en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ቤተ መፅሀፍት

ቤተ መፅሀፍት

Open in Telegram

እንኳን ደህና መጡ ዉድ አንባቢያን በዚህ ቻናል የተመረጡ ሀገርኛ እና የዉጭ ሀገር መፅሀፍቶችን ያገኛሉ። ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋል።

Show more
1 071
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+530 days
Posts Archive
photo content

ደራሲ ተውኔት ፀሐፊና ገጣሚ የሆነው ዊልያም ጎልዲንግ ነው ስለ ሴቶች እንዲህ ይላል << እኔ እንደማስበው ሴቶች ከ ወንዶች እኩል ነን ብለው ማሰባቸውና ራሳቸውን ማስመናቸዉ ሞኝነት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሴቶች ከ ወንዶች እጅግ የላቁና የበለጡ ናቸው ለሴት ልጅ ምንም ነገር ብትሰጣት እጥፍ ድርብና አብዝታ ትመልስልሀለች፡፡ለምሳሌ ዘርህን ብትሰጣት ልጅ ትሰጥሀለች ቤት ብትሰጣት የሞቀ ጎጆ አድርጋ ታስረክብሃለች ግሮሰሪ ብትሰጣት ምግብ ቤት አድርጋ ግሮሰሪህን በደምበኛ ታጥለቀልቀዋለች ፈገግታህን ብትሰጣት ልቧን ትቸርሀለች ማንኛውንም ነገር ለሴት ልጅ ብትሰጣት አብዝታና አተልቃ ታስረክብሃለች፡፡ ; : : ; ብትሰድባት እንኳን ብዙ ቶን ስድቦችን በማዥጎድጎድ ልክህን ትነግርሀለች > @Ethio_Library1 @Ethio_Library1

ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ፤ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም ። @Ethio_Library1

📖📚ርእስ -ሞገድ ⭐️📝📝ድርሰት - ኸርቪንግ ዋላስ ✅ትርጉም - ጋሽ ተሾመ ዳምጠው 🔘ይዘት - ልብወለድ የገፅ ብዛት - 383 ከጀመሩት የማያስቀምጡት እጅግ አጓጊ፣ ከህሊና ፍፁም የማይጠፋ ዘመን አይሽሬ ድንቅ መጽሐፍ! ‹‹አስደናቂ. . .የማያቋርጥ ሴራ …….. @Ethio_Library1 @Ethio_Library1

ከኦሮማይ መፅሀፍ የተወሰደ (በአሉ ግርማ) እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል ግን እንባ ከየት አባቱ! ደርቋል ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ላይስቅ ጥርሴ ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነፍሴ፡፡ " ጀምበሯ ለመጥለቅ አቆልቁላለች፡፡ አድማሱ ቀልቷል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ቀለበቷን ብቻ አልነበረም በጫማው ረግጦ የለጋው ፣ የገዛ ሕይወቷን ነበር እንጂ፡፡ ቻው ፊያሜታ አለ በልቡ፡፡ መቃብሯ ጸጥ ብሎአል፡፡ ከመቃብር ጸጥታ ባሻገር የናቅፋ ተኩስ ተሰማው፣ የጀግኖችን ደም ጩኸት እየሰማ ልቡ ወደዚያ ሔደ ፡፡ ሁሉን ትወዳለህ፣ በመጨረሻም ሁሉን ታጣለህ፡፡ ሴ ላ ቪ ! ኦሮማይ፡፡ @Ethio_Library1 @Ethio_Library1

"... [አለቃ ገብረሐና] የሚጠሉት አንድ ፉንጋ ቄስ ነበር፡፡ ታዲያ ቄሰ ሆዬ የአባ ገብረሐናን ሸፋፋነት ያውቅ ኖሮ ‹‹አባ ሽፍን ጫማ በሸዋ በኩል መጥቷል ይባላልና እንዳያመልጥዎ›› ሲል ያሽሟጥጣቸዋል፡፡ [አለቃ ገብረሐናን] በነገር የሚቀድማቸው የለም፣ ‹‹አንተ ፊት ግዛና›› ብለው ኩምሽሽ አደረጉት፡፡” “[አለቃ ገብረሐና] ብቸኝነቱ ቢጫጫናቸው … ሴት ማዘውተር ጀመሩ፡፡ ሆኖም ጠላቶቻቸው ይከታተሏቸው ኖረው አንድ ቀን ሴት ቤት አድረው ሲወጡ ያያቸው ካህን ሲገሰግስ ራጉኤል ሄዶ ጉዳያቸውን ነገረባቸው፡፡ አለቃ አገር ሰላም ብለው ቤተክርስቲያን ሊገቡ ሲሉ ተከለከሉ፡፡ ‹‹ለምን?›› ‹‹ሴት ስለነኩ›› ‹‹አይ ጥሩ›› ብለው አለቃም ተመለሱና ሳይታዩ የሴቶች መግቢያ በር ላይ ቆመው የመጡትን ሴቶች ሁሉ ‹‹መግባት ተከልክሏል›› ብለው መለሷቸው፡፡ ካህናቱ አንዲት የሔዋን አምሳል እንኳን በግቢ ውስጥ ቢያጡ ተደናግጠው ሁኔታውን ሲያጣሩ አለቃ ሁሉንም መመለሳቸውን ሰሙ፡፡ ካህናቱ ወዲያውኑ ንጉሡ ዘንድ ሄደው ከሰሷቸው፡፡ ‹‹ሴት ቤት አድረው ከመምጣታቸውም በላይ ሴቶችን ሁሉ ቤተክርስቲያን አትሳሙ ብለው መልሰዋል›› ሲሉም ወነጀሏቸው፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ አደረግህ ገብረሐና?›› ‹‹እንዴ ጃንሆይ! እኔ ነካህ ተብዬ ስከለከል እነሱ ይዘውት ይግቡ እንዴ?›› ብለው ምኒልክን አሳቋቸው፡፡” @Ethio_Library1 @Ethio_Library1

በቃኝ እሳት ሆኜ ስነድ ፣ አንቺ ቆፈን ወርሶች ሎሚ ብወረውር ፣ እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ ዝምድና ሳያንሰን ፣ እየቆየሽ ባዳ መላመድ ሳይጎድለን ፣እያደርሽ እንግዳ፤ እንግዲህ ደህና ሁኝ! ምኞቴም በረደ ፣ ቁጣዬም አለፈ ከእድሉ ጋር ታግሎ ፣ ማነው ያሸነፈ። ✍️✍️በዕውቀት ሥዩም (የማለዳ ድባብ) @Ethio_Library1 @Ethio_Library1

መልክአ ሕይወት ቧልትን ከፈገግታ ሣቅን ከፌዝ ጋራ ባ'ንድ ላይ ቀይጠን አቅልመን በጥብጠን በሐዘን ባሕር ላይ ፣ ብናንቆረቁርም ባሕሩ ሰፊ ነው ፣ መልኩን አይቀይርም። [ በዕውቀቱ ስዩም ] @Ethio_Library1

ጸሃፊው አኒስ መንሱር ተጠየቀ፡- "የሰዎችን እውነታዊ መልክ እንዴት እናውቃለን?" እርሱም አለ፦ "ባል ሚስቱ የታመመችበት እለት  ሚስትም ባሏ ድሃ በሚሆንበት ጊዜ ያውቃሉ፤ ወዳጅ በችግር ወቅት ይታወቃል፤ ልጆች ወላጆቻቸው ሲያረጁ ይታወቃሉ፤ ወንድሞች ውርስ በደረሰ ጊዜ ይተዋወቃሉ፤ እውነተኛ ፍቅርም ከእኛ በራቀ ጊዜ፤ አማኝም በፈተናው ሰዓት ይታወቃል። " @Ethio_Library1

ፅጌን ከወደዱ ከነ'ሾሁ🥀 ............................... መሄጃ ከሌለ እግር ምን ያደርጋል ጎዳናው እሾህ ነው ለመሄድ ያሰጋል ቢሆንም.... ቢሆንም ግዴለም እግሬ ይቁሰል ይድማ ነብስስ ይሰጥ የለም ወይ ለወደዱትማ እንደዚህ ነው ፍቅር እንደዚህ ነው መውደድ እኔ አግር ስሆን አንቺ ደግሞ መንገድ @Amharic_book_pdf @Amharic_book_pdf

+1
መኀልየ_መኀልይ_ዘካዛንቺስ_ተድባበ_ጥላሁን.pdf35.90 MB

+6
እግረ_መንገድ_ስብሀት_ገብረ_እግዚአብሔር.pdf35.36 MB