cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Show more
Advertising posts
429Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
መጽሐፍ ቅዱስን #ለመረዳት ✧ መጽሐፍ ቅዱስ በእድሜ ባለጸጋ መጽሐፍ ነው!! ተጽፎ ለመጠናቀቅ እንኳን ከ1500 ዓመታት በላይ ፈጅቷል!! ✧ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል የተነበበ መጽሐፍ የለም!! ከዚህም ዘመን በኋላ ገና ይነበባል!! ✧ መጽሐፍ ቅዱስ ተወዳጅ መጽሐፍ ነው፤ ተነቦ የሚጣል መጽሐፍ አይደለም!! በዚህ ጊዜ ራሱ ሰው ሮጦ ያነሳው፥ ወጥቶ የፈለገው መጽሐፍ ቅዱስን ነው!! ✧ መጽሐፍ ቅዱስ በሽያጭ ተወዳዳሪ የሌለው መጽሐፍ ነው!! በየዓመቱ በብዙ ሚሊዮን ኮፒዎች ይሸጣል!! በቅርቡ አማዞን ሽጦ እንደጨረሰ ማሳወቁን ሰምተናል!! ✧ የማተሚያ ማሽን የተሰራው መጽሐፍ ቅዱስን ለማባዛት ጭምር ነበር፡፡ Johann Gutenberg በ1455 ዓ.ም መጽሐፍ ቅዱስን በጀርመንኛ ቋንቋ በማተም የሕትመት ታሪኩን ጀመረ። ✧ መጽሐፍ ቅዱስ "የእግዚአብሔር መንፈስ ደራሲው" የተባለለት ብቸኛ መጽሐፍ ነው!! ✧ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የሚፈልገው ብቸኛ መጽሐፍ ነው!! ሌሎቹ መጻሕፍት ...ከእርሱ የሚነሱ ወይም እርሱን የሚተረጉሙ ናቸው!! ✧ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ መጽሐፍ ብቻ አይደለም፤ በሁለቱም ኪዳናት የተጻፉ ቅዱሳት መጽሐፍትን በውስጡ አካቶ ይዟል!! ✧ እያንዳንዱ መጽሐፍ በምዕራፍ እና በቁጥር የተከፈለ ሲሆን አጠቃላይ 1,189 ምዕራፎች እና ከ 31,000 በላይ ቁጥሮች አሉት!!
Show all...
ተለቀቀ!!! Watch "በሕይወት መዝገብ ጻፍከኝ #ከድቅድቁ ጨለማ ወደ ሚደንቅ ልዩ ብርሃን #ጻፍከኝ #Zemari hawaz tegegn #New song 2022 #Behiwot mezgeb" on YouTube https://youtu.be/samKE6hCfr0
Show all...
ለስልክ መጥሪያ Ringtone ቡሩክ ትሁን ጌታን ያወቅሁባት እለት ወንጌል የተረዳሁበት ቡሩክ ትሁን ጌታን ያወቅሁባት እለት ዳግም የተወለድኩበት   https://t.me/tetelestaye
Show all...
ለሁሉ መልስ ያለውን መልስ አግኝተነዋል!! #ኢየሱስ፦ ውኃ አጠጪኝ? ሳምራዊቷ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? ...አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበር። ይህን ጥያቄ አንድ ሌላ አይሁዳዊ ሊጠይቃት እንደማይፈልግ ታውቃለች!! #ኢየሱስ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር። ...ለመስጠት መነሻችን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው!! "ውኃ አጠጪኝ" ያላት የሚጠጣ ውኃ ነው!! ወደ እርሷ የመጣው ውኃ ፈልጎ አይደለም፤ እርሷን እንጂ!! ...የእርሱን ማንነት ብትረዳ የሚበልጥ የሕይወት ውኃ ለእርሷ አለው!! ሳምራዊቷ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል። ...እርሱ ሙሉውን ውኃ ሰጠ፥ ሰው መቅጃ አዘጋጀ!! #ኢየሱስ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ። ... እርሱ የሚሰጠውን ውኃ ባሕርይ አስረዳት፤ ይሄኛውን ያዕቆብ ቆፍሮ አያወጣውም!! ይሄኛው ውኃ አንዴ ከጠጡት (ከምንጩ ጋር መገናኘት) ለዘላለም አያስጠማም!! ከጉድጓድ ሳይሆን ከውስጥ የሚፈልቅ ነው!! ሳምራዊቷ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ? ...አሁን ስፍራዋን ያዘች፦ ለማኝ እንጂ ተለማኝ አይደለችም!! እርሱ ለቃሉም በቃሉ ለተገኘውም ውኃ ምንጭ ነው!! ውኃ እርሱ እንጂ እርሷ የላትም!! በእርግጥ ያለ ቀጠሮ ያገኛት ይሄን ውኃ ሊሰጣት ገዶት ነው!! #ኢየሱስ፦ ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ። ሳምራዊቷ፦ ባል የለኝም!! #ኢየሱስ፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ። ..."በዚህስ እውነት ተናገርሽ" ሳምራዊቷ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ። ...በመጀመሪያ እንደ ገመተችው አይሁዳዊ ብቻ እንዳልሆነ ገባት!! ከእርሷ ወይም ከተራው አይሁድ በተለየ መንገድ እንደሚያይ ገባት። አባቷ ያዕቆብ የሌለው ነገር እርሱ ውስጥ አየች። ጥያቄዋን ከፍ አደረገችው። ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለአይሁድም ለሳምራውያንም ከባድ እና አከራካሪ የሆነ ጥያቄ አነሳች። "አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም(አይሁድ) ፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ" ...የፈለገችው ሳምራውያን ወይም አይሁድ ከሚያስቡት የተለዬ መልስ ነው!! #ኢየሱስ፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ...የአዲሱ ኪዳን የአምልኮ ባሕርይ ተብራራላት!! ሳምራዊቷ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ #ሲመጣ #ሁሉን ይነግረናል!! ...መሲሑ በአይሁድም በሳምራውያንም እየተጠበቀ ነበረ፤ ሁሉን መናገር የሚችል መፍትሔ መሆኑን ያምኑ ነበር!! አይደንቅም? የሴቲቱ ልብ እርሱን ይጠብቅ ነበረ፤ መሲሁን የምትጠብቀው ደግሞ ከፍ ላለ ነገር ነው፤ የግሏን ጥያቄ ሳይሆን ብሔራዊ ጥያቄ አቀረበች። #ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ!! ...ለካ መልሱ ነው የሚመልስላት!? ያዋራት ... የጠበቀችው (የተቀባው) የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው!! ..."መሲሁ ነኝ" ሲላት አፍራ እና ፈርታ ወደ ራቀቻቸው ወገኖቿ ሄደች፤ እንስራዋን የመያዝ አሳብ እንኳን አልመጣላትም!! ወገኖቿ ይህን ሰበር ዜና እስኪሰሙ ቸኮለች፤ የከተማው ሰው ግልብጥ ብሎ መጣ!! ሃሌ ሉያ!! ይህ ጌታ አግኝቶናል!! ሃሌ ሉያ መሲሁን አግኝተነዋል!! ከአሕዛብ ወገን ስለነበርን የተስፋ ቃሎቹ አልነበሩንም ነበር!! እግዚአብሔር የሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ በእርሱ አዎን ሲሆን [ሲፈጸም] ግን ምስራቹ እኛም ጋር ደርሶ ለሁሉ መልስ ያለውን መልስ አግኝተነዋል!! አሜን!!
Show all...
❝የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤❞ —ቆላስይስ 3፥16። https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን እይታ ማመን በአንድ ወቅት እስራኤላውያን ...በምድያማውያን ከፍተኛ ጥቃት ይደርስባቸው ነበረ። በዚህም ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ ፍርሃት ወደቀ። በዚህ ጊዜ ነበረ፦ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ጌዴዎን የመጣው። መልአኩም፦ "አንተ #ጽኑዕ #ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው" አለው። [መጽሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 6 ይመልከቱ] ጌዴዎን ይህን መገለጥ ሲቀበል በምን ሁኔታ ነበር? ምድያማውያንን #ፈርቶ #ተደብቆ ስንዴ እየወቃ ነበር!! እግዚአብሔር ...ይህን ሰው ነው፦ "አንተ #ጽኑዕ እና #ኃያል ሰው" ያለው!! ምላሹ፦ "ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል" የሚል ነበር። ከንግግሩ ...በጥያቄ የተሞላ፣ ተስፋ የቆረጠ፣ ራሱን እና ሕዝቡን እንደ ተጣሉ የቆጠረ ሰው መሆኑን መረዳት እንችላለን። እግዚአብሔር ...ይህን ሰው ... "አንተ #ጽኑዕ እና #ኃያል ሰው" ሲለው በደስታ ነው!! ጌዴዎን ይህን የእግዚአብሔር እይታ ከመቀበል ይልቅ የወገኑን ተጠቂነት እና የራሱን ታናሽነት መናገር ቀጠለ!! ❝እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ ከምናሴ ነገድ #ከሁሉ ይልቅ #የተጠቃ ነው፤ እኔም በአባቴ ቤት #የሁሉ #ታናሽ ነኝ አለው።❞ —መሳፍንት 6፥15። እግዚአብሔር ግን ከአቋሙ ፍንክች አላለም!! የእርሱ አብሮነት የሚያመጣውን ውጤት ያውቃል!! ❝እግዚአብሔርም፦ በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው።❞ —መሳፍንት 6፥16። እንደ አንበጣ እየተግተለተሉ የሚመጡ ምድያማውያንን እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው!! ጌዴዎን ግን ተጨማሪ ምልክት ጠየቀ፤ ክፍሉን ተመልከቱት!! የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር ስለእኛ ካየው በተቃራኒው ማሰብ የለብንም!! አንድ ነገር አስረግጨ ልንገራችሁ? እግዚአብሔር ስለራሳችን ያለንን የተሳሳተ አመለካከት መቼም አያጸድቅልንም!! እርሱ የሚቆጥረው በክርስቶስ ያደረገንን ነው!! እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን እይታ ማመን ይጠበቅብናል!! አሁን በምን ሁኔታ እንዳላችሁ አላውቅም፤ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ፤ #እናንተን ያላችሁበት ሁኔታ አይተረጉማችሁም!! ትክክሉ ...እናንተ ስለራሳችሁ ያመናችሁት ሳይሆን እግዚአብሔር ስለእናንተ ያለው ነው!! ራሳችንን፣ ቤተሰባችንን እና ዙሪያችንን አይተን ... ስለራሳችን የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ የለብንም!! ከእግዚአብሔር እይታ ተነስተን ራሳችንን ብናየው እንዴት አስደናቂ እንደሆንን በቃላት ልገልጽላችሁ አልችልም!! ፈሪ፣ ድንጉጥ፣ የተጠቃ፣ የተተወ፣ የማይጠቅም ... አድርጎ ራሱን የቆጠረውን ሰው ... እግዚአብሔር "...አንተ #ጽኑዕ #ኃያል ሰው፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ" አለው!! እይታውን አስተካክሎ እንዲዘምት አደረገው፥ የአባቱን ጣኦት አፈረሰ፥ ምድያምን ድል አደረገ፥ የእስራኤል ምድር አርባ ዓመት አረፈች። እግዚአብሔር ስለእኛ ያለውን እይታ እንያዝ!! እግዚአብሔር ስለራሳችን እንዲገባን የፈለገውን ከተረዳን ያስፈሩንን ሁሉ ድል እናደርጋለን!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ፍቅርህ ልቤን ከነካው ከለወጠው ሰንብቷል ያኔ ለጋ ሳለሁ ከውስጠቴ ዘልቆ ገብቶ ቤቱ አስቀረኝ ነፍሴን ማርኮ (2x) አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ፀጋህና ምህረትህ ለመዳኔ ምክንያት ሆነኝ ለማምለጥ ከኩነኔ በመስቀል ላይ በሰራኀው ታላቅ ስራ እኖራለሁ በመስቀል ላይ በሰራኀው ታላቅ /ገድል ይሄው አለሁ አዝ፦ ነፍሴ አጥታልህ ለአንተ መግለጫ እንዲህ ትላለች ቢያረካህ ብላ (2x) ሕይወቴ ያክብርህ በቀረው ዘመኔ ከእንግዲህ አይኑረኝ ምኖረው ለእኔ (2x) ወደእግዚአብሔር የሚያደርሰው እውነት ሕይወት መንገድ ኢየሱስ ነው የሰው ልጅ በከንቱ እንዳይለፋ ሁሉን ፈጸመ ሰጠው ተስፋ የዳነ ሰው ጌታ ያለው በማንነቱ ከቶ አይደለም መወደዱ መመረጡ ዓለም ገና ሳይፈጠር በክርስቶስ የመረጠውን አጸደቀው አከበረው ማንም እንዳይመካ በስራው አይደለም ማንም እንዳይታበይ በስራው አይደለም (2x) https://t.me/tetelestaye
Show all...
ልዩነታችን / Liyunetachen /grace worship sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ https://t.me/tetelestaye
Show all...
መመገብ . . . የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ መመገብ አለብን። ሰውነታችን ለመኖር ምግብ እና ውሃ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ነፍሳችንም መንፈሳዊ ምግብ ያስፈልጋታል። መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት እንጀራ ሲሆን አዘውትሮ ማንበብ ለመንፈሳዊ ጤንነታችን አስፈላጊ ነው። በየቀኑ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ጊዜ በማሳለፍ እንዲናገረን እና እንዲመራን መፍቀድ አለብን። “የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ . . .” — ቆላስይስ 3፥16 (አዲሱ መ.ት ) 💎 Rev. Tezera Yared Blessed day! https://t.me/tetelestaye
Show all...
Helina Dawit " ይቅርታዬ " የክብር ልብሷን ለብሳ እንደ ቆመች ንጉሱ ፊት የወርቁንም ዘንግ እንደ ነካች ጥያቄዋን እንደመለሰላት እኔም እየሱስን ለብሼ አብ ፊት ሞገስ አገኘው አባ አባት ማለት ድፍረቴ ተመለሰልኝ ወደ ህይወቴ አባቴ የማለት እምነቴ ተመለሰልኝ ወደ ቤቴ የመማጸኛ ከተማዬ ዘልዬ የማመልጥበት ከአሳዳጅ ከአስጨናቂዎቼ ተሸሽጌ ምገባበት እየሱስ በተባለው ድንቅ ስም ነፍሴ አርፋለች ከምንም እርሱ የከፈለውን ዋጋ አልፎ ማነው እኔን ሚነካ በደም የከፈለውን ዋጋ ደፍሮ ማነው እኔን ሚጠጋ ከሳሾቼ ብዙ ናቸው ተጨባጭ መረጃ አላቸው በህጉ መሰረት ቢሄዱ አሳማኝ ነው ምክኒያታቸው በየትኛው ቅድስናዬ ልጋፈጥ ልቁም ለራሴ አንገት መድፋት መሸማቀቅ ዝምታ ብቻ እንጂ መልሴ የቤቴ ክፍተት ሳይገፋው ገፍቶ ባይገባ ከደጄ የልቤ ርቀት ሳይመልሰው ባያቅፈኝ ባይሆን ወዳጄ ሁሉን በራሱ ፈጽሞ ባያደርገኝ ኖሮ ቀና ጽድቄ ብዬ ማስቆጥረው የማሳየው ምን አለና ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ኢየሱስ ሆኖኝ ነው ይቅርታዬ ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ስለሆነኝ ነው ይቅርታዬ ____ like & share በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ https://t.me/tetelestaye
Show all...
እንደ ንስር መታደስ ❝ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ #ጕልማስነትሽን #እንደ #ንስር ያድሳል።❞ መዝሙር 103፥1-5። እፎይ!! ነፍሳችንን እንደ ዳዊት እንዲህ እናውራት!? ውለታውን፣ ፍቅሩን፣ ምሕረቱን፣ መልካምነቱን፣ በጎነቱን፣ ቸርነቱን፣ አባትነቱን፣ ባርኮቱን፣ እረኝነቱን፣ ፈዋሽነቱን፣ አቅርቦቱን እና ቅርብነቱን ለነፍሳችንን እናስታውሳት!! እግዚአብሔር መልካም ነው!! እንዴት ድንቅ አምላክ ነው!? ቀናችንን እንዲህ በእርሱ በመደነቅ እንጀምረው!! እግዚአብሔር ይባረክ!! ሃሌ ሉያ!! ዳዊት "ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ" ካለ በኋላ 6 የምስጋና ርእሶች ጠቅሷል!! • ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ • ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ • ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ • በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ • ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ • ጕልማስነትሽን #እንደ #ንስር ያድሳል!! ለዛሬ "ጕልማስነትሽን #እንደ #ንስር ያድሳል" የሚለው ቃል ላይ ጥናት እናደርጋለን። ዳዊት ነፍሱን እንዴት እንዳገለገላት አስተዋላችሁ? እኛም (በክርስቶስ ያለን አማኞች) የነፍሳችንን መዳን መቀበል ወይም አእምሯችንን ማደስ ይጠበቅብናል!! (ሮሜ 12፥2፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፥8-9)። "እንደ ንስር መታደስ" ... የሚለውን በጥልቀት ለመረዳት የንስርን አኗኗር እንመልከት!! 1. ንስር በከፍታ ላይ ይበራል!! ንስር የሚበርበትን ከፍታ ሌሎች የወፍ ዝርያዎች ሊደርሱበት አይችሉም!! ❝የንስር መንገድ በሰማይ❞ —ምሳሌ 30፥19። እኛም በክርስቶስ የከፍታ ስፍራ ይዘናል!! ከማይመጥነን ስፍራ እና አኗኗር እንላቀቅ!! 2. ንስር አጥርቶ ያያል!! ንስሮች 5 ኪሜ ርቀት ድረስ የማየት አቅም ተሰጥቶታል!! በቃሉ እና በመንፈሱ ሕይወትን አጥርተን እንይ!! ነገሮችን እግዚአብሔር እንደሚያይ ማየት እንጀምር!! ይህ የተባረከ እይታ ነው!! ንስር አርቆ አጥርቶ እንደሚያይ እኛም ጥሪያችንን እና የመጥራቱን ተስፋ አጥርተን እንይ!! 3. ንስር የሞተ ነገር አይመገብም!! ንስር ጥምብ አንሳ አይደለም!! ምን እንደምንሰማ? ምን እንደምናይ? እንጠንቀቅ!! ከኢየሱስ በሆነው ጤናማ ቃል አእምሯችንን እናድስ!! (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥3)። 4. ንስር አውሎ ነፋስ አይፈራም!! የንፋሱን ብርታት ከደመና በላይ ለመብረር ይጠቀምበታል!! ኃይለኛ ነፋስ ሲነሳ ሌሎቹ አእዋፋት ይደበቃሉ!! ንስር ግን አውሎ ነፋሱን ወደ ከፍታ መውጫ ያደርገዋል!! የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች ለመልካም እንጠቀማቸው!! 5. ንስር ፈትኖ ያምናል!! ሴቷ ንስር ወንዱን ንስር ከመገናኘቷ በፊት በትክክል እንደሚወዳት ማረጋገጥ ትፈልጋለች!! ራሷን ወደ ትልቅ ከፍታ ካወጣች በኋላ ክንፎቿን ሰብስባ ወደ መሬት ለመድረስ ጥቂት እስኪቀራት ድረስ ትወረወራለች። ያን ጊዜ ወንዱ ተወርውሮ ካልያዛት እና ካላነሳት መሬት ሳትደርስ አፋፉ ላይ ራሷ ትነሳለች። ወንዱ ባል እንዲሆናት አትፈቅድም። ሁሉን እንድንፈትን፥ መልካሙን እንድንይዝ በቃሉ ታዘናል!! (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥ 20-21)። 6. ንስር ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል!! ሴቷ ንስር ከመውለዷ በፊት ለሚወለደው ንስር ቤት ያዘጋጃሉ። እግዚአብሔር ለሚፈልገው አላማ በቃሉና በመንፈሱ እንዲያዘጋጀን እንፍቀድ!! ቀጥሎ በሕይወታችን ምን እንዲሆን እንፈልጋለን? ሊሆን ላለው ነገር በነገር ሁሉ እንዘጋጅ!! 7. ንስር ራሱን በማደስ ያምናል!! እድሜው ሲያረጅ እንደ ቀድሞው ከፍ ብሎ መብረር ይከብደዋል። ያኔ ራቅ ያለ ስፍራ ይመርጣል፤ ላባውን እየነቀለ ያራግፋል፤ አዲስ ላባ እስኪያበቅል ይቆያል። ከዚያ በአዲስ ኃይል ይመለሳል። እኛም የአሮጌውን ሰዋችንን ባሕርይ እና አስተሳሰብ አውልቀን እንጣል!! የአዲሱን ሰው ባሕርይ እና አስተሳሰብ እንግለጥ!! ❝...ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።❞ (ኤፌሶን 4፥22-24)። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ ... #ጕልማስነትሽን #እንደ #ንስር ያድሳል!! አሜን!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ካረካህ ከወደድከው | ዳንኤል አ/ሚካኤል sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ https://t.me/tetelestaye
Show all...
እኔ #እረኛውን አውቀዋለሁ!? የተለያዩ የተሰጥኦ ውድድሮች የሚካሄዱበት አዳራሽ ነው። እንደ ወትሮው ጢም ብሎ ሞልቷል። በየጊዜው ብቃቱን በማሳየት አሸናፊ የሆነው ዝነኛ ድምፃዊ ወደ መድረክ ወጣ። ታዳሚው በፉጨት፣ በጩኸት እና በጭብጨባ ተቀበለው። እርሱም ቀኝ እጁን አንስቶ እጅ ነሳ። ማይኩን አንቆ ያዘ። በሰላምታ ንግግር ጀመረ። "ዛሬ ያልተለመደ ነገር አቀርብላችኋለሁ። ሰሞኑን አንድ መዝሙር ሰምቼ ወድጄዋለሁ፤ የዳዊት መዝሙር ነው አሉ፤ በተለይ ዜማው እጅግ በጣም ይገርማል" አለ። መዝሙር ሃያ ሦስትን በዜማ ያንጎራጉረው ጀመረ፤ ሕዝቡ በጩኸት ማጀቡን ቀጠለ። ድምፁ ያምራል፤ ዝነኛ ነው፤ መዝሙሩን በደንብ አጥንቶታል፤ ሜጀር ጠብቆ ነው እያዜመ ያለው። ሙዚቃው አብዷል። አዳራሹ ድብልቅልቅ አለ። ዝነኛው ጨረሰ። አድናቂዎቹ እጃቸውን እስኪያልበው ማጨብጨብ ቀጥለዋል። ከዚያ አንድ ያልተለመደ ሰው ወደ ፊት እየተራመደ ወጣ። ወደ መድረኩ ተጠጋ። አርቲስቱን "እባክህ ይህን መዝሙር ደግሜ እንድዘምረው ፍቀድልኝ" አለው። ዝነኛው አቀንቃኝ "እሽ፥ በደስታ፥ እባክህ ና" ብሎ ወደ መድረኩ ጋበዘው። ማይክ ሰጠው። እርሱም ሰላምታ ለሕዝቡ ሰጠና። መዘመር ጀመረ። ድምፁ ብዙም አያምርም። ታዋቂ አይደለም። እርሱ ግን መዝሙሩን ቀጥሏል። አዳራሹ ውስጥ ሰው የሌለ እስኪመስል ድረስ ፀጥታ ነገሰ። የሚጮህ ወይም የሚያጨበጭብ ሰው አልነበረም። መዝሙሩ ግን እየተዘመረ ብዙ ደቂቃዎች አልፈዋል። ጨረሰ። ሁሉም ከተቀመጠበት ተነስቶ አጨበጨበ። በጣም የሚገርመው ፀጥታው የመነካት ምልክት ነበረ። መዝሙሩ እስኪያልቅ ሁሉም እያለቀሰ ነበረ። በነገሩ የተደነቀ አንድ ጋዜጠኛ ወደ መድረክ መጣና "እኔን ጨምሮ ሁላችንም በጣም ተነክተን ነበረ፤ እያለቀስን ነበረ፤ ፤ ምንድን ነው የተለየ ያደረከው ነገር?" አለው። ዘማሪው "ምንም የተለየ ነገር አላደረኩም፤ ነገር ግን #እረኛውን አውቀዋለሁ" አለው። ዝነኛው ዘፋኝ #መዝሙሩን ያውቀዋል፤ ይሄኛው ደግሞ እረኛውን ማለትም #የሚዘመርለትን እግዚአብሔርን ያውቀዋል። ስለ እርሱ መዘመር እና እርሱን መዘመር ይለያያል። መዝሙሩን ማወቅ እና ተመስጋኙ ጌታ ጋር መነካካት ይለያያል። "እረኛዬ እረኛዬ ነህ፤ የነፍሴ ጠባቂ፤ ከአንበሳ እና ከድብ ከአውሬው ከነጣቂ፤" እያለ አንዱ ዘማሪ ሲዘምር የምር የእረኛው ሕልውና ይታወቅሀል፤ እረኛው ራሱ እዚያ እንዳለ ይሰማናል!! ሌላው ሲዘምር ደግሞ አብረን እንዘምራለን ግን .... ጆሮ ያለው ይስማ!! እረኛውን የምታውቁ ለሌሎች ሸር አድርጉ ልበላችሁ? https://t.me/tetelestaye
Show all...
. "ያለ ምክንያት" ዘማሪ ሀና ተክሌ 〰〰〰〰〰〰〰 ስፈራ ስቸር ማልተነፍሰው ሚስጥሬ በዝቷል እኔ ባልናገር የልብ ወዳጄ የውስጤን ያውቃል እርሱ እንደሚያውቀኝ ሰው አያውቀኝም እንጂ መቆም አልችልም እንኳን በንጉሥ በራሴም ደጅ የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል (፪x) ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ ነው የልብ ወአጄ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ እንዳትወደኝ በመልካምነቴ ይህ አይደለም ማንነቴ እንዳትጠላኝ ደግሞ በጥፋቴ ፍቅር ነህ አያስችልህም አባቴ ያለ ምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም የአንተ ፍቅር መነሺያው ከራስህ የመውደድ ልብ የማያልቅብህ (፪x) የእኔ ጌታ ከወዳጅ ከፍቶ ልጅህ ድርሻዬን ብሎ እርም እንዳላለ አልመች ቢለው የሸፈተበት አባቴን አለ አባትነቱን የበደል ብዛት መች ይሽረዋል ሁልን እረስቶ ደግሞ እንደገና ልጄ ይለዋል በምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ ነው የልብ ወአጄ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ 🎼🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣 🌻 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 🎼🎼 https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቃል ሥጋ ሆነ ከሂጶው ቅዱስ አውግስጢን “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ….ቃልም ሥጋ ሆነ፤” ዮሐ ፩፥፩–፪፤፲፬ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”(ዮሐ ፩፥፩) አቤት፣ እንዴት ያለ ታላቅ ስብከት ነው! ከቃል በፊት ስለነበረው ማወቅ ስለምን ትሻላቹ? በቃ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥”፡፡ ቃል የተፈጠረ ቢሆን ኖሮ፣ ቅዱስ መጽሐፍ በዘፍጥረት ላይ “በመጀመሪያው እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ፡፡” (ዘፍ ፩፥፩) እንዳለው፣ “በመጀመሪያው እግዚአብሔር ቃልን ፈጠረ፡፡” ይለን ነበር፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቃልን አልፈጠረም፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው ቃል ስለነበረ፡፡ እንኪያስ ይኼ በመጀመሪያው የነበረው ቃል የት ነበር? ጸሐፊውን ተከተሉት እባካቹ! “በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡” ይላቹኻል፡፡ ግና በእኛ ማኅበረሰብ ሠርክ የሰዎችን ቃላት ስንሰማ ስለምንውል፣ ቃል የሚለውን ስያሜ እንደ ተራ ነገር ልንወስደው እንችላለን፡፡ ይሄንን ቃል እንደ ተራ ነገር እንዳታዩት፣ ይሄ “ቃል እግዚአብሔር ነበርና፡፡” ይኼው ቃል ደግሞ፣ “ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፥ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳችስ እንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” ተብሎለታል፡፡ እባካችኹ ወገኖቼ ልባችሁን አስፍታቹ ደካማ አነጋገሬን አግዙልኝ፡፡ መግለጽ ለቻልኩት ነገር ጆሮ ስጡ፣ መግለጽ ላቃተኝ ነገር ደግሞ እናንተው በጥልቅ ተመሰጡበት፡፡ አውጠንጥኑት፡፡ ስለዘላለማዊ ቃል ማን ሊያብራራ ይችላል? ሁሉም ቃሎቻችን ድምጽ አላቸው፤ ግን ይጠፋሉ፡፡ ማን ዘላለማዊውን ቃል ሊያብራራ ይችላል? ማንስ በውስጡ ያደረውን ቃል ሊያከርም ይችላል? ይሄን ዘላለማዊ ቃል ታብራሩ ዘንድ ትሻላችኁን? እንግዲያውስ ሟች ሥጋችሁን አትከተሉ፡፡ ምክንያቱም ሟች ሥጋችሁ ጊዜያዊ ነውና፤ ዘላለማዊነትም በእርሱ ዘንድ የለምና፡፡ ልክ በስውር እንዳለው የተፈጥሮ የውኃ ምንጭ ሰዎች ይወለዳሉ፤ ይኖራሉ፤ ይሞታሉ፡፡ ከየት እንደመጡ ወዴት እንደሚሄዱ አናውቅም፡፡ ስውር ውኃ ነው፤ ከምንጩ ከወጣ በኋላ ይፈሳል፤ በመንገዱም ሲፈስ ይታያል፤ ደግሞ እንደገና እባህር ውስጥ ገብቶ ይደበቃል፡፡ ይሄ ትንሽ ጅረት ይፍሰስ፣ ይሩጥ፣ ይሰወር እንተወው፡፡ “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤”ጸንታች ልትኖሩ ትሻላችኁን? “የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።” (፩ኛ ጴጥ ፩፥፳፬–፳፭) ግን እኛን ለመታደግ፣ “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥” (ዮሐ ፩፥፲፬)፡፡ ቃል ሥጋ ሆነ ስንል ምን ማለታችን ነው? ወርቁ ሣር ሆነ ማለታችን ነው፡፡ ሣር የሆነው በእሳት ለመቃጠል ነው፤ ሣሩ ሲቃጠል ወርቁ እንዲቀር፡፡ ወርቁ ከሣሩ ጋር አብሮ አይጠፋም፤ ሣሩን ይለውጠዋል እንጂ፡፡ እንዴት ይለውጠዋል? ያስነሳዋል፤ ይቀሰቅሰዋል፤ ወደ ሰማይ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በአብ ቀኝም ያስቀምጠዋል፡፡ ምን አልባት አንድ ሰው “ግን እንዴት ሊሆን ይችላል? ዓለም ሁሉ ለእርሱ የሚገዛለት፣ ያለውና የነበሩት በእርሱ የተፈጠሩበት፣ ያ የእግዚአብሔር ቃል እንዴት ራሱን አሳንሶ በአንዲት ድንግል ማኅጸን ውስጥ አደረ? እንዴትስ መልዓክቱን ትቶ፣ በአንዲት ድንግል ማኅጸን ውስጥ ራሱን ገደበ? ” ብሎ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ የመለኮትን ነገር ትረዱ ዘንድ አትችሉምና፡፡ የሚሳነው የሌለ የመለኮት ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ እንዳለ ከእግዚአብሔርነቱ ሳያጎድል፣ ወደ እኛ መጣ፤ በሥጋ እኛ ዘንድ እንደመጣው ሁሉ በእግዚአብሔር አብ እቅፍም ሆነ፡፡ በሥጋ ባይወለድ እንኳን ከጥንትም ታናሽ አልነበረም፡፡ ከሥጋው በፊት እርሱ “ነበር”፤ እናቱንም ፈጠራት፡፡ በማኅጸኗ የሚያድርባትን እናቱን አስቀድሞ መረጣት፤ ሥጋ የሚሆንባትን እናቱን ፈጠራት፡፡ ስለምን ትደነቃላቹ? እማወጋቹ ያለሁት እኮ ቃል እግዚአብሔር የነበረ ስለመሆኑ ነው፡፡ በእኔ ዘንድ ቃል ነበር፤ ያም ቃል በድምጽ አድርጎ እናንተ ዘንድ ተገለጠ፤ የእግዚአብሔር ቃል በአብ ዘንድ ነበር፣ እርሱም በሥጋ ተገለጠ፡፡ ታዲያ እሱ በሥጋው ያሻውን እንደሚያደርገው ሁሉ እኔም በድምጼ ላይ ላደርግ እችላለውን? ድምጼ ከእኔ ከወጣ በኋላ የእሱ ጌታ አይደለሁምና፤ እርሱ ግን እንዲወለድ፣ እንዲኖር፣ ግብሩን እንዲከውን የሚያደርገው የቃሉ ጌታ ብቻ ሳይሆን፣ ቢሞትም እንኳን ሕያው የሚያደርገውና የሚያስነሳውም፣ እኛ ዘንድ ከመምጣቱ በፊት፣ ቀድሞ ከነበርው ከአባቱ ክብር ዘንድ ከፍከፍ የሚያድርግም ጭምር እንጂ፡፡ የክርስቶስን ሥጋ ሸማ ብላቹ ልትጠሩት ትችላላቹ፣ መሣሪያ ብላቹ ልትጠሩት ትችላላቹ፣…. በመጨረሻም እርሱ ራሱ ደጋግሞ እንደነገረን “መቅደስ” ብላቹ ልትጠሩት ትችላላቹ፡፡ ይሄ መቅደስ ከእንግዲህ ሞት አያውቀውም፡፡ መኖሪያ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ነው፡፡ በዚሁ መቅደስ በቶሎ ይመጣል፤ በሙታንም ላይ ይፈርዳል፡፡ በቃል ያስተማረውን በኑሮው አሳይቶ ምሳሌነቱን አሳይቷል፡፡ በገዛ ሥጋው ላይ ያሳየው፣ በሥጋ ላሉት ተስፋ ማድረግ እንዳለባቸው ይነግራቸዋል፡፡ ምንም እንኳን የሚታይ ነገር ባይኖሩ ተስፋ የሚታደርጉትን በቶሎ በእጃቹ የሚያስገባ እምነት ነው - ይሄ ተስፋ፡፡ አሁን የሚያስፈልጋቹ፣ የማታዩትን በማመን መጽናት ነው፤ የማታዩትን የምታዩበት ጊዜ በመጣ ቀን አንዳታፍሩ ያደርጋችኋል፡፡ https://t.me/tetelestaye
Show all...
. #ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንደፈወስከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንደማርከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንዳቆምከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንዳፅናናኸኝ ይታወቅልኝ በቃ በተባለው ላይ በቃ እኔ ባልኩት ላይ በቃ ሰዎች ባሉት ላይ እረዳቴ መተህ የለወይ ልጠይቀኝ መተህ የለወይ ልትፈታኝ መተህ የለወይ ልትፈውሰኝ መተህ የለወይ ጠያቂዬ መተህ የለወይ ወንድም ጋሼ መተህ የለወይ የሞተ ነገሬን ጎበዝ ተነስ ያለው ማነው የጠፋ ነገሬን ጠርቶ ያመጣው ማነው ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው ወድሀለው መድሀኒቴ ስለመጣህ ወደ ቤቴ ስለመጣህ ወደ ህይወቴ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ይታወቅልኝ -||- በረከት ተስፋዬ መልካም ቀን ♥️ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ክርስቶስ ማን ነው? እውቁ እንግሊዛዊ የወንጌል አገልጋይ የሆነው ጆርጅ ዋይትፊልድ (1714-1770 ዓ.ም) የዛሬ ሦስት መቶ ዓመት፣ ዊሊያምስበረግ በሚገኘው የብሩቶን ፓሪሽ ቤተክርስቲያን ውስጥ በታህሳስ 16፣ 1739 ዓ.ም በማቴዎስ 22፡42 ላይ ተመስርቶ አንድ ስብከት ሰብኮ ነበር፤ ስብከቱን እያዳማጡት ለነበሩት ምዕመናን፣ ከአንድ ሺ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን የጠየቀውን ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቋል፤ “ስለ ክርስቶስ ምን ታስባላችሁ?”፡፡ የዋይትፊልድ አጠያየቅ ከጌታችን ጥያቄ ትንሽ ለየት ቢልም፣ ጥያቄው የሚያስከትለው ዘላለማዊ ምላሽ ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢየሱስ ይሄን ጥያቄ በጠየቀበት በወቅት የነበሩት አንዳንድ ምላሾች —“መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ ነው”፤ “ከነብያት አንዱ ነው”፤ “ኤልያስ ነው” (ማር 8፡ 27-28 ይመልከቷል) —ዋይትፊልድ ጥያቄውን ባነሳበት ጊዜ ይሰጡ ከነበሩ መልሶች ጋር ተመሳስሎሽ አላቸው፡፡ በዲይዝም አስተሳሰብ ከተጠመቱ እንደ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ያሉ (የዋይትፊልድ ወዳጅ ነው) ሰዎች ኢየሱስ ተወዳዳሪ የማይገኝለት አስተማሪ ነበር እንጂ ምንም የመለኮትነት ባሕሪ የሌለው ሰው ነበር ብለው ይናገሩ ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መለኮትነቱን ያምኑና በአንዳንድ ነገሩ መለኮትነቱ ከአብ ያነሰ ነው ይላሉ፡፡ ዋይትፊልድ ግን “ኢየሱስ ክርስቶስ ‘ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እወነተኛ አምላክ’ ባይሆን፣ ከእንግዲህ ወንጌል አልሰብክም፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ካልሆን ወንጌል ሊሆን አይችልም፤ እንዲያ ከሆነ ወንጌሉ አንድ የሞራል ሥነምግባር ሥርዓት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡” ብሎ ለቃሉ ታማኝ በመሆን ያለምንም መሸማቀቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ መሆኑን ለሰዎች መስክሯል፡፡ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለመሆኑ ምስክር በመላው ዐዲስ ኪዳን እናገኛለን፡፡ ኢየሱስ “አምላካችንና መድኃኒታችን” (ቲቶ 2፡13) ተብሎ በማያሻማ ሁኔታ ተጠርቷል፡፡ የእግዚአብሔር ሙላት በእርሱ ይኖራል (ቆላ 1፡19፤ 2፡9)፡፡ በብሉይ ኪዳይ ‘ያህዌ’ ብቻ ይጠራባቸው የነበረባቸው ስሞች እርሱም ተጠርቶባቸዋል (ኢሳ 44፡6 እና ራዕይ 1፡17 በማዛመድ ይመልከቷል)፡፡ ተመላኪ ሆኖ ቀርቧል (ዕብ 1፡6)፤ ሐዋሪያት ወደ እርሱ ጸልየዋል (ሐዋ 7፡59-60፤ 1ኛ ቆሮ 16፡22፤ 2 ቆሮ 12፡8)፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውንም አደርጓል (ዮሐ 1፡3፤ ቆላ 1፡16)፤ ኀጢአትን ይቅር ብሏል (ማር 2፡5-10፤ ቆላ 3፡13) በመጨረሻውም ቀን በኀጢአተኞች ላይ ይፈርዳል (ሐዋ 10፡42፤ 17፡31፤ 2ቆሮ 5፡10)፡፡ መላኤ ኵሉነት [omnipresence] (ዕብ 1፡3፤ኤፌ 4፡10)፣ አማሬ ኵሉነት [omniscience] (ራዕ 2፡23)፣ ሃሌ ኵሉነት [omnipotence] (ማቴ 26፡18) እና ኢ-መዋቲነት [immutability](ዕብ 13፡8) ብለን የምንጠራቸው የመለኮት ባሕሪያት ሁሉ ጌታችን አሉት፡፡ የክርስቶስ ፍጹም አምላክነት የወንጌል ሙልዓት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሆነ ሌላ አመለካከት ዐዲስ ኪዳኑን ያዛባል፡፡ ትሥብዕት (Incarnate) የሆነ ነው ስለ ክርስቶስ ማንነት፣ ዐዲስ ኪዳን ሌላም እውነት ይመሰክርልናል—ይኸውም ፍጹም ሰው ስለመሆኑ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ 1ኛ ጢሞ 2፡5 ላይ “ሰው የሆነው ክርስቶስ” ብሎ እንደጻፈው ነው፡፡ ያደገውም እንደማንኛው ሰው ሆኖ ነው (ማቴ 13፡55)፤ መራብን አይቷል (4፡2)፤ መታረዝና መጠማትንም አይቷል (ዮሐ 4፡6-7፤ የሀዘን ዕንባ አፍስሷል (11፡35)፡፡ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ይሁን እንጂ፣ ያለ ኀጢአት ነበር፡፡ የክርስቶስን ሕይወት ስንመለከት፣ “ይኸው ኀጢአቱ” ብለን ልንጠቁምበት የምንችለው አንድም ኀጢአት የለበትም፡፡ የኢየሱስን ሰውነት መካድ፣ ወንጌሉን መሸርሸር ነው (1ዮሐ 4፡1-3፡ 2 ዮሐ 7-9 ይመልከቷል)፡፡ ለድነታችን… ተሰቀለ አያሌ መልካም ነገሮችን ካደረገ፣ ድዊያንን ከፈወሰ እና ወንጌሉን ከሰበከ በኋላ፣ ኢየሱስ በአይሁድና በሮማ ባለሥልጣናት ተያዘ፡፡ እውነተኛውና እንከን አልባው የእግዚአብሔር ወዳጅ፣ አምላክን በመስደብ ክስ ተከሰሰ፡፡ በአይሁድ ዘቦችና በሮማውያን ወታደሮች ሀፍረት በተሞላበት ሁናቴ ተሰቃየ፤ ተገረፈ፤ ወታደሮቹና ዘቦቹ ተዘባበቱበት፡፡ ልብሱን ተገፎ፣ የሚያገለድመው አንዳች እራፊ ጨርቅ ሳይኖረው እርቃኑን በመስቀል ላይ ሞተ (ማር15፡24፤ ዮሐ 19፡23-24)፡፡ ሞቱ በሮማውያን ዘንድ የውርደትና ስቃይ የተሞላበት እንደሆነ በሚታሰበው የመስቀል ሞት ነበር (ዮሐ 19፡16-18፤ ዕብ 12፡2)፡፡ የሕይወት ባለሥልጣን የሆነውና ሙታንን ያስነሣው ጌታ፣ እመቃብር አደረ፡፡ ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ፣ ሲሞት ነፍሱን ሸብቧት የነበረው በአብ የመተው ስሜት ነበር (ማቴ 27፡46፤ ማር 15፡34)፤ በዚያች ቅጽበት በሞቱ በኀጢአተኞች ላይ የነደደውን የእግዚአብሔር ቀጣ ተቀብሏልና (1ቆሮ 15፡3፤ 2 ቆሮ 5፡21፤ ዕብ 9፡11-14፤ 28)፡፡ ሞቱ የምትክነት ሞት ነበር፤ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማብረጃ፡፡ ይሄንን መካድ፣ ወንጌሉን መካድ ነው፡፡ ሞት ግን ኢየሱስን ሊያሸንፈው አልቻለም፤ ሞትም ሆነ ሰይጣን በእርሱ ላይ አንዳች ሥልጣን የላቸውማ (መዝ 16፡10፤ ሐዋ 2፡24-31)፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አብ፣ በመንፈስቅዱስ ኢየሱስን ከሞት አስነሣው (ማቴ 28፡6-7፤ ሐዋ 2፡32፤ ሮሜ 8፡11)፤ ከትንሣኤው በኋላ ለሐዋሪያቱና ለተመረጡት በተለያዩ አጋጣሚዎች ታያቸው (ሐዋ 1፡3-8፤ 1ቆሮ 15፡4-8)፡፡ የሥጋ ትንሣኤውን ገሸሽ ማድረግ፣ ከሥጋ ብዝዎት ተስፋችን ያጎድለናል፡፡ ይሄ ነው ዐዲስ ኪዳን የሚያስተምረን ወንጌል፡፡ ዋይትፊልድ የሰበከው፤ ዛሬ እኛም እንካችሁ የምንለው ወንጌል ይሄ ነው፦ ፍጹም አምላክ የሆነው ክርስቶስ፣ ለእኛ ድነት ሲል ሰው ሆነ፤ ስለ ኀጢአታችንም ሞተ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ተነሣ፡፡ በዚህ ወንጌል እመኑ፤ ትድናላችሁ፡፡ _______
Show all...
ስምህን ጠርቼ ድኛለሁኝና አምላኬ በላይ በላዩላይ ልደርብ ምስጋና አምላኬ እረ እኔ አመለጥኩኝ አንተን በባመኔ አምላኬ በሰዉነቴ ላይ ታወቀኝ መዳኔ አምላኬ ታዲያ እንዴት ዝም ይላል የተደረገለት አምላኬ በድቅድቅ ጨለማ ብርሀን የሆንክለት አምላኬ አምላኬ*6 ክብሬነህ ማረጌ
Show all...
በጸሎት ለአገሮች መጋደል ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ (መዝሙር 2፡8) ሜሴጅ የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሪ ጥቅሳችንን እንዲህ ያስቀምጠዋል፥ “ምን ትፈልጋለህ? ንገረኝ! አገሮችን እንደ ስጦታ? አህጉሮችን እንደ ሽልማት?" ይህን ጥቅስ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁት በ15 ዓመቴ ነው፥ በዚህ ጥቅስ መሠረትም ወደ ጌታ ጸለይኩ። በምላሹ የጌታ መንፈስ፥ “አገሮችን ሰጥቼሃለሁ!” አለኝ። በዚያ ለጋ ዕድሜ፥ በዓለም አገሮች ውስጥ ስላሉ የማያምኑ ሰዎች እና ስላሉበት አስከፊ ሁኔታ ያሳስበኝ ነበር። በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ናቸው እንዲሁም ከእግዚአብሔር ሕይወት ተለይተው ርቀዋል። ተስፋ የሌላቸው እና ያለ እግዚአብሔር ናቸው። ስለዚህ፥ የዓለም ካርታዎች ያሉበት መጽሐፍ (አትላስ) አግኝቼ፥ ብዙ ጊዜ እጆቼን በእሱ ላይ አድርጌ፥ በዓለም መንግስታት እና በሰዎች ሕይወት ላይ እናገራለሁ እንዲሁም እተነብያለሁ። በዓለም ላይ ላሉ ለችግረኞች በጸሎት አምጫለሁ። በጌታ ፊት በብዙ እምባ በተሰበረ ልብ ጸልያለሁ አልቅሻለሁም። አቤት! ለዓለም አገሮች በጸሎት እንዴት እንዳነባሁ! ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድም አገር በእኔ ላይ በሩን ሊዘጋ እንደማይችል ተረድቻለሁ። ዛሬ፥ ጌታ በእኛ በኩል በዓለም አገሮች ውስጥ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን እየሠራ ነው። “ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ... እሰጥሃለሁ” ብሎ ሲናገር፥ ስለ ሰዎች እየተናገረ ነው፥ በወንጌል እና በእግዚአብሔር ጽድቅ ሕይወታቸው ላይ ለውጥን ስለማድረግ ነው። ሐዋርያት ያደረጉት ያንን ነው፥ እኛም ዛሬ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፥ ምንም ነገር ሊያግደን አይችልም። ጳውሎስ በኤፌሶን ቃሉን ሲሰብክ፥ በእርግጥ ብዙ ተቃውሞዎች ነበሩ፥ ነገር ግን የወንጌልን ሥራ የማስቆም አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።” (የሐዋርያት ሥራ19፥20):: የዚህ ዓይነት ውጤት ቁልፉ በጸሎት መጋደል ነው። ለአገራችሁ፣ ለከተማችሁ፣ ለትምህርት ቤታችሁ፣ ለመሥሪያ ቤታችሁ፣ ወዘተ በጸሎት ተጋደሉ፥ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል በዚያ በኃይል ያድጋል፥ ያሸንፋልም። ሃሌ ሉያ! ጸሎት ውድ አባት ሆይ፥ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃንህ እንዲመጡ፥ ከልብ በመነጨ ጸሎት እንድማልድ እና ለጠፉት ወንጌልን እንድሰብክ ፍቅርህ ግድ ይለኛል። ቃልህ በከተማዬና በአገሬ፥ በዓለምም ዙሪያ ያሸንፋል፥ የጌታም ስም ይከበራል። አሜን። https://t.me/tetelestaye
Show all...
✍️ ባልወድሽ ነው ወይ ** በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽሳ በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽሳ እስኪ መልሺ ፣ በይ ልጠይቅሽ በሀዘን ሳይሆን ፣ በመውደዴ አልቅሽ በይማ አንቺዬ...... ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ክብሬን መጣሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መመሳቀሌ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ችንካር የበሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ስቃይ ያስገሳኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መንገላታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ዝም ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ይማርሽ ያልኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግፍ የታገስኩት ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ውርደት መጥገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ፍቅር ማንገቤ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ጥም ያነደደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ አባቴ ያረደኝ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ልሙት ማለቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ መቁሰል መድማቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሲዖል መውረዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ግርዶሽ መቅደዴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ሞትን መርታቴ ባልወድሽ ነው ወይ ፣ ድሉን መስጠቴ እስኪ መልሺ ፣ ልጠይቅሽ ቆይ ሁሉን መሆኔ ፣ ላንቺ አይደለም ወይ በቃ አይወደኝም ፣ ትያለሽ ምነው በቃ ጠልቶኛል ፣ ትያለሽ ምነው እንዲያ መሆኔ ፣ ባልወድሽን ነው በይ ራስሺን ፣ ጠይቂ ራስሽ እንድትመለሽ ፣ በገዛ መልስሽ በስስት አይኖች ፣ በማይዝሉ እጆች እንደ ውድ ሚስት ፣ ልክ እንደ ልጆች ዕቅፍፍፍፍፍ ያረገሽ ፣ ያቀማጠለሽ ሞትሽን ወስዶ ፣ በሞቱ ያዳነሽ አለሽ ወይ ሌላ ፣ እንዲህ 'ወዳጅ ሰው የሞተ ላንቺ ፣ በተደገሰው የሷን ሞት ልሙት ፣ ብሎ ያለልሽ ነፍሱ ላይ ቆርጦ ፣ የጨከነልሽ እና አይወድኝም ፣ ማለትሽ ምነው እኔ 'ምወደው ፣ አንቺን ብቻ ነው ስሚ ይልቅስ አድምጭኝማ ፣ ልንገርሽ ውዴ በአንቺነትሽ ፣ በሥራሽ ሳይሆን በ'ኔነቴ ነው ፣ አንቺን መውደዴ ይሄው ለዚህ ነው በቃ አይወደኝም ፣ እያልሽኝ እንኳን አንደምወድሽ ፣ መንገር 'ማይደክመኝ ባንቺ ተክዬ ፣ የፍቅሬን ድንኳን!! እወድሻለሁ❤❤❤❤❤ #ሄኖክ_አሸብር https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር በማንኛውም ሰአት ትኩስ ነው፤ ቀዝቅዞ አያውቅም! በዘላለም ፍቅር ነው የወደደን! እኛን ያልወደደበት ጊዜ ኖሮ አያውቅም፤ ሁልጊዜ እንደወደደን ነው!? ሃሌ ሉያ!! (ኤር. 31፥3) መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
ብሩክ ትሁን ጌታን ያወኩበት ቀን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀé ሰናይ ምሽት ♥️ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ራሳችንን ባልመረጥንበት ምርጫ መርጦናል!! ከእኛ ባልጀመረ ፍቅር ወዶናል!! ከእኛ ምንም መዋጮ ሳይጠይቅ አድኖናል!! መቼም ልንደርስበት በማንችለው ሰማያዊ ስፍራ አስቀምጦናል!! ማንም ሊሰጠን በማይችለው መንፈሳዊ በረከት ባርኮናል!! አሁንም የጸጋውን ባለጸግነት ይገልጥብናል!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ሰው እንኳን ያለ መንፈስ ቅዱስ ያለ ልብስ ያስፈራል!! ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር መዋል እና ማደር ሲጀምር የሆነ እውቀት አይደለም የሚያውቀው፤ ከመታወቅ የሚያልፈውን ራሱን እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ ከመንፈሱ ጋር ስንጠጋጋ የሆነ መገለጥ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ይገለጥልናል፡፡ ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር መነካካት ይሆንልናል፡፡ የበራልን እውቀት አይደለም፤ የእውቀት ምንጭ ነው፡፡ የሆነ ጥበብ ገብቶን አይደለም፤ ራሱ ጥበብ ውስጥ ገብተን ነው፡፡ "እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን" (መዝ 118:27) በያንዳንዱ ማይክሮ ሰከንድ የመንፈስ ቅዱስ አብሮነት (Presence) ያስፈልገናል፡፡ በእያንዳንዱ ውሳኔያችን የመንፈስ ቅዱስ ምክር (Counseling) ያስፈልገናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የማያስፈልገን ጊዜ የለም፡፡ ለብቻችን ከሆንን የምናበላሸው ይበዛል፡፡ ከእርሱ እንክብካቤ ውጭ ያለ ሕይወት በምሬት እና በጉስቁልና የተሞላ ነው፡፡ ሰው እንኳን ያለ መንፈስ ቅዱስ ያለ ልብስ ራቁቱን ያስፍራል፤ ያሳፍራል፡፡ "በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።" (ዘካርያስ 4:6) ሐዋርያት ከኢየሱስ እንኳን ተምረው ያለ መንፈስ ቅዱስ አልተሠማሩም፤ እስኪ ወርድ መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ (ሐዋ. 1፥8) ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 በፊት እና በኃላ ያላቸውን የሕይወት ልዩነት ስናይ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አስፈላጊነት ይገባናል፡፡ በገረድ ፊት <አላውቀውም> ብሎ ያፈረበት ጴጥሮስ (ማቴ. 26፥74) በሺዎች ፊት በስልጣን ቃል ደፍሮ የመመስከሩ ምስጢር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ (ሐዋ. 2፥1)። የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ያለ መንፈስ ቅዱስ አይታሰብም፡፡ ስለዚህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሥራ፤ ሙሽራዋ (ቤተ ክርስቲያን) ያለ መንፈሱ ምንም ልትሠራ አትችልም፡፡ " ና " ያሉት ሙሽራ ኢየሱስ እስኪመጣ እየሠራት ይሠራባታል፡፡ (ራእይ 22፥17)፡፡
Show all...
ወንጌል ምንድ ነው? በአንድ በኩል ሲታይ፣ ጠቅላላው መፅሐፍ ቅዱስ ወንጌል ነው፡፡ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ስንዳስስ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆን የእግዚአብሔርን ድንቅ መልዕክት እናነባለን፡፡ ሙሉ መፅሐፍ ቅዱስን ያነበቡ አያሌ ሰዎች ግን ስለ ወንጌል ያላቸው መረዳት ከወንጌሉ ፍጹም የተለየ ነው ወይም ደግሞ የተምታታ ነው፤ አንዳንዴም ያፈጠጠ ስህተት ሆኖ ይገኛል፡፡ አንዳንዶች ወንጌልን ከእግዚብሔር የተቸረ የገንዘብ ብልፅግና አድርገው ይሰብካሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በክርስቶስ ስም እንከን-አልባ የፖለቲካ ዓለም የሚፈጠርበት ምትሐት አድርገውም ያቀርቡታል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ወንጌል ክርስቶስን መከተል፣ መንግስቱን መውረስ እንዲሁም ቅድስናን መከታተል እንደሆነ አፅንዎት ይሰጣሉ፡፡ በእርግጥ ከነዚህ ጭብጦች መሐል አንዳንዶቹ፣ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ አላቸው፡፡ አንዳቸውም ግን የወንጌልን መሠረታዊ ጭብጥ አይገልፁም፡፡ እንደ እድል ሆኖ የወንጌልን ምንነት በግልፅ የሚነግሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ስላሉን እነሱን መመልከት ከብዥታ የጠራ መረዳት እንዲኖረን ይረዳና፡፡ ለምሳሌ ያህል ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “ከሁሉ በላይ [ፊተኛ] የሆነው” መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልዕክት ምን እንደሆነ እንደሚከተለው ያብራራልናል፤ “አሁንም፣ ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ እወዳለሁ፤ የሰበኩላችሁ ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትጸናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው፡፡ እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሐፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሐፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤” ፩ቆሮ ፲፭፥፩–፬ (ዐ.መ.ት) ጳውሎስ ለቆሮንቶስ አማኞች የወንጌሉን መልዕክት እና ከእነርሱ ጋር ያለውን መስተጋብራዊ ፋይዳ ያስታውሳቸዋል፡፡ ይህ ወንጌል የተቀበሉት ነው፤ የቆሙበት ነው፤ የሚድኑበት ነው፡፡ የቆሮንቶስ ሰዎች፣ ጳውሎስ የነገራቸውን ይሄን ወንጌል አጽንተው ሲይዙ፣ ይሄ ሁሉ ቅዱስና ድንቅ በረከት በሕይወታቸው ሁሉ ፈሰሰ፡፡ በርግጥ የቆሮንቶስ ሰዎች ለእንዲህ ያለው በረከት የተገቡ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ወንጌል ላልተገባቸው በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የተሰበከልን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፡፡ እንደ ወንጌል ሊቆጠሩ የሚችሉ አያሌ ድንቅ ነገሮች አሉ፤ አንዳቸውንም ግን ጳውሎስ “ከሁሉ የበላይ” ወይም ፊተኛ መልዕክት ናቸው ብሎ አልወሰዳቸውም፡፡. እንግዲህ ታዲያ ወንጌል ምንድ ነው? ካልን፣ በመጀመሪያ ደረጃ ወንጌል ከእግዚአብሔር የሆነ ``ክርስቶስ ለኀጢአታችን ሞተ`` የሚል የምስራች ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አዳምን በፍጥረት ላይ እንዲገዛ፣ ኀጢአት አልባና ንፁሁ አድርጎ እንደፈጠረው ይነግረናል (ዘፍ ፫)፡፡ አዳም ግን ከእግዚኣብሔር ተለየ፡፡ እኛንም ከራሱ ጋር ወደ ኩነኔ፣ ወደ ጥፋት እና ወደ ዘላለማዊ ክስረት አግተልትሎ ወሰደን(ዘፍ ፭)፡፡ እግዚአብሐር ግን በድንቅ ፍቅሩ ለእኛ ለኣመጸኞች ልንኖረው የተሳነን ፍፁም የጽድቅ ሕይወት የኖረውን፣ መሞት የማንፈልገውን የውርደት ሞት የሞተልንን ኋለኛውን አዳም፣ የተሻለውን አዳም ላከልን፡፡ “ክርስቶስ ለኀጢአተኞች ሞተ`` እኛ በእግዚብሐር ፊት ለሠራነው ወንጀል እርሱ በመስቀል ተቀጣ፡፡ “ኢየሱስ በእኛ ምትክ ሞተ፡፡ በህዝቡ ሐጥያት ምክንያት የተነሳውን የእግዚአብሔር ቁጣ በራሱ ላይ አኖረ፡፡” አንድም ዕዳ ሳያስቀር ሁሉንም ከፈለ፡፡ እርሱ እራሱ በመስቀል ላይ “ተፈፀመ” አለ፡፡ (ዮሐ፲፱፥፴) እኛም ለዘላለም “ለታረደው በግ ክብር ይገባል”(ራዕ ፭፥፲፪) እንላለን፡፡ ሲቀጥል ወንጌል የኢየሱስ ሞትና ስቃይ፣ ፍጽም እውነተኛ፣ ስቃዩም ከስቃዮች ሁሉ የከፋ የነበረ መሆኑን አጽንዖት እየሰጠ፣ “ተቀበረ” ይለናል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ በማቴ ፳፯፥፷፮ “እነርሱም ሄደው መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት።” ይለናል፡፡ ጠላቶቹ ከገደሉት በኋላ ሁሉም ሰው የሞቱ ወሬ እርግጥ እንደሆነ እንዲቀበሉ ሊያደርጉ ጥረዋል፡፡ የጌታችን ሞት፣ ሞት ብቻ አልነበረም፣ ውርደትም የታከለበት ሞት ነበር፤ “ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥” (ኢሳ ፶፫፥፱) በድንቅ ፍቅሩ ኢየሱስ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጠረ፡፡ ኀጢአታችንን እና መከራችንን አንድም ሳይስቀር ተካፈለ፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ወንጌል ``በሦስተኛ ቀን ከሙታን ተነሳ`` የሚል ነው፡፡ ከዓመታት በፊት ኤስ. ልዊስ ጆንሰን ይህን ሐሳብ እንዲህ ባለ መልኩ ሲገልፀው ሰምቻለው፣ “ትንሣኤው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ‘ተፈጸመ’ ላለው፣ የእግዚአብሔር ‘አሜንታ’ ነው፡፡” ኢየሱስ “እኛን ጻዲቅ አድርጎለ ማቅረብ ከሞት ተነሣ!” (ሮሜ ፬፥፳፭) በመስቀል ላይ የሠራው ሥራ ከኀጢአት አንጽቶናል፤ እውነት ነው፡፡ ይበልጥ ደግሞ፣ “በትንሣኤው በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ተግልጧል፡፡” ሮሜ ፩፥፬ ይኸውም ዘላለም የሚገዛው ድል አድርጊው መሢህአችን ነው፡፡ ከሙታን የተነሣው ክርስቶስ ብቻ ነው፣ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።” (ራዕ ፩፥፲፯–፲፰) ያለው፣ ማለትም የሚችለው፡፡ ሕያው ጌታችን፣ ሞትን ድል ነሥቶ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከእርሱም ጋር ለዘላለም በደስታ የሚኖርበትን ዐዲስ ሰማይ እና ዐዲስ ምድር እያዘጋጀ አለ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ለእኛ ለኀጢአተኞች የተበረከተልን የእግዚአብሔር የጸጋ ወንጌል፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ቢባል፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ ሥራዎች የበለጠ እናውቃለን እንጂ፣ ከዚህ ወንጌል ሌላ የሚጨመር ወንጌል መጽሐፍ ቅዱሳችን የለውም፡፡ እንግዲያውስ የተሰበከልንን ቃል አፅንተን እንያዝ፡፡ ይህንን ወንጌል ከሆነ ያመነው፣ ለከንቱነት አላመንም፡፡ መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
. ያለኝ ይበቃኛል 💐Betelhem Tezera መልካም ቀን!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ወደ #ኢየሱስ ካልመጣህ #ትክክል አትሆንም፤ ተሳስተህ እንደነበረም አትረዳም!! ❝አሮጌ የወይን ጠጅ ሲጠጣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤ አሮጌው #ይጣፍጣል ይላልና።❞ —ሉቃስ 5: 37-39። አሮጌ የሚጠጣ አዲሱን አይፈልግም፤ አሮጌው ይጣፍጠዋል። አዲሱን እስካልቀመስነው የተሻለ መሆኑ አይገባንም። አዲሱን መጠጣት ስንጀምር አሮጌው መናኛ (የማይጠቅም) ፤ አዲሱ ደግሞ ከሁሉ የተሻለ መሆኑ ይገባናል። ኢየሱስ በቃናው ሠርግ ውኃን ወደ ወይን ጠጅ ባይቀይር ኖሮ ደጋሾቹ የጠመቁት ወይን መናኛ መሆኑ አይታወቅም ነበር። (ዮሐ. 2፥1-11)። ይህ ታሪክ ኢየሱስ ከሁሉ የተሻለ እንደሆነ ይጠቁማል። አብ የጠመቀው ወይን የተሻለ ይጣፍጣል። ነገር ግን ሰው ወደ ኢየሱስ እስካልመጣ ይህን አያስተውለውም። ወደ ኢየሱስ ካልመጣህ ትክክል አትሆንም፤ ተሳስተህ እንደነበረም አትረዳም!! ሰው ወደ ኢየሱስ ካልመጣ ትክክል አይሆንም፤ መሳሳቱን አያምንም!! የነበርንበት አስተሳሰብ፣ ሃይማኖት እና በብልሃት የተፈጠረ እውቀት ልክ እንዳልነበረ የገባን መንፈሱ ወደ እውነት ማለትም ወደ ኢየሱስ ከመራን በኋላ ነው። ሰው ወደ ኢየሱስ እስካልወጣ ጨለማ ነው(ኤፌ. 2፥8)፤ በጨለማም ነው። ይህም የሚገባን ወደ እግዚአብሔር ብርሃን ከመጣን ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ወደ እርሱ የመጡ ብርሃን ናቸው፤ በብርሃን ናቸው፤ እኛም ነን፥ ሃሌ ሉያ!! በእርሱ ብርሃን እንመላለስ። አዲሱን ወይን ኢየሱስን አብ እንደጋበዛቸው ስንናገር ብዙ ሰዎች ይቃወማሉ፤ "ያለንበት ተስማምቶናል" ይላሉ፤ አሮጌውን ይዘዉ ይከራከሩለታል። እባክህ አዲሱን ቅመሰዉ፦ አዲሱ ለመንፈስህ፣ ለነፍስህ እና ለሥጋህ የተጠመቀ ምርጥ ወይን ነው፤ ሰው ያዘጋጀው አይደለም፤ አብ ከዘላለም ያዘጋጀው ነው፤ በየቀኑም ትኩስ ነው፤ አያረጅም፤ ያረጁትን ያድሳል እንጂ። ኢየሱስ የጥንት ነው፤ ደግሞ አዲስ ነው!! የሰዎችን ጥንት ተተህ ወደ እግዚአብሔር ጥንት ስትመጣ አዲስ ፍጥረት ትሆናለህ!! ወደ ኢየሱስ #አሁን እንኳን ብትመጣ አልዘገየህም!! እግዚአብሔር የሚያነሣሣውን ለውጥ እውን ማድረግ ዋጋ ያስከፍላል። "እኛ ደግሞ ካለንበት ምቾት እና የተደላደለ ሁኔታ ስለሚያወጣን ብዙ ጊዜ ለውጥን እንቃወማለን፡፡ በተፈጥሮአችን የለመድናቸው አሠራሮች እና ሁኔታዎች እስረኞች ነን፡፡ የለውጥን መንገድ ብንቀበል እንኳን የለመድነውን ምቾት ስለሚነሣን ከዚያ ጋር መጣጣም ያቅተናል፡፡ የግድ ግን ለውጥን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለብን፡፡" "ሃይማኖታዊ መንፈስ (Religious Spirit) እግዚአብሔር በቀደመው ዘመን ያደረገውን አጥብቆ ያምናል፤ አሁን እያደረገ ያለውን ግን ይቃወማል፡፡" አሮጌው ኪዳን አያሳስበን፤ በጊዜው ጥሩ አገልግሎ አልፏል። አሁን ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ አዲስ ኪዳን አድርጓል። ስለዚህ ሊያሳስበን የሚገባው እግዚአብሔር አሁን ዓለምን የሚያስተዳድርበት መርህ ወይም ስፍረ ዘመን ነው። ይህም የጸጋ ዘመን ይባላል። ጸጋ አዲሱ ወይን ጠጅ ነው። ጸጋ ከሁሉ #የሚልቅ፥ #ሁሉን ቀላል ያደረገ፥ #ለሁሉም የሆነ፥ #አሁን የሚሠራ የእግዚአብሔር የማዳን መንገድ ነው። ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የሠራውን #ያለ ክፍያ በመስጠት ሰዎችን ከድካማችን አሳርፎናል። በእርግጥ አሮጌውን ወይን ጠጅ (ሕግን) የለመደ ሰው በድንገት ተነሥቶ አዲሱን ወይን ጠጅ አይፈልግም፡፡ ምክንያቱም የልማዳችን እና "ገባን ያልነው ነገር" እስረኞች ስለሆንን ነው። የኛን ልማድ ጥለን እግዚአብሔር እንድንለምድ ለፈለገው ነገር እንገኝ። ለውጥን በደስታ መቀበል አለብን። በተሟላው የክርስቶስ የሕይወት ልቀን መራመድ አለብን። የራሳችንን አሰራር እና ስሌት የሙጥኝ ብሎ ከመያዝ የእግዚአብሔር ጸጋ ያትርፈን። እስኪ የሚሞግቱንን እውነቶች ጨክነን እንማር፥ መንፈስ ቅዱስ የሚያሸክመንን ለመሸከም እንዘጋጅ!! መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
የኔ ኢየሱስ ለኔ ልዩ ነው፤ ፍቅሩም እንደማለዳ ጠል ነው፤ ስጋና ደምን ዘልቆ ጅማትን፤ ዘልቆ ይገባል ያረካል ውስጥን፤ የማያቋርጥ ደስታን የሚሰጥ፤ መራራን ኑሮ የሚያጣፍጥ፤ ከኢየሱስ ልብ የሚመነጨው፤ የፍቅሩ ዘይት ልቤን አራሰው። መልካም ቀን ♥️ https://t.me/tetelestaye
Show all...
የኢየሱስ ስም ከመቼውም ጊዜና ከማንም የሚበልጥ ስም እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። ለዘመናት በዓለም ዙሪያ ላሉ በቢሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተስፋ እና መነሳሻ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። እና ዛሬ በዓለም ላይ ለበጎ ነገር ኃይለኛ ኃይል ሆኖ ቀጥሏል። መልካም ቀን!!! ሬቨ ተዘራ ያሬድ https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር ለነገረን ነገር ሰዎች #ማረጋገጫ መስጠት አይችሉም!! ❝ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥❞ —ገላትያ 1፥15-16 እስካሁን የራሳችንን መንገድ መጥተናል፤ እስኪ ቆም ብለን ለምን እንደ ፈለገን እናስብ!! እስከ ዛሬ ለራሳችን ኖረናል፤ አሁን የምንኖለትን አላማ ስለማሟላት እንኑር!!እኛን ከማህፀን ለለየበት #አላማ (Purpose) መገኘት ይሁንልን!! ኑሮ ያለውን ኑሮ ለማየት ዓይናችን ይብራ!! ሳንከፍል የተጠራንበት ሕይወት አለ!! እግዚአብሔር እኛን ላየበት ሕይወት ለመገኘት ከሥጋና ደም ጋር መመካከር አያስፈልግም!! ሥጋ የመንፈስ ነገር አይገባውም!! እግዚአብሔር ለነገረን ነገር ሰዎች ማረጋገጫ መስጠት አይችሉም!! ሰው ለእግዚአብሔር አሳብ ማስተካከያ ወይም ማሟያ መስጠት አይችልም!! የልጁ ሕይወት በእኛ ሁኔታ እንዲተረክ የአብ ፈቃዱ ነው!! #ልጁ #በልጆቹ ይነገራል!! ይተረካል!! ይገለጣል!! ይወራል!! ኢየሱስ ከበራልህ ባበራልህ ብርሃን መጠን መስክረው፤ አትቆጥበው!! ጳውሎስ "ልጁን #በእኔ ሁኔታ #ሊገልጥ በወደደ ጊዜ" ማለቱን ልብ እንበል፤ ጳውሎስ በጴጥሮስ ሁኔታ አልሰበከም። ጴጥሮስ በዮሐንስ ሁኔታ አልሰበከም። በእኛም ልጁ ሲገለጥ በእኛ ሁኔታ ነው የሚገለጠው፤ በሌሎች ሁኔታ ማገልገል ወይም ሌሎችን ለመምሰል መታገል የለብንም!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ስለ ምህረትህ ስለ ጥበቃህ ስለ ውለታህ ጌታ ሆይ ምንስ ልክፈልህ አንተን ካገኘው ጀምሮ ህይወቴ ባንተ አምሮ የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት የምህረትህን በብዛት አልችልም ልገልጻት የፈሰሰው ሰማያዊ ጸጋ አኑሮኛል ከአንተጋር የመረጥከኝ ተበረክልኝ በመስቀል ላይ ስለ እኔ ሞተሃል አበሳዬን ወስደሃል ምን ልክፈልህ እንዲያው ልገዛልህ (፪x) ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው ታሪኬን ለውጦ ከሞት አስመልጦ ጌታ ሆይ ተመስገን (፪x) የምህረትህ የፍቅርህ ብዛቱ አልበረደም ግለቱ ያዘምረኛል ተድላዬ ሆኖኛል ያዘምረኛል ሞገሴ ሆኖኛል ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው ታሪኬን ለውጦ ከሞት አስመልጦ ጌታ ሆይ ተመስገን (፪x) በመረቅህልኝ አዲስ ህያው መንገድ ደስ እያለኝ ልራመድ መጨረሻዬ ኢየሱስ ጌታዬ መጨረሻዬ አንተ ነህ ጌታዬ የሩቅ አገር የፅዮን ተጓዥ ነን በሠማይ አገር ያለኝ ታድያለሁ አገሬ ገባለሁ ታድያለሁ ዘለዓለም አርፋለሁ ዘማሪት ራሄል ሰናይ ምሽት ♥️
Show all...
ዘማሪ:- እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ የማታረጀው ፡ ማትቀደደው ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት:ግርማ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ         ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ አንተን ፡ ለብሶ ፡ ተጐናፅፎ እራቁቱን ፡ ማንስ ፡ ቀርቶ የለበሰህ ፡ ከበረ ፡ እንጂ መቼ ፡ ቆመ ፡ ውርደት ፡ ደጅ       አንተን ፡ ያለ ፡ የታደለ ፡ እራቆቱ ፡ ተሸፈነ ___ ዘላለማዊ RUHAMA ALEMAYEHU
Show all...