ። ኤጲስቆጶሱም ጨኹት ሰምቶ ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ደረሰ ማርታንም በአያት ጊዜ "የእግዚአብሔር ቤቱ የከበረና የነጻ እንደ ሆነ አታውቂምን አንቺም የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገቢ ዘንድ አይገባሽም" አላት። በዚያን ጊዜም አለቀሰች "ንስሐ እገባለሁ እንጂ ወደዚህ ሥራ እንግዲህ አልመለሰም ብትቀበለኝም እመነኵሳለሁ" አለችው። ኤጲስቆጶሱም "ገንዘብሽንና ጥሪትሽን ሁሉ ወደዚህ አምጥተሽ በፊትሽ ካላቃጠልነው አላምንሽም" አላት። ያን ጊዜም ሒዳ ጥሪቷንና ወጋው ብዙ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶስ ፊት ጣለችው እርሱም በፊቷ አቃጠለው። ❤ ከዚህም በኋላ የራስዋን ጠጉር ተላጨች ኤጲስቆሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት በዚያም ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች ነፈሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር "በጭቃና በደንጊያ ወደ ታነፀው ቤት ለመግባት ካልተዉሽ በብርሃን ወደ ተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ" ሁለተኛም "በጸሎቷ አቤቱ ቤተ ክርስቲያንህን ከሚጠብቀው የደረሰብኝን ኅፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ" አለች። ❤ ይችም ቅድስት ሰይጣን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሃያ አምስት ዓመት ስትጋደል ኖረች በዚህ ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም ከዚህም በኋላ በሰላም ሰኔ 3 ቀን ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ማርታ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ኤጲስቆጶስ_አባ_ኤላርዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከሀዲውን ንጉሥ ዮላኪዮስ ጣዖታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር። ንጉሥ ዮላኪዮስም "አይሁድ የተሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሀዲ ትለኛለኛለህ እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ" አለው። ❤ ከዚህ በኋላም ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኰንን ሰጥቶ ባለመራራት ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እንዲአሠቃየው አዘዘው መኰንኑም ወስዶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አንዲት ቀን እንኳን ከቶ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ እያሠቃየው አንድ ዓመት ሙሉ ኖረ። በዓመቱም ፍጻሜ በእሳት ውስጥ ጣሉት እርሱም ከእሳት መካከል ቁሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ስለዚህችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ ከዚህም በኋላ ከአታክልት መካከል እንደ ሚወጣ ሁኖ ከእሳት አወጡት። መኰንኑም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ በእርሱ ላይም የሚያደርገውን በአጣ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕታት አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኤላርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 3 ስንክሳር።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለማርታ_ጥዕምተ_ዝክር_ወዜና። ዘተዐጽፈት ሠቀ አልባሰ ወርቅ መኒና። አመ ገሠጸ ኢትባእ ውስተ ቤተ መቅደስ እንበለ ንጽሕና። እስከነ ሞዓቶ ለእኩይ ሕሊና። ዓቃቤ ኆኅት ምክንያተ ኮና"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_3።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "አርኅው ሊተ አናቅጸ ጽድቅ። ዕባእ ውስቴቶን ወእግነይ ለእግዚአብሔር። ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር"። መዝ 117፥19-20። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 2፥1-4፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 20፥16-25። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 7፥37-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠልስቱ ምዕት ቅዳሴ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን..