en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
601
Subscribers
-124 hours
-87 days
-1830 days
Posts Archive
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፳፩ (21) ቀን። እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።                  መስከረም ፳፩ (21) ቀን። እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል #በግሸን_በመስቀለኛው_ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ #ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ሃይማኖታዊ_ውሳኔ ለመወሰን፤ #በኒቅያ_ጉባኤ_አርዮስን_ለማውገዝ ከሩቅ #ለተሰባሰቡበት_ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው #ለቅዱስ_ጢባርዮስ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ #ለቅዱስ_ቆጵርያኖስና_ለድንግሊቱ #ቅድስት_ዮስቴና ሰማዕትናት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                 #በዚችም_ቀን_ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት የአንዱ ሐዋርያ #የቅዱስ_ጢባርዮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                 #ቅዱስ_ቆጵርያኖስና_ድንግሊቱ_ቅድስት_ዮስቴና፦ ይህም ቅዱስ ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሀዲና ሥራየኛ ነበር እርሱም ለሥራየኞች ሁሉ አለቃቸው ነው። በሥራዩም ሥራ ከመመካቱ ብዛት የተነሣ በሥራይ የሚበልጠው ካለ ሊያይና ከዚያ ሊማር ከሌለ ግን በእነርሱ ላይ ሊመካባቸው ወደ አንጾኪያ አገር ሔደ። "#ሰላም_ሰላም_ለጢባርዮስ_ስንዕ። ምስለ ፸ወ፪ቱ አርድእተ እግዚእ። በዕለተ ዕረፍትከ ዮም ብሔረ ተድላ ወፍግዕ። ባርከነ ለደቂቅከ በውስተ ዛቲ ምሥዋዕ። እስመ ለመምህር ቡራኬ ሥሩዕ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_21።

የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከሬን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ። መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ. /አዲስ አበባ) በሀሌሉያ ሆስፒታል
+4
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከሬን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ። መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ. /አዲስ አበባ) በሀሌሉያ ሆስፒታል  ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር  አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል። በሥነሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብሰት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል። EOTC TV

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፳ (20) ቀን። እንኳን #ለእስክንድርያ_ሃያ_ስምንተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_አትናቴዎስ_ካልዕ_ለዕረፍት_በዓልና ስለ #መስቀል ለሚ
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።              መስከረም ፳ (20) ቀን። እንኳን #ለእስክንድርያ_ሃያ_ስምንተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_አትናቴዎስ_ካልዕ_ለዕረፍት_በዓልና ስለ #መስቀል ለሚነገርበት (ዘመነ መስቀለ) #ዕለተ ሰንበት   በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ #ከድንግል_መሊዳማ በሰማዕትነት ከዐረፈች፣ #ከድንግል_አቴና፣ #ከፊና_ከፊላ፣ ከመነኰስ #አብርሃም_ከታዴዎስ_ከአቢናፍንዮስ፣ #ከጻድቁ_አርማንዮስ፣ #ከኢየሩሳሌም፣ ከኤጲስቆጶሳት አለቃ ሰማዕት ከሆነ #ከስምዖን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፫ "#ዝንቱ_መስቀል_ቤዛነ_መድኃኒትነ ለአይሁድ ስደተ ኮነ #ዝንቱ_መስቀል_ቤዛነ_መድኃኒትነ ወለነኒ ሕይወተ ኮነነ #ዝንቱ_መስቀል_ቤዛነ_መድኃኒትነ ዮም #መስቀል_ተሰብሐ_ዮም_መስቀል_ለአኅው_አብርሃ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኅኒትነ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኅኒትነ። ትርጉም፦ #መስቀል_ለእኛ_መድኃኒታችንና_ሕይወት_ሆነን፣ ለአይሁድ ግን ስደታቸው ሆነ፤ ዛሬ መስቀል ተመሰገነ (ከበረ) ዛሬ መስቀል ለወንድሞች አበራ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው።       ዘመነ መስቀል በዚህ ወቅት ከመስከረም ፲፮ – ፳፭ ቀን ድረስ ባለው ክፍለ ክረምት ነገረ መስቀሉን የሚመለከት ትምህርት በቤተ ክርስቲያናችን በሰፊው ይነገራል፡፡ "#ሰላም_ለአትናቴዎስ_ለእስክንድርያ_ሥዩማ። ወማኅቶት ብሩህ ዘይነብር ዲበ ተቅዋማ። ዓዲ ለፊላ ወመሊዳማ። አእዳወ ዝንቱ ወእማንቱ ይኩናኒ ግርማ። በማእተበ ሕይወት መስቀል ፍጽምየ ይኅትማ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)

የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከሬን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ። መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ. /አዲስ አበባ) በሀሌሉያ ሆስፒታል  ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር  አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል። በሥነሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብሰት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል። EOTC TV

ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ  ሥርዓተ ቀብርን አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጠ። (መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም) +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++! ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 6 ሰዓት ይፈጸማል ሲሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገለጹ። የቅዱስ  ሲኖዶስ  ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ  እና  አካባቢው ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ  አቡነ ጴጥሮስ  (ዶ/ር) እንደገለጹት  የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ  ክቡር አስክሬን ነገ ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 9 ሰዓት ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም የሚመጣ ሲሆን ለሊቀ ጳጳስ በሚመጥን ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐት ሲፈታ አድሮ በማኅሌትና በቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎቱ የሚከናወን ይሆናል። እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቅዳሴ በኃላ የብፁዕነታቸው ክቡር አስክሬን ወደ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚሄድ ሲሆን በዚያ አስፈላጊው መንፈሳዊ ሥርዓት ተከናውኖ ግብአተ መሬት እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል ዘመድ ወዳጆቻቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በመርሐ ግብሩ መሠረት ተገኝተው አባታችንን እንዲሸኙ ጥሪ ቀርቧል። EOTC TV

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፱ (19) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጵያ_ንጉሥ_ለናዖድ_ልጅ ለከበረችና ለተባረከች #ለቅድስት_ሮማነ_ወርቅ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።                 መስከረም ፲፱ (19) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጵያ_ንጉሥ_ለናዖድ_ልጅ ለከበረችና ለተባረከች #ለቅድስት_ሮማነ_ወርቅ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ #ለከበረ_ለመስቀል_ለበዓሉ መታሰቢያ፣ ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት ለሆነ #ለአርማንያ_ሊቀ_ጳጳሳት #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ከዐዘቅት_ለወጣበት ለመታሰቢያ ቀን በዓልና በሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ዘመነ ለሆነ #ለከበረ_ለገዳማዊ_ቂርቆስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።                                #በዚችም_ቀን_ደግሞ_የከበረ_መስቀል_የበዓሉ መታሰቢያ ነው በተገኘ ጊዜ ሦስት ቀኖች ያህል በፍጹም ደስታ በዓልን አድርገውለት ነበርና እኛም እንዲሁ በታላቅ ደስታ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ድኅነታችን በእርሱ ተደርጎልናልና። በመስቀሉ ለአዳነን ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን ሁላችንን የሐዋርያት የሆነች የከበረች የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለእኛ የተቀበለውን መከራውን የምናስበውን በባለሟልነትና በፍቅሩ ወደእርሱ ያቅርበን ለዘላለሙ አሜን።                                 #በዚችም_ቀን_የኢትዮጵያ_ንጉሥ_የናዖድ_ልጅ የከበረችና #የተባረከች_ሮማነ_ወርቅ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። እርሷም መጾምና መጸለይን የምትወድ ድኆችንና ችግረኞችን የምትጎበኝ ነበረች እግዚአብሔር በቅድስት ሮማነ ወርቅ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። "#ሰላም_ለቂርቆስ_ለነቢረ_ገዳም ዘአፍቀራ ይሰቲ ሐሊበ ቶራ። ድኅረ አመከሮ ሰይጣን በዘዚአሁ መከራ። አዕይንቲሆሙ ለኤጲስቆጶሳት ነጸራ። በጊዜ ዕረፍቱ ዘኮነ ነከራ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት #የብፁዕ_አቡነ_ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት #የብፁዕ_አቡነ_ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት ያስተላለፉት አባታዊ የሐዘን መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። «መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት:–ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው?» መዝሙር ፹፱፥፵፰ የትህትና፣ የጸሎት ሕይወት እና የመልካምነት ምሳሌ የነበሩት #ብፁዕ_አባ_ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሰማነው በታላቅ ሐዘን ነው። ያለንበትን ፈተና የበዛበት ዘመን በጸሎት የሚያሻግሩ አባቶችን ማጣት  ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ቢሆንም በቅዱስ መጽሐፍ ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ መኖር የሚችል ማን ነው? እንደተባለ ሰው በምድር ላይ የሚኖርበት ዘመን በእግዚአብሔር ዘንድ የተቆጠረ እና የተለካ በመሆኑ ብፁዕነታቸው  ሃይማኖትን ጠብቀውና መልካሙን ገድል ፈጽመው  ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር  በክብር ተሸጋግረዋል። ብፁዕነታቸው በዕረፍተ ሥጋ ከእኛ በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ቢሰማንም በሰማይ የሚጠብቃቸውን ክብር እያሰብን እንጽናናለን። የብፁዕነታቸውን ነፍስ በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት አጠገብ ያሳርፍልን! ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውም መጽናናትን ያድልልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ይቀድስ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መስከረም 18 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፰ (18) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ወደ አርማንያ አገር ሲሆዱ ኢያሪኮ ባሕር በአጽፍቸው እንጀልባ አድርገው ለተሻ
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።               መስከረም ፲፰ (18) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ወደ አርማንያ አገር ሲሆዱ ኢያሪኮ ባሕር በአጽፍቸው እንጀልባ አድርገው ለተሻገኑ #ለከፍሌ_ባሕር #ለአቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ለዕረፍት_በዓል፣ አሁን ሶፍ ዑመር ዋሻ እየተባለ የሚጠራው የጸሎት በዓታቸው ለነበረ #ለጽጋግ_መምህር_ለአቡነ_አኖሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።                                #ከፋሌ_ባህር_አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ክርስቶስ ሞዓ የእናቱ ስም ስነ ሕይወት ይባላል ሁለቱም ደጋጎች እግዙአብሔርን የሚፈሩና በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ነበሩ ። ከዘህም በኋላ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ይህን ቅዱስ ወለዱት ስሙን የጌታ ጥብቅ ብለው ሰየሙት። በአደገም ጊዜ የዳዊትን መዝሙርና የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን አስተማሩት። እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ_ጌታችን_በደሃ ሰው ተመስሎ ተገልጦ ቁራሽ እንጀራ ለለመናትን በኋላም በጀርባዋ አዝላ ለሸኘችው፤ በጎኗ ተኝታ ለማታውቅ፤ #በጌታችን_40_ጾም_ወራት ከሰንበት በቀር ምንም የማትቀምስ፤ ነብሮች የእግሯን ትቢያ ይልሱላት ለነበረች #ለታላቋ_እናትን_ለቅድስት_ጸበለ_ማርያም ለዕለፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። "#ሰላም_ለያዕቆብ_መስተጋድል ጽሙድ። እንተ ነበረ ዐሪጎ መልዕልተ ነዋኅ ማኅፈድ። ለአህጒሎ ንጉሥ ከሀዲ ዓጻሬ ሰማዕታት በምክያድ። አይኅአ በጸሎቱ ወዘንመ ነድ። ምስለ ደመና ጸሊም ወጸዩዕ በረድ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)                                 

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፯ (17) ቀን። እንኳን #ለጌታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለተሰቀለበት #ለከበረ_ለመስቀሉ_በዓል (ቁፍሮ ለተጀመረበት)፣ ለከበረች
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።                መስከረም ፲፯ (17) ቀን። እንኳን #ለጌታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለተሰቀለበት #ለከበረ_ለመስቀሉ_በዓል (ቁፍሮ ለተጀመረበት)፣ ለከበረች ለሮማዊት #ለቅድስት_ታኦግስጣ_ለዕረፍቷ_በዓልና ለእስክንድር ዐሥራ አራተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዲዮናስዮስ_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ሊቢባ፣ #ከኪርያኖስ፣ #ከዮስጢና፣ #ከቴክሴልጥስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                #የዕለቱ_ምልጣን_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "#ሞገሰ_መስቀሉ የኀሉ ምስሌነ ለኢየሱስ ክርስቶስ እስመ ውእቱ ሰላምክሙ ዘረሰዮሙ አሐዱ ለክልዔሆሙ ወነሰተ አረፍተ ማእከል እንተ ጽልእ"። ትርጉም፦ ቅድመ ዓለም የነበረ ዛሬም ያለ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የጌታችን የመስቀሉ ሞገስ ከሁላችን ጋር ይኑር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላማችሁ ነውና፤ ሁለታቸውን አንድ ያደረገ የጸብን ግድግዳ አፈረሰ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                                                          መስከረም_ዐሥራ_ሰባት በዚች ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተሰቀለበት #ለከበረ_መስቀል_በዓሉ ነው። ይህም የጻድቁ ንጉሥ የቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ከተሠወረበት የገለጠችው ነው። የጎልጎታን ኮረብታ በአስጠረገች ጊዜ የከበረ መስቀልን አገኘችው ታላቅ ኮረብታም የሆነበት ምክንያት እንዲህ ነው። ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብሩና ከመስቀሉ የሚገለጡ ሁነው ሙታን ይነሡ ነበርና የጎበጡና በሽተኞች ሁሉ ይፈወሱ ነበር።

🌼ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት ወይድኅኑ ፍቁራኒከ"🌼 ✨✨ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው ወዳጆችህ እንዲድኑ" መዝ 59፣4✨ ቸር አምላክ
🌼ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት ወይድኅኑ ፍቁራኒከ"🌼 ✨✨ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው ወዳጆችህ እንዲድኑ" መዝ 59፣4✨ ቸር አምላክ ትናንቱን አሳልፎ እኛንም ለዛሬ አድርሶ ይቺን የተባረከች የመስቀል ዕለት እንድናከብር ስላደለን ስሙን እናመሰግነዋለን፣ መስቀልን ስናስብ እውነትን እናስባለን በዚህም የመስቀል ዕለት ጮማ እየቆረጥ፣ ውስኪ እየተጎንጨ ከሆነ ምኑን መስቀል ሆነው፣   መስቀሉን ከፍ አድርገው ለማክበር ሲተጉ ጠላት አይሆንም ይህን መስቀል አስወግዱ እያለ መደንገጡን ሊያስተጋባ የቆመ ጭፍራ ካለ ያን ጊዜ መስቀል እያከበርን ነው። ማነው መስቀሉን በዕለተ አርብ የጌታን ስቃይ እያሰበ የሚያከብረው፣ እኔስ እላለው በመስቀሉ ጠላት ተዋርዷል፣ በዘመናችንም የተዋረደው ዳቢሎስ በሰዎች እያደረ ከፍ ያለው መስቀል ይጠላ ዘንድ ቢሰራም መውደቁ የማይቀር ነው። ለዚህም እኮ ነው መስቀሉ ለሶስት መቶ ዓመት የተቀበረ ቢሆንም እግዚአብሔር  ንግስት ዕሌኒን አስነሳ፣ መስቀሉ ከፍ ብሎ ተሰቀለ ዳቢሎስ ዳግም ተዋረደ፣ መልኩን እየቀየረ ልዩ ልዩ ተንኮሎች ቢያዘጋጅም መስቀሉን ሊያጠፋ አይችልም በዚህም መስቀሉን ተደስተንም ሆነ ተከፍተንፈተና ብናከብረው ያው ነው። ለተደሰቱት የመስቀሉ ድህነት ነው እያዘኑ የሚያከብሩት የመስቀሉን  እየተጋፈጡ ነው። ጌታችን ሊወደኝ የሚሻ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ያለው ታዲያ በመስቀል እራስን ካልካዱ ድል የለም፣ለዓለም እያረበረቡ መስቀል ቢሉ እነሱ የፉኝት ልጆች እንጂ የክርስቶስ መቼ ይሆኑና የክርስቶስስ ተከታዮች ስለመስቀሉ እራሳቸውን የካዱ፣ ለሆዳቸው ያላደሩ፣ እውነትን እውነት ውሸትን ውሸት የሚሉ ናቸው። በመስቀሉ ለምታምኑ ሁሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን። 💥💥💥💥 ፍኖተ ብርሃን 💥💥💥💥

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፮ (16) ቀን። እንኳን #ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ መቃብር ላይ #ቤተክርስቲያን_ለታነፀችበትና_ለተቀደሰችበት በዓል፣ በኢየሩ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።               መስከረም ፲፮ (16) ቀን። እንኳን #ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ መቃብር ላይ #ቤተክርስቲያን_ለታነፀችበትና_ለተቀደሰችበት በዓል፣ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ ለተሠሩበትና ለከበሩበት በዓል (ለደመራ በዓል)ና በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር ለተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ ለሆነ ለገባኤል ልጅ ለቅዱስ ጦቢት ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ከወርቅላ፣ ከስምዖን፣ ከመርቄኖስ፣ ከሐሊ፣ ከሮቂኖስ፣ ከሉክያኖስ፣ ከአርዝማኖስ፣ ከጴጥሮስ፣ ከሐና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           የዕለቱ አንገርጋሪ፦ ሃሌ ሉያ "ዝኒ ኮነ በፈቃደ እግዚአብሔር ዝንቱ ኵሉ ኮነ ወአንቲኒ ታቦት እምኀበ መጻእኪ ወኀበኒ ተሐውሪ መድኃኒተ ኩኒ ታቦት ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ"። ትርጉም፦ የንጉሥ የሕጉ ታቦት መድኃኒትን ሁኚ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ሆነ፤ አንቺ ታቦት ከወዴት መጣሽ ወዴትስ ትሄጃለሽ።                                                      በዚች ቀን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን የታነፀችበትና የተቀደሰችበት ነው። ደግሞ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ።

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፭ (15) ቀን። እንኳን #ለኢትዮያዊው_ጻድቅ_ማኅሌተ_ጽጌ #ከአባ_ጽጌ_ድንግል ጋር በአንድነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።               መስከረም ፲፭ (15) ቀን። እንኳን #ለኢትዮያዊው_ጻድቅ_ማኅሌተ_ጽጌ #ከአባ_ጽጌ_ድንግል ጋር በአንድነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ለደረሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ገብረ_ማርያም_ዘደብረ_ሐንታ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።                             አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ፦ ጻድቁ  ሃይማኖታቸው ከቀና፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው ከሰመረ ደጋግ ወላጆቻቸው ከአባታቸው ኒቆዲሞስ እናታቸው አመተ ማርያም በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት ኅዳር 24 ቀን ተወለዱ፡፡ ዕደሜአቸው ለትምህርት ሲደር እነዚህ ደጋግ ወላጆቻቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ አሳደጓቸው፡፡                                 "#ሰላም_እብል_ለጴጥሮስ_ብሕትወ። ኮከበ ጠራው። ወውስተ ዓለም ኅሩም እምበሊዐ ኅብስት ወጼው። እስከ አስተርአየ በአምሳለ ምትሐት ሕስው። ተሴስዮ ሣዕር አብደረ በበድው"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)                

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፬ (14) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጽያውያኑ_ጻድቃን #ከሰባቱ_ከዋክብት_ለአንዱ ለቀዳማዊው ንጉሥ #ለዓምደ_ጽዮን_ልጅ ለነበሩና ድ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።              መስከረም ፲፬ (14) ቀን። እንኳን #ለኢትዮጽያውያኑ_ጻድቃን #ከሰባቱ_ከዋክብት_ለአንዱ ለቀዳማዊው ንጉሥ #ለዓምደ_ጽዮን_ልጅ ለነበሩና ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ ለተሻገሩት ለታላቁ አባት #አቡነ_ያሳይ_ዘማንዳባ እና እጆቻቸው እንደፋና እያበሩ #ለጣና_ሐይቅ_ገዳማት_በመብራትነት_ያገለግሉ ለነበሩት #ለፃህና (ጣና) መምህራን ለሆኑ አባቶች ዐሥራ አንደኛ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአቡነ_ጴጥሮስ ቀዳማዊ ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን አቡነ_ያሳይ_ዘማንዳባ፡- አቡነ ያሳይ "ሰባቱ ከዋክብት" ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እነዚህም "ሰባቱ ከዋክብት" የተባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ ናቸው፡፡ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኲሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኰሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ "ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን" በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን ያመነኰሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፫ (13) ቀን። እንኳን #ታላቁና_ቅዱስ_የሆነ_የቂሣርያ_ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ባስልዮስ አንድ ጎልማሳ አገርልጋይ የጌታውን ልጅ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።                መስከረም ፲፫ (13) ቀን። እንኳን #ታላቁና_ቅዱስ_የሆነ_የቂሣርያ_ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ባስልዮስ አንድ ጎልማሳ አገርልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት እርሷንም ከመውደዱ የተነሣ እርሷን ለማግባት ብሎ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔዶ እግዚአብሔር ክዶ በሰይጣን አምኖ በእጁ ፈርሞ ለሰይጣን ሰጠው ይህንን የጽሕፈት ደብዳቤ በእግዚአብሔር ኃይልና በጸሎቱ #ቅዱስ_ባስልዮስ በመደምሰስ ድንቅ ተአምር ላደረገበት ለመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከከበረ_ከባሕታዊ_ከአባ_ይስሐቅ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                     "#በዛቲ_ዕለት_እግዚአብሔር_ገብረ። #በእደ_ባስልዮስ መንክረ። በአፍቅሮ ወለት አሐቲ ኀበ መሠርይ ዘሖረ። እንዘ ይከሥት በቅድመ መጽሐፈ ክህደቱ ስውረ። እምእደ ሰይጣን አንገፈ ወፄወወ ገብረ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፪ (12) ቀን። እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል እግዚአብሔር ወደ #አሞፅ_ልጅ_ወደ_ነቢዩ_ኢሳይያስ #ለንጉሡ_ሕዝቅያስ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፲፪ (12) ቀን። እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል እግዚአብሔር ወደ #አሞፅ_ልጅ_ወደ_ነቢዩ_ኢሳይያስ #ለንጉሡ_ሕዝቅያስ ከደዌው እንዳዳነው #በዕድሜው_ላይ ዐሥራ_አምስት_ዓመት እንደተጨመረለት ንገረው ብሎ ለተላከበት ለወራዊ መታሰብያ በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእመቤታችን እናት አባት #ከቅዱስ_ኢያቄምና_ከቅድስት_ሐና ከመታሰቢያቸው #ከሰማዕት_ቅዱስ_አፍላሆስ ከመታሰቢያውና ከሥጋው ፍልሰት፣ #ከእስክድርያ አገር ከሆኑ #ከባልንጀሮቹ ሰማዕታትም ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕታት #ከቅዱሳን_ከሉዩራስና_ባሌኒኮስ፣  እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።     እንኳን #በኤፌሶን_አገር_በ431 ዓ.ም (ሦስተኛው ጉባኤ) ሁለት መቶ ኤጲስ ቆጶሳት ሁለት ባሕሪ ሁለት አካል ብሎ የተነሣው #ከሀዲውን_ንስጥሮስን #በእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት_በቅዱስ_አባ_ቄርሎስ ሊቀ መንበርነት ለማውገዝ ለተሰበሰቡበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             በዚችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን ከተማ የቅዱሳን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።  "#ሰላም_ለምቅወምከ_ዘልዑል_ማዕረጋ። እምቅዋመ አእላፍ እንግልጋ። #ሚካኤል_መንፈስ ዘንበለ ሥጋ። ታድኅን ዘተመንደበ ለማዕበለ ባሕር እምጹጋ ወለእለ በበድው ትባልሕ በጸጋ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_12።                            

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲፩ (11) ቀን። እንኳን #ለአንጾኪያ_ነገሥታት_አባታቸው፤ መካሪያቸው ለሆነ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ለነበረው፤ ጌታችን ከሞት እያ
 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፲፩ (11) ቀን። እንኳን #ለአንጾኪያ_ነገሥታት_አባታቸው፤ መካሪያቸው ለሆነ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ለነበረው፤ ጌታችን ከሞት እያስነሣው በጽኑ ሥቃይና ተጋድሎ ሲጋደል ለኖረው ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱስ_ፋሲለደስ፣ #በቅዱሳን_አባቶቻችን_ሐዋርያት ዘመን እግዚአብሔርን ያገለገለ #የጭፍራ_አለቃ (፻አለቃ) ለሆነ ትሩፋቱና ገድሉም ላማረ ለጻድቁ ሰው #ለቅዱስ_ቆርኔሌዎስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለእስክድርያ አገር በንጉሥ ዘይኑን ዘመን ለነበረች #ለቅድስት ታዖድራ ለዕረፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የስሟ ትርጓሜ ጣፋጭ ከሆነ ከከበረች #ከሰማዕቷ_ከቅድስት_በነፍዝዝ ከዕረፍት በዓል፣ #ስማቸው_ሱርስ_አጤኬዎስና_መስተሐድራ ከሚባሉ ሦስት ገበሬዎች ከእስና አገር ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ #ከቅዱሳን_ከባስልዮስ ሰማዕትና #ከኢየሩሳሌም_ኤጲስቆጶስ_ከቴዎድሮስ ከሰማዕት አለቃ #ከቀውስጦስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                        "#ሰላም_ለጸአተ_ነፍስከ እምቤተ ሥጋሃ ንጹሕ። በስሑል መጥባሕት ወበአፈ ሰይፍ በሊህ። #ሊቀ_ሰማዕታት_መርዓዊ_ቅዱስ_ፋሲለደስ_ፍሡ። ለነፍስከ ጊዜ ጸአታ ምስከ ቃለ ወይሌ ወላህ። ሰብአ ሀገር በከዩ እንዘ ይብሉ አህ"። #መልክዐ_ቅዱስ_ፋሲለደስ።

🌼🌼🌼🌼🙏🙏🙏🙏🌼🌼🌼🌼 "ሰላም ለሥዕልኪ ሓፈ ማኅየዌ፥ በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ፥ ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፥ ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵ
🌼🌼🌼🌼🙏🙏🙏🙏🌼🌼🌼🌼 "ሰላም ለሥዕልኪ ሓፈ ማኅየዌ፥ በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ፥ ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፥ ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፥ ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ኀላዌ፡፡ ትርጓሜ በጼዴንያና በግብፅ ያለ ሐሰት ፈዋሽ ወዝን ላፈሰሰ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው ማርያም ሆይ ጸሎትሽ ከጥፋት ዘመን ሁሉ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት ቋሚ ጠባቂ ይሁነን፡፡" ሰዓታት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 🌴🌴🌴🌴🌼🌼🌼🌼🌴🌴🌴🌴

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፲ (10) ቀን። እንኳን #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በፄዴንያ_አገር_በማርታ_ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል #ከእመቤታ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፲ (10) ቀን። እንኳን #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #በፄዴንያ_አገር_በማርታ_ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል #ከእመቤታች_ሥዕል ከሠሌዳዋ #ቅባት_እየተንጠፈጠፈ ተአምር ለሠራችበት ቀን መታሰብያ በዓል፣ #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ለተወለደችበት_ለልደቷ በዓል መታሰቢያ (ይህም የአስቄጥስ ገዳም የከበረ አባ መቃርስ በጻፈው መጽሐፈ ግጻዌ ተጽፎል እንዲሁም ደግሞ በላዕላይ ግብጽ በሚገኝ መጽሐፈ ግጻዌ የከበረች ድንግል እመቤታችን የከበረች ሐና በታኅሣሥ ወር በዐሥራ ሰባት እንደፀነሰቻትና መስከም በዐሥር ቀን እንደወለደቻት ተጽፍአል)፣ ለከበረች  ሰማዕትነት ለተቀበለችበት #ለቅድስት_መጥሮንያ_ሰማዕትነት ለተቀበለችበት በዓል ዕረፍት፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #የጌታችን_የአምላካችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ #ቅዱስ_መስቀል_ወደ_አገራችን_ኢትዮጵያ ድንበር ከደረሰበት (ተቀጽል ጽጌ) አፄ መስቀል) ቀን ለመታሰቢያ በዓልና ከከሀዲው #ሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ካዳነቻቸው ከጥበበኛ ከከበረች #ከቅድስት_ዮዲት በዓለ ዕረፍትና #ከቅድስት_አትናስያና_ሦስት_ልጆቿ_ከመታሰቢያቸው በረከትና ረድኤትን ያሳትፈን።                          "#ሰላምለ_ሥዕልኪ ሀፈ ማኅየዌ። #በፄዴንያ_ወኢትዮጵያ በአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመፀብሐዊ #ማቴዎስ_ማርያም እንተረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ፀሎትኪ እምዘመነኵሉ ምንሳዌ። ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ"። #መልክዐ_ሥዕል።

Repost from N/a
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፱ (9) ቀን። እንኳን በሮሜ_አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ #በመላእክት_አለቃ_በቅዱስ_ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን #ላ
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።             መስከረም ፱ (9) ቀን። እንኳን በሮሜ_አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ #በመላእክት_አለቃ_በቅዱስ_ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን #ላደረገው_ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ከኃላፊው #ከዚኽ_ዓለም_መንግሥቱ_መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ ለፈጸመ፤ የደረቀውን ግንድ ላለመለ፣ ለጽጌ፣ ለፍሬ ለአደረሰ ላሳየ እግዚአብሔርን ደስ ላሰኘ #ለንጉሥ_ለቅዱስ_ለአባ_ያሳይ ለዕረፍት በዓልና ለመጺል ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ቢሶራ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ_ጋር_ዐሥራ_አራት_ሺህ_ሰባት መቶ #ሠላሳ_ወንዶችና_ሰባት_ሴቶችም በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ሰላም_ለአባ_ያሳይ_ብእሴ_ሰማይ፤ ለአምላኩ ቀናኢ፤ ሐራይ መዋኢ"። ትርጉም፦ ድል ነሺ ጭፍራ ለአምላኩ ቀናተኛ የሰማይ_ሰው_ለኾነ_ለአባ_ያሳይ ሰላምታ ይገባል።

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። መስከረም ፰ (8) ቀን። እንኳን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ #ለቅዱስ_ዘካርያስ
"በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።            መስከረም ፰ (8) ቀን። እንኳን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ አባት ለበራክዩ ልጅ ለካህንና ለነቢዩ ለሆነ ለከበረ #ለቅዱስ_ዘካርያስ_በንጉሥ_ሄሮድስ_እጅ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለእግዚአብሔ_ሰው ለሆነ፣ ለየዋሁ፣ ለቅኑ፣ ለጻድቁ፣ ለነቢያት አለቃ #ለቅዱስ_ሙሴ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከከበረ_ቅዱስ_ዲማድዮስ ከግብጽ ደቡብ ደንጡ ከሚባ አውራጃ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ ምግቡ የአጋዝን ወተት ከሆነ በዕረፍቱም ጊዜ ብዙ ተአምራትን ከአደረገ ከከበረ #ከገዳማዊ_ከቅዱስ_ቂርቆስ ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ሉክዮስ ከመታሰቢያው፣ #ከቅዱስ_ኤርምያስና_ከቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከቅዱስ_አንዲዎና_ከቅዱስ_ኤልያኖስና ከመነኰስ #አሞንም_ከመታሰቢያቸወ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           በዚች_ቀን_የዓመቱ_ወሮች_መቊጠራያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣ ይኸውም መናዝል የሚለው ነው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውኅራ አሉ ምግብናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው።      "ሰላም_ለዘካርያስ_ካህን_ወነቢይ ዘርእዮ ለካህን ዐቢይ #ዘስሙ_ዮሴዕ ዘይነብር ውስተ ምሥዋዒሁ ለእግዚብሔር"። ትርጉም፦ በእግዚአብሔር መሠዊያ ውስጥ #ስሙ_ዮሴዕ የሚባል ታላቁን ካህን ተቀምጦ ላየው #ለካህኑና_ለነቢዩ_ለቅዱስ_ዘካርያስ ሰላምታ ይገባል።

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ - Statistics & analytics of Telegram channel @finote_media