ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Open in Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Show more612
Subscribers
-124 hours
+17 days
-1030 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምልጣን_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "በኃይለ አጥናን ዘሞዖ ለሰይጣን አሐዱ ቅዱስ እምቅዱሳን ጊዮርጊስ ረባን ሰባኬ ትንሣኤሃ ለእመ ብርሃን አማን ምዑዝ ከመ ዕጣን"። ትርጉም፡- በቅድስት ሥላሴ ኃይል (በሰባቱ ሀብታት ኃይል ሰይጣንን ያሸነፈው) ከቅዱሳን አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መኰንን (የነገሥታት ዘር) ለብርሃን እናት ትንሣኤዋን የሚመሰክር በእውነት እንደ ዕጣን መዓዛው ያማረ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለጊዮርጊስ_ተውላጠ_ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል (ዮም) ተቶስሐ ፍልሰተ ዓፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ አሜሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ"። #መልክአ_ፍልሰታ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ16።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ4፥4-5 ወይም መዝ 121፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው ሮሜ 8፥31-ፍ.ም 2ኛ ዮሐ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ወንጌል ማቴ 26፥26-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤዋና የዕረገቷ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ለትንሣኤዋና_ለዕርገቷ በዓል፣ ለሰማዕታት አለቃ #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሥጋው_ከፋርስ አገር ወደ #አገሩ_ልዳ_በክብር_ለፈለሰበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሶርያ መስፍን ከታላቁ ሰማዕት ከቅዱስ ጊጋር (በስደቷ ጊዜ እመቤታችንና ልጇን መድኀኔዓለምን ዮሴፍን ሰሎሜን አብሮ ወደቤቱ አስገብቶ በመደበቅ ከሄሮድስ ጭፍሮች ያዳናቸው ነው) ከዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ በዚህች ቀን #አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ። የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም "የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት "የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ"። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ። አባቷ ዳዊትም "ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች" እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።
❤ ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።
❤ ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና "የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል" አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።
❤ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው "አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን"።
❤ በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም "በመፍራት ቁሙ" አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
❤ ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት "በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው"።
❤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው "ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ"። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ።
❤ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ በዚህችም ዕለት የሰማዕታት አለቃ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሥጋው_ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሆኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያወቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት በእኛ ላይ ምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የሶሪያ_መስፍን_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊጋር፦ ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኄሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዳገኟቸው አሸሻቸው።
❤ ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ።
❤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊጋር በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅድስት እንባመሪናን ጠርቶ ይገሥጻትና ይረግማት ጀመረ እርሷም ስለምን እንደሚረግማት አላወቀችም ነበር በአወቀችም ጊዜ ከእግሩ በታች ወደቃ "እኔ ወጣት ነኝና በደሌን ይቅር በለኝ" ብላ ለመነችው እርሱም አጅግ ተቆጥቶ ከገዳሙ አባረራት እርሷም ከገዳም ውጭ ሁና እየተጋደለች ኖረች።
❤ ያቺም ልጅ በወለደች ጊዜ የልጅቷ አባት ሕፃኑን አምጥቶ ለቅድስት እንባመሪና ሰጣት እርሷም እግዚአብሔርን እያመሰገነች ተቀበለችው በላሞችና በበጎች ጠባቂዎች ዘንድ ለሕፃኑ ወተትን እየለመነች መዞርን ጀመረች እንደዚህም አድርጋ ሕፃኑን አሳደገችው። ከሦስት ዓመትም በኋላ መነኰሳቱ ተሰብስበው አባ ምኔቱን ለመኑት አባ እንባመሪናን ይቅርታ አድርጎለት ወደ ገዳሙ ይመልሰው ዘንድ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከመነኰሳቱ ጋራ ቀላቀላት ይኸውም ከባድ ቀኖና ከሰጣት በኋላ ነው።
❤ ከዚህም በኋላ ጭንቅ የሆኑ ሥራዎችን ትሠራ ጀመረች የመነኰሳቱንም ቤቶች ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳሙ ውጭ ትጥለዋለች ውኃንም ቀድታ ታጠጣቸዋለች ምግባቸውንም ታዘጋጃለች። ያም ሕፃን አደገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ መነኰሰ።
❤ አርባ ዓመትም ሲፈጸም ሦስት ቀኖች ያህል ታማ በሰላም አረፈች ደወልንም ደውለው መነኰሳቱ ሁሉ ተሰበሰቡ ሊገንዙም ገብተው ልብሶቿን በገለጡ ጊዜ እርሷ ሴት እንደ ሆነች አግኝተዋት ደነገጡ መሪር እንባንም አለቀሱ አበ ምኔቱም በመጣም ጊዜ ያለ በደሏ ከባድ ንስሐ ቀኖና ስለ ሰጣትና በእርሷ ላይ ስለ አደረገው ተግሣጽ መሪር ዕንባን አለቀሰ።
❤ ከዚህም በኋላ መልእክተኞችን ልኮ የዚያችን የሐሰተኛ ልጅ አባቷን አስመጥቶ እንባመሪና ሴት እንደሆነች ነገረው ። ከዚህም በኋላ በድኗን ተሸክመው ይቅር ይበለን የሚል ቃል ከበድኗ እስከ ሰሙ ድረስ "አቤቱ ክርስቶስ ማረን" እያሉ ጸለዩ ከዚያም በኋላ በዝማሬና በማኅሌት ከብዙ ልቅሶ ጋር ገነዟት ከሥጋዋም ተባርከው ቀበሩዋት።
❤ እነሆ እግዚአብሔር ክፉ ሰይጣንን አዝዞት ያቺን ሐሰተኛ ሴት ልጅና ድንግልናዋን የደፈረውን ጉልማሳ ያዘው እያጓተተም አሠቃይቶ ይቀጣቸው ጀመረ ወደ ቅድስት እንባመሪና መቃብር ሔደው ኃጢአታቸውን በሕዝቡ ሁሉ ፊት እስከሚአምኑ እጅግ አሠቃያቸው። ከመቃብርዋም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት እንባ መሪና በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ለውረንዮስ፦ በንጉሥ ዳስዮስ ቄሣር ዘመን ሰማዕትነት የተቀበለ ነው። ይህም ቅዱስ በሃይማኖት የጸና ነው የክብር ባለቤት ስለ ሆነ ስለ ክርስቶስ ሃይማኖት ሊቀ ዲቁና ተሹሞ የሊቀ ጵጵስናውን ገንዘብ ይጠብቅ ነበር።
❤ ንጉሥ ስለርሱ ሰምቶ አምጥተው ከወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ በአስገቡትም ጊዜ በዚያ ዕውር ሰውን አገኘና "አይኖችህ ይገለጡ ዘንድ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ አምነህ በስሙ ትጠመቃለህን?" አለው ዕውሩም "አዎን ጌታዬ" አለ። ያን ጊዜም በውኃው ላይ ጸልዮ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀው ያን ጊዜም አይኖቹ ተገለጠ። እንዲህም ብሎ ጮኸ "በአገልጋዩ ለውረንዮስ ጸሎት ዐይኖቼን የገለጠ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመስገን" ብሎ ጮኸ። ይህንንም ድንቅ አይተው ብዙዎች አመኑ።
❤ ንጉሡም በሰማ ጊዜ የከበረ ለውረንዮስን ወደርሱ ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ በአቀረቡትም ጊዜ ለአማልክት እንዲሰዋ አግባባው እምቢ ባለውም ጊዜ ጥርሶቹን በደንጊያ ሰበሩ ልብሶቹንም ገፈው በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ሥጋው እስከሚቀልጥ ከበታቹ እሳትን አነደዱ።
❤ እርሱም ነፍሱን እስከአሳለፈ ድረስ ወደ ፈጣሪው ይጸልይ ነበር። መላእክትም ሃሌ ሉያ እያሉ ተቀብለው ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አስገቡት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ለውረንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለላለሙ አሜን፡፡ ምንጭ፦ የነሐሴ 15 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥18-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን አምላክን ስለወለደችን #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋን ለመግነዝ #ሐዋርያት_ለተሰበሰቡበት ቀን፣ #ጌታችን ከከበሩ #ቅዱሳን_መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ላጠመቃት፣ #ቅዱስ_ሚካኤል በእሳጉጠት ቅዱስ ሥጋውን ክብር ደሙን ላቀበላትና ዋስ ለሆናት በተአምራቷም ሠላሳ ሺህ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ላሳመነችው ለመኰንን ርባኖስ ልጅ ለታላቋ ሰማዕት #ለቅድስት_ክርስጢ ለዕረፍት በዓል፣ ሴት ሆና እንደ ወንድ መስላ ከወንዶች ገዳም ገብታ ገድሏን ለፈጸመች ታላቅ እናት #ለቅድስት_ከአባ_እንባመሪና ለዕረፍት በዓልና በንጉሥ ዳንዮስ ቄሣር ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ለውረንዮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሠላሳ ሺህ ዐሥራ ሁለት #ከቅድስት_ክርስጢና_ማኅበረ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚህች ቀን አምላክን ስለወለደች #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋን ስለመገነዝ የሐዋርያት ስብሰባ ሆነ። ጸሎቷና በረከቷ የሐዋርያትም በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የመኰንን_ርባኖስ_ልጅ_ታላቋ_ሰማዕት
#ቅድስት_ክርስጢና፦አባቷ ጣዖታትን የሚያመልክ ነው። እርሷም አባቷ እንደ አስተማራት ታጥናቸው ነበር። በአንዲት ዕለትም አስባ ተመራመረች በልቧም እግዚአብሔርን መፍራት አደረ ተነሥታም ፊቷን ወደ ምሥራቅ መልሳ ቆመች የምትጓዝበትንም የሕይወት መንገድ ይመራት ዘንድ ጸለየች መንፈስ ቅዱስም አንድነቱንና ሦስትነቱን ገለጠላት።
❤ አባቷም በመጣ ጊዜ "ልጄ እንዴት አለሽ" አላት "በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሕይወት አለሁ" አለችው። አባቷም ሰምቶ ደነገጠ "ልብሽን ምን ለወጠው" አላት እርሷም "ከሰማይ አምላክ ተማረኩ" አለችው። ከዚህም በኋላ አባቷ እያዘነ ሔደ። እርሷም ተነሥታ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንዲህ አላት "በርቺ ከሦስት መኳንንት ትሠቃዪ ዘንድ አለሽ" አዳኝ በሆነ በጌታችን ክርስቶስ መስቀልም አማተመች ሰማያዊ ኅብስትንም ሰጣት።
❤ ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጣዖታቱ ወደ አሉበት ቤት ገብታ ቀጠቀጠቻቸው። አባቷም አይቶ እጅግ ተቆጣ ልጁንም ይገርፏት ዘንድ አዘዘ ከሥጋዋም ስለ ደም ፈንታ ማር ወጣ። ሁለተኛም በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታችዋ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ እርሷን የነካት የለም ግን ከአረማውያን ብዙዎችን አቃጠለ።
❤ ዳግመኛም በታንኳ አድርገው ወደ ባሕር ይጥሏት ዘንድ አዘዘ በጸለየችንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክት ጋራ መጥቶ ራሱ አጠመቃት ቅዱስ ሚካኤልም በእሳት ጉጠት የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሥጋና ደም አቀበላት ከጣዖታት እድፍም አነጻት በዚያችም ሌሊት አባቷ ርባኖስ ሞተ ። ስሙ ድዮስ የሚባል ሌላ መኰንን መጣ ቅድስት ክርስጢናን አምጥተው ራቁቷን ሰቅለው ከበታችዋ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ። ሴቶችም ራቁትነቷን አይተው መኰንኑን ረገሙት እነርሱም በሰይፍ አስቆረጣቸው እርሷን ግን ምንም ምን አልነካትም ሕዝቡም ይህን ተአምር አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሠላሳ ሺህ ዐሥራ ሁለት ሰዎች አምነው በሰማዐትነት ሞቱ
ከሀዲው መኰንን ድዮስም በድንገት ሞተ።
❤ ሦስተኛም መኰንን መጣ የከበረች ክርስጢናንም ይዞ ለአማልክት ትሠዋ ዘንድ አባበለት እርሷም እንዲህ አለችው። "አንተና አማልክቶችህ ለዘላለም ወደማ ይጠፋ የገሀነም እሳት ትወርዳላችሁ"። እጅግም ተቆጥቶ ወደ እሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨምርዋት አዘዘ ምንም የነካት የለም። ዳግመኛም ለአራዊት ይጥሏት ዘንድ አዘዘ እነርሱም የእግርዋን ትቢያ ላሱ እባቦችንም የሚያጠምደውን ነከሱትና ወዲያውኑ ሞተ።
❤ ሁለተኛም ምላሷንና ጡቶቿን ቆረጡ የምላሷንም ቁራጭ አንሥታ ከመኰንኑ ዐይኖች ላይ ጣለችውና ዐይኖቹን አሳወረችው። ቁጣውንም ተመልቶ ለእባቦች እንዲጥሏት አዘዘ አንዲቷም እባብ ልቧን ነደፈቻት አንዲቱ ደግሞ ጐኗን እንዲህም የምስክርነቷን ተጋድሎ ፈጸመች ነፍሷንም አሳልፋ የድል አክሊልን ተቀዳጀች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ሰማዕት በቅድስት ክርስጢና በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_አባ_እንባ_መሪና፦ የዚችም ቅድስት የእናቷ ስም ማርያም ይባላል ሕፃንም ሁና ሳለች እናቷ ሞተች አባቷም አድጋ አካለ መጠን እስከምታደርስ መልካም ትምህርትን እያስተማረ አሳደጋት። አባቷም እሷን አጋብቶ እርሱ ወደ አንድ ገዳም ሒዶ ይመነኲስ ዘንድ ወደደ ። እርሷም አባቷን "ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ታጠፋለህን" አለችው። እርሱም "ስለ አንቺ እንዴት አደርጋለሁ ከገዳም ውስጥ ሴትን አይቀበሉምና" አላት እርሷም እንዲህ አለችው "አባቴ ሆይ የሴቶችን ልብስ ከላዬ አስወግደህ የወንዶችን ልብስ አልብሰኝና ከአንተ ጋራ ውሰደኝ"።
❤ የልቧንም ጽናት አይቶ የወንድ ልብስ አልብሶ ከእርሱ ጋር ወሰዳት የቀድሞ ስሟ መሪና ነበር እርሱ ግን ስሟን ለውጦ እንባመሪና ብሎ ጠራት ገንዘቡንም ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች በተነ ልጁንም በወንድ ስም እየጠራ ከእርሱ ጋራ ወስዳት ወደ አንድ የመነኰሳት ገዳምም ደርሰው በዚያ እየተጋደሉ ኖሩ።
❤ ከዚህም በኋላ አባቷ ታመመ ለሞትም በቀረበ ጊዜ አበ ምኔቱን ጠርቶ እርሷን ልጁን አደራ ሰጠው ስለ ገዳም አገልግሎት ከገዳም እንዳትወጣ ከዚያም በኋላ አረፈና ቀበሩት። የከበረች እንባመሪናም ከአባቷ ተለይታ ብቻዋን ቀረች በጾም በጸሎት በስግደት ከቀድሞዋ ዕጥፍ አድርጋ ተጋድሎ ጀመረች።
❤ ከዚህም በኋላ የገዳሙ መነኰሳት "ይህ ወጣት መነኰስ ከእኛ ጋራ ለገዳሙ አገልግሎት ለምን አይወጣም" ብለው ተቃወሟት እንዲህም አበምኔቱን በአሰጨነቁት ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ ሰደዳት። ለመነኰሳቱ ቀልብ የሚሆነውን የገዳሙን እህል የሚሰበስብ አንድ ሰው አለ መነኰሳቱም በሚወጡ ጊዜ ከእርሱ ዘንድ አድረው እህላቸውን ይጭናሉ የእንግዳ መቀበያ ቤትም አለው በዚያ ያድራሉ።
❤ በዚያችም ዕለት ከጐረቤቱ አንድ ጐልማሳ ሰው መጥቶ በዚህ ሰው ቤት አድሮ የልጅን ድንግልና አጠፋ። እንድህም አላት "አባትሽ ማን ደፈረሽ ብሎ የጠየቀሽ እንደሆነ አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኰሴ ደፈረኝ በይው"። በፀነሰችም ጊዜ አባቷ አወቀ "ማነው የደፈረሽ" ብሎ ጠየቃት እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት "አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኵሴ ደፈረኝ"።
❤ ያን ጊዜም ተነሥቶ ወደዚያ ገዳም ሒዶ መነኰሳቱን ይረግማቸው ጀመረ። አበምኔቱም ሰምቶ ወጣና "መነኰሳቱን ለምን ትረግማቸዋለህ እግዚአብሔርን አትፈራውምን" አለው እርሱም በልጁ ላይ የሆነውን ነገረው አንዲህም አለው "አባ እንባመሪና የሚሉት ወጣት መነኰሴ የልጄን ድንግልና ስለደፈረ ነው" አለው። አበ ምኔቱም በሰማ ጊዜ እውነት መሰለውና እጅግ አዘነ ሰውየውንም እንዲህ ብሎ ለመነው "በአንድ ሰው በደል ንጹሐን የሆኑ መነኰሳትን በሕዝባውያን ፊት አታዋርዳቸው ይህንንም ነገር ሠውር"።
❤ ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱን የምንኵስናን ልብስ ያለብሳቸው ዘንድ ለመኑት እነርሱ በቆቡ ላይ የብርሃን አክሊል አድርጎ መላእክትም ከበውት አንዱን መነኰስ አይተዋልና ሰለዚህም ፈጥነው ይመነኵሱ ዘንድ ተጉ።
❤ ከዚያም በማግስቱ አበ ምኔቱ የምንኲስናን ልብስ አለበሳቸው በቀን እንደሚተያዩ በሌሊትም እርስበርሳቸው የሚተያዩ እስቲሆኑ በፊታቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን በራ ሁለተኛም በዚህ መነኵስ ላይ እንዳዩ በራሶቻቸው ላይ የብርሃን አክሊል አዩ።
❤ ከዚህም በኋላ ከመነኰሳቱ መካከል ተለይተው ወደ በረሀ ይገቡ ዘንድ ኀሳብ መጣባቸው። በዚያችም ሌሊት ብርሃንን የለበሰ ሰው ለአበ ምኔቱ ተገልጾ "የክርስቶስ በጎች እንዲወጡ የገዳሙን በር ክፈት" አለው በነቃም ጊዜ ወደ በሩ ሒዶ ተከፍቶ አግኝቶት እያዘነና እየተከዘ ሳለ ሊወጡ ፈለገው እሊህ ቅዱሳን መጡ በፊታቸውም በትረ መንግስትን አየ። በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት ተገናኛቸው እነርሱም በልባቸው ያሰቡትን ነግረውት እንዲጸልይላቸው ለመኑት ለረጅም ጊዜም አለቀሰ ከዚህም በኋላ ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ በቀኙና በግራው አቆማቸው እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ጸሎት አድርጎ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠበቃቸው። ከዚያም በፍቅር አሰናበታቸው።
❤ ከዚህም በኋላ አርጋኖን ወደ ምባል ወንዝ ሔዱ በዚያም አንድ ገዳማዊ በዚያን ወራት ያረፈ በውስጡ የኖረበትን በዓት አገኙ በውስጡም ያ ሽማግሌ ገዳማዊ ሲመገበው የነበረ ለምግባቸው የሚያስፈልጋቸውን የእህል ፍሬዎችን አገኙ ምግባቸውን በአዘጋጀላቸው በእግዚአብሔርም እጅግ ደስ አላቸው።
❤ በድንግያ ውርወራ ርቀት መጠን አንዱ ከሁለተኛው የተራራቁ ሁነው ሰፊ በሆነ ተጋድሎ ቡዙ ዘመናት ኖሩ። ሰይጣንም ቡዙ ጊዜ ይፈታተናቸው ነበር ግን አባታቸው ቅዱስ ኒቅዮስ በራእይ ወደ እሳቸው መጥቶ ስለ እነርሱ ይጸልያል ተኝተውም ሳሉ የዳዊትን መዝሙር ያስተምራችዋል በነቁም ጊዜ ያስተማራቸውን ሁሉ በትክክል ያነቡታል እጅግም ደስ ይላቸዋል። አምላካዊ ራእይም ተሰጣቸው ተአምራትንም ያደርጋሉ በዚያችም በረሀ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ኃይል ሰይጣንን ድል እስከ አደረጉት ድረስ የቀኑን ሐሩር የሌሊቱን ቊር ታግሠው ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነሩ።
❤ ከዚህም በኋላ ስምዖን ወንድሙ ዮሐንስ እንዲህ አለው "በዚህ በረሀ በመኖራችን ምን እንጠቃማለን ና ወደ አለም ወጥተን ሌሎችን እንጥቀማቸው እናድናቸውም" ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለው "ወንድሜ ሆይ ይህ ኀሳብ ከሰይጣን ቅናት የተነሣ ይመስለኛል"። ስምዖን እንዲህ አለው "ከሰይጣን አይደለም በዓለም ላይ እንድዘብትበት እግዚአብሔር አዞኛልና ነገር ግን ና እንጸልይ" ያን ጊዜም በአንድነት ጸለዩ ልብሳቸውንም እስከ አራሱት ድረስ እርስበርሳቸው ተቃቅፈው አለቀሱ። ከዚህም በኋላ ስምዖን እስከሚሞትባት ቀን ሥራውን ይሠውርለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ጎዳናውን ተጓዘ።
❤ ወደ ዓለምም ገብቶ ራሱን እንደ እብድ አደረገ እብዶችንም የፈወሰበት ጊዜ አለ እሳትን በእጁ የሚጨብጥበትም ጊዜ አለ። ከዚህም በኋላ ከከተማው በር የሞተ ውሻ አግኝቶ በመታጠቂያውም አሥሮ እየጐተተ እንደሚጫወት ሆነ ሰዎች እስከሚሰድቡትና እስከሚጸፉት ድረስ።
❤ በአንዲት ቀን እሑድ ከቅዳሴ በፊት የኮክ ፍሬ ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ መቅረዞችንም ሰበረ።ሴቶችንም መትቶ ከእርሳቸው ጋራ እንደሚተኛ ጐተታቸው ባሎቻቸውም ደበደቡት።
❤ ዕረፍቱም ሲቀርብ የእግዚአብሔር መልአክ የእርሱንም የወንድሙ የዮሐንስንም የዕረፍታቸውን ጊዜ ነገረው ወደ ወይን ሐረግ ሥር ገብቶ ከወንድሙ ዮሐንስ ጋራ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ባስሊቆስ፦ በእሥር ቤትም እርሱ ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት እንዲህ አለው "የምስክርነትህ ፍጻሜ ደርሷልና ሒደህ ዘመዶችህን ተሰናበታቸው"።
❤ ከዚህም በኋላ ወታደሮችን ከእርሱ ጋራ ወደ ቤቱ ይሔዱ ዘንድ ለመናቸው ሒደውም ወደ ቤቱ ገቡ እናቱንና ዘመዶቹንም ተሰናበታቸው። በማግሥቱም የከበረ ባስሊቆስን ወደ ፍርድ ሸንጎ አቀረቡትና በሁለት ምሰሶዎች መካከልም አሥረው ሲደበድቡት ዋሉ በእግሮቹም ችንካሮችን አደረጉበት ደሙም በምድር ላይ ፈሰሰ ያየው ሁሉ አለቀሰለት።
❤ ከዚህም በኋላ ከደረቀ ዕንጨት ላይ አሠሩት ዕንጨቱም በቀለና ቅርንጫፍና ቅጠሎችን አወጣ። ሰዎችም የልብሱን ጫፍ ለመንካት የሚጋፉ ሆኑ በበሽተኞችና በዚህ ዕንጨት ላይ ያደረገውን ተአምር አይተዋልና።
❤ ከዚህም በኋላ ዋርሲኖስ ወደሚባል አገር በመርከብ ወሰዱት ወታደሮችም "እንዳትሞት እህልን ብላ" አሉት እርሱም "እኔ ከሰማያዊ መብል የጠገብኩ ነኝ ምድራዊ መብልን አልመርጥም" አላቸው። ወደ መኰንኑም በአቀረቡት ጊዜ "ለአማልክት መሥዋዕትን አቅርብ" አለው የከበረ በስሊቆስም "እኔ አንድ ለሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የምስጋና መሥዋዕትን አቀርባለሁ" አለው።
❤ ሁለተኛም ወደ ጣዖታቱ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ እርሱም ቁሞ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ያን ጊዜ እሳት ወርዶ ጣዖታቱን አቃጠላቸው መኰንኑም ፈርቶ ሸሽቶ ወደውጭ ወጣ። ቁጣንም ተመልቶ ይገድሉት ዘንድ ያ መኰንን አዘዘ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስሊቆስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መከራውን ይሳተፍ ዘንድ ስለ አደለውም አመሰገነው።
❤ ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ብዙዎችም መላእክት ነፍሱን ሲያሳርጓት አዩዋት ጌታችን ኢየሱስም "ወዳጄ ባስሊቆስ ወደ እኔ ና እኔ የምዋሽ አይደለሁም ተስፋ ያስደረግሁህን እፈጽምልሃለሁ" ብሎ ጠራው። እንዲህም ተጋድሎውን ፈጸመ። እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ባስሊቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ ምንጭ፦ የነሐሴ 14 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለተአምሪሁ_ክቡድ። እስከ አምኑ ቦቱ ጉባኤ አይሁድ። ሶበ በመስቀል ረገዞ ብእሴ ሙስና ወካህድ። ወሰላም ካዕበ ዘምስለ አምኃ ወሰጊድ፡፡ ኀበ አውኀዘ ደመ መስቀሉ ለወልድ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ14።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘአዘዝከ መድኃኒቶ ለያዕቆብ። ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ። ወበስምከ ናኀሥሮሙ ለዕለ ቆሙ ላዕሌነ"። መዝ 43፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 1፥10-19፣ ያዕ 1፥12-22ና እና የሐ ሥራ 10፥30-44። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥14-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ወይም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን #ለክብር_ባሌቤት_ለጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመስቀሉ በእስክድርያ ሀገር ድንቅ ተአምርን ለአደረገበት ስለርሱም ከአይሁድ ብዙዎች አምነው በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #በአባ ቴዎፍሎስ እጅ ለተጠመቁ መታሰቢያ በዓል፣ ለታላቁ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ባስሊቆስ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአባ_ስምዖንና ለወዳጁ #ለዮሐንስ_ለዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአርድእቱ ጋር በድንጋይ ከተወገረ ተአምራትንም ከሚያደርግ #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ድምጥያ_ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚህች ቀን የክብር ባለቤት#ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በእስክንድርያ ሀገር ድንቅ ተአምርን አደረገ። ስለርሱም ከአይሁድ ብዙዎች አምነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ቴዎፍሎስ እጅ ተጠመቁ እርሱም ለቅዱስ ቄርሎስ የእናቱ ወንድም ነው። ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ አገር ስሙ ፈለስኪኖስ የሚባል አይሁዳዊ ባለጸጋ ሰው ይኖር ነበር እርሱም እንደ አባቶቹ የኦሪትን ሕግ የሚጠብቅና እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው።
❤ ዳግመኛም ሙያተኛዎች ሁለት ድኃዎች ክርስቲያኖች አሉ በአንደኛውም ላይ ሰይጣን የስድብ መንፈስ አሳድሮበት ጓደኛውን "ወንድሜ ሆይ ክርስቶስን ለምን እናመልከዋለን እኛ ድኆች ነን ይህ ክርስቶስን የማያመልክ አይሁዳዊ ፈለስኪኖስ ግን እጅግ ባለጸጋ ነው" አለው። ጓደኛውም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ዕወቅ አስተውል የዚህ ዓለም ገንዘብ ከእግዚአብሔር የሆነ አይደለም ምንም አይጠቅምም ጥቅም ቢኖረው ጣዖትን ለሚያመልኩ ለአመንዝራዎች ለነፍሰ ገዳዮች ለዐመፀኞች ሁሉ ባልሰጣቸውም ነበር። አስተውል የከበሩ ነቢያት ድኆች ችግረኞችም እንደነበሩ ሐዋርያትም እንደርሳቸው ችግረኞች እንደነበሩ። ጌታችንም ድኆችን ወንድሞቼ ይላቸው እንደነበረ"። ሰይጣን ግን የጓደኛውን ምክር እንዲቀበል ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ለውጦ ነፍሱን እስከማጥፋት ድረስ አነሣሣው ቀሰቀሰው እንጂ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ፈለስኪኖስ ሒዶ "በአንተ ዘንድ እንዳገለግል ተቀበለኝ" አለው። ፈለስኪኖስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "በሃይማኖቴ የማታምን አንተ ልታገለግለኝ አይገባም ከቤተ ሰቦቼም ጋራ የማትተባበር ልቀበልህ አይገባኝም"። ሁለተኛም ይህ ጐስቋላ "ወዳንተ ተቀበለኝ እኔም ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ ያዘዝከኝንም ሁሉ አደርጋለሁ" አለው።
አይሁዳዊው ባለጸጋም ከመምህሬ ጋር እስከምማከር ጥቂት ታገሠኝ ብሎ ከዚያም ወደ መምህሩ ሒዶ ድኃው ክርስቲያናዊ ያለውን ሁሉ ነገረው መምህሩም "ክርስቶስን የሚክድ ከሆነ ግረዘውና ተቀበለው" አለው።
❤ አይሁዳዊውም ተመልሶ መምህሩ የነገረውን ለዚያ ድኃ ነገረው ያም ምስኪን "የምታዙኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ። ከዚህም በኋላ ወደ ምኵራባቸው ወሰደው የምኵራቡም አለቃ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ጠየቀው። "ንጉሥህ ክርስቶስን ክደህ አይሁዳዊ ትሆናለህን?" እርሱም "አዎን እክደዋለሁ" አለ። የምኵራቡም አለቃ መስቀል ሠርተው በላዩ የክርስቶስን ሥዕል እንዲአደርጉ መጻጻንም የተመላች ሰፍነግ በዘንግ ላይ አሥረው ከጦር ጋራ እንዲሰጡት አዘዘ ከዚያም ከተሰቀለው ላይ ምራቅህን ትፋ መጻጻውንም አቅርብለት "ክርስቶስ ሆይ ወጋሁህ እያልህ ውጋው" አሉት።
❤ ሁሉንም እንዳዘዙት አድርጎ በወጋው ጊዜ ብዙ ውኃና ደም ፈሰሰ ለረጂም ጊዜም በምድር እየፈሰሰ ነበር በዚያን ጊዜም ያ ከሀዲ ደርቆ እንደ ደንጊያ ሆነ። በአይሁድ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ወደቀባቸው "በእውነት የአብርሃም ፈጣሪ ስለእኛ ተሰቅሏል እኛም ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደሆነ አመንበት" እያሉ ጮኹ።
❤ ከዚህም በኋላ አለቃቸው ከዚያ ደም ወስዶ የአንድ ዕውር ዐይኖችን አስነካው ወዲያውኑ አየ ሁሉም አመኑ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ሒደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ ተነሣ አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋራ አለ። ወደ አይሁድ ምኵራብም ሒዶ ውኃና ደም ከእርሱ ሲፈስ መስቀሉን አገኘው ከዚያም ደም ወስዶ በግንባሩ ላይ ቀብቶ በረከትን ተቀበለ ሕዝቡንም ሁሉ ግንባራቸውን በመቀባት ባረካቸው። ያንንም መስቀል አክብረው ተሸክመው እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደው ያኖሩት ዘንድ አዘዘ። ደም የፈሰሰበትንም ምድር አፈሩን አስጠርጎ ለበረከትና ለበሽተኞች ፈውስ ሊሆን በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኖረው።
❤ ከዚህም በኋላ ፈለስኪኖስ ከቤተ ሰቦቹ ሁሉ ጋራ ሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስን ተከተለው ከአይሁድም ብዙዎቹ የቀደሙ አባቶቻቸው በሰቀሉት የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ከእርሱ ጋራ አንድ አደረጋቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ ለዘላለሙ ክብር ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደየቤታቸው ገቡ። እኛንም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን በመስቀሉ ኃይል ያድነን አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ስምዖንና_አባ_ዮሐንስ፦ እሊህ ቅዱሳንም በአማኒው ዮስጦንስ ዘመን መንግሥት የነበሩ ናቸው እሊህም ወንድሞች የከበሩ ክርስቲያን ናቸው።
❤ ከዚህ በኋላ ለከበረ መስቀል በዓል ቅዱሳት መካናትን ሊሳለሙ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ ሥራቸውንም አከናውነው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ ኢያሪኮ ቀረቡ። ዮሐንስም በዮርዳኖስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳም አይቶ ወንድሙ ስምፆንን "ወንድሜ ሆይ ለእሊህ ገዳማት እኮ የእግዚአብሔር መላእክት ይኖራሉ" አለው ዮሐንስም "ከእርሳቸው ጋራ ከሆን አወን ልናያቸው እንችላለን" አለው።
❤ ከዚያም ከፈረሶቻቸውን ወርደው ለሰዎቻቸው ሰጥተው "እስከምናገኛችሁ በየጥቂቱ ተጓዙ" ብለው እንደሚጸዳዱ መስለው ወደ ዱር ገቡ።
የዮርዳኖስንም ጐዳና ተጒዘው ከሰዎቻቸው በራቁ ጊዜ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ጸሎት እናድርግ ከእኛም አንዳንችን ወደ መነኰሳቱ ገዳም በምታደርስ ጐዳና ቁመን ዕጣ እንጣጣል እግዚአብሔር ከፈቀደ ዕጣችን ወደ ወጣበት እንሔዳለን"።
❤ ከዚህም በኋላ ስምፆን በዮርዳኖስ ጐዳና ቆመ ዮሐንስም ወደ ሀገራቸው በሚወስድ ጐዳና ላይ ቆመ ዕጣውንም በአወጡበት ጊዜ ዮርዳኖስ ጐዳና ላይ ወጣ እጅግም ደስ አላቸውና ስለ ደስታቸው ብዛት እርስ በእርሳቸው ተያይዘው ተሳሳሙ። አንዱም አንዱ ወደኋላ እንዳይመለስ ስለጓደኛው ይጠራጠርና ይፈራ ነበር አንዱም ሁለተኛውን ይመክረውና ለበጎ ሥራ ያተጋው ነበር። ዮሐንስ ስለ ስምፆን ይፈራ ነበር ስለ ወለላጆቹ ፍቅር አንዳይመለስ ስምፆንም ስለ ዮሐንስ ይፈራ ነበር እርሱ በዚያ ወራት መልከ መልካም የሆነች ሚስት አግብቶ ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ እንዲህም አሉ "በውስጧ እንመነኵስ ዘንድ ለኛ የተመረጠች ገዳም ደጃፍዋ ክፍት ሆኖ ብናገኝ ምለክት ይሆናል"። የገዳሙም አለቃ ኒቆን የሚሉት በተሩፋት ፍጽም የሆነ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርግ ሀብተ ትንቢት የተሰጠጠው ሲሆን በዚያች ሌሊት "በጎቼ ይገቡ ዘንድ የገዳሙን በር ክፈት" የሚለውን ራእይ አየ። ወደርሱም በደረሱ ጊዜ "የክርቶስ በጎች ሆይ መምጣታችሁ መልካም ነው" አላቸውና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተላኩ ሰዎች አድርጎ ተቀበላቸው።
ጨርሰው ሊሔዱ ሲሉ መቋሚያቸው ያስተምሩበት በነበረው ቦታ ላይ በተኣምር ተተክላ ሥር ሰዳ ተገኘች፤ እርሳቸውም ሊያንቀሳቅሷት ስላልቻሉ ተጨንቀው "አቤቱ ጌታ ሆይ! ምንድነው ያጠፋሁት?" ብለው እግዚአብሔርን በጸሎት ሲጠይቁት የታዘዘ መልአክ መጥቶ "…መቋሚያህ ለሀገሪቱ በረከት ትሆን ዘንድ ከዚሁ ትቀመጥ" አላቸው። መቋሚያዋም ለምልማ ቅጠል አውጥታ ትልቅ ዛፍ ሁና ከሥሯ ጠበል ፈልቆ ጠበሉ እስከአሁን ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል።
❤ የክብር ባለቤት ለአቡነ ቡሩከ አምላክ የገባላቸው ቃልኪዳን፡- "በእጅህ የባረክኸው በእግርህም የረገጥከው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በመንፈስ ለአንተና ለልጆችህ ያዘጋጀሁት ይሁንህ" አለው። ዳግመኛም "በገዳምህ ለሚያገለግለውና መታሰቢያህን ለሚያደርገው እምርልሃለሁ ብየ ቃል እንደገባሁልህ በራሴ ማልሁልህ፤ ለባሪያዬ ለኖኅ፣ ለወዳጄ አብርሃም፣ ለታማኜም ለዳዊት ቃል ኪዳን የገባሁ እኔ ነኝ፤ እኔ ሲኦልን በዕለተ ዓርብ እንደበዘበዝኳት ለአንተም የእሳት ፈረስ ሰጠሁህ፤ አንተም ዳግመኛ ሲኦልን ትበዘብዛታለህ፤ መባርቅታና ነጎድጓድ ይከተሉሃል፤ መላእክትም በየወገናቸው ይሸኙሃል፤ ስለገባሁልህ ቃል ኪዳን ሲኦልን ለመማረክ ከአንተ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ በሞት ከማረፍህ በፊት በሕይወት ሳለህ ሲኦልን ትበረብራት ዘንድ ፈቀድሁልህ፤ አንተ ከሲኦል የምታወጣቸው ነፍሳት በቊጥራቸው ከሰማይ ከዋክብትና ከምድር አሸዋ ይበዛሉ፤ እንደ ጻድቃንና እንደ ሰማዕት እንደ ሐዋርያትና እንደ ነቢያት ይኽን ሁሉ ፈጸምህ፤ ዳዊት "የድካምህን ዋጋ ተመገብ" እንዳለ። ይኽን ሁሉ የኦሪትና የነቢያትን የወንጌልንና የሐዋርያትን ሥራ የብሉይንና የሐዲስ ትእዛዛትን ፈጸምህ። እኔ የአምስት ገበያ የሚያህሉ ሰዎችን እንዳስተማርኩ አንተም እንዲሁ ስላስተማርህ ቃል ኪዳኔን ሰጠሁህ፤ ዐራቱ ወንዞች ገነትን እንደሚያጠጧት በአራቱ የምድር ማዕዘኖች ወንጌልን አስተማርህ፤ ያልተጠመቁትን ይድኑ ዘንድ ያጠመቅህ፤ ያላመኑትንም ያሳመንህ አንተ ቡሩከ አምላክ ነህ፤ የተጣሉትንም አስታረቅህ፤ በጾምና በጸሎትም አስደሰትከኝ፤ የሰማዕታቱን የጊዮርጊስን የፋሲለደስንና የገላውዴዎስን ተጋድሎ ትፈጽም ዘንድ ገድል ተዘጋጅቶልሃል፤ አንገትህ በሰይፍ ይቆረጣል፤ ጎንህም በጦር ይወጋል"።
❤ አባታችን የሀገረ ገዥ ልጅ ሆነው ሳለ እርሳቸው ግን ለሰማያዊ ንግሥና ራሳቸውን አጭተው ገና በሕፃንነት ዕድሜያቸው ወደ ሀገራችን በመምጣት በብዙ ተጋድሎ ቢኖሩም በዐፄ ዳዊት ዘመን የነበሩ ክፉዎች ወደ አቡነ ቡሩክ ገዳም ወደ ደብረ ኮል መጥተው ስለሃይማኖታቸው ጽናት በሰማዕትነት ገድለዋቸዋል። አቡነ ቡሩከ አምላክም ይህ እንደሚሆን አስቀድመው በራእይ ታይቷቸው ነበርና ገዳዮቻቸውን ተዘጋጅተው ይጠብቋቸው ነበር። የሰማዕትነት አክሊል እየታያቸው ከእርሳቸው ጋር የነበሩ መነኰሳትም "እኔ ነኝ የምቀድመው፣ እኔ ነኝ መጀመሪያ የምሞተው…" ብለው እየተሽቀዳደሙ ነሐሴ 14 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ።
❤ አባታችን በሰማዕትነት የሚያርፉበትን ዕለት አስቀድመው በመንፈስ ቅዱስ ያውቁት ስለነበር ለተከታዮቻቸው እንዲህ አሏቸው፡- "ከእንግዲህስ ከዚኽ ዓለም የምለይበት ኹለት ሳምንት ብቻ ቀረኝ። ከእናንተ መካከልም በሱባዔው ፍጻሜ ነሐሴ ዐሥራ ዐራት ቀን ሕይወቴን አታዩም፤ ሞቴን ግን ታያላችሁ። ያልኳችሁንም በልባችሁ አኑሩት። ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር አልኖርም። በእግዚአብሔር ፊት በደና እንገናኝ"። ይኽን ካላቸው በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ጸሎቱ ሥፍራ ሔደ። አቡነ ቡሩከ አምላክ ሲጸልይ በነበረበት ቦታ ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ! የሰማዕትነትህ ቀን ደረሰ" አለው። በዚያች ዕለትም እግዚአብሔርን የማይፈራው አንድ ሽፍታ መጥቶ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። አቡነ ቡሩከ አምላክን ገዳዮቹ ጐናቸውን ከወጓቸው ቦታ ላይ ንጹሕ ጠበል ፈልቆ አሁንም ድረስ በርካታ ሕሙማንን እየፈወሰ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል። መጠኑም በክረምት አይጨምርም በበጋም አይቀንስም፤ ይኽም እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ድረስ እንዲሁ እንደሚቆይ ገድላቸው ይናገራል።
❤ ጻድቁ በሕይወት ሣሉ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነጭ ፈረስ ሰጥቷቸው ስለነበር በሰማዕትነት ከማረፋቸውም በፊት "ስምህን የጠራ፣ ዝክርህን የዘከረ፣ ገድልህ የጻፈና ያጻፈ፣ በስምህ ለተራበ ያበላ፣ ለተጠማ ያጠጣ፣ ለታረዘ ያለበሰ፣ ለገዳምህ ምብዓ ዕጣን ሻማ ስንዴ ወይን የሚሰጥ፣ ቤተ ክርስቲያንህን በትጋት የሚያገለግል፣ የሚሳለም፣ በጠበልህ በእምነት የሚታጠብ፣ በሰጠሁህ በዚህ ነጭ ፈረስ በእሳት መካከል እኔ አሻግረዋለሁ" የሚል ድንቅ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል። አባታችን አዳም "አዳም ሆይ! መሬት ነበርክና ወደ መሬት ትመለሳለህ" እንደተባለ አቡነ ቡሩከ አምላክም 63 ዓመት በገዳማቸው በደብረ ኮል፣ 62 ዓመት በደብረ ማርያምና አስቀድመው በቤተሰባቸው ዘንድ በጠቅላላ በ125 ዓመታቸው ነሐሴ 14 ቀን 1415 ዓ.ም በክፉዎች ሰዎች እጅ በሰማዕትነት ዐርፈው ከዚህች መከራና ኃጢአት ከበዛባት ዓለም ወደማታልፈው መንግሥተ ሰማያት ተሸጋገሩ።
በተቀበሩበት ቦታ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸ ሲሆን ከመቃብራቸው ውስጥም ፈዋሽ ጠበል ፈልቆ ብዙ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል። ሕሙማንም ከጥንት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ከተለያዩ ዓለማት እየመጡ የጻድቁን መካነ መቃብር ተሳልመው ጠበሉን ጠጥተው እየተፈወሱ ይሔዳሉ።
❤ የአቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳም ከአስመራ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 73 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመንደፈራ ወደ እምኒ ሓይሊ-ዓዲ ሓውያ በሚባል ቦታ ልዩ ስሙ መራጉዝ በሚባል ቦታ ይገኛል። ገዳሙ "ሙራደ ቃል ደብረ ኮል አቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳም" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዱር የተሸፈነ በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው። በእግር አንድ ሰዓት ተኩል የሚፈጅ የእግር መንገድ አለው። ገዳሙን የመሠረቱት አቡነ ቡሩከ አምላክ ሲሆኑ እርሳቸውም ከታላቁ ጻድቅ ከአቡነ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም ተምረው በዚያም ሲያገለግሉ ከኖሩ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ መራጉዝ ሔደው ገዳማቸውን ገድመዋል። ገዳሙ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት የሚደረጉበት፣ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትንና መምህራንን ያፈራ፣ የበቁ ባሕታውያንም መናኸሪያ ነበር። ከአቡነ ቡሩከ አምላክ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን በገብረ ሥላሴ የተዘጋጀ መጽሐፍ ገጽ 125_134።
እንደ ቤተልሔም፣ እንደ ተሰቀልኩባት ቀራንዮ የከበረች ትሆናለች…" በማለት ጌታችን ስለ ገዳሙ ደብረ ኮል ነገረው።
❤ አቡነ ቡሩከ አምላክ የአቡነ አብሳዲ ልጅ ሆነው በደብረ ማርያም ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በኋላም ለዘለዓለም ማረፊያቸው ወደሆነችው ወደ መራጉዝ መጥተው ገዳማቸውን ደብረ ኮልን መሠረቱ። የአቡነ ቡሩከ አምላክ ትውልዱ ከያፌት ወገን ነው፤ ሀገሩ ከዘጠኙ ቅዱሳን ሀገር ከሮም ነው፤ ጥንተ ሙላዱም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ከሚከተሉ ከሮም ነገሥታት ወገን ነው፤ አባቱም የሮም ንጉሥ ነበረ፤ ዘውድ ደፍቶ ሃይማኖታቸው በቀና ሰዎች ላይ ነግሦ ነበረ። ተላላኪው አባ ጌርሎስም ያዘዘውን ኹሉ ይላላከው ነበረ። አቡነ ቡሩከ አምላክንም የቀናች ቅድስት ሥላሴን ማመንን በምትናገር በቀናች የተዋሕዶ ሃይማኖት ያጠመቀው አባ ጌርሎስ ነበረ። አቡነ አብሳዲ ጾሙንና ጸሎቱን፣ ትሕትናውን፣ መላላኩንና ክህነቱን ተመልክቶ "እንግዲህስ አዳምን ለማዳን ሰው የሆነ የጌታህን የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝና የእኔን ትዕዛዝ ፈጽመሃል" አለው። ዳግመኛም "በቅድስት ሥላሴ ስም በመንፈስ ቅዱስና በወንጌል ትምህርት ከአንተ የሚወለዱ ብዙ ሕፃናት እንዲሁም ብዙዎች በምንኵስና ቀንበር ከአንተ ይወለዳሉ። ስብከትህና ወንጌል ማስተማርህ በዓለሙ ሁሉ ይሰማል። የመንፈስ ልጅህ የልጅ ልጅህ ለዘላለም ይኖራል። ትንቢታቸውና ትምህርታቸው እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ አይጠፋም፤ እነርሱም እንዲሁ አይጠፉም። እኔ የአምላኬን ፈቃድ ፈጽሜአለሁና ዛሬም የእኔ ፈቃድ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንጂ። አንተም የፈጣሪህን ትእዛዝ ፈጽም። ይህ ነገር ከእኔ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነውና ስለተናገረኝ እንዲህ እልሃለሁ"። አቡነ ቡሩከ አምላክም ራሱን ዝቅ አድርጎና ከእግሩ በታች ሰግዶ "እሺ በጄ" አለው። አቡነ አብሳዲም ከእንባ ጋር ከምድር አንሥቶ ሳመው፤ "እግዚአብሔር ወደፈቀደልህ ሂድ፤ እኔን ያሳየኝ እሸኝህ ዘንድ ነው" አለው። አቡነ አብሳዲ ይኽንም ያየው በደብረ ማርያም አበ ምኔት ሆኖ ሳለ ነበረ።
❤ በንጉሥ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከኢትዮጵያ ተነሥቶ ወደ አርማንያ ሔደ። ዕዝራ ቅድስት ሀገርን በምታለቅስ ሴት አምሳል እንዳያት አባ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ሆኖ ሲጸልይ ሳለ አቡነ ቡሩከ አምላክ በኢትዮጵያ ሆኖ በጸሎት ሲተጋ ሲሰግድና የብርሃን ምሰሶ ከሚጸልይበት በኣት ተተክሎ ያይ ነበረ። እግሩ ከረገጠበት ቦታም ኤፍራጥስና ጤግሮስ ኤፌሶንና ግዮን ይመላለሱ ነበሩ። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም ይኽን ባየ ጊዜ "ወንጌል የሚያንሰው ይበልጠዋል እንዳለ ይኽም ሕፃን እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነትና እንደ አቤል መሥዋዕት ከእኔ ይበልጣል" አለ።
❤ ከዚኽም በኋላ ጻድቁ ወግረ ስኂን ተብሎ ከሚጠራው ከደብረ ማርያም በወረደ ጊዜ የዱር አራዊት ሁሉ ተቀበሉት። እነርሱም አንበሶችና ነብሮች፣ ዝሆኖችና ቀይ ቀበሮዎች፣ ሽኮኮዎች፣ አሳማዎች፣ አውራሪስ፣ ጦጦዎችና ዝንጀሮዎች ናቸው። ኹሉም በስምምነት "አባ ክቡር ሆይ! የት ትሔዳለህ?" እያሉ ሰገዱለት። እግዚአብሔር የአቡነ ቡሩከ አምላክን ሥራ ይገልጥ ዘንድ የሰውን ቋንቋ ገልጦላቸዋልና። አባታችን ወደ ደብረ ኮል ከገቡ በኋላ እያስተማሩ ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቊጥራቸው እጅግ ብዙ ሆነ። አባታቸው አቡነ አብሳዲም ጌታችን በቃሉ አዝዟቸው በደመና ተጭነው መጥተው ጎብኝተዋቸው ሹመትንም ሰጥተዋቸዋል። አባታችን ቡሩከ አምላክ ያመነኰሷቸውን ቊጥራቸው መቶ የሚሆኑ ሴቶች መነኮሳይያትን በአንድ ጸንተው እንዲኖሩ ካስተማሯቸው በኋላ ታላቋንና መጻሕፍትን የምታውቀውን ጸበለ ማርያም እመ ምኔት አድርው ሾሙላቸው።
❤ ጻድቁ ሃይማኖቱ በቀና በኢትዮጵያው ንጉሥ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ኹለት ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትን አምላክን በወለደች በክብርት እመቤታችን ስም ጋርፋ በምትባል ሀገር እንዲሁም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አነጹ፤ ነገር ግን የቅዱስ ሚካኤልን ሕንጻ ቤተ መቅደስ ኹለተኛው ሄሮድስ የተባለ ግራኝ አህመድ አቃጠላት። የእመቤታችን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግን ተሰወረችው። አባታችን ገዳማትን መጎብኘት በፈለገ ጊዜ ደመና ጠርቶ በደመና ተጭኖ ይሔድ ነበረ። ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደተወለደባት ወደ ቤተልሔም ይሔድ ነበረ፤ መጋቢት ሃያ ሰባት ቀንም ጌታ ወደ ተሰቀለበትና ወደ ተቀበረበት ወደ ጎልጎታ፤ ወደ እናቱ መቃብር ወደ ጌቴሴማኒ እንዲሁም ጌታችን ከእናቱ ጋር ወደ አደረባት ወደ ደብረ ቊስቋም በደመና ተጭኖ ይሔድ ነበረ። ይኽንንም ሲያደርግ ከፈጣሪው በቀር ሰው አያውቅበትም ነበረ። ለመነኰሳትም ቤቱ ውስጥ ጸሎት የሚያደርግ ይመስላቸው ነበረ። ከትሕትናውም የተነሣ በቤተ ክርስቲያን በአገልግሎት ጊዜ "መጻሕፍትን አንብብ" በሚሉት ጊዜ "አላነብም አትሮንስ አቀርባለሁ፣ ጥላና መጽሐፍን እይዛለሁ እንጂ" ይላቸው ነበረ። "ዋና ሠራኢ ካህን ሆነህ ቀድስ" በሚሉት ጊዜ "አልችልም" ይል ነበረ። አንድ ቀን ሠራዒ ሆኖ የሚቀድስ ሰው ጠፋ። እነርሱም "እባክህ ዛሬ በሠራዒ ቀድስ" አሉት፤ እርሱም "እሺ በጄ" ብሎ በቀደሰ ጊዜ ከመሬት በአንድ ክንድ ከፍ አለ። ቊጥር የሌላቸው መላእክትም መቅደሷን ከበቧት። "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ባለ ጊዜ እና "ሀበነ ንኅበር" ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል በአቡነ ቡሩከ አምላክ ላይ ረበበ። ቀሳውስቱም ይኽንን ተመልተው ገረማቸው፤ "በእውነት ይኽ መነኵሴ ከእኛ ይበልጣል" አሉ። እንዲሁም የካቲት ዐሥራ ስድስት ቀን አባታችን ሠራዒ ሆኖ በቅዳሴ ማርያም ላይ "አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም" ባለ ጊዜ አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ወረደች። እንዲሁ ግንቦት አንድ ቀን "ኦ ማርያም በእንተ ዝ ነዐብየኪ ወናፈቅረኪ" ባለ ጊዜ ቃል በቃል አነጋገረችው፤ "ወዳጄና የልጄ ወዳጅ ቡሩከ አምላክ ሆይ! የአዳምና የሔዋን ብቻ አለኝታ አይደለሁም፣ ለእናትህና ለአባትህ በልጄ ዘንድ አለኝታቸው እኔ ነኝ፤ አንተንም ያገኙህ በእኔ በኩል ነው" አለችው። ዳግመኛም "በጸጋ በጸጋ ሰጠሁህ፤ በሚያምረው ዜማህ ተደስቻለሁና። መኖሪያህንም ከሶርያው ኤፍሬምና ከብህንሳው ከአባ ሕርያቆስ ጋር አደርጋለሁ። አስቀድሜ ከአንተ አልተለየሁም፣ ከእንግዲህም ወዲያ ከአንተ አልለይም" አለችው። እመቤታችን ይኽን ብላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገች።
❤ አቡነ ቡሩከ አምላክ በዚህ ገዳም በብሕትውና ተጋድሎ ለ63 ዓመታት ኖረዋል። ጻድቁ በገዳመ ደብረ ኮል ያደረጓቸው ታላላቅ ተኣምራት ተቆጥረው የሚያልቁ አይደሉም። እግዚአብሔር በሰጣቸው ጸጋ እንደ ሙሴ ከዐለት ላይ ያፈለቁት ጠበል ብዙ በደዌ የተያያዙ ምእመናንን እየፈወሰ ይገኛል። ለአቡነ ቡሩከ አምላክ አባታቸው አቡነ አብሳዲ የሰጧቸው ኹለት መቆሚያዎች ነበሯቸው። አንደኛዋ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደገፉባት ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ ለአገልግሎት በየቦታው ሲዘዋወሩ ሕሙማንን የሚፈውሱባት ናት።
ከዕለታት በአንደኛው ቀን ወደ ሀገረ እምብርት (ዓዲ ሕምብርቲ) ሔደው ሕዝቡን ወንጌል አስተምረው
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ልክ #እንደ_እመቤታች ገና #በእናታቸው_ማኅጸን_ሳሉም_ድዉይ_ይፈውሱ ለነበሩት፣ እንደ ዘጠኙ ቅዱሳን ከሮም ወደ አገራችን ኢትዮጵያዊ በመምጣት ኤርትራ አገር የሚገኘውን ታላቁ ገዳም #ሙራደ_ቃል_ደብረ_ኮል ለመሠረቱት ለታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ቡሩክ_አምላክ_ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ቡሩከ_አምላክ፦ ከሴም ወገን ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው ሮም ነው። አባታቸው ቴዎቅሪጦስ እናታቸው ሚሊዳማ የሚባሉ ከነገሥታት ወገን ሲሆኑ ኹለቱም እንደ አብርሃምና ሣራ በቃል ኪዳን የጸኑ ነበሩ። እነርሱም ብዙ ሀብትና ንብረት ቢኖራቸውም ልጅ ስለሌላቸው ሁልጊዜ እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ይለምኑ ነበር። ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ሚሊዳማ በመላክ እንዲያበሥራት አዘዘው። ሚሊዳማ ዕድሜዋ እንደ ሣራ ገፍቶ ስለነበር ብሥራቱን ስትሰማ መልአኩን "…በዚኽ ዕድሜዬ እንዴት ይሆንልኛል?" አለችው። ቅዱስ ሚካኤልም "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" አላት፤ እርሷም እመቤታችንን አብነት አድርጋ "…እሺ እንደ ፍቃዱ ይሁንልኝ" አለች።
❤ አባታችን አቡነ ቡሩክም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በዕለተ ጽንሰቷ ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሰው በዕለተ ልደቷም ግንቦት 1 ቀን 1290 ዓ.ም ተወለዱ። ጻድቁ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉም ድዉይ እንደፈወሱ በገድላቸው ላይ ተጽፏል። ከእናቷ ማሕፀን ጀምሯ የታመመች አንዲት ሴት ነበረች። አቡነ ቡሩከ አምላክ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የሮሙ ንጉሥ አባታቸውና ንግሥቲቱ እናታቸው ግብዣ አድርገው ሳለ ከተወለደች ጀምሮ እስከ ሠላሳ አምስት ዓመቷ ድዉይ የነበረችው ያቺ የታመመች ሴት ወደ ግብዣው መጥታ ሳለ የአቡነ ቡሩከ አምላክ እናት የሚሊዳማ ጥላዋ ቢያርፍባት ከነበረባት ሕመም ፈጥና ዳነች።
❤ አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም በእናቷ በቅድስት ሐና ማሕፀን ሳለች ብዙ ሕሙማንን እንደፈወሰች ኹሉ አቡነ ቡሩከ አምላክም እንዲሁ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ድዉይ ፈወሱ። ሴቲቱም ፈጽማ ድና እግዚአብሔርን እያመሰገነች በእግሮቿ ቀጥ ብላ ቆማ ወደ ሀገሯ ሔደች። ባልም አግብታ ልጆችን የወለደች ሲሆን ልጆቿ በኋላ የአቡነ ቡሩከ አምላክ ተከታዮችና አገልጋዮች ሆነዋል። አቡነ ቡሩከ አምላክ ገና በተወለዱ በ5ኛ ቀናቸው "አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። ዳግመኛም "ለድንግል ማርያም ምስጋና፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይሁን" እያሉ ከእናታቸው ማሕፀን ጀምሮ የጠበቃቸውን አምላካቸውን አመሰገኑ። በ40ኛ ቀናቸውም ሥርዓተ ጥምቀት ሲፈጸምላቸው እስከመጨረሻ ድረስ "…አሜን ይሁን" እያሉ ይቀበሉ ነበር። ስመ ጥምቀታቸውም ዓምደ ሚካኤል ይባላል። ከጥምቀታቸውም በኋላ ዘወትር ረቡዕና ዐርብ የእናታቸውን ጡት አይጠቡም ነበር፣ ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ምስጋና ከአፋቸው አይለይም ነበር። ሦስት ዓመት ሲሆናቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማሩ ወላጆቻቸው ለመምህር ቢሰጧቸውም እርሳቸው ግን እግዚአብሔር የመጻሕፍትን ምሥጢር ስለገለጠላቸው ቅዱሳን መጻሕፍትን በፍጥነት አጥንተው ዐወቁ።
❤ አባታችን ከልጅነታቸው ጀምረው ምግባቸውንና ልብሳቸውን ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር፤ እርሳቸው ግን ከመምህራቸው ሳይለዩ በጾም በጸሎት ተግተው ይኖሩ ነበር። ከዚኽም በኋላ ዕድሜያቸው እንደደረሰ ወላጆቻቸው ሚስት እንዲያገቡ ወሰኑላቸው ነገር ግን አባታችን ከዚኽ ሀሳብ ይድኑ ዘንድ በጸሎት እንዲያግዟቸው ለመምህራቸው በመንገር እርሳቸውም በጸሎት ተግተው እየጸለዩ ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ከዚያ ሀገር ተነሥተው ወደ ምድረ አግዓዚ እነ አቡነ አብሳዲና እነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ እንዲሔዱ ነገራቸው። በዚያም የብዙዎች አባት እንደሚሆኑና በእርሳቸው አማካኝነት ብዙዎች እንደሚድኑ ነገራቸው። አቡነ ቡሩክም ማንም ሳያያቸው በመንፈቀ ሌሊት ተነሥተው በመልአኩ መሪነት ቀድሞ ወደነገራቸው ቦታ ወደ ደብረ ማርያም መጡ።
❤ አቡነ ቡሩከ አምላክን እግዚአብሔር እንደነ ነቢዩ ኤርምያስ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ስለመረጣቸው በ7 ዓመታቸው ዲቁና ከተቀበሉ ከ5 ዓመት በኋላ መመንኰስ እንደሚፈልጉ ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ነገሯቸው። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም "ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘህ ምንኵስና የምሰጥህ እኔ አይደለሁም፣ ወደ ልጄ አብሳዲ ሒድ" ብለዋቸው ወደ ዓረዛ ቆላ ሰራየ ሔዱ። በዚያም በ12 ዓመታቸው በአቡነ አብሳዲ እጅ መነኰሱ፤ ስማቸውንም ብሩከ አምላክ አሏቸው። አቡነ ቡሩከ አምላክ ከመነኰሱ በኋላ የክብር ባለቤታችን ጌታችን "እኔን ሊያገለግለኝ የሚወድድ ሰው ቢኖር ነፍሱን ይጥላት፣ ጨክኖ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ፣ ነፍሱን ሊያድናት የሚወድድ ሁሉ ይጣላት፤ ነፍሱን ስለ እኔ ብሎ የጣላት ያገኛታል"፤ ዳግመኛም "ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? ለነፍሱ ቤዛስ ምን ይሰጣል?" በማለት የተናገረውን አስበው የምኵስናን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ገባ የተባለ እሾህ አምጥተው ወንድማቸውን "እኔ መንኵሴ ልባል የማይገባኝ ኃጢአተኛ ነኝና የኃጢአት ማስተሠረያ ይሆነኝ ዘንድ በዚኽ ግረፈኝ" አሉት። በእሾሁም በተገረፉ ጊዜ ደማቸው እንደ ውኃ ፈሰሰ።
❤ አቡነ ቡሩከ አምላክ የተገረፈባት ሀገር እስከዛሬ ድረስ ዓዲ-ጋርፋ እየተባለች ትጠራለች። ትርጕሙም የመገረፍ ሀገር ማለት ነው። ምልክቷም ብዙ መነኰሳይያት ይኖሩባታል። ይኽም ገባ በሚባል እሾህ የተገረፈባት ማለት ነው። በሌላም ጊዜ ቆዳው እስኪሰነጣጠቅና ቊስል እስኪሆን ድረስ በሸንበቆ የሚገረፍበት ጊዜ ነበረ፣ ከዚኽም በተጨማሪ መላ አካሉ ቈስሎ ሳለ በላዩ ላይ ግርፋቶችን ይጨምርበታል። በዚኽ ዓለም በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ በብረት ችንካሮች እጆቹንና እግሮቹን እንደተቸነከረ የጌታችንን ሕማማቱን እያሰበ ሥጋውን አያሳርፋትም ነበረ። ከታናሽነቱ ጀምሮ የንጉሥ ልጅ ሲሆን ምድራዊ መንግሥትን ትቶ እግዚአብሔርን አገለገለ። ጌታችን በወንጌሉ "ማንም ቢሆን ስለ ስሜ ብሎ ርስትንና ልጆችን፣ ወንድሞችንና እኅቶችን፣ እናትንና አባትን ያልተወ መንግሥተ ሰማያትን ሊወርስ አይችልም" ብሎ የተናገረውን አስቦ ከታናሽነቱ ጀምሮ ጌታውን አገለገለ። ❤ ከዕለታትም በአንዲቱ እህልና ውኃ ወደማይገኝበት ምድረ በዳ ሔደ። ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ሥጋውን በረኃብና በውኃ ጥም ቀጣ፤ ከሰንበቶች በስተቀር ምንም አልቀመሰም። እንደ መላእክት ንጹሕ፣ ለጸሎት ትጉ፣ እውነተኛ መነኵሴ፣ ችግርን ወዳጅ፣ መንግሥትን መናኝና መስቀል ተሸካሚ የሆነ አቡነ ቡሩከ አምላክ ከዚኽ ዓለም አንዳች ነገርን የራሱ አላደረግም።
❤ ጻድቁ የዲቁናና የቅስና ማዕረግ የተቀበሉት ወደ ሸዋ ምድር በመምጣት ነው፤ በዘመኑም የነበረው የኢትዮጵያ ንጉሥ ዐፄ ዳዊት ነበረ። አቡነ ቡሩከ አምላክ በመንፈቀ ሌሊት ቆሞ እየጸለየ ሳለ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ተገልጦለት "የኤፍራጥስና የጤግሮስ፣ የኤፌሶንና የግዮን አምሳል ደጋግ መነኰሳት የሚኖሩባት፣ ከጎንህ ውኃ የሚፈስባት የምትኖርባትና በሞት ዐርፈህ የምትቀበርባት ቦታ ደብረ ኮል ናት፣ አጋንንት ከእርሷ ይርቃሉ፤ በእርሷ ዘንድ በጸሎት ውኃዋ ሕሙማን ይፈወሳሉ፣ መላእክትም በውስጧ ይወርዳሉ ይወጣሉ፣ ገዳምህ ደብረ ኮል እንደ ተወለድኩባት
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችን_ልክ_በደብረ_ታቦር ለእነ #ቅዱስ_ጴጥሮስ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠላቸው ሁሉ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለአባታችን #ለአቡነ_ሊቃኖስም እንዲሁ በበዓታቸው #በደብረ_ቆናጽል_ገዳም ሳሉ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ ለአሳያቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በሀገራችን በሚገኘው በደብረ ቆናጽል ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል። የተገለጠውም እንደነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፋንታ የለተሰወሩት ለአቡነ ሊቃኖስ ነው።
❤ አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ "ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ" በማለት ይገልጸዋል፡፡ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡
❤ የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡
❤ ጌታችን ነሐሴ 13 ቀን ልክ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በዚህ በፎቶው ላይ በሚታየው በአቡነ ሊቃኖስ ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል።
❤ አቡነ ሊቃኖስ በደረቅ ጭንጫ ላይ ውሃ በተአምራት አፍልቀው ለቅዳሴ ማይ ጸሎት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ አቡነ ሊቃኖስም እንደ መሴ ከጭንጫ ላይ ያፈለቁትን ውሃ በወንፊት አድርገው ለአቡነ ገሪማና ለአቡነ ጰንጠሌዎን ይልኩላቸዋል፡፡ ከዳግማዊው ሙሴ ከአቡነ ሊቃኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ። ወይሴብሑ ለስምከ። መዝራዕትከ ምስለ ኃይል"። መዝ 88፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥23-30፣ 2 ጴጥ 1፥15-ፍ.ም እና የሐ ሥራ 7፥44-54። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥28-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላችን_ለመድኃኒታች #ለኢየሱስ_ለክርስቶስ_ከዘጠኙ_ዐበይት በዐል ለአንዱ ለሆነው #በደብረ_ታቦር_ተራራ ላይ ለቅዱስሙሴ ለቅዱስ ኤልያስ ለሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ለቅዱስ ያዕቆብና ለለቅድስጨዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዐልና እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና ቀጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ነቢያት_ከቅዱስ_ሙሴ ከልደቱ፣ #ከብንያምም ከመታሰቢያው፣ ከተጋዳይ #ከአባ_ጋልዮን ከዕረፍቱና በሰማዕትነት ከዐረፈች #ከቅድስት_ኦፍራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና #የጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ታላቅና_ክቡር_በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን #ቅዱሳን_ጴጥሮስ_ያዕቆብንና_ዮሐንስን_ይዞ_ወደ_ታቦር_ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
❤ ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
❤ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት።
❤ ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና።
❤ እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነነቱ የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"።
❤ ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
❤ ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ያስነሳቸው ማንም አይችልም።
❤ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
❤ የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ።
❤ ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
❤ እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት። ሰው ካልሆ በበረት እንዴት አስተኙት አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
❤ ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ።
❤ ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ተጋዳይ_አባ_ጋልዮስ፦ ይህም በቀንና በሌሊት ጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጎልማሳ ሆኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጪ አልወጣም ከማህበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።
❤ ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት "እኛ ተሰውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋር ልንወስድህ ወደን ወደ አንተ መጣን" ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደ ማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሯቸው ሔደ።
❤ ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጡለት እነርሱም የዳዊት መዝሙር ያገቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁቱ በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእነርሳቸው ጋር ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእርሳቸው ጋር አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።
❤ ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው "ወዴት ነበርክ" አለው እርሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ ነሐሴ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጋልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የነሐሴ 13 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ጸርሐ_አብ_ኪያከ_በውዳሴ። ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዳሴ። አመ ገበርከ በታቦር እግዚኦ ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። ኤልያስ መንገለ ቆመ ወኀበ ሀለወ ሙሴ። ዘመለኮትከ ወልደ ከሠትከ ሥላሴ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_13።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል። ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉአን። ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ። መዝ 67፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥1-14።
