cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎ

በዚህ ቻናል የቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎእናዮእሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Show more
Advertising posts
233
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት) (የዐብይ ጾም እኩሌታ) ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓልሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው። ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡ ፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች "እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡ ፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/ ፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች “ራብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/ ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ተዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት አይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ “እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/ ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው። “ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል። አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ  “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል። የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና። “የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/ ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ ያስተዉል እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል። “ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሐሰተኞች ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሐንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ  “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።https://t.me/melkbirhttps://t.me/melkbir
Show all...
ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ 14 ዓመት በኋላ በ 628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ አንድም ዘወረደ ማለት «ዘወረደ » ማለት « የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ዮሐ.3-13፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው ፡፡ ዘወረደ ማለት? ምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ነው ፡ ዘወረደ ስንል አምላክ መጣ ፤ ረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ፤ ፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው ፡፡ ወረደ በአምላክ ትህትና ክብረ አዳም የሚነገርበት ነው ፡፡ ምላክ ሰው በመሆኑ ሰው አምላክ ሆነ ፤ ከበረ ፤ ገነነ ፤ ነገሠ ፡፡ ያው አምላክ ክርስቶስ በቅድስት ሞቱ ሟቹን አዳም ዘላለማዊ ሕያው አደረገው ፡፡ አምላክ ወልደ አምላክ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶ ለአዳም ያለውን ታላቅ ፍቅር ገለጸ ፡፡ ተጣላውን አዳምን በፈቃዱ ታረቀው ፡፡ ላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ፥ ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በሕይወቱ እንድናለን ፡፡ ሮሜ. 5 ፥ ፲ ፡፡ በዚህም ትህትናን ፍቅርን አስተማረን ፡፡ በዚህ በመጀመርያው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦ በግዕዝ፦ እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ በአማርኛ፦ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። ምስጋናና ውበት በፊቱ ነው፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። (መዝ.፺፭(፺፮)፡፭ በዚህ በመጀመርያው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ! ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንምይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? ማቴ.፮፡፲፮-፳፭ ጾም ስጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለስጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነዉ፡፡ ሆኖም የጾም ወቅት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም ማንኛዉም ሰዉ ጾሙን ሲጀምር የሚከተሉትን ጉዳዮች በደንብ ሊያጤናቸዉ ይገባል፡፡ የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል። በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰበሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን። ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።https://t.me/melkbir
Show all...
አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎ

በዚህ ቻናል የቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎእናዮእሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

✝እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን የካቲት 13 ☞ፆም ማለት ምን ማለት ነው? ☞የአብይ ስያሜዎች ስንት ናቸው ☞የአብይ ፆም ለምን ታላቁ ጾም ተበለ ☞የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት ☞የአብይ ጾም ለስንት ሳምነታት ይጾማል ☞ስለ መጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ምን ያውቃሉ 1ኛ. ፆም ማለት ምን ማለት ነው? ፆመ ፦ ተወ " ታቀበ"ታረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። ፍቹም ምግብን መተው ' መከልከል' መጠበቅ ማለት ነው። ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት ነው። ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው ። ፆም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ፆም አለ። ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው ። ነብያት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር።//ዘፀ ፴፬÷፳፰//34*28// በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በፆም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። //ዮሐ ፪÷፯_፲// 2*7-20// በሐዲስ ኪዳንም ፆም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ ስጋዌው የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።//፬÷፪// 4*2// ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በፆም እሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል።// ማቴ ፲፯÷፳፩// 17*21/ሐ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙ ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በፆም እና በፆለት ላይ እንዳሉ ነበር።// የሐዋ ፲፫÷፪//13*2// ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በፆምና በፆለት ነበር።//የሐዋ፲፫÷፫//13*3// ፆምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው። ፆም ማለት፦ጥለላት ማባልዕትን ፈፅሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ ፣መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ፆም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ፀጋን የምትሰጥ ፣የወንጌል ስራ መጀመሪያ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው ፣የንፅህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የእንባ መገናኛ መፍለቂያ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምትነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒት ነፍስ ናት። ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገስታት፣ካህናት በፆምና በጸሎት ፅሙድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልንም እንዲያጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል። በሀድስ ኪዳን ፆም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው። // ማቴ፭÷፮// 5*6// ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ስጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው። ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች:አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው። ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች። ~~~ስለዚህ የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል። በእምነት ሁኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን ምስጢር ለማየት ከአለማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል። በአለም እየኖረ ከአለሙ ይለያል። ከአለም አይደለምና// ዮሐ፲፭÷፲፱//15*19 // 2ኛ. ዐቢይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው፡፡ ዐቢይ ጾምየተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐቢይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ /መዝ.47፥1፣ መዝ.146፥5/፡፡ ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው፡፡፣ /አሞ.7፥1/፡፡ ሦስተኛ በዓተ ጾም ይባላል፡፡ የጾም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓት ማለት ነው፡፡ አራተኛ ጾመ አርባ ይባላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 /ዓርባ/ ቀን ስለሆነ፣ /ማቴ.4፥1/ አምስተኛ ጾመ ኢየሱስይባላል፡፡ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣ ስድስተኛ ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው፡፡ ዐቢይ ጾምጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ማቴ.4፥1 ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት /55 ቀኖች/ አሉት፡፡ ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሑድ ይገኛሉ፡፡ አሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡ 3ኛ. የአቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች 1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው። 2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው። 3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው። ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው። 4ኛ. የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤ ዘወረደ ቅድስት ምኩራብ መጻጉዕ ደብረዘይት ገብርሔር ኒቆዲሞስ ሆሣዕ ሰለ ተትርጉማቸው ከታች ከተለጠፈው ሰንጠረዥ ተመልከት 5ኛ. ለምን አብይ / ታላቅ ተባለ አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም በመሆኑ ነው 6ኛኛ. የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ 614 ዓ . ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! አብይ ጾም ------------------------------- @Ethiopian_Orthodox ------------------------------- ጾም ማለት "ተወ" ታቀበ "ታረመ"ካለው የግዕዝ የቃል የተገኘ ነው። ፍቺውም ምግብ መተው መከልከል መጠበቅ ማለት ነው። ጾም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት ነው። ወይም ሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው። ጾም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ። 🌿ጾም በብሉይ ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው። ነብያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር። (ዘፀ 30÷34*28) 🌿በኃጢአት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። (ዮሐ2÷7-10//2*7-20) 🌿በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሲ መድሐኒታችን በመዋዕለ ሰጋዌው የሰራ መጀመሪያ አድረጎ የተሰራ ህግ ነው። 🌿ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግራል።//ማቴ 17÷21 🌿ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙት ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በጾም እና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር// ሐዋ 13÷2// 🌿ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር።የሐዋ// 13÷3// ጾምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው። ፆም ማለት ጥለላት ማባልዕት ፈፅሞ መተው ሰውነትንም ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንሰሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበረከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ፆም ነፍስን ቁስልን የምትፈውስ፣ ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምትሰጥ የወንጌል ስራ መጀመሪያ ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው የንፅህና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት የእንባ መገናኛ መፍለቂያ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድሐኒት ነፍስ ናት። ከህግ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገሥታት፣ ካህናት በፆም ናበጸሎት ፅመድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልም እንዲጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል። በሀዲስ ኪዳን ጾም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው።// ማቴ 5÷6// ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ሰጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው። ጾም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው። ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች ~~~ ስለዚህም የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል። በእምነት ሆኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን ምስጢር ለማየት ከዓለማዊነት ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል። በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል። ከዓለም አይደለምና //ዮሐ 15÷19// ✝አብይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው። አብይ ጾም የተለያዩ ስሞች አሉት: ፩. አብይ ጾም: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐብይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ //መዝ 47÷1 መዝ 146÷5// አቢይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆን ለማሳወቅ ነው። ይህ ጾም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መጾሙና ከሌሎች አፅዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾምም በመሆኑ ነው። ፪. ሁዳዴ ጾም: ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው።፣ /አሞ 7÷1 // ፫. በዓተ ጾም : ፆም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓል ማለት ነው ፬. ጾመ አርቦ: ጌታችነ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉ 40// አርባ ቀን ስለሆነ ነው //ማቴ 4÷1 ፭. ጾመ ኢየሱስ : ጾሞ ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣ ፮. ጾመ ሙሴ : ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ "ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት" እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው። 🌿አቢይ ጾም ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው። //ማቴ 4÷1 ምእመናንም ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል። 🌿አቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት //55 ቀኖች // አሉት። 7//ሰባት ቅዳሜ 8//ስምንት እሁድ ይገኛሉ። አስራ አምስት ቀን 55//ማለት ነው። ከጥሉላት እንጂ ከእህል ወኃ ስለማይጾሙ የጾሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል። የአብይ ጾም ሶስት ክፍሎች ፩. ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል) ፣ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ያረሰ ያለው 7 ቀን ነው። ፪. የጌታ ጾም ፣ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው አርባ ቀን ነው። ፫. ሕመማት፤ ይህ ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጡበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት ፰ ቀን ሕማማት ነው። ይህም ፯+፵+፰=፶፭(7+40+8=55)ቀን ይሆናል። የአብይ ጾም ሳምንታት ፰ ሲሆኑ:     ፩. ዘወረደ     ፪. ቅድስት     ፫. ምኲራብ     ፬. መጻጉዕ     ፭. ደብረ ዘይት     ፮. ገብርሔር     ፯. ኒቆዲሞስ እና     ፰. ሆሣዕና ናቸው። ጾሙን ጾመን ድኅነት የምናገኝበት የበረከት እንዲሁም ቤተክርሰቲያናችንን ከመዓት የምንታደግበት ያድርግልን! አሜን! ://t.me/melkbir https://t.me/melkbir
Show all...
አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎ

በዚህ ቻናል የቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎእናዮእሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

[ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዛሬው ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ] "ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው "ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስም እስካሁን ከሚጠቀሙበትም ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የኤጲስ ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። ሀይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል። ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል። በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ" "አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል። 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ[ቤተ ክህነት] ገብተዋል። ... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን ።"https://t.me/melkbir https://t.me/melkbir
Show all...
አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎ

በዚህ ቻናል የቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሥልሳዎእናዮእሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

በጾም ወቅት ኅሊናችን ማሰላሰል ያለበት ሰው ምን አለ? ወይም ምን አደረገ? በሚለው ሳይሆን እግዚአብሔር በፊቱ ምን ዓይነት ሰው እንድንሆንለት ይፈልጋል? በሚለው ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ጾማችን በዚህ መንፈስ የተቃኘ ፍቅረ፣ እግዚአብሔርንና ፍቅረ ቢጽን ማእከል ያደረገ፣ መጠራጠርንና አለመተመማንን ያስቀረ፣ የተለያዩትን ያቀራረበ፣ የተሳሳቱትን ያረመ በአንጻሩ ደግሞ ሁላችንን በሰላምና በፍቅር አንድ አድርጎ ያስተሳሰረ ይሆን ዘንድ በዚህ መንፈስ ተነቃቅተን እንድንጾመው አባታዊ ጥሪያችንን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻም በሀገራችን እየታየ ያለው የሰላም ጭላንጭልና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ዝንባሌ ለሁለንተና ልማታችንና ለዕድገታችን እንደዚሁም ለተሟላ አንድነታችን ጠቃሚነቱ የጎላ ስለሆነ እግዚአብሔር ለዘለቄታው እንዲያሳካልን ከልብ እንድናዝንና ወደ አምላካችን በተመሥጦ እንድንጸልይ በአጽንዖት በማሳሰብ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ መልካም የጾም ወራት ያድርግልን! እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
የዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያስተላለፉት መልእክት! • በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ! እንደ ስሑትና ደካማ ሰብአዊ ባሕርያችን ሳይሆን እንደ አባታዊ ቸርነቱ ሁል ጊዜ በምሕረቱ የሚጐበኘን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዐቢይ ጾም አደረሰን፤ አደረሳችሁ! • “ንጹም ጾመ፣ ወናፍቅር ቢጸነ፣ እስመ ከማሁ አዘዘነ፤ ጾምን እንጹም፤ ባልንጀራችንንም እንውደድ፣ እንዲህ አዞናልና” (ቅዱስ ያሬድ) እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ስንኖር እንድናደርገው ያዘዘን ዐቢይ ነገር ቢኖር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ እየመገበ የሚገኘው በፍቅር ነው፡፡ እኛንም ከፍዳ ኃጢአት ያዳነን በፍቅር ነው፤ ሕይወታችንና ንብረታችን ተጠብቆ የሚኖረው ፍቅር ሲኖር ነው፡፡ ግላዊና ማኅበራዊ ኑሮአችን እንዲሁም ሃይማኖታዊ አምልኮአችንና የተግባር እንቅስቃሴአችን በሙሉ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ፍቅር ሲኖር ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ በረከት እንጂ ጉድለት የለም፤ በፍቅር ውስጥ ጤና እንጂ በሽታ የለም፤ በፍቅር ውስጥ ጽድቅ እንጂ ኃጢአት የለም፤ በፍቅር ውስጥ እግዚአብሔር እንጂ ዲያብሎስ የለም፡፡ ይህም በመሆኑ ቅዱስ መጸሐፍ ፍቅርን ‹‹የሁሉም ነገር ማሰሪያ ነች›› በማለት ይገልጻታል፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሁሉም የምትበልጠው ታላቋ ትእዛዝ ‹‹ፍቅር›› እንደሆነች ከመግለጹም በላይ ኦሪትና ነቢያት ሁሉ በእርሷ እንደሚጠቃለሉ አስተምሮናል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ፍቅርን እንደ ዓይን ብሌን ስንጠብቃት በእጅጉ የምትጠቅመንን ያህል ስንተዋት ደግሞ በእጅጉ ትጎዳናለች፡፡ በፍቅር እጦት የሚደርሰው ጉዳት በተወሰነ ነገር ብቻ ሳይሆን በነፍስም ሆነ በሥጋ፣ በምድርም ሆነ በሰማይ እጅግ በጣም የገዘፈና የሰፋ ነው፡፡ በሀገራችን የሆነውና እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡ ፍቅርን ባጣንባቸው ዓመታት ከየት ወዴት እንደደረስን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚገነዘበው ነው፡፡ ያተረፍነው ነገርም ምን እንደሆነ የምናውቀው ነው፡፡ ይሁንና የፍቅር እጦት ምን ያህል እንደጎዳን ራሳችን ተገንዝበን ወደ ሰላሙ መንገድ መመለሳችን የተሻለ አማራጭ መሆኑን ሳንመሰክር አናልፍም፡፡ የተጀመረው የፍቅርና የሰላም ጉዞም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ልባዊ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡ ይህንን ሰላም እንዲመጣ ያደረጉ ወገኖችም ሁሉንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ ምክንያቱም በሰዎች መካከል ፍቅርንና ሰላምን የሚያደርጉ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚባሉ ጌታ እንደ አስተማረን ብፅዕና ይገባቸዋልና ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፱) የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! የፍጹም ፍቅር መገኛ የሆነው ቅዱስ ወንጌል የሚያስተምረው ፍቅር ራስን ማፍቀር ወይም መውደድ ሳይሆን ራስን መጥላት ባልንጀራን ግን መውደድ እንደሆነ ነው፡፡ “ወንጌላዊ-ፍቅር ፍጹም ነው” የሚያሰኘውም ቅሉ ይህ ነው፡፡ ለሁለት ሺህ ዘመናት ያህል በቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ባህልም ይህን ፍቅር ጠብቆ የሚጓዝ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አበው መነኮሳት ከነበራቸው ፍቅርና ትሕትና የተነሣ፣ የሹመት ሽሚያ አያውቁም ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር ትልቁን ሥልጣን ይቅርና የአንድ ገዳም መሪ ለመሆንም በእግር ብረት ታስረው በግድ ካልሆነ በቀር እሺ ብለው በፈቃደኝነት ሹመትን አይቀበሉም ነበር፡፡ ራሱን በራሱ መሾም ወይም እኔን ሹሙኝ ብሎ መናገርና የሌላን ድጋፍ መጠየቅ ለኢትዮጵያውያን መነኮሳት ጭራሽ ነውርና ጸያፍም ነበር፡፡ ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ለሦስት ሺህ ዘመናት የዘለቀው ሃይማኖታችን ምንም ዓይነት መለያየት ሳያጋጥመው አንድ ሆኖ ሊዘልቅ የቻለው ያም በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያናችን ጠንካራ አንድነት ለሕዝቡም በመትረፉ የሀገሪቱን አንድነትና ነጻነት አስጠብቆ እስከ ዘመናችን ሊደርስ ችሎአል፡፡ በዚህም ቤተ ክርስቲያናችን የሕዝብንና የሀገርን አንድነትና ነጻነት ለማስጠበቅ ያደረገችውና የምታደርገው ጥረት ሊያስመሰግናት እንጂ ሊያስወቅሳት አይገባም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ከቅርብ ቀናት ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ተከሥስቶ የነበረውን ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት የቤተ ክርስቲያናችንን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ባሕላዊ መርሕን የናደ፣ እንደዚሁም በኢትዮጵያ ይቅርና በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ድርጊት እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ድምፅ በመስማትና በመቀበል ሕዝበ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር ባቀረቡት ኀዘንና ጸሎት እንደዚሁም ባደረጉት መጠነ ሰፊና ዙርያ መለስ የሆነ የድጋፍ ርብርብ ስሕተቱ ሊታረም ችሏል፡፡ ለተገኘው መንፈሳዊ ውጤትም ጠቅላይ ሚንስትርና መንግሥታቸውን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲከበር ከፍተኛ መሥዋዕትነት ለከፈለው መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሁም ይህ ስሕተት እንዲታረም ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ተሰልፈው ድምፃቸውን ላሰሙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርብላቸዋለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ግልጽ ማድረግ የምንፈልገው ከቤተ ክርስቲያናችን ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት መከበር እንደዚሁም ከሉዓላዊ አንድነቷ መጠበቅ በመለስ ያለው ጥያቄ ለማስናገድ ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መሆኗን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ሕዝቦች በቋንቋቸው የመማር፣ የማስተማርና የማምለክ እንዲሁም የመተዳደር መብትን ካሁን በፊትም፣ አሁንም፣ ካሁን በኋላም የምትነፍግበት መሠረት እንደሌለም ሁሉም ሊያውቀው ይገባል፡፡ ይህም በመሆኑ በቋንቋ የመጠቀም መብት በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ምዕራፍ ፪ አንቀጽ ፭ ከቁጥር ፩ እስከ ፫ ባለው አንቀጽ በሚገባ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ስለሆነም በቋንቋ የመጠቀም ጥያቄ በሕግ ደረጃ ተመልሶ በተግባር እየተሠራበት የሚገኝ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡ የተወዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ዛሬ ታላቁን ጾም በፍቅር ሆነን የምንጾምበት ወቅት ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ጾም ማለት ሥጋዊ ፈቃድን በመግታት ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ለማድረግ የሚካሄድ መንፈሳዊ ተጋድሎ ነው፡፡ በጌታችን ጾም በተግባር እንዳየነው ጾም ማለት ዲያብሎስ የሚሸነፍበት በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አሸናፊዎች የሚሆኑበት ኃይል ነው፡፡ ስለሆነም ጾም የተጋድሎና የሙዓት ሜዳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የምንታገለውም ልብሰ ሥጋ ሰውን ሳይሆን ረቂቅ ፍጡር የሆነው ሰይጣን በሰው አድሮ የሚነዛውን አጥፊ ሐሳቡንና ድርጊቱን ነው፡፡ ከዚህም ጋር ሰውነታችን ለዚህ ክፉ መንፈስ ታዛዥ እንዲሆን የሚገፋፉ ጥሉላት መባልዕትን መተው፣ ኃይለ ሥጋን መቈጣጠር፣ ኃይለ መንፈስን ደግሞ ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ በጾም ወቅት የተራቡትን ማጉረስ፣ የታረዙትን ማልበስ፣ የተበደሉትን መካስ፣ ፍትሕና ርትዕ በማኅበረ ሰብ ውስጥ ማንገሥ ያስፈልጋል፡፡
Show all...
ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡ ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡ በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡ በመግለጫውም፡- ፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡ ፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡ በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
Show all...
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ:: በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡ በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡ ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡
Show all...
መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር “እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ” የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Show all...