en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
603
Subscribers
-324 hours
-87 days
-1730 days
Posts Archive
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ከቅዱ ዮሐንስ ጋር ጌታችን እንደአዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገሪቱንም ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም አግኝቶ ክፉ ነገርን ተናገሩት። ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስንም አለው "አባቴ ሆይ የእሊህ ጎስቋሎች ክፍታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በጌታችን ስም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆ ይሆን እንዴትስ ሃይማኖትን እናስተምራለን"። ቅዱስ ጴጥሮስም "ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘን" አለው። ✝ ከዚህም በኋላ ወደ ከተማ መካከል ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማውም ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮችም በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸው አጎሳቋሏቸውም ግማሽ የእራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አሥረውም በግንብ ውስጥ ጣሏቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ወደያውን ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፊል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው "የመረጥኳችሁ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተ ጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም"። ለመዘባባቻም በራሷችሁ መኳካከል ስለላጩአችሁ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብርን የክህነት ሥርአትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዝህ ምክንያት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አልችልም። ይህ መልእክት እያለው የሚሞት ካህምን ኃጢያቱም ይሰረይለታል" ይህን ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን ተገናኘው "የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድን ነው" አለው እርሱም "ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትን አለቃ በእኔ ላይ ባደረጉት አምሳል አድርገውበታልና" አለው። ቅዱስ ጳውሎስ አጽናናቸው እንዲህ አላቸው "እኔ በጌታችን ፍቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባቸዋለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖታቸውንም እንደሚያመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲያቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲይቃቸው የከተማውን መኳንን አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲያቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ስለሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም "ድንቆችንና ተአምራቶችን የሚያደርግ ለክርስቶስ ወደ መዛሙርቶቹ እንደሆኑ ነገሩት። ዳግመኛም "እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁ" አለቸው እነርሱም "አዋ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ ከእናቱ ማኅፀን እውር ሁኖ የተወለደውን አይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውን ከተባላሸ በኋላ ከመቃብር አሥነሱት። ንጉሡና የከተማ ሠዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውሃን አፈለቀ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው። ❤ ከዚህም በኋላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ቡዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዎቻቸውና ከከቡቶቻቸው እንዳሰጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ቅዱስ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ ዮሐንስም ወደ እነርሱም ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው "ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒደ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመልሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሰርክ ነህ ብሎሀል በለው"። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንደአዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ቡዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር አውርዶ ጥሎ አጠፍው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዢ የአክሮጶስ ቊባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ቡዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው እርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ። ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስ ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሆድ ወደ ቅዱ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማ ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና "አቤቱ ጌታዬ ወዲት ትሆዳለህ" አለው ጌታዬም "ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እህሔዳለሁ" ብሎ መለሰለት። ቅዱስ ጴጥሮስ "አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን?" አለው። ❤ ያን ጊዜም "ጎልማሳ ሳለህ ወገብህ በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሳና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደ ማትወደው ይወስድሃል" ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅ አዘኑ። ❤ ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉት በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው "የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ላይ ሁኖ ስለተሰቀለ እኔ ቊልቊል ልሰቀል ይገባኛል"። ወዲያውንም እንደነገራቸውም ሰቀሉት። ተሰቅሎም ሳለ ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ሐምሌ 5 ቀን ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታች በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘለላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፦ ይህም ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራ ይኸውም ልሳነ ዕረፍት፣ የክርስቶስ አንደበት፤ የዕውቀት አዘቅት፤ የቤተ ክርስቲያን መብራት፤ እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው። ❤ ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበር፤ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሳሪሳዊ ልጅ ነው። ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ማለት ነው። ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበር። ❤ እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ። ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አሳዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ መንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኵራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ። ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም "ሳውል ሳውል ለምን" ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ። ❤ ሳውልም "አቤቱ አንተ ማነህ" አለው "አንተ የምሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል" አለው። እየተንቀጠቀጠም አደነቀ "አቤቱ ምን እንዳደርግ ትሻለህ" አለው ጌታም "ተነሥና ወደ ከተማ ግባ ልታደርግ የሚገባህን ከዚያ ይነግሩሃል" አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤               ❤ #ሐምሌ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን #ለብርሃናተ_ዓለም_ለቅዱስ_ጴጥሮስ፣ #ቅዱስ_ጳውሎስ_በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ ሰማትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሳቁኤል_ለበዓሉ መታሰቢያ፣ #ለሰባ_ሁለቱ_አርድእት_ለመታሰቢያቸው_በዓላቸው፣ #ለአባታችን_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ #ከይስሐቅና_ከደብረ_ዓሣ_ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የሐዋርያት_አለቃ_ቅዱስ_ጴጥሮስ፦ ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ የነበረ ዓሣ አጥማጅም ነበረ ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግስት አግኝቶ መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው። መድኀኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲያገለግለው ኖሩ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ❤ ጌታችን ም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች "ኤርምያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለ። ጌታችንም "የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ" ብሎ ብፅዕና ሰጠው "የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ" አለው። ❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተበቀለ በኋላ ተናገሪዎች ከሆኑ በዚህ ዓለም ተኲላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው። ጌታችንም የማይቈጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸው ሦስት መልእክቶችንም ጽፎ ለምእመናን ላከቸው። ለማርቆስም ወንጌሉን ተርጒሞ አጽፎታል። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና" የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገረ። በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የደንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ "አሜን" አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ። ከሰባ ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያደረበት አንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ። መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ። ❤ ከከተማ መኳንንቶችም ቀውስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ የምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኆችም ስመራራትና የመሳሰለውን ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት እንዳስተማረ ነገራት። እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቃታ "ይህ ገገር መልካምና ድንቅ ነው" አለች። ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በኋላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም። ❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ሥራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህ በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም። ምክንያትም አመካኝቶ ይሰወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ። እርሷ ግን "ምክንያት አታድር ነገር ግን ወደ ንጉሥ ሒድ የቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን ጎዳናህን ያቅናልህ" አለች። እርሱም ነገሯን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሡም ደረሰ ንጉም በደስታና በክብር ተቀበለው። ❤ ከሦስት ዓመት በኋላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለቱ ልጆቹ የተመረዘ ውሃ ጠጥተው እነሆ ሞተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለችለት በኋላ ነገረችው። በሰማ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናል የቅዱስ ጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው"። ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀወስጦስና አክሮስያ "የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሱ ቀውስጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ እሊህም ከሞት የተነሱ ልጆች ለቅዱስ ጴጥሮስ ቀደ መዝሙሮቹ ሆኑ የአንዱ ስሙ ቀሌምንጦስ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥሮስ ያየውንና ጌታች በሥጋ ወደ ሰማይ በሚያርግ ጊዜ የገለጠለትን ምስጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምጦስን ሊቀ ከጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብራን በምሳሌ አየ። በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላዪዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳን ውስጥም አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸው ውስጥ የነበልባል ጦሮችና ሰይፈችን ያያዙ መላክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበር። እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር። "ከእርሷ የደኅንነት ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ ማኅፀንስሽም የእግዚአብሔር በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ"። ❤ ሁለተኛም እንዲህ ይሏት ነበር " የብርሃን እናቱ ሆይ የምሕረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረት ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ"። መላእክት ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናገወች ሊነገር የማይቻል ምሥጢራትንም ገለጠላት። ❤ ከዚህም በኋላ መድኀኒታችን ለአገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ቅዱስ ጴሮስን አዘዘው ቅዱስ ጴጥሮስም መጥቶ ሔደ ኢዮጴም ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጴ ሳለ ብርሕት ደመና ዞረችው። እነሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድረ በዳ አውሬዎችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር። "ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ" የሚል ቃልም ከሰማይ ጠራው። ቅዱስ ጴጥሮስም "አቤቱ አይገባኝም እርኲስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም" አለ። ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገው አንተ ርኲስ ነው አትበል" አለው ያም ቃል ሦስት ጊዜ መላልሶ እንዲህ ነገረው። በየንግግሩም ወደ እሪያዎች፣ ወደ አራዊትና ወደ አእዎፍ ሥዕሎች ጣት ያመለክተው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ አደነቀ ይህም ራእይ ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ። ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃል እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው።

ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህም እንዲህ ነው እሊህ ቅዱሳን የካቲት ስድስት ቀን ሰማዕታት ሆነው በሞቱ ጊዜ ምእመናን ሥጋቸውን ተሸክመው ወስደው በእስክንድርያ ከተማ በስተሰሜን ባለች በቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥውር አኖሩዋቸው እስከ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ዘመንም በዚያ ኖሩ። ❖ የእግዚአብሔር መልአክም ለቅዱስ ቄርሎስ ተገለጸለት ወደ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ሔዶ የቅዱሳን የአቡቂርንና የዮሐንስን ሥጋቸውን አውጥቶ እንዲሸከም አዘዘው፤ እርሱም ተነሥቶ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ሕዝቦች ነበሩ በደረሱም ጊዜ ጸለዩ ምድሩንም ሲቆፍሩ ሥጋቸው በውስጡ ያለበት ቦታ ተገለጠላቸው በባሕር ዳርቻ ወደ አለች ወደ ሌላዪቱም የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ተሸክመው አድርሰው በዚያ አኖሩ። ❖ በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው በዚችም ቀን ታላቅ በዓል አደረጉ ከሥጋዎቻቸውም ድንቆች ተአምራት ተገለጡ አረማውያንም ተሰበሰቡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ትተው ክርስቲያኖች ሆኑ፤ በዚያቺም የጣዖቶች ቤት አሸዋ በላይዋ ተከመረባት ታላቅ ኮረብታም ሆነ፤ የቅዱሳንም ሥጋቸው ታምራትንና ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስን ያደርጋል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ዕብል ለዮሐንስ ወለአቡቂር። እለ ነበሩ ኅቡአ በእስክንድርያ ሀገር። ከመ አስተርአዮ መልአክ ለቄርሎስ ማር። አፍለሶሙ ዮም በዕበይ ወክብር። ኀበ ቤተ ክርስቲያን ዘሀሎ በጽንፋ ለባሕር። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ቀን ደግሞ የአማርያ ልጅ፣ የሴዴቅያስ ልጅ፣ የጎዶልያ ልጅ፣ የኩሲ ልጅ የሶፎንያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፤ እርሱም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ተናገረ፤ እንዲህም አለ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ፈጽመው ይጠፋሉ አለ ከብቶችና ሰዎች ያልቃሉ፤ የባሕር ዓሣዎችና በሰማይ የሚበሩ አዕዋፍም ያልቃሉ። ❖ ዳግመኛም ስለሞአብ እንዲህ አለ ስለዚህ ሞአብ እንደ ሰዶም ትሆናለች የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ልጆች ይሆናሉ ደማስቆም እንደ እህል ታልቃለች፤ እርሱ እንደ ተነበየው እነዚያ አገሮች በናቡከደነጾር ምርኮ ይጠፋሉና። ❖ ዳግመኛም ስለ ፋርስና ስለ ነነዌ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ የፋርስን ሰዎች አጠፋቸዋለሁ ነነዌንም ፍርስራሽና ውኃ እንደሌለባት ምድረ በዳ አድርጋታለሁ መንጋዎችም በመካከሏ ይሠማሩባታል፤ ይህቺም ከተማ በመቄዶናዊው እስክንድር እጅ ጠፍታለች። ❖ ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ መምጣት እንዲህ ተናገረ፤ ያን ጊዜም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራ ዘንድ በአንድ ሕግም ይገዙልኝ ዘንድ የአሕዛብን ሁሉ አንደበት ወደ ሕግ እመልሳለሁ፤ ደግሞም እንዲህ አለ ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ መሥዋዕቴን ያመጡልኛል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለከ ሶፎንያስ ክቡር። ዘተነበይከ በእንተ ይሁዳ ኅልቀተ ኃጥአን እምድር። እንዘ ትብል ከመዝ እንበለ ሠናይ ምግባር። ኢያድኅን ወኢይትቤዘው ብሩር። አመ ምጽአተ እግዚእ ዕለተ ፍዳ ዘድምፃ መሪር። ዳግመኛም በዚች ቀን ስለ ክርስቶስ ትንቢታቸውን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያጐረፉ የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለክሙ ነቢያተ እስራኤል ኲሉ። ዘርኢክሙ ገሀደ ምሥጢረ ዘሀሎ ወይሄሉ። በእንተ ክርስቶስ እግዚእ ወበእንተ ቅዱስ ወንጌሉ። ይወጽእ ሕግ እምጽዮን ዘትብሉ። ወእምኢየሩሳሌም ካዕበ ለአብ ቃሉ። ከአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት በረከት ይክፈለን::

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤             ❤ #ሐምሌ ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_አራተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለአምደ ሃይማኖት መናፍቁ ንስጥሮስ በጉባኤ ኤፌሶን ተከራክሮ ረቶ ላወገዘው ለታላቁ #ለአቡነ_ቄርሎስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ ለነበረው ለሮሜ ሊቀ ጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ክልስቲያኖስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ቄርሎስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ (ለግብጽ) ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ ነው። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ፤ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍትን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው። ❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርትን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። ❤ ከዚህም በኋላ ሁል ጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር ለሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው። ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። ❤ አባ ቴዎፍሎስ በዐረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስነ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ። ይህ አባት ቄርሎስን መረጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት ንስጥሮስንም ተከራከረው ስህተቱንም ገለጠለት ከስህተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ከመንበረ ሲመት አሳደዱት። ❤ ይህም አባት ቄርሎስ አሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ። በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ። ከዚህም በኋላ ግን ብዙዎች ድንሳናትን ተግሳጻትንና መልእክቶችን ደረሰ። እሊህም በሁሉ ቦታ በመምእመናን እጆች ይገኛሉ። ❤ ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትሥብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራ ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕሪይ እንደሆነ አስረዳ። ይህኀኀዕዐዐዐዘፈዐጸዐሬፈጰም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ አሥራ ስምንት አባቶ ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስ ወደ ሁለት የሚከፍሉት መናፍቃንን ሁሉንም አውግዞ ለያቸው። ❤ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነኄዐጸዘጨዐዐዐው ሥራውም ፈጽሞ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቄርሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የሮሜ_ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_አባት_አባ #ክልስቲያኖስ፦ ይህ አባ ዮናክንዲዮስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን "በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ" ብሎ አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፈንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በዚያ ወራት ደግ ንጉሥ አኖርዮስ ነበር ከእርሱም በኋላ አመጸኛ ሉልያኖስ ነገሠ እርሱም ክርስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መናፍቁን ንስጥሮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው። የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክርስቲያስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድለውም ይሻ ነበር። እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሆደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤልን ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾክያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው "በዚያም ኑር" አለው። "ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድልህ ዘንድ በልቡ አስባልና"። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱም ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስ አገኘው ከአመጸኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው። ❤ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሊቃ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲዮስ በሌሊት ዕራይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋራ የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበር። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው "ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ"። ንጉሥም ጌታዬ "ምን ላድርግ" አለው እነዚያም ሁለትም አባቶች "በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን" ብለው መለሱለት "እኔ አምናለሁ" አላቸው "ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስ ወደ መንበሩ መልሰው" አሉት። ❤ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልክትን ጽፌ ወደ ድምትራያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ "ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሲመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን በመላእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሀለሁ"። መልአክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። ❤ የንስጥሮስም ክህደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምንክያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ ይህ አባት ክልስቲያኖስ በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደ ጉባኤው መምጣት አልተቻላቸውም ነገር ግን ንስጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋር ሁለት ቀሳውስትን ላከ። ❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲዮስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት "ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርተሀልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው" አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው "ተኩላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ"። ❤ ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ "እንነሳና እንሂድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው በዚችም ሰዓት በዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን አገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው" ይህንንም ብሎ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 3 ሰንክሳር።                                                       ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እነግሮሙ ስመከ ለአኃውየ። ወበማዕከለ ማኅበር እሴብሓከ። እለ ትፈርህዎ ለእግዚአብሔር ሰብሕዎ"። መዝ 21፥22-23። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 3፥18-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቄርሎስ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤              ❤ #ሐምሌ_፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን ቀድመው ወደ አገራች ኢትዮጵያ ለመጡ #ደብረ_ሊባኖስ_ገዳም በስማቸው ለተሰየመላቸው ከዐለት ጠበል እያፈለቁ ድውያንን ለሚፈውሱት ለተአምረኛው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሊባኖስ (መጣዕ) ለልደት በዓልና ዐፄ ገብረ መስቀል በስማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያሠራው ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                       ✝ ✝ ✝ ❤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ልደት፦ የዚህም የቅዱስ አባታችን የአባ ሊባኖስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱ ስም ንግሥት ነው። እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የከበሩ ነበሩ ሀገራቸውም ሮም ትባላለች ይህቺውም በቊስጥንጥንያ ሀገር አቅራቢያ ናት፤ ከኒህም ደጎች ሰዎች አባታችን አባ ሊባኖስ ሐምሌ ሦስት ቀን ተወለዱ። ❤ ከዚህም በኋላ በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት በነፃነትም ሁሉ መልካም ሆኖ አደገ የመልኩም ደም ግባት ያማረ ነገሩም እንደ ማር የጣፈጠ ነበር፤ ጥበብንና ተግሣፅን ብሉይና ሐዲስን ሁሉ ተማረ።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ዐፄ_ገብረ_መስቀል_ስለአሠሩት_የአቡነ_ሊባኖስ_ቤተ_ክርስትያን_ቅዳሴ_ቤት፦ ...ንጉሡ ገብረ መስቀልም የአባታችን ዕረፍት በሰማ ጊዜ ደብረ ወርቅ ወደ ምትባል ደብር ሄዶ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ቤተ ክርስቲያኑን ሠራ ሠርቶም ከጨረሰ በኋላ ጳጳስ አምጥቶ ሐምሌ ሦስት ቀን አስባረካት። በዚች ቀን ክቡር አባታችን አባ ሊባኖስ ተወልዶባታልና ስሙንም ገበዘ ገብረ መስቀል አለው። ሚስቱም የማርያምን ደብር ሠራች ልጁም አምስት አድባራትን ሠራ። እኒህም ሰባቱ አድባራት የመናንያን መቀመጫዎች ታላላቅ ገዳማት ሆኑ፤ ብዙ ርስት ጉልትም ተከለላቸው፤ በአባታችን በአባ መጣዕ (ሊባኖስ) ማደሪያም ዐሥራ ዘጠኝ አብያተ ክርስቲያናት ተሰሩ፤ በስሙም የተሠሩት አድባራት ቁጥሮቸው ሰማንያ ይሆናሉ። ይህም ሁሉ ሐሰት አይምሰላችሁ በአክሱም ታሪክ ይገኛል። ከጽዮን ሕግ ይወጣል በኢየሩሳሌምም ሕግ ይነገራል እንደተባለ። ❤ የካሌብ ልጅ ንጉሡ ገብረ መስቀልም ቤተ ክርስቲያኑን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ ደሙን ከጎን አንቅቶ አባቴ ሆይ ሥጋዬ ከሥጋህ ጋር እንደተጨመረ በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋር ጨምረኝ ብሎ ከክቡር አባታችን ከአባ ሊባኖስ መቃብር ላይ ደሙን ጨመረው፤ እኛንም ለመንግሥተ ሰማያት ከእርሱ ጋር ያኑረን ለዘለዓለሙ አሜን። ከአባታችን አቡነ ሊባኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ሊባኖስ።

❤ ከዚህ በኋላ በላ መርፌው ቀዳዳው ጠባብ የሆነውነ መርፌ በአቀረበለት ጊዜ "ኃይልህ ግለጥ" ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ እጁንም ዘርግቶ በአለ ገመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋር በመርፎ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ" አለው ገብቶም አለፈ "ሕዝቡም የፈጣሪያች የክርስቶስ ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ" አለው። ባለ ገመሉም በመርፎው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከገመሉ ጋር አልፎ ሆደ። ❤ ሕዝቡም አይተው "ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከህያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" እያሉ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ያም ጎልማሳ ባለጸጋ መጥቶ ከሐዋርያው እግር በታች ወድቆ ሰገደና ኃጥያቴን ሁሉ ይቅ በለኝ ገንዘቤንም ሁሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፍፍልልኝ" አለው። እንደ ለመነውም አደረገለት የሃይማኖትንም ሕግ አተምሮ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ሥጋውንና ደሙ አቀበለው ሁሉንም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ❤ ከዚህ በኋላ ከዚያ ወጣ በሰላምም ሸኙት በቡዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ ከአይሁድና ከአረማውያን መከራ ደረሰበት ከዚህም በኋላ ሐምሌ 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 1 ስንክሳር።                               ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለታዴዎስ_ምንዳቤ_ሕንቀት_ዘተወክፈ። እንበይነ ጥሪቱ ወብዕሉ አመ ባዕለ ዘለፈ። ለትውልድ ደኀሪ እስከ ተአምሩ ተጽሕፈ። ሰቀለ ብእሲተ በነፋስ ዘትዜሙ ዘልፈ። ወበስቊረተ መርፍዕ ካዕበ ገመለ አኅለፈ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_2።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወወስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥24-33።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ሐወጸካ ለምድር ወአርወይካ። ወአብዛኅኮ ለብዕላ። ፈለገ እግዚአብሔር ምሉዕ ማያት"። መዝ 64፥9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 9፥1-13፣ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 5፥17-33። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥16-30። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤              ❤ #ሐምሌ ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ላሳለፈ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ታዴዎስ ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ፦ ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለት ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልአኩ በሚአምር ጎልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ "ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከእንተ ጋራ እኖራለሁና" አለው። ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ❤ ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና "ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን" አሉት። እርሱም "ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ" አላቸው። እነርሱም " እንዳልክ ይሁን" አሉት። ❤ ያሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ "ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኀፍረት ነው ያሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና" አለ። ይህንኔም ብሎ ተነሥቶ እርፋን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበርና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችኖም አረሰ። ❤ የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ "እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን" አላቸው እነርሱም "እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም" አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው "ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱባት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን"። "ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት። እኛም ወዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውጧ ለመኖር እንሻለን" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው "አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ" አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት። ❤ ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን" ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ "ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም" አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። "ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው" አሉት እርሱም "ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻቸችሁ ታይዋቸዋላችሁ" አላቸው። ❤ ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ "እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ" አሉ። እኩሌቶቹም "ልገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማ መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም" አሉ። ❤ እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም በአያት ጊዜ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላክልን" አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ሰዎችም አዩዋት ያቺ ሴትም በከተማው መኳንንቶ "አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች" ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ሰደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለትውን ሴት አወረዳት። ❤ ከዚህም በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። ❤ በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ እውሮች አየ፣ ሀንካሶችም በትክክል ሔዱ፣ ዲዳዋች ተናገሩ፣ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ፣ አጋንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን ስኪያምኑ ሙታን ተነሱ። ❤ ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልቡ አድሮ በሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ላይ አነሳሳው ወደእርሱም ሰገደለትና እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ" አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን "ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻው በሌላው ላይ አታድርግ፣ ደግሞም ገንዘብህ ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለዓለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ" አለው። ይህንንም በሰማ ጊዜ ቊጣን ተመልቶ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ይገድለው ዘንድ አነቀው የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሳ አይኖቹ ተመዘው በወጡ ነበር። ❤ አባት ቅዱስ ጴጥሮስም "የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ" አለው። ያን ጊዜም ተወው። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም "ጌታችን እንደአንተ ላለው ሀብታም ባለፀጋ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ገመል በመርፎ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" ብሎ በእውነት ተናገረ አለው። ጎልማሳ "ባለፀጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል" አለ። ❤ በዚያ ጊዜም በዚያ ጎዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያው ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያው እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣል" አለው።

❖ ሐዋርያው ቶማስም ጠራው ልጄ ሆይ አትፈር ንገረኝ የእግዚአብሔር ቸርነት በግልጽ ዘልፎሃልና አለው፤ ያም ሰው ከሐዋርያው እግር በታች ሰገደ መልካም ሥራ የሠራሁ መስሎኝ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁ አንዲት የጠጅ አበዛ ሴት ነበረች አስቀድሞ ወደርሷ እኔ እገባ ነበር፤ አንተም በንጽሕና እንድንኖር አስተማርከን ያችም ሴት ከእርሷ ጋራ እተኛ ዘንድ ነዘነዘችኝ ስለዚህም ሰይፍ አንሥቼ አረድኳት ሐዋርያውም እንዴት እንዲህ ያለ ቁጣና የአውሬ ሥራን ሠራህ አለው። ❖ ከዚህ በኋላም ውኃ ያመጡ ዘንድ ሐዋርያው አዘዘና በውኃው ላይ ጸለየ ጐልማሳውንም በእግዚአብሔር ታምነህ እጆችህን ታጠብ አለው ሲታጠብም ዳነ፤ፐከዚህም በኋላ የዚያች ሴት በድን ወደ አለበት ና ምራኝ አለው ያም ጐልማሳ መርቶ ወደ ቦታዋ አደረሰው በደረሰም ጊዜ አይቷት እጅግ አዘነ። ❖ ወደ ውጭም አውጥተው በዐልጋ ላይ ያኖሯት ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ እጁንም በላይዋ ጭኖ ጸለየ፤ ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጐልማሳውን ሒድ እጇን ይዘህ እኔ ቀድሞ በእጄ ገደልኩሽ አሁን ግን በሃይማኖት በእኔ እጅ ክርስቶስ ያስነሣሽ በላት አለው፤ እርሱም እንዳዘዘው አደረገ እጇንም ይዞ ሳባት ፈጥናም ተነሣች ሐዋርያውንም አየችው ዐልጋዋንም ትታ ከሐዋርያ ቶማስ እግር በታች ሰገደች የልብሱንም ጫፍ ይዛ በአንተ ዘንድ አደራ ያስጠበቀኝ ባልንጀራህ ወዴት አለ አለችው። ❖ ሐዋርያም ወደየት ደርሰሽ ነበር ንገሪኝ አላት እርሷም አንተ ከእኔ ጋራ እያለህ እንዴት ንገሪኝ ትለኛለህ አለችው ያየሽውን ንገሪ አላት፤ ከሥጋዬ በተለየሁ ጊዜ አንድ ልብሱ የቆሸሸ ሽታውም የሚከረፋ ጠቋራ ተቀበለኝ የእሳት ጉድጓድና የእሳት መንኰራኵር ወደአለበት ቦታ ወሰደኝ ደግሞም እድፍንና ትልን የተመላ ጉድጓድን አየሁ ነፍሳትም በውስጡ ይንከባለላሉ። ❖ በዚያም በምላሳቸው የተንጠለጠሉ አሉ በጠጉራቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በእጆቻቸውም በእግሮቻቸውም የተንጠለጠሉ አሉ በላያቸውም ድኝ ይጤስባቸዋል ያስጨንቋቸዋልም፤ ያ የሚመራኝም እኒህ ነገረ ሰሪዎች፣ ሐሰተኞች፣ አመንዝራዎችና ቀማኞች፣ ሌቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ድኆችንና በሽተኞችን የማይጐበኙ፣ የእግዚአብሔርንም ሕግ የማያስታውሱ ናቸው ስለዚህ እንደ ሥራቸው ይቀጣሉ አለኝ አለች። ❖ ሐዋርያው ቶማስም ከዚያ የነበሩትን ይቺ ሴት የምትለውን ሰማችሁን ያለው ሥቃይ ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ከዚህ የሚከፋ አለ እናንተም የኃጢአትን ሥራና ክፉ አሳብን ትታችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ ትሕትናን፣ የዋህነትንና ፍቅርን፣ ንጽሕናንም ጠብቁ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ጸጋን ትቀበላላችሁ አላቸው። ❖ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሕዝብ አመኑ ለድኆችም ምጽዋትን ሊሰጡ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው አመጡ ለድኆች ምጽዋት መስጠት ለሐዋርያው ልማዱ ነበርና፤ ወሬውም በየሀገሩ ሁሉ ደርሶ በሽተኞችን ሁሉ አጋንንት የያዟቸውንም አምጥተው በጎዳና ዳር አኖራአቸው ሁሉንም በእግዚአብሔር ኃይል አዳናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለቶማስ ድኅረ ለብእሲት አሕየዋ። በቤተ መያሲ ዘሐረድዋ። ሶበ ተሰአላ ትንግሮ ኀበ በጽሐት በነሶሳዋ። እንዘ ምስሌየ ሀሎከ ትቤሎ ነዋ። እፎ ትሴአኒ ለዘለከ ፄዋ።

መስተጋድልት ቅፍሮንያ ሰማዕት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ እርሷም በደናግል ገዳም ቁጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች፤ የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው፤ ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት፤ በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያት የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት። ❖ ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር፤ ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች፤ በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር። ❖ ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ፤ እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ፤ እመ ምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች። ❖ በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኞች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም፤ ቅድስት ቅፍሮንያም በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት አለቻቸው፤ እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው። ❖ ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት። ❖"ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦሪያናም አንተ ከሀዲ ይቺን ታናሽ ብላቴና እንዳጐሳቈልሃት እግዚአብሔር ያጐሳቍልህ ዘንድ አለው ብላ ጮኸች፤ መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህቺን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲያሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች። ❖ ከዚህም በኋላ ደግሞ ምላሷንና ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ሕማም አስነሣት፤ መኰንኑም እሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች፤ አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ታአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ቅድስት ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለቅፍሮንያ አስናኒሃ ዘሰበሩ። ወመለያልያቲሃ ዘመተሩ። ወዘንተ ኲሎ እንዘ ይገብሩ። ኢክህሉ በጽንዖሙ ለዲዮቅልጥያኖስ ማኅበሩ። ከመ ይሚጥዋ ለክርስቶስ እምፍቅሩ። ዳግመኛም በዚች ቀን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት የክልዮስና የበርተሎሜዎስ የጻድቁ መነኰስ የገብረ መድኅንም የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ቀን ቅዱሳን መስተጋድላን ብዮክና ብንያሚን አረፉ፤ እሊህም ቅዱሳን በግብጽ ደቡብ በቴዎዳ አውራጃ ቱና በሚባል አገር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ነበሩ፤ እነርሱም ወንድማማች ነበሩ፤ አባታቸውም የቤተ ክርስቲያን ሹም የሆነ ደግና የዋህ ሰው ነበረ እሊህም ሁለቱ ልጆቹ በእግዚአብሔር ጸጋና በቅድስና ፍጹማን ነበሩ። ❖ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ተአምራትን ያደርግ ነበር በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር እነርሱም ከቤተ ክርስቲያኑ የጉድጓድ ውኃ ቀድተው በሽተኞችን ያጥቧቸዋል ወዲያውኑም ከበሽታቸው ይድኑ ነበር። ❖ የአባታቸው የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ በዚያን ሰዓት ቀሲስ ብንያሚን ቍርባን ያሳርግ ዘንድ የቅዳሴ ልብስ ለብሶ በቤተ መቅደስ ነበረ መልዕክተኞችም መጥተው አባቱ ለመሞት እንደ ተቃረበ እርሱንም እንደሚፈልገው ነገሩት። ❖ ብንያሚንም የቍርባኑን ሥርዓት ሳልፈጽም ልብሰ ተክህኖውን አላወልቅም ከመሞቱ በፊት እንዳየው እግዚአብሔር ከፈቀደ ይቆየኛል ካልሆነም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አለ፤ አባቱም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ላከ አባ ብንያሚን ግን የቍርባኑን ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ አባቱ ሔደ ሙቶም አገኘው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅድሳትም እጅግ አዘነ እነርሱ በእርሱ ዘንድ እየኖሩ ዕቃዎችን ያኖረበትን ቦታ አላመለከታቸውም ነበርና። ❖ ወንድሙ ብዮክም አባታቸው ስለ አስቀመጠው ንዋየ ቅድሳት ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ ቅዱሳን አረጋውያን ሒዶ እንዲጠይቅ መከረው፤ አባ ብንያሚንም በሔደ ጊዜ የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት አባ ዳንኤልን አገኘው አባ ዳንኤልም ስለርሱ የመጣበትን ሥራ ሁሉ ነገረው ነገር ግን ወደ አንድ ጻድቅ ሰው እንዲሔድ አዘዘው እርሱም ንዋየ ቅድሳቱ ያለበትን እንደሚያስረዳው ነገረው፤ በሔደም ጊዜ እንደ አመለከተው ያንን ጻድቅ ሰው አገኘው፤ እርሱም ገልጾ አስረዳው በተመለሰም ጊዜ እንዳስረዳው አገኘው። ❖"ከዚህም በኋላ በመልካም ገድል ሁሉ ከወንድሙ ጋራ ተጠምዶ ኖረ፤ ለሕሙማን ነፍሳችው ሳትወጣ ያቀብሏቸው ዘንድ ከቅዱስ ቍርባን ከፍለው በሣጥን የማኖር ሥርዓት ነበራቸው ሰይጣንም ከይሲን አነሣሣውና ሣጥኑን ቀድዶ ከዚያ ከቅዱስ ቍርባኑ በላ፤ ብዮክና ብንያሚንም ይህን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዘኑ ከይሲውንም ገደሉት ከዚህም በኋላ የተቀደሰውን ቍርባን ስለ በላ ከይሲውን ይበሉት ዘንድ ተማከሩ ፈቃዱም ከሆነ እንዲያስረዳቸው እግዚአብሔርን ለመኑት የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጸላቸውና ያን ከይሲ ይበሉት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም በሉት። ከበሉትም በኋላ አረፉ። ❖ እግዚአብሔርም ሥራቸውንና ገድላቸውን ለአንዲት ድንግል ሴት ገለጸ እርሷም የእሊህን ቅዱሳን ገድል ለሕዝብ ተናገረች እነርሱም የአማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ዕብል ለብንያሚን ወብዮክ። በጸሎት ዘተግሁ ወበአስተብቊዖ ውሱክ እስከ ኅቤሆሙ መጽአ እምኀበ አምላክ። በእንተ ዘበልዐ እምሥጋ ቡሩክ። በሊዐ ከይሲ ዘይኤዝዝ መልአክ። በዚችም ቀን የሊቀ ጳጳሳቱ የአግናጥዮስ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር አሜን። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ዳግመኛም በዚች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት በአረዷት ሴት ላይ ተአምርን አደረገ፤ ሥራ የሚሠራ አንድ ጎልማሳ ነበር ከሐዋርያው ቶማስም እጅ የተባረከ እንጀራ ከሕዝብ ጋራ ተቀበለ ወደ አፉም ሊጨምረው በወደደ ጊዜ እጆቹ ደረቁ፤ ያዩት ሰዎች ግን በዚህ ሰው ላይ የሆነውን ለሐዋርያው ነገሩት።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለፅንሰትከ እንበለ ኃጢአት ወግማኔ። #ወለልደትከ_ሰላም_አመ_፴ሁ_ለሰኔ። #ዮሐንስ_ዘኮንከ_ደመና ሰማይ ኮናኔ። እዝንም መና አእምሮ ውኅብስተ ጥበብ መድኃኔ ኀበ ውስተ ልብየ ኀብሩ ወገብሩ ኩርጓኔ"። ትርጉም፦ ያለ ኃጢያትና ያለርኩሰት በቅድስና ሕግ ለተፈጸመው ፅንሰትህ እና #በወርኃ_ሰኔ_በሠላሳኛው_ዕለት_ቀን_ለሚከብረው #ልደትህ_ሰላምታ_ይገባል። የሰማይ ደመና ታዝዝ ዘንድ ሥልጣን የተሰጠህ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በልቤ ውስጥ ተሰብስበው በአንድነት ወደ ተከማቹት ህዋሳቶቼ የጥበብ እንጀራ ሰማያዊ መና አዝንምልኝ። #መልክዐ_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ።                               ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለዮሐንስ_ግፋዕ_ወቅቱል_ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤               ❤ #ሰኔ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለነቢዩ_ለሰማዕቱ_ለካህኑ_ለሐዋርያው #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለተወለደበት_ለልደት_በዓልና #በሕንደኬ_ካሉ_ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ #ለአባ_ጌራን_ለዕረፍት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ማርያና_ከማርታ_ከመነኰስ #ገብረ_ክርስቶስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #ነቢይ_ሰማዕት_ሐዋርያ_መጥምቁ_ቅዱስ #ዮሐንስ_ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። ❤ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት። ❤ አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ❤ ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። ❤ "የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"። ❤ ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። ❤ ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ገድለኛው_የሆነ_አባ_ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር። ❤ ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት። ❤ በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ። ❤ ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች። ❤ ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት። ❤ ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን። ❤ የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወተወከልኩከ እንዘ ሀሎኩ ውስተ አጥባተ እምየ። ላዕሌከ ተገደፍኩ እማኅፀን። እምከርሠ እምየ አንተ አምላኪየ"። መዝ 21፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 7፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-10 እና የሐዋ ሥራ 19፥1-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥57-80። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤               ❤ #ሰኔ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለነቢዩ_ለሰማዕቱ_ለካህኑ_ለሐዋርያው #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለተወለደበት_ለልደት_በዓልና #በሕንደኬ_ካሉ_ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ #ለአባ_ጌራን_ለዕረፍት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ማርያና_ከማርታ_ከመነኰስ #ገብረ_ክርስቶስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #ነቢይ_ሰማዕት_ሐዋርያ_መጥምቁ_ቅዱስ #ዮሐንስ_ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። ❤ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት። ❤ አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ❤ ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። ❤ "የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"። ❤ ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። ❤ ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ገድለኛው_የሆነ_አባ_ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር። ❤ ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት። ❤ በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ። ❤ ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች። ❤ ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት። ❤ ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን። ❤ የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወተወከልኩከ እንዘ ሀሎኩ ውስተ አጥባተ እምየ። ላዕሌከ ተገደፍኩ እማኅፀን። እምከርሠ እምየ አንተ አምላኪየ"። መዝ 21፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 7፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-10 እና የሐዋ ሥራ 19፥1-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥57-80። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና። ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር። ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር"። መዝ 146፥8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 3፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4፥9-18 እና የሐዋ ሥራ 9፥20-23። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ቴዎድሮስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን። ✝ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም እና ፌስቡኬ ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያሉት ሊንኮች ይጫኑት።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤             ❤ #ሰኔ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለንጹሕ_ጻድቅ ለሆነ ለሮሜ ንጉሥ #ለቅዱስ_ማርቆስ_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ_በዓል፣ #ከቆና_ገዳም_ለሆኑ_ለሰባት_መስተጋድላን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዐረፍታቸው በዓል መታሰቢያና #ለቅዱሳን_ለአባ_ሖር_ለአባ ብሶይና #ለእናታቸው_ይድራ ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ ለሆነ #ለአባ_ሖርሳም_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከክብር ባለቤት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደበት #ከልደቱ _ከበዓለ_ወልድ_ከወራዊ_ከመታሰቢያ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝ ✝ ✝ ✝️ #ለሮሜ_ንጉሥ_ቅዱስ_ማርቆስ፦ ይህም ቅዱስ ንጹሕ ጻድቅ ነበር። በድንግልናው አምስት ዓመት ነገሠ ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ። እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስቱን እንዲአገባ መኳንንቱ አስገደዱት እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቁሞ ጸለየ "እመቤቴ ሆይ ላንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደ ምሔድበት ምሪኝ" አላት። እርሷም "ወደ ቶርማቅ ተራራ ሒድ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይኑር" አለችው። ✝️ ከዚህም በኋላ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕር ወደብም በደረሰ ጊዜ ያለ መርከብ ተሻግሮ ወደ ቶርማቅ ተራራ ደረሰ ያም ቦታ ደረቅ ነበረ ከአጋንት ጋራም እየተጋደለ በውስጡ ስልሳ ዓመት ኖረ። ሰኔ 29 ቀን በዐረፈ ጊዜም መላእክት በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ንጉሥ በቅዱስ ማርቆስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ✝️ #በቆና_ገዳም_የነበሩ_ሰባት_መስተጋድላን ሰማዕታት፦ የእሊህም ስማቸው አባ አብሲዳ፣ አባ ኮቶሎስ፣ አባ አርድማ፣ አባ ሙሴ፣ አባ እሴይ፣ አባ ኒኮላስና አባ ብሶይ ናቸው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጾ እንዲህ ብሎ "አዘዛቸው ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ግለጡ"። ✝️ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ሊሔዱ ተነሡ መርከብንም አገኙ በመርከቧም ውስጥ አምስቱን መስተጋድላን አገኙአቸውና ከእነርሱ ጋር ተስማሙ ወደ መኰንኑም ደርሰው በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመኑ። መኰንኑም ከእርሳቸው አንዱን ስለ ሀገራቸው ጠየቀው እርሱም ቆና ከሚባል አገር እንደሆኑ አስረዳው መኰንኑም ያሥሩዋቸው ዘንድ አዘዘ። ✝️ ከዚህም በኋላ ደግሞ ከእሥር ቤት አውጥተው ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩአቸው ዘንድ ደግሞም በአንገቶቻቸው ከባድ ደንጊያዎችን አንጠልጥለው እንዲአሥሩዋቸው አዘዘ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በውህኒ ቤት ውስጥ ተገለጠላቸው አጽናናቸውም ቃል ኪዳንም ገባላቸው። ✝️ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላካቸው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው። ከዚህም በኋላ ዝፍትና ድኝ በተመሉ ከሁለት የብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩአቸው ነበልባሉም ሃያ ክንድ ከፍ ከፍ እስሚል ድረስ ከታች እሳትን አነደዱባቸው ከምጣዶችም ውስጥ አውጥተው በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩአቸው ጌታችንም ዳግመኛ ተገልጾ ያለ ምንም ጉዳት አዳናቸው። ✝️ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው መቶ ሠላሳ ሰዎች በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ከዚህም በኋላ አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ እነርሱም አጵሎን የሚሉትን ጣዖት በወንበር እንደ ተቀመጠ አምጥቶ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው እነርሱም ግን በእግሮቻቸው ረገጡትና ከመንበሩ ወድቆ ተሰበረ። ✝️ መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እግሮቻቸውንም እንዲቆርጡ አዘዘ የቅዱስ ቀሲስ አብሲዳንን ግን ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ምስክርነቱን ፈጸመ እንዲሁ ደግሞ እሊያ አምስቱንም ራሶቻቸውን ቆረጡ ቅዱስ ኮቶሎስን ግን በእሳት አቃጠሉት ሁሉም የሰማዕትነት አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰባቱ መስተጋድል ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ✝️ #ቅዱሳን_አባ_ሖር_አባ_ብሶይና እናታቸው #ቅድስት_ይድራ ከአንጾኪያ ንጉሥ ሠራዊት ውስጥ የሆነ #አባ_ሖርሳ፦ እሊህም ወደ እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም አባ ብሶይን ይዘው ቀኝ እጁንም አሥረው በከተማዎች ሁሉ በበሬዎች እንዲጐትቱት አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ የተዘረጉ ብረቶችን በእሳት አግለው በሥጋው ውስጥ አደረጉ የግራ እጁንም ቆረጡ እርሳስም አቅልጠው በአፉ ጨመሩ ጊንጦችና እባቦች ወደ ተከማቹበት ውስጥ ጣሉት እነርሱ ግን ከቶ አልቀረቡትም። ❤ ከዚህም በኋላ በብረት በትሮች ይደበድቡት ጀመር እርሱም "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ" ብሎ ጮኸ ጌታችንም አጸናው እንደቀድሞውም ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ አስነሣው። ❤ ከዚህም በኋላ እናቱ ወደርሱ መጥታ አረጋጋቸው በመጋደሉም ደስ ተሰኘችበት። ስለ እርሷም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ወደ እርሱ አስቀርቦ እያስፈራራ "ለአማልክት ሠዊ" አላት። እርሷ ግን አልፈራችውም ትእዛዙንም አልሰማችም የብረት በትሮችንም አግለው በጎኖቿ ውስጥ እንዲአደርጉ አዘዘ ይህንም በእርስዋ ላይ በአደረጉ ጊዜ ደስ ብሏት ዘመረች ስለ ቅዱስ ስሙም መከራ እንድትቀበል ያደረጋት እግዚአብሔርን አመሰገነችው ከዚህም በኋላ ነፍሷን ሰጠች የሰማዕትነትም አክሊል ተቀዳጀች። ❤ ቅዱስ አባ ሖርንም ከቅባትና ከተቀመመ የነዳጅ ቅመም ጋራ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት እርሱም ያለ ሕማም ሁኖ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር ይህንንም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም እጅግ አደነቀ ደነገጠም። ንጉሡ ግን ተቆጣ በእጁም ጦር እንዳያዘ ወደ ብረት ምጣዱ ሒዶ ቅዱስ ሖርን ወጋው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ❤ እንዲሁም ወንድሙ አባ ብሶይን ብዙ ሥቃይን ካሠቃዩት በኋላ ራሱን በይፍ ቆረጡት። ሁሉም በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለማርቆስ_ጊዜ_ተሠልጠ_ዘመኑ። እንዘ ሀሎ ደብረ ቶርማቆ መካኑ። ወንጌል ቅዱሰ እንተ ማቴዎስ ይዜኑ። ሶበ ይብይ ለመልአከ ሰማይ ልሳኑ። መነጠ ፭ቱ እመት ተለዓለ በድኑ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ29።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ 109፥3።የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥1-13።