cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የበገና መዝሙር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . @Begnamzmure የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
576
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:38
Video unavailableShow in Telegram
ማርቆስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁴ ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ³⁵ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። ³⁶ ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ³⁷ ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ³⁸ በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል። https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
00:20
Video unavailableShow in Telegram
✝ማቴዎስ 5✝ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ✝⁴³ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። ⁴⁴-⁴⁵ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ⁴⁶ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ⁴⁷ ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ⁴⁸ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።✝ https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ:" ሰቆቃው ኤርሚያስ 1:10 የዮሐንስ ራእይ 12 12፤ ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና። 13፤ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
​​"ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን"- ቅዱስ ሲኖዶስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ "የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ! ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"        ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል። በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ
Show all...

ሀይማኖት፣ ፍቅር፣ ትህትና ከሌላችሁ ጨው እንደሌለው ምግብ ናችሁ። ሰው ሆይ እስከ መቼ ትሰንፋለህ ጠዋት የተመገብከው ሲመሽ አሠር አንደሚሆን አታቅምን ምሽት የተመገብከው ጠዋት አሰር የሚሆን አይደለምን በመቃብር ውስጥ ያንተ መትላት ከቆሻሻ ይልቅ ይበልጣል ፈጥኖም ይደረጋል ሩቅም አይደለም። ከዚህ በኋላ ጨለማ ይጠብቅሀል ይህ ከሆነ እንዳንተ ያሉ ሠዎችን ለምን ትንቃለህ ለምን እንዳንተ ያለውን ሰው አታከብረውም ለምን እንደራስህ አድርገህስ አቶደውም ነገር ግን ከእግር  ጥፍርህ እስከ ራስ ፀጉርህ ትዕቢት የተሞላህ አንተ በሀሣብህ እስከ ደመናዎች ከፍታ ድረስ ከፍ ከፍ አልክ እነሆ የሚያስፈሩ ትዕቢታቸው የጣላቸው ጥቁር የሆኑ መልአክ ወዳሉበት ጥልቅ ትወርዳለህ ። @raiye_mariyam
Show all...
00:38
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ተወዳጆቼ ፡ ሆይ! #በኢየሱስ_ክርስቶስ ፡ ስም ፡ እለምናችኋለሁ! የመዳናችሁን ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ ቸል ፡ አትበሉ!! +ርእሰ-መነኮሳት አባ እንጦንዮስ [እንጦንዮስ እንጦንስ ፣ እንጦኒ] በኹሉም ቦታ ለሚኖሩ ዝርዋን ወንድሞች ከላከው ሁለተኛ መልእክት... @raiye_mariyam
Show all...
*ነፍስህን ይፈልጓታል* *መልካም ንባብ!* *ምስጢሩን ይግለጥልን* ✝️ (ሉቃ 12 ) ------------ 16 *ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት።* 17 *እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ።* 18 **እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤* 19 *ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።** 20 *እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።* 21 *ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።* ✝️ይገርማል! ይህን ታሪኩ የተነገረለት ሰው ሁሉ ነገር የተ ሳካለት ትርፋማ ሰው፣ እርሻው እጅግ ፍሬያማ የሆነችለት ሰው: ብሎ ነው ጌታችን የገለጠው። ✝️እናም ይህ ሰው እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ትርፋማ ነበር። ✝️አሁን ወደ ሜዳ ወጥቶ ከትርፋማነቱ የተነሳ ደስታውን መ ቆጣጠር አቅቶት ብቻውን ያወራ ጀመር፦ ✝️ *ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ* *ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ* ። ✝️ *ይገርማል! ሰውየው ሥራ መስራቱ መልካም፣ ትርፋማ መሆኑ መልካም ነበር: ምን ያደርጋል! መመጻደቁ እና ነፍሱን መርሳቱ አከሰረው እንጂ።* ✝️ *በሀሳቡ እንኳን እግዚአብሔር ከሰጠው ፍሬ ላይ አስራት ሊያወጣ አላሰበም፣ መንገድ ላይ ለወደቁት ችግረኞችም አላሰበም፣ለድሆች ዘመዶቹም አካፍላለሁ አላለም...በቃ ሀሳቡ ሌላ መጨመር ...እና ነፍሴ ብይ፣ ጠጭ እያለ ስለ ምግብ እና መጠጥ ሆኖ ነበር!* ✝️ *ይህን ሰው የመሰሉ ብዙዎች ዛሬም ድረስ በየሰፈሩ አሉ። አንዱን ይዘው በተሰጣቸው ሳያመሰግኑ፣ የእግዚአብሔርን አስራት ሳያወጡ ሌላው የሚያምራቸው...ሀሳብ ንግግራቸው ስለ ራሳቸው ብቻ ለዚያውም ስለ ሥጋ ብቻ የሆነ....ከዚህ ይሰውረን።* ✝️ *እናም ስለሚሰራው ጎተራ፣ ስለሚበላው ምግብ፣ ስለሚጠጣው መጠጥ እያሰበ ሲደሰት: በዚያችው ደቂቃ እግዚአብሔር መጣ፣ ነፍስህ በዚህች ሌሊት ትወሰዳለች አለው። ጨምሮም ይህ ያጥራቀምከው ሁሉ ለማን ይሆናል???? አለው። ተናግሮም አልቀረ ነፍሱን በዚያችው ቅጽበት ወሰዳት!* ✝️ *የዘራውን ሳያጭ ድ: ያከማቸውን ሳይበላ: የቀዳውን ሳይጠጣ በሞት ተነጠቀ። የምድሩንም የሰማዩንም አጣ። እኔ ጀግናው! እኔ ትርፋማው! ...ሲል የነበረው ሰው ከሰረ! እግዚአብሔር አምላካችን ከዚህ ይሰውረን!* ✝️ *ወገኖቼ ሁሉ ያልፋል። በተሰጠን ፍሬ እግዚአብሔርን እናክብርበት። እርሱ እግዚአብሔር ከሰጠን ላይ ለእርሱ ለእግዚአብሔር አስራት እናውጣ።ቤተ ክርስቲያንን እናስባት! በየስፍራው በግፍ ተፈናቅለው፣ ጎዳና የወደቁትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን፣ ልጆቻችንንም እናስባቸው። በተሰጠን ደግሞ እናመስግን ለሌሎች ማካፈልን፣ ድሆችን ማሰብን ህይወታችን እናድርግ። ለብዙ ዘመን የሚበቃኝ አለኝ ልብላ ልጠጣ እያልን እንደዚህ ሰው እንዳንከስር በማስተዋል እንኑር። በዚህች ሌሊት ነፍስህን እወስዳታለሁ ተብለን ድንገት ወደ መሬት ከመሄዳችን በፊት እናስብበት: አደራ! መንፈሳዊነት ይህ ነውና።* ✝️ *የመስቀለ ኢየሱስ በረከት በየቤታችን ይግባ።* ✝️ *ብሩህ ቀን* ✝️
Show all...
04:23
Video unavailableShow in Telegram
Show all...