cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Inclusive Education - Afar Region (Channel)

A Channel for inclusive education reference materials

Більше
Рекламні дописи
336
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ህጻናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር፣ በህክምና መዳን ይቻላል! #clubfootawareness
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አካል ጉዳተኝነቱ ውጤታማ ከመሆን ያላገደው የፈጠራ ባለቤት ከማል አብዱራህማን ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ገደብ አሳሳ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የኦሮሚያ ክልልን ወክሎ የቀረበው ከማል ከገጠመው አካል ጉዳት በመነሳት ነበር ህይወቱን ለማቅናት በራሱ ጥረት ዊልቸርን እና ባጃጅ ለመስራት የበቃው፡፡ ከማል በእግር መንቀሳቀስ የማያስችል አካል ጉዳት ስለገጠመው የሚፈልገው ቦታ ለመንቀሳቀስ እና ትራንስፖርት ለመጠቀም የሰው ድጋፍ ይፈልግ ነበር፡፡ በዕለ ተለት እንቅስቃሴው ሰው ከማስቸግር እና የሰው እጅ ከማይ ለምን ከጥገኝነት የምላቀቅበት ፈጠራ ይዤ አልመጣም ብሎ ወሰነ፤ አደረገውም፡፡ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች እና ካረጀ ሞተር ከልጅነት ጀምሮ መፍታትና መግጠም ላይ የነበረውን ተሰጥኦ በመጠቀም የሚንቀሳቀስበት ዊልቸር ሰራ፡፡ ዊልቸር ሰራሁ ብሎ ረክቶ አልተቀመጠም፡፡ ከልመና የሚያላቅቀኝ ዘላቂ ሥራ መስራት የሚያስችለኝ ለምን ባጃጅ አልሰራም ሲል በድጋሚ አሰበ፡፡ ጥረቱን ቀጠለ። በመጨረሻም ሁሉም ነገሩ ለአካል ጉዳተኛ ምቹ የሆነ ባጃጅ ሰራ፡፡ በአሁን ወቅት አቶ ከማል የሁለት ባጃጅ እና አንድ ዊልቸር ባለቤት ነው፡፡ እራሱ በሰራቸው በእነዚህ ባጃጆች በቀን ቢያንስ እስከ 500 ብር ድረስ ገቢ ያገኛል፡፡ በዚህም እራሱን ከጥገኝነት ማላቀቅ ችሏል፡፡ ዊልቸር ከራሴ አልፌ እንደኔ ችግር ውስጥ ለነበሩ ሁለት ሰዎች ሰርቻለሁ፡፡ እነሱም ቀደም ሲል እኔ ካየሁት አይነት ስቃይ ተገላግለዋል ሲል ያብራራል፡፡ አካል ጉዳተኝነት ማለት አለመቻል አይደለም የሚለው ከማል በቀጠይ ለሥራው አመቺ የሆነ ቦታ ከተመቻቸለት የዊልቸር መገጣጠሚያ እስከመክፈት የደረሰ ህልም እንዳለው ይናገራል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡ @inclusiveafar
Показати все...
የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት (Cognitive development of child) እንደ ስዊዝ ተወላጁ ስይኮሎጂስት ፒያዤ (Jean Piaget) መሰረት የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተለያዩ ማነቃቂያዎች (stimulus) ምላሽ በመስጠት (response) እና በመላመድ ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ (awareness) እና የባህሪ ግንባታ እንዳለው ይገልጻል። የአንድ ልጅ የባህርይ ጸባይ የሚመሰረተው ከአካባቢው ጋር ባለው ቁርኝት ሲሆን፤ ይህም በልጁ የአዕምሮ ግንዛቤ ንድፍ (Schema) ለይ የሚመሰረት ነው። በዚህም መሰረት ልጆች 4 የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት ደረጃዎች አላቸው፦ 1. ሴንሰሪሞቶር| Sensorimotor stage (ከ ተወለደ እስከ 2 አመት) በዚህ ጊዜ ጨቅላው ልጅ ከአካባቢው ጋር የሚዛመደው በእንቅስቃሴ እና በስሜቶች ሲሆን፤ ለተለያዩ ማነቃቅያዎች እንቅስቃስያዊ ምላሽ ይሰጣል። እያደገ ሲመጣ (ወደ 2 አመቱ ሲጠጋ) የነገሮችን /ቁሶችን መኖር ይገነዘባል፤ እናም ህጻኑ የቁሶችን ምስል በአዕምሮው ጠብቆ ማቆየት ይጀምራል እና ከእይታው ውጪም ቢሆን ቁሱ እንዳለ መገንዘብ ይችላል፣ ለመፈለግም ይጥራል። 2. ፕሪ ኦፕሬሽን| Pre-operational stage (2–6 አመት) ህፃኑ የነገሮችን፣ ቁሶችን እንዲሁም ክስተቶችን አዕምሯዊ ምስሎችን ከመፍጠር ባሻገር፤ ለሌላ ጊዜ እንዲጠቀሙበት በአእምሮ ውስጥ በማስቀመጥ ምሳሌያዊ ግንዛቤን ያዳብራል። ልጁ እንቅስቃሴ እና የቋንቋ እድገት ክህሎቶችን በማዳበር የአካባቢያዊ ተግባቦት ችሎታ ያዳብራል። የልጁ አመክንዮ ግንዛቤ (logical thinking) ገና ያልዳበረ ስለሆነ ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ለማገናዘብ አይችሉም፤ ስለዚሀ ራስ ተኮር (ego centric) እና ምትሀት ተኮር (magical thinking) አስተሳሰብ ይዘው ያድጋሉ። ሆኖም ግን በመልካም ወይም በመጥፎ ነገር ላይ በመመርኮዝ የሞራል አስተሳሰብ ግንዛቤ ማዳበር ይጀምራሉ። 3. ኮንክሪት ኦፕሬሽን| Concrete operational stage (7-11 አመት) በዚህ እድሜ ዉስጥ የሚገኙ ልጆች አመክንዮአዊ (logical) እና ምክንያታዊ (Rational) አስተሳሰብን ያዳብራሉ። የራስ ተኮር አስተሳሰብ በእጅጉ ይቀንሳል፤ ብሎም ፅንሰ-ሀሳባዊ (conceptual) ግንዛቤዎች የጎለብታሉ፣ የሌሎችን አስተያየት መገነዘብ ይጀምራሉ። የቃላት፣ የሰውነት ተግባቦትን በደንብ ያለያሉ፤ በአጭሩ ተግባራዊ ይሆናሉ። 4. ፎርማል ኦፕሬሽን| Formal operational stage (ከ 12 አመት በኋላ) በዚህ እድሜ ለይ ያሉ ልጆች ረቂቅ አስተሳሰብን (ሀሳቦችን መመርመር እና የንድፈ-ሀሳቦችን የማመንጨት የማስተናገድ ችሎታ)የአመክንዮ አስተሳሰብ እድገት (ከአንድ አጠቃላይ ሃስብ በመነሳት ወደ ውስን የማውረድ ችሎታ (deductive reasoning)፣ እና ፅንሰ-ሀሳባዊ አስተሳሰብ ትርጉም መስጠት ግንዛቤ ያዳብራሉ። ሃላፊነት መውሰድ የሚላማመዱበት ወቅት ነው። ስለዚህ ወላጆች የልጆቻችሁን የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት በዚህ መልክ መከታተል ይረዳችሁ ዘንድ እንደተጠቀሙበት እመክራለሁኝ። ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (ሳይካትሪስት) @melkam enaseb
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የአዕምሮ ህሙማንና የሚደርስባቸው መገለል - ለችግሩም የመፍትሄ አቅጣጫ! የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል በአለም አቀፍ ደረጃ በየትኛውም የማህበረሰብ ክፍል በስፋት የተሰራጨ ችግር ከመሆኑም ባሻገር ይሄም በጤና ባለሙያዎች ዘንድም የሚታይ አመለካከት ነው። የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግለል በታካሚዎች ዘንድ ከማህበረሰቡ እራሳቸውን እንዲያገሉና የህክምና እርዳታ እንዳይሹ የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ይሄንንም በማህበረሰቡ የሚደርስባቸውንና እንደግለሰብ የምናደርስባቸውን ማግለል ለመከላከል ከመንቀይሰው ስልት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:- 1. ማግለልን መቃወም "የአዕምሮ ህመምተኞችን የማግለል ተቃውሞ ዘመቻ" ማድረገ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የሚደረገውን ማግለል ለመቀነስ ይረዳል። 2. ማስተማር በማስተማር እያንዳንዱ ሰው ስለ አዕምሮ ህመም መንስዔ፣ የህመሙ መገለጫ ምልክቶች፣ የህክምና እርዳታና ተያያዥ ውጤቱን በማሳወቅ ሰዎች በአዕምሮ ህመምተኞች ላይ የሚያደርሱትን ማግለል መከላከል እንችላለን። 3. የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግኘት በተለያዩ የአዕምሮ ህክምና በሚሰጥባቸው ቦታዎችና የማገገሚያ ማዕከላት ብሎም መርጃ ማዕከላት (ሜቄዶኒያንና ጌርጌሴኖንን) እና የተለያዩ የአዕምሮ ህክምናና የሱስ ማገገሚያ ማዕከላት ሄደን ህመምተኞችን መጎብኘት ስለህመሙ ስለህመምተኞችና የሚደርስባቸውን ጫና ለመረዳት ያስችላልና የማግለል ሁኔታውን በመቀነስ የራሱን ሚና ይወጣል። እናንተስ ስለህሙማኑ ምን አሰባችሁ? የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል ይቁም! ቃልኪዳን ዮሐንስ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ) @melkam_enaseb
Показати все...
ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (Autism Spectrum Disorder) የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የአንድን ሰው ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት እና ባህሪ የሚጎዳ እክል ነው። እነዚህ እክሎች መለስተኛ፣ ከባድ፣ ወይም መካከለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የቡድን ስም ሲሆን በውስጡ አምስት እክሎችን የያዘ ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ባለሙያዎች የሚጠቅሷቸው የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር አይነቶች አሉ። እነዚህም፦ 1.አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome) 2.ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder) 3.ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder) 4.ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder) 5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome) ናቸው። 1. አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome) ይህ የኦቲዝም አይነት ቀለል ያለ የሚባለው ነው። አስፐርገርስ የሆኑ ልጆች በጣም አስተዋይ እና የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡ - እነርሱ በሚወዷቸው ወይም በተሳቡባቸው ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።   - እነዚህ ልጆች ማኅበራዊ ክህሎታቸው ላይ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል። - በተጨማሪም የንግግር እና ቋንቋ ክህሎታቸው ላይ እምብዛም እክል አይታይባቸውም።   2. ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder) - ይህ እክል ከአስፐርገርስ ሲንድሮም ካጋጠማቸው ልጆች የከፋ ሲሆን ነገር ግን ኦቲስቲክ ዲስኦርደር ካላቸው ልጆች የከፋ አይደለም፡፡ 3. ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder) - ይህ የቆየ ቃል ያለው ከአስፐርገርስ እና ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር የበለጠ እክል ነው፡፡ - ይህም ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶችን ያጠቃልላል ግን በጣም ኃይለኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። - ይህም የልጆችን ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት፣ ባህርይ፣ ስሜት እና ጨዋታ የሚጎዳ እክል ነው። 4. ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder) ይህ እክል እጅግ በጣም ከባዱ እና እጅግ የከፋው የስፔክትረም ክፍል እንደሆነ ይገለፃል። - ይህ እክል ያጋጠማቸው ልጆች በመደበኛነት የሚያድጉ እና ከዚያም ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 4 ባለው መካከል ሲሆን ብዙ ማህበራዊ፣ ቋንቋ እና አእምሯዊ ክህሎቶችን በፍጥነት የሚያጡ ልጆች ናቸው። - አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ልጆች የሚጥል ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። 5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome)   ሬት ሲንድሮም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ነው? ሬት ሲንድሮም ያለባቸው ሕፃናት ብዙውን ጊዜ ከአቲዝም ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ባሕሪዎች አሏቸው። ባለሙያዎቹም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር መካከል ካሉት ቡድኖች ውስጥ ይመድቡት ነበር፤ አሁን ግን በጄኔቲክ ሚውቴሽን ምክንያት እንደሚከሰት ስለታወቀ በማለት እንደ ASD አይቆጠርም፡፡ በማሕሌት አዘነ (Speech & Language Therapist) @melkam_enaseb
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🔊 ዳውን ሲንድረም(Down syndrome) ምንድነው ❓️ ክፍል 1 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘 🔴 March 21 : የአለም የዳውን ሲንድርም ግንዛቤ ማስጨበቻ ቀን እንደሆነ ያውቃሉ❓️ 🌍 በአለም ላይ ከሚወለዱ 800 ህፃናት በአንዱ ህፃን ላይ ዳውን ሲንድረም  ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ❓️ ♀️♂️ ማንኛዉም ሰዉ ገና በማህፀን ዉስጥ ሲፀነስ 23 ዘረመል ከእናቱ 23 ዘረመል ከአባቱ ወስዶ ሰዉ እንደሚሆንስ ያውቃሉ❓️ ✍️  በሰውነታችን ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ ህዋሶች 23 ዘረመል ከእናት♀️ ተጨማሪ 23  ዘረመል ከአባት ♂️ወስደው ይሰራሉ :: ስለዚህ ባጠቃላይ አንድ ሰዉ 46 ዘረመሎች በ እያንዳንዱ ህዋስ ዉስጥ አለሉት ማለት ነው❗️ ✍️ ሆኖም አልፎ አልፎ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት በተለያየ ምክንያት ሳይሳካ ሲቀር አንደኛ ዘረመል ቦታ(ላይ ሁለት ከመሆን ይልቅ ሶስት ዘረመሎች ይሆናሉ:: ✍️  ከ 46ቱ ዘረመሎች በ 21ኛው ዘረመል ቦታ ላይ ሁለት ዘረመል መሆን የነበረበት ቦታ ላይ ሶስት ዘረመል ሆኖ ሲገኝ ዳውን ሲንድሮም(Down syndrome) ያለው ልጅ ሊፈጠር ይቺላል:: 👉 ስለዚህ በ አጭሩ ዳውን ሲንድረም ማለት የዘረመል አፈጣጠር ችግር ሲሆን ዘላቂ የሆነ የተለያዩ የጤና እክሎች ሊያመጣ የሚቺል ተፈጥሮ ነው :: 👉 ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እሰከ ከባድ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ 🔺የአይምሮ የእድገት ዉስንነት 🔺 የአየር ቱቦ እና አተነፋፈስ ችግር 🔺 የልብ አፈጣጠር ችግር 🔺የሆርሞን ችግሮች 🔺 የደም ችግሮች 🔺የአንጀት ችግሮች #Down #syndrome ምልክቶቹ ምንድናችው❓️ 👉 ዳውን ሲንድረም ያለበት/ባት ህፃን የሚከተሉትን አካላዊ ምልክቶች ይታዩባቸዋል:: ለምሳሌ 🔘 ጠፍጣፋ እና ለየት ያለ የፊት ገፅታ 🔘 ከፈት ያለ አፍ እና ተለቅ ብሎ የሚታይ ምላስ 🔘 አጭር አንገት 🔘 ዝቅ ያለ ጆሮ 🔘 የአይን ቅድ(አከፋፈት) አቀማመጥ ወደ ላይ ከፍ ማለት 🔘 የአይን ሽፋሺፍት ቆዳ መብዛት 🔘 ደካማ/የላላ ሰውነት ጡንቻ 🔘 አጭር እና ትንሽ መዳፍ 🔘 አጫጭር ጣቶች 🔘 አንድ ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመር እና የመሳሰሉት ሊኖሩት ይቺላሉ 👉 ኦቲዝም እና ዶውን ሲንድረም ልዩነታቸው ምንድነው❓️ 👉 የዳውን ሲንድረም ሕክምናው ምንድነው ❓️ መልሱን ነገ በዝህ በቴሌግራም ቻናችን ላይ ያገኙታል❓️ 👉 በቴሌግራም ቻናላችንን Join በ ማድረግ እንዲሁም የፌስ ቡክ ገፃችንን like & follow በማድረግ ይከታተሉን:: አዘጋጅ : ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር) 🛑 ዶ/ር ፋሲልን ስለ ዳውን ሲንድረም እና የጤና እክሎቹ ወይም ከዝህ ዉጭ ላሉ  የህፃናት ጤና የሚመለከቱ ነገሮችን ማማከር ወይም ሕክምና ማድረግ ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ/Application/ ከ playstore/Googleplay አውረደው ማማከር ይቺላሉ:: አጠቃቀሙን ለመረዳት በነፃ 9394 ይደውሉ እና ይጠይቁ :: 🛑 መተግበሪያውን ወደ ስልኮ ለማውረድ እና ለመጠቀም ከፈለጉ ከታች ያለውን link ተጭነው ይክፈቱ:: በመቀጠልም down load ያርጉ:: 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient 🛑 በአካል ሆስፒታል መተው የ ህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ማግኘት እና ሕክምና ከፈለጉ በከታች ባሉት ስልኮች ቀጠሮ ያስይዙ:: ☎️ 0984650912 👨‍👩‍👦 ለእርስዎ ፣ለልጆዎ እና ለቤተሰቦዎ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የጤና ፣የህፃናት አስተዳደግ እና አመጋገብ መረጃዎችን በየጊዜው እንደደርሶ ከፈለጉ ከታች ያለውን የቴሌግራም ማስፈንጠሪያ በመጫን ቀጥሎም የቴሌግራም ቻናላችንን ላይ join በማድረግ ቤተሰብ መሆን እና ማንበብ ይችላሉ :: 💯 በእርግጠኛነት ታተርፉበታላችሁ ‼️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil 🔷 FB:fb.me/drfasilpediatrician
Показати все...
WeCare ET Patient - Apps on Google Play

Search and book verified Health Professionals In Ethiopia.

Фото недоступнеДивитись в Telegram
Talking to other people can help reduce stress and help you find ways to cope better. That may not be easy: you may not feel like being socially connected when your mood is low, but do let family and friends know that they can help by reaching out to you. Take a break, let’s talk. #WHO @inclusiveafar
Показати все...
በኢትዮጵያ ከ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለባቸዉ ተነገረ የአዕምሮ እድገት ውስንነት የዓለም ዳውንሲንድረም ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአለም አቀፍ ደረጃ ማርች 21 ወይም መጋቢት 12 በአለም ለ12ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለ8ተኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በተያዘው ዓመትም እሁድ መጋቢት 10 በእግር ጉዞ ይከበራል። ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር፣ ከኢፌዲሪ ሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን "ከእኛ ጋር ስለእኛ እንስራ " በሚል ዓለም አቀፍ መሪ ቃል ቀኑ ተከብሮ እንደሚውል ተገልጿል።በኢትዮጵያ ከ4 እስከ 5 ሚሊየን የሚሆኑ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ የፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ቦርድ ፕሬዝዳንት የሆኑት ምህረት ንጉሱ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረተ ከአለም ህዝብ በአማካይ 3 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለባቸው ይገለጻል።የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ስልጠና የሚወስዱበት ሆነ የሚውሉበት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ተቋማቶች ውስን ከመሆናቸው በተጨማሪ ዋጋቸው ውድ በመሆኑ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። በመኖሪያ ቤታቸው የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች በማበረታታት ወላጆች ትልቁን ሚና መጫወት እንዳለባቸው እና ማህበረሰቡ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ እኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማወቅ አለበት ሲሉ ምህረት ንጉሱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...