የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Open in Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Show more4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
4 374
ረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡
[የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከማያልቀው በረከትሽ አብዝተሽ አሳድሪብን]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
፡ ፡ ፡ ፡ ፡
፡ ፡ ፡ ፡ ፡
፡ ፡ ፡ ፡ ፡
✞✞✞ #አስተርእዮ_ማርያም ✞✞✞
፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡
ወር በገባ በ21ኛው ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የምናስብት ቀን ነው፡፡ ለመሆኑ ምክንያቱ ምንድር ነው?
:
ምክንያቱ የእመቤታችንን በዓለ እረፍት የምናስብት በመሆኑ ነው፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር 21
እሑድ ነው ።
:
#ጥር_21 አስተርእዮ ማርያም ይባላል፡፡ አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፡ ተገለጠ
ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ
የተገለጠበት(የታየበት) ፣አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት
በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
፡
የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን
አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን🙏አሜን🙏
4 374
#የእመቤታችን_በዓለ_ዕረፍት
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
✞✞✞ #አስተርእዮ_ማርያም ✞✞✞
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖♥ ጥር 21 የእመቤታችንን በዓለ ዕረፍት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች። የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡
♥ በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ፸፪ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ ፩፥፲፬)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡
♥ ከዚያም ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፡፡
♥ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ቁጥሩ ከ72 ቱ አርድዕት የኾነው ቅዱስ ኢቮዲደስ እንደጻፈው የእመቤታችን ዕረፍቷ ሲደርስ ጌታ ተገልጾ እናቱን እንዲኽ አላት:-
❖♥ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ።
♥ ጌታም በመለኮታዊዉ እና ግሩም ድምፁ የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ ፪፥፲)፤ የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ፪፥፲፫) አላት፤ አንቺ ከቄዳር ልጆችም በላይ ውብ ቆንዦ ነሽ (መሓ ፩፥፭)፤ አንቺ የተመረጥሽ ጎጆ ሆይ የመልካማ ርግብ መኖርያ ነሽ፤ አንቺ የተመረጥሽ የአትክልት ስፍራ ያለምንም ዘር እና የወንድ ሩካቤ መልካሙን ፍሬ ያፈራሽ (መሓ ፬፥፲፪)።
♥ አንቺ የወርቅ መሶብ ሆይ መናው እውነተኛው መና እኔ እንኳን የተሰወርኹብሽ (ዘፀ ፲፮፥፴፫-፴፬)፤ አንቺ ስዉር ቅርስ እውነተኛው ብርሃን የተሰወረብሽ እና ከአንቺም ውስጥ ወጥቶ በመገለጽ በሰው ልጆች ላይ የተትረፈረፈ ሀብት ያስገኘላቸው፡፡
♥ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ የእኔ ውብ ርግብ ሆይ (መሓ ፮፥፱) የእኔ ቅድስት መርዐት (መሓ ፬፥፰)፣ የእኔ ንጽሕት መስክ፣ ከእኔ ጋር ወደ አትክልት ስፍራው እወስድሻለኊ (መዝ ፸፩፥፮) ከርቤ እና ጣፋጭ ቅመማ ቅመሜን እደረድርልሻለኊ (መሓ ፬፥፲፬) ከበታችሽም እንድታርፊበት ያማረውን ምንጣፍ አነጥፍልሻለኊ፤ ማርያም እናቴ ሆይ አንቺ የተባረክሽ ነሽ ወደ ምድር ወልደሽ አምጥተሽኛልና፡፡
♥ እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡
♥ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡
♥ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡
♥ ከዚያም ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው።
♥ ከዚያም ልጇ “የእኔ እናት ማርያም ሆይ እግዚአብሔርን (እኔን) የሳምሽባቸው ከናፍሮችሽ የተባረኩ ናቸው፤ ወደ ምድር ሲመለከት መሠረቶቿ እንዲናጉና እንዲሸበሩ ለማድረግ የሚችለውን ከኀሊውን ልጅሽንና አምላክሽን (እኔን) ያየሽባቸው ዐይኖችሽ የተባረኩ ናቸው፤ ከሰማያት ነዋሪዎች ጋር በመላእክት ቋንቋዎች ስነጋገር የሰማሽባቸው ዦሮዎችሽ የተባረኩ ናቸው።
♥ አንቺ ሆይ በቃሉ ኀይል ምድርን የተሸከማትን የተሸከሙት የኖርኹባቸው ታናናሾች ክንዶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ ፍጥረትን ኹሉ የምመግበውን የመገቡት እና ያጠቡት ጡቶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ በኀያሉ ዙፋን ላይ በክብር የምቀመጠውን እኔን በፍቅር ያስቀመጡኝ ጉልበቶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ ለዘጠኝ ወራት የተሸከሙኝ ማሕፀኖችሽም የተባረኩ ናቸው፡፡ በመለኮታዊነቴ ብርሃን ብሩሃት የኾኑት ሥጋሽና ነፍስሽ የተባረኩ ናቸው” አላት::
♥ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡
♥ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
♥ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበ
4 374
#የልዳው_አንበሳ
የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ
ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/
#አዝ........
በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ..........
ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ.........
በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ
ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ..........
ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ
ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም.
ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ
ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን
መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ
በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡
❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን
ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ
አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን
በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ
የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና
ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት
በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ
መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም)
አለ፡፡
❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን
ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር
ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ
በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም
ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው
ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤
ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤
ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች
በጌታችን አመኑ፡፡
❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን
አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት
ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ
ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ
የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ
ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር
ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር
ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ
ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና
ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡
❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ
አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን
አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው
በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት
ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን
ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ
እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው
የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡
❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ
እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም
ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን
ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤
ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ
ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡
❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ
ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም
ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦
“ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ”
(የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ
የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ
ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን
ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨
❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ
ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡-
“ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ
ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ
በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ
ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ
ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ”
(ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ
ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ
ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና
ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡
❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ
ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር
ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር
ዘማእከለ ሰማይ ወምድር
ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር
ብእሲ አዛል ወመስተጋድል
ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡
(ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን
ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤
ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት
ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨
❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦
"እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ
ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ
ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ"
(ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን
ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨
👇👇👇👇👇👇👇
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞✞✞
✞✞✞ ጥር 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
+" #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ልዳዊ "
✞✞✞ መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ
ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በኋላ ተሰይፏል:: ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም
(ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ)
ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም
በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች
ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት
ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ
ስምዕ) ደረሰ::
+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል
ይጠራል:: "ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::
+ከ7 ዓመታት መከራ በኋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም
ወርደውለታል::
+" ዝርወተ ዓጽሙ "+
+ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ
ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::
+በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን
ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::
+በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: (ምቅናይ)
+እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ
ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይህቺ ዕለት
ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው::
+ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ:
አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
+" ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባው "+
+'ጃንደረባ' የሚለው ቃል በግዕዙ 'ሕጽው' ተብሏል:: ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን የተለመደ እንጂ እንግዳ አይደለም:: መድኃኒታችን እንዳለው በተፈጥሮ የሆኑ: ሰዎች እንዲያ
ያደረጉዋቸውና ራሳቸውን ስለ ጽድቅ ጃንደረባ ያደረጉ ብዙዎች ናቸውና::
+ኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ቅዱስ ባኮስም (አንዳንዴ አቤላክ / አቤሜሌክም ይባላል):-
*በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ኢትዮዽያ ተወልዶ ያደገ
*ነገሥታቱንና ሃገሩን በሙያው ያገለገለ
*በተለይ ከ34 እስከ 46 ዓ/ም ለነገሠችው ንግሥት ሕንደኬ ገርስሞት በገንዘብ ሚንስትርነት ያገለገለ
*በገንዘቧ ላይ ሁሉ አዛዥ (ታማኝ) የነበረ
*ጃንደረባ በመሆኑ ለንግሥቲቱና ቤተሰቧ ቅርብ የነበረ
*መጻሕፍትን የሚያነብና የሚመረምር
*ዘወትር ወደ ኢየሩሳሌም እየሔደ ከቅዱሳት መካናት የሚሳለም በጐ ሰው ነበር::
+በግብረ ሐዋርያት ምዕ. 8:26 ላይ እንደ ተጠቀሰው
ቅዱሱ ከኢየሩሳሌም ለፋሲካና ለእሸት በዓል ነበር የሔደው::
ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልዾስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል:: በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ: በክርስቶስ
አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቁዋል::
+ክርስትናን ለኢትዮዽያ በ34 ዓ/ም አምጥቷል:: "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ
አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ: ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል::
+ቀጥሎም ሃብቱን ንቆ (መንኖ): ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድ
ወንጌልን ሰብኮ በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ዐርፏል::
(ተሰውሯል የሚሉም አሉ)
<< በእውነት ለቅዱስ ባኮስ ክብር ይገባል:: >>
+" ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን "+
+ይህ ቅዱስ ሰው:--
*እጅግ የተመሠከረለት ሊቅ
*በፍጹም ትሕርምት የኖረ ገዳማዊ
*በርካቶችን ወደ ክርስትና ያመጣ ሐዋርያዊ
*ለአእላፍ ምዕመናን እረኛ የሆነ የንጽቢን (ሶርያ) ዻዻስ
*ለጀሮ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የሠራ ገባሬ መንክራት
*ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንትን ያፈራ ታላቅ መምሕር
*ለክርስቶስና ለእመቤታችን ታጥቆ የተገዛ የፍቅር ሰው
*እጣቶቹ እንደ ፋና የሚያበሩለት ማኅቶት
*ራሱን ዝቅ አድርጐ በቆሸሸ ልብስ የሚኖር የትህትና ሰው ነው::
+በ325 (318) ዓ/ም: በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡና አርዮስን ሲያወግዙ እርሱ አንዱ ነበር::
በሥፍራውም ሙት አስነስቶ ሕዝቡን አስደምሟል:: በዚያም የቤተ ክርስቲያንን
ሥርዓት ሠርቶ ወደ ሃገሩ ተመልሶ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን
ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
+"+ ደናግል ማርያ ወማርታ +"+
+በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው
ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት-
ከኃጢአት የተመለሰች': 2ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
+በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል 12:1 ላይ
ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን
እናታችን ነው::
+ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ
ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
+በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው::
አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
+ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት
ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ
በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: (ዮሐ.11)
+ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን
አስነሳው:: ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር
አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: (ዮሐ. 12:1)
+በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ
በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
+
4 374
" #ሰማያት_የእግዚአብሔርን_ክብር_ይናገራሉ__የሰማይም_ጠፈር_የእጁን_ሥራ_ያወራል። " መዝ፡19፥1
✿ትላንት ማታ ጨረቃ ላይ የጌታችንንና የመጥምቁን ሥዕል ያዩ ምእመናን (ለመዋሸት ምንም ምክንያት የሌላቸው ወንድሞች ሳይቀር) በደስታ ሲነግሩን ፎቶ ሲልኩልን አምሽተዋል። ነገሩን ለማጣራት መቼም "ጨረቃ ሆይ አንድ ጊዜ ድገሚው" ማለት አንችልም። ይህን አምኖ ፈጣሪን ማመስገን አያስነቅፍም። ያየውን የሚመሰክር ሰው ሲገጥመንም ዝም ብለን አንነቅፍም። ይሁንና "ላይሆን ይችላል" ብሎ መጠርጠርም (Sceptical መሆንም) በምልክት ማመን የእምነት መለኪያ ስላልሆነ አያስቀጣም። ደቀ መዛሙርቱም ክርስቶስን ተከትለውት ተአምር አዩ እንጂ ተአምር አይተው አልተከተሉትም።
ጨረቃን የፈጠረ ብለን የምናመልከው አምላክ በጨረቃ ላይ ምልክት ቢያሳየንም ባያሳየንም አምላክ ነው። እስከ ጨረቃ ድረስ የሚያይ ዓይናችንን እንደ ቴሌስኮፕ የገጠመው እርሱን በጨለማ የምታበራዋን ኳስ የፈጠራትን እርሱን ለማድነቅ በሚልየን የሚቆጠሩ ብዙ ምክንያቶች አሉን።
በጨረቃ ላይ በታየው ነገር ለየሰዉ የሚታየው ነገር እንደማንነቱ ነው። መንፈሳዊ ዓይን ያለው መንፈሳዊ ነገር ያያል። ሌላው ደግሞ ድራገን ፣ ጊንጥ ወዘተ አየሁ ሊል ይችላል። በሌላው ዓለም ዜና ማሠራጫዎችም የየራሱ ትንታኔ ተሠጥቶታል። ጥምቀትን ላከበረው ክርስቲያን ምእመን ግን መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቅ ታይቶታል።
በአንድ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ተማሪዎች ማታ ወጥተው ሲዘምሩ አምሽተዋል። ወጣቶች በሌሊት ተነሥተው ወደ ጭፈራ ቤት ከመሔድ ይልቅ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ ከማደራቸው በላይ ምን ተአምር አለ? ጨረቃ ላይ ከታየው መሬት ላይ የታየው በለጠ ያሰኛል። ጨረቃ ላይ ፍጡር ካለ ወደ ምድር ቁልቁል እያየ ይኼን ዝማሬ ማድነቅ ይኖርበታል።
ከዚያ ውጪ እኛ ኦርቶዶክሳውያን መጥምቁ ዮሐንስን ግን ጨረቃ ላይ ካየነው ቆይተናል።
መጥምቁ ዮሐንስ ራሱ ጨረቃ ነው። ጨረቃ በጨለማ ያበራል ፣ ፀሐይ ሲወጣ ለፀሐይ ሥፍራውን ይለቅቃል። መጥምቁ በጨለማው የብሉይ ኪዳን ዘመን ካበሩ ነቢያት የመጨረሻውና ከሁሉ የሚበልጠው ነቢይ ነበር። "እርሱ የሚነድ መብራት ነበረ ፣ ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ" እንደተባለ መጥምቁ ዮሐንስ በሌሊት ያበራ ጨረቃ ነበረ። (ዮሐ 5:35)
ፀሐይ ከወጣች በኋላ ጨረቃ ብርሃንዋ እንደማያስፈልግና ለፀሐይ ቦታዋን እንደምትለቅ መጥምቁ ዮሐንስም እውነተኛው ፀሐይ ክርስቶስ ሲመጣ "እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል" ብሎ ሥፍራውን ለቀቀ። (ዮሐ 3:30)
ዮሐንስ በራእዩ ያያት ፀሐይን ተጎናፅፋ ፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ዘውድ የሆኑላት ፣ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ሴትም በአንድ በኩል ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በሌላ በኩል "ወንድ ልጅ ወለደች" የሚለው ቃል እንደሚያስገድደን ድንግል ማርያም ናት። ፀሐይ ክርስቶስን የተጎናጸፈችውም በማኅፀንዋ ማደሩ ከእርስዋ በመወለዱ ሲሆን ከዋክብቱም የከበቧት ሐዋርያት ነበሩ። ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ጨረቃ ገና በእናቱ ማኅፀን እያለ የሰላምታዋን ድምፅ ሰምቶ የሰገደው መጥምቁ ዮሐንስ ነው።
ኦርቶዶክሳውያን መጥምቁ ዮሐንስን ጨረቃ ላይ ስናየው ቆይተናል። ጨረቃ ላይ ሥዕሉን ብናይም ባናይም ጨረቃን ባየን ቁጥር መጥምቁ ዮሐንስን ማሰባችን አይቀርም። በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
4 374
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል_ከከበሩት_ከሰባቱ_ሊቃነ_መላእክት_አንዱ_እኔ_ሩፋኤል_ነኝ። ጦቢት፡12፥13
ጥር 13
እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ የእብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው፡፡ ሩፋ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን ኤል ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው ይህም « መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ . አታስመርሩት» (ዘጸ.23÷20-22) እዳለው ነው፡፡
ታዲያ ሩፋኤል የሚለው በጥምረት ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3)
ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12)
በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)
« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመናብርትን ድንቅ ገቢር ተአምራቱን ያዩ ምዕመናን
……የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ
ስለተሸመ ከጌታ
አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም
ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም
በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ የባላገር ሴቶች ሁሉ
የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ
ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ ……
እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡ በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ
~~~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡
~~~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡
~~~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው
~~~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት ያሳድርብን አሜን !!!
