cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Show more
Advertising posts
60 066
Subscribers
+3124 hours
+997 days
-19330 days
Posts Archive
📌 ለወንድምህ ዱዐ አድርግለት “ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።” ረሱል (ﷺ)
Show all...
560👍 151
ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ! 🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢 በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ። እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት። እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል። እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት.... ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?! ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ። አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?! ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።" [ሐሳቡ (አላህ ይዘንላቸውና)የዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ነው።] ©️ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
Show all...
398👍 180
01:30
Video unavailableShow in Telegram
🔴 የመንግስት ቢሮዎች ላይ የሙስሊሙ ቁጥር ለምን አናሳ ሆነ? 📌 T.me/ahmedin99
Show all...
383👍 117
01:07
Video unavailableShow in Telegram
🔴ሴኩላህ የሚሆነው ተማሪው ነው ወይስ የትምህርት ስርዓቱ? 📌 T.me/ahmedin99
Show all...
369👍 149
01:25
Video unavailableShow in Telegram
‘ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀይማኖታቸው ምክንያት እየተበጠሩ ወደ ዳር እየተደረጉ ነው።”
Show all...
440👍 136
01:05
Video unavailableShow in Telegram
አመተ ምህረት ምንድነው? 📌 @ahmedin99
Show all...
444👍 135
አመተ ምህረት ምንድነው? https://vm.tiktok.com/ZMMx6t4Vd/
Show all...
25👍 16
“አላህ የታመፀባቸውን ሁሉንም ወንጀሎች ምህረት ያደርጋል። በሱ ላይ አጋርቶ የሞተ ሲቀር።” ረሱል (ﷺ)
Show all...
👍 178 83
“Ramadaana soome sooma ji'a shawwaal guyyaa 6 itti aansee soome akka waggaa guutuu soomeetti lakkaa'amaaf.” Ergamaa Rabbii (ﷺ)
Show all...
191👍 49
“ረመዳንን ፆሞ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆምን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል።” ረሱል (ﷺ)
Show all...
356👍 107
የ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል #በወልቂጤ ከተማ በፎቶ!
Show all...
👍 205 118
ወሎ ከሚሴ የኢድ ሶላት ድባብ
Show all...
246👍 68
የ1445 ዓ.ሒ ዒድ አል‐ፊጥር በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ስታዲየም 📷 Abel Gashaw
Show all...
281👍 61
📌 ከአነስ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ እንዲህ ይላሉ፦ “ረሱል (ﷺ) ለኢደል ፊጥር ሶላት አይወጡም ነበር፤  ቴምር ተመግበው ቢሆን እንጂ። የሚመገቡት ደግሞ ዊትር አድርገው ነበር።” ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 953
Show all...
266👍 64
Photo unavailableShow in Telegram
254👍 85
የኢድ ተክቢራ T.me/ahmedin99
Show all...
159👍 49
የመጨረሻው የረመዳን አኢፍጣር ከማፍጠራችሁ በፊት ለብሎኬት ማምረቻ ማሽን ግዢ ካላቸቸው ላይ ሳይሰስቱ የአቅማቸውን ከ1 ብር ጀምሮ እስከ 300ሺህ ብር ለሰደቁ ወንድም እህቶቻችን ዱዓ እንዲደረግ አደራ ልበላችሁ። አላህ ተውፊቅ ሰጥቶት የሁላችንም የሆነን ኃላፊነትና ግዴታ ግንባር ቀደም ሆነው የወገኑ ሰዎች ናቸው! አላህ ይቀበላቸው። ያሰቡት ይሳካ። መዒሻቸው ይመር። ወንጀላቸው ይማር። ዐይባቸው ይሰተር። ዙሪያቸው ይባረክ። ባወጡት ይተካ። የቀራቸው ይበርክት። አሚን!
Show all...
165👍 51
Photo unavailableShow in Telegram
የፈጠራ ውድድር የምረጡኝ ቅስቀሳ ********************************* የተከበራችሁ ወዳጆቼ፣ እኔ ዶ/ር ዘይኑ ዙቤር በአለርት ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ስሆን የሰው ልጅ ላይ አደጋ ሲደርስ የረጃጅም አጥንቶች ስብራትቶችን ለማከም የሚያስችልን የአጥንት ህክምና መሳሪያን ሀገር ውስጥ ማምረትንና እንሰት(ቆጮ) ስብራትን በቶሎ የሚጠግንበትን ጥቅል ፈጠራ ሰርቼ እሁድ መጋቢት 29 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በETV ዜና ቻናል ላይ በነጋድራስ የፈጠራ ውድድር ላይ ፈጠራዬን አቅርቤያለሁ። ። እሁድ ፕሮግራሙ ከተላለፈበት 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሀሙስ ከቀኑ 6 ሰአት ድረስ NG2ን ወደ 800 አጭር ቁጥር ሜሴጅ በመላክ እንዲመርጡኝ በማክበር እየጠየቅኩ ጥቅል ለሚጠቀሙ ሜሴጁ ስለማይሰራ አዲስ ካርድ ሞልተው በአንድ ስልክ ደጋግሞ መምረጥ ይቻላል በተባለው መሰረት እርስዎም የቻሉትን ያህል ደጋግመው ቢመርጡኝ የህክምናችን መሻሻል ላይ የራስዎን አሻራ አኖሩ ማለት ነው ! አመሰግናለሁ። የኢቲቪውን ቪዲዮ ለመመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ። https://youtu.be/Ixzq6Ut4ETU?si=aoyYNGO1PeWiulck
Show all...
👍 172 46
Photo unavailableShow in Telegram
👍 245 122
📌የኢባዳ ትጥቅህን እንዳትፈታ… ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻ የረመዳን ሌሊት ላይ ፈልጉት።”
Show all...
221👍 73
📌 ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡ ለግንዛቤ ያህል ዘካተል ፊጥር ከዘካተል ማል ይለያል ። 📌ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው 🔴 ሙስሊም በሆነ 🔴 ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ 🔴 በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ። 📌 መቼ ነው የሚወጣው? ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው ፡፡ ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።
Show all...
👍 99 45
📌አልሀምዱሊላህ! አልሀምዱላህ 8 ሚሊየን ብር ደርሰናል! እዚህ እንድንደርስ አሻራችሁን ያኖራችሁ በሙሉ አላህ ይቀበላችሁ። ያወጣችሁትን ሁሉ አላህ ይተካላችሁ። የቀራችሁንም አላህ ይባርክላችሁ። ወንጀላችሁ በሙሉ ይማር። አይባችሁ ይሰትር። ልጆቻችሁን ከምታስቡት በላይ ሷሊህ ያድርግላችሁ። በልጆቻችሁ ተካሱ። ያማረ ኻቲማን አላህ ይወፍቃችሁ። ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡ ባሮቹ መካከልም ያድርጋችሁ አሚን።
Show all...
187👍 60
በቻናላችን ለብሎኬት ማምረቻው ቻሌንጅ "ነይቻለሁ፤ አላስገባሁም" ያላችሁ ወዳጆቼ አላችሁ። ታዲያ ኒያኮ ለአላህ የተገባ ቃል ነው። ጥብቅ ቃልኪዳን ነው። ነገ እናስገባለን ብላችሁ ከሆነ ነገ የናንተ ነው ወይ? ነገ የናንተ ካልሆነ ኒያችሁን ሳትፈፅሙ አጀል ከቀደማችሁ ቁጭቱን አትችሉትምና አሁኑኑ ኒያችሁን ለአኺራ አሻግሩ። ባረከላሁ ፊኩም!
Show all...
112👍 48
📌ገንዘብህ የበላኸው ለብሰህ የጨረስከው የሰደቅከው ብቻ ነው ሌላው ለወራሽ ነው ። መልዕክተኛው صل الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል "የአደም ልጅ ገንዘቤ ገንዘቤ ይላል የአደም ልጅ ሆይ በልተህ ከጨረስከው ምግብ ለብሰህ ከጨረስከው ልብስ ለአኼራ ካስቀመጥከው ሰደቃ ውጪ ምን ገንዘብ አለህ? ። " ሙስሊም ዘግበውታል
Show all...
👍 141 71