en
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Show more
4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
  🍀✞ #ቡሄ_በሉ ✞🍀 ቡሄ በሉ (2) ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆ    የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባ ረቀው ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን (2) ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) በተዋህዶ ልጆች ሆ ወልድ የከበረው ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደ ማርያም ነው ሆ ቡሄ በሉ (2) የአዳም ልጆች ሆ ብረሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን ለኛ_መጣልን(2) አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አክስቴም አለኝ ለከት ሆ ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ   #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ  ያላችሁ ሆ ባህላችሁን ሆ ያዙ ሆ አጥብቃችሁ ሆ ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ    #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)     ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)  ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በጋሽዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት  ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በእማምዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና       #እንዲሁ_እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅርያ ድርሳችሁ #ክርስቶስ_በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ #እንዲሁ_እንዳለን በፍቅር አይለየን #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅር ያድርሰን #አማኑኤል_በቀኙ በፍቅር ያቁመን  #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርገን የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት እንቁም በሃይማኖት ፀንተንበትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት #ባህላችንን_የአባቶች_ትውፊት (3) ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን #ለደብረ_ታቦር በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!!! እነሆ በዓሉን የሚመለከት ድንቅ ዝማሬ፦ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Orthodox2921 Group

🌾✞ #ስለ_በዐለ_ደብረ_ታቦር ✞🌾 በብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገሪማ (ዶክተር) የተሠጠ የሚያስደንቅ አስተምሮ ማንም ሳያነብ እንዳይቀር፤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

​ነሐሴ 13/12/2010 ዓ.ም #ደብረ_ታቦር ✞ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30 ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51 #ምስባክ፦ መዝ 88፥12-14 ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኀይል #ትርጉም፦ ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል ስምህንም ይመሰግናሉ ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው #ወንጌል፦ ሉቃ 9÷28-38 #ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ

🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾 ❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9) ❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው። ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡ ❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት፦ መጀመሪያ አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡ ❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡ ❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ሲኾን ሙሴና ኤልያስም ጌታቸው ፈጣሪያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በተራራው ላይ መስክረዋል፡፡ ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡ ❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው። ❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡ ❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡ ❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦ 1⃣ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት 2⃣ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመን የነቢያትንና የሐዋርያትን ክብርና ምልጃ እንደምታስተምር ለማሳየት ነው፡፡ 3⃣ ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ 4⃣ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት 5⃣ ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡ 6⃣ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ 7⃣ ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨ 8⃣ ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨ 9⃣ ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡ ❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡ ❖ ሌላው “ብሑዕ” ማለት የቦካ ማለትን ሲያመላክት በዚኽ ቀን የሚጋገረውን ሙሉሙል ዳቦ የሚያመለከክት ነው፡፡ ❖ በዚህ በዓል የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ነሐሴ 12 ማታ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡ ❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡ [በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው] ✍መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ t.me/EOTC2921

❖ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ” (ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣ ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡ ❖ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በአርጋኖን መጽሐፉ ላይ የዜና ጽንሰቷን ነገር ሲገልጽ “ወይእዜኒ ኦ ውሉደ እግዚአብሔር ወማኅበረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናስተብፅዖሙ ለሐና ወለኢያቄም...” (አኹንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት? ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት?) በማለት የፅንሰቷን ነገር አድንቋል። ❖ ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ በቊ ፴፰ ላይ “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ” (ድንግል ሆይ በኀጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለሽም በሕግ በኾነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ) በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ ኀጢአት ካመጣው መርገም በፅንሰቷ ጊዜ እንዳትያዝ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀ መኾኑን ተናግሯል፡፡ ❖ “ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡ ❖ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦ “ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ” (ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡ ❖ ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል፤ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል፡፡ ✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯