ቤተ መፅሀፍት
前往频道在 Telegram
እንኳን ደህና መጡ ዉድ አንባቢያን በዚህ ቻናል የተመረጡ ሀገርኛ እና የዉጭ ሀገር መፅሀፍቶችን ያገኛሉ። ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋል።
显示更多1 071
订阅者
无数据24 小时
-17 天
+530 天
帖子存档
1 071
ደራሲ ተውኔት ፀሐፊና ገጣሚ የሆነው ዊልያም ጎልዲንግ ነው ስለ ሴቶች እንዲህ ይላል << እኔ እንደማስበው ሴቶች ከ ወንዶች እኩል ነን ብለው ማሰባቸውና ራሳቸውን ማስመናቸዉ ሞኝነት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሴቶች ከ ወንዶች እጅግ የላቁና የበለጡ ናቸው ለሴት ልጅ ምንም ነገር ብትሰጣት እጥፍ ድርብና አብዝታ ትመልስልሀለች፡፡ለምሳሌ ዘርህን ብትሰጣት ልጅ ትሰጥሀለች ቤት ብትሰጣት የሞቀ ጎጆ አድርጋ ታስረክብሃለች ግሮሰሪ ብትሰጣት ምግብ ቤት አድርጋ ግሮሰሪህን በደምበኛ ታጥለቀልቀዋለች ፈገግታህን ብትሰጣት ልቧን ትቸርሀለች ማንኛውንም ነገር ለሴት ልጅ ብትሰጣት አብዝታና አተልቃ ታስረክብሃለች፡፡
;
:
:
;
ብትሰድባት እንኳን ብዙ ቶን ስድቦችን በማዥጎድጎድ ልክህን ትነግርሀለች >
@Ethio_Library1
@Ethio_Library1
1 071
Repost from ቤተ መፅሀፍት
📖📚ርእስ -ሞገድ
⭐️📝📝ድርሰት - ኸርቪንግ ዋላስ
✅ትርጉም - ጋሽ ተሾመ ዳምጠው
🔘ይዘት - ልብወለድ
የገፅ ብዛት - 383
ከጀመሩት የማያስቀምጡት እጅግ አጓጊ፣ ከህሊና ፍፁም የማይጠፋ ዘመን አይሽሬ ድንቅ መጽሐፍ!
‹‹አስደናቂ. . .የማያቋርጥ ሴራ ……..
@Ethio_Library1
@Ethio_Library1
1 071
ከኦሮማይ መፅሀፍ የተወሰደ
(በአሉ ግርማ)
እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል
ግን እንባ ከየት አባቱ!
ደርቋል ከረጢቱ
ሳቅ ሳቅም ይለኛል
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነፍሴ፡፡ "
ጀምበሯ ለመጥለቅ አቆልቁላለች፡፡ አድማሱ ቀልቷል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ቀለበቷን ብቻ
አልነበረም በጫማው ረግጦ የለጋው ፣
የገዛ ሕይወቷን ነበር እንጂ፡፡
ቻው ፊያሜታ አለ በልቡ፡፡
መቃብሯ ጸጥ ብሎአል፡፡
ከመቃብር ጸጥታ ባሻገር የናቅፋ
ተኩስ ተሰማው፣ የጀግኖችን ደም ጩኸት እየሰማ ልቡ ወደዚያ ሔደ ፡፡
ሁሉን ትወዳለህ፣ በመጨረሻም ሁሉን ታጣለህ፡፡
ሴ ላ ቪ ! ኦሮማይ፡፡
@Ethio_Library1
@Ethio_Library1
1 071
"... [አለቃ ገብረሐና] የሚጠሉት አንድ ፉንጋ ቄስ ነበር፡፡ ታዲያ ቄሰ ሆዬ የአባ ገብረሐናን ሸፋፋነት ያውቅ ኖሮ ‹‹አባ ሽፍን ጫማ በሸዋ በኩል መጥቷል ይባላልና እንዳያመልጥዎ›› ሲል ያሽሟጥጣቸዋል፡፡ [አለቃ ገብረሐናን] በነገር የሚቀድማቸው የለም፣ ‹‹አንተ ፊት ግዛና›› ብለው ኩምሽሽ አደረጉት፡፡”
“[አለቃ ገብረሐና] ብቸኝነቱ ቢጫጫናቸው … ሴት ማዘውተር ጀመሩ፡፡ ሆኖም ጠላቶቻቸው ይከታተሏቸው ኖረው አንድ ቀን ሴት ቤት አድረው ሲወጡ ያያቸው ካህን ሲገሰግስ ራጉኤል ሄዶ ጉዳያቸውን ነገረባቸው፡፡ አለቃ አገር ሰላም ብለው ቤተክርስቲያን ሊገቡ ሲሉ ተከለከሉ፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹ሴት ስለነኩ››
‹‹አይ ጥሩ›› ብለው አለቃም ተመለሱና ሳይታዩ የሴቶች መግቢያ በር ላይ ቆመው የመጡትን ሴቶች ሁሉ ‹‹መግባት ተከልክሏል›› ብለው መለሷቸው፡፡ ካህናቱ አንዲት የሔዋን አምሳል እንኳን በግቢ ውስጥ ቢያጡ ተደናግጠው ሁኔታውን ሲያጣሩ አለቃ ሁሉንም መመለሳቸውን ሰሙ፡፡
ካህናቱ ወዲያውኑ ንጉሡ ዘንድ ሄደው ከሰሷቸው፡፡ ‹‹ሴት ቤት አድረው ከመምጣታቸውም በላይ ሴቶችን ሁሉ ቤተክርስቲያን አትሳሙ ብለው መልሰዋል›› ሲሉም ወነጀሏቸው፡፡
‹‹ለምን እንዲህ አደረግህ ገብረሐና?››
‹‹እንዴ ጃንሆይ! እኔ ነካህ ተብዬ ስከለከል እነሱ ይዘውት ይግቡ እንዴ?›› ብለው ምኒልክን አሳቋቸው፡፡”
@Ethio_Library1
@Ethio_Library1
1 071
በቃኝ
እሳት ሆኜ ስነድ ፣ አንቺ ቆፈን ወርሶች
ሎሚ ብወረውር ፣ እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ
ዝምድና ሳያንሰን ፣ እየቆየሽ ባዳ
መላመድ ሳይጎድለን ፣እያደርሽ እንግዳ፤
እንግዲህ ደህና ሁኝ!
ምኞቴም በረደ ፣ ቁጣዬም አለፈ
ከእድሉ ጋር ታግሎ ፣ ማነው ያሸነፈ።
✍️✍️በዕውቀት ሥዩም
(የማለዳ ድባብ)
@Ethio_Library1
@Ethio_Library1
1 071
መልክአ ሕይወት
ቧልትን ከፈገግታ
ሣቅን ከፌዝ ጋራ
ባ'ንድ ላይ ቀይጠን
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባሕር ላይ ፣ ብናንቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው ፣ መልኩን አይቀይርም።
[ በዕውቀቱ ስዩም ]
@Ethio_Library1
1 071
ጸሃፊው አኒስ መንሱር ተጠየቀ፡-
"የሰዎችን እውነታዊ መልክ እንዴት እናውቃለን?"
እርሱም አለ፦
"ባል ሚስቱ የታመመችበት እለት ሚስትም ባሏ ድሃ በሚሆንበት ጊዜ ያውቃሉ፤ ወዳጅ በችግር ወቅት ይታወቃል፤ ልጆች ወላጆቻቸው ሲያረጁ ይታወቃሉ፤ ወንድሞች ውርስ በደረሰ ጊዜ ይተዋወቃሉ፤ እውነተኛ ፍቅርም ከእኛ በራቀ ጊዜ፤ አማኝም በፈተናው ሰዓት ይታወቃል። "
@Ethio_Library11 071
ፅጌን ከወደዱ ከነ'ሾሁ🥀
...............................
መሄጃ ከሌለ እግር ምን ያደርጋል
ጎዳናው እሾህ ነው ለመሄድ ያሰጋል
ቢሆንም....
ቢሆንም ግዴለም እግሬ ይቁሰል ይድማ
ነብስስ ይሰጥ የለም ወይ ለወደዱትማ
እንደዚህ ነው ፍቅር እንደዚህ ነው መውደድ
እኔ አግር ስሆን አንቺ ደግሞ መንገድ
@Amharic_book_pdf
@Amharic_book_pdf
