♥♥♥♥
ዶክተሩ በድንገት ተደውሎለት ለአስቸኳይ የቀዶ ህክምና በጥድፊያ ወደ ሆስፒታል
እየገባ ነው። በተቻለው አቅም የስልክ ጥሪውን በአግባቡ አስተናግዷል። የህክምና
ልብሱን ባስቸኳይ ቀይሮ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እያመረ ሳለ ኮሪደር ላይ የዶክተሩን
መምጣት እየተንጎራደደ ይጠብቀው የነበረውን ሰው አገኘው።
”እንዴት ለመመጣት ይህን ያህል ጊዜ ይፈጅብሀል?! የልጄ ህይወት ሊጠፋ
አደጋ ላይ እንዳለች አይታይህም?! ህሊና የለህም?!” ብሎ ዶክተሩ ላይ ጮሀበት።
ዶክተሩ በትንሹ ፈገግ አለና
“አዝናለው ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም። የስልኩን ጥሪ ከተቀበልኩ በኃላ በቻልኩት
ፍጥነት እዚህ ለመድረስ
ጥሪያለው። አሁን አንተም ብተረጋጋ እኔም ስራዬን ብሰራ መልካም ነው።“ ብሎ
ሊያረጋጋው ሞከረ ሰውየው ግን
“ተረጋግተህ ነው ያልከው? ያንተ ልጅ ቢሆንስ አሁን ….እዚህ ክፍል ውስጥ ሆነህ
ትረጋጋ ነበር?! ልጅህ ቢሞት ምን ታደርግ ነበር? ” አለ አባትዬው በንዴትና በቁጣ::
ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰ።
”የአምላክ ፈቃድ ይሁን" ዶክተር ህይወት ሊያራዝም.. ሊያጠፋም… ሊተካም …
አይችልም ግን የቻልነውን ያክል እንጥራለን እንደ አምላክ ፍቃድ ልጅህም ይድንልሃል።”
አለው
ሰውየውም “ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው።” አለ
እያጉረመረመ።
ቀዶ ጥገናውም የተወሰኑ ሰአታትን ወስዶ ተጠናቀቀ። ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ
ጥገና ክፍል ውስጥ ወጣ።ለአባትየውም
“ፈጣሪ ይመስገን ልጅህ ተርፏል።” ብሎት የአባትየውን መልስ ሳይጠብቅ “ማንኛውም
ጥያቄ ካለህ ሌሎች
ረዳት ዶክተሮችን መጠየቅ ትችላለክ” ብሎት ዶክተሩ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ።
የልጁም አባት “ለምንድነው ዶክተሩ እንዲህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው? ምናለ አሁን
አንድ ደቂቃ ስለ ልጄ ሁኔታ ብጠይቀው? ሲል ተናገረ ይህን ሲል የሰማችው ነርስ
እንባዋ በጉንጮቿ እየጎረፉ...
“ትላንት ነበር የዶክተሩ ልጅ በመኪና አደጋ የሞተው። ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት
የልጁ ቀብር ላይ ነበር።
አሁን ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ የራሱን ልጅ ደሞ የቀብር ስርዐት ሊጨርስ በሩጫ
ሄደ።” አለችው
በማንኛውንም ሰው ላይ በችኮላ አንፍረድ። ነገሮችን ከአንደበታችን ከመውጣቱ በፊት ቆም ብሎ ማሰብ ከከባድ ፀፀት ታድነናለች:: አባትየው ከሰአታት በፊት ዶክተሩ ያሳየውን
ፈገግታ እያሰበ ተንሰቀሰቀ........
Show more ...