WorksheetWorsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡ ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ። 📌 የአጠናን መንገድ(ስልት) እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔? 🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ። 🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ። 🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው። ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔 🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷♀። ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ 🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው። 🎯 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ። 🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው። 🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን። 📌 የጊዜ አጠቃቀም ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው። 📌 አለመሰልቸት ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል። 📌 ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን። ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ። 📌