cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Show more
Advertising posts
429
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ለሰው ልናሳየው የማንፈልገውን የሕይወታችንን ክፍል ለመንፈስ ቅዱስ መግለጥ እንችላለን!! ከሰው ጋር ልናወራው የሚከብደንን ነገር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ማውራት እንችላለን!! መንፈስ ቅዱስ ጨርሶ ቢያውቀንም ገልጸን እንድናሳየው ይፈልጋል!! እርሱ የልብ ወዳጅ ነው!! መፍትሔ የላቸውም ብለን ለምናስባቸው ነገሮች እርሱ መንገድ አለው፤ ሁሉን ሊያስተካክል ይችላል!! መንፈስ ቅዱስ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ስም አይተረጎምም፥ #የኢየሱስ ስም ብቻ በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሞአል። የሚደንቀው ተተርጉሞም #ኃይሉ አልቀነሰም። እኛ እንኳን ስሙን የምንጠቀመው ተተርጉሞ ነው። ኢየሱስ በመጀመሪያ በHebrew ቋንቋ #Yehoshua ተብሎ እየተጠራ ነው ያደገው። ከትንሣኤው በኋላ ስሙ ስለከበረ በሰዎች ቋንቋ ሁሉ ተተረጎመ፤ ስለተተረጎመ የስሙ ስልጣን አልቀነሰም፤ ለሁሉም በሁሉም ይሠራል!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
. ላንተ መኖር ዮሐንስ ግርማ
Show all...
. ነፍሴ በአንተ ላይ ይስሃቅ ሰዲቅ
Show all...
"#አንተን_ባየ_ዓይኔ" ዘማሪ በረከት ለማ(orginal song ) ሰናይ ምሽት❤️
Show all...
"ኢየሱስ ይማልድልኛል" ብትል ይማልድልሃል። "አይማልድልኝም" ካልክም ትክክል ነህ። ምክንያቱም በእርሱ የሚያምኑት ብቻ የምልጃው ተጠቃሚ ይሆናሉና! (ዕብ 7 ) ------------ 24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
ከዝና በፊት ትህትና፤ ከውድቀት በፊት ትዕቢት መጽሐፍ ቅዱሳችን ከሚያስተምረን የስነምግባር መርሆች ውስጥ አንዱ ትህትና ነው። ትህትና የትዕቢት ተቃራን ነው። ሰዎች ባላቸው ነገር በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ይታበያሉ፤ የትዕቢትንም ቃል ይናገራሉ። ለምሳሌ፤ የካህኑ ሳሙኤል እናት የነበረችው ሐና መካን በነበረች ጊዜ ጣውንቷ ጠዋትና ማታ በትዕብት አስተያየቷና እንደ ጦር በሚወጉ የትዕቢት ቃላቶቿ አማካኝነት ስታስጨንቃት እንደነበር እናስታውሳለን። ሐና ግን በአንጻሩ ለጣውንቷ መልስ ከመስጠት ወይም ከመሳደብ ይልቅ በፍጹም ትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ መንፈስ በእግዚአብሔር ፊት ታለቅስ እና ራሷን ታዋርድ ነበር። የተዋረዱትን የሚያከብር አምላክ ግን ስሙ እስከዛሬ ድረስ የሚዘከር ድንቅ ወንድ ልጅ በመስጠት ቀንዷን በጠላቶቿ ፊት ከፍ ከፍ አደረገላት። በዚህ ጊዜ ነው ታዲያ ሐና ስትዘምር “አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ እግዚአብሔር አዋቂ ነው” ብላ የዘመረችው። ወንድማችን ጴጥሮስም በመልዕክቱ የመከረን ይህ ነው፦ “ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ” (1ጴጥ. 5፡5_6) ትህትና የሚመነጨው እግዚአብሔርን ከመፍራት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የሆነለት ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደሆነ በብርቱ ስለሚያምን ለራሱ ክብርና እውቅና አይሰጥም። እግዚአብሔር አዋቂ ነው ሲባል እርሱ ትዕቢተኞችን እንዴት እንደሚያዋርድ ትሁታንን ደግሞ በጊዜው ከፍ ማድረግ የሚያውቅ ጻድቅ ፈራጅ እንደሆነ የሚያስረዳ ነው። ዛሬ የተዋረደው ነገር ይከብራል፤ ዛሬ ያጣው ነገ ያገኛል፤ ዛሬ የሚያለቅስ ነገ ይስቃል፤ ይህ ሁሉ ኩነት ያለው ግን በእግዚአብሔር እጅ ነው። ለዚህ ነው ንጉስ ሰለሞን “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፤ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች (The fear of the Lord is the instruction of wisdom; and before honour is humility)" ብሎ የተናገረው (ምሳ. 15፡33)። ጌታችን ኢየሱስም ሐዋሪያቱን ሲመክራቸው “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን” ነበር ያላቸው (ማር. 9፡35)። ምስጢሩ ይህ ነው፤ እኛ ባለን ነገር የምንታበይ ከሆነና ሀብታችንን፣ እውቀታችንን፣ የጸጋ ስጦታዎቻችንን ሌሎችን ለመጉዳት ወይም ለማሸማቀቅ የምንጠቀምበት ከሆነ ያ ያለን ነገር በማናውቀው ጊዜና ሁኔታ ከእጃችን ጠፍቶ እናጣዋለን። ነገር ግን፤ አሁን ስላለን ነገር እግዚአብሔርን ብናመሰግንና ያለን ነገር ለእርሱ ክብር ለሰዎችም በረከት በሚሆን ሁኔታ ብንጠቀምበት እግዚአብሔር ከዚህ የበለጠ ነገር ያደርግልናል፤ “በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል” ነውና መርሁ። ትህትና ዝናን/ክብረትን እንደሚቀድም ሁሉ ትዕቢትም ውድቀትን/ውርደትን የሚቀድም እንደሆነ ቃሉ ተናግሮናል። በአንድ ወቅት በትዕቢት ተነፍተው አገር ምድሩን አንቀጥቅጠው የነበሩ ሰዎች ተዋርደው የቀሩትም ይህን መርህ ባለመከተል ነው። ራስን ዝቅ ማድረግ ግን በጌታ ዘንድ ሽልማት አለው። በኢየሱስ ስም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በጌታ ፊት ራሳችንን ዝቅ ማድረግ ይሁንልን! ቅድሚያ ለወገኖቻችን መስጠት፤ ካለን ነገር ይልቅ በሚያኖረን እግዚአብሔር ላይ ልባችን መጣል ይሁንልን! በእርሱ ብቻ መመካት የሚያስችል የሚረዳ ጸጋ ይጨመርልን! አሜን! መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
አነጋገርህ ያስታውቃልና አንተም ከእርሱ ጋር ነበርክ የኢየሱስ ወደ ጎልጎታ ጉዞ ካስተማረን ጠቃሚ ነገሮች አንዱ የጴጥሮስ ክህደት ነው። በመጀመሪያ ጌታችን ገዳዮቹ ገመድና በትር ይዘው ሊይዙት በመጡ ጊዜ “የምትፈልጉት የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን ይሂዱ ተውአቸው” (ዮሐ. 18፡8) ብሎ ከተናገረ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ትተውት ሸሹ። አንዳንዶች ግን በርቀት እየተከተሉ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ ነበር። ከእነዚህ መካከል ሐዋሪያው ጴጥሮስ ይገኝበታል (ማቴ. 26፡70_77)። በዚህ ጊዜ ነበር እንግዲህ፤ በአንዱ ባለሥልጣን ቅጥር ግቢ ውስጥ እያሉ የነበረውን ከባድ ብርድ ለመቋቋም ሲሉ እሳት የሚሞቁ ሰዎች አይቶ ጴጥሮስም አብሯቸው እሳቱን ለመሞቅ ፈልጎ ተቀላቀላቸው። ነገር ግን፤ የኢየሱስ ተከታይ እንደሆነ እንድነቃበት አይፈልግም ነበር። የኢየሱስ ግብረ አበር ተብሎ እንዳይፈረድበት ፈርቶ ነበረና። እናም በተቻለው አቅም ሰዎቹን መስሎ ለመቆየት ጥረት እያደረገ በወሬያቸው እየተሳተፈ፤ የሚናገሩት ነገር ባያስቀውም እንኳን የውሸት እየሳቀ፤ ባልገባው ነገር አንገቱን እየነቀነቀ ስምምነቱ እየገለጸ ያሳልፍ እንደነበር በዝርዝር ባይጻፍልንም እንኳን ከነበረው ከባቢያዊ ሁኔታ መገመት እንችላለን። ይሁን እንጂ፤ ከአፉ እያመለጡ የሚወጡ ቃላቶችና የአነጋገር ዘይቤዎቹን ተቆጣጥሮ እስከመጨረሻው ማቆየት የቻለ አይመልስም። በነገሮች ላይ ያለው እይታ የቡድኑ አባላት ካላቸው እይታ ፍጹም የተለየ ነው፤ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ እርሱ የሚሰጣቸውና ሌሎቹ የሚሰጡት አስተያየት ፍጹም አይገናኝም። ሦስት አመት ሙሉ በጌታው እግር ስር ሲሰለጥን የከረመ እንደመሆኑ መጠን አንዳንድ የአነጋገር “ስታይሎችንም” ከመምህሩ ሳይኮርጅ የቀረም አይመስልም (ወይም ለምዶታል)። በዚያው ላይ የወቅቱ አንገብጋቢ አጀንዳ የኢየሱስ ክርስቶስ አጠቃላይ እንቅስቃሴና የመታሰሩ ጉዳይ በመሆኑ፤ እነዚህ ሰዎችም የወሬ አጀንዳቸው ይሄው ጉዳይ እንደሚሆን መገመት አይከብድም። ጥቂቶች የአድናቆት፤ ሌሎችም የንቀት፤ አንዳንዶች የእውነት፤ ሌሎች ደግሞ በሀሰት መረጃ ላይ የተመሰረተ አስተያየት በኢየሱስ ሕይወትና ማንነት ላይ እየሰነዘሩ ሊሆን ይችላል። ታድያ፤ ጴጥሮስ እንዴት ያስችለው? ዘው ብሎ ገብቶ ሳይታወቀው ነገሮችን ማብራራት ይያያዛል። “ይሄ መሰሪ እኮ ቤተ መቅደስን አፍርሼ በሶስተኛው ቀን እሰራለሁ ብሎ የተናገረ ሰው ነው፤ ደፋር!” ብሎ አንዱ ከተናገረ ጴጥሮስ ቀበል አድርጎ “አይ ያ ንግግሩ እንኳን ስለምድራዊ ቤተ መቅደስ አይመስለኝም፤ ድብቅ መንፈሳዊ ትርጉም ይኖረዋል” ብሎ ሊመልስ ይሞክራል። ሌላው ተነስቶ “ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል ሁሉ ያደርጋል አሉ” ብሎ ካለ ጴጥሮስ በውስጡ ይናደድና በድንገት “በፍጹም በፍጹም፤ አንድም ቀን እንዲህ ብሎ አያውቅም። እንደውም አንድ ቀን….” ብሎ ያኔ ግብር የሚሰበስቡ ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው ግብር ሲጠይቁት ሮጥ ብሎ ወደ ኢየሱስ መጥቶ “ግብር እየጠየቁን ነው፤ ምን ላድርግ” ባለ ጊዜ ጌታ ኢየሱስም “ባህር ውስጥ ካለው አሣ አፍ ውስጥ ያለውን ሁለት ብር ወስደህ ክፈል” በማለት ያደረገውን ተዓምር ሊተርክላቸው ጀምሮ ደንግጦ ይተዋል። እንዲህ እየተጨናነቀ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ አንዷ ገረድ ቀረብ ብላ “አንተ ከኢየሱስ ደቀመዛሙርት አንዱ ነበርክ መሰለኝ” ስትለው ጴጥሮስ ክው ያለው። አይደለሁም ብሎ ሲከራከር ከቅድሙ ጀምረው አብረውት ሲጫወቱ የነበሩ ሰዎች አስረግጠው “እንደውም አነጋገርህ ያስታውቃልና ከእርሱ ጋር ነበርክ” ሲሉት ጴጥሮስ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋበት። እኔ የምትሉትን ሰውዬ (ጌታ ኢየሱስ መሆኑ ነው) አላውቀውም፤ እናቴ ትሙት! (ብሎ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ “ጴጥሮስም ይምልና ይገዘት ጀመር” ስለሚል)። ማንም ሊያምነው ግን አልቻለም ነበር። ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? አንዳንድ ጊዜ የዓለም ሰዎች የኑሮ ሁኔታ ጋር ተመሳስሎ ለመኖር ጥረት እናደርጋለን። የክርስቶስ ተከታዮች፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንደሆንን ሰዎች እንዲያውቁብን የማንፈልግባቸው ወቅቶች ይኖራሉ። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። በትውልድ መንደራቸው የኳየር፤ ወይም የጸሎት ቡድን አባላትና መሪዎች የነበሩ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ “ላይፍ ለመቅጨት” ሲሉ (ለመቅጨት ወይስ ለመቀጨት? አላውቅም) መልካቸውን ለውጠው ንግግራቸውን በግቢው ሁኔታ አስተካክለው፤ አለባበሳቸውን ቀይረው ለመደበቅ ጥረት ያደርጋሉ። ነገር ግን፤ ያስታወቅባቸዋል፤ መደበቅም አይችሉም። የሰቀቀን ውሎ ነው የሚውሉት። ከክርስቶስ ጋር የዋለ ሰው ሌላ ውሎ አይመቸውም። የእርሱ ጠረን የለመደ ሰው ሌላው ጥሩ ጥሩ አይሸተውም። የጽሑፉ መልዕክት፡ በይፋ የክርስቶስ ተከታዮች መሆናችንን ዓለም አውቆ ይኑር። አንደበቅ፤ ከኢየሱስ ጋር የነበርን መሆናችንን ንግግራችን ብሎም ሌላው ሁኔታችን መግለጡ ላይቀር ጊዜ መግዛት አይጠቅመንም። በክፉዎች ወንበር ተቀምጦ እሳት መሞቅ ይቅርብን፤ ከሙቀቱ ጉዳቱ ይበልጣልና። “እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2ቆሮ. 3፡18) መልካም ቀን ጸጋው ከሁላችን ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
አዲስ ኪዳን የመጽሐፍ ስም አይደለም ብዙዎቻችን “አዲስ ኪዳን” ሲባል ቶሎ ወደ አዕምሮአችን የሚመጣው ከማቴዎስ ወንጌል ጀምሮ በየዮሐንስ ራዕይ የሚያበቃ የ27 መጽሐፍቶች ስብስብ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ታዋቂው የመረጃ ቋት የሆነው ዊክፕዲያም አዲስ ኪዳንን “The new testament is the second division of the Christian bilblical canon, the first being the old testament which is based primarily upon the Hebrew Bible” ይህም በአማርኛ “አዲስ ኪዳን ሁለተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። የመጀመሪያው በዋናነት በዕብራውያን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ብሉይ ኪዳን ነው” ይላል። እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ከአንዱ ጀ. ፕርስቶን የተባለ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚ ከጻፈው ማብራሪያ በስተቀር እውነተኛውን የአዲስ ኪዳን ትርጉም የሚገልጹ ምንጮችን ማግኘት አልቻልኩም። ሁሉም አዲስ ኪዳንን የመጽሐፉ ስም እንደሆነ ብቻ ያብራራሉ። ይሁን እንጂ፤ አዲስ ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱስ ስም አይደለም። እነዚያ አራቱን ወንጌላት፤ ሀያ አንድ የተለያዩ ደብዳቤዎች፤ አንድ የታሪክ መጽሐፍ እና አንድ የትንቢት መጽሐፍ ስብስብ ወደ አዲስ ኪዳን እንዲመሩን በአዲስ ኪዳን ዘመን የተጻፉልን እንጂ በራሳቸው አዲስ ኪዳን አይደሉም። ኢየሱስ አዲስ ኪዳንን ሲመሰርት የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት አልነበሩም። የአዲስ ኪዳን መመስረቻ መርሃ ግብር ላይም ኢየሱስ መጽሐፍ ሳይሆን የደሙ ምሳሌ የሆነውን ጽዋ አንስቶ “እንኩ ጠጡ፤ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው (This cup is the new testament in my blood, which is shed for you)” ነበር ያለው (ሉቃ. 22፡20)። እዚህ ላይ ኢየሱስ “አዲስ ኪዳን በመጽሐፍ ውስጥ ነው”ም አላለም፤ ይልቅ “በደሜ ውስጥ የሚገኝ አዲስ ኪዳን (the new testament in my blood” በማለት ገልጿል (በነገራችን ላይ፤ አዲስ ኪዳን የተጀመረው ኢየሱስ ሞቶ ከሙታን በተነሳ ጊዜ ነው፤ እንጂ ማቴ. 1፡1 ላይ አይደለም)። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር አዲስ ኪዳን ማለት በእኛ ላይ የፈሰሰ የእግዚአብሔር ልጅ ሕይወት ነው ማለት ነው። የእንግሊዝኛው “testament” የሚል ቃል ከግሪኩ DIATHEKE ከሚለው የተተረጎመ ሲሆን ፍቺውም “a covenant.” ወይም በአማርኛ “ሕጋዊ ስምምነት” የሚል ይሆናል። ይህም እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር የገባውን አዲስ ቃል ኪዳን ወይም ስምምነት የሚያመላክት ነው። እርሱም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን የመስጠት ስምምነት ነው። አዲሱና አሮጌው ኪዳን በብዙ መልኩ የተለያዩ ናቸው። አሮጌው የእግዚአብሔር ኪዳን በእንስሳት ደም አማካኝነት የተፈጸመ ሲሆን አዲሱ ኪዳን ደግሞ በኢየሱስ ክቡር ደም ተመርቆ የተከፈተ ነው። በተጨማሪም፤ የአሮጌው በፊደል ላይ የተመሰረተ ኪዳን በአዲሱ በመንፈስ ላይ በተመሰረተ ኪዳን የተተካበት ነው። እኛም ለዚህ ክቡር የመንፈስ ኪዳን አገልጋዮች ተደርገን የተጠራን ነን። "እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል” (2ቆሮ. 3፡6) ይህን ሀሳብ የማነሳው በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ ክርስቲያኖች የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን በእጃቸው ይዘው የአሮጌው ኪዳን አኗኗር ሲኖሩ ስለማይ ነው። አዲስ ኪዳንን ማንበብና በአዲስ ኪዳን ውስጥ መኖር ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ መሆን ማለት በራሱ በኢየሱስ ውስጥ መኖር ማለት ነው። በሥጋ ጥረት ወደ እግዚአብሔር ፍጽምና ለመድረስ ከመሞከር ይልቅ በመንፈስ ሆነው ጌታ ኢየሱስን ለመዳደሰስ መብቃት ነው አዲስ ኪዳን። አዲስ ኪዳን አብ በረካው በኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ ረክተን የዘላለም ሕይወት አሁን እንዳለንና ጽድቃችን ብለን የምንለውም ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ማመንና መተማመንን ይጠይቃል። መልካም ቀን ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
የያዕቆብ መሰላል ልክ እንደ አሁኑ ዘመናችን ምድር በክፋት ተሞልታ ዘግናኝ ነገሮችን እንጂ መልካም ነገር መስማት ብርቅ በሆነበት ጊዜ ነበር አንድ ናትናኤል የተባለ መልካም ሰው በዛፍ ስር ተቀምጦ የነበረው። ዙሪያው ሁሉ ክፋት ከሆነ ለጻዲቅ ሰው ምቹ ቦታ ከዛፍ ስር ለብቻው ከመቀመጥ ሌላ ምን አማራጭ ይገኛል? በዚህ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አንድ ፊልጶስ የተባለ ወዳጁ እየሮጠ ወደርሱ መጣና “በነብያት የተመሰከረለትን የናዝሬቱን ኢየሱስ ክርስቶስን አግኝተነዋል” ብሎ ‘Surprize’ አደረገው። ይሁን እንጂ፤ ይህን መልካም ዜና አምኖ መቀበል ለናትናኤል ቀላል አልነበረም። ምክንያቱም ከናዝሬት መልካም ነገር መውጣት ካቆመ ዓመታት ተቆጥረዋልና ማመን አቃተው። “ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?” ብሎ ገና ሳይጠየቅ የተመለሰ የሚመስል ጥያቄ ጠየቀ። ለማመን የሚከብድ ቢሆንም “አዎ ከናዝሬት መልካም ነገር፤ ለዚያውም የያዕቆብ መሰላል ተገኝቷል!” Congratulations! ናትናኤል ኢየሱስን ለመገናኘት በመጣ ጊዜ እንደ ሰው ልማድ “እንተዋወቅ” ብሎ ለመተዋወቅ አስቦ ሳይሆን አልቀረም። ነገር ግን፤ እንዳሰበውም አልሆነም፤ ገና በሩቅ ሳለ ኢየሱስ ወደርሱ እያመለከተ “ተንኮል የሌለበት ሰው መጣ” ብሎ ሲናገር፤ ናትናኤል ክው ብሎ ቀረ። “እንዴት አወቅኸኝ? ማለት እንዴት አወቅኸኝ?” ናትናኤል ደንግጦና ግራ ተጋብቶ ይጠይቃል። ኢየሱስም “ፊልጶስ ሳይገናኝህ በፊት በበለስ ዛፍ ስር እያለህ አይቼሃለሁ”። ናትናኤልም ከዚህ በላይ ተጨማሪ ምልክት አልፈለገም ዘሎ “በቃ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ የእስራኤልም ንጉስ” አለው። ጌታም መለሰለት “ቆይ እንደዚህ የማንከው በበለስ ዛፍ ስር ተቀምጠህ አይቼሃለሁ ስላልኩህ ብቻ ነዋ? ገና ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ፤ ሰማይ ተከፍቶ መልዓክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው (ዮሐ. 1፡46-52)። Wow! እኛም ይህን ቃል ስናነብ ሀሳባችን ወደ አንድ የብሉይ ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሄዱ አይቀርም፡ እንዲህ ወደሚል፦ “ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር” ዘፍ. 28፡10:12። እንግዲህ ይህ መሰላል ነው ሥጋ ለብሶ በአካል ለናትናኤል የተገለጠለት። አዎን ሰማይንና ምድርን ማለትም ሰውን እና እግዚአብሔርን ያገናኘ መሰላል እርሱ ነው። ይህ መሰላልነት የነፍስ ዋጋ የተከፈለበት በመሆኑ፣ ደስ እንዳለህ ለማንም አንስተህ የምትሰጠው ማዕረግ አይደለም፤ አይቻልምም። የትኛውንም ሰብዓዊ ፍጡር ከምትችለው በላይ ልትወደው የክብር ስምም ልትሰጠው ትችላለህ፤ ነገር ግን፤ ይህን የኢየሱስ ቦታ ለሌላ ሰው ወይም መልአክ የሰጠህ ቀን የራስህን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝህን መሰላል በፈቃድህ እንዳቃጠልከው ቁጠረው። ኢየሱስ ወደ አብ የምንወጣበት ብቸኛው መሰላላችን ነው። የበጎች በር ኢየሱስ ብቻ ነው። እርሱም በታማኝ ምስክርነቱ እንዲህ ብሏል “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል (ዮሐ. 10፡9)። በአንድ ወቅት ሰዎች በራሳቸው ጥረት እስከሰማይ ድረስ የመዝለቅ ፍላጎት ስለነበራቸው ለራሳቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ ለመስራት ተነስተው ነበር (ስለ ባቢሎን ግንብ ነው የማወራው)። እናም ጭቃ ሰብስበው፤ በእሳት አቃጥለው በጡብ ሸክላ ግንቡን ለመስራት በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔር ከላይ ወርዶ ቋንቋቸውን በማደባላለቅ ሀሳባቸው እንዲከሽፍ አድርጎአል (ዘፍ. 11)። እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ሰዎች በራሳቸው ጥረት ወደ እርሱ ሊደርሱ ስለማይችሉ ነው። የሚገርመው በዘመናችን እንኳን የራሳቸውን ወደ ሰማይ የሚዘለቅ መሰላል በራሳቸው ለማበጀት (ሕግን ጠብቀው በመልካም ሥራቸው ለመዳን የሚፍጨረጨሩ) ብዙዎች አሉ። ለእኛ ግን እግዚአብሔር ራሱ በዘላለም ሀሳቡ አቅዶ መሰላል አዘጋጀልን። ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ተመርቆ በተከፈተልን በዚህ መሰላል አማካኝነት ወደ አብ መግባት ሆኖልናል (ዕብ. 11፡ 19-20)። ስለተደረገልን ነገር እግዚአብሔርን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። ሰዎች ኢየሱስ አምላክም ሰውም እንደመሆኑ መጠን ሰውን እና አምላክን ማገናኘት የሚችል የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እርሱ ብቻ መሆኑን እንዲያውቁና ክብሩንም ለሌላ ለማንም እንዳይሰጡ ባለመታከት እንለምናለን። አንድ መሰላል፤ አንድ መካከለኛ፦አንድ ጌታ ኢየሱስ! ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ትህትና ትህትና በሌሎች መካከል ራስን ዝቅ አድርጎ ማየት ወይም ስለ ራስ የተጋነነ እይታን አለመያዝ ነው። ትሁት ሁን ማለት የበታችነት ስሜት ይሰማህ ማለት አይደለም። ትህትና “እኔ ትንሽ ነኝ” ብሎ ማሰብ ሳይሆን ራስን ትንሽ አድርጎ መቁጠር ነው። ይህ ማለት፤ ሀብታም ብትሆንም በድሆች መካከል እንደ ደሃ ራስህን ዝቅ ታደርጋለህ፤ እውቀት ቢኖርህም እንኳን ከአንተ የሚያንሱትን ታግሰህ ታዳምጣቸዋለህ፤ የበላይ ባለሥልጣን ብትሆንም እንኳን በበታችህ ያሉትን ሁሉ በትህትና ታናግራቸዋለህ/በየዋህነት ታዝዛቸዋለህ ማለት ነው። ትህትና ይበልጥ የሚገለጸዉ ካንተ የሚያንሱትን ሰዎች በአመለካከትህ ካንተ አስበልጠህ ስትመለከታቸው ነው። ማለትም፤ በአንተ ዘንድ ዝቅ ካለዉ ሰው ፊት ዝቅ ብለህ ስትታይ ትሁት መሆንህን በተግባር ታስመሰክራለህ። በሌላ በኩል ካንተ በሀብት፤ በእውቀት ወይም በሥልጣን በሚበልጥህ ሰው ዘንድ ራስህን ዝቅ ብታደርግ ማድረግ የሚገባህን አደረግህ እንጂ ትሁት አትባልም። ለምሳሌ፤ አንዳንድ ሰዎች አንዱን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በጀርባ ሊጠሉት፤ ሊያሙት ብሎም እየሰደቡት እርስ በርስ ሲነጋገሩ ሳለ ያ በለሥልጣን አጠገባቸው ሲደርስ መንገድ ይለቁለታል፤ ወይም ከእነርሱ አንዱ ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ ቢሮው ሲሄድ የውስጡን ጥላቻ በሆዱ ይዞ በትልቅ አክብሮት እና መልካም ቃላቶች ያናግረዋል። ታዲያ ይህ ትህትና አይደለም። ይልቅ በባለሥልጣኑ ፊት በትዕቢት መናገር የሚያስከፍለውን ዋጋ ተረድቶ ተገቢውን ክብር መስጠቱ ነው እንጂ። ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱ (ተማሪዎቹ) ጌታና አምላክ ሆኖ ሳለ እነርሱን ዝቅ ብሎ ማገልገሉና እግራቸውን ማጠቡ የትህትናን ጥግ ያሳያል። እኛም የእርሱን ፈለግ ተከትለን ራስን ዝቅ ማድረግን ወይም ትህትናን እንድንለማመድ ተጠርተናል። ትሁት መሆን ማለት ሞኝ መሆን ማለት ግን አይደለም። ጌታችን ያስተማረን ትሁት ብቻ እንድንሆን ሳይሆን ብልሆችም እንድንሆን ነው። ሁሉም ነገር ገደብ አለው፤ ወይም ሁሉም ጊዜ አለው። ስለሆነም፣ እርግብ ለመሆን ጊዜ አለው፤ እባብ ለመሆንም ጊዜ አለው። በግ ለመሆን ጊዜ አለው፤ ፊየል ለመሆንም ጊዜ አለው። ትህትና እና ብልህነት እኔ በዚህ ጽሁፌ ሊገልጸው የሚችለው ግልጽ ድንበር የለውም። ድንበሩን ለመለየት መንፈሳችንን እና አዕምሮአችንን መጠቀም መቻል አለብን። መጽሐፍስ እንደ ባለአዕምሮ አስቡ ይል የለ? አዎ! ያለንነው ትህትና በተመናመነበት፣ ትዕብት በወፈረበት ዘመን ውስጥ ነው። ታዲያ በዚህ ጊዜ ትሁት ሆኖ መገኘት የእውነተኛው ክርስቲያናዊነት መገለጫ ነው። የትዕቢት መዲኃኒቱ ትህትና ነው። አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር፤ ማንም ሰው “እኔ ትዕቢተኛ ነኝ” እያለ አይታበይም። ይህም የሚሆነው፤ አንዳንዱ ስለራሱ ስለማያውቅ፤ ሌላው ደግሞ ስለራሱ ህሊናው የሚነግረውን ማመን ስለማይፈልግ ነው። ስለሆነም የእኔ ባህሪይና ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው የሚገለጸው? ትሁት ነኝ ወይስ ትዕቢተኛ? ብሎ ራስን መጠየቅ ያስፈልጋል። ነገር ግን፤ በደፈናዉ እንዲህ ብለን ጠይቀን የምናገኘው መልስ ትክክለኛ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም፤ ሁሉም ሰው ለራሱ ትሁት የሆነ ይመስለዋልና ነው። ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱም አይደል ብሂሉ? ስለሆነም የሚከተሉትን ዝርዝር ጥያቄዎች ጠይቆ ለራስ መልስ መስጠት እውነተኛውን የትህትና ወይም ትዕቢት ባህሪያችንን ይነግረናል ብዬ አስባለሁ። 1. ሁል ጊዜ፣ በሁሉ ቦታና ሁኔታ ከሰዎች የተሻልሁ እንደሆንኩ ይሰማኛል? 2. ሰዎችን እያገላመጥኩ ወይም አጎንብሼ ነው የማየዉ ወይስ በመልካም እይታ ነው የማየዉ? 3. ሁል ጊዜ የእኔ ሀሳብ ብቻ ትክክለኛ ይመስለኛል? ሰዎች ሲናገሩ በአግባቡ አዳምጣለሁ? ወይስ የራሴን አውርቼ ከጨረስሁ ስለ ሌሎች ሀሳብ አይገደኝም? 4. ሰዎች አስተያየት ሲሰጡኝ ስህተቴን ላለማመን አጉል እከራከራለሁ፤ እናደዳለሁን? ወይስ ስህቴቴን አምኜ ይቅርታ እጠይቃለሁ? 5. ሁል ጊዜ ጥቅሜን ለማስከበር ብቻ ነው የምታገለው ወይስ አንዳንዴ ሌሎች እንዲጠቀሙ ጥቅሜ አሳልፌ እሰጣለሁ? 6. ሁል ጊዜ ሰዎች እንዲያከብሩኝ፤ እንዲያመሰኑኝ፤ እንዲያጨበጭቡልኝ ባጠቃላይ የተለየ ቦታ እንዲሰጡኝ እጠብቃለሁ? እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ያለንበትን ቦታ በመለየት፤ ትህትና ካልፈጠረብን ሀሁ ብለን ትህትናን ልንማር፤ አስቀሞ ትህትና ካለን አጠናክረን ለመቀጠል ልንወስን እንችላለን። ትህትና እያወቁ እንደማያውቁ፤ እያላቸው እንደሌላቸው፤ እየበለጡ እንደሚያንሱ መቁጠር ነው። ሌሎችን ቅድሚያ መስጠት ነው። እውነት ለመናገር፤ በሀገራችን ትህትና ተገቢ ቦታ እንዳልተሰጠው ይሰማኛል። አንዳንድ ሰዎች ራስህን ዝቅ ስታደርግ ሲያዩህ በበታችነት ስሜት ውስጥ የምትማቅቅ አድርገው ሊያስቡህ፤ ትሁት ስትሆን ሞኝ እንደሆንክ ልቆጥሩህ ይችላሉ። መምህር ሆነህ ተማሪዎችህን በትህትና የምታስተናግዳቸው ከሆነ አንዳንዱ ያልሰራውን ውጤት ጨምርልኝ እያሌ ቢሮህን ያንኳኳል። ትሁት ነጋዴ ከሆንክም የእቃውን ዋጋ እያወቁ አንተን ግን ዋጋውን በግማሽ እንድትቀንስላቸው ይጠይቁሃል። ቢሆንም ትሁት ሁን! ለእነዚያ ሰዎች ብለህ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሽልማት የሚያስገኝልህን ትህትናህን መተው የለብህም። እርሱ በቀኑ ከፍ እስኪያደርገን ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ ያዘዘው ራሱ እግዚአብሔር ነውና። ለእነዚያ ሰዎች ግን ተገቢውን ጊዜና ቦታ መርጠህ ትሁት ብቻ ሳትሆን ብልህም እንደሆንክ ታሳያቸዋለህ። "እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ" (ቆላ. 3፡12) https://t.me/tetelestaye
Show all...
የልቦና አይኖች ሲከፈቱ…. የትኛውም በክርስቶስ የሆነ እውነተኛ አማኝ የእግዚአብሔር ልጅ እና ወራሽ ነው። የአሁኑ የኑሮ ሁኔታ ሳይገድበው፤ ወጣት ሽማግሌ ሳይባል፤ የተማረ ያልተማረ ተብሎ ሳይለይ በኢየሱስ በማመኑ ብቻ ቤዛነትን ያገኘ፤ የርስቱ ቀብድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ የተሰጠው ክቡር ሰው ነው። የልቦና አይኖች ካልተከፈቱ በስተቀር በአንድ ጎስቋላ አማኝ ውስጥ ያለውን ክቡር ማንነት ሰው ሊረዳዉ አይችልም። ሰዎች ሲመለከቱህ አሁናዊ አለባበስህ፤ የምትኖርበት ቤት ሁኔታ፤ የቤተሰቦችህ የኑሮ አቅም ፊታቸው ላይ እየተደቀንባቸው እና እየጋረዳቸው በክርስቶስ ያለህን ክቡር ማንነት ሳያስተውሉ ይቀራሉ። እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ ያሉ የልቦና አይኖቻቸው የተከፈቱላቸው ብቻ ናቸው በክርስቶስ ውስጥ አድርገው ሊመለከቱህ እና ሊያከብሩህ የሚችሉት። ለዚህ ነው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሀብታም እና ደሃ፤ የተማረ እና ያልተማረ እየተባለ መደብ ተቀምጦ ያለው። በዚህ ረገድ ጥቂት አቃፊ እና የተመሰገኑ የቤተ ክርስቲያን አጥቢያዎች እንዳሉ ባይካድም፤ በአብዛኞቹ ዘንድ ግን ይህ ችግር በስፋት ይስተዋላል። “የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ፦ አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም፦ አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን?” ያዕ. 2፡2-4። ጳውሎስ ለአብያተ ክርስቲያናት በላከው ደብዳቤ ሁል ጊዜ ስለ አማኞች እንደሚጸልይ ይናገራል። የጸሎቱ ዋና ነጥብ ደግሞ ክርስቲያኖች የልቦና አይኖቻቸው ተከፍተው በአማኝ ወንድሞቻቸው ውስጥ ያለውን የርስት ክብር እንዲያውቁ ነው። “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው” ይላል (ኤፌ. 1፡18-19)። ለእኛም በዚህ የጳውሎስ ጸሎት እና የያዕቆብ ምክር መሠረት መኖር እና የልቦና አይኖቻችን ተከፍተው ክርስቲያን እህት ወንድሞቻችንን በክርስቲያንነታቸው ብቻ መቀበልና ማክበር ይሁንልን! መልካም ቀን https://t.me/tetelestaye
Show all...
የንጉሥ ካህናት መጽሐፍ ቅዱሳችን በ1ጴጥ 2፡9 ላይ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ" ይለናል። እዚህ ቦታ ላይ የንጉሥ ካህናት የሚለው ቃል በአማርኛው እትም ላይ ባግባቡ ስላልተተረጎመ ብዙ ጊዜ በስህተት እንድንረዳው ምክንያት ሆኖአል። ይህም "የንጉሥ ካህናት" የሚለውን "ንጉሥ" ያለው እግዚአብሔርን እንደ ሆነ በማሰብ "የእግዚአብሔር ካህናት" እንዳሚል አድርገን ስንረዳ ቆይተናል። ይሁን እንጂ በቦታው የተጠቀሰው ያ አይደለም። የእንግሊዝኛውን እትም ስናነብ "Royal priesthood" ይላል። ይህም በቀጥታ ሲተረጎም "ከንጉሣዊ ቤተሰብ የሆኑ ካህናት" የሚል ፍቺ ይሰጠናል። ይህ ትልቅ ምሥጢር አለው። በብሉህ ኪዳን አንድ ሰው በተመሣሣይ ሁኔታ ካህን እና ንጉሥ መሆን አይችልም ነበር። ከይሁዳ ነገድ የሆነ ሰው ብቻ ንጉሥ መሆን የሚችል ሲሆን ከሌዊ ወገን የሆነ ሌዋዊ ብቻ ካህን ይሆናል። አንድ ንጉሥ ልክ እንደ ካህን እሆናለሁ፣ መስዋዕት አቀርባለሁ ወይም አጥናለሁ ብሎ ቤተ መቅደስ ቢገባ ወይ ይቀሰፋል ወይ በለምፅ (የቆዳ በሽታ) ተመቶ ይወጣል እንጂ በደህና አይመለስም። በአዲስ ኪዳን ግን ነገሮች ተለዋውጠዋል። ለውጡን ያመጣው ደግሞ መስቀል ላይ የተሰራው ሥራ ነው። ክርስቶስ በሥጋው የይሁዳ አምበሣ ስለ ሆነ የንጉሥ ቤተሰብ ነው። እርሱ ደግሞ ከአብ ጋር የሚያስታርቀንን የማስተሰሪያውን መስዋዕት ያቀረበ ልቀ ካህን ነው። እርሱ ሁሉ በሁሉ ነው። በዚህ ምክንያት በእርሱ ያመንነውን እኛን ደግሞ ንጉሥም ካህንም አደረገን። በምድር ላይ ብዙ ነገሮችን የምንቀይር ነገሥታት ነን። ደግሞም በጨለማ ውስጥ የሚኖርን ሰው ጠርተን ከእግዚአብሔር ጋር የምናስታርቅ ካህናት ነን (2ቆሮ 5፡20)። እንደ ንጉሥነታችን ወደ ጎን (horizontal) ስንሠራ እንደ ክህነታችን ደግሞ ወደ ላይ (vertical) እናገለግላለን። ብዙ ነገሥታት ስላሉ የወንድሞች በኩር የሆነው ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ (ንጉሠ ነገሥት) ሲሆን፣ ደግሞም ብዙ ካህናት ስላሉ እርሱ ልቀ ካህን ነው። ክብር የኢየሱስ አባት ለሆነው ለእግዚአብሔር ይሁን! በልጁ መስዋዕትነት ይህን አድርጓል። እኛ የንጉሥ ካህናት ነን። ይህን የሚያነብም "አዎ ነኝ" ይበል! ጸጋው ይብዛላችሁ! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ስለ ሰው ኖሮ ስለ ሰው የሞተ ሰው ጌታችን ኢየሱስ የሰውን ልጆች ኃጢአት ተሸክሞ በመስቀል ላይ እንደሞተ እናምናለን። ነገር ግን፤ እርሱ እኛን ወክሎ በምድር ላይ የኖረውን ኑሮ ብዙ ጊዜ እያስተዋልን አንመላለስም። እርሱ አምላክ እንደ መሆኑ መጠን ለዘላለም የተቀደሰ ቢሆንም በምድር ላይ በነበረው ቆይታው ስለ እኛ ራሱን ቀድሶ (ከኃጢአት ተለይቶ) ኖሮአል። ሕግ ሰጪ የሆነው አምላክ ራሱን የሕግ ተገዥ አደረገ። ፍጥረታትን ማዘዝ የሚያውቅ ጌታ መታዘዝን ተማረ። እኛ በእርሱ ቦታ ሆነን ጻዲቃን እንድንሆን እርሱ የእኛን በደል ወስዶ ኃጢአት ሆኖአል። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦ ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤ ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ (ሮሜ. 5፡12-15) ብዙ ሰዎች በመጀመሪያው አዳም ጥፋት ምክንያንት በወቅቱ ኖረው ከሰውዬው ጋር ባይተባበሩም እንኳን የእርሱ ልጆች በመሆናቸው ብቻ በደለኞች እንደተደረጉ በሙሉ ልባቸው ያምናሉ። ይሁን እንጂ፤ የኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) እነርሱን ወክሎ በሰራው ሥራ በሌሉበት በተወሰነው ውሳኔ ጻድቃን እንደተደረጉ በሙሉ ልባቸው መቀበል ይተናነቃቸዋል። እንደተባለውም አምላክ ጽድቅን የጠገበ ቢሆንም ራሱን ዝቅ አድርጎ የታዘዘው ጽድቅ የተራቡትን ጽድቅን ለማጥገብ ነው። እርሱ ከሕግ በታች ሆኖ የኖረው ብዙዎችን ከሕግ በላይ ለማድረግ ነው። አምላክ የማይሞት ቢሆንም ሰው የሆነው አምላክ ግን የእኛን ሞት ሞቶ፤ ሞታችንን እንቅልፍ አደረገው። ስለሆነም፤ አንድ አማኝ ኢየሱስ እርሱን ወክሎ እንደ ሞተ ብቻ ሳይሆን እርሱን ወክሎ የጽቅድ ሕይወት እንደኖረም ጭምር ማመን አለበት። ይህ ብቻም በቂ አይደለም። ኢየሱስ አማኙን ወክሎ በአብ ፊት ለመታየት በሰማያዊ መቅደስ እንደሚኖርም መቀበል አለበት። ይህን ያልተረዳ ሰው የራሱን ጽድቅ አቡክቶ ለመጋገር ሲታትር እድሜውን ይጨርሳል። የአዲስ ኪዳኑን እውነት የተረዳ ግን በእግዚአብሔር በሰራለት ሥራ አርፎ ይቀመጣል። እውነቱም ኢየሱስ ስለ ሰው ኖሮ፤ ስለ ሰው ሞቶ፣ ስለ ሰውም ከሙታን ተነሥቶ የሚኖር ተወዳጅ አምላክ መሆኑ ነው። ክብር ይሁንለት! መልካም ቀን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
"በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?" መጽሐፍ አላለም! የእግ/ር ልጆች እንደምን ቆያችሁ? መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መልካም ነው። የምናነበው ግን ተጠንቅቀን ካልሆነ የምናነበውን ነገር በስህተት እንድንረዳው ያደርገናል። ስህተቱ ሳይታረም ደጋግመን ማንበባችን ደግሞ ስህተቱ እውነት እስኪመስለን ድረስ በውስጣችን እንዲታተም ያደርግ ይሆናል እንጂ ወደ እውነት አያደርሰንም። ከላይ በርዕሱ ላይ የተቀመጠው አረፍተ ነገር ከገላቲያ መጽሐፍ 3:2 ላይ የተወሰደ ነው። ጳውሎስ በዚህ ክፍል የገላቲያን ሰዎች ''በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?" አላላቸውም። ይልቅ ያላቸው ''በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጸማላችሁን?" ነው። እንግሊዝኛውን ስታነቡ ደግሞ "Are ye so foolish? having begun in the Spirit, are ye now made perfect by the flesh?" ይላል። ከዚህ ላይ ማስተዋል እንደምትችሉት ትፈጽማላችሁ (finish) ማለትና ትፈጸማላችሁ (made perfect) ማለት ከፍተኛ የሆነ የትርጉም ልዩነት አለው። የመጀመሪያው መፈጸም (ጸ ላልቶ ሲነበብ) ነገርን ወይም ተግባርን ወደ መጨረሻ ማምጣት የሚለውን ትርጉም ሲይዝ ሌላኛው መፈጸም (ጸ ጠብቆ ሲነበብ) ደግሞ ፍጹም መሆን ወይም መጽደቅን የሚያመላክት ነው። ይህን ጥቅስ ለምሳሌ፤ ሁለት ሰዎች ውይይታቸው በጸሎት ጀምረው በኋላ በኋላ ወደ ክርክር ሲገቡ አይተን "ተው እንጂ፤ በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?" ብለን ከጠቀስንላቸው እኛ ራሳችን የገላቲያን ክፍል አልተረዳነውም ማለት ነው። ጥቅሱን አንሻፍፈን ላልተጻፈበት አውድ ከምንጠቀም የሰዎቹን ጥልና ክርክር መከልከያ ሌላ ጥቅስ ብንፈልግ ይሻላል። ሀሳቡ ጠቅለል ተደርጎ ሲቀርብ ጳውሎስ እያለ ያለው "እናንተ በህግ ሥራ ጽድቅ እንደማይገኝ ተረድታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የተቋደሳችሁ የገላቲያ ሰዎች አሁን ምን ነክቶአችሁ ነው በሥጋ (በህግ ሥራ) ፍጹማን ልትሆኑ የምታስቡት ወይም የምትታገሉት? ስለጽድቅ ባሰባችሁ ቁጥር ወደ አይነ ህሊናችሁ ይመጣ የነበረው እናንተን ለማጽደቅ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለው ኢየሱስ ነበር። እግዚአብሔርም በዚህ እምነታችሁ ምክንያት በመካከላችሁ ብዙ ታምራትን አድርጓል። ታዲያ ያኔ መንፈስ ቅዱስ የወረደላችሁ ጸንታችሁ የሙሴን ህግ በመጠበቃችሁ መሰላችሁን? 'በኢየሱስ እመን ትድናለህ' የሚለውን የወንጌል ቃል በማመን ብቻ አልነበረም እንዴ የዳናችሁት? ታዲያ ዛሬ በሥራ መጽደቅ ይቻላል ብላችሁ እንዲታስቡ ያደረጋችሁ እና አዚም የዘራባችሁ ማን ነው?" ነው። ወገኔ፤ ጽድቅ በእምነት ብቻ ነው። "በሥራ ጽድቅ የለም ክርስቶስ ነው ጽድቄ..." እንዳለው ዘማሪ እዝራ። መልካም ቀን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
📢 ገንዘብ የሌላችሁ ኑ ግዙ እንደምን ቆያችሁ የኢየሱስ ወዳጆች? ዛሬ እንደተለመደው ከመጽሐፈ ቅዱስ ክፍል አንድ ነገር ላካፍላችሁ። እርሱም ያለ ገንዘብ መግዛት ስለሚቻልበት ሁኔታ ነው። ይህ ከገበያ ሥርዓት ውጭ የሆነው የግብይት ሥርዓት አንድ ልዩ ነገር እንደሚያስተምራችሁ እርግጠኛ ነኝ። ስለ ቅዱስ ቃሉ የጌታችን ስም ይባረክ! "እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።" ኢሳ. 55:1 ልብ በል "ገንዘብ የሌላችሁ ኑ ውሰዱ ሳይሆን ግዙ ነው የሚለው"። ይህንን ጥቅስ የሚያነብ አንድ ችኩል ሰው ክፍሉ የአጻጻፍ ችግር እንዳለበት ሊደመድም ይችላል። ምክንያቱም ገንዘብ የሌላችሁ ኑ ግዙና ብሉ! ይላልና። ሰው ገንዘብ ሳይኖረው እንዴት ገዝቶ ልበላ ይችላል? እውነት ነው መግዛት የሚቻለው ገንዘብ ሲኖር ብቻ ነው። ነገር ግን፤ አንዳንድ ጊዜ አንተ ገዝተህ ሌላው ከፍሎልህ የምትመለስበት ቀን ይኖራል። በዚህን ጊዜ ምንም ያህል ከኪስህ አውጥተህ ባትከፍልም እንኳን ስለገዛኸው እቃ በራስህ ትተማመናለህ። ራስህ እንደገዛኸው ስለምትቆጥር አትሸማቀቅም። ምንድን ነው የሚገዛው? በክፍሉ የተጠቀሰው ምግብ የሚያወራው መንፈሳዊ መብል ስለሆነው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። ሰዎች ይህን ጽድቅ በራሳቸው የሚያገኙ እየመሰላቸው ብዙ ጥረዋል። እየጣሩም ነው። ነገር ግን የዚህ ጽድቅ ዋጋው እጅግ ውድ ስለሆነ የሰው ልጅ በጭራሽ ሊያገኘው አልቻለም፦ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋልና(ሮሜ 3፡23) ሰው በሥራ የሚገኝን ጽድቅ እየፈለገ እንኳን ውደ ጽድቅ ወደ ሕግ ራሱ መድረስ አልቻለምና (ሮሜ. 9:31)። ታድያ፤ ጽድቅን እየፈለጉ ነገር ግን መግዛት ያቃታቸው ሁሉ ያለገንዘብ መግዛት የሚችሉበትን አሰራር እግዚአብሔር ዘርግቷል። ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ዋጋውን ስለከፈለላቸው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ይህን ጽድቅ የራሳቸው ማድረግ ይችላሉ። እርሱ በመስቀል ላይ የከፈለው ውድ ዋጋ ለእግዚአብሔርን ጽድቅ የቀረበ ዋጋ ነው። በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን እንደሚል። የራስህን ጽድቅ ለማስቆጠር ብትጥር አትችልም። ጽድቅን በዋጋ አትግዛ። አያጠግብህም። ያለዋጋ መግዛት ይሻልሃል! እንዴት ነው ያለ ዋጋ መግዛት የምችለው❓ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የጌታ ደም አንተን ለማጽደቅ እንደሆነ ብቻ በማመን የኢየሱስን ጽድቅ የራስህ ማድረግ ትችላለህ። "እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና" (ሮሜ. 9:31፤ 10:3-4) የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!
Show all...
እውን ኢትዮጵያ ቅድስት አገር ናትን? ይወራል። ትምክህቱም ብዙ ነው። ኢትዮጵያ ቅድስት አገር ስለሆነች አትነካም የሚል። በመሠረቱ የሀገር ቅዱስ እና ርኩስ የለም። የሰው ርኩስ እና ቅዱስ ግን ሊኖር ይችላል። አለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛዋ ቅድስት የተባለችው በእሥራኤል ሀገር የምትገኝ የኢየሩሳሌም (ጽዮን) ከተማ ነች። ሌላው ቀርቶ ሰማሪያ የእሥራኤል ክፍለ ሀገር ናት። ግን ቅዱስ ተብላ አልተጠራችም። እንግዲህ ኢትዮጵያም ቅድስት ሀገር ናት እየተባለ ነው። በርግጥ እኔም እንደማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ ሀገሬ ቅድስት ብትሆን ደስ ይለኛል። ግን በስሜት አይደለም። ምክንያትዊነትን ይጠይቃል። ቅድስት ሳትሆን ቅድስት ነች ብል ቅድስት ስለማትሆን። የኢትዮጵያን ቅድስትነት ከሚያቀነቅኑ ሰዎች የምሰማው አንዱ ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሟ መጠቀሱ ነው። ዌል እንግዲህ! ቅድስትነት መለኪያው የሀገር ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መጠቀስ ከሆነ እስቲ እንይ። ሀገራችን በመጽሐፍ 43 ጊዜ የተጠቀሰች ሲሆን እስራኤል ሀገር 2331 ጊዜ ስሟ ሲጠራ፣ ግብጽ 568 ጊዜ፣ ፍልስጥኤም 255 ጊዜ፣ ግሪክ 40 ጊዜ፣ ሶሪያና ህንድን ጨምሮ ሌሎችም በአቅምቲ ተጠቅሰዋል። ታዲያ የሀገር ቅድስና በስም መጠቀስ ከሆነ ከላይ የዘርዘርኳቸው አበይት ሀገራት በሙሉ ቅዱስ ሀገራት ናቸው ማለት ነዋ! ቁምነገሩ ግን ሀገሬ ስሟ በበጎ ወይስ በክፉ ተነሳ የሚለው ይመስለኛል። እውነት ለመናገር፤ በአብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የኢትዮጵያ ስም በመልካም አልተንሳም። ለአብነትም “እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ” የሚል አለ፤ እንዲሁም “ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል” የሚል ይገኙበታል (2ዜና 14:12 ሕዝ 30:4)። ወደ ሌላኛው የኢትዮጵያን ቅድስትነት ለማስረዳት ወደሚቀርበው ምክንያት ሳልፍ፤ “ኢየሱስ ለእናቱ ኢትዮጵያን አሥራት አድርጎ ሰጠ” የሚል ነው። ይህ እንኳን ብዙ አያከራከረንም። ሲጀመር አሥራት ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ነው ወይስ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠው ሥርዓት ነው? የሚለውን ማሰብ ብቻ በቂ ነው። ነገር ግን ሌላ አንድ ጥያቄ አለኝ፤ እርሱ ብቻ ይመለስልኝ። አሥራት ማለት ከአስር አንድ ማለት ነው። ይህም ሰው ካለው ወይም ከሚያገኘው አስር ነገር አንዱን ለእግዚአብሔር እንዲሰጥ የሚያዝ ነው። ትዕዛዙን የሰጠው ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር ነው። ማለትም ኢየሱስ። የማይሆነው ሆነ ብለን እናስብና አምላክ ለሰው ልጅ አሥራት ሰጠ እንበል። የአሥራቱ አይነት ደግሞ ሀገር ነው። መቼም ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሔር ናትና ጌታ በምድር ላይ በትንሹ 195 ሉዓላዊ ሀገራት አሉት። ታድያ ራሱ የሰጠውን ህግ ራሱ አይጥስምና ከእነዚህ ሀገራት አሥራት (ከአስር አንድ) ሲያወጣ በድምሩ 19 ሀገራት ይሆናሉ ማለት ነው። የኔ ጥያቄ ኢትዮጵያ አንዷ ከሆነች ቀሪው አሥራት 18 ሀገራት እነ ማን ናቸው? የሚል ነው። መሠረት ከሌለው ሀገራዊ ቅድስና ወደ ግላዊ ቅድስና ብናተኩርና ሁሉም ዜጋ አዕምሮው በጎጥ ከሚያስብበት ወጥቶ ፈጣሪን ደስ የሚያሰኝና ሀገርን የሚጠቅም ነገር እያለመ ለእግዚአብሔር ራሱን ቢቀድስ እልፍ እጥፍ ጠቃሚ ይመስለኛል። በተረፈ በባዶ ማነጀብ የትም አያደረሰንም። ክፋትን የተካነ ሰው በሞላበት ስለ ሀገር ቅድስና ማውራት የነገር ጣዕም የለውም። ካልሆነ ግን ኢትዮጵያ ዜጎችዋ በቀን ሦስት ጊዜ የማይመገቡባት ብቸኛዋ ቅድስት ሀገር እየተባለች ትቀጥላለች ማለት ነው። ይሄው ነው፤ እውነት አርነት ያወጣል! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ዳግመኛ መወለድ እና የውሃ ጥምቀት ብዙ ሰዎች የውሃ ጥመቅትን ከዳግመኛ መወለድ ጋር አንድ ወይም ተመሳሳይ አድርገው ሲያቀርቡ ይታያሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ሁለት ነገሮች እርስ በርሳቸው የማይቃረኑ ነገር ግን የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ በዛሬው ጽሑፌ ግልጽ ለማድረግ እፈልጋለሁ። ዳግመኛ መወለድ ማለት አንድ ሰው አዳማዊ ወይም አሮጌ ማንነቱን ጥሎ በክርስቶስ አዲስ ሰው የሚሆንበት መንፈሳዊ አሰራር ነው። ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ምንም ያህል መልካም ሥራ ቢኖረው የእግዚአብሔር ልጅ ሊሆን፤ መንግስተ ሰማያትንም ሊወርስ አይችልም። በመሆኑም፤ አንድ ሰው ዳግመኛ ወይም ለሁለተኛ ጊዜ ተወለደ የምንለው ሰውዬው ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኙ አድርጎ በተቀበለ ቅጽበት ነው። ይህ ውልደት የሚከናወነው አማኙ በእግዚአብሔር ልጅ ባመነበት ቅጽበት በሚጠመቀው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እንጂ ከእምነቱ በኋላ በሚያደርገው የውሃ ጥምቀት ሥነ ሥርዓት እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። አንዳንድ ግለሰቦች እና የኃይማኖት ድርጅቶች ዳግመኛ መወለድን ከውሃ ጥምቀት ጋር አንድ አድርገው መረዳታቸው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆኑ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አድርጓቸዋል። የጨቅላ ሕጻናት የውሃ ጥምቀት ጽንሰ ሀሳብም ከዚሁ የተሳሳተ አረዳድ የመነጨ ነው። በመሠረቱ የውሃ ጥምቀት ሰውን አያድንም። ጌታችን “ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል” ብሏል (ማር. 16፡16)። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር የሚፈረድበት ሰው ያልተጠመቀ ሳይሆን ያላመነ ነው። ያላመነ ሰው ቢጠመቅ ባይጠመቅ ለውጥ ስለማያመጣ ማለት ነው። ያመነ ሰው ግን የውሃ ጥምቀትን ተግባራዊ የሚያደረገው እንደ አንድ የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ነው። የውሃ ጥምቀት ትርጉሙ “ከክርስቶስ ጋር ሞቼ ከእርሱ ጋር ተነስቻለሁ” የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ነው። ወደ ውሃ ውስጥ በምንሰጥምበት ቅጽበት “ክርስቶስ ስለ እኔ ሞቶ እንዲህ ተቀበረልኝ፤ እኔም ከእርሱ ጋር ተቀብሬአለሁ” የሚል መልዕክት በምልክት የምናስተላልፍ ሲሆን ከውሃው ውስጥ በምንወጣበት ቅጽበት ደግሞ “ክርስቶስ እንዲህ ከሙታን ተነስቶልኛል፤ እኔም ከእርሱ ጋር ተነስቻለሁ” የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን ማለት ነው። በዚሁ አጋጣሚ የአንድንድ ቤተ እምነቶች ውሃ የመርጨት ልማድ የሚተቸውና እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውሃ ጥምቀት የማይቆጠረው ከላይ የተጠቀሰው ምስጢር ምልክት ሆኖ ማገልገል ስለማይችል ነው። ከዚህ ውጭ የውሃ ጥምቀት በራሱ የሚያድን ወይም ዳግመኛ ከመወለድ ጋር አንድ አድርጎ መረዳት ፍጹም ስህተት ነው። በአዲስ ኪዳን ታሪክ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለአህዛብ ወንጌልን እንዲያደርስ የተላከ አንጋፋ የወንጌል ሰው እንደሆነ እናውቃለን። በእርሱ የወንጌል ስርጭት ብዙዎች አምነው ከጨለማው መንግስት ማምለጥ ወይም መዳን ችለዋል። ይሁን እንጂ ይህ ሐዋሪያ ወንጌልን ለመስበክ የሚጥረውን ያህል ሰዎችን ለማጥመቅ ሲጥር አይታይም። ይህም የውሃ ጥምቀት የተከበረ የቤተ ክርስቲያን ስነ ሥርዓት ከመሆን ባለፈ በራሱ የሚያድን ያለመሆኑ ማሳያ ነው። ሐዋሪያው በ1ቆሮ. 1፡14_17 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተናግሯል፦ “በስሜ እንደ ተጠመቃችሁ ማንም እንዳይል ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ አንድን እንኳ ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ጨምሬ ሌላ አጥምቄ እንደ ሆነ አላውቅም። ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም” በተመሳሳይ ሁኔታ ፊልጶስ የተገናኘው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ወንጌልን ሲሰማ ነበር። ፊሊጶስ ስለ ክርስቶስ በመጽሐፍ የተጻፉትን ክፍሎች እያብራራለት ሲጓዙ ወደ አንድ ውሃ ደረሱና ጃንደረባው በራሱ ጊዜ “መጠመቅ እፈልጋለሁ” አለ። የፊልጶስ ምላሽ ምን ነበር? “በፍጹም ልብህ ካመንክ መጠመቅ ተፈቅዶልሃል” አለው። ጃንደረባውም መልሶ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” አለ። ይህ ነው የሚፈለገው። ጃንደረባው የውሃ ጥምቀት ስነ ሥርዓት ላይ ከመሳተፉ በፊት በእምነት ዳግመኛ መወለድ ነበረበት። ከዚህ በኋላ እንደ ማንኛውም አማኝ የአዲስ ኪዳን ሥርዓት የሆነውን የውሃ ጥምቀት ማከናወን ይችላልና ፊልጶስ አጠመቀው (ሐዋ. 8፡26_38) አንድ አማኝ እድሉ እስካለው ድረስ የውሃ ጥምቀት ስነ ሥርዓትን ማከናወን አለበት። ይሁን እንጂ፤ የውሃ ጥምቀት ዳግመኛ ከመወለድ ጋር ተመሳሳይ አይደለም። በሌላ አገላለጽ፤ ዳግመኛ መወለድ የሚያስችለው እምነት እንጂ የውሃ ጥምቀት አይደለም። ዳግመኛ መወለድ የሚፈጸመው በመንፈስ ጥምቀት አማካይነት ነው። የውሃ ጥምቀት ግን ሰው በመንፈስ ዳግመኛ መወለዱን የሚገልጽበት አካላዊ ምልክት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ደካማው ብርቱ ነኛ ይበል! እንደምን ቆያችሁ ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች። ዛሬ ደግሞ የሚገርም የአባቴን ቃል ላካፍላችሁ ወደድኩ። መነሻ ሀሳብ አድርጌ የወሰድኩት ትንቢተ ኢዩኤል 3፡10 ላይ የሚገኝ " ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም። እኔ ብርቱ ነኛ ይበል" የሚል ጥቅስ ነው። ክብር ለኢየሱስ ይሁን! በክርስቶስ አምነን የዳንን ሁላችን ስለ መዳናችን የሠራነው አንዳች ሥራ የለም። ማንም በጽድቁ ምክንያት የዳነ በድካሙ ምክንያት የቀረም የለም። ሁላችንም የእግዚአብሔር ጽድቅ ተቆጥሮልን ነው እንጂ አስቆጥረን አይደለም። ይሁን እንጂ ያመንን እኛ ለመዳን ሳይሆን ስለ ዳንን፣ ለማስቆጠር ሳይሆን ስለ ተቆጠረልን የቅድስና ኑሮ መኖር እንሻለን። ነገር ግን በጎ ለማሰብ እና ለመሥራት በታገልን ቁጥር እያቃተን ሲመጣ አንድ ነገር እንገነዘባለን፦ የዳነው መንፈሳችን እንጂ ሥጋችን እንዳልሆነ። ይህ ያለ ምክንያት አይደለም። ቃሉ እንደሚናገር ሥጋ ለእግዚአብሔር ህግ አይገዛም። መገዛትም ተስኖታል" (ሮሜ 8፡7) ተብሎ የተጻፌ ሀቅ ነው። በዚህ ምክንያት በዚህ ሥጋችን ውስጥ እስካለን ድረስ ይህ ድንኳን ከብዶን እንቃትታለን (2ቆሮ 5፡4)። ታዲያ ስንቃትት ምን አይነት ምላሽ እንስጥ ወይስ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንቅረብ የሚለው የጽሑፌ ዋና ነጥብ ነው። እኛ ብዙ ጊዜ የለመድነው እና እውነቱ ያልገባቸው አንዳንድ አስተማሪዎች ያስተማሩን ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ በፍርሀት እንድሆን ነው። በእርሱ ፊት "አምላኬ ሆይ፦ እኔ የማልረባ፣ እኔ ወራዳ፣ እኔ ርኩስ ነኝ" ማለት እንደ ትህትና፣ እንደ ጥሩ ንስሃም ይቆጠራል። ይህን ስናደርግ አምላክ በደንብ የሰማን ይመስለናል። እውነታው ግን ያ አይደለም። ጳውሎስ በተደጋጋሚ በክርስቶስ ያገኘንነውን ድፍረት እንዳንጥል አስተምሮናል። " እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ" ዕብ 10፡35፣ " ብሎናል። ደግሞም "እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት (bodily) እንቅረብ" ዕብ 4፡16 ይላል። ምን ጊዜም ቢሆን ሰው በኃይሉ ሊበረታ አይችልም። ምክንያቱም " እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና" 1 ሳሙ 2፡9 የሚለው ቃሉ የታመነ ነው። ከጨለማ ለመውጣት እኮ ይታገላሉ። ግን አይችሉም። ሰው በራሱ ስለማይበረታ! የሰው ልጅ "በርታ!" አይባልም። መቼም አይበረታም። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን 'በርታ' አላለውም። ነገር ግን " እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ" 2ጢሞ 2፡1) ይለዋል። አዎ፤ ጸጋው ብቻ ነው ሰውን የሚያቆመው። የማይቻለውን የሚያስችል ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ደካማው ብርቱ ነኛ ይበል! ይህ ከንቱ ፉከራ አይደለም። በመንፈስ አሠራር የሚሠራ እምነት እንጂ። ታዲያ ይህን የሚያነብም ብርቱ ነኝ ይላል! ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ተፈጽሞአል! እግዝአብሔር በኃጢአተኛው ላይ የማይጨክነው ያኔ በልጁ (በኢየሱስ) ላይ ጨክኖ ስለ ነበረ ነው:: እግዚአብሔር መተላለፍህን የሚያልፍበት ምክንያት፥ መተላለፍህን በሙሉ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ በአንዲያ ልጁ ላይ ጭኖ ስለ ነበረ ነው (1ቆሮ 5:21፥ 1ኛ ጴጥ 2:24):: አሁን አንተ በኢየሱስ ብታምን (ወሳኝ ጉዳይ ነው፥) ኃጢአትህ ከብዙ አመታት በፊት ተወግዶልሃል:: በርሱ ማመን ማለት ምንድነው? በርሱ ማመን "እርሱ አምላክና አዳኝ ነው" ብሎ ማመን ብቻ አይደለም:: ነገር ግን ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ለዘለዓለም ጭራሽ ሊያጠፋህ እንደማይችል በርሱ መተማመንም ጭምር ነው-በቃ ጌታህ፥ መምህርህና ሁሉ ነገርህ አድርገህ መቀበል:: አሁን እርሱን ከተቀበልኸው፥ እርሱ አስቀድሞ ተቀብሎሃል:: አንተ ብቻ በሙሉ ልብህ ካመንኸው እውነቱን ልንገርህ? ወደ ገሃነም አትሄድም:: ይህም የክርስቶስ መስዋዕትነት ዋጋ ቢስ ሆኖ እንዳይቀር ነው:: አብ መስዋዕቱን ከተቀበለ በኋላ መስዋዕቱ የቀረበለትን ኃጢአተኛ ማጥፋት ሊሆን የማይችል ነገር ስለሆነ ነው:: እውነተኛ አማኝ ይጠፋል ወይም ይኮነናል ብለህ የምታምን ከሆነ፥ ያ አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የቀረበው መስዋዕት ለምን አስፈለገ? ኢየሱስ እኔን ተክቶ እስከ ሞተ ድረስ: እኔ ደግሞ ስለ ምን እሞታለሁ? ስለዚህ ማንም ያን የበግና የጥጃ ያልሆነውን ክቡር መስዋዕት የተማመነ አማኝ ዳግም ሊጠፋ እንደማይችል ዛሬ ላይ እርግጠኛ መሆን ይችላል:: አብ በገዛ ልጁ ደም የተሰረዘውን ኃጢአቴን ሊያነብ፥ ሊቆጣኝም አይችልም:: በቃ የማይቻል ሆኖአል:: የምህረት ፏፏቴ በሆነው በኢየሱስ ለኃጢአተኛው ሰው የተሰጠው ጸጋ ምን ያህል አስተማማኝ እንደ ሆነ ማን ያስተውላል? እርሱ ግን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ (ዮሐ 19:28-31)፥ ተፈጸመ ብሎአል! መልካም ቀን!
Show all...
6 እና 9 ጥንታዊነት አልፎ ዘመናዊነት ሲመጣ የሰው ልጅ የአኗኗርና የአስተሳሰብ ዘይቤ ተቀይሯል። ዘመናዊነትም በሚበልጠው ዘመናዊነት ተሸንፎ ስፍራውን ለድህረ ዘመናዊነት ለቋል። የድህረ ዘመናዊነት (post modernism) የ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተወልዶ ከ40 አመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ ፍልስፍናው ለንድፈ ሀሳቡ አንጻራዊነትን (relativism) መሠረት ያደረገ ሲሆን ማንኛውም ነገር መዳኘት ያለበት በአንጻራዊነት ነው ብሎ ያምናል። ማለትም የቁስ መኖር፤ የግብረ ገብነት (moral) ጉዳይ፣ እውነትን (truth) በተመለከተ፣ የሰው ተፈጥሮ እና የመሳሰሉት ነገሮች በጊዜ በሁኔታ እና በአመለካከት ላይ የተመሰረተ እንጂ አንድ ወጥ ዓለም አቀፋዊ ትርጉም ሊሰጣቸው አይገባም የሚል አስተሳሰብ ነው። የቁስ እውነታን በተመለከተ የሚናየው ነገር ተጨባጭ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ብለው ያምናሉ። እንደ እነርሱ እይታ ከሆነ፤ አሁን ይህን ጽሑፌን እያነበብክበት ያለው ስልክ ወይም ኮምፑተር በገሀድ ያለ ስለመሆኑ በምን እርግጠኛ ትሆናለህ? እንደውም የመላኩን ፖስት እያነበብክ ስለመሆኑስ በምን ታውቃለህ? አይንህን ታምነዋለህን? ትባላለህ። ግብረ ገብነትን በተመለከተም “ትክክል” ና “ስህተት” የሚባል ነገር የለም። አንተ ትክክል ያልከው ነገር ለሌላው ትክክል ላይሆን ይችላል፤ ተገላቢጦሹም እንደዛው። አንድት ሴት ራቁትዋን ገብያ ብትወጣ፣ ሁለት ወንዶች እርስ በርሳቸው ቢጋቡ፤ ሰው ሰውን ቢገድል፤ ወ.ዘ.ተ እንደየሁኔታው ትክክል ሊሆን ላይሆንም ይችላል እንጂ በደፈናው ኢሞራላዊ የሆነ ነገር የለም ይላሉ። እውነትና ሐሰት የሚባል ነገርም የለም። ለአንተ 6 ቁጥር በተቃራኒ በኩል ለቆመ ሰው 9 ነው። ወሳኙ ቁጥሩን የምታነብበት ፖዚሽን ነው ይሉሃል። ነገር ግን፤ ቁጥሩን የጻፈውን ሰው ጠይቆ እውነቱን መረዳት ነው እንጂ በመሰለኝ መጓዝ አይገባም። እኔ መሠረታዊውን እውነት ፈልጌ አላገኘሁም ማለት ነገሩ እውነት አልነበረውም ማለት አይደለም። በሀገራችንም ብዙ ሰዎች በተለይም ወጣቱ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ እየሆነ መምጣቱ ሸፍነን የማንደብቀው እውነት ነው።እንደሚታወቀው ብዙዎቻችን የተገኘውን ፍልስፍና ሳናላምጠው የመዋጥ ልማድ አለብን። ቻይናውያን የተገኘውን ሁሉ ወደ አፋቸው የመክተት ችግር ስላለባቸው የሕጻንነት የዕድሜ ክልል (infancy stage) ላይ ናቸው ብለው የሚተቿቸው አሉ። እንዲሁም፤ በሀገራችን ብሎም በአፍርካ የተገኘውን ሁሉ ወደ አዕምሮአችን የመክተት ችግር አለ። ይህም ሕጻንነት ነው። ሕጻናት የተነገራቸውን ሁሉ ያምናሉ፤ ይተገብራሉም። የምንሰማውና የምናየው ነገር እንደ የአይነቱ እኛን ወደ ከፍታ የመውሰድ አሊያም ገደል ውስጥ የመክተት አቅም አለው። ለዚህም ነው ጌታችን ኢየሱስ “ምን እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ” ያለን። በመሆኑም ወንድም እህቶቻችንን በሚሰሙት ነገር እንዳይወሰዱ መታደግ ይኖርብናል። እምነትህ የተሳሳተ እምነት (illusion) ነው ከሚል እሉዥን ነጻ መውጣት ያስፈልጋቸዋል። ዩንቨርስ የሚመራው በአንድ ወጥ ሥርዓት ነው። የፕሮቶኖችና የኤሌክትሮኖች መሳሳብና የተመሳሳይ ቻርጆች እርስ በርስ መገፋፋት ሥርዓት እግዚአብሔር ከትንጥዬው አተም እስከ ትልቁ ሶላር ስስተም ድረስ እንዲመሩበት የሰጠው ሥርዓት ነው። የሰው ልጅም የሚመራበት ሥርዓት የተጻፈ ህግ (ለእሥራኤል) እና ያልተጻፈ የህሊና ህግ (ለአህዛብ)ሰጥቶአቸዋል። ሁሉም ነገር በሥርዓት ብቻ ነው ህሊውናውን አስጠብቆ የሚኖረው። አንባቢዬ፡ አሁን እኔ “የስልክህን ጀርባ የያዙትን አራቱን ጣቶችህን ከስልክህ ላይ አንሳቸው” ብዬ ባዝህ ታደርገዋለህ? በፍጹም አታደርገውም። ለምን? የስልክ አያያዝ ሥርዓቱን ብትጥስ ስልክህ ወድቆ እንደሚሰበር እርግጠኛ ስለሆንክ ነው። የድህረ ዘመናዊነት ፍልስፍና ይህን ሀቅ ይክዳል። የሴትና ወንድ ጋብቻ ልጅ ማስገኘቱ፤ የወንድና ወንድ ጋብቻ ግን ፍሬ አልባ መሆኑ በራሱ የእግዚአብሔርን ቋሚ ሥርዓት ሊያስረዳቸው ሲገባ በራሳቸው ሀሳባዊ ዓለም ውስጥ ያለ ዕረፍት ይዳክራሉ። የነገሮች አንጻራዊነት ሰው ሁሉ የመሰለውን እንዲያደርግና የሰው ልጆች እንደ ማህበረሰብ እንዳይቀጥሉ የሚያደርግ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ነው። የመንግሥት ሥርዓት እንኳን የተፈጠረው ህግና ሥርዓትን በማዘጋጀት ግለሰባዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ በውጤቱም ማህበረሰባዊ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ነውና። ይህ ካልሆነ በመጽሐፍ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር” (መሣፍንት. 17፡6) ተብሎ እንደተጻፈ ይሆናል ማለት ነው። በበኩሌ ከዘመናዊነት ወደ ድህረ ዘመናዊነት የተደረገውን የአስተሳሰብ ጉዞ “የሰው ልጅ ሀሳብ ከፈሳሺነት (liquid state) ወደ ጋዝነት (gaseous state) የተደረገ ጉዞ ነው” ብዬ እገልጸዋለሁ። በጥንት ዘመን ሰዎች ጠንካራ ማህበራዊ ሞራልና ሥርዓት ነበራቸው። በዘመነ ዘመናዊነት ግን፤ ይህ ጠንካራ ባህል ተሸርሽሮ የሰዎች አስተሳሰብም ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላ አቅጣጫ በቀላሉ የሚፈስበት ሁኔታ ተፈጥሮ ቆይቷል። አሁን ደግሞ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ጭራሽ ሊጨበጥ ወደማይችልበትና ትነታዊ ሁኔታ አድጎ ይገኛል። ይህም ሠይጣን የሰው ልጅ ዕረፍት አልባ ሕይወት እንዲኖር አልሞ የሠራው ሥራ ነው። እግዚአብሔር ይገስጸው! በመጨረሻም፤ Roger Scruton የሚባል ሰው እንዲህ ብሎአል “እውነት የለም ወይም እውነት አንጻራዊ ነው የሚልህ ሰው ይህን በማለቱ እርሱን ራሱን እንዳታምነው እየጠየቀህ ነው። እናም አትመነው”። መልካም ቀን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
መግለጥ vs ማጋለጥ “ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ” ኤፌ. 5፡11 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮንፌረንሱ ተገኝተዋል። የተሰወረውን የመግለጥ የጸጋ ስጦታ ያለው (ወይም አለኝ ብሎ የሚያምነው) ሰው ይነሳና መናገር ይጀምራል፦ “አንቺ እዛ ጥግ ላይ የተቀመጥሽው ቀይ ለባሽ ተነስተሽ ቁም!”። ህዝቡ ሁሉ ምን ሊላት እንደሆነ ለመስማት እየቋመጠ ይጠብቃል። “ትላንት ማታ የት ነበርሽ?” ነቢዩ ቀጠለ “ከአንድ ወንድ ጋር ስታመነዝሪ እንዳደርሽ የጌታ መንፈስ ያሳየኛል”። በዚህ ጊዜ የሰው ሁሉ ዓይን በልጅቷ ላይ ይፈጥጣል። ልጅቷም የቆመችበት መሬት ተሰንጥቃ ብትውጣት እየተመኘች በእፍረት አንገቷን አቀርቅራ “በእግዚአብሔር ሰው” ፊት ቆማለች። በዚህ ጊዜ የነቢዩ በራስ መተማመን ይጨምራል። “እስቲ ዓይን ዓይኔን እያየሽ ንገሪኝ፤ ዋሽቻለሁ?” ብሎ ሲያፈጥባት “እ..እ..ው...ነት ነው” ትላለች ኃጢአተኛዋ። ነቢዩም ጉባኤውን አንዴ በአይኑ ገርመም ያደርጋል። የተለመደውን ጩኸታችሁን አቅልጡት እንጂ ማለቱ ነው። በዚህን ጊዜ ለማጨብጨብ እንጂ ለማሰላሰል ያልታደለው ታዳሚ ነቢዩ የተናገረው ስለተገናኘለት አዳራሹን በጭብጨባና ጩኸት ያጨሰዋል። ልጅቷም አፍራ ዳግም ጉባኤው ላትመጣ ትሰደዳለች። “ለመሆኑ ነቢዩ ልጅቱን እንዲህ በአደባባይ ከሚያሳፍራት ለብቻዋ አግኝቶ ለምን ንስሃ እንድትገባ አይነግራትም?” ብሎ የሚጠይቅ አይኖርም። ቢኖርም ጆሮ ሰጥቶ የሚሰማው አይገኝም። ይልቅ “የጨለማን ሥራ ግለጡት ተብሎ ተጽፏል” የሚል ቃል ጠቅሰው አፉን ሊያስዙት ይሞክራሉ እንጂ። በምሳሌ ያየንነው አገልጋይ ወንድማችን ያደረገው ነገር “መግለጥ ወይስ ማጋለጥ”? መጽሐፍ ቅዱሳችን ክርስቲያኖች ወንድማቸው በኃጢአት ውስጥ ወድቆ ካገኙት ወይም መንፈስ ቅዱስ ከገለጠላቸው እንዲያርሙት ያዛል። ገና ከጅምሩ ለእሥራኤል የተሰጠው ምክር “ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው” የሚል ነበር። ነገር ግን ግሣጼውን በምን መልኩ ማድረግ እንዳለብን የሚነግሩን የአዲስ ኪዳን ክፍሎችም አሉ። የተወሰኑትን፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” ገላ. 6፡1_2 እዚህ ላይ ጳውሎስ በኃጢአት የተወሰደውን ወንድማችንን እንድንመልሰው ሲነግረን ይህንንም በየውሃት መንፈስ (spirit of gentleness) እንድናደርገው አስጠንቅቆናል። ለማረም በምናደርገው ጥረት ውስጥ ሰውዬውን መጉዳትም ስላለ ጥንቃቄ እንድናደርግ ተመክረናል። በተጨማሪም በኃጢአተኛው ላይ እንደውጫዊ ሰው መናገር ብቻ ሳይሆን የወንድማችንን የኃጢአት ሸክም እንድንሸከም፤ ማለትም ስሜቱ እንዲሰማንና የሥጋን ደካማነት ተረድተን ለወንድማችን/እህታችን እንድንራራለት/ላት ክርስቲያናዊ ኃላፊነት አለብን። ያዕቆብ በበኩሉ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሚከተለውን ጠንካራ መልዕክት አስቀምጦልናል፦ “ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ” ያዕ. 5፡19። ኃጢአተኛን ከስህተት መንገዱ የሚመልስ የሰውየውን ነፍስ ከሞት ያድናል። ይህን የሚያደርገው ግን በመግቢያው ላይ እንዳየንነው ኃጢአተኛውን በአደባባይ በማዋረድ ሳይሆን ኃጢአቱን በመሸፋፈን መሆን ይገባዋል። በመግቢያ ላይ የጠቀስኩትን ነቢይ እንደምሳሌ ወሰድኩት እንጂ ሁላችንም ከዚህ ችግር የጸዳን አይደለንም። ምናልባት በጠባብ ክፍል ውስጥ በጥቂት ሰው ፊት ሊሆን ይችላል፤ ብቻ ግን የራሳችን የጓዳ ምስጢር እስካልታወቀብን ድረስ ኃጢአተኛውን የመውቀስ ፍላጎትና ዝናባሌ በሁላችንም ላይ አለ። እኛም ያልተገለጠ ኃጢአት እንዳለብን ልብ ልንል ይገባናል። እርሱ አመንዝሮ ቢሆን አንተ ደግሞ ዋሽተሃል፤ ማመንዘርና መዋሸት ሁለቱም ኃጢአት ናቸው። እርሱ ሲሰርቅ ተይዞ ሊሆን ይችላል፤ አንተ ግን ሰውን እያማህ አልተያዝክም፤ ዳሩ ግን ስርቆትና ሐሜት በጌታ ፊት እኩል ኃጢአት ናቸው። በመሆኑም በግብዝነት የወንድማችንን ወይም የእህታችንን ልብ እንዳንሰብር መጠንቀቅ አለብን። ኃጢአተኛውን ስንገሥጽ እኛ ደግሞ በግብዝነትና በትዕቢት ስሜት ውስጥ በመግባት ኃጢአት ላይ እንዳንወድቅ “አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ” የሚል ወሳኝ ምክር ተቀምጦልናል። ለማጠቃለል፤ አንዳንዶች ወንድማቸው በኃጢአት ውስጥ ተዘፍቆ እያዩ በምን አገባኝ ስሜት ሳያርሙት ያልፋሉ። ሌሎች ደግሞ በኃጢአተኛው ወንድማቸው ላይ በመፍረድ፤ በማዋረድን በማሸማቀቅ ከእግዚአብሔር ማህበር ያርቁታል። ሁለቱም የስህተት ጎራዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ግሣጼ ግን ትህትናና የውሃነት ያለበት፤ ኃጢአተኛውን ወደ እውነተኛው መስመር መመለስን ዓላማው የሚያደርግ ነው። ሁላችንም ይህን የማድረግ ኃላፊነት አለብን። ይህን መፈጸም እንድንችል መንፈሱ ይርዳን! “ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” 1 ተሰ. 5፡14 https://t.me/tetelestaye
Show all...
የዘላለም ሕይወት ምንድነው? በዛሬው ጽሁፌ ትኩረት የማደርገው በዘላለም ሕይወት ላይ ነው። የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? እንደሚታወቀው በምድር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኃይማኖቶች ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ። ይህም ሁሉም የእምነታቸውን መሠረት ያደረጉት በዓለም መጨረሻ የእምነቱ ተከታዮች ሊኖራቸው የሚችለውን "የዘላለም ሕይወት" ነው። በርግጥ ኃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት የማይሄድ ሰው የዘላለም ጥፋት እንደሚጠብቀውም ይታመናል። ታዲያ የክርስትና (ማለትም የእውነተኞቹ የአዲስ ኪዳን አማኞች እምነት) ከዚህ የሚለየው በምንድን ነው? አንተስ የዘላለም ሕይወት አለህ? ወይስ ወደፊት ይኖርሃል? መልሱን ቀጣዩን አንቀጽ ከማንበብህ በፊት ለራስህ መልሰው! የዘላለም ሕይወት የሆነ ነገር (something) ሳይሆን የሆነ ማንነት (someone) ነው። ይህም ማንነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጌታችን "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ" ብሏል (ዮሐ 14:6)። ይህ ሕይወት የዛሬ 2000 ዓ.ም በፊት በአካል ተገልጦ ሰዎች አይተውታል፣ ዳስሰውታልም። "ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን" (1ዮሐ 1:2) አዎ፤ የዘላለም ሕይወት ራሱ ኢየሱስ ነው። አንድ አማኝ "በኢየሱስ ስም አምኛለሁ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት እንደማገኝ እርግጠኛ አይደለሁም" የሚል ከሆነ በአረዳዱ ላይ የሆነ የተምታታ ነገር አለ ማለት ነው:: ነገር ግን መጽሐፍ እንደሚነግረን ኢየሱስ አንድ የዘላለም ሕይወት ሌላ አይደለም። ታዲያ የዘላለም ሕይወት የሚኖረን መቼ ነው? በምድር ላይ ያሉ ኃይማኖቶች እንደሚሰብኩት የዘላለም ሕይወት በዓለም መጨረሻ ለደጋግ ሰዎች የሚቸር ነገር አይደለም። የዘላለም ሕይወት የነገ ቀጠሮ አይደለም። ኢየሱስ አለህ?.... በቃ የዘላለም ሕይወት አለህ። 1ኛ ዮሐ.5:11-13 "እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ"። እውነቱ የገባት አንዷ ዘማሪ እንዲህ ዘምራለች: "ገነት ገብቻለሁ እዚሁ ምድር ላይ.. ሌላ አልጠብቅም እስክሄድ ሰማይ ላይ.. ገነቴ ኢየሱስ ነው እዚሁ ምድር ላይ.. አልጠብቅም ሌላ እስክሄድ ሰማይ ላይ" አውነት ነው! መጽሐፍ መዳን በመጨረሻው ቀን ነው አይልም:: ይልቅ "በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው" ተብሎ ተጽፏል (2ቆሮ 6:2)። ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ያድናል። ልጁ ያለው ሕይወት አለው። የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። እንኳን የዘላለም ሕይወት፤ ፍርድ እንኳን የተፈረደው አሁን ነው። የመጨረሻው ቀን ፍርዱ የሚፈጸምበት ቀን ብቻ ነው። ቃሉ እንደሚናገረው "በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል" ነውና (ዮሐ 3:18)። ነገር ግን የፍጻሜው ቀን እስኪደርስ ድረስ ሰው በኢየሱስ ስም በማመን ከፍርድ ማምለጥ ይችላል። ስለዚህ፤ ያላመነ አምኖ ይዳን:: በስሙ ያመነ መዳኑን አረጋግጦ በጌታ አርፎ ይቀመጥ። ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ድንቅነሽ አትወክለኝም! ገና ርዕሱን አንብበህ ሳትጨርስ “ድንቅነሽ ማን ናት?” ብለህ የጠየከኝ ልጅ ቆይ ተረጋጋና ቀስ ብለህ አንብብ። ከ3 ደቂቃ የማይበልጥ ነገር ነው የፖስተኩት (ምን የዘመኑ ሰዎች የማንበብ ትዕግስት እንደሌላቸው የማላውቅ መሰለህ? አንተን ግን አያካትትም)። በል ቀጥል! በ1974 ዓ.ም (እንደ ፈረንጆቹ) ከአፋር ምድር ተቆፍራ ተገኝታለች። ከ3.2 ሚሊዮን ዓመት በፊት የነበረች ኮረዳ ነች አሉ። ገና በ12 አመቷ ነበር የሞተችውም ተብሎአል። እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ የሞቷ ምክንያት ያልታወቀ ቢሆንም ኢቢሲ ትናንት ባወጣው ዘገባ መሠረት ከሆነ ሴቲቱ ከዛፍ ላይ ወድቃ ነበር የሞተችው። የሆነ ሆኖ፤ በቁፋሮ የተገኙት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአጥንት ቁርጥራጮችዋ ተሰብስበው ነው ከታች በምስሉ የሚትመለከቷትን ሉሲ ወይም ድንቅነሽ የተባለችውን ሴት የሰጡን። ለነገሩ ፈረንጆች አውስትራሎፕትኩስ (Australopithecus) ብለው ነው ስም ያወጡላት። እርሱ ራሱ ድንቅ ስም ነው (ትርጓሜውን በኋላ እነግርሃለሁ)። ይህች ሴት የዋዛ አይደለችም፤ ውጭ ሀገር ድረስ ሄዳ ነበር የመጣችው። እንደውም ስድስት አመት ሙሉ በአሜሪካ ምድር ስትዞር ቆይታ ነበር “የሉሲ ለጋሲ” የተባለ ኤግዝቢሽን እየተዘጋጀላት። ምን ይሄ ብቻ፤ ወደ ሀገሯ ከተመለሰችም በኋላ ካልተሳሳትኩ እንደውም ባለፈው አመት የሰላም አምባሳደር ሆና አብዛኛውን የሀገራችንን ክፍል ተዘዋውራ ጎብኝታለች (ነው ወይስ ተጎብኝታለች? ብቻ ዞራለች)። እውነትም ድንቅነሽ! እንደ ስሟ፤ ድንቅ ነው ሥራዋ! እንደውም አጽሟ ለሰላም አምባሳደርነት ተሰይሞ ሲዞር የነበረ ጊዜ፤ ያን ሰሞን ሉሲ ለሀገሯ ሰላም ስትታገል የተዋደቀች ሰማዕት ሁሉ መስላኝ ነበር (ለነገሩ መንግስትም ልፋ ቢለው ነው እንጂ ሽማግሌውን፣ ፓስተሩን፣ ሼኩን እና ሊቀ ጳጳሱ ያልሰማ ህዝብ ሉሲን ሊሰማ ነው? እኔ እንጃ!)። አልሰማህም እንዴ? ባለፈው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት ክቡር አቶ ተመስገን በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ ለማድረስ በሄዱበት ወቅት (ለበጎ ተግባራቸው ትልቅ አድናቆት አለኝ) ንግግር ሲያደርጉ “ሉሲ ከዚሁ ከአፋር ነበር የተገኘችው፤ እኛ ሁላችንም የሉሲ ልጆች ነን፤ እናም ወደ ጥንት ምድራችን በመምጣታችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል (ንግግራቸውን ቃል በቃል አላሰፈርኩትም)። ፕሬዝዳንቱ የተገኙት ታላቋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በደንብ ከተስፋፋችበት ምናልባትም ወደ ሀገራችን ስትገባ አንድ ብላ እግሯን ካሳረፈችበት አካባቢ እንደመሆኑና ቤተ ክርስቲያኒቱም አስተምህሮቷ ከሉሲ ጋር የሚስማማ ስላልሆነ፤ ደግሞም ክቡር ፕሬዝዳንቱ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ ናቸው ብዬ ስላሰብኩም ነው መሰለኝ ንግግራቸውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት! እግዚኦ ማርነ ክርስቶስ! እሱን እንኳን ተውት ቦሎትካ ነው። ቦሎትካ ፎርሙላም የለው፤ ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያስገኝልህን ነው የምትናገረው፤ የምትተገብረውም። ምን ባለፈው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኖርቬይ ሲሸለሙ የሽልማት ኮሚቴ ሰብሳብዋ ተነስታ “የሰው ልጅ መነሻ ኢትዮጵያ ናት፤ ከዚህ መነሻነት ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን” ብላ ስትናገር ከተቀመጥክበት ተነስተህ አላጨበጨብክም እንዴ? እኔም በጣም ደስ ነበር ያለኝ። ግን ለምን ነበር ደስ ያለኝ? ያው ቦሎትካ ነዋ! ለማንኛውም፤ የአውስትራሎፕትከስን የስሟን ትርጓሜ ነግረህ ልሂድ። ቃሉ ከሁለት ቋንቋዎች የተውጣጣ ነው፡ ከላቲኑ አውስትራሊስ (Australis) እና ከግሪኩ ፕተኮስ (Pithekos)። የመጀመሪያው “ደቡባዊ” የሚል ትርጓሜ ያለው ሲሆን የኋለኛው ደግሞ “ጦጣ” የሚል ትርጉም ይኖረዋል። አንድ ላይ እንግዲህ “ደቡባዊቷ ጦጣ” ማለት ነው (ምን አልከኝ? ለካ ለዚያ ነዋ ከዛፍ ወድቃ የሞተችው” ነበር ያልከው? እኮ!)። በሩጫ የልጆቻችሁን ስም “ሉሲ” ብላችሁ የሰየማችሁ ሁላ እንግዲህ ምን ትሆኑ! በነገራችን ላይ ለአርክዮሎጂ ሳይንስቶች ትልቅ ክብር አለኝ። የእኔ ተቃውሞ ሉሲ ለምን ተገኘች ሳይሆን ሉሲ ለምን የሰው ልጅ መገኛ ተባለች ነው። አውቃለሁ፤ ይህች ሴት ስሟ ዝነኛ እንደመሆኑ መጠን ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ሲሳይ ሆና እያገለገለች የምትገኝ ስለሆነች ስለ እርሷ ክፉ እንዲወራ ብዙም አይፈለግም። የገንዘብ ምንጭ ናታ ለዛውም የዶላር! ባትደግፋትም እንኳን በአደባባይ ልትቃወማት አይገባህም፤ ዝም ማለት አለብህ ብለው የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው። እኔም “ዝም በል!” ከተባልኩ ዝም እላለሁ፤ ግድ የለም። አንድ ጊዜ ብቻ ይህችን ቃል ተናግሬ ዝም ልበል፦ እኔ ክርስቲያን ነኝ። እግዚአብሔር በአምሳያው እንደፈጠረኝ የሰውም መጀመሪያ አዳም እና ሄዋን እንደሆኑ፤ ሰው ከተፈጠረም ገና 8ሺህ ዓመት ገደማ ብቻ እንደሆነ በሙሉ ልቤ አምናለሁ። ይህ እምነት በሌለበት ክርስትና የለም! ባጭሩ፤ ድንቅነሽ አትወክለኝም ለማለት ፈልጌ ነው። በቃ ሄጃለሁ፤ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን!
Show all...
የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ወደ ምህረት ቀን ተቀይሯል ወዳጆች እግዚአብሔር የሚበቀልበት ቀን የነበረው አምላክ ሲሆን ያም ቀን የሰውን ዘር በሙሉ ኃጢአት በልጁ ላይ በማድረግ የተበቀለበት ቀን ነበር። ስለዚህ አሁን ለእኛ የምህረት ቀን እንጂ የበቀል ቀን የለውም። "የበቀል ቀን በልቤ አለ፤ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአል። ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤ የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤ የገዛ ቊጣዬም አጸናኝ፤" (ኢሳይያስ 63:4 - 5 NASV) "በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም። በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው።" (ኢሳይያስ 53:3 - 6 NASV) "እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን። ..... ገና ደካሞች ሳለን፣ ልክ ጊዜው ሲደርስ፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቶአልና። ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል። አሁን በደሙ ከጸደቅን፣ ይልቁንማ በእርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ቊጣ እንዴት አንድንም! የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን።" (ሮሜ 5:1 ፤ 6 - 11 NASV) "እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤" (2 ቆሮንቶስ 5:19 NASV) "እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ። በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።" (ዕብራውያን 4:14 - 16 NASV) Pastor Alex's
Show all...
(መዝ 103 ) ------------ 1 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። 2 ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤ 3 ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ 4 ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ 5 ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል። 6 እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል። 7 ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን። 8 እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። https://t.me/tetelestaye
Show all...
የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ና ዳግም ምዕጻት አንድ ናቸው ወይስ ልዩነት አላቸው?? በመጀመርያ ስለ መነጠቅ ማለት ምን ማለት ነው:-መነጠቅ ማለት በላቲን ቋንቋ"ራፔመር" ማለት ስሆን ትርጉሙ "ወደ ላይ መወሰድ፣ወደ ላይ መነሳት ማለትም ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ዞር ማለት ሳይሆን ከታችኛው ወደ ላይኛው ክፍል መንቀሳቀስ ማለት ነው የቃሉ ትርጓሜ።በመጽሐፍ ቅዱሳችን ስለ መነጠቅ ትርጉሙ፡- እየሱስ ከሰማይ ስመጣ በአየር ላይ እርሱን እየሱስን ለመቀበል ወደ ተወሰነ የሰማይ ክልል የሚደርግ የቅዱሳን /የቤተ ክርስቲያን/ በሕይወት የነበሩ የሚሞተው የማይሞተው ፣የሚበሰብሰው የማይበሰብሰው የትንሳኤ አካል ልብሰው ስነሱ ደግሞ በሕይወት ያሉ በቅጽበት አይን የከበሬውን አካል ለብሰው ወደ ላይ ከምድር ስበት በላይ የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያመለክት ነው ትርጉሙ፣ይህም ማለት መነጠቅ የሚሆነው የኃለኛው መለከት በሚነፋበት ጊዜ ነው ።1ኛቆሮ 15፡20-57 1ኛተሰ 4፡13-17 ስለ መነጠቅ ትርጉም ከቃል ፍቺው ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም አንጻር እንዲህ ካነሳን ፣ታዲያ የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምዕጻት ልዩነት አላቸውን? መልስ፡-ልዩነትማ አላቸው ፣አንድ አይደሉም ፣በጊዜ ሁነታ ፣በሚሆኑት ድርጊቶች፣በምመለከታቸው ሰዎች ይለያያሉ!!!! 🎸ልዩነቱ ምንድነው? 1ኛ ልዩነታቸው 👉በመነጠቅ ጊዜ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እየሱስ ለቅዱሳን ማለት ወደ ሰማይ ክልል ጉዞ ላደርጉት ብቻ ይታያል።1ኛተሰ 4፡17 " ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።" (1 ተሰ 4: 17) 👉በዳግም ምጽአት ጊዜ ለዓለም ሁሉ ይታያል፣ማንም አለማየት እርሱን አይችልም ፣ለሁሉም ይገልጻል። ማቴ 24፡30 ራዕይ 1፡7 " እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።" (ራእ 1: 7) 2ኛ ልዩነታቸው 👉በመነጠቅ ጊዜ ፡-ጌታችን እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ለመቀበል በሰማይ ክልል ላይ ይገለጣል፣መሬትን አይረግጥም ማለት በአየር ውስጥ ይገለጣል። 1ኛተሰ 4፡17 👉በጌታችን ዳግም ምዕጻት ጊዜ ፡-ወደ ምድር ይመጣል ራዕ 19፡11-19 ማቴ 24፡30 ሐዋ 1፡11 " ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።" (የሐዋ 1: 11) 3ኛ ልዩነታቸው 👉በመነጠቅ ጊዜ፡-ጌታቻን ክርስቶስ እየሱስ ቅዱሳን ለመውሰድ ይመጣል።ዮወ 14፡3 " ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።" (ዮሐ 14: 3) 👉በዳግም ምጽአት ጊዜ፡-ጌታችን ክርስቶስ እየሱስ ከቅዱሳን ጋር ይመጣል።ራዕይ 19፡14 ይሁዳ 14-15 " ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ፦ እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።" (ይሁዳ 1: 14-15) 4ኛ ልዩነታቸው 👉በመነጠቅ ጊዜ ፡-ጌታችን ክርስቶስ እየሱስ በቅዱሳን ልከበርና ልገሬም ይመጣል።2ኛተሰ 1፡9-10 👉በዳግም ምጽአት ጊዜ:-ጌታችን ክርስቶስ እየሱስ በምድር ነዎርዋችና በቅዱሳን ልከበር ይመጣል ።2ኛተሰ 1፡10 5ኛ ልዩነታቸው 👉በመነጠቅ ጊዜ፡-ጌታችን ክርስቶስ እየሱስ ለመዋጋት ሳይሆን ቅዱሳንን ለመውሰድ ነው የሚመጣው ። ራዕይ 19፡10 👉በዳግም ምጽአት ጊዜ :-ጌታችን ክርስቶስ እየሱስ ለመዋጋትና በጽድቅ ለመፍረድ ይመጣል ። 1ኛተሰ 4፡17-18 6ኛ ልዩነታቸው 👉የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ፡-ሐሰተኛው ክርስቶስ ሳይገለጥ በፊት ነው።2ኛተሰ 2፡3-8 👉የጌታችን ክርስቶስ እየሱስ ዳግም ምጽአት ጊዜ ፡-ሐሰተኛው ክርስቶስ ተገልጾ ከሰራ በኋላ ነው የጌታችን ከቅዱሳኑ ጋር መምጣቱ።2ኛተሰ 2፡3-8 7ኛ ልዩነታቸው 👉የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ፡-ከመከራ ዘመን በፊት ስሆን ። 👉የጌታችን ክርስቶስ እየሱስ ዳግም ምጽአት ደግሞ ፡-የመከራ ዘመን እንደ አለቀ ነው ። 🎸የቤተ ክርስቲያን መነጠቅና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምጽአት አንድ አይደሉም ፣ልዩነት ያላቸው ትልቅ ትኩረት የተሰጣቸው ክንውኖች ናቸው ። ልዩነቱ ከላይ እንዳለው ነው።የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቅሶች ማየትና ማጥናት አስፈላጊ ነው። " የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።" (2 ቆሮ 13: 14) https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ሁለቱ ኪዳኖች! * አዲስ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን አንፃር! " በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥" (ወደ ዕብራውያን 13:20) > ብሉይ ኪዳን ሲመረቅ ተዋዋዮቹ እግዚአብሔር እና ከግብፅ የወጣው የእስራኤል ሕዝብ ነበሩ። እነርሱ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ ለማድረግ ተስማምተው፣ በምላሹም እግዚአብሔር ሊባርካቸው/በሕይወት ሊኖሩ በሚለው መርዕ ኪዳኑ ተመሰረተ(ዘፅ፡19÷8)። > በምርቃቱ ወቅት ደም ውሉ በሆነው በህጉና በህዝቡ ላይ ተርጨቶ ነበር። " ስለዚህም ፊተኛው ኪዳን እንኳ ያለ ደም አልተመረቀም።" (ወደ ዕብራውያን 9:18) > ይህ ደም እስራኤላውያኑ ሕጉን ባይጠብቁ ምን እንደሚጠብቃቸው የሚናገር ነበር። ሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው በውሉ ተስማሙ። # ውጤቱ ምን ሆነ? > ዘፀአት 32ን ስናነብ ገና ውሉ ተፅፎ ሳይጠናቀቅ አፈረሱት። እናም ገና ከጅምሩ ደማቸው በሰይፍ መፍሰስ ጀመረ። 2000 ዓመታት ሙሉ ሕጉን ሲተላለፉ ከረሙ። መጨረሻቸው የቁጣ ሰይፍ ሆነ(ዘዳ፡28÷58-68፣ ኢሳ፡1÷20)። በውሉ ባለመፅናታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ቸል አላቸው (ዕብ.8:9)። # ነገሩ በዚህ አበቃን? > በፍፁም! ሌላ ኪዳን እግዚአብሔር አዘጋጀ። ይህም ኪዳን በደም የተመረቀ ነው። ነገር ግን እንደ ብሉዩ፣ ሰው ካልጠበቀው ሞት እንደሚጠብቀው የሚናገር ደም ሳይሆን፣ በኪዳኑ ውስጥ ያሉት አካላት ሁሉ የኃጢአታቸው ዋጋ እንደተከፈለ የሚናገር የክቡር የክርስቶስ ደም ነው። ጌታ እንዲህ አለ "ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።" (የሉቃስ ወንጌል 22:20) > ከዚህ ደም የተነሳ እግዚአብሔር በአዲሱ ኪዳን፣ "ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም" (ዕብ.10:17) አለ። ኃጢአቱ ታስቦ የቁጣው ሰይፍ የሚበላው ማንም የለም። ምክንያቱ ሰይፉ አንዴ በእረኛው ላይ አርፎአል(ዘካ፡፡13÷7)። > እናም ይኸኛው ኪዳን ዋስትናው የኢየሱስ ደሞ እንጂ የሰዎቹ ሕግን መፈፀም ባለመሆኑ፣ እንደቀደመው ኪዳን "ብሉይ/ያረጀ/ፊተኛው …" ሊባል አይችልም። እንደውም መቼም እንደማይፈርስ እና በሌላ እንደማይተካ መፅሐፉ ሲናገር "የዘላለም ኪዳን" ይለዋል። " በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥" (ወደ ዕብራውያን 13:20) # የዚህ አዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንዴት ብፁሃን ናቸው! " እርሱም … ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:6) https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ኢየሱስ ወደ ሲኦል ወርዷልን? * > ብዙ ጊዜ የሐዋ፡2÷27 ጥቅስ ይነሳና ጌታችን በሞተ ጊዜ ወደ ሲኦል እንደኤደ ይነገራል። በዚህም ምክንያት በምድር ሳያምኑ፣ ሞተው አሁን በሲኦል ያሉ ነፍሳት እድል እንዳላቸው ይነገራል። ጥቅሱ እንዲህ ይላል " ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም።" (የሐዋርያት ሥራ 2:27) > ከሁሉም በፊት የሲኦል ስብከትን ለሚያምኑ ሰዎች የተወሰኑ ጥያቄዎችን እናንሳ 1ኛ፡ መፅሐፍ ቅዱስ፣ ለሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያም በኋላ ፍርድ እንደተመደበ ይነግረናል(ዕብ፡8÷27)። ሰው ከሞተ በኋላ ፍርድ የሚጠብቀው ከሆነ፣ የሲኦል ስብከት የሚባለው ነገር ከዚህ ጋር አይጋጭምን? 2ኛ፡ ጌታችን በተናገረው፣ በሉቃ፡16÷19-31 ምሳሌ መሰረት፣ በአብርሃም እቅፍ በተባለው ስፍራ እና በሲኦል መካከል በፍፁም ግንኙነት እንደሌለ፣ ማንም ከሲኦል ሆኖ ለምህረት ቢጮኸ እንኳ እንደማይሰማ ተፅፏል። ታዲያ በሲኦል ስብከት አለ ምን ማለት ነው? 3ኛ፡ በዛው በሉቃ፡16 ምሳሌ ላይ፣ የሞተው ባለጠጋ ስለወንድሞቹ መዳን ተጨንቆ ሲጠይቅ የተመለሰለት ምንድነው? በሕይወት ሳሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ አይደለምን(16÷29)? 4ኛ፡ በቃሉ ውስጥ፣ "በሲኦል ተሰብኮላቸው ዳኑ" ተብሎ የተፃፈው የቱ ጋር ነው? 5ኛ፡ ለምን ተብሎ፣ ያ ለእሳት ባህር ያልዳኑትን ነፍሳት ማቆያ ስፍራ ኢየሱስ ይወርዳል? የኃጢአት ዋጋ እንደሆነ ተከፍሎ ያለቀው መስቀል ላይ አይደለምን? > እጅግ ብዙ ጥያቄ ማንሳት ብንችልም፣ በስህተት ወደ ሚጠቀሰው ጥቅስ እንመለስ። > ጥቅሱ ከመዝ፡15/16፥10 ላይ የተጠቀሰ ሲሆን የእንግሊዘኛው ትርጉሞች(ASV, JND …) እንዲህ ያስቀምጡታል "For thou wilt not leave my soul to Sheol, neither wilt thou allow thy Holy One to see corruption." (Ps. 16:10) > ትክክለኛው የዕብራይስጡ ቅፅላ በአማርኛው መፅሐፍ ቅዱስ እንደተፃፈው "በ/in" ሳይሆን "ለ/to/unto" ነው። ስለዚህ "ለሲኦል" እንጂ "በሲኦል" የሚል ቃል የለውም። በሐዋርያት ስራም እንደ ዋናው ጥቅስ መነበብ ያለበት "ለ" ተብሎ መሆን አለበት(ለበለጠ ማብራሪያ W. Kelly ፁሁፍን ማንበብ ይቻላል)። > ከዚህ ውጭ በሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቅፅላው "ለ" መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል 1ኛ፡ ጌታችን በስጋ ሊሞት ሳለ ነፍሱን የሰጠው ለአባቱ ነው(ሉቃ፡23÷46)። 2ኛ፡ ከሞተም በኋላ ነፍሱ በገነት እንጂ በሲኦል አልነበረችም(ሉቃ፡23÷43)። 3ኛ፡ የትኛውም አማኝ ሲያንቀላፋ ነፍሱ ወደ ጌታ እንደምትሄድ በተደጋጋሚ ተፅፏል(የሐዋ፡7÷59፣ ፊል፡1÷23፣ 1ተሰ፡4÷14 …)። ይህ ማለት ማንም አማኝ ወደ ሲኦል በጭራሽ እንደማይኤድ ያሳያል። እናም በምድር ላልዳኑት የምንሰብከው እኛ፣ በሲኦል ስብከት አለ ከተባለ፣ ለምን ወደዚያ እንደምንላክ ቃሉ አይናገርም? > ኢየሱስ የሰበከው በምድር በሕይወት ላሉት እንደሆነ ሁሉ እኛም ያንን እንፈፅማለን። ኢየሱስ በሲኦል እንዳልሰበከ፣ አማኝም ፈፅሞ በዚያ አይሰብክም። # በጠቅላላው ኢየሱስ በመዝሙረኛው አፍ የተናገረው፣ የራሱን ነፍስ በተመለከተ "ስለመተውና ስላለመተው" እንጂ "የሲኦል ስብከት" የሚል ቃል ጥቅሱ ውስጥ አለመኖሩን ማስተዋል ይገባል፣ የስህተት አስተማሪዎች ሲኦል ከመውረድ አልፈው፣ በዚያ ስብከት፣ ቀጥሎ የሰዎችንም መዳን ይናገራሉ። > ኦው፣ እግዚአብሔርም በመስቀል ያከበረውን ኢየሱስን ፈፅሞ "ለሲኦል" እንደማይተወው የታመነ እውነት ነው። https://t.me/tetelestaye
Show all...
*የሕይወት እንጀራ!* ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ የሆነው በምን ምክንያትና መቼ ነው? > ይህን ጥያቄ ቆም ብዬ ሳሰላስለው በበረሃ ላይ በጥም ያለ ሰው ቀዝቀዝ ያለ ውሃ ሲያገኝ እንደሚረካ ነፍሴም እርክት ትላለች፡፡ > እስቲ ጥቂት አስቡት፡- ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ የሆነው በምን ምክንያት እና መቼ ነው? በመስቀል ስለሞተ ነውን? ባይሞት ኖሮስ? #አዎን ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ የሆነው ስለሞተልን ሳይሆን በማንነቱ ነው፡፡ መጽሐፉ የሚለው የሕይወት እንጀራ ከሰማይ መጣ ነው (ዮሐ.6፡32-33)፡፡ እርሱ በራሱ ሕይወት ነው (ዮሐ. 11፡25፣ 14፡6)፤ 1ዮሐ.5፡20 እንዲህ ይላል “የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።” 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 > እናም ጌታ የሕይወት እንጀራ ነው ስንል በማንነቱ እንጂ ስለሞተልን አይደለም፡፡ እርሱ ከመስቀሉ የተወሰኑ ጊዜያት በፊት ወይም ከመስቀሉ በኋላ ሳይሆን ከሰማይ ሲወርድም የሕይወት እንጀራ ሆኖ ነው፡፡ #ታዲያ ወንጌል ሲሰበክ የሕይወት እንጀራነቱና ሞቱ አብረው የሚጠቀሱት ምን አገናኝቷቸው ነው? > አዎን ጌታ ኢየሱስ በማንነቱ እና ገና ከሰማይ ሲወርድ የሕይወት እንጀራ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ያንን መመገብ የምንችለው ወይም የሕይወት እንጀራ ወደ እኛ መድረስ የሚችለው በሞቱ በኩል ነው፡፡ > ይህ ማለት ጌታ ሥጋና ደሙ ካልተለያየ ወይም ካልሞተልን እና እኛ ደግሞ የተለያዩትን ሥጋና ደሙን ካልበላን ማለትም ልክ ምግብ ሲበላ ሰውነት ውስጥ እንደሚዋሃድ፣ እኛም የእርሱን ሞት ከልባችን ካልተቀበልን፣ ውስጣችን ካልተዋሃደ የሕይወት እንጀራን መብላት አንችልም፡፡ #የሕይወት እንጀራ ስንቴ የምንመገበው ነው? > ጌታ ኢየሱስ ለነፍስ የሕይወት ዘመን ምግብ ነው፡፡ በሞቱ ካመንበት ሰዓት አንስቶ ለዘላለም ነፍሳችን እርሱን መመገብ አታቆምም፡፡ ምክንያቱም ያገኘነው ሕይወት ምግቡ ኢየሱስ ነው!!! “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።” — ዮሐንስ 6፥35 https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ኢየሱስ፦ የዳዊት ጌታ፣ የዳዊት ልጅ፣ የዳዊት ስር፣ የዳዊት ዘር! * > መፅሐፍ ቅዱስ ከዳዊት ጋር አያይዞ ስለኢየሱስ እነዚያን ቃላት ይናገራል (ማር.12:35-37፣ ራዕ፡22÷16)። ኢየሱስ የዳዊት ልጅ፣ በዛኑ ቅፅበት ደግሞ ጌታው፣ የዳዊት ዘር፣ በዛው ቅፀበት የዳዊት ስር ሆኖ ቀርቦልናል። > ይህ ለፈሪሳውያን ግራ ያጋባ እና መልስ ያሳጣቸው እውነት ነው። በተፈጥሮው ስርሃት መቼም ቢሆን ልጅ፣ ለቀደመው አባቱ ጌታ ሊሆን አይችልም፤ የቀደመውም አባት የሚመጣውን የልጅ ልጁን፣ በአካል የማያውቀውን፣ ጌታዬ እያለ ሊጠራው ሆነ ሊገዛለት አይችልም። > ልክ እንደዚሁ ሰው ከቀደሙት አባቶቼ ዘር ተገኝቻለው ብሎ ያቆማል እንጂ እነርሱ ከእኔ ተገኝተዋል ሊል አይችልም። > ንጉስ ሰለሞን የዳዊት ልጅ እንጂ ጌታው፣ ዘሩ እንጂ ስሩ አይደለም። ኢየሱስ ግን የዳዊት ልጅ ብቻ ሳይሆን ጌታው፣ ዘሩ ብቻ ሳይሆን ስሩ ነኝ ሊል ተችሎታል። በፍፁም ሰውነቱ፣ እኛን በትክክል እንደመሆኑ፣ የዳዊት ልጅ ሲሆን፣ እኛን የሆነው ግን ራሱ ያህዌ ነውና ዳዊት በስጋ ሳይገለጥ ተመልክቶት "ጌታዬ" ሲል ተገዝቶለታል፣ ይገዛለታልም። > ስጋን ሲለብስ ከዳዊት ቤት ዘር የተቆጠረለት፣ ስለትውልዱ መፅሐፍት የዘገቡለት እርሱ፣ ዳዊትን ያስገኘው፣ የዳዊት ስር፣ የሕይወት ምንጭ ያህዌ ነው። ዳዊትን አስገኝቶ፣ እርሱ ራሱ በስጋ ከዳዊት መጣ! > ይህ ማለት አብሮን ያለው፣ ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ የሆነው ኢየሱስ፣ ራሱ ያህዌ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው። ቃል ስጋ ሆነ፣ አማኑኤል፣ እግዚአብሔር በስጋ ተገለጠ የመሳሰሉት ጥቅሶች የጌታን ክብር አንፀባራቂዎች ናቸው። በእርግጥም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው! " እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" (የማቴዎስ ወንጌል 1:23) https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው መቼ ነው? * ከዘላለም ወይስ ሥጋ ሲለብስ! > የመጠበቂያ ግንብ መስራች ሩሴል ጨምሮ ሌሎች የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ የሚሰራባቸው ሰዎች፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ከማርያም ሲወለድ ነው፣ የእኛና የእርሱ ልጅነት አንድ ነው ወዘተ ይላሉ። # እውነት ይህ አነጋገር ከቃሉ ወይስ ከሰይጣን የመነጨ ነው? አጭር መልስ 1ኛ፡ እነዚህ ሰዎች ልጅነት ሲባል የሚያውቁት በመወለድ ወይም በመፈጠር ብቻ ነው። መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምሳሌ የነጎድጓድ ወይም የዲያብሎስ አሊያ የፅዮን ልጆች የሚል እናገኛለን (ማር፡3÷17፣ ሰቆ.ኤር 4÷2)። ይህ ልጅነት የባህሪ ወይም የጠባይ ነው። 2ኛ፡ የክርስቶስ ልጅነት ምን ያሳያል የሚል ካለ፣ የአብ አባትነት ምን ያሳያል ብዬ እጠይቀዋለሁ። መልሱ መለኮትነትን መሆኑ ግልፅ ነው! እንደው ተጨማሪ እንዲሆን ጥቅሶችን ላስቀምጥ (ማቴ፡28÷20፣ ዮሐ፡5÷17፣23፣ 8÷31፣ 10÷31፣ ዮሐ፡17÷1-5፣ 24፣ ዕብ፡1÷2፣ 1÷8) ወዘተ። > ታዲያ የእግዚአብሔር ልጅነቱ መለኮትነቱን ካሳየ፣ የሚያመለክተው በጠባይ ወይም በባህሪ ወይም በማንነት ከአብ ጋር አንድ መሆንን ነው። መለኮትነት የሚወለድ፣ በሆነ ሰዓት የሚገኝ ወዘተ አይደለም። 3ኛ፡ ክርስቶስ ልጅ የሆነው መቼ ነው ለሚለኝም አብ፣ አብ የሆነው መቼ ነው ስል መልሼ እጠይቀዋለሁ። ከዘላለም መሆኑ ግልፅ ነው! አብ አባትነቱ ከዘላለም ከሆነ ወልድም ወልድነቱ (ልጅነቱ) ከዘላለም ነው። ያለ ልጅ አባት የሚባል ነገር የለም! ይህ ማለት የክርስቶስ ልጅነት የባህሪ መሆኑን ሌላ ማሳያ ነው። > ነገር ግን ለዚህም ተጨማሪ ጥቅስ ላስቀምጥ፤ ኢየሱስ በብሉይ ልጅነቱ ተጠርቷል (ምሳ፡30÷1-4)፣ ዓለም የተፈጠረው በወልድ ነው (ዕብ፡1÷2)፤ አብ የላከው ልጁን እንጂ ገና ልጅ የሚሆንን አይደለም (ዮሐ፡3÷16፣ 5÷30፣ 10÷36፣ 16÷22…)። የጌታ የልጅነት ክብር ዘላለማዊ ነው (ዮሐ፡17÷1-26)። ማቴ፡28÷20 አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ብሎ የጠራው አንድም ስም አድርጎ ነው። ያ ማለት ማለት ነጣጥለህ አብ ከዚህ በኋላ፣ ወልድ እንደዚያ ማለት አትችልም። 4ኛ፡ ታዲያ ሉቃ፡1÷35 ላይ ለምን ጌታ "የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ተባለ? ይሄንንም በጥያቄ ልመልስ፤ ታዲያ ከዘላለም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ሥጋ ሲለብስ ምን ሊባል ነው? የእግዚአብሔር ልጅ ነዋ። የሚለወጥ ነገር የለም፣ ሲወለድም ሌላ ማንም ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው። > ሲወለድም፣ ምድር ላይ ሲመላለስም፣ መስቀልም ላይ እያለ፣ በሥጋ ሲሞትም፣ ሲነሳም የሚለወጥ ነገር የለም (ሮሜ፡1÷3)። መለኮትነት የሚለወጥ ነገር አይደለም። 5ኛ፡ እግዚአብሔር ለምን ወለድኩ አለ? (መዝ፡2÷7)። ለዚህም ጥያቄ ላንሳ፣ ከወለድኩ በፊት ግን ምን እንደሚቀድም አይተሃል? "አንተ ልጄ ነህ" ከፊት አለ። ለሰው ወለድኩ ስለዚህ ልጄ ነህ ሲባል፣ ለጌታ ግን ልጄ ነህ ከዛህ ዉለድኩ ነው። ምክንያቱም ልጅነቱ ቀድሞ ከዘላለም የነበረ ነው። > ስለዚህ ወለድኩ የሚያሳየው እግዚአብሔር ልጁ ሥጋ እንዲለብስ ማድረጉን ነው(ዕብ፡10÷5)!!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
*የክርስቶስ ልጅነትና የእኛ ልጅነት ይለያያልን?* # የክርስቶስ ልጅነትና የእኛ ልጅነት አንድ ነው የሚሉ ሰዎች ወይም ትምህርት ስሰማ የመጀመሪያ የምጠይቀው ጥያቄ፣ የክርስቶስ ልጅነት የሚያመለክተው ምኑን ነው? አምላክነቱን ወይስ ሰውነቱን? > መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ የክርስቶስ ልጅነት መለኮትነቱን የሚያሳይ መሆኑን በማያሻማ ቃል ነግሮናል። ማቴ፡28÷19 ላይ "በአብ በወልድ(በልጅ) በመንፈስ ቅዱስ ስም(ስሞች እንደማይል ልብ እንበል" የሚለው ክፍል የክርስቶስ ልጅነት መለኮትነቱን የሚያሳይ እንደሆነ ያስረዳል። > ከዚህ በተጨማሪ የክርስቶስ ልጅነት ከፈጣሪነቱ ጋር ተያይዞ ቆላ፡1÷13-17፣ እንዲሁም ዕብ፡1÷2 ጋር ተጠቅስዋል። ዮሐ፡9÷35-38 ላይ በልጅነቱ ምክንያት አምልኮ ተቀብሏል። ዮሐ፡5÷17 እና 17÷5 ላይ በልጅነቱ ምክንያቱ ከአብ እኩል የሚሰራ፣ ክብሩም ከአባቱ ጋር ሆኖ ተገልጧል። > ዕብ፡1÷8 ላይ ደግሞ ከአምላክነቱ ጋር ተያይዞ ተነግሯል። በዮሐንስ ወንጌል ከም፡1 ጀምሮ ደግሞ የክርስቶስ ልጅነት ከዘላለም እንደሆነ በዝርዝር ተቀምጧል። አብን እና ወልድን መለየት አይቻልም። ለአብ የምትለው ወልድን፣ ለወልድ የምትለው አብን ገላጭ ነው (ዮሐ፡10÷30፣ 14÷10፣ 17÷10 …)። # ታዲያ የኢየሱስ ልጅነት መለኮትነቱን ካሳየ እንዴት ሆኖ ነው ከእኛ ልጅነት ጋር አንድ የሚሆነው? የማነው ደፋር "አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ" በሚለው ስም ውስጥ "የእኔ ልጅነት እንደ ክርስቶስ ነው" በማለት ስሙን በወልድ ፋንታ ወይም አብሮ ማቴ:28÷19 ላይ የሚከት? > ጥቂት ነጥቦችን ላንሳ 1ኛ፡ ስለ ኢየሱስ ልጅነት ስንናገር የባህሪ ሲሆን የእኛ ደግም ዳግም የመወለድ ጉዳይ ነው (ማቴ፡28÷19ን ከዮሐ፡1÷13 ጋር አነፃፅር)። 2ኛ፡ ኢየሱስ የባህሪ ልጅ በመሆኑ "አንድያ" ተብሏል። ምክንያቱም ማንም መለኮት መሆን አይችልም። እኛ ግን ብዙዎች ስንሆን፣ ልጅነታችንም የሚያሳየው እግዚአብሔር ምን ያህል እንዳቀረበን፣ እንዳከበረን፣ እንደወደደን ነው (ዮሐ፡1÷18 ከዮሐ፡1÷12)። 3ኛ፡ የኢየሱስ ልጅነት በሆነ ጊዜ የሚጀምር አይደለም፤ የእኛ ግን ዳግም ስንወለድ የሚፈጠር ነው(ዮሐ፡1÷18፣ 3÷16 … ከዮሐ፡1÷12-13)። #ሰዎች ለምን የክርስቶስ ልጅነትን ከእኛ ጋር አንድ አድርገው ይናገራሉ? > ሁለት ምክንያት ይታየኛል 1ኛ፡ ያለበቂ እውቀት የሚናገሩ ምስኪን አማኞች መፅሐፍ ቅዱስ ያስቀመጠው የልጅነት ትምህርት ፈፅሞ አልገባቸውም። 2ኛ፡ የሄደኑ እባብ ሰዎችን "እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ" በሚለው የሐሰት ስብከቱ የሰበሰባቸው ልጆቹ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን፣ ሰይጣን ደግሞ የክርስቶስን ክብር ለመንካት የሚያደርጉት ሙከራ ነው። https://t.me/tetelestaye
Show all...
* መንግስተ ሰማይና ቤተክርስቲያን አንድ ናቸው ወይስ ይለያያሉ? * #አጭር ንፅፅር 1ኛ፡ መንግስተ ሰማብ (ከሰማይ የሆነው መንግስት) በብሉይ ዘመን በስፋት የሚታወቅና በእውነተኛ አይሁዶች ዘንድ የሚጠበቅ ሲሆን ቤ/ን ግን በብሉይ አትታወቅም (ለምሳሌ፦ ትንቢተ ዳንኤል ም፡2÷44-46)። 2ኛ፡ መንግስተ ሰማይ የመጥምቁ ዮሐንስና የጌታ ኢየሱስ የመጀመሪያ የስብከት ርዕስ የነበረች ሲሆን(ከማቴ፡1-12)፣ አይሁድ ግን የመንግስቱን ንጉስ ባለመቀበላቸው ጌታ ከማቴ፡16 በኋላ ወደ ቤ/ን ዘወር ብሏል። 3ኛ፡ መንግስተ ሰማይ መላ ነገሯ ከአይሁድ ጋር የተገናኘ ሲሆን(ለምሳሌ፦ የመንግስቱ መቀመጫ ኢየሩሳሌም ነው ኢሳ፡1÷26-27፣ ም፡2)፣ ቤ/ን ግን ከአይሁድና ከአህዛብ አንድ አዲስ ሰው የተፈጠረባት ነች። 4ኛ፡ መንግስተ ሰማይ ዛሬ ንጉሱ ተቀባይነት በማጣቱ በምስጢር ወይም በስውር ያለች ሲሆን(ማቴ፡13)፣ ቤ/ን ግን ግልፅ ነች። 5ኛ፡ መንግስተ ሰማይ ሰይጣን የዘራቸው እንክርዳዶች እስከመጨረሻው ሲቆዩባት፣ ቤ/ን ግን የበደለውን ከመካከሏ ታስወግዳለች(ማቴ፡13÷29ን ከ1ኛቆሮ፡5 ጋር አነፃፅሩት)። 6ኛ፡ መንግስተ ሰማይ በምስጢርነቷ እስከ ዓለም ፍፃሜ ማለትም እስከ ሰባቱ የመከራ ዘማን መጨረሻ ስትዘልቅ፣ ቤ/ን ግን ከመከራው ዘመን በፊት ትነጠቃለች (ማቴ፡13 እና 1ኛተሰ፡4÷13-18 አነፃፅሩ)። 7ኛ፡ ይህች መንግስት ይፋ የምትሆነው ኢየሱስ ከቤ/ን እና ከብሉይ አማኞች ጋር ለመንገስ ሲገለጥ ነው፡ ራዕ፡20 የሺው ዓመት መንግስት ይለዋል። 8ኛ፡ መንግስተ ሰማይ መንግስት ስትሆት፣ ቤ/ን ግን ሙሽራ ነች። https://t.me/tetelestaye
Show all...