cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ

ይሄ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊሱን) በተመለከተ የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል ነው አላህ መልካም መገጠሙን ይወፍቀን ስህተት ስታዩ በውስጥ መጥታችሁ አስተያየት ስጡን እናንተንም አላህ በአዱኒያም በአኼራም መልካሙን ይወፍቃችሁና !

Show more
Advertising posts
408
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይሄ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊሱን) በተመለከተ የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል ነው አላህ መልካም መገጠሙን ይወፍቀን ስህተት ስታዩ በውስጥ መጥታችሁ አስተያየት ስጡን እናንተንም አላህ በአዱኒያም በአኼራም መልካሙን ይወፍቃችሁና ! https://t.me/YewereiluweredaandketemaMejilis
Show all...
የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ

ይሄ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊሱን) በተመለከተ የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል ነው አላህ መልካም መገጠሙን ይወፍቀን ስህተት ስታዩ በውስጥ መጥታችሁ አስተያየት ስጡን እናንተንም አላህ በአዱኒያም በአኼራም መልካሙን ይወፍቃችሁና !

ሰበር ዜና አልሀምዱ ሊላህ‼‼️ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ መጅሊስ ከፍተኛ ምክር ቤት የከተማውን የ02ቀበሌ  መጅሊስ አዋቀረ። ሃምሌ 07/11/2016 👉 ዛሬ ከፍተኛ የወረዳውና የከተማው መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ እንድሁም ፀሃፊውና ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮች እና አባሎች ባሉበት ተመርጧል ። 👉 ከፍተኛ የወረዳውና የከተማው መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ እንድሁም ፀሃፊውና ሌሎች አባሎች ባሉበት ተመርጧል በዚህም መሰረት መላ ጉባኤተኞችን አስመልምሎ 7 የስራ አመራሮችን በማስመረጥ እጅግ የተሳካ ስራ ሰርቷል። በዚህም መሰረት 1, ሙሀመድ እንድሪስ (ጉልማ) ፕሬዝዳንት 2, ኡመር ጌታነህ  ም/ፕሬዝዳንት 3, ጀማል እንድሮ  ዋና ፀሀፊ 4, ሙባረክ አደም  ህዝብ ግንኙነት  5, ሰይድ የሱፍ  አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ 6,  ሙሀመድ ጋሻው ሃጅና ዑምራህ 7 , ጀማል ይማም መስጅድና አዉቃፍ ዘርፍ ተጠሪ አድርጎ ማስመረጡ ታዉቋል። ሱመ አልሀምዱሊላህ!! ይቀጥላል 👉ለበለጠ መረጃ ወደ ፔጁ ጎራ ይበሉ 👇👇👇👇 👉የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ https://t.me/YewereiluweredaandketemaMejilis/2121
Show all...
ሰበር ዜና አልሀምዱ ሊላህ‼‼️ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ መጅሊስ ከፍተኛ ምክር ቤት የከተማውን የ01 ቀበሌ  መጅሊስ አዋቀረ። ሃምሌ 07/11/2016 👉 ዛሬ ከፍተኛ የወረዳውና የከተማው መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ እንድሁም ፀሃፊውና ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮች እና አባሎች ባሉበት ተመርጧል በዚህም መሰረት መላ ጉባኤተኞችን አስመልምሎ 7 የስራ አመራሮችን በማስመረጥ እጅግ የተሳካ ስራ ሰርቷል። በዚህም መሰረት 1, መህድ ሁሴን ፕሬዝዳንት 2, ሱለይማን ሙሀመድ   ም/ፕሬዝዳንት 3, አራጋው ሁሴን   ዋና ፀሀፊ 4, አብዱሰላም ሙሀመድ   ህዝብ ግንኙነት  5, አዳል ይማም  አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ 6,  ኑሩ አህመድ  ሃጅና ዑምራህ 7 , አህመድ አበበ መስጅድና አዉቃፍ ዘርፍ ተጠሪ አድርጎ ማስመረጡ ታዉቋል። ሱመ አልሀምዱሊላህ!! ይቀጥላል .... ለበለጠ መረጃ ወደ ፔጁ ጎራ ይበሉ 👇👇👇👇 👉የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ https://t.me/YewereiluweredaandketemaMejilis
Show all...
የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ

ይሄ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊሱን) በተመለከተ የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል ነው አላህ መልካም መገጠሙን ይወፍቀን ስህተት ስታዩ በውስጥ መጥታችሁ አስተያየት ስጡን እናንተንም አላህ በአዱኒያም በአኼራም መልካሙን ይወፍቃችሁና !

ኡስታዝ  ሳዳት  ከማል በእዉር ድንብር የሚጓዘዉ የለተሞ ቡድን የአብዱል ሀሚድ ለተሞ የቪዲዮ ጉዳይ የኢኽላስ ጉዳይ https://t.me/Menhaje_Selef/  
Show all...
ዐብዱል ሀሚድ አል-ለተሚ_93.mp326.76 MB
Photo unavailableShow in Telegram
🗓 በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም 🍂 የአዲስ አበባ እምብርት በሆነችው ሜክሲኮ ጀርመን ግቢ ተባረክ መስጅድ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እናንተን ይጠብቃል።  ተጋባዥ ዳዒዎች:  1⃣ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ 2⃣ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር 3⃣ ኡስታዝ ሳዳት ከማል ለሴቶችም በቂ እና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።  🚗 መኪና ይዘው ለሚመጡ በቂ መኪና ማቆሚያ አለ።  🗓 ቀን: ማክሰኞ ዙልቂዳህ 20 /45  ወይም ግንቦት 20/2016 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ☎️ ለበለጠ መረጃ  : +251936650001                                 : +251921543862                                 : +251941961928 አዘጋጅ: የሸይኽ  ጃማዕ እና ተባረክ መስጅድ ወጣቶች! ⚠️ ድንገት መምጣት ላልቻሉ በቴሌግራም የቀጥታ ስርጭት ለመከታተል: 👇👇                  t.me/nurmesjed መቅረት አይደልም ማርፈድ ያስቆጫል‼ t.me/Darutewhide
Show all...
ኢስላም ያለ አንድ ሰይፍ አውሮፓን እያጥለቀለቀ ነው ~ ኢስላም በአሁኑ ሰዓት በምእራቡ አለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው። ብሪታንያን እንደ ምሳሌ እንመልከት። መረጃዎቼን የወሰድኩት የኢስላም በሃገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት እንቅልፍ የነሳው ፀሐፊ “ለንደን 500 ቤ/ክርስቲያናትን ዘግታ 423 አዳዲስ መስጂዶችን ከፈተች” በሚል ርእስ ከፃፈው አርቲክል ሲሆን በዚህ ድረ ገፅ ታገኙታላችሁ። http://yournewswire.com/london-churches-mosques/ ኢስላም ብሪታንያን እየዋጣት ነው ይላል የፅሁፉ ጭብጥ። ይህንን ለማሳየትም የተለያዩ መረጃዎችን ዘርዝሯል። ሀሳቡ ሲሰበሰብ የሚከተለውን ይመስላል:- በሂያት ዩናይትድ ቤ/ክ በግብፃውያን ኮሚዩኒቲ ተገዝቶ መስጂድ ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ ቤ/ክ “መዲና መስጂድ” ተብሎ ተቀይሯል። ብሪክ ሌን መስጂድ ቀድሞ የሜተዲስት ቤ/ክ ነበር። ህንፃው ያለ ምክንያት አልተቀየረም። ህዝቡም እየተቀየረ ሆኖ እንጂ። አዎ የሰለምቴዎች ቁጥር በእጥፍ አድጓል። ፀሐፊው ዴይሊ ሜይልን አጣቅሶ እንደፃፈው በለንደን እምብርት ውስጥ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ቤ/ክ እና መስጂድ ይገኛሉ። ይሄ ምንም አይደንቅም። የሚደንቀው 1,230 ሰዎችን ለማስተናገድ የተዘጋጀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በተሰኘው ቤ/ክ ውስጥ ሳምንታዊ ባእልን ለማክበር የተገኘው ክርስቲያ 12 ሰዎች ብቻ መሆናቸው ነው። በሳንታ ማሪያ ደግሞ 20 ብቻ። በአንፃሩ በአቅራቢያው የሚገኘው የብሩን ስትሬት ኢስቴት መስጂድ የገጠመው ችግር ከዚህ የተለየ ነው፣ ለሰጋጆች የሚበቃ ቦታ በማነሱ መጨናነቅ! መስጂዱ 100 ሰዎችን ብቻ የሚያስተናግድ ጠባብ ክፍል ያለው በመሆኑ ለጁሙዐ የሚታደመው ምእመን ጎዳና ላይ ሊፈስ ግድ ሲለው ይታያል። ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ክርስትና በእንግሊዝ ወደ ታሪካዊ ቅርስነት እየተቀየ ሲሄድ ኢስላም ግን የሃገሪቱ የወደፊት ሃይማኖት ይሆናል። ይህን ግምት የሚያጠናክሩ ተጨባጭ እውነታዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከሃገሪቱ ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ግማሽ (50%) አካባቢው ከ25 አመት እድሜ በታች መሆኑ ሲሆን ከክርስቲያኑ ህዝብ ደግሞ ሩቡ (25%) ከ65 አመት እድሜ በላይ ያሉ አዛውንቶች መሆናቸው ነው። ይህም ከ20 አመታት በኋላ ወደ ቤ/ክ ከሚሄዱ ክርስቲያኖች የሚልቁ ንቁ ሙስሊሞች ይኖራሉ ማለት ነው፤ የናሺናል ሴኪዩላር ሶሳይቲ ዳይሬክቴር የሆነው ከይዝ ፖርቺየስ እንደገለፀው። በሌላ በኩል የሃገሪቱ ክርስቲያን በየጊዜው ለክርስትናው ጀርባውን እየሰጠ በመሆኑ የተነሳ የቤ/ክርስቲያናቱ ቁጥር በፍጥነት እያሽቆለቀለ ነው። ከ2001 ጀምሮ ለንደን ውስጥ ብቻ 500 ቤ/ክርስቲያናት ወደግል መኖሪያነት ተቀይረዋል። በተመሳሳይ ጊዜ በሃገሪቱ የሚገኙ መስጂዶች ቁጥር ሲታይ ግን በከፍተኛ ፍጥነት እያሻቀበ ነው ያለው። ከ2012 እስከ 2014 ባሉት አመታት ራሳቸውን የአንግሊካን ክርስትና ተከታዮች እንደሆኑ ሲገለፁ የነበሩ እንግሊዛውያን ቁጥር ከ21% ወደ 17% በማሽቆልቀል በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ ቤ/ክርስቲያኗ የ1.7 ሚሊዮን ተከታይ ኪሳራ ደርሶባታል። የሙስሊሙ ቁጥር ግን በአንድ ሚሊዮን አካባቢ እድገት አሳይቷል። ይሄ 5% ከማይሞላው ከሃገሪቱ የሙስሊሙ ቁጥር አንፃር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ እድገት ነው። (ይስተዋል! በጁላይ 2015 በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የእንግሊዝ ህዝብ ብዛት 64 ሚሊዮን ሲሆን የሙስሊሙ ቁጥር ከዚህ ውስጥ 4.4% ነው።) ሆኖም ግን ግምቶች እንደሚያስቀምጡት በ2020 የጀማዐ (ህብረት) ሶላት ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ቁጥር ቢያንስ ወደ 683ሺ ያሻቅባል ተብሎ ይጠበቃል። በአንፃሩ ሳምንታዊው በዓል ላይ የሚገኙት ክርስቲያኖች ቁጥር ወደ 679ሺ ይወርዳል ተብሎ ይገመታል። ወደ ቤ/ክ የሚመላለሰው ህዝብ ቁጥር ወደ መስጂድ ከሚመላለሰው ሙስሊም ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በአንድ ትውልድ ዘመን ውስጥ ብቻ ሶስት እጥፍ ያነሰ ይሆናል። በ2015 በተደረገ ትንተና በሃገሪቱ የብዙ ሰዎች ስያሜ በመሆን ልቆ የተገኘው “ሙሐመድ” የሚለው ስም ነው። ታላላቅ የሃገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የሙስሊም ቁጥር አላቸው። ማንቸስተር 15.8%፣ በርሚንግሀም 21.8%፣ ብራድፎርድ 24.7%። በክርስቲያን ቤተሰብ ከሚወለደው ይልቅ በሙስሊም ቤተሰብ የሚወለደው ህፃን ቁጥርም የላቀ ነው። በብራድፎርድና በሌስተር ከከተማዎቹ ህፃናት ግማሾቹ ሙስሊሞች ናቸው። ከተወሰኑ አመታት በኋላ የከተማዎቹ ነዋሪዎችን የህዝብ ብዛት ስብጥር ይገምቱ እንግዲህ። በሌላ በኩል ለንደን ውስጥ ብቻ ኦፊሻሊ የሚታወቁ 100 የሸሪዐ ፍርድ ቤቶች አሉ። የሃገሪቱ ህግ አንዳንድ የሸሪዐ ህጎችን እንዲያካትት በሃገሪቱ ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች ሳይቀሩ እየጠየቁ ነው ያሉት። የብሪታኒያ ዩኒቨርሲቲዎችም ኢስላማዊ ህግ እያስተማሩ ነው። (የኛዎቹ ያሉትንም እየዘጉ እንደሆነ ልብ ይሏል።) በሳዑዲ ዐረቢያ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆነው ሲሞን ኮሊስ ኢስላምን ተቀብሎ ወደ መካ በመሄድ ሐጅ አድርጓል። ጠላቶቹ የፈለገ ቢያሴሩ መጪው ዘመን የኢስላም ነው። በሃገራቸው ያለው አንፃራዊ ነፃነት ለኢስላም መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሆነ የገባቸው ምእራባውያን በነፃ መድረኩ “ፍልሚያ” ኢስላም ልቆ እየወጣ እንደሆነ ቢረዱ ጊዜ በሙስሊሞች ላይ የነፃነት ምህዳሩን ማጥበብ፣ ሃይማኖቱን ጭራቅ አድርጎ የመሳል (islamophobia) ሰፋፊ ዘመቻዎችን መደገፍ፣ እንደ ዳዒሽ (isis) ያሉ ጠርዘኞችን በስውር መደገፍ፣ ኢስላማዊ ሃገራትን ማፈራረስና ሙስሊሞችን በገዛ ቀያቸው መጨፍጨፍ እንዲሁም ፀረ ኢስላም ፖሊሲ የሚያራምዱ አምባገነን ሃይላትን በፀረ ሽብር ዘመቻ ስም ያልተገደበ ድጋፍ ማድረግ አማራጭ ፖሊሲያቸው ሆኖ በገሃድ እየታየ ነው። “ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል” እንዲሉ መስሏቸው እንጂ የኢስላም ግስጋሴን ምድራዊ ሃይል አይገታውም። ምክንያቱም ከላይ የተገባ መለኮታዊ ቃል አለና። { یُرِیدُونَ لِیُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ } “የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ። አላህም ከሃዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው።” [አሶፍ፡ 8] (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 03/2010) = * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
Show all...
[{ የሸሪያ ዕውቀት አስፈላጊነት }] 🎙  በኡስታዝ አህመድ ሙሀመድ አርባ ምንጭ /ገራዶ ➽ በሙሐደራው ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል ➪  ሸሪያዊ ዕውቀትን መፈለግ  ያለው ደረጃ ➱ ዕቀትን ለመፈለግ በዋነኝነት ምንድነው የሚያስፈልገን? ➱ የዕውቀት ዓይነቶች ፈርዱል ዓይን ፈርዱል ኪፋያ ሱና ➩ የሸሪያን ዕውቀት መፈለግ ብይኑ ምንድነው? ➩ ዕውቀትን ከማን ነው የምንወስደው             🕌በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ ጁመዓ 4/08/2016 ከመጝሪብ እስከ ኢሻ የተደረገ ዳዕዋ የጁመዓ ኹጥባውንና ከጁመዓ በሗላ የተደረገውን ዳዕዋ ኢንሻ አላህ እንለቃለን ...         https://t.me/tewuhidWereilu/5270
Show all...
ስለ ዕውቀት በኡስታዝ አህመድ _13-10-38.mp314.75 MB
🌙 👉ረመዷናዊ ምክር - 09👈🌙 🎙🎙🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም ሀፊዘሁላህ 📖ስለ "መልካም ስነምግባር "   ተዳሷል 🗓ዛሬ እሮብ ረመዷን 17-1445 (መጋቢት  18-2016) ከዓሱር ሰላት በኃላ ፉሪ አቡበክር አስ'ሲዲቅ መስጂድ የተሰጠ ምክር ነው ። 👉 👉https://t.me/furiselsebla 👉https://t.me/furiselsebla
Show all...
09-ረመዷናዊ ምክር رمضان ١٧-١٤٤٥.mp37.50 MB
ችግራችን የጥላቻ መርዝ በመርጨት አይፈታም ~ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ የወሎ ህዝብ ከሌሎች ለየት ባለ መልኩ ብዙ ግፍ አስተናግዷል። የግፉ ዶፍ ዛሬም አላባራም። የሃገራችን የፖለቲካ ስሪት ከጉራማይሌው የወሎ ማንነት ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ ፈተናው ገና የሚቀጥል ይመስላል፣ አላህ በቃ ይበለው እንጂ። ይሄ ጉራማይሌ ማንነቱ ምቾት የሚነሳቸው በዚያም በዚህም ማዶ አሉ። ከማዶ አጀንዳ የሚቀበል ክፍል ደግሞ መሀል ላይ አለ። ሰፊው ህዝብ ግን ሌላ አለም ውስጥ ነው ያለው። የወሎ ህዝብ አማርኛ ተናጋሪውም፣ ኦሮምኛ ተናጋሪውም፣ ዛሬ አማርኛና ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆነው አርጎባም እጅግ የተሳሰረ፣ ሁለ ነገሩ የሚመሳሰል ህዝብ ነው። ይህንን ህዝብ ለመለያየት የምትሰሩ ሁሉ ወላሂ አትጠቅሙትም። ችግር ያለባቸው አካላት ሁሉም ጋር አሉ። አዎ ለክሳችሁ ማሳመኛ የምታደርጓቸው ጣት የምትጠቁሙባቸው ተንኮለኞች በሌላኛው በኩል መጥቀስ ትችላላችሁ። ግን ደግሞ "የኛ" በምትሉት በኩልም በርግጠኝነት መሰል አካላት አሉ። "የኛ" በምትሉት በኩል ያሉ እኩዮችን እያለፋችሁ ሌላው ዘንድ ያሉ ክፉዎችን እየመዘዛችሁ ህዝብን በጅምላ የምትወርፉ አላህን ፍሩ። እንኳን ዛሬ ኢንተርኔት ተቋርጦ በሰላሙም ጊዜ ሰፊው ህዝብ ሚዲያ ላይ የለም። ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የሚታዩ ጋጠ ወጦችን መነሻ እያደረጋችሁ ድፍን ህዝብ አታጠልሹ። ክፉ ስለሚጎላ እንጂ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካለው ተሳታፊ ራሱ ተንኮለኞቹ ትንሽ መባልም የሚበዛባቸው እጅግ ጥቂቶች ናቸው። ደግሞም ችግሮች ቢኖሩ እንኳ "እነ እከሌ እንዲህ ናቸው" ማለት ጥላቻን ከማስፋት፣ ልዩነትን ከማካረር ባለፈ ለማንም አይፈይድም። ለሁሉም የሚበጀው መልካም እሴቶችን፣ ተምሳሌት የሚሆኑ ክስተቶችን እያጎሉና እያዳበሩ በሌሎቹ ላይ መመካከርና መተራረም ነው። = * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

📔 አላህን መፍራት (ተቅዋ) ማለት ምን ማለት ነው ? 🎙በወንድም ኑረድን አል ዓረቢ ሃፊዘሁላህ በወረኢሉ ከተማ 🕌 በዘምዘም መስጅድ 13/06/2016 ከኢሻ ሶላት እስከ ተራዊህ ድረስ https://t.me/YeZemzemMesjidJemea/20172
Show all...
አላህን_መፍራት_ማለት_በኑረድን_አልዓረቢ_22_14_39_47.mp33.96 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.