cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጽሞና ቲዩብ

ሰላም ውድ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች እንኳን ወደ ጽሞና ቲዩብ የቴሌግራም ቻናል በደና መጡ 🙏🙏🙏 በቻናላችን ላይ የተለያዩ ✔️መዝሙሮች ከነ ግጥማቸው ✔️አጫጭር አስተማሪ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ✔️ እና ከመናፍቃን የሚመጡ ይርጥሮችን በተቻለው ሁሉ መልስ ለመስጠትና ወደቀናችው ሀይመኖት እንዲመለሱ ፣ እኛም በሃይማኖታችን እንድንፀና ፣ እንወያያለን።

Show more
Advertising posts
1 181
Subscribers
-324 hours
-107 days
-5230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እግዚአብሔር ሲቀጣን "አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገጽ 36)
Show all...
1
Look Here 🙄 👀👀 😱
Show all...
Show all...
Story of 𝘿𝙖𝙫𝙚_𝙮𝙚_𝙖𝙧𝙨𝙚𝙢𝙖_𝙡𝙞𝙟

#ጸሎታቸው_የማይሰማው_ለምንድን_ነው? ክቡር ዳዊት ሲናገር፡- “እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል” ብሏል (መዝ.4፡3)፡፡ በዚህ መነሻነትም፡- “ታዲያ ብዙ ሰዎች ጸሎታቸን የማይሰማው ለምንድን ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነዚህ ሰዎች የማይጠቅማቸውን ጸሎት ስለሚጸልዩ ነው፡፡ አዎ! በዚህ ጊዜ ጸሎታቸው ባይሰ’ማ ለእነርሱ በጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር የማይረባንን ነገር በለመንነው ጊዜ፥ ልመናችንን የሚሰማ ቢኾን ኖሮ ጸሎታችን በመሰማቱ ብቻ ደስ ባልተሰኘን ነበርና፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን ተጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመስግነው፡፡ የማይረባንን ነገር ለምነነው ጸሎታችን ከሚሰማን ባይሰማን ይሻለናልና፡፡ አንዳንድ ጊዜም ጸሎታችን በግድየለሽነት የሚቀርብ ከኾነ፥ እግዚአብሔር መልሱን ያዘገይብናል፡፡ ለምን? ከልብ የመነጨ ጸሎት እስክናደርስ ድረስ! ይህ በራሱ ለእኛ የሚሰጠው በቁዔት ቀላል አይደለምና፡፡ መጽሐፍ እንዳለ “እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ ከእናንተ በላይ የስጦታን ምንነት፣ መቼ መስጠት እንደሚገባ፣ ምን መስጠትም እንዳለበት የሚያውቅ እግዚአብሔርም መስጠት ያውቅበታል።" (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው። ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ’ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ’ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
Show all...
Show all...
Notcoin

Probably nothing @notcoin

Show all...
TikTok · Memeher Dr Zebene Lemma

439 likes, 79 comments. “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች @Memeher Dr Zebene Lemma”

​​ እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የኪዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
🌷✝ 7ቱ ኪዳናት ✝🌷
=>'ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት' እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው:: +እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን:: "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ" "ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)
1. " ኪዳነ አዳም "
=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1) +አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)
2. " ኪዳነ ኖኅ "
=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)
3. " ኪዳነ መልከ ጼዴቅ "
=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር:: +እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)
4. " ኪዳነ አብርሃም "
=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)
5. " ኪዳነ ሙሴ "
=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)
6. " ኪዳነ ዳዊት "
=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)
7. " ኪዳነ ምሕረት "
=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ:: +በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው:: +የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: +የእርሷ ኪዳን 6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ የኪዳናት ማሕተም ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው:: +እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ: ማርያም እሙ ለእግዚእነ: በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"
=>የአርያም ንግሥት: የሰማያውያንና ምድራውያን ኁሉ እመቤት: የአምላክ እናት: ቅድስት: ስብሕት: ክብርት: ልዕልት: ቡርክት: ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት: ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት:: በዚህች ዕለት የካቲት 16 ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጁዋ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል:: በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳት አያይም ብሏታል::
=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን:: በዓሉንም የሰላም: የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::
✞ የካቲት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት / የእመቤታችን አክስት / የሶፍያ ልጅ) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም) ✞ ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 2.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 3.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 4.አባ ዳንኤል ጻድቅ
=>" . . . ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች:- አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጀሮየ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና:: ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈፀማልና ያመነች ብፅዕት ናት:: "[ሉቃ. 1:39]
✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞ ✞ወለወላዲቱ ድንግል ✞ ✞ወለመስቀሉ ከቡር አሜን ✞ @Tsimonatube
Show all...
🥰 2
"አንች ሱላማጢ ሆይ ተመለሺ" የፅጌ የስደተኛዋ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በእንባ የሚዘመር የንስሀ መዝሙር ተመለሺ ሱላማጢስ “አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ።” (መኃልየ. 7፥1) ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ(እመቤቴ) ተመለሺ የአባትሽን ቤት አትርሺ ኢሳይያስ ተንብዮልሽ ፈጣን ደመና ያለሽ ጌታን በጀርባሽ አዝለሽ በግብጽ በረሃ የዞርሽ የበረሃው ሙቀት ንዳድ የሌሊቱ ግርማ ከባድ በአራዊቱ ድምጽ ሁካታ ልብሽ በጭንቅ ሲንገላታ #አዝማች ስለ ልጅሽ ተርበሻል ጥማትንም ተጠምተሻል ድካም መንገድ እንግልቱ እንዴት ቻልሽው አዛኝቱ የልጅሽን ነፍስ የሻቱ ጠላቶቹ ስለሞቱ መሰደዱ ይበቃሻል ቅድስት አገር ይሻልሻል #አዝማች በኢትዮጲያም እለፊ ደብረ ቁስቋም ላይም እረፊ ለዘላለም ከብረሽ በአርያም ንገሽ #አዝማች የበደሌ ሸክም በዝቶ ብሰደድም ጽድቄ ጠፍቶ በይ መልሺኝ ከደጃፍሽ በክንዶችሽ እቅፍ አርገሽ በዓለም ስጓዝ አንቺን ትቼሽ ከእኔ ርቆ ፍቅር ጣዕምሽ በበደሌ በኃጢአቴ ዛሬ እንኳን ብሸሽ ተመለስ በይኝ እመቤቴ በእናትነትሽ #አዝማች ለአዳም ተስፋው መድኃኒቱ ድንግል ማርያም አዛኝቱ በኃዘንሽ በስደትሽ ታጥቦ ይጥራ እድፌ በእንባሽ በቃኝ ዛሬስ ተሸነፍኩኝ እናቴ ሆይ በይ መልሺኝ ፍቅር ጣዕምሽ ታትሞብኝ ዛሬ ድኅነት በአንቺ እንዳገኝ ተመለሺ እመቤቴ ተመለሺ በልቤ ኑሪ ተመለሺ ስለ ኃጢአቴ አትሽሺ https://t.me/Abele88475927 https://t.me/Abele88475927
Show all...