en
Feedback
𝖊-𝖘𝖆𝖋𝖊

𝖊-𝖘𝖆𝖋𝖊

Open in Telegram

This channel is mainly focused on - Programming tutorial - Technology news - Technology tips & - job opportunities our market channel @esafemarket contact @esafeSupport

Show more
1 115
Subscribers
No data24 hours
-97 days
-1830 days
Posts Archive
ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከፍተኛ በጀት የመደቡ ሀገራት ሀገራት የሰው ልጅን ስራ ያቀላል ለሚሉት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በየአመቱ በቢሊየን ዶላር ይመድባሉ። ቴክኖሎጂው በየጊዜው እያደገና ፉክክሩም እ
ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከፍተኛ በጀት የመደቡ ሀገራት ሀገራት የሰው ልጅን ስራ ያቀላል ለሚሉት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በየአመቱ በቢሊየን ዶላር ይመድባሉ። ቴክኖሎጂው በየጊዜው እያደገና ፉክክሩም እየተጠናከረ ቢሄድም ከፍ ያሉ ስጋቶችም ተደቅነውበታል። ለዘርፉ ከፍተኛ በጀት የመደቡ 10 ሀገራትን ከፎቶው ላይ ይመልከቱ

የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባ የአሜሪካውን ቻትጂፒቲ የሚፎካከር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስራቱን ይፋ አድርጓል። “ቶንጂ ሽዌን” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትጂፒቲ የሚሰጠውን አገልግሎት ሁሉ ይሰጣል ተብሏል። በአሊባባ ቢዝነስ ላይ ስራ ይጀምራል የተባለው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በይፋ አገልግሎት የሚጀመርበትን ጊዜ ግን ኩባንያው አላሳወቀም። “ቶንጂ ሽዌን” በግርድፉ “በሺዎች ለሚቆጠሩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ” የሚል ትርጉም እንዳለው ሬውተርስ ዘግቧል። በቻይንኛ እና እንግሊዝኛ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው “ቶንጂ ሽዌን” በአሊባባ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ “ዲንግቶክ” ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ዳኔል ዣንግ ተናግረዋል። አሊባባ የ“ቶንጂ ሽዌን” ሰው ሰራሽ አስተውሎት እንደ አማዞኑ አሌክሳ በድምጽ ምላሾችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል። “ቶንጂ ሽዌን” ንግግርን ወደ ጽሁፍ መቀየር፣ የኢሜል መልዕክቶችን የመጻፍና የቢዝነስ ንድፎችን የማዘጋጀትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣልም ነው የተባለው። ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ህዳር ወር ላይ የአሜሪካው ኦፕን አይ ኩባንያ ቻትጂፒቲን ይፋ ካደረገ በኋላ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መሰል አገልግሎት የሚሰጡ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራ ላይ ተጠምደዋል። ማይክሮሶፍት፣ ጎግል፣ የቻይናው ባይዱን ጨምሮ ቢሊየን ዶላሮችን ያፈሰሱባቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችም ስራ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ይህ የቴክኖሎጂ ፉክክርም በህግ ማሰሪያ ካልተበጀለት አደገኛ ነው ያሉ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት መመሪያዎችን እያወጡ ነው። የትዊተር ባለቤቱ ኤለን መስክም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፉክክር ጤናማ አይመስልም፤ “ሰብአዊነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ካሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሪዎች አንዱ ነው። የኢንቨስትመንት ባንኩ ጎልድማን ሳች በቅርቡ ባወጣው ጥናት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የ300 ሚሊየን ሰዎችን ስራ ሊተካ እንደሚችል ማመላከቱ የሚታወስ ነው። https://t.me/esafeSoftwareSolution

“የሞቱ ሰዎችን መንትያ መፍጠር ችለናል”- ተመራማሪዎች አዲሱ ቴክኖሎጂ ከፈረንጆቹ 2050 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ተመራማሪዎች ተናግረዋል የሞቱ ሰዎችን መንትያ መፍጠር እንደሚቻል ተመራማሪዎች ተናገሩ። ያለንበት ዘመን ሩጫ እና ወክቢያ የበዛበት ዘመን እየሆነ ይገኛል። በዚህምክንያ ብዙዎች እንደራሳቸው አልያም ከዛም በላይ የሚወዷቸውን ሰዎች ሲያጡ በሀዘን ይጎዳሉ። የብሪታንያው ራቭንስቦርን ዩንቨርሲቲ ግን የሞቱ ሰዎችን መንትያ ዳግም መፍጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ማግኘቱን አስታውቋል። በዩንቨርሲቲው የኮምፒውቲንግ እና ቢዝነስ ተመራማሪው ዶክተር አጃዝ ለሜይል ኦንላየን እንዳሉት አርቲፊሺያል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሞቱ ሰዎችን መንትያ መፍጠር ይቻላል ብለዋል። “ሞትን ለማስቀረት እየሰራሁ ነው” ያለው “አልቶሰ ላብስ” ተመራማሪው እንዳሉት ምስጋና ለአርቲፊሺያል ቴክኖሎጂ ይሁንና የሚወዱትን ሰው በሞት ቢያጡ ከአጠገብዎ እንዲሆን ዳግም ማቆየት ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ፈጠራ አማካኝነት አንድ የሚወዱት ሰው በህይወት እያለ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ፣ እንደሚያስብ፣ ደምጹ እና ሌሎች መገለጫዎቹን በቴክኖሎጂ በመውሰድ ህይቱ ሲያልፍ የነበሩትን ነገሮች ሁሉ በአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ህይወት እንዳለው ሰው ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል ተብሏል፡፡ ይህ ፈጠራ በተለይም የፍቅር አጋራቸው ለሞተባቸው፣ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት እና ለሌሎችም የሚወዷቸውን ቤተሰብ በማጣት በሀዘን ይጎዱ ለነበሩ ሰዎች ፍቱን መሆኑንም ተመራማሪው አክለዋል፡፡ አዲሱ አርቲፊሺያል ቴክኖሎጂ የአያቶቻቸውን ተረቶች እየሰሙ ለሚያድጉ ነገር ግን ወላጆቻቸውን በሞት እያጡ ሀዘን ላይ ለሚወድቁ ህጻናት መፍትሄ እንደሚሆን በዘገባው ላይ ተገልጿል፡፡ የቴክኖሎጂ ፈጠራው በሞት ያጡት ሰውን ትክክለኛ ድምጽ፣ በተለያዩ ስሜቶች ውስጥ ሆነው ያወጧቸው የነበሩ ድምጾችን ሳይቀር ልክ በህይወት ያሉ ያህል እንዲነጋገሩ ማድረግ ያስችላልም ተብሏል፡፡ ይሁንና ይህ ቴክኖሎጂ ከፈረንጆቹ 2050 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ እንደሚውል ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡ https://t.me/esafeSoftwareSolution

The first programming language is widely considered to be Fortran (FORmula TRANslation), which was developed by IBM in the 1950s. It was designed to allow engineers and scientists to write formulas and equations for scientific calculations. However, there were some earlier programming languages that were developed before Fortran, such as the machine language used by early computers, which consisted of binary code that had to be entered manually. There were also assembly languages developed in the 1940s and 1950s, which used mnemonics to represent machine language instructions. But Fortran was the first high-level programming language that allowed programmers to write code using more human-readable expressions, and it paved the way for many other programming languages that have been developed since then. https://t.me/esafeSoftwareSolution

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው። የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል። የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል። የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ? - መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል። - የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። - ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው። - ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ? ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። https://t.me/esafeSoftwareSolution

በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሊያዙ ይችላሉ የተባሉ የዓለማችን ስራዎች ይፋ ሆነዋል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚተኩ የስራ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? በየጊዜው ይፋ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሰው ልጆችን ህይወት በማቅለል ይታወቃሉ። እነዚህ ፈጠራዎች በየጊዜው እየዘመኑ እና እየተሻሻሉ የመጡ ሲሆን አንዳንዶቹ መልሰው የሰው ልጆችን ፍላጎት ሲጋፉ ይስተዋላል። በቀርቡ በአሜሪካው ኦፕን አይ ኩባንያ ይፋ የተደረገው ቻትጅፒቲ የቴክኖሎጂ ስራ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ብዙዎችን አስገርሟል። የሙዚቃ ግጥም እና ዜማን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን ይሰራል የተባለው ቻትጅፒቲ አሁን ደግሞ በሰው ልጆች ይሰራሉ የተባሉ እልፍ ስራዎችን በመረከብ በፍጥነት ያከናውናል ተብሏል። የሰው ልጅ ህዝብ ቁጥር እና የስራ ፍላጎት እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ይህ ቴክኖሎጂ ሰዎችን ተክቶ መስራቱ ጉዳቱ ያመዝናልም እየተባለ ይገኛል። ዩሮ ኒውስ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ይዞት በወጣው ዘገባ መሰረት በቻትጅፒቲ ቴክኖሎጂ ሊተኩ የሚችሉ ስራዎችን እንደሚከተለው አስቀምጧል። እንደ ባለሙያዎቹ አስተያየት በቻትጅፒቲ ቴክኖሎጂ ብዙ ስራዎች በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ሊተኩ ይችላሉ ብለዋል። ከቋንቋ ጋር የተያያዙ 86 የስራ ዘርፎች ሙሉ ለሙሉ በቻትጅፒቲ ሊተኩ ይችላሉ የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ 15 ጠቅላላ የሙያ መስኮች በዚሁ ቴክኖሎጂ ይተካሉ ተብሏል። ከዚህ በፊት በሰው ልጆች ሲከናወኑ የነበሩ በቀጣይ ግን ሙሉ ለሙሉ በቻትጅፒቲ ቴክኖሎጂ ይተካሉ ከተባሉ ሙያዎች ውስጥም የሒሳብ ስራ፣ የግብር መረጃ ዝግጅት ፣ የፋይናንስ ትንታኔዎች፣ ድርሰት እና ጽሁፍ ስራዎች፣ የዌብሳይት ዲዛይን እና ማስተዳድር ስራዎች ዋነኛዎቹ ናቸው። እንዲሁም የጥናት ስራዎች፣ትርጉም ስራዎች፣ የህዝብ ግንኙነት ፣ የእንስሳት ሳይንስ እና ከቋንቋ ጋር የተያያዙ ሌሎች ስራዎችም ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል በዚህ ቴክኖሎጂ ሊከናወኑ እንደሚችሉ ተገልጿል። በተጨማሪም የጋዜጠኝነት ስራዎች፣ የአየር ንብረት ፖሊሲ፣ ክሊኒካል ዳታ ፣ የህግ ጉዳዮች ጽህፈት፣ የፍርድ ቤት ሪፖርት እና የአርትኦት ስራዎች በቻትጅፒቲ ሊከናወኑ እንደሚችሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ይሁንና ይህ የአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ የተሳሳቱ ውጤቶችን እና ሪፖርቶችን የመስራት እድሉ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። https://t.me/esafeSoftwareSolution

+6
Civics TG G12.pdf7.63 KB

+5
GeoTGG11.pdf13.43 MB

+6
Physics TG10-1.pdf29.16 MB

+5
Grade 9 Geography TG.pdf1.20 MB

ብዙ ሰወች Teacher guide app እንፈልጋለን እያላችሁ ጠይቃችሁኛል አፑን ለመስራት ጊዜ ስላላገኘሁ ከ 9-12 ያሉትን በ PDF እለቅላችኋለሁ ለ ሌሎች ሼር አድርጉ። https://t.me/esafeSoftwareSolution

✅👌በጣም የሚገርም ዕድል Italy በተለያዩ ፊልዶች full scholarship apply ማድረግ የሚፈልግ በ @ethscholarship አውሩኝ:: both BSc and MSc

Repost from N/a
ማንኛውም ዕቃ ከ Aliexpress ላይ መግዛት የሚፈልግ ሰው በ @esafeSupport ያናግረኝ
ማንኛውም ዕቃ ከ Aliexpress ላይ መግዛት የሚፈልግ ሰው በ @esafeSupport ያናግረኝ

account የከፈታችሁ mine አንዲያደርግ ቢያንስ በ 24 ሰዓት 1 ጊዜ መክፈት አለባቸሁ:: ያልከፈታችሁ ደግሞ ብትከፍቱ ምንም አትጎዱም:: እውነት የሆነ ቀን ታመሰገናላቸሁ::

I am sending you 1π! Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 35 million members worldwide. To clai
I am sending you 1π! Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 35 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/shambi21 and use my username (shambi21) as your invitation code. PI ገና ኤክስቼንጅ ማድረግ አይቻልም ግን ሊኖረው የሚችለው ዋጋ ከላይ በ ፎቶ እንደምታዩት ነው። እና አሁን አፕልኬሽኑን አውርዳችሁ ማይን ማድረግ ብትጀምሩ ምንም አይጎዳችሁም። ገና እንደከፈታችሁ 1 pi ይሰጣችኋል። ከዚህ በፊት ማይን ማድረግ የጀመራችሁም ካላችሁ ገብታችሁ KYC test ውሰዱ። @esafeSoftwareSolution

TELEGRAM ያለ proxy ወይም VPN በስተቀር መስራት  አቁሙዋል Vpn ይጠቀሙ ወይ ከስር ያለውን ሊንክ ነክተው በ proxy Connect ያርጉ። https://t.me/proxy?server=cheha-ba-jan-khod-door-az-rokh-janan-khod-kardam.sbs&port=443&secret=7vQ1mpsyX_HR5QhN8OD3U3ttc24uY29t https://t.me/esafeSoftwareSolution