en
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Show more
4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
https://t.me/EOTC2921 🌾✞ #ማርያም_አርጋለች ✞🌾 ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪) የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = =

☞❀በ69 ዓ.ም. ያረፈው ከ72ቱ አርድዕት የኾነው የአንጾኪያ የመጀመሪያው ጳጳስ ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩ የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮ የተከናወነ በዓለ ዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውን “ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” (Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary) በሚል ርዕስ ሲጽፍ የዚኽ መጽሐፍ ቅጂ በታችኛው ግብጽ ይነገር በነበረው በቦሃይሪክ ቅጅ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጻፈው ተገኝቷል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፍ ላይ ያንብቡ፨ ☞❀ቅዱስ ሚሊቶ በምዕራብ አናቶሊያ በሲሚርና አጠገብ በሳርዴስ ጳጳስ የነበረ ሲኾን በግሪክ (Μελίτων Σάρδεων Melíton Sárdeon) ሲባል ዕረፍቱም በ፻፹ (180) ዓ.ም ነው፤ ሊቁ ጀሮም የብሉይ ኪዳን ቀኖናን ሚሊቶ ሠርቶ እንደነበር መስክሮለታል፡፡ የጻፋቸውም መጻሕፍት ዝርዝር አውሳብዮስና ጀሮም ጽፈውት እናገኛለን፡፡ ብዙ መጻሕፍት ሲኖሩት በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ኅልፈተ ሕይወትና አካላዊ ዕርገት አስመልክቶ "የሳርዲሱ ቅዱስ ሚሊቶ የቡርክት ማርያም ኅልፈተ ሕይወት ትምህርት" The Passing of Blessed Mary) በሚል ርዕስ ርሱም እንደ ሐዋርያትና ሰባ አርድእት ጽፏል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ በነገረ ማርያም በሊቃውንት ተተርጉሟል። ☞❀በ380 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (Timothy of Jerusalem) ሲገልጽ “Wherefore the Virgin is immortal…” (ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም. ጀምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት ክቡር ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ ስፍራ አለችና ነው፡፡ ☞❀ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ400 ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል። ☞❀የሚገርመው ቅሪቶች ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን የሚልና የሚሞክር ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ የቅድስት ድንግል ማርያም አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ ነው፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡ ☞❀ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች ከዕውቀት የራቁ መናፍቃን የካዱትን ይኽነን እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ፦ "Elijah was transported body and soul in a chariot of fire; ...he was not buried in any Church bearing his name,…It is for this reason, we believe, that the pure and immaculate embodiment of the Mother of God, the Virgin Mary, the Temple of the Holy Spirit, that is to say her saintly body, was carried up to heaven by the angel." (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን) በማለት ጽፏል (Heinrich Bullinger, cited in Thurian, page 89, 197, 198) ☞❀ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ ያጋልጥባቸዋል፡፡ ☞❀ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ከሚታሰብባቸው ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት ይገኛሉ (Columbus World Travel Guide, 25th Edition) 🙏እመቤታችን ሆይ ከልጅሽ መንግሥት ለይቶ ሳጥናኤል ከሰራዊቱ ጋር ወደ ሚገባበት ዘላለማዊ እሳት ውስጥ ከሚያስጥል የሃይማኖት ክሕደት እኛ ልጆችሽን በምልጃሽ ጠብቂ አሜን🙏 [ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

#የቅድስት_ድንግል_ማርያምን_እውነተኛ_ዕርገት_ክደው_ለሚያስክዱ_በዘመናችን_ለተነሡ_ሐሰተኞች_የተሰጠ_ምላሽ ☞❀ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ሥር በአደራ የተቀበለ ፲፭ ዓመት ከርሷ ጋር የኖረ በ፷፬ ዓመቷ የኾነ ዕረፍቷን፣ ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን፣ ዕርገቷን በዐይኑ ያየው ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም የበቃች የአምላክ ታቦት ካረገች በኋላም በሰማያት ያላትን ታላቅና ፍጹም ክብር በራእ ፲፩፥፲፱ ላይ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ከተናገረ በኋላ በተከታይነት አሕዛብንም ኹሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች ርሷ በሰማይ ፀሓይን ተጐናጽፋ፣ ጨረቃን ተጫምታ፣ ከዋክብትን ደፍታ እንዳያት ጽፏል፡፡ ☞❀ዮሐንስ የአምላክ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያምን በዕርገቷ በሰማያት ያላትን ክብር በዐይኑ ዐይቶ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ሲጽፍልን፤ ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ዳዊት ደግሞ አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” በማለት ክብር ይግባውና ልጇ በሥልጣኑ አስቀድሞ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ለዐይን ቅጽበት እንኳን ወዳልተለየው ወደ ጌትነቱ ዙፋን ወደ ሰማይ እንዳረገ ኹሉ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችው ታቦቱ ቅድስት ድንግልም በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ እንደምታርግ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ ☞❀በዚኽ አማናዊ ምስክርነት በሰማይ ዮሐንስ ያያት ታቦት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ያረገችው የአምላክ ታቦት ንግሥተ ሰማያት ወምድር ቅድስት ድንግል ናትና ኢትዮጵያዊዉ ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ “ወታቦተ ራእየ ምስጢረ ኅቡአቲሁ ለዮሐንስ አቡቀለምሲስ ረኣዬ ኅቡአት” (የተሰወረ ነገርን የሚያይ የራእይ አባት የዮሐንስ የምስጢራቱ ምስጢር ራእይ ታቦት አንቺ ነሽ) በማለት በትክክል ገልጾታል፡፡ ☞❀ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ ፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ተጠቅሷል። ☞❀ነቢዩ ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡ ☞❀ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ናትና በመቃብር ፈርሶ መቅረት አይስማማትም። ☞❀አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ጀርባዋ፤ ብሩሃት የሚኾኑ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን ነሥቶ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ☞❀የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የነበረ አስተምህሮ ሲኾን ይኽን ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈው በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ነው ብሎ መጻፍ የመጨረሻው የአለማወቅ ጥግ ነው ቢባል አያስከፋም፨ ☞❀ዮሐንስም የዕረፍቷንና የዕርገቷን ነገር በዐይኑ በማየቱ ስለአምላክ እናት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምስክርነት (The Account of St. John the Theologian of the Dormition of the Holy Mother of God) በሚል ርዕስ የጻፈው ሲኾን፤ ይኽም ጽሑፉ በእኛ በብራና በሚገኘው በነገረ ማርያም መጽሐፍ ላይና በመጽሐፈ ፍልሰታ ላይ በቀደምት መተርጒማኖቻችን የተተረጐመልን በመኾኑ ይኽነን የተቀደሰ ታሪክ ቀደምት የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን አስቀድማ አግኝታዋች፤ ይኽ በግሪክ ቋንቋ ተጽፎ የሚገኘው የዮሐንስ ምስክርነት አስቀድሞ በሱርስትና በዐረብኛ ቋንቋ የተተረጐመ ሲኾን በኋላም ወደ ተለያዩ የዓለም ቀደምት ቋንቋዎች ጽሑፉ ተተርጒሟል፤ በዚኹ ምዕራፍ በክፍል ኹለት ላይ ከጽርዕ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ተጽፎ ያለውን ሙሉውን ምስክርነት ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ ተርጉሜዋለኹና ያንብቡ። ☞❀የአርማትያሱ ዮሴፍም ከጌታ ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ያልተለየና ዐብሯቸው የነበረ በመኾኑ የቅድስት ድንግል ማርያምና ዕረፍትና ዕርገት በዐይኖቹ በማየቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገትን ርሱም እንደ ዮሐንስ “ዮሴፍ ዘአርማትያስ የጻፈው የቡርክት ድንግል ማርያም ኅልፈት” (Joseph of Arimathea, The Passing of the Blessed Virgin Mary) በሚል ርዕስ ከእመቤታችን ዕርገት በኋላ የጻፈላት ሲኾን ይኽም አስቀድሞ በላቲንና በሱርስት ቋንቋዎች ተተርጒሞ ይገኛል፤ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ያለውን የአርማትያሱ ዮሴፍን ሙሉውን ምስክርነት በነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ በአማርኛ ቋንቋ አስፍሬዋለኊ፡፡

~~~✞ #ግጥም ✞~~~ https://t.me/EOTC2921 🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾 መለኮት ተገለጦ ብርሃንን አበራ፣ በተቀደሰችው የታቦር ተራራ። የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት፣ በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት። ዮሐንስ ጴጥሮስ ያዕቆብን ጠርቶ ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አሥነስቶ ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ በሕያው መለኮት በብርሃናት ደምቆ አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና፣ የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና። እርሱን ብቻ ስሙት እስከ ዘለዓለም፣ ሕይወትን በእርሱ እንጂ ያለርሱ አትድኑም። ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ፣ አምላክነቱንም በተግባር ነገረ። "...ታቦርና አርሞንዔም በስምኽ ደስ ይላቸዋል፤ ክንድኽ ከኀይልኽ ጋራ ነው፤ እጅኽ በረታች ቀኝኽም ከፍ ከፍ አለች።" መዝ ፹፰፥፲፪ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯