en
Feedback
Inclusive Education - Afar Region (Channel)

Inclusive Education - Afar Region (Channel)

Open in Telegram

A Channel for inclusive education reference materials

Show more
336
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
February '24
February '24
+10
in 0 channels
January '24
+26
in 0 channels
Get PRO
December '23
+12
in 1 channels
Get PRO
November '230
in 0 channels
Get PRO
October '230
in 0 channels
Get PRO
September '230
in 0 channels
Get PRO
August '23
+12
in 0 channels
Get PRO
July '23
+11
in 0 channels
Get PRO
June '23
+19
in 0 channels
Get PRO
May '23
+14
in 0 channels
Get PRO
April '23
+14
in 0 channels
Get PRO
March '23
+12
in 0 channels
Get PRO
February '23
+12
in 0 channels
Get PRO
January '23
+21
in 0 channels
Get PRO
December '22
+23
in 0 channels
Get PRO
November '22
+23
in 0 channels
Get PRO
October '22
+31
in 0 channels
Get PRO
September '22
+231
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
16 February0
15 February0
14 February0
13 February+1
12 February+1
11 February+1
10 February0
09 February0
08 February+1
07 February0
06 February+1
05 February+1
04 February0
03 February+1
02 February+1
01 February+2
Channel Posts
ህጻናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር፣ በህክምና መዳን ይቻላል! #clubfootawareness
ህጻናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር፣ በህክምና መዳን ይቻላል! #clubfootawareness

2
አካል ጉዳተኝነቱ ውጤታማ ከመሆን ያላገደው የፈጠራ ባለቤት ከማል አብዱራህማን ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ገደብ አሳሳ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የኦ
አካል ጉዳተኝነቱ ውጤታማ ከመሆን ያላገደው የፈጠራ ባለቤት ከማል አብዱራህማን ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ገደብ አሳሳ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የኦሮሚያ ክልልን ወክሎ የቀረበው ከማል ከገጠመው አካል ጉዳት በመነሳት ነበር ህይወቱን ለማቅናት በራሱ ጥረት ዊልቸርን እና ባጃጅ ለመስራት የበቃው፡፡ ከማል በእግር መንቀሳቀስ የማያስችል አካል ጉዳት ስለገጠመው የሚፈልገው ቦታ ለመንቀሳቀስ እና ትራንስፖርት ለመጠቀም የሰው ድጋፍ ይፈልግ ነበር፡፡ በዕለ ተለት እንቅስቃሴው ሰው ከማስቸግር እና የሰው እጅ ከማይ ለምን ከጥገኝነት የምላቀቅበት ፈጠራ ይዤ አልመጣም ብሎ ወሰነ፤ አደረገውም፡፡ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች እና ካረጀ ሞተር ከልጅነት ጀምሮ መፍታትና መግጠም ላይ የነበረውን ተሰጥኦ በመጠቀም የሚንቀሳቀስበት ዊልቸር ሰራ፡፡ ዊልቸር ሰራሁ ብሎ ረክቶ አልተቀመጠም፡፡ ከልመና የሚያላቅቀኝ ዘላቂ ሥራ መስራት የሚያስችለኝ ለምን ባጃጅ አልሰራም ሲል በድጋሚ አሰበ፡፡ ጥረቱን ቀጠለ። በመጨረሻም ሁሉም ነገሩ ለአካል ጉዳተኛ ምቹ የሆነ ባጃጅ ሰራ፡፡ በአሁን ወቅት አቶ ከማል የሁለት ባጃጅ እና አንድ ዊልቸር ባለቤት ነው፡፡ እራሱ በሰራቸው በእነዚህ ባጃጆች በቀን ቢያንስ እስከ 500 ብር ድረስ ገቢ ያገኛል፡፡ በዚህም እራሱን ከጥገኝነት ማላቀቅ ችሏል፡፡ ዊልቸር ከራሴ አልፌ እንደኔ ችግር ውስጥ ለነበሩ ሁለት ሰዎች ሰርቻለሁ፡፡ እነሱም ቀደም ሲል እኔ ካየሁት አይነት ስቃይ ተገላግለዋል ሲል ያብራራል፡፡ አካል ጉዳተኝነት ማለት አለመቻል አይደለም የሚለው ከማል በቀጠይ ለሥራው አመቺ የሆነ ቦታ ከተመቻቸለት የዊልቸር መገጣጠሚያ እስከመክፈት የደረሰ ህልም እንዳለው ይናገራል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡ @inclusiveafar
0
3
የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት (Cognitive development of child) እንደ ስዊዝ ተወላጁ ስይኮሎጂስት ፒያዤ (Jean Piaget) መሰረት የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተለያዩ ማነቃቂያዎች (stimulus) ምላሽ በመስጠት (response) እና በመላመድ ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ (awareness) እና የባህሪ ግንባታ እንዳለው ይገልጻል። የአንድ ልጅ የባህርይ ጸባይ የሚመሰረተው ከአካባቢው ጋር ባለው ቁርኝት ሲሆን፤ ይህም በልጁ የአዕምሮ ግንዛቤ ንድፍ (Schema) ለይ የሚመሰረት ነው። በዚህም መሰረት ልጆች 4 የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት ደረጃዎች አላቸው፦ 1. ሴንሰሪሞቶር| Sensorimotor stage (ከ ተወለደ እስከ 2 አመት) በዚህ ጊዜ ጨቅላው ልጅ ከአካባቢው ጋር የሚዛመደው በእንቅስቃሴ እና በስሜቶች ሲሆን፤ ለተለያዩ ማነቃቅያዎች እንቅስቃስያዊ ምላሽ ይሰጣል። እያደገ ሲመጣ (ወደ 2 አመቱ ሲጠጋ) የነገሮችን /ቁሶችን መኖር ይገነዘባል፤ እናም ህጻኑ የቁሶችን ምስል በአዕምሮው ጠብቆ ማቆየት ይጀምራል እና ከእይታው ውጪም ቢሆን ቁሱ እንዳለ መገንዘብ ይችላል፣ ለመፈለግም ይጥራል። 2. ፕሪ ኦፕሬሽን| Pre-operational stage (2–6 አመት) ህፃኑ የነገሮችን፣ ቁሶችን እንዲሁም ክስተቶችን አዕምሯዊ ምስሎችን ከመፍጠር ባሻገር፤ ለሌላ ጊዜ እንዲጠቀሙበት በአእምሮ ውስጥ በማስቀመጥ ምሳሌያዊ ግንዛቤን ያዳብራል። ልጁ እንቅስቃሴ እና የቋንቋ እድገት ክህሎቶችን በማዳበር የአካባቢያዊ ተግባቦት ችሎታ ያዳብራል። የልጁ አመክንዮ ግንዛቤ (logical thinking) ገና ያልዳበረ ስለሆነ ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ለማገናዘብ አይችሉም፤ ስለዚሀ ራስ ተኮር (ego centric) እና ምትሀት ተኮር (magical thinking) አስተሳሰብ ይዘው ያድጋሉ። ሆኖም ግን በመልካም ወይም በመጥፎ ነገር ላይ በመመርኮዝ የሞራል አስተሳሰብ ግንዛቤ ማዳበር ይጀምራሉ። 3. ኮንክሪት ኦፕሬሽን| Concrete operational stage (7-11 አመት) በዚህ እድሜ ዉስጥ የሚገኙ ልጆች አመክንዮአዊ (logical) እና ምክንያታዊ (Rational) አስተሳሰብን ያዳብራሉ። የራስ ተኮር አስተሳሰብ በእጅጉ ይቀንሳል፤ ብሎም ፅንሰ-ሀሳባዊ (conceptual) ግንዛቤዎች የጎለብታሉ፣ የሌሎችን አስተያየት መገነዘብ ይጀምራሉ። የቃላት፣ የሰውነት ተግባቦትን በደንብ ያለያሉ፤ በአጭሩ ተግባራዊ ይሆናሉ። 4. ፎርማል ኦፕሬሽን| Formal operational stage (ከ 12 አመት በኋላ) በዚህ እድሜ ለይ ያሉ ልጆች ረቂቅ አስተሳሰብን (ሀሳቦችን መመርመር እና የንድፈ-ሀሳቦችን የማመንጨት የማስተናገድ ችሎታ)፣ የአመክንዮ አስተሳሰብ እድገት (ከአንድ አጠቃላይ ሃስብ በመነሳት ወደ ውስን የማውረድ ችሎታ (deductive reasoning)፣ እና ፅንሰ-ሀሳባዊ አስተሳሰብ ትርጉም መስጠት ግንዛቤ ያዳብራሉ። ሃላፊነት መውሰድ የሚላማመዱበት ወቅት ነው። ስለዚህ ወላጆች የልጆቻችሁን የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት በዚህ መልክ መከታተል ይረዳችሁ ዘንድ እንደተጠቀሙበት እመክራለሁኝ። ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (ሳይካትሪስት) @melkam enaseb
0
4
No text...
0
5
የአዕምሮ ህሙማንና የሚደርስባቸው መገለል - ለችግሩም የመፍትሄ አቅጣጫ! የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል በአለም አቀፍ ደረጃ በየትኛውም የማህበረሰብ ክፍል በስፋት የተሰራጨ ችግር ከመሆኑም ባሻገር ይሄም
የአዕምሮ ህሙማንና የሚደርስባቸው መገለል - ለችግሩም የመፍትሄ አቅጣጫ! የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል በአለም አቀፍ ደረጃ በየትኛውም የማህበረሰብ ክፍል በስፋት የተሰራጨ ችግር ከመሆኑም ባሻገር ይሄም በጤና ባለሙያዎች ዘንድም የሚታይ አመለካከት ነው። የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግለል በታካሚዎች ዘንድ ከማህበረሰቡ እራሳቸውን እንዲያገሉና የህክምና እርዳታ እንዳይሹ የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ይሄንንም በማህበረሰቡ የሚደርስባቸውንና እንደግለሰብ የምናደርስባቸውን ማግለል ለመከላከል ከመንቀይሰው ስልት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:- 1. ማግለልን መቃወም "የአዕምሮ ህመምተኞችን የማግለል ተቃውሞ ዘመቻ" ማድረገ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የሚደረገውን ማግለል ለመቀነስ ይረዳል። 2. ማስተማር በማስተማር እያንዳንዱ ሰው ስለ አዕምሮ ህመም መንስዔ፣ የህመሙ መገለጫ ምልክቶች፣ የህክምና እርዳታና ተያያዥ ውጤቱን በማሳወቅ ሰዎች በአዕምሮ ህመምተኞች ላይ የሚያደርሱትን ማግለል መከላከል እንችላለን። 3. የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግኘት በተለያዩ የአዕምሮ ህክምና በሚሰጥባቸው ቦታዎችና የማገገሚያ ማዕከላት ብሎም መርጃ ማዕከላት (ሜቄዶኒያንና ጌርጌሴኖንን) እና የተለያዩ የአዕምሮ ህክምናና የሱስ ማገገሚያ ማዕከላት ሄደን ህመምተኞችን መጎብኘት ስለህመሙ ስለህመምተኞችና የሚደርስባቸውን ጫና ለመረዳት ያስችላልና የማግለል ሁኔታውን በመቀነስ የራሱን ሚና ይወጣል። እናንተስ ስለህሙማኑ ምን አሰባችሁ? የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል ይቁም! ቃልኪዳን ዮሐንስ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ) @melkam_enaseb
0
6
ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (Autism Spectrum Disorder) የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የአንድን ሰው ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት እና ባህሪ የሚጎዳ እክል ነው። እነዚህ እክሎች መለስተኛ፣ ከባድ፣ ወይም መካከለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የቡድን ስም ሲሆን በውስጡ አምስት እክሎችን የያዘ ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ባለሙያዎች የሚጠቅሷቸው የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር አይነቶች አሉ። እነዚህም፦ 1.አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome) 2.ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder) 3.ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder) 4.ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder) 5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome) ናቸው። 1. አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome) ይህ የኦቲዝም አይነት ቀለል ያለ የሚባለው ነው። አስፐርገርስ የሆኑ ልጆች በጣም አስተዋይ እና የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡ - እነርሱ በሚወዷቸው ወይም በተሳቡባቸው ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።   - እነዚህ ልጆች ማኅበራዊ ክህሎታቸው ላይ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል። - በተጨማሪም የንግግር እና ቋንቋ ክህሎታቸው ላይ እምብዛም እክል አይታይባቸውም።   2. ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder) - ይህ እክል ከአስፐርገርስ ሲንድሮም ካጋጠማቸው ልጆች የከፋ ሲሆን ነገር ግን ኦቲስቲክ ዲስኦርደር ካላቸው ልጆች የከፋ አይደለም፡፡ 3. ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder) - ይህ የቆየ ቃል ያለው ከአስፐርገርስ እና ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር የበለጠ እክል ነው፡፡ - ይህም ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶችን ያጠቃልላል ግን በጣም ኃይለኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። - ይህም የልጆችን ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት፣ ባህርይ፣ ስሜት እና ጨዋታ የሚጎዳ እክል ነው። 4. ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder) ይህ እክል እጅግ በጣም ከባዱ እና እጅግ የከፋው የስፔክትረም ክፍል እንደሆነ ይገለፃል። - ይህ እክል ያጋጠማቸው ልጆች በመደበኛነት የሚያድጉ እና ከዚያም ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 4 ባለው መካከል ሲሆን ብዙ ማህበራዊ፣ ቋንቋ እና አእምሯዊ ክህሎቶችን በፍጥነት የሚያጡ ልጆች ናቸው። - አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ልጆች የሚጥል ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። 5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome)   ሬት ሲንድሮም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ነው? ሬት ሲንድሮም ያለባቸው ሕፃናት ብዙውን ጊዜ ከአቲዝም ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ባሕሪዎች አሏቸው። ባለሙያዎቹም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር መካከል ካሉት ቡድኖች ውስጥ ይመድቡት ነበር፤ አሁን ግን በጄኔቲክ ሚውቴሽን ምክንያት እንደሚከሰት ስለታወቀ በማለት እንደ ASD አይቆጠርም፡፡ በማሕሌት አዘነ (Speech & Language Therapist) @melkam_enaseb
0
7
No text...
0
8
🔊 ዳውን ሲንድረም(Down syndrome) ምንድነው ❓️ ክፍል 1 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘 🔴 March 21 : የአለም የዳውን ሲንድርም ግንዛቤ ማስጨበቻ ቀን እንደሆነ ያውቃሉ❓️ 🌍 በአለም ላይ ከሚወለዱ 800 ህፃናት በአንዱ ህፃን ላይ ዳውን ሲንድረም  ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ❓️ ♀️♂️ ማንኛዉም ሰዉ ገና በማህፀን ዉስጥ ሲፀነስ 23 ዘረመል ከእናቱ 23 ዘረመል ከአባቱ ወስዶ ሰዉ እንደሚሆንስ ያውቃሉ❓️ ✍️  በሰውነታችን ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ ህዋሶች 23 ዘረመል ከእናት♀️ ተጨማሪ 23  ዘረመል ከአባት ♂️ወስደው ይሰራሉ :: ስለዚህ ባጠቃላይ አንድ ሰዉ 46 ዘረመሎች በ እያንዳንዱ ህዋስ ዉስጥ አለሉት ማለት ነው❗️ ✍️ ሆኖም አልፎ አልፎ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት በተለያየ ምክንያት ሳይሳካ ሲቀር አንደኛ ዘረመል ቦታ(ላይ ሁለት ከመሆን ይልቅ ሶስት ዘረመሎች ይሆናሉ:: ✍️  ከ 46ቱ ዘረመሎች በ 21ኛው ዘረመል ቦታ ላይ ሁለት ዘረመል መሆን የነበረበት ቦታ ላይ ሶስት ዘረመል ሆኖ ሲገኝ ዳውን ሲንድሮም(Down syndrome) ያለው ልጅ ሊፈጠር ይቺላል:: 👉 ስለዚህ በ አጭሩ ዳውን ሲንድረም ማለት የዘረመል አፈጣጠር ችግር ሲሆን ዘላቂ የሆነ የተለያዩ የጤና እክሎች ሊያመጣ የሚቺል ተፈጥሮ ነው :: 👉 ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እሰከ ከባድ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ 🔺የአይምሮ የእድገት ዉስንነት 🔺 የአየር ቱቦ እና አተነፋፈስ ችግር 🔺 የልብ አፈጣጠር ችግር 🔺የሆርሞን ችግሮች 🔺 የደም ችግሮች 🔺የአንጀት ችግሮች #Down #syndrome ምልክቶቹ ምንድናችው❓️ 👉 ዳውን ሲንድረም ያለበት/ባት ህፃን የሚከተሉትን አካላዊ ምልክቶች ይታዩባቸዋል:: ለምሳሌ 🔘 ጠፍጣፋ እና ለየት ያለ የፊት ገፅታ 🔘 ከፈት ያለ አፍ እና ተለቅ ብሎ የሚታይ ምላስ 🔘 አጭር አንገት 🔘 ዝቅ ያለ ጆሮ 🔘 የአይን ቅድ(አከፋፈት) አቀማመጥ ወደ ላይ ከፍ ማለት 🔘 የአይን ሽፋሺፍት ቆዳ መብዛት 🔘 ደካማ/የላላ ሰውነት ጡንቻ 🔘 አጭር እና ትንሽ መዳፍ 🔘 አጫጭር ጣቶች 🔘 አንድ ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመር እና የመሳሰሉት ሊኖሩት ይቺላሉ 👉 ኦቲዝም እና ዶውን ሲንድረም ልዩነታቸው ምንድነው❓️ 👉 የዳውን ሲንድረም ሕክምናው ምንድነው ❓️ መልሱን ነገ በዝህ በቴሌግራም ቻናችን ላይ ያገኙታል❓️ 👉 በቴሌግራም ቻናላችንን Join በ ማድረግ እንዲሁም የፌስ ቡክ ገፃችንን like & follow በማድረግ ይከታተሉን:: አዘጋጅ : ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር) 🛑 ዶ/ር ፋሲልን ስለ ዳውን ሲንድረም እና የጤና እክሎቹ ወይም ከዝህ ዉጭ ላሉ  የህፃናት ጤና የሚመለከቱ ነገሮችን ማማከር ወይም ሕክምና ማድረግ ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ/Application/ ከ playstore/Googleplay አውረደው ማማከር ይቺላሉ:: አጠቃቀሙን ለመረዳት በነፃ 9394 ይደውሉ እና ይጠይቁ :: 🛑 መተግበሪያውን ወደ ስልኮ ለማውረድ እና ለመጠቀም ከፈለጉ ከታች ያለውን link ተጭነው ይክፈቱ:: በመቀጠልም down load ያርጉ:: 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient 🛑 በአካል ሆስፒታል መተው የ ህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ማግኘት እና ሕክምና ከፈለጉ በከታች ባሉት ስልኮች ቀጠሮ ያስይዙ:: ☎️ 0984650912 👨‍👩‍👦 ለእርስዎ ፣ለልጆዎ እና ለቤተሰቦዎ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የጤና ፣የህፃናት አስተዳደግ እና አመጋገብ መረጃዎችን በየጊዜው እንደደርሶ ከፈለጉ ከታች ያለውን የቴሌግራም ማስፈንጠሪያ በመጫን ቀጥሎም የቴሌግራም ቻናላችንን ላይ join በማድረግ ቤተሰብ መሆን እና ማንበብ ይችላሉ :: 💯 በእርግጠኛነት ታተርፉበታላችሁ ‼️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil 🔷 FB:fb.me/drfasilpediatrician
0
9
Talking to other people can help reduce stress and help you find ways to cope better. That may not be easy: you may not feel
Talking to other people can help reduce stress and help you find ways to cope better. That may not be easy: you may not feel like being socially connected when your mood is low, but do let family and friends know that they can help by reaching out to you. Take a break, let’s talk. #WHO @inclusiveafar
0
10
በኢትዮጵያ ከ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለባቸዉ ተነገረ የአዕምሮ እድገት ውስንነት የዓለም ዳውንሲንድረም ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአለም አቀፍ ደረጃ ማርች 21 ወይም መጋቢት 12 በአለም ለ12ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለ8ተኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በተያዘው ዓመትም እሁድ መጋቢት 10 በእግር ጉዞ ይከበራል። ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር፣ ከኢፌዲሪ ሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን "ከእኛ ጋር ስለእኛ እንስራ " በሚል ዓለም አቀፍ መሪ ቃል ቀኑ ተከብሮ እንደሚውል ተገልጿል።በኢትዮጵያ ከ4 እስከ 5 ሚሊየን የሚሆኑ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ የፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ቦርድ ፕሬዝዳንት የሆኑት ምህረት ንጉሱ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረተ ከአለም ህዝብ በአማካይ 3 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለባቸው ይገለጻል።የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ስልጠና የሚወስዱበት ሆነ የሚውሉበት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ተቋማቶች ውስን ከመሆናቸው በተጨማሪ ዋጋቸው ውድ በመሆኑ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። በመኖሪያ ቤታቸው የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች በማበረታታት ወላጆች ትልቁን ሚና መጫወት እንዳለባቸው እና ማህበረሰቡ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ እኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማወቅ አለበት ሲሉ ምህረት ንጉሱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
0
11
Verified 𝗜𝗳 𝗻𝗼𝘁 𝘁𝗿𝗲𝗮𝘁𝗲𝗱, diabetes can cause: 👁️ blindness ❗️kidney failure 🫀 heart attack 🧠 stroke 🦵 lower li
Verified 𝗜𝗳 𝗻𝗼𝘁 𝘁𝗿𝗲𝗮𝘁𝗲𝗱, diabetes can cause: 👁️ blindness ❗️kidney failure 🫀 heart attack 🧠 stroke 🦵 lower limb amputation Access to early diagnosis and treatment is key to prevent such complications. #WHO t.me/inclusiveafar
0
12
https://www.bbc.co.uk/news/uk-northern-ireland-64783013
0
13
DYK: Depression is a leading cause of disability worldwide and is a major contributor to the overall global burden of disease
DYK: Depression is a leading cause of disability worldwide and is a major contributor to the overall global burden of disease. Depression can happen to anyone. 𝘋𝘰𝘯'𝘵 𝘣𝘦 𝘢𝘧𝘳𝘢𝘪𝘥 𝘵𝘰 𝘴𝘦𝘦𝘬 𝘩𝘦𝘭𝘱. With the right support, you can get better. ❤️ WHO @inclusiveafar
0
14
Strategies For Teaching Independent Skills @inclusiveafar+5
Strategies For Teaching Independent Skills @inclusiveafar
0
15
#Epilepsy is not contagious. Here are 5️⃣ steps you can take to help a person having a seizure #WHO @afargcs
#Epilepsy is not contagious. Here are 5️⃣ steps you can take to help a person having a seizure #WHO @afargcs
0
16
It's International Epilepsy Day. Know the facts about epilepsy: ➡ It's a common neurological disorder. ➡ It's something anyon
It's International Epilepsy Day. Know the facts about epilepsy: ➡ It's a common neurological disorder. ➡ It's something anyone can develop at any age ➡ It's treatable ➡ It's not contagious #WHO @inclusiveafar @inclusiveafar @inclusiveafar @inclusiveafar @inclusiveafar @inclusiveafar
0
17
#የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ማሳወቂያ የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃ
#የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ማሳወቂያ የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል። የትምህርት ሚኒስቴር
0
18
ሶሻል ፎቢያ (Social phobia) --------------------------------------- ሶሻል ፎቢያ  ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ሰዎች ባሉበት ዘና ማለት አይችሉም፡፡ ሌሎች ሰዎች የእነሱን ንግግር ወይም ድርጊት የሚገመግሙና የሚተቹ ስለሚመስላቸው ይፈራሉ፡፡ስህተት እንዳይሰሩና እንዳይዋረዱ ስለሚፈሩ ዘና ብለው እንደሚፈልጉት ከሰዎች ጋር መጫወት ይከብዳቸዋል ፡፡ አብዛኛው ሰው ካልለመደው ሰው ጋር ሲሆን የአለመመቸት ስሜት ይፈጠርበታል፡፡ ሶሻል ፍቢያ ሲሆን ግን ፍርሀቱ በጣም የበዛ ይሆናል፡፡ ሶሻል ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች አብሯቸው ያሉ ሰዎች ሲጫወቱ ፣ሲስቁ ፣ሲያወሩ እነሱ መሣተፍ ስለማይችሉ ብቸኝነት ይሰማቸዋል፡፡ ብቻቸውን ግን አይደሉም፡፡ ከአስር ሰው አንዱ ተመሣሣይ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ነገ መንገድ ላይ ሲሄዱ አስር ሰዎች ይቁጠሩ ከዛ ውስጥ አንዱ ሶሻል ፍቢያ አለበት/አለባት፡፡ የሶሻል ፎቢያ ምልክቶች በጥቅቱ፦ -ከቤት ውጪ ምግብ ባይበሉ ይመርጣሉ፡፡ለብቻቸው ሬስቶራንት ገብተው፣ ባዶ ጠረጴዛ ፈልገው፣ 'ያ ሁሉ ሰው' እያያቸው መመገብ ይከብዳቸዋል፡፡ -ዝግጅቶች ላይ በግድ ነው የሚገኙት (እሱንም ከተገኙ!)-እስከቻሉት ድረስ ምክኒያት ፈጥረው ለመቅረት ይሞክራሉ፡፡ -በአብዛኛው የድካም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ -ሰዎች ሲሰበሰቡ ከመጨነቅ ጋር ተያይዞ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ትንፋሽ ቁርጥ-ቁርጥ ማለት፣ ማላብ - ነገሮች እጅግ አስከፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ በማሰብ መጨናነቅ ፣እንቅልፍ ማጣት ከላይ የተዘረዘሩትን ሶሻል ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች ይረዱታል፡፡ ሌሎች ግን ቀለል አድርገው ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ሶሻል ፎቢያ: ☞ ተማሪዎች እውቀት እያላቸው ጥሩ ውጤት እንዳይኖራቸው፤ ☞ ሰራተኞች ችሎታ እያላቸው የሚገባቸውን እድገት እንዳያገኙ፣ እንዲሁም ለሚወዱት ሰው ፍቅራቸውን መግለፅ እንዳይችሉ ያደረጋል፡፡ ሶሻል ፎቢያን ማሸነፍ ይቻላል ነገር ግን ትዕግስትና ቁርጥኝነት ይጠይቃል፡፡ በራሳችን ልናደረግ የምንችለው: 1. ሀሣብን መገምገም፦ በሶሻል ፎቢያ የሚቸገሩ ሰዎች ጭንቀትን የሚያባብሱ ሀሳቦች አላቸው፡፡ ለምሳሌ ፡- ፡"እንደ ሞኝ መቆጠሬ አይቀርም፡፡" "መናገር ስጀምር ድምፄ ይንቀጠቀጥና ራሴን አዋርዳለሁ፡፡ " "አንደፈራሁ ሰዎች ያውቁብኛል፡፡" እነዚህን ሀሣቦች መገመገምና መሞገት ጭንቀቱን ይቀንሣል፡፡ 2. ከሰዎች ጋር ሲሰበሰቡ ሌሎች ላይ ማተኮር፤ በራስ ጭንቀት ከመጠመድና ፍርሃትን ስለመሸፈን ከመጨነቅ ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትና  የሚናገሩት ነገር ላይ ማተኮር ጭንቀትን ይቀንሳል ፡፡ ሰዎች በአብዘኛው የሚያስቡት ስለራሳቸው ስለሆነ የሚገምተውን ያህል መፍራታችንም አያውቁም፡፡ 3. አተነፋፈስን ማስተካከል - በፍርሃት ጊዜ በአብዛኛው  ከላይ-ከላይና ቶሎ-ቶሎ ነው የሚተነፈሰው ፡፡ ይህ ጭንቀትን ያባብሳል ፡፡- በቀስታ በጥልቀት መተንፈስ  ረጋ ያለ ስሜትን  ይፈጥራል ፡፡ 4. አነቃቂ ነገሮች የጭንቀት ስሜትን ስለሚያባብሱ እነሱን መቀነስ፡፡ እነዚህ ተደረገው አሁንም ስሜቱ ካለ የህክምና እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!! ዶ/ር ዮናስ ላቀው t.me/inclusiveafar
0
19
ነጩ እና ጥቁሩ የዓይነ-ስውርነቶች በዓለም ላይ በከፍተኛ  መጠን ዓይነ-ስውርነቶች ከሚያስከትሉ  ምክንያቶች ሁለቱ ቀዳሚዎቹ  ነጩ እና ጥቁሩ ዓይነ-ስውርነቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ነጩ - ሞራ ግርዶሽ ሌንስ፡- የዓይን ፊተኛዉ ክፍል ዉስጥ ያለ ንዑስ-ዓይን አካል  ሲሆን - በተፈጥሮዉ ጥርት ያለ ነዉ፡፡ ስራዉ ብርሃንን  ወደ ኃለኛዉ የዓይን ክፍል - የብርሃን ግድግዳ(ረቲና) - መርቶ ማሰተላለፍ አንዱ ነዉ፡፡ ሞራ ግርዶሽ፡- ሌንስ ጥራቱን በተለያዩ ምክንያት ሲያጣ - በተለያየ መጠን ወደ ነጭነት ሲቀየር እና ዋናዉ አገልግሎቱ ሲታወክ - ሞራ ግርዶሽ ተከሰተ ይባላል፡፡ ይህ ዓይነ-ስዎርነትን ከሚያመጡ ምክንያቶች በዓለም ላይ በአንደኛ ደረጃ ይቀመጣል ፡ ይህም ከግማሽ በላይ ይይዛል፡፡ ሞራ ግርዶሽ  አብዛኛዉ  ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚክሰት ሲሆን ሌላው ደግሞ ከእድሜ መግፋት ጋር ያልተያያዘ ነዉ፤ በብዙ ምክንያት ሊመጣ ይችላል ፡ ለምሳሌ .. ከግርዶሹ ጋር አብሮ በመወለድ(ብዙ ምክንያቶች አሉት)፣  በምት ፣ እስቴሮይድ መድሃኒት ከመጠቀም ጋር የተየያዘ፣ በዉስጣዊ የዓይን ቁጣ፣… ወዘተ ሆኖም ይህ የሞራ ግርዶሽ በቀዶ-ጥገና የሚግላገሉት የዓይነ-ስዉርነት ምክንያት ነዉ፡፡  በዚህም ምክንያት ከጥቁሩ - ግላኮማ ይልቅ ነጩ-ሞራ ግርዶሽ  ለታማሚዉም  ለሀኪሙም  ቀዶ-ጥገና ከተከናወነ በኃላ ትልቅ የእርካታ እና የደስታ ምንጭ ነዉ፡፡ የሀዘን እና የብስጭት ምንጭ የሚሆነዉ ሞራ-ግርዶሹ ተጉዳኝ የዓይነ-ስዉርንት የሚያመጣ ምክንያት ካለዉ/ካሉት ነዉ….አንዱም ያ..ጥቁር-ግላኮማ ሊሆን  ይችላል፡፡ ጥቁሩ - ግላኮማ የዓይን ነርቭ፡- የዓይን ህዋሳት ከብርሀን ግድግዳ (ረቲና) ተሰባስበዉ ህብረ-ህዋስ ፈጥረዉ በኃለኛዉ የዓይን ክፍል ወደ አንጎል የሚጉሀዙበት ገመድ ነዉ፡፡ ስራዉም ብርሃንን እና ያየነዉን ምስል/እንቅስቃሴ በነርቭኛ ተርጉሞ ወደ እይታ-አንጎል ክፍል መማስተላላፍ ነዉ፡፡ ግላኮማ፡- የአይን ነርቭ መጎዳት ሲሆን ፤ የዓይናችን ነርቭ ጉዳት ለመገንዝብ ያህል በግላኮማ ምክንያት እና በሌላ ምክንያት ብለን መክፈል እንችላልን፡፡ ግላኮማ -  በጊዜ ሂደት ጉዳቱ የሚጨምር ፣ የማይድን ግን የሚታከም የራሱ አይነተኛ አጎዳድ ያለዉ፤ የራሱ አይነተኛ የዓይን -አድማስ እክል የሚያምጣ ነዉ፡፡ ለግላኮማ አጋላጭ ከሆኑት ዉስጥ ዋናው ከፍተኛ የዓይን ግፊት (ከ 21 ሚሜ.ሜር በላይ) ሲሆን ፤ ነገር ግን የግድ ከፍተኛ ግፊት ላይኖር ይችላል፡፡ ብዙ አይነት ግላኮማ አለ… በመንስኤዉ - የሚታወቅ እና የማይታወቅ፣ በእድሜ - የህጻናት ፡ የወጣቶች እና የአዋቂዎቸ፤ በማዕዘኑ(የዓይን ፈሳሽ የሚፈስበት ቦይ)- ማዕዘነ ክፍት እና ማዕዘነ-ዝግ… ተብሎ በዋናነት ይከፍላል፡፡ የህጻናት ገላኮማ፡- ከ4 ዓመት በታች ያለዉን እድሜ ክልል የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ከሌላዉ ዕድሜ የሚለየው አልፎ አልፎ የሚከሰት መሆኑ፤ ሁሌም ክፍተኛ የዓይን ግፊት መኖሩ፣ ጉዳቱ የዓይን ነርቭ ላይ ብቻ ሳሆን ሁሉም እድገታቸዉን ያልጨረሱ የዓይን ክፍሎች ላይ መሆኑ፤ ጠቁሮ ያልጠቆረ…የሚታይ ምልክቶች ማለትም ሶስትዮሽ መገለጫ ያለዉ …ማንባት፡ ብርሃን መፍራት እና የዓይን ቆብን መጭመቅ፡፡ ህክማናዉም የዓይኑን ግፊት በቀዶ-ጥግና መቀነስ ነዉ፡፡ ጉዳቱ እንዳይቀጥል ማድረግ ነዉ ህክምናዉ….የደረሰዉ ተጎዳ አይምለስም፡፡ የወጣቶች እና አዋቂዎች ግላኮማ፡- እነዚህ በጥቁር የሚመሰሉት … ሲጀመሩ ምንም ምልክት የማያሳዩ፤ በጭለማ እንደሚዘርፍ ልባ … ከፍተኛ ጉዳት  ካመጡ በኃላ ነዉ የሚታወቁት ምክንቱም የዓይን እይታን መጀመርያ ኣከባቢ ምንም አቀንሱም፡፡ የአይን አድማስ በከፍተኛ ሁኔታ ጠቦ ከነገሮች ጋር ስንጋጭ ወይም ዓይነ-ስዉርት ሲክስተ ነዉ የሚታወቀዉ… ይህ እንግዲህ በዓለም ከነጩ-ሞራ ግርዶሽ  ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ዓይን-ስዉርነትን ከሚያመጣዉ የማዕዘነ-ክፍት ግላኮማ  አይነት መገለጫ ነዉ፡፡ ይህም ዕድሜያቸዉ ከ40 ዓመት በላይ ተጋላጭ ሲሆኑ….ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነትም ይጭምራል፡፡  ለዚህም ሲባል በዚህ ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያለ ሰዉ ቢያንስ አንዴ የዓይን ምርመራ ማድረግ  ይመከራል፡፡ ተጨማሪ ተጋላጭነት ያላቸዉ ሰዎች ለምሳሌ  የቅርብ ቤተሰብ አባል በግላኮማ የተጠቃ ካለ….የቅርብ ክትትል ያሰፈልጋቸዋል፡፡ ወደ ህክምናዉ ስንመጣ ብቸኛዉ ማከሚያዉ (የማይድን ነዉ ብለናል) መንገድ የዓይን ግፊቱን ካለበት መነሻ መቀነስ ነዉ፡፡ ይህም ጉዳቱን ባለበት ማቆም ወይም ዓይነ-ስውርነትን እንዳይከሰት ማቆየት ነው፡፡  ግፊቱን ካለበት ለማዉረድ ሶስት ዓይነት ህክመና አማራጮች አሉት….እናሱም የአይን ጠብታ፣ ጨረር እና ቀዶ-ህክምና ናቸዉ፡፡ ነጩም ይዳን፤ ጥቁሩም ይታከም! ብርሃኖን ይጠብቁ፡፡ ሙሉቀን ጎ.ኃ፣ ሐኪም የዓይን ህክምና ሪዝደንት- አአዪ @HakimEthio t.me/inclusiveafar
0
20
+2
No text...
0