en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
603
Subscribers
-324 hours
-87 days
-1730 days
Posts Archive
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፩ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" 📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፩ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የሰኔ ወር ቀኑ ዐሥራ አምስት ሰዓት ነው፤ ከዚህም በኋላ ይጎድላል፤ ሰኔ አንድ ቀን በዚች ቀን ከእርሱ ተአምራት የተገለጡ የሶርያ ሰው የሆነ የቅዱስ ለውንትዮስ የቤተ ክርስቲያኑ ቅዳሴ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አሳለፈ ? ➡️ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ሰይሟል። ➡️ ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁም #ከመጽደቁ_በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ➡️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ #የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገልጿል። ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ወስኗል። ➡️ #ከሀገር_ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ ፦ - በሙያ ብቃታቸው፣ - በምግባራቸው - በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት #በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ወስኗል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦ ° " #ግድሉ " ° " #ዘርህ_ይጥፋ " ° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል። ይህ ንግግራቸው ፦ ➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል ➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የጎነ ➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል ➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ ➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ ➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል። የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል። በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል። ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስክበት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት
+3
የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል። " ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል። ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል። በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል።

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ✨✨✨ክቡራን የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች እንደሚታወቀው በሰ/ት/ቤታችን የፊታችን እሁድ(18/09/2016) የ
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ✨✨✨ክቡራን የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች እንደሚታወቀው በሰ/ት/ቤታችን የፊታችን እሁድ(18/09/2016) የሚደረግ ጉዞ ተዘጋጅቷል፣ ምዝገባውም እየተካሄደ ነው። ፦፦፦፦ ስለሆነም ላልተመዘገባችሁ እና መሄድ ለምትፈልጉ እስከ አርብ(16/09/2016) ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ በትህትና እገልፃለን። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ግንቦት ፩ እንኳን በሰላም ለዚህች ቀን አደረሳችሁ! በዚህች ዕለት ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ፣ አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና ሊባኖስ
ግንቦት ፩ እንኳን በሰላም ለዚህች ቀን አደረሳችሁ! በዚህች ዕለት ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ፣ አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና ሊባኖስ በተባለ ተራራ ተወለደች ! ልመናዋ ክብሯ ፣ የልጅዋ ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን። እመቤታችን በአማላጅነቷ ፣ በቃልኪዳኗ ትጠብቀን።                   አሜን ! 🌹<  ወስብሐት ለእግዚአብሔር  >🌹                   

ኀሙስ ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡ ዐርብ የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡ ቀዳሚት ሰንበት በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡ እሑድ ሰንበት በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤ ሰኞ የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡ ማክሰኞ ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ረቡዕ ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡