cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዝማሬ ማህደር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። #ዝማሬማህደር የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። @AfomeDanZeMikahal ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ካላችሁ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል 👇👇👇 https://t.me/DanZ11

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
192
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ምንም ባይገባህም ቤተ ክርስቲያን መምጣትህን አታቁም። ምንም የቅዳሴውን ዜማ ባታቀው ቁመህም ቁጭ ብለህም ስማ። ምንም መምህራኑ የሚሉት ባይገባህ ዝምብለህ ጉባዔ ውስጥ ተገኝ። ምንም ጸሎት የማታውቅ ከሆነ አምላክህን አባትህን እንደምታዋራው አዋራው። እግዚአብሔርን በየዋህነት ተከተለው እርሱ በጥበብ ወደራሱ ይመራሃል። ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ ✍✍✍✍✍✍✍✍ ✍ @dnJohannes ✍ ✍ @dnJohannes ✍ ✍ @dnJohannes ✍ ✍ @dnJohannes ✍ ✍✍✍✍✍✍✍✍
Show all...
​​የብፁዕ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ ቀብርን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ፤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰብሳቢነት የመከረው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓተ ቀብራቸውን የሚያስፈጽም ዐቢይ ኮሚቴ አቋቁሟል። የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ከአምስት ያላነሡ ንዑሣን ኮሚቴዎችን በማቋቋምና ሥራዎችን በየዕለቱ እየተከታተለ፣ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ሥራዎችን በወጣው መርሐ ግብር መሠረት እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መሠረት፦ ከሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ይፋዊ የኃዘን ቀናት ታውጆ፥ የእምነት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎችና ተወካዮች፣ የውጭ ሀገራት ኤምባሲ አምባሳደሮች፣ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በመገኘት በተዘጋጀው የኃዘን መግለጫ መዝገብ ላይ በጽሑፍ ኀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛል። በቀጣይ ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የቅዱስነታቸው አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በክብር ወደ መስቀል አደባባይ ያመራል፤ በመስቀል አደባባይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየድርጅትና የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ምእመናንና ምእመናት ለዕለቱ የተዘጋጀው መርሐ ግብር ተከናውኖ ከተጠናቀቀ በኋላ በክብር ታጅቦ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጉዞ በማድረግ ያርፋል። በመንበረ ፓትርያርክ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ፣ ልዩ ልዩ የሐዘን መግለጫና መንፈሳዊ መልእክቶች ከተላለፉ በኋላ፥ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የክብር ሽኝት ይደረጋል። በዚያም ሌሊቱን በሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር፣ ከነግህ ጀምሮ ጸሎተ ቅዳሴ ከደረሰ በኋላ፤ በመርሐ ግብሩ መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከውጭ ሀገራት የሚመጡ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች፣ የእምነት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትና ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል። ምንጭ፡-የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Show all...

Photo unavailableShow in Telegram
" ከአቡነ ሰላማ እስከ አቡነ ማትያስ "የኢትዮጵያ ጳጳሳት ሰም ዝርዝራቸው" # ታደለ ጥበቡ Share, በማድረግ ማሳወቅ መልካመነት ነው! ------------------++++++++---------------------- በአብርሃና በአጽብሃ ዘመን የነበሩ 1-ግሪካዊው ቅዱስ ፍሬምናጦስ (አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን) -እነህ አባት የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው።ከአክሱም ወደ ግብጽ በ325 አ.ም ሄደው በ20ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ አቡነ አትናቴዎስ "ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ" ተብለው በቅባትና በአንብሮተ እድ ሹሞ ልኮታል። (ታሪካቸውን ለማንበብ ለጠየቃችሁኝ -Historieb Ecclesiastic,p.L.xxi.478-80 -A London,the lesser Ebstefn churches,London,1913 p.295 -storia D'Ethiopia,C.Rossini,p 149-151 ተመልከቱ) -ፍሬምናጦስ ጳጳስ የሆነው በ341 አ.ም ሲሆን በ350 አ.ም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነ አንዳዶች በ315 ይሉታል ሩፊኖስ ግን በ350 ነው የሚለው። (RufInus loc.cit l.ix 2-አቡነ ሚናስ ካልዕ(ሰላማ)ናቸው።አንዳዶች አባ ሙሴ ይሏቸዋል። -ዘመኑ በንጉሥ እለዓሜዳ ዘመነ መንግሥት ነው(471-479) በዚህን ጊዜ ዘጠኙ ቅዱሳን (አረጋዊ፣ጰንጠሊዮን፣ገሪ ማ፣ሊቃኖስ፣ይምዓታ፣ፅህማ፣ጉባ፣አፍፄ እና አሌፍ)በ480 አ.ም ከሶርያና ከታናሿ እስያ ይታመናል። 3-አባ ጴጥሮስ 1ኛ 4-አባ ማቴዎስ 1ኛ 5-አባ ማርቆስ 1ኛ 6-አባ ዮሐንስ 1ኛ 7-አባ ገብርኤል 1ኛ 8-አባ ዮሐንስ 2ኛ 9-አባ ገብርኤል 2ኛ 10-አባ ሚናስ 2ኛ 11-አባ ሚካኤል 1ኛ 12-አባ ይስሐቅ 13-አባ ስምዖን 1ኛ 14-አባ ጴጥሮስ 2ኛ 15-አባ ሚካኤል 2ኛ 16-አባ ገብርኤል 3ኛ 17-አባ ዮሐንስ 3ኛ 18-አባ ማቴዎስ 2ኛ @ የዛጎዌ ስርዎ ክርስቶስ ወይንም ገብረማርያም በመራ ተክለሃይማኖት (912-925 አ.ም ) ከተመሰረተ በኋላ በሰባተኛው ንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ (1077-1157 አ.ም)ጀምሮ የነበሩት:- 19-አባ ሚካኤል 3ኛ 20-አባ ስምዖን 2ኛ 21-አባ ዮሐንስ 4ኛ 22-አባ ማርቆስ 2ኛ 23-አባ አብርሃም ናቸው። -የዛጎዌ ስርወ መንግሥት ከ912-1245 አመታቶች ለ330 አመት ያህል የቆዬ ሲሆን 11 ነገሥታት አስተዳድረውታል።እነርሱም መራ ተክለሃይማኖት፣ጠጠውድም፣ጃን ስዩም፣ግርማ ስዩም፣መይራራ፣ሐርቤ 1ኛ፣ይምርሃነ ክርስቶስ፣ቅዱስ ሐርቤ 2ኛ፣ቅዱስ ላሊበላ፣ቅዱስ ነአኩቶለአብ እና ይትባረክ ናቸው። @በቅዱስ ላሊበላ (1157-1197)እና በቅዱስ ነአኩቶ ለአብ (1197-1237) የኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት:- 24-ጌርሎስ (ቄርሎስ) 1ኛ 25-አባ ዮሐንስ 5ኛ ናቸው። -አባ ጌርሎስ በአጼ ነአኩቶለአብ ዘመን የነበረ እና ለኢትዮጵያዊው አቡነ ተክለሃይማኖት የድቁና ማዕረግ የሰጠ ነው።አባ ጌርሎስ ከሞቱ በኋላ ግን የግብጽ ሡልጣኖች ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ጳጳስ ይከለክሉ ስለነበር ከእስክንድርያ ጳጳስ ማስመጣት ስላልተቻለ የኢትዮጵያ ሊቃውንት አቡነ ተክለሃይማኖትን ጳጳስ አድርገው ሾሞዋል።አቡነ ተክለሃይማኖትም በተሰጣቸው ሐይማኖታዊ ሥልጣን በቅንነት ሲያገለግሉ ቆይተው አባ ዮሐንስ 5ኛ ጳጳስነት ተሹመው ከእስክንድርያ ሲመጡ መንበረቸውን ሰጥተው እርሳቸው ወደገደሙት ደብረ ሊባኖስ መኖር ጀምረዋል። @የዛጉዌ ስርዎ መንግሥት ተጠናቆ የሰሎሞናዊ ስርዎ መንግሥት በአጼ ይኩኑ አምላክ (1253-1268) ከተመሰረተ በኋላ በሁለተኛው ንጉሥ አጼ አግብዓ ጽዮን (1268-1277) የመጡት:- 26-አባ ሚካኤል 4ኛ 27-አባ ስምዖን 3ኛ 28-አባ ጴጥሮስ 3ኛ 29-አባ ማቴዎስ 3ኛ 30-አባ ያዕቆብ 1ኛ ናቸው።አባ ያዕቆብ በአጼ አምደ ጽዮን (1297-1327 አ.ም) የነበሩ ጳጳስ ናቸው።አባ ያዕቆብ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ፊልጶስን ጠርቶ ለሸዋ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሹመውታል። @ከአጼ አምደ ጽዮን በመቀጠል በነገሰው አጼ ሰይፈ አርዕድ (1327-1355) ጀምሮ የነበሩት ጳጳሳት:- 31-አባ ፊቅጦር 1ኛ 32-አባ ቄርሎስ 2ኛ 33-አባ ቆዝሞስ 1ኛ 34-አባ ዮስጦስ 1ኛ 35-አባ ሚካኤል 5ኛ 36-አባ ገብርኤል 4ኛ 37-አባ ሚካኤል 6ኛ 38-አባ ማቴዎስ 4ኛ 39-አባ ዮሳብ 1ኛ 40-አባ ዮሴፍ 1ኛ 41-አባ ቆዝሞስ 2ኛ 42-አባአቃፊላታዎስ 43-አባ ጴጥሮስ 4ኛ 44-አባ ዮሐንስ 6ኛ 45-አባ ፊቅጦር 2ኛ 46-አባ ዮስጦስ 2ኛ 47-አባ በርምያ 48-አባ ሚካኤል 7ኛ 49-አባ ገብርኤል 5ኛ 50-አባ ሚናስ 3ኛ 51-አባ ዮሐንስ 7ኛ 52-አባ ዮሐንስ 8ኛ 53-አባ አብርሃም 2ኛ 54-አባ ማርቆስ 3ኛ 55-አባ መቃርስ 1ኛ 56-አባ ሚካኤል 8ኛ 57-አባ ማቴዎስ 4ኛ 58-አባ ሚካኤል9ኛ 59-አባ ገብርኤል 6ኛ 60-አባ ዮሐንስ 9ኛ 61-አባ ቄርሎስ 2ኛ 62-አባ ሚናስ 3ኛ 63-አባ ማቴዎስ 5ኛ 64-አባሚካኤል10ኛ 65-አባ ገብርኤል 7ኛ 66-አባ ማርቆስ 6ኛ 67-አባ ገብርኤል 8ኛ 68-አባ ማቴዎስ 6ኛ 69-አባ ዮሐንስ 10ኛ 70-አባ ሚናስ 4ኛ 71-አባ ማርቆስ 7ኛ 72-አባክርስቶዶሉ 1ኛ 73-አባ ዘካርያስ 74-አባ ፊላታዎስ2ኛ 75-አባ ሱንትዮስ 76-አባ ገብርኤል9ኛ 77-አባ ዮሐንስ11ኛ @በአጼ ዘርዓያዕቆብ (1426-1460) የነበሩት:- 78-አባ ሚካኤል11ኛ 79-አባ ገብርኤል10ኛ ናቸው። @ከአጼ ዘርዓያዕቆብ በመጠል በነገሱት በአጼ በእደ ማርያም (1460-1470) የነበሩት:- 80.በርቶሎሜዎስ 81-አባ ማቴዎስ 7ኛ 82-አባ ዮሐንስ 12ኛ @በአጼ ናኦድ ዘመነ መንግሥት (1487-1500) የነበሩት:- 83-አባ ማርቆስ 7ኛ 84-አባ ይስሐቅ 2ኛ 85-አባ ከላድያኑ 86-አባ ጴጥሮስ5ኛ @በአጼ ልብነድንግል ዘመነመንግሥት (1500-1532) የነበሩት:- 87-አባ ማቴዎስ 8ኛ 88-አባ ስምዖን 4ኛ @በአጼ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት(1532-1551) የነበሩት:- 89-አባ ዮሳብ 2ኛ 90.አባሚካኤል12ኛ 91-አባ ማቴዎስ 9ኛ 92-አባ ማርቆስ 8ኛ @የጎንደር አብያተ መንግሥታት በአጼ ሠርፀድንግል (1555-1589) አ.ም ነው የጀመረው።መንበረ ስልጣኑን ከአጼ ሠርጸድንግል ጀምሮ እስከ ተክለጊዮርጊስ (1773-1771) 18 ነገሥታቶች አስተዳድረውታል። በእነዚህ ነገሥታቶችም ከእስክንድርያ ጳጳስ እየሾመ ወደ ኢትዮጵያ የተላከ ሲሆን በአጼ ያዕቆብ (1589-1594) እና በአጼ ዘድንግል (1594-1596) ከነበሩት መካከል:- 93-አባ ጴጥሮስ 6ኛ ናቸው። አቡነ ጴጥሮስ በአጼ ያዕቆብና በአጼ ሱስኒዮስ ጦርነት በወታደር የተገደሉ አባት ናቸው። @በአጼ ሱስኒዮስ (1596-1624) የነበሩት:- 94-አባ ስምዖን 5ኛ ይባላሉ።አባ ስምዖን 5ኛም አጼ ሱስኒዮስ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖታቸውን በመቀየራቸው አውግዘው ከሎሌው ዮልዮስ ጦርነት ጎን በመሰለፍ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እራሱን አሳልፎ የሰጠ አባት ነው።በጦርነቱም በጦር ተወግቶ ሞቷል። @በአጼ ፋሲል (1624-1659) የነበሩት:- 95-አባ ማርቆስ 9ኛ እና
Show all...
96-አባ ሚካኤል 12ኛ ናቸው። በመሀል የአጼ ፋሲል ወንድም ገላውዴዎስ ያስመጣው 97-አባ ዮሐንስ 13ኛ ይባላል። @በደጉ አጼ ዮሐንስ 1ኛ (1659-1674) የነበሩት:- 98-አባ ክርስቶዶሉ 2ኛ 99-አባ ሲኖዳ ናቸው። @በአጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ 1ኛ (1674-1698) የነበሩት:- 100-አባ ማርቆስ 10ኛ ናቸው። @በአጼ ዳዊት 3ኛ (1708-1713) የነበሩት:- 101-አባ ክርስቶዶሉ 3ኛ ይባላል። @ከዚህ ቀጥሎ በዘመነ መሳፍንት የመጡ ናቸው።ዘመነ መሳፍንት ከትልቁ ራስ አሊ እስከ ትንሹ ራስ አሊ (1777-1845) ለ68 አመታት የቆየ ስርአት ነው።ለሰባት አመት በነገሰው አጼ ሕዝቅያስ የነበሩት:- 102- አባ ዮሐንስ 14ኛ 103-አባ ዮሳብ 3ኛ 104-አባ መቃርዮስ (ጎንደር ሳይደርሱ መንገድ ላይ ሞተው የቀሩ)ናቸው። 105-አባ ቄርሎስ 4ኛ-ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች በተከፋፈለች ጊዜ የመጡ ናቸው። @በአጼ ቴዎድሮስ 2ኛ (1847-1860) የነበሩት;- 106-አባ ሰላማ 3ኛ 107-አባ አትናቴዎስ ናቸው። @በአጼ ዮሐንስ 4ኛ (1864-1881) የነበረው:- 108-አባ ጴጥሮስ 7ኛ ናቸው። @በአጼ ምኒልክ ሁለተኛ (1882-1906) እና በንግሥት ዘውዲቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳስ 109- አቡነ ማቴዎስ 7ኛ ናቸው። ከላይ በዘረዘርነው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ለ1600 አመታት በግብጽ ኮፒትክ ቤተክርስቲያን ሥር ሁና የራሷን ጳጳስ ሳትሾሞ ዘልቃለች ማለት ነው።ከ1928 አ.ም በኋላ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን 4 ሊቃውንቶች ወደ ግብጽ ሄደው ሥልጣነ ጵጵስና አግኝተዋል።እነርሱም:- 1-አቡነ ጴጥሮስ 2-አቡነ ሚካኤል 3-አቡነ ይስሐቅ 4-አቡነ አብርሃም ናቸው። አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል በፋሽት ጣሊያን በግፍ የተገደሉ የሐይማኖት አርበኞች ናቸው።በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የነበሩት 110-አቡነ ቄርሎስ ነበሩ። ጣሊያን ሀገሪቱን በወረራት ጊዜ ፈርተው ወደሀገራቸው ሸሽተው ነበር።በእሳቸው ፈንታ አቡነ አብርሃም ማእረገ ክህነት ሰጥተው ስለነበር ፋሽት ወራሪው ሀገር ለቆ ሲወጣ ተመልሰው በአቡነ አብርሃም እጅ ክህነት የተቀበሉትን ዲያቆናትና ቀሣውስትን እንዳይቀድሱ አወገዙ። በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ሊቃውንት፣ካህናት፣መነኮሳት እና መምህራን እንዲሁም ምእመናን ጉባኤ አዘጋጅተው መክረው ዘክረው ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስን ወደ ሀገራቸው መልሰው የኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ለመሾም እንቅስቃሴ ጀመሩ።አጼ ሀይለስላሴም የሀሴባቸው ደጋፊ ሆኑ። ትግሉ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥር 6 ቀን 1943 አ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሊቀጳጳስ ተብለው ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ካይሮ ላይ በግብጹ አቡነ ዮሳብ ሁለተኛ ተሰየሙ።የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከ1951 አ.ም ከሊቀ ጵጵስና ወደ ፓትርያርክነት መንበር ከፍ አለች።ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሆኑ። በመቀጠል:- 2ኛ-አቡነቴዎፍሎስ 3ኛ-አቡነ ተክለሃይማኖት 4ኛ-ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ 5ኛ-አቡነ ጳውሎስ 6ኛ- አሁን ላይ አቡነ ማትያስ በመንበረ ጵጵስናው ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!! (የበለጠ ለመረዳት የኀሩይ ወልደ ሥላሴ "ዋዜማ" የሚለውን መጽሐፍ እና የመ/ር ደሴ ቀለብ "ታሪከ ነገሥትን" ይመልከቱ) ከጥበቡ ፔጅ
Show all...
✞✝✞ እንኩዋን ለታላቁ "የጌታ ጾም (ጾመ እግዚእ)" በሰላም አደረሳችሁ ✞✝✞ +*" ጾመ እግዚእ "*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል:: +"7ቱ" አጽዋማት:- 1.ዓቢይ ጾም 2.ጾመ ፍልሠታ 3.ጾመ ሐዋርያት 4.ጾመ ነቢያት 5.ጾመ ድኅነት 6.ጾመ ነነዌ እና 7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ:: +በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለው:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል:: +ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን:: +ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት : ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ¤ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) ¤አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን:: +የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11 ሰዓት ይጾማል:: በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል:: +ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል:: በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ በጨው እየበላ: ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል:: በእነዚህ 55 ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ አይጐሰምም:: ጸናጽል አይጸነጸልም:: ተድላ ደስታም አይደረግም:: +አብዝቶ መብላት : ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም:: ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡ በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን : በመዓልት ቅዳሴውን : በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል:: +በእነዚህ 55 ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ ልትሰለጥን ግድ ነውና:: ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው:: በዚያውም ላይ ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን መስማት (ማንበብ) ይገባል:: በትዳር ውስጥ ላሉም መኝታን መለየት ግድ ነው:: =>ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም= 1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም 2.የጌታ ጾም 3.ጾመ ሑዳድ 4.የድል ጾም 5.የካሳ ጾም 6.አርባ ጾም 7.የፍቅር ጾም . . . በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል:: =>የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ= 1.ጾመ ሕርቃል 2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት 3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል:: =>ጾሙን የሰላም : የፍቅር : የምሕረት : የፀጋ : የበረከት ያድርግልን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡ =>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ትን. ኢዩኤል 2:12) ✞✝✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✝✞
Show all...
✝ ዐቢይ_ጾም ✝ ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-ጌታችን መድኃኒጻችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ፣ በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ እና ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በጾሙ ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡- 1. #ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡ 2. #ቅድስት ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡ 3. #ምኩራብ ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡ 4. #መጻጉዕ ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡ 5. #ደብረ_ዘይት ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡ 6. #ገብርኄር ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡ 7. #ኒቆዲሞስ ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ 8. #ሆሳዕና ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው:: ✝የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አመታዊ እና ወርሃዊ✝ ✝ ክብረ በዓላት እንዲሁም አፅዋማት ✝ ✝ መገኛ ቻናል ✝ {{ @Orthodox_bealat }} 💠 @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot
Show all...
#ነነዌ_እና_የአጽዋማትና_በዓላት_አወጣጥ ❖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዐት መግቢያቸውና መውጪያቸው የሚዘዋወር የሐዲስ ኪዳን አጽዋማትና በዓላት 11 ናቸው፡፡ እነዚህም ጾመ ነነዌ ፣ በአተ ጾም(ዐቢይ ጾም) ፣ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ስቅለት ፣ ትንሣኤ ፣ ርክበ ካህናት ፣ ዕርገት ፣ ጰራቅሊጦስ ፣ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ድኅነት ናቸው፡፡ ሁሉም የሚገቡበትን ለማወቅ መሠረታቸው ነነዌ ነው፡፡ → ዐቢይ ጾም ነነዌ በገባ በ14ኛው ቀን ይገባል፤ → ደብረ ዘይት ነነዌ በገባ በ41ኛው ቀን ይውላል፤ → ሆሣዕና ነነዌ በገባ በ62ኛው ቀን ይውላል፤ → ስቅለት ነነዌ በገባ በ67ኛው ቀን ይውላል፤ → ትንሣኤ ነነዌ በገባ በ69ኛው ቀን ይውላል፤ → ርክበ ካህናት ነነዌ በገባ በ93ኛው ቀን ይውላል፤ → ዕርገት ነነዌ በገባ በ108ኛው ቀን ይውላል፤ → በዓለ ኀምሳ ነነዌ በገባ በ118ኛው ቀን ይውላል፤ → ጾመ ሐዋርያት ነነዌ በገባ በበ119ኛው ቀን ይገባል፤ → ጾመ ድኅነት ነነዌ በገባ በ121ኛው ቀን ይገባል፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ የነነዌ መግቢያ ከታወቀ ሌሎቹን ማግኘት ቀላል ነው፡፡ ❖ ነነዌን ለማግኘት ደግሞ ጥልቅ ከሆነው የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ ግድ ነው፡፡ ከብዙ መንገዶች ውስጥ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡ ❖ ነነዌን ለማግኘት ዓመተ ዓለም፣ መጥቅዕ፣ ወንበር፣ መደብ፣ የዕለታት ተውሳክ፣ መባጃ ሐመር፣ ዐቢይ ቀመር፣ ማእከላዊ ቀመር፣ ንኡስ ቀመር የተባሉትን የስሌት ጽንሰ ሐሳቦችን መረዳት ተገቢ ነውና በቅድሚያ እነርሱን እያብራራን እናስላ፡፡ ✥ ዓመተ ዓለም፦ የዘመነ ብሉይና የዘመነ ሐዲስ ድምር ነው፡፡ በመሆኑም የዘንድሮው ዓመተ ዓለም 5500 + 2014 = 7514 ይሆናል፤ ✥ ዐቢይ ቀመር፦ በባሕረ ሐሳብ ትምህርት በየ502 ዓመቱ የሚመጣውን ዑደት (ሳይክል) ዐቢይ ቀመር እንለዋለን፡፡ (ወንጌላውያን በየዐራት ዓመቱ የሚመጡ መሆናቸውን ዐውደ ወንጌላውያን በሚለው ቃል፣ ዓመት የ365/6 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ዓመት በሚለው ቃል፣ ወር የ30 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ወርኅ በሚለው ቃል፣ ሳምንት የ7 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ሳምንት በሚለው ቃል እንደምንገልፀው በየ502 ዓመቱ የሚከሰቱ ክስተቶችን በዐውደ ቀመር እንጠራቸዋለን፡፡ ቁጥሩንም ዐቢይ ቀመር እንለዋለን፡፡) ብዙ ማብራሪያ ያለው ቢሆንም ለጊዜው ዐቢይ ቀመር 502 ዓመት መሆኑን መያዝ በቂ ነው፤ ✥ ማእከላዊ ቀመር፦ ይህ 76 ዓመት ነው፤ ✥ ንኡስ ቀመር፦ ይህ 19 ዓመት ነው፤ ✥ መደብ፦ ማለት ዓመተ ዓለም ለዐቢይ ቀመር ተካፍሎ፣ ቀሪው እንደገና ለማእከላዊ ቀመር ተካፍሎ፣ የዚህም ቀሪ እንደገና ለንኡስ ቀመር ተካፍሎ ከውጤቱ ባሻገር የሚገኘው ትርፍ/ቀሪ ነው፡፡ ★ የ2014 ዓ.ም መደብ → ዓመተ ዓለም / ዐቢይ ቀመር = 7514/ 502 = 14 ደርሶ 486 ይቀራል፤ → ቀሪው/ ለማእከላዊ ቀመር = 486/76 = 6 ጊዜ ደርሶ 30 ይቀራል፤ → ቀሪው / ለንኡስ ቀመር = 30/19 = 1 ደርሶ 11 ይቀራል፤ ★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መደብ 10 ነው፡፡ ✥ ወንበር፦ ማለት ደግሞ ዓመተ ዓለም ለንኡስ ቀመር ተካፍሎ ከውጤቱ ባሻገር ከሚገኘው ቀሪ ላይ 1 ሲቀነስ የሚገኘው ውጤት ነው፡፡ ★ የ2014 ዓ.ም.ወንበር → 7514 / 19 = 395 ደርሶ 9 ይቀራል → 9 – 1 = 8 ★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም ወንበር 8 ነው፡፡ ✥ መጥቅዕ፦ ማለት ነጋሪት ማለት ነው፡፡ ነጋሪት ሲመታ ሕዝብ አንደሚሰበስብ በመጥቅዕ የተሰየመው ዕለት ደግሞ አጽዋማትንና በዓላትን ስለሚሰበስብ መጥቅዕ ይባላል፡፡ መጥቅዕን ለማግኘት የዘመኑን ወንበር በ19 በማባዛት ውጤቱ ከ30 ቢበልጥ ለ30 ከተካፈለ በኋላ የሚገኘው ትርፍ የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል፡፡ ከ30 ባይበልጥ ግን የተገኘው ውጤት የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል፡፡ ★ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ = የ2014 ዓ.ም ወንበር X 19 = 8 X 19 = 152 → 152 ከ30 ስለሚበልጥ ለ30 እናካፍለዋለን። → 152 / 30 = 5 ደርሶ 2 ይቀራል፤ ★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነው። ✥ መጥቅዕ ከ14 ከበለጠ በመስከረም፣ ከ14 ካነሰ በጥቅምት ይውላል፡፡ ❖ የዘንድሮው መጥቅዕ 2 በመሆኑና ከ14 በማነሱ የሚውለው በጥቅምት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው፡፡ የ2014 ዓ.ም ጥቅምት 2 የዋለው ማክሰኞ ዕለት ነበር፡፡ ✥ የዕለታት ተውሳክ፦ ማለት ምን እንደሆነና ከየት እንደተገኘ ለማወቅ አንባቢን ከመጻሕፍት እንዲያነብ በመጋበዝ የዕለታት ተውሳክን እንጠቁም። √ የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው፤ √ የእሑድ ተውሳክ 7 ነው፤ √ የሰኞ ተውሳክ 6 ነው፤ √ የማክሰኞ ተውሳክ 5 ነው፤ √ የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው፤ √ የሐሙስ ተውሳክ 3 ነው፤ √ የዓርብ ተውሳክ 2 ነው፡፡ ✥ መባጃ ሐመር፦ በዓለ መጥቅዕና የበዓለ መጥቅዑ ዕለተ ተውሳክ ተደምረው የሚገኘው ውጤት ከ30 ባይበልጥ መባጃ ሐመር ይባላል፡፡ የበዓለ መጥቅዑና የዕለቱ ተውሳክ ተደምረው ድምሩ ከ30 ቢበልጥ ከድምሩ ላይ 30 ተቀንሶለት ተራፊው መባጃ ሐመር ይባላል፡፡ መባጃ ሐመር ጾመ ነነዌን ለማግኘት የሚያገለግል ቁጥር ነው፡፡ ★ የ2014 ዓ.ም መባጃ ሐመር → የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ + የመጥቅዑ ዕለተ ተውሳክ (የመጥቅዑ ተውሳክ 5 ነው ምክንያቱም ጥቅምት 2 ማክሰኞ ስለዋለና የማክሰኞ ተውሳክ ደግሞ 5 ስለሆነ ነው፡፡) → 2 + 5 = 7 ★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መባጃ ሐመር 7 ነው፡፡ ✥ በመሆኑም የ2014 ዓ.ም ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 ይገባል ማለት ነው፡፡ በዚህ መንገድ ነነዌ አንዴ ከተገኘ ሌሎቹን አጽዋማትና በዓላት በመደመር ብቻ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ ✥ የ2014 ዓ.ም ዐቢይ ጾም የሚገባው መች እንደሆነ ለማወቅ ቀደም ሲል «ዐቢይ ጾም ነነዌ በገባ በ14ኛው ቀን ይገባል» ስላልን ከነነዌ ተነሥተን በመቁጠር ማወቅ እንችላለን። • የ2014 ዓ.ም ዐቢይ ጾም መግቢያ = የካቲት 7 + 14 = የካቲት 21 • የ2014 ዓ.ም ደብረዘይት = የካቲት 7 + 41 = መጋቢት 18 • የ2014 ዓ.ም ሆሣዕና = የካቲት 7 + 62 = ሚያዝያ 9 • የ2014 ዓ.ም ስቅለት = የካቲት 7 + 67 = ሚያዝያ 14 • የ2014 ዓ.ም ትንሣኤ = የካቲት 7 + 69 = ሚያዝያ 16 • የ2014 ዓ.ም ርክበ ካህናት = የካቲት 7 + 93 = ግንቦት 10 • የ2014 ዓ.ም ዕርገት = የካቲት 7 + 108 = ግንቦት 25 • የ2014 ዓ.ም በዓለ ኀምሳ (ጰራቅሊጦስ) = የካቲት 7 + 118 = ሰኔ 5 • የ2014 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት = የካቲት 7 + 119 = ሰኔ 6 • የ2014 ዓ.ም ጾመ ድኅነት = የካቲት 7 + 121 = ሰኔ 8 አጽዋማቱንና በዓላቱን የበረከትና የረድዔት ያድርግልን፡፡
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.